WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ :- 2005 የተስፋ ዘመን
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 43, 44, 45 ... 53, 54, 55  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Mon Apr 23, 2012 10:38 pm    Post subject: Reply with quote

የተከበርክ ልጅ ተድላ እንደምን አለህ ?
ዕሁድ እለት የተካሄደውን የለንደን ማራቶን በደንብ ተመልክቼዋለሁ ::
ከመቶ ቀናት በታች ለቀረው የኦሎምፒክ ዝግጅት በማራቶን ምን ተስፋ ይኖራል የሚለው ጉጉታችን ቀዝቅዞብናል ::
ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት ጀርመናውያኑ የስፖርት ተንታኞች የሰጡትን አስተያየት በፊልም አስደግፈው አቅርበውት ነበር ::
ኬንያዊውን የድል ባለቤት ከፊል ታሪክና ችሎታውን የሚያሳዩ መረጃዎችንም አቅርበው ለውድድሩ ትልቅ ግምት ሰጥተውት ነበር እንዳሉትም በጥሩ ሁኔታ አሸንፏል ::
ኬንያ በማራቶን ወደፊት ሊኖራት የሚችለውን ተስፋ ከመንግስታቸው ጀምሮ ለስፖርቱ የሰጡት ግምት በጣም አስደሳች ነው ::
በስፖርት ዘመናቸውም ከዚያ በኍላም በጣም ከተሳካላቸው ሰዎች ኃይሌን ቁጥር አንድ ብለውታልም የተዋጣለት ቢዝነስ ማን ሆኗል ብሎታል ጋዜጠኛው ::
ጀርመናውያኑ ጋዜጠኞች የኢትዮጵያ አትሌቶችን በጣም ስለሚወዷቸው በውድድር ወቅት በቁልምጫ ነው የሚጠሯቸው ::
ይገርምሀል የጥሩነሽ እህት ውድድሩን አቋርጣ ስትወጣ የተናገሩት የቁጭት አነጋገር ስሜትን ይነካ ነበር ::
ጸጋዬ ከበደ በጣም ብቁ አትሌት ነው ሁለተኛ የሆነው ልጅ ግን እግሩን እየጠበቀ እንዳለና አልፎት ሊሄድ እንደሚችል ተመልካች መረዳት ይችል ነበር ::
ግሪክ ላይ ሂሻም ኤልጉራዥ ቀነኒሳን ለማለፍ የተጠቀመውን አይነት ዘዴ ይሄም ኬንያዊ በጸጋዬ ላይ ተጠቅሞ ተሳክቶለታል ::
በመጪው የለንደን ኦሎምፒክ የረዥም ርቀት ውድድርን በሚመለከት ድሉ ከባለቤቶቹ ኬንያና ኢትዮጵያ ባይወጣም
ኬንያውያን እንደበፊቱ ይከተሉናል ብዬ የምተማመንበት አይመሰለኝም ::
በኢትዮጵያ አትሌትና ፌዴሬሽን አይግባቡም አሰልጣኝና አትሌቶችም እንዲሁ አይግባቡም ::
በግሪክ ኦሎምፒክ በብርሀኔ አደሬና በፌዴሬሽኑ መካከል የነበረው ሁኔታ አስተምሮናል ይበልጥ ሊማሩ የሚችሉት ግን እነሱ ሆነው ሳለ አሁንም አልተማሩም ::
በየአመቱ የሚከሰት ተመሳሳይ ችግር መቼ እንደሚጠፋና እንደሚቀር በውነት አላውቅም ::
ደግነቱ ኢትዮጵያዊ አትሌት ከፊቱ የሚያየው ባንዲራውን ስለሆነ አያሳፍረንም እንጂ የኛ ስፖርት መሪዎች አሳፋሪዎች ናቸው ::
ቀነኒሳ በቀለ ከብዙ የጉዳት ጊዜ በኍላ አሁን ከህመሙ አገግሞ ባለፈው ሳምንት የአመቱን ፈጣን ሰዐት አስመዝግቧል ወዲያውም ለንደን ላይ ተስፋ እንዳለም ተናግሯል እኛም እንተማመንበታለን ::
ቀነኒሳን በዚህ በከፍተኛ ዝግጅት ሰዐት ምን ያህል እንዳስቸገሩት ሁላችንም የምናውቀው ነው ::
ባጠቃላይ ዘንድሮ ብዙ እንዳላዝን ብዙ እንዳልጠብቅ አይነት ነው ለንደንን የምናፍቀው ::
የለንደን ማራቶን የለንደንን ኦሎምፒክ አስፈርቶኛል ::
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ

ራስብሩ ወልደገብርዔል
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዞብል 2

አለቃ

Joined: 30 Jan 2004
Posts: 2031

PostPosted: Tue Apr 24, 2012 1:45 am    Post subject: Reply with quote

ጤናይስጥልኝ ራስ ብሩ በውድድር ጊዜ የኢትዮጵያ አትሌት ባንዲራውን የሚያየው ብለህ የተናገርከው ትክክል ነው !! በለንደን ኦሎምፒክም አያሳፍሩንም Exclamation Exclamation

ዞብል ከአራዳ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Apr 24, 2012 3:53 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ራስ ብሩ :-

የትንሣኤ በዓል እንዴት አለፈ ? ዳግሚያ -ትንሣኤስ ? ወርኃ -ፋሲካ መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ ::

ስለ መጪው የሎንዶን ኦሎምፒክ ያለህን ሥጋት እኔም እጋራለሁ :: እንዲያው ለነገሩ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሊወዳደሩ ከሚችሉባቸው የውድድር ዓይነቶች መካከል በየትኞቹ ውጤት መጠበቅ ይቻል ይሆን ?

በሴቶች ምድብ
400 ሜትር ሩጫ
800 ሜትር ሩጫ
1,500 ሜትር ሩጫ
3,000 ሜትር የመሠናክል ሩጫ
5,000 ሜትር ሩጫ
10,000 ሜትር ሩጫ
ማራቶን

የወንዶች ምድብ
800 ሜትር ሩጫ
1,500 ሜትር ሩጫ
3,000 ሜትር የመሠናክል ሩጫ
5,000 ሜትር ሩጫ
10,000 ሜትር ሩጫ
ማራቶን

በየውድድር ዓይነቱ ማንን ለውጤት እንጠብቅ ? እንወያይበት ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Tue Apr 24, 2012 10:02 pm    Post subject: Reply with quote

ጤና ይስጥልኝ
ውድ ዞብል ስለ አስተያየትህ አመሰግናለሁ !
ትክክል ነህ አዎ አያሳፍሩንም ::
ልጅ ተድላ የፋሲካ በአል ዘንድሮ በጣም ደስ በሚል ሁኔታ ነው ያለፈው : ፍራንክፈርት በድምቀት የሚከበረው በዓል መስቀል ነው :
ሀበሻው ከመላው ቡንደስ ላንድ (ግዛት ) ነው የሚመጣው ብል ስህተት አይመስለኝም :: በጣም ደስ የሚል የበዓል ጊዜ ነው መስቀል ::
ያቀረብከው የመወያያ ርዕስ ተገቢና ወቅታዊም ነው :
400 ሜትር ርቀት በኢትዮጵያ ያለው ቤስት ሠዓት 52.00 በላይ ይመስለኛል እስካለፈው አራትና አምስት አመታት ያለውን አውቅ ነበር ::
ይህም ማለት በአለም ቤስት የሴቶች ሰዐት ያልተሻለ ነው ::
በአለም የመጀመሪያው ሪኮርድ የተመዘገበው መቼ እንደሆነ አላስታውስም እንጂ ሰዐቱ ግን 47 ሴኮንድ አካባቢ ነው ::
ከዛ በኍላ አስደናቂ ሪኮርድ ያስመዘገበው ማይክል ጆንሰን 43,18 በመሮጥ ነው ::
ይሄንን ሪኮርድ ለመስበር ያሰበም ሳይፈጠር ብዙ ቆይቷል ::
በምስራቅ አፍሪካ ኬንያና ኢትዮጵያ የታወቁ የረዥም ርቀት ሳንባ ያላቸው ስለሆኑ አጭር ርቀትን ብዙም አይወዱትም መሰለኝ :
ልጅ ተድላ በአጭር ርቀት በተለይም 400 ሜትር የአለምን ቤስት ሚኒማ እንኳን አሟልተን ለውድድር ብንቀርብም ወርቅ ማግኘት የሚሆንልን አይመስለኝም : አሜሪካና ጃይማካም አያስቀምሱንም ::
800 ሜትር የአዶላዋ ቁጥሬ ዱለቻ ተደጋጋሚ ድሎችን በማስመዝገብ ኢትዮጵያን የርቀቱ ተጋሪ እንድትሆን ካደረጓት አትሌቶች ዋንኛዋ ናት ::
ቁጥሬ በዚህ ርቀት የአለምን የሩጫ ትራኮች ተቆጣጥራቸው የነበረ ቢሆንም ያላት ቤስት ሰዓት 1.59.37
ነው ::
ቁጥሬ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ታሪክ 1500 ሜትር ርቀት ብዙ የወርቅ ሜዳልያዎችን ያጠለቀች ከመሆኗም ባሻገር ለተተኪ አትሌቶች ትልቅ ሞራል ሆናለች ::
ከቁጥሬ ጋር የማልረሳት የዚህ ርቀት ሯጭ ሞዛምቢካዊቷ ማሪያ ሉርደስ ሙቶላ ነች ::
ሙቶላ 1,56 በታች 800 ሜትርን ሮጣለች ::
እንግዲህ በዘንድሮውን የለንደን ኦሎምፒክ 800 ሜትር በሴቶቹ በኩል ብዙም የምጠብቀው ባይኖርም ገለቴ ቡርቃ እና ፋንቱ ሞገስን እጠብቃለሁ ::
በወንዶቹ ሜዳልያ ሰንጠረዥ ውስጥ እንደምንገባ ምንም ጥርጣሬ አይገባኝም ::
ወጣቱ መሀመድ አማን ባለፈው ጊዜ ያስደሰተንን ደስታ በድጋሚ እናገኘዋለን ብዬ አምናለሁ ::
በየትኛው ውጤት እንጠብቅ ለሚለው ጥያቄህ መነሻዬ በወንዶቹ 800 ሜትር ነው ምክንያቱም ኦሎምፒክ ነውና ::
ጊዜ አጠራቅሜ በሚቀጥሉት ርቀቶች ላይ ያለኝን አስተያየት እስክሰጥ ደህና ቆዩ :

ራስብሩ ወልደብገርዔል
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Apr 24, 2012 11:51 pm    Post subject: Reply with quote

ራስብሩ እንደጻፈ(ች)ው:
ጤና ይስጥልኝ
ውድ ዞብል ስለ አስተያየትህ አመሰግናለሁ !
ትክክል ነህ አዎ አያሳፍሩንም ::
ልጅ ተድላ የፋሲካ በአል ዘንድሮ በጣም ደስ በሚል ሁኔታ ነው ያለፈው : ፍራንክፈርት በድምቀት የሚከበረው በዓል መስቀል ነው :
ሀበሻው ከመላው ቡንደስ ላንድ (ግዛት ) ነው የሚመጣው ብል ስህተት አይመስለኝም :: በጣም ደስ የሚል የበዓል ጊዜ ነው መስቀል ::

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አንድ ቀን ዱብ ብዬ አንዱን በዓል አብሬያችሁ እሣተፍ ይሆናል ::

400 ሜትር በሴቶች ምድብ በተደጋጋሚ በውድድር ላይ የምናያት እና ጥሩ ውጤት ያላት ወጣቷ ሯጭ ፋንቱ ማጌሦ ናት (ምንጭ ) :: እርሷ የሮጠችበት ጥሩ ጊዜ 52.9 ሴኮንድ ሲሆን ውጤቱን ያስመዘገበቸው አምና በጋቦሮኒ በተደረገው የአፍሪቃ የወጣቶች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ነበር :: በአፍሪቃ ደረጃ ሬኮርዱ 49.10 ሴኮንድ (በናይጄሪያዊቷ ፋሊላት ኦጎንኮያ ... በጁላይ 27/1996 የተመዘገበ ሬኮርድ ) ነው :: በዘንድሮው ... 2012 የውድድር ዘመን እስካሁን በሴቶች ምድብ የተመዘገበው የርቀቱ ፈጣን ጊዜ 50.94 ሴኮንድ ሲሆን ሁለት ሯጮች በደባልነት ይዘውታል -ዴዲ ትሮተር (የአሜሪካ ) እና አማንትል ሞንጥሾ (ቦትስዋና ) (ምንጭ )::

ፋንቱ በዚህ የውድድር ዓመት 400 ሜትር የተሻለ ጊዜ አላስመዘገበችም :: ስለዚህ በውድድሩ ለመሣተፍ ከቻለች እንኳን ትልቅ እርምጃ ነው :: ከፋንቱ ሌላ በዚህ የውድድር ዓይነት የተሻለ ጊዜ ያስመዘገበች ማንጠግቦሽ መለሰ ናት :: ማንጠግቦሽ አምና በማፑቶ (ሞዛምቢክ ) በተደረገው የመላው አፍሪቃ ጨዋታዎች ውድድር በመጀመሪያው ዙር ማጣሪያ 55.73 ሴኮንድ እንዲሁም በግማሽ ፍፃሜው ውድድር 55.84 ሴኮንድ አጠናቃለች :: የእርሷ ሰዓት ከፋንቱ ይዘገያል (ምንጭ )::

በወንዶች ምድብ 400 ሜትር ውድድር ገና እየገባን ይመስለኛል :: በአምናው የማፑቶ ውድድር በረከት ደስታና ሀጎስ ታደሰ ተወዳድረዋል :: በተለይ በረከት ደስታ ማጣሪያዎቹን አልፎ በፍፃሜው ውድድር ለመሣተፍ ችሏል :: ያስመዘገባቸው ሰዓቶች :- ማጣሪያ (ከምድብ 3 2 ደረጃ 46.74 ሴኮንድ ) : በግማሽ ፍፃሜ (ከምድብ 1 3 ደረጃ 46.39 ሴኮንድ ) : በፍፃሜው (46.56 ሴኮንድ 4 ደረጃ ፈፅሟል ) :: (ምንጭ )

አንተም እንዳመለከትከው እንኳን በዓለም ደረጃ ይቅርና በአፍሪቃም ደረጃ ቢሆን ያሉን የዚህ ሩጫ ዓይነት ሯጮች ገና ይቀራቸዋል :: በኦሎምፒክ ለመሣተፍ ቢበቁ እንኳን ትልቅ መሻሻል ይሆናል ::

800 ሜትር ጀምሮ ወደላይ ባሉት እመለስባቸዋለሁ ::

በል ሰላም ሁንልኝ ::

አክባሪህ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu Apr 26, 2012 1:11 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

800 ሜትር ሩጫ
የወንዶች ምድብ

ከኢትዮጵያውያን የመካከለኛ ርቀት ሩጫ ተወዳዳሪ አትሌቶች መካከል በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ማግኘት የቻለው መሐመድ አማን ገለቶ ነው (ምንጭ :- Len Johnson (for the IAAF), Sunday, March 11, 2012. Teenager Amans rise continues with Ethiopias first 800m gold) :: መሐመድ በዓለም አቀፍ ውድድር ውጤት ማስመዝገብ የጀመረው የዛሬ 4 ዓመት በሰኔ 16 ቀን 2000 .. (June 23, 2008) በአቡጃ (ናይጄሪያ ) በተደረገ ውድድር 800 ሜትር ሩጫ ነበር :: ያኔ ያስመዘገበው ሰዓት 1 ደቂቃ 50.29 ሴኮንድ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ያለው የግሉ ጥሩ ሰዓት 1 ደቂቃ 43.37 ሴኮንድ ነው (ምንጭ ) :: ከአራት ዓመት ባነሠ ጊዜ 6.28 ሴኮንድ ማሻሻል አሣይቷል :: በአሁኑ ጊዜ የርቀቱ የዓለም ሬኮርድ ባለቤት የሆነውን ኬንያዊውን ዴቪድ ሉኩታ ሩዲሻ ባለፈው መስከረም 6 ቀን 2004 .. (September 18, 2011) በሚላን (ጣሊያን ) ውድድር ማሸነፍ የቻለው እርሱ ብቻ ነው (ምንጭ )::

ስለዚህ ምናልባት መሐመድ አማን 800 ሜትር የመጀመሪያውን የኦሎምፒክ ሜዳሊያ ሊያስገኝልን ይችላል ::

በዚህ ርቀት ያሉን ሌሎች ተወዳዳሪዎች አዳዲሶች ናቸው :- ሽፈራው ወሌ (1:47.95) : እሥራኤል አወቀ (1:49.35) : ተሾመ ወየሣ ሰሎሞን (1:50.29) (ምንጭ ) :: እነዚህ ወጣቶች ለወደፊቱ በዓለም ሻምፒዮና ተፎካካሪ ሊሆኑ ይችላሉ :: ነገር ግን ለሎንዶን ኦሎምፒክ ተፈላጊውን ሚኒማ እንኳን አሟልተው መቅረብ ይችሉ እንደሆነ እርግጠኛ አይደለሁም ::

የሴቶች ምድብ
በመካከለኛ ርቀት ሩጫ ሴቶቻችን ከወንዶቹ ቀድመው የውጤት ባለቤት ለመሆን በቅተዋል :: ስለዚህ ፈር -ቀዳጆቹ እነርሱው ናቸው :: ቁጥሬ ዱለቻ ካለበቂ አሠልጣኝ በራሷ ጥረት ለረዥም ጊዜ 800 እና 1,500 ሜትር ርቀት ሩጫን ተቆጣጥራ ኖራለች :: እርሷ በምትወዳደርበት ዘመን የሞዛምቢኳ ልዕልት ማሪያ ማቶላ በመኖሯ ምክንያት ቁጥሬ ጎልታ ልትወጣ አልቻለችም ነበር :: በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ተስፋ ሊጣልባቸው የሚችሉ 800 ሜትር ሯጮች አሉን :: ነገር ግን ከውድድር ውድድር ውጤታቸው ለምን እንደሚዋዥቅ ምክንያቱ ግልጽ ሊሆንልኝ አልቻለም (ምናልባት የአሠልጣኝ ዕጦት እንዳይሆን ):: እስኪ ከሚከተሉት ሯጮች ለውጤት ማንን መጠበቅ እንችላለን Question

የርቀቱ የዓለም ሬኮርድ (1:53.28 ከሃያ ዘጠኝ ዓመታት በፊት 'July 26, 1983' በቼክ ሪፓብሊካዊቷ ጀርሚላ ክራቶችቪዮላ ) እንዲሁም የዓመቱ ፈጣን ሰዓት (1:59.58 በደቡብ አፍሪቃዊቷ ካሥተር ሠሚኒያ ) (ምንጭ ) ::

እነ ገለቴ ያላቸው ሰዓት ከዓለም ሬኮርድ ይቅርና ከቁጥሬ ጥሩ ሰዓት ጋር ሲነፃፀር (1:59.37) (ምንጭ ) እንኳን ይዘገያል :: ስለዚህ በሴቶች ምድብ 800 ሜትር ውድድር ሚኒማ ቢያሟሉ እንኳን ከተሣትፎ የዘለለ ውጤት ለመጠበቅ እቸገራለሁ ::

ይቀጥላል ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu Apr 26, 2012 9:03 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የአትሌቲክስ አፍቃሪዎች :-

ሻምበል አበበ ቢቂላ በሮም ኦሎምፒክ ሬኮርዱን 7 ደቂቃ 47 ሴኮንድ አሻሽሎ 2 ሰዓት 15 ደቂቃ 16.2 ሴኮንድ በመግባት የመጀመሪያው አፍሪቃዊ የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ለመሆን የቻለ ታላቅ የማራቶን ጀግና እንደሆነ በተደጋጋሚ ተወስቷል :: አበበ የሠበረው የማራቶን ሬኮርድ የሌላ ብዙም የማይታወቅ አትሌት ውጤት ሣይሆን በኦሎምፒክ ታሪክ በአንድ የውድድር ዘመን በሦሥት የርቀት ዓይነቶች ተወዳድሮ : በሦሥቱም ሬኮርድ ሠብሮ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ለመሆን የበቃው የቼኩ ጀግና የኢሚል ዛቶፔክ ሬኮርድ በመሆኑ ጭምር ነው :: ኢሚል ዛቶፔክ 1944 .. (... 1952) በተደረገው 15ኛው የሄልስንኪ ኦሎምፒያድ 5,000 : 10,000 እና የማራቶን ውድድሮች በሦሥቱም ተወዳድሮ በሦሥቱም ሬኮርድ ሠብሮ ታሪኩን በወርቅ ቀለም የጻፈ ታላቅ አትሌት ነበር (ምንጭ :- Emil Zá topek):: አበበን አሁንም ደግመን : ደጋግመን ልናስታውሰው የሚገባን አትሌት በመሆኑ ስለእርሱ የሮም ድል የተዘጋጀውን የቪዲዮ ፊልም እና አንድ በጥሩ ሁኔታ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተጻፈ መጣጥፍ አቅርቤያለሁኝ ::

ምንጮች :-

1 ..... Posted by: Dave, April 26, 2012 at 09:52. Ethiopia: 50 stunning Olympic moments No24: Abebe Bikila runs barefoot into history.

2 ..... Uploaded by 5cense on Aug 23, 2010. Abebe Bikila wins marathon in 1960 Rome Olympics... barefoot.

Quote:
Few could have predicted when Italy hosted the 1960 Olympic Games that come the opening ceremony Rome would be cavorting in the midst of an economic boom. But the legacy of Fascist rule, which had ended 17 years earlier, still remained. And while many axes and insignia had been chipped away in a post-regime iconoclastic orgy, nowhere in the capital was the regime's presence more evident than around the two Olympic sites.

Paved with ancient-style mosaics of Fascist sportsmen, slogans and 264 references to Benito Mussolini, the Via dell'Impero, the main Foro Italico thoroughfare leading from the imposing Mussolini obelisk to the Olympic stadium, courted most controversy. Flanked by huge blocks of travertine stone, it was etched with key events in Fascist history, in the midst of which was the conquest of the Abyssinian capital Addis Ababa in 1936. It was into this environment that Abebe Bikila, a private in Haile Selassie's Imperial Army, stepped.

Small, lean, barefooted, in bright red shorts and a green vest sporting the number 11, Bikila was a last-minute replacement in the marathon for an injured team-mate. His challenge was taken far from seriously. "Who's this Ethiopian," questioned one commentator. He was not alone.

Ethiopia: 50 stunning Olympic moments No24: Abebe Bikila runs barefoot into history Bikila's unofficial personal best for the 42.2km better than the world record was widely dismissed as impossible. He arrived in Rome with one pair of running shoes but they were ruined in training in the month before the Games. With his new ones causing blisters, his decision to compete barefoot, feet toughened by miles of shoeless training on the high Ethiopian plains, only added to the general derision.

The marathon began in the heat of the late afternoon at the Campidoglio, Rome's civic centre set above the Forum. The athletes followed Mussolini's triumphant thoroughfare past the Coliseum, the Palatine Hill and the Circus Maximus.

Here, settled at the back of the leading pack, Bikila glided past the Obelisk of Axum that had been plundered from Abyssinia. Continuing south and exiting the city, a breakaway pack began to materialise: "With the English Kiley, there's the Irishman Messipy [Messitt], the Belgian Van der Blicher, the Morrocans Rhadi and Saudy, and there's that unknown Ethiopian we saw earlier," announced the commentator. "He's called Abebe Bikila. He's barefoot."

At the 32km mark, in Rome's peripheral countryside, with the sun disappearing behind the city, the runners turned from a somewhat bizarre section of the capital's orbital road and on to the Appian Way that used to connect the ancient city with Brindisi, on Italy's south-eastern coast.

Breaking with the tradition of daytime Olympic marathons that concluded in the stadium, the early evening start maximized the spectacle as the athletes negotiated 8km of the cypress-tree-lined Appian Way, in darkness. As Bikila's bare feet rhythmically kissed the uneven stones, the half moonlight, the illuminated ancient Roman monuments and hundreds of torch-bearing soldiers intensified the atmosphere and added to the drama. As Alberto Cavallari wrote in his Corriere della Sera report: "It wasn't a marathon it was 'Aida', with the Romans roadside making up the chorus."

Re-entering the city at the Porta San Sebastiano, with impeccable timing Bikila left his sole pursuer, the Moroccan Rhadi Ben Abdesselam, just as he repassed the Axum obelisk. Finishing in 2hr 15min 16sec, Bikila shattered the Olympic record and set a new world best, before dancing a jig of joy beneath the Arch of Constantine where many of his rivals simply collapsed.

Coming less than 25 years after Mussolini's forces had conquered his capital at the end of a cruel colonial war, it was the significance of his victory as much as the ease with which he had consumed the capital's kilometres that fascinated.

Marking the rise and future dominance of East African middle- and long-distance runners, in the presence of the all-white South African team that the International Olympic Committee chose not to challenge, and against the vastly better funded and better equipped Soviet, US and European athletes, Bikila ran his name and that of his country into history.

But his victory was not simply that of Ethiopia, it was also a triumph for Rome and the Games. Transcending his lack of shoes, for which he is most fondly remembered, he dramatically closed the final event under the lights and arch of a long-departed emperor while, at the same time, eclipsing the memory of a more recent wannabe.

Following the fierce parliamentary debates over the negative image presented by the Fascist-built venues to the outside world, and the retaliatory neo-Fascist graffiti that marked the city in the buildup the Games, there was no better, more apt or powerful demonstration of Italy's break from the past than this glorious, individual victory by an ex-colonial subject.

As the editor of the British Olympic Association's magazine World Sports condescendingly concurred, in his report from Rome: "It is a scene to remember a moment of theatrical drama; a moment so unusual in modern world athletics, when a virtual unknown from an insignificant country crosses the seas and conquers the heroes. It is a fine, unsophisticated, illogical victory [] This [] was an historic Olympic marathon both in terms of performance and backcloth [] its drama was in its setting, presentation and outcome."

Despite the years of preparation, the Games' greatest and most enduring moment was not only completely unplanned, it was totally unimaginable. Bikila, this tiny, barefoot former colonial subject, mixed the unexpected with drama to create a scriptwriter's dream and become the greatest symbol of the new, rejuvenated, post-Fascist country.

What the Observer said

The Observer: Sunday 11 September 1960

Bikila Abebe, a 28-year-old member of Emperor Haile Selassie's bodyguard, won the marathon gold medal in the last big event of the Olympics last night. Abedisiem Rhadi of Morocco was second and B. Magee, of New Zealand. Third. Abebe's time was 2hr 15min 16.2sec, which was 7min 47sec better than Emil Zatopek's Olympic record. In fact, the first 15 all improved on the old record. Prowess in big international cross-country races on the Continent had made Rhadi one of the more fancied competitors, but none outside East Africa had heard of Abebe, who won the greatest marathon in the 64 years of Olympic history.
What happened next?

Six weeks before the 1964 Tokyo Olympics, Bikila was taken ill with appendicitis and underwent surgery. Still recovering when he arrived in Japan, he went on to become the first athlete to retain the Olympic marathon title. In 1968, a car accident in the city of Sheno, 76km from Addis Ababa, left Bikila confined to a wheelchair. His competitive spirit undiminished, he won gold in a 25km cross-country sledge competition in Norway in 1970. Suffering complications from his paralysis, he died in October 1973 and was buried in the presence of Selassie.

On the 50th anniversary of his win, the 2010 Rome marathon was dedicated to Bikila's memory and, appropriately, Ethiopia claimed a male and female double. The women took first, second and third places, and the men's winner, Siraj Gena, picked up a 5,000 bonus, offered by the race organiser, for completing the final 300m barefoot. Although few visitors to Rome could have noticed the small plaque mounted on the wall of the Foro dei Imperiali dedicated to Bikila, he remains a local hero, the "escaping Ethiopian" who ran Italy into the democratic dawn.

Sport Italia by Simon Martin, published in 2011 by IB Tauris, narrates the history of modern Italy through the national passion of sport.

This article was amended on 26 April 2012 to clarify that the person referred to in a commentary as Messipy, was in fact Bertie Messitt.
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Apr 29, 2012 8:46 pm    Post subject: Reply with quote

እሑድ ሚያዝያ 21 ቀን 2004 ..

የማራቶን ውድድር ወሬዎች ::

ዛሬ የጀርመንን የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን ሯጮች ሬኮርድ እየሠበሩ ተቆጣጥረዋቸው ውለዋል ::

27ኛው የሐስፓ ማራቶን : ሐምቡርግ (ጀርመን )
ዳዊት አብዱላ ሹሚ የሥፍራውን የውድድር ሰዓት በማሻሻል (እርግጠኛ ባልሆንም 1 ደቂቃ ባላነሠ ጊዜ ) 2 ሰዓት 5 ደቂቃ 58 ሴኮንድ አሸናፊ ሆኗል :: የአገሩ ልጆች ያሚ ዳዲ 2 : ደቻሣ ሹሜ 4 : እና ለማ ፈቃዱ 6 ሆነው ውድድራቸውን አጠናቀዋል ::

በሴቶች ምድብ ደግሞ ነፃነት አብዩ እና አታለማሁ ኪዳኔ 2ኛና 3 ሆነው ጨርሠዋል ::

ምንጭ :- Pat Butcher (organisers for the IAAF), Sunday, 29 April 2012. Dawit again sub-2:06 as course records tumble in Hamburg.

10ኛው የዱስልዶርፍ (ጀርመን ) ሜትሮ ቡድን ማራቶን ::
ሠቦቃ ድሪባ ቶላ (ሥሙ በትክክል የተጻፈ አይመስለኝም ) የውድድሩን ሬኮርድ 5 ሴኮንዶች በማሻሻል 2 ሰዓት 8 ደቂቃ 27 ሴኮንድ በማጠናቀቅ አሸናፊ ሆኗል :: በሴቶች ምድብ መልካም ግዛው 2 ሰዓት 27 ደቂቃ 50 ሴኮንድ በማጠናቀቅ 3 ወጥታለች ::

ምንጭ :- Jö rg Wenig (organisers for the IAAF), Sunday, April 29, 2012. Tola and debutante Jeruto break course records in Dü sseldorf.

ስለዚህ ዛሬ እሑድ በጀርመን ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የፌሽታ ቀን ሆኖ እንደሚያልፍ እገምታለሁ ::

በዚህ ዓመት በተደረጉት የማራቶን ውድድሮች እጅግ ተቀራራቢ በሆነ ሰዓት የገቡ ተፎካካሪ የማራቶን ሯጮች በብዛት ስላሉ በሁለቱም ፆታዎች ኢትዮጵያን ወክለው በሎንዶን ማራቶን የሚሣተፉ አትሌቶችን ለመምረጥ ምን መሥፍርት ሥራ ላይ ሊውል እንደሚችል ለመገመት ይከብደኛል ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኮሎኔል

ኮትኳች

Joined: 07 Apr 2006
Posts: 196
Location: zimbabwe

PostPosted: Mon Apr 30, 2012 3:53 pm    Post subject: Reply with quote

Quote:
በዚህ ዓመት በተደረጉት የማራቶን ውድድሮች እጅግ ተቀራራቢ በሆነ ሰዓት የገቡ ተፎካካሪ የማራቶን ሯጮች በብዛት ስላሉ በሁለቱም ፆታዎች ኢትዮጵያን ወክለው በሎንዶን ማራቶን የሚሣተፉ አትሌቶችን ለመምረጥ ምን መሥፍርት ሥራ ላይ ሊውል እንደሚችል ለመገመት ይከብደኛል ::

ጥሩ ብለሀል ልጅ ተድላ ሊያውም ቀደም ጥሩ ጥሩ ሰአት ከነበራቸው የተሻሉም ልጆች መጥተዋል :
ኢትዮጵያ ዳግም በማራቶን ልትጀምር ነው መሰል :
ወትሮስ አለም ያወቀን በማራቶንም አይደል ?
ማራቶንን አንስተህ አበበን የሚመለከት ያቀረብከው ጽሁፍ መቼም እንዴት ያለ መሰለህ አስተዋይ ጸሀፊ ነው የጻፈው :: ከዚ በፊት እንዳልኩህ አበበን በደንብ አውቀዋለሁ ብርቱ አትሌት ነበር ::
ከራስብሩም የጀመራችሁት አስተያየት የሚያስደስት ነው ቀጥሉ ::
ዘንድሮ ሎንዶን ላይ የቤጂንግን ያህል ሜዳል አናጣም ::
አክባሪያችሁ ኮሎኔል
_________________
Ethiopia
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon Apr 30, 2012 10:52 pm    Post subject: Reply with quote

ኮሎኔል እንደጻፈ(ች)ው:
Quote:
በዚህ ዓመት በተደረጉት የማራቶን ውድድሮች እጅግ ተቀራራቢ በሆነ ሰዓት የገቡ ተፎካካሪ የማራቶን ሯጮች በብዛት ስላሉ በሁለቱም ፆታዎች ኢትዮጵያን ወክለው በሎንዶን ማራቶን የሚሣተፉ አትሌቶችን ለመምረጥ ምን መሥፍርት ሥራ ላይ ሊውል እንደሚችል ለመገመት ይከብደኛል ::

ጥሩ ብለሀል ልጅ ተድላ ሊያውም ቀደም ጥሩ ጥሩ ሰአት ከነበራቸው የተሻሉም ልጆች መጥተዋል :
ኢትዮጵያ ዳግም በማራቶን ልትጀምር ነው መሰል :
ወትሮስ አለም ያወቀን በማራቶንም አይደል ?
ማራቶንን አንስተህ አበበን የሚመለከት ያቀረብከው ጽሁፍ መቼም እንዴት ያለ መሰለህ አስተዋይ ጸሀፊ ነው የጻፈው :: ከዚ በፊት እንዳልኩህ አበበን በደንብ አውቀዋለሁ ብርቱ አትሌት ነበር ::

ሰላም ውድ ኮሎኔል :-

አዎ በማራቶን ውድድር ኢትዮጵያን በሎንዶን ኦሎምፒክ የሚወክሉትን ለመለዬት ከባድ ሥራ ሣይሆን አይቀርም ::

ስለ ሻምበል አበበ ቢቂላ እና ሻምበል ማሞ ወልዴ የሚያስታውሱትን ቢያካፍሉን እንዴት ጥሩ ነበር ::

ኮሎኔል እንደጻፈ(ች)ው:
ከራስብሩም የጀመራችሁት አስተያየት የሚያስደስት ነው ቀጥሉ ::
ዘንድሮ ሎንዶን ላይ የቤጂንግን ያህል ሜዳል አናጣም ::
አክባሪያችሁ ኮሎኔል

ራስ ብሩ ጠፋብኝ እንጂ Rolling Eyes እኔ እቀጥላለሁ ::

ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ ጨዋታዎች በአንድ ወቅት እስካሁን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሜዳሊያ ያገኘችው 1992 .. (... 2000) በተደረገው 27ኛው የሲድኒ ኦሎምፒክ ነበር (4 የወርቅ : 1 የብር እና 3 የነሐስ ) : ባለፈው የቤጂንግ ላይ የተገኘው ውጤት በአንድ የነሐስ ሜዳሊያ ያንሣል (4 የወርቅ : 1 የብር እና 2 የነሐስ ) (ምንጭ :- Olympic.org - Official Site of the Olympic Movement ):: ስለዚህ ዘንድሮ ብዙ አይጠብቁም ማለት ነው ?

ሰላም ይሁኑልኝ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon Apr 30, 2012 11:08 pm    Post subject: Reply with quote

ሰኞ ሚያዝያ 22 ቀን 2004 ..

የያንግዝሁ -ጂያንዝኸን (ቻይና ) ዓለም አቀፍ የግማሽ ማራቶን ውድድር

ትላንት እሑድ በተደረገው በዚህ ውድድር የዘንድሮው የዱባይ ማራቶን አሸናፊ አየለ አብሽሮ 1 ሆኗል :: በሴቶችም ውድድር ፈይሴ ታደሰ ሁለተኛ ሆናለች :: ዝርዝር ውጤቶቹ የሚከተለውን ይመሥላሉ ::

ምንጭ :- የያንግዝሁ -ጂያንዝኸን (ቻይና ) ዓለም አቀፍ የግማሽ ማራቶን ውድድር የውጤት ሠንጠረዥ ::

የወንዶች ምድብ
1 ..... አየለ አብሽሮ ___ 1 ሰዓት 1 ደቂቃ 11 ሴኮንድ (ለዓመቱ በርቀቱ ያስመዘገበው ጥሩ ሰዓት )

የሴቶች ምድብ
2 ..... ፈይሴ ታደሰ ______ 1 ሰዓት 11 ደቂቃ 8 ሴኮንድ
4 ..... ብዙነሽ በቀለ ______ 1 ሰዓት 11 ደቂቃ 15 ሴኮንድ (ለዓመቱ በርቀቱ ያስመዘገበችው ጥሩ ሰዓት )
7 ..... አሠለፈች መርጊያ ___ 1 ሰዓት 11 ደቂቃ 41 ሴኮንድ (ለዓመቱ በርቀቱ ያስመዘገበችው ጥሩ ሰዓት )

ዘንድሮ ማራቶን እና የኢትዮጵያ አትሌቶች የተፋቀሩ ይመስላል ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Tue May 01, 2012 8:08 pm    Post subject: Reply with quote

ጤና ይስጥልኝ ወገኖች
ኮሎኔል እንደምን አሉ ?
ልጅ ተድላ አልጠፋሁም በደንብ እየተከታተልኩህ ነው የኔን ነገር እንደምታውቀው ነው በቂ ጊዜ አለኝ ብዬ ካላሰብኩ ቁጭ ማለት አይሆንልኝም ::
መልክቶችን ለማንበብ ስራላይም ሆኜ በየትንንሽዋ እረፍት እችላለሁ ለመፃፍ ግን ጊዜ እንደማንበብ አይቀልም ለዛም ጭምር ነው ::
የለንደን ኦሎምፒክ አሁን የሚያነጋግረን ጉዳይም ስለሆነ ባለኝ እካፈላለሁ አንተ ግን ሳትሰለች አዳሲስ ክስተትቶችን እና ውጤቶችን እንድናውቅ ሁልጊዜም ወቅታዊ ስለምታደርገን በውነት ያለኝ አክብሮት ከፍተኛ ነው :: ስፖርቱ ውስጣችን እንዲቆይ ስለምትረዳን ጉብዝናህንም አደንቃለሁ ::
ራስብሩ
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu May 03, 2012 4:57 am    Post subject: Reply with quote

ራስብሩ እንደጻፈ(ች)ው:
ልጅ ተድላ አልጠፋሁም በደንብ እየተከታተልኩህ ነው የኔን ነገር እንደምታውቀው ነው በቂ ጊዜ አለኝ ብዬ ካላሰብኩ ቁጭ ማለት አይሆንልኝም ::
መልክቶችን ለማንበብ ስራላይም ሆኜ በየትንንሽዋ እረፍት እችላለሁ ለመፃፍ ግን ጊዜ እንደማንበብ አይቀልም ለዛም ጭምር ነው ::

አይዞን ትንሽ ልቆሥቁሥህ ብዬ እንጂ ችግርህን እረዳልሃለሁ ::

ራስብሩ እንደጻፈ(ች)ው:
የለንደን ኦሎምፒክ አሁን የሚያነጋግረን ጉዳይም ስለሆነ ባለኝ እካፈላለሁ አንተ ግን ሳትሰለች አዳሲስ ክስተትቶችን እና ውጤቶችን እንድናውቅ ሁልጊዜም ወቅታዊ ስለምታደርገን በውነት ያለኝ አክብሮት ከፍተኛ ነው :: ስፖርቱ ውስጣችን እንዲቆይ ስለምትረዳን ጉብዝናህንም አደንቃለሁ ::
ራስብሩ

ከስፖርት ዓይነቶች አትሌቲክስ : በተለይም ደግሞ የረዥም ርቀት ሩጫ እና ማራቶን በዓለም ላይ በጥሩ ጎን የሚታዩልን መለያዎቻችን ናቸው :: ማንም ኢትዮጵያዊ በእኒህ በጎ እሴቶች ላይ ህልውናውን ሣያጠናክር በሌለ ነገር ላይ መድከም የለበትም :: የእኔ ዕምነት ይህ ነው :: ስለዚህ ነው ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ አንድ አምድ ለብቻው ከፍቼ የምቸከችከው :: አንተም ሆንክ ሌሎች ተሣታፊዎችና አንባቢዎች ይህንን ኃሣቤን እንደምትጋሩኝ አምናለሁ ::

ወደ ሠሞኑ ጉዳይ ስንመለስ :- አሁንም ማራቶን ... ፖል ቴርጋት ዛሬ ለሮይተርስ በሠጠው ቃለ መጠይቅ የዓለም የማራቶን ሬኮርድ ባለቤት የሆነው ኬንያዊው ፓትሪክ ማካው አገሩን በሎንዶን ኦሎምፒክ እንዳይወክል መደረጉ ጥሩ እንዳልሆነና እንዲያውም ኢትዮጵያውያን አሁን ባላቸው ብቃት ሜዳሊያውን ሊነጥቁ እንደሚችሉ ሥጋቱን ገልጿል :: በሴቶች ምድብ ግን ኬንያውያት የማራቶን ሯጮች ሁሉንም ሜዳሊያዎች ጠቅልለው እንደሚያሸንፉ ተንብይዋል :: እስኪ እናያለና Rolling Eyes

ምንጭ :- Reuters, (Editing by David Clarke and Alison Wildey), Wed May 2, 2012. Olympics-Makau rues omission from Kenyan marathon team.

Quote:
TERGAT SUPPORT

Makau has support for his inclusion in the team from compatriot and former world record holder Paul Tergat.

"I personally would have wanted Makau in the team. He should even have been there as a reserve. Marathon training is tough and anything can happen to the three athletes already selected," Tergat told Reuters.

"After all, (Athletics Kenya) paraded him after he broke the world record in Berlin last year and announced to the world that he would be in the team for the Olympics," said Tergat, who won silver in the 10,000 metres at the 1996 and 2000 Games.

He said Ethiopia's marathon runners had shunned competitive races in recent months and could be in fine form come July, unlike the Kenyan runners picked after the London race.

"I am not doubting their maturity, experience and capability. But our running and training schedule is very different from the Ethiopians and I fear that we may be in for a shock.

"We have run in many races lately compared to the Ethiopians and the team that ran in London may not have enough recovery time to put up a strong fight in Olympic Games in July," said Tergat, whose world record of 2:04:55 set in Berlin in 2003 lasted until 2007.

"The Ethiopians' last serious marathon was in Dubai (in January). That's where they selected their team for the Olympics. They ran 2:04 there and they started preparations for the Olympics then," he said.

However, Tergat was confident the Kenyan women could sweep the marathon medals in London.

Mary Keitany, world champion Edna Kiplagat and Priscah Jeptoo were selected for the team after taking the top three places in the London marathon.

"Our women are set. They have come of age and may even beat our men to the medal haul in the London Games," said Tergat.

"It is inspiring to see our women compete and beat the world. This was not the case some 10 years ago."
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu May 03, 2012 9:23 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

ለዛሬ በታሪክ ጎማ ትንሽ ወደኋላ አሽከረክራችሁና ያለፉ ዘመን ትዝታዎችን አስታውሣችኋለሁ ::

ሻምበል ማሞ ወልዴ :- 400 ሜትር እስከ ማራቶን ባሉ የርቀት ዓይነቶች የተወዳደረ ሯጭ ::
ሟቹ ሻምበል ማሞ ወልዴ (አፈሩ ይቅለለውና ) የሩጫ ስፖርት የጀመረው በአጭር ርቀት 4 400 ሜትር የዱላ ቅብብል እስከ 1,500 ሜትር የሩጫ ውድድሮች በመሣተፍ ነበር : ዘመኑም 1948 .. (... 1956) : 16ኛው ኦሎምፒክ : ሜልቦርን (አውስትራሊያ ):: በኦሎምፒክ ጨዋታዎች የውድድር ዘመኑን የፈፀመው ደግሞ 20ኛው ኦሎምፒክ የማራቶን ሩጫ የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ በመሆን ነበር : ሥፍራውም ሙኒክ (ጀርመን ) 1964 .. (... 1972):: በኦሎምፒክ ደረጃ ትልቁን ሽልማት ያገኘው 19ኛው ኦሎምፒክ : 1960 .. (... 1968) : ሜክሲኮ ሲቲ (ሜክሲኮ ) በተደረገው ውድድር ነበር :: በዚያ ውድድር በማራቶን ሩጫ የወርቅ ሜዳሊያ በማሸነፍ አገሩን ኢትዮጵያን በተከታታይ 3 ጊዜ ማራቶንን እንድታሸንፍ አስችሏል ::

ሻምበል ማሞ ወልዴ ለአገሩ ይህንን ያህል ክብር ቢያቀዳጅም መጨረሻው ግን የእስራትና የሥቃይ ነበር :: ወያኔ ለኢትዮጵያ ትልቅ አገልግሎት ያበረከቱ ዜጎቿን እንደሚያዋርደውና እንደሚያሠቃየው ሁሉ ሻምበል ማሞ ወልዴንም ባልፈፀመው ነገር "የቀይ ሽብር ወንጀለኛ " ተብሎ 1985 ጀምሮ ለዘጠኝ ዓመታት ከርቸሌ ታሥሮ በሕመም ሲሠቃይ ቆይቶ ሊሞት ጥቂት ጊዜያት ሲቀረው ቢፈታም 1994 .. አርፏል ::

የሻምበል ማሞ ወልዴ የኦሎምፒክ ሬኮርዶች :-
  1 ..... 4x400 ሜትር ዱላ ቅብብል ሩጫ (1948 .. ሜልቦርን : አውስትራሊያ ) (በቡድን : ደረጃ 5 : የመጀመሪያ ማጣሪያ ) 3 ደቂቃ 30.0 ሴኮንድ (በእጅ ሰዓት ) : 3 ደቂቃ 29.93 (በአውቶማቲክ ሰዓት )

  2 ..... 800 ሜትር ሩጫ (1948 .. ሜልቦርን : አውስትራሊያ ) 1 ደቂቃ 58.0 ሴኮንድ (በእጅ ሰዓት ) (በመጀመሪያ ማጣሪያ ደረጃ 7)

  3 ..... 1,500 ሜትር ሩጫ (1948 .. ሜልቦርን : አውስትራሊያ ) 3 ደቂቃ 51.0 ሴኮንድ (በእጅ ሰዓት ) (በመጀመሪያ ማጣሪያ 11)

  4 ..... 5,000 ሜትር ሩጫ (1960 .. : ሜክሲኪ ሲቲ : ሜክሲኮ ) 14 ደቂቃ 29.8 ሴኮንድ (በእጅ ሰዓት ) : 14 ደቂቃ 29.85 ሴኮንድ (በአውቶማቲክ ሰዓት ) (በመጀመሪያው ዙር ከምድቡ 3)

  5 ..... 10,000 ሜትር ሩጫ (1960 .. : ሜክሲኪ ሲቲ : ሜክሲኮ ) 29 ደቂቃ 28.0 ሴኮንድ (በእጅ ሰዓት ) : 29 ደቂቃ 27.75 ሴኮንድ (በአውቶማቲክ ሰዓት ) (የብር ሜዳሊያ አሸናፊ )

  6 ..... የማራቶን ሩጫ :- (1960 .. : ሜክሲኪ ሲቲ : ሜክሲኮ ) 2 ሰዓት 20 ደቂቃ 26.4 ሴኮንድ (የወርቅ ሜዳሊያ ) በጥሩ ሰዓት የገባው በሙኒክ ኦሎምፒክ ነበር (2 ሰዓት 15 ደቂቃ 8.4 ሴኮንድ ) :: ነገር ግን ደረጃው 3 ስለነበረ የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆኖ ነበር ::

ምንጭ :- Sports Reference LLC.

ኢትዮጵያ በመጀመሪያ ጊዜ ስለተሣተፈችበት የሜልቦርን ኦሎምፒክ ሠፋ ባለ ሁኔታ ለማቅረብ እሞክራለሁ ::

ቸር እንሠንብት ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወርቅነች

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Oct 2010
Posts: 968

PostPosted: Fri May 04, 2012 8:38 am    Post subject: Reply with quote

Quote:
ለዛሬ በታሪክ ጎማ ትንሽ ወደኋላ አሽከረክራችሁና ያለፉ ዘመን ትዝታዎችን አስታውሣችኋለሁ ::

ቅቅቅ ..ፈዛዛው እውነት አለህ እንድምትረታንም እናውቃለን ..ግን የሚያሳዝን አንድ ነገር አለ እንዴት ነው ጎማውን ያሸከረከርከው እግርህን ሞያሌ ጨርሶታል መጀምሪያ አሰተካክለው ትለሀለች ጀሚላ ከቸችል ጎዳና Laughing Laughing Laughing

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም የአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

ለዛሬ በታሪክ ጎማ ትንሽ ወደኋላ አሽከረክራችሁና ያለፉ ዘመን ትዝታዎችን አስታውሣችኋለሁ ::

ሻምበል ማሞ ወልዴ :- 400 ሜትር እስከ ማራቶን ባሉ የርቀት ዓይነቶች የተወዳደረ ሯጭ ::
ሟቹ ሻምበል ማሞ ወልዴ (አፈሩ ይቅለለውና ) የሩጫ ስፖርት የጀመረው በአጭር ርቀት 4 400 ሜትር የዱላ ቅብብል እስከ 1,500 ሜትር የሩጫ ውድድሮች በመሣተፍ ነበር : ዘመኑም 1948 .. (... 1956) : 16ኛው ኦሎምፒክ : ሜልቦርን (አውስትራሊያ ):: በኦሎምፒክ ጨዋታዎች የውድድር ዘመኑን የፈፀመው ደግሞ 20ኛው ኦሎምፒክ የማራቶን ሩጫ የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ በመሆን ነበር : ሥፍራውም ሙኒክ (ጀርመን ) 1964 .. (... 1972):: በኦሎምፒክ ደረጃ ትልቁን ሽልማት ያገኘው 19ኛው ኦሎምፒክ : 1960 .. (... 1968) : ሜክሲኮ ሲቲ (ሜክሲኮ ) በተደረገው ውድድር ነበር :: በዚያ ውድድር በማራቶን ሩጫ የወርቅ ሜዳሊያ በማሸነፍ አገሩን ኢትዮጵያን በተከታታይ 3 ጊዜ ማራቶንን እንድታሸንፍ አስችሏል ::

ሻምበል ማሞ ወልዴ ለአገሩ ይህንን ያህል ክብር ቢያቀዳጅም መጨረሻው ግን የእስራትና የሥቃይ ነበር :: ወያኔ ለኢትዮጵያ ትልቅ አገልግሎት ያበረከቱ ዜጎቿን እንደሚያዋርደውና እንደሚያሠቃየው ሁሉ ሻምበል ማሞ ወልዴንም ባልፈፀመው ነገር "የቀይ ሽብር ወንጀለኛ " ተብሎ 1985 ጀምሮ ለዘጠኝ ዓመታት ከርቸሌ ታሥሮ በሕመም ሲሠቃይ ቆይቶ ሊሞት ጥቂት ጊዜያት ሲቀረው ቢፈታም 1994 .. አርፏል ::

የሻምበል ማሞ ወልዴ የኦሎምፒክ ሬኮርዶች :-
  1 ..... 4x400 ሜትር ዱላ ቅብብል ሩጫ (1948 .. ሜልቦርን : አውስትራሊያ ) (በቡድን : ደረጃ 5 : የመጀመሪያ ማጣሪያ ) 3 ደቂቃ 30.0 ሴኮንድ (በእጅ ሰዓት ) : 3 ደቂቃ 29.93 (በአውቶማቲክ ሰዓት )

  2 ..... 800 ሜትር ሩጫ (1948 .. ሜልቦርን : አውስትራሊያ ) 1 ደቂቃ 58.0 ሴኮንድ (በእጅ ሰዓት ) (በመጀመሪያ ማጣሪያ ደረጃ 7)

  3 ..... 1,500 ሜትር ሩጫ (1948 .. ሜልቦርን : አውስትራሊያ ) 3 ደቂቃ 51.0 ሴኮንድ (በእጅ ሰዓት ) (በመጀመሪያ ማጣሪያ 11)

  4 ..... 5,000 ሜትር ሩጫ (1960 .. : ሜክሲኪ ሲቲ : ሜክሲኮ ) 14 ደቂቃ 29.8 ሴኮንድ (በእጅ ሰዓት ) : 14 ደቂቃ 29.85 ሴኮንድ (በአውቶማቲክ ሰዓት ) (በመጀመሪያው ዙር ከምድቡ 3)

  5 ..... 10,000 ሜትር ሩጫ (1960 .. : ሜክሲኪ ሲቲ : ሜክሲኮ ) 29 ደቂቃ 28.0 ሴኮንድ (በእጅ ሰዓት ) : 29 ደቂቃ 27.75 ሴኮንድ (በአውቶማቲክ ሰዓት ) (የብር ሜዳሊያ አሸናፊ )

  6 ..... የማራቶን ሩጫ :- (1960 .. : ሜክሲኪ ሲቲ : ሜክሲኮ ) 2 ሰዓት 20 ደቂቃ 26.4 ሴኮንድ (የወርቅ ሜዳሊያ ) በጥሩ ሰዓት የገባው በሙኒክ ኦሎምፒክ ነበር (2 ሰዓት 15 ደቂቃ 8.4 ሴኮንድ ) :: ነገር ግን ደረጃው 3 ስለነበረ የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆኖ ነበር ::

ምንጭ :- Sports Reference LLC.

ኢትዮጵያ በመጀመሪያ ጊዜ ስለተሣተፈችበት የሜልቦርን ኦሎምፒክ ሠፋ ባለ ሁኔታ ለማቅረብ እሞክራለሁ ::

ቸር እንሠንብት ::

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 43, 44, 45 ... 53, 54, 55  Next
Page 44 of 55

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia