WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ :- 2005 የተስፋ ዘመን
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 44, 45, 46 ... 53, 54, 55  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት


 
View previous topic :: View next topic  
Author Message
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች


Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Fri May 04, 2012 8:40 pm    Post subject: Reply with quote

ጤና ይስጥልኝ
ውድ ልጅ ተድላ ያቀረብከው የኢትዮጵያ ማራቶን (አበበ ቢቂላ ) ታሪክ ሌሎች ካነበብኳቸው በተሻለ ጥም የሚያረካ ሆኖ አግኜቼዋለሁ ::
አንድ ግዜ በስራ ላይ እያለሁ አንዲት አሮጊት ከስተመር ይመጡና በጨዋታ የተነሳ ከየት ነህ አይቀርም እኔም ከኢትዮጵያ መሆኔን ስነግራቸው ያስከተሉልኝ ጉዳይ ማራቶን ነበር ::
አበበ ቢቂላን አውቀዋለሁ : አሉኝ ሲጀምሩ ...
የመጀመሪያ ልጄ አበበ ቢቂላ ሮም ላይ ያደረገውን አስደናቂ ታሪክ ከዛም በጃፓን ያገኘውን ድል በቴሌቪዥንና በሬዲዮ በደንብ ያውቅ ስለነበር
እዚህ ሀገራችን በሙኒክ ኦሎምፒክ እንደሚመጣ በቴሌቪዥን ሰምቶ ይህንን ሰው ልታሳዪኝ ይገባሻል
ብሎ አስቸገረኝ ::
ከዛም : በውድድሩ ወቅት ሙኒክ ይዤው እንደምሄድ ነገርኩትና ተደሰተ ::
እኔ ግን የታላቅ እህቴ ባለቤት የኦሎምፒክ ስፖርት አስተማሪ ስለነበረ ለሱ ነግሬው ይዘሺው ነይ አበበ በእንግድነት ስለሚመጣ አስተዋውቃቸዋለሁ እንዳለኝ አልነገርኩትም ነበር ምክንያቱም ሰርፕራይዝ
ላደርገው ብዬ ነው ::
ጊዜው ሲደርስም ሙኒክ ሄድንና እንዳለውም የእህቴ ባለቤት እጁን ይዞ ሄዶ ከአበበ ቢቂላ ጋር
አስተዋወቀው አበበም ብድግ አድርጎ ጉልበቱላይ አድርጎት ፎቶግራፍ አንስቻቸዋለሁ ::
አሁንም ፎቶው በክብር አለ : በውድድሩም እሱ እንግዳ ሆኖ ያሸነፈው ኢትዮጵያዊ ነው (ማሞ ወልዴ ነበረ ) በኃይል ገርሞን ነበር በማለት ስታጫውተኝ በደስታ ነበር ያዳመጥኳት ::
ብዙ ጊዜ ኢትዮጵያ ስትነሳ አበበ እንደባንዲራችን ቀለም ተለይቶ የሚጠራ መታወቂያችን ነው ቀዳማዊ ኃይለስላሴም ሌላው መታወቂያችን ናቸው ::
ምናልባት ጊዜ ጊዜን እየወለደ ሲሄድ የነበረው እያረጀ አዲሱ እየታወቀ ስለሚመጣ ቀጣዩ የኢትዮጵያ መለያ ኃይሌ ገብረስላሴ እንደሚሆን አልጠራጠርም ::
( በአትሌቲክሱ መድረክ ማለቴ ነው )
ይህ ትውልድ ወደፊት የሚጠራው የዚህ ዘመን ድንቅ ሰው ኃይሌ ስለሆነ ማለቴ ነው ::
አንዴም እንደዚሁ ወደ ወደብ ከተማ ሀምበርግ በግሩፕ ስንሄድ የአውቶብሱ ሹፌር 40 ዐመታት በፊት
ኢትዮጵያ ለኮንስትራክሽን ስራ ሄዶ እንደነበረና
አብረው የሄዱትም አንድ ላይ አበበ ቢቂላን
ጋብዘውት ግብዣቸው ላይ ከነባለቤቱ ተገኝቶ ተዋውቀውት ተደስተው መመለሳቸው እንዳስደሰታቸው አጫውቶናል ::
ስለኳስ ጨዋታም አንስቶልናል እንደዛ ያለ ሜዳ አይቶ እንደማያውቅ ኳሷ ስትመታ በትክክል አትሄድም እያለ ሲነግረኝ አስቆናል ::
ማራቶን ሲነሳ ኢትዮጵያ ትነሳለችና ማራቶን የኛ ስም ሆኖ ቆይቷል ::
በኢትዮጵያ በጣም ለረዥም ዘመናት ከሀያ አመታት በላይ የዘለቀ የድል ድርቅ ገብቶ የነበረበት ዘመን ትዝ ይለኛል ::
በላይነህ ዴንሳሞ ሮተርዳም ላይ በማይደፈር ክብረወሰን የቆየውን ድል አድሶ የኢትዮጵያን ስፖርት
ወዳድ ትንፋሹን ውጦ እንዳይቀር አድርጎታል ::
የበላይነህ ድል ለረዥም ጊዜ ሳይደፈር እንደቆየ አስታውሳለሁ እንደገናም አንበሳው ኃይሌ መልሶ ድሉን ወደቤቱ ያመጣው ቢሆንም አሁንም እንደሚመለስ ምንም አልጠራጠርም ::
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri May 04, 2012 11:35 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

ሰላም ወንድሜ ራስ ብሩ :-

ስለ ማራቶን ስናወራው ውለን ስናወራው ብናድር የሚሠለች አይደለም :: ምክንያቱም ከእኛነታችን ጋር የተዋሃደ ስፖርት ስለሆነ :: ብዙዎቹ ጓደኞቼ ለእግር ኳሣ ብቻ እንጂ ስለ አትሌቲክስ ስፖርት ስሜቱም የላቸውም :: ለእኔ ግን እግር ኳስ ስሜትን የሚገዛ ስፖርት ቢሆንም ከማንነቴ ጋር የተዋሃደው ስፖርት አትሌትክስ (በተለይም ማራቶን ) ነው :: ምክንያትም አለኝ :- እስከዛሬ ድረስ ኢትዮጵያውያን በእግር ኳስ ምን ጥሩ ሥም አለን ? ለዓለም ሕዝብስ ያበረከትነው ማን የሚባል ታዋቂ ተጫዋች አለን ? ስለዚህ በማንጠራበት ግብዣ ቅልውጥ እየሄድን ራሣችንን ማዋረድና ማቅለል የለብንም :: ይህ ማለት ግን የእግር ኳስ ስፖርትን መውደድ ማቆም አለብን ሣይሆን ልካችንን እና ገደባችንን ማወቅ ይኖርብናል የሚል አቋም አለኝ ::

ስለ ማራቶን ብቻ ሣይሆን ስለ ኦሎምፒክ ውድድሮች የጀመርኩትን ዘገባ እቀጥላለሁ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sat May 05, 2012 3:36 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም የአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

16ኛው ኦሎምፒክ : ሜልቦርን (አውስትራሊያ ) : 1948 .. (... 1956) ::

ኢትዮጵያ በኦሎምፒክ ጨዋታዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የተሣተፈችበት የሜልቦርን ኦሎምፒክ ነበር :: በዚያን ጊዜ ለውድድሩ ስለተደረጉት ዝግጅቶችና ወደ ሜልቦርን ስለነበረው አድካሚ የጉዞ ሁኔታ ሟቾቹ ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ እና የማራቶን ሯጩ ባሻዬ ፈለቀ ሲተርኩት ሣዳምጥ በጣም የሚሥበኝ ታሪክ ነበር :: ጉዟቸው ከአዲስ አበባ በኤደን (የመን ) አድርገው ወደ ሲንጋፖርና ፊሊፒንስ አቅንተው ከስድስት ቀናት በኋላ ሜልቦርን መድረሣቸውን አውስተዋል :: የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ በተካፈለበት ውድድር የቡድኑ አባላት በሁለት የስፖርት ዓይነቶች ተካፍለው ነበር :- በአትሌቲክስና በቢስክሌት ውድድሮች :: የቡድኑ አባላት : የተወለዱበት ዘመንና ዕድሜያቸው : የተወዳደሩባቸው የስፖርት ዓይነቶች እንዲሁም ያገኙት ደረጃም ሆነ ሜዳሊያ እንደሚከተለው ቀርቧል ::

..___ ሥም ________ የተወለዱበት ዘመን (ዕድሜ ) _____________________ የተወዳደረበት የስፖርት ዓይነት __ ደረጃ (ሜዳሊያ )

1 ..... አበበ ኃይሉ __ መሥከረም 9 ቀን 1926 .. (Sep. 19, 1933) (23) ___ 100 : 200 እና 400 ሜትሮች ሩጫ :: 4x100 እና 4x400 ሜትር ዱላ ቅብብል __ 5 : 6 : 4 : 5 : 5 (ሜዳሊያ - የለም )
2 ..... ንጉሤ ሮባ ___ ጳጉሜን 5 ቀን 1929 .. (Sep. 10, 1936) (20) ______ 100 እና 200 ሜትሮች ሩጫ :: 4x100 ሜትር ዱላ ቅብብል __ 6 : 5 : 5 (ሜዳሊያ - የለም )
3 ...... በየነ ለገሠ ____ 1926 .. (... 1934) (22) _______________ 100 : 200 እና 400 ሜትሮች ሩጫ :: 4x100 እና 4x400 ሜትር ዱላ ቅብብል __ 6 : 5 : 5 : 5 (ሜዳሊያ - የለም )
4 ...... አየነው በየነ ___ ኅዳር 1 ቀን 1928 .. (Nov. 11, 1936) (20) ________ 400 እና 800 ሜትሮች ሩጫ :: 4x400 ሜትር ዱላ ቅብብል __ 5 : 8 : 5 (ሜዳሊያ - የለም )
5 ...... ማሞ ወልዴ ___ ሰኔ 5 ቀን 1924 .. (Jun. 12, 1932) (24) ________ 800 እና 1,500 ሜትሮች ሩጫ _______ 7 : 11 (ሜዳሊያ - የለም )
6 ...... ባሻዬ ፈለቀ ____ 1909 .. (... 1917) (39) ____________________ማራቶን _____________ 29 (ሜዳሊያ - የለም )
7 ...... ገብሬ ብርቅአየ __ 1918 .. (... 1926) (30) __________________ ማራቶን ______________ 32 (ሜዳሊያ - የለም )
8 ...... ገረመው ደንቦባ __ ጥር 6 ቀን 1927 .. (December 15, 1934) (21) ______ የግል ግልቢያ እና የቡድን ቅብብሎሽ _____________ 25 : 9 (ሜዳሊያ - የለም )
9 ...... መሥፍን ተስፋዬ __ ??? ____________ (___ ??? ____) (?) ______________ የግል ግልቢያ እና የቡድን ቅብብሎሽ _____________ 36 : 9 (ሜዳሊያ - የለም )
10 .... ፀሐዬ ባህታ ______??? _________ (___ ??? ____) (?) _________________ የግል ግልቢያ እና የቡድን ቅብብሎሽ _____________ 38 : 9 (ሜዳሊያ - የለም )
11 .... ንጉሤ መንግሥቱ __ መጋቢት 2 ቀን 1924 .. (March 11, 1932) (24) _____ የግል ግልቢያ እና የቡድን ቅብብሎሽ _____________ ውድድሩን አልጨረሠም : 9 (ሜዳሊያ - የለም )

ምንጮች :-
1 ..... Abraha Belai, Aug 16, 2004. Ethiopia at the Olympics: 1956-2004.

2 ..... Vettenniemi, Erkki, April of 2002. The Life and Trials of Malmo Wolde: Soldier, Olympian, Prisoner... The Many Sides of Ethiopia's 1968 Olympic Gold Medalist.

3 ..... SR Olympic Sports. Ethiopia Athletics at the 1956 Melbourne Summer Games - Athletics.

4 ..... SR Olympic Sports. Ethiopia Athletics at the 1956 Melbourne Summer Games - Cycling.

_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
anferara

ኮትኳች


Joined: 27 Sep 2006
Posts: 384

PostPosted: Mon May 14, 2012 10:07 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ተድላ

በየሳምንቱ የምትዘግበው የስፖርት ዜና ሰሞኑን የለም :: በሰላም ነው ? ሁሉ ነገር ደህና እንደሆነ ተስፋ አለኝ ::
_________________
http://ethiopian-books.blogspot.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon May 14, 2012 9:52 pm    Post subject: Reply with quote

anferara እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ተድላ

በየሳምንቱ የምትዘግበው የስፖርት ዜና ሰሞኑን የለም :: በሰላም ነው ? ሁሉ ነገር ደህና እንደሆነ ተስፋ አለኝ ::

ሰላም ወንድሜ "anferara" ደህና ነህ ወይ ? አንዳንዴ ቅዳሜ እና እሑድ ዙረት ይኬድና ጊዜ አይበቃ ይሆናል :: ደግሞም የእኛ አትሌቲክስ ስፖርት አንዳንድ ቀዳዳዎች እየታዩበትና እኒያም እየሠፉ ስለሄዱ ሥጋትም አለ :: ለማንኛውም ሠፋ ያለ ዘገባ ይኖረኛል ::

አክባሪህ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon May 14, 2012 11:07 pm    Post subject: Reply with quote

ሰኞ ግንቦት 6 ቀን 2004 ..

ያለፈው ሣምንት መጨረሻ የአትሌቲክስ ስፖርት ዘገባ ::


ባለፉት ሦሥት ቀናት የኢትዮጵያን አትሌቲክስ ስፖርት ከሥር መሠረቱ ሊንዱ የሚችሉ ውሣኔዎች በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባለሥልጣኖች ተወስኗል : ወደ መጨረሻው አብራራዋለሁ :: በመጀመሪያ ስለተደረጉት ውድድሮችና የተገኙት ውጤቶች እናምራ ::

የቅዳሜ ግንቦት 4 ቀን ውሎ :-
የዓመቱ የአልማዝ ደረጃ የአትሌቲክስ ውድድሮች በዶሃ (ቃጣር ) ተከፍቷል :: በዚህ ሥፍራ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለመዱት የርቀት ዓይነቶች ያስመዘገቡት አመርቂ ውጤት አልነበረም :: እንዲያውም ቀነኒሣ በቀለ 3,000 ሜትር ርቀት ተወዳድሮ 7 መውጣቱ የሥጋት ምንጭ ሊሆነን ይገባል :: ከውድድሩ ሥፍራ የተሠሙት ብሥራቶች የፋንቱ ማጌሦ ማኔዶ 800 ሜትር ሩጫ እንዲሁም የሮባ ጋሪ 3,000 ሜትር የመሠናክል ሩጫ ውድድሮች የኢትዮጵያን ሬኮርዶች መሥበራቸው ነው ::ዝርዝር ውጤቶቹ የሚከተለውን ይመስላሉ ::

የሴቶች ምድብ
ምንጭ :- 800 ሜትር ሩጫ ውድድር ውጤት ሠንጠረዥ ::

2 ..... ፋንቱ ማጌሦ ማኔዶ ___ 1 ደቂቃ 57.90 ሴኮንድ (የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬኮርድ )

ምንጭ :- የሴቶች 3,000 ሜትር ሩጫ ውድድር የውጤት ሠንጠረዥ ::
2 ..... መሠረት ደፋር _____ 8 ደቂቃ 46.49 ሴኮንድ
4 ..... ገለቴ ቡርቃ _______ 8 ደቂቃ 48.92 ሴኮንድ
12 .... ጎቲቶም ገብረሥላሤ _ 9 ደቂቃ 00.97 ሴኮንድ

የወንዶች ምድብ
ምንጭ :- የወንዶች 1,500 ሜትር ሩጫ ውድድር የውጤት ሠንጠረዥ ::

7 ..... መኮንን ገብረመድህን ___ 3 ደቂቃ 33.38 ሴኮንድ

ምንጭ :- የወንዶች 3,000 ሜትር የመሠናክል ሩጫ ውድድር የውጤት ሠንጠረዥ ::
3 ..... ሮባ ጋሪ _____________ 8 ደቂቃ 06.16 ሴኮንድ (የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬኮርድ )
14 ... ናሆም መሥፍን ታሪኩ ___ 8 ደቂቃ 32.97 ሴኮንድ

ምንጭ :- የወንዶች 3,000 ሜትር ሩጫ የውጤት ሠንጠረዥ ::
7 ..... ቀነኒሣ በቀለ _____ 7 ደቂቃ 40.00 ሴኮንድ
8 ..... አበራ ኩማ ______ 7 ደቂቃ 40.85 ሴኮንድ (በግሉ ለርቀቱ ጥሩ ሰዓት )

የእሑድ ግንቦት 5 ቀን ውድድሮች

ምንጭ :- የፕራግ (ቼክ ሪፓብሊክ ) የማራቶን ውድድር :: Andy Edwards (organisers for the IAAF), Sunday, May 13, 2012. Kiprop dashes Cheromeis hopes while Chimsa lives up to expectations in Prague.


በወንዶች ምድብ ደሬሣ ጪምሣ ተከታዩን 50 ሴኮንዶች በመቅደም 2 ሰዓት 6 ደቂቃ 06 ሴኮድን አሸናፊ ሆኗል :: በሴቶች ምድብ መሠረት ደባልቄ 3 (2:27:15) እና ምሥክር መኮንን 5 (2:29:46) ሆነው ውድድራቸውን አጠናቀዋል ::

ዓመታዊው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ::

በየዓመቱ በሚደረገው የዘንድሮው ውድድር ረቡዕ ግንቦት 1 ቀን ተጀምሮ ትላንት እሑድ ተጠናቋል :: አዳዲስ አሸናፊዎች ታይተዋል :- በወንዶች ምድብ 10,000 ሜትር ሩጫ ጠበሉ ዘውዴ : 5,000 ሜትር ሩጫ ሙክታር እድሪስ እንዲሁም 1,500 ሜትር አብዮት አብነት ድል ቀንቷቸዋል :: በሴቶች ምድብ 1,500 ሜትር ዓለም አምባዬ እንዲሁም 5,000 ሜትር ብዙዬ ድሪባ አዲስ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊዎች ናቸው ::

ምንጭ :- Elshadai Negash with the assistance of Bizuayehu Wagaw (for the IAAF), Monday, May 14, 2012. Driba and Endris impress at Ethiopian Champs


ከአትሌቲክስ ፈዴሬሽን ባለሥልጣኖች አካባቢ የሚሠማው ውሣኔ ለሎንዶን ኦሎምፒክ ሌላ የእክል ምንጭ ሣይቀሰቅስ አይቀርም :: ዘገባውን ከሪፖርትር ሥቤ አምጥቼዋለሁ : አንብቡት ::

ምንጭ :- ደረጀ ጠገናው : ሪፖርተር ጋዜጣ : እሑድ ግንቦት 5 ቀን 2004 ..:: ቀነኒሳ በባለፈው ዓመት ሰዓቱ ለኦሊምፒክ እንዲቀርብ የቀረበውን ጥያቄ ፌዴሬሽኑ ውድቅ አደረገው ::

Quote:
ኢትዮጵያን በለንደን ኦሊምፒክ 10 ሺሕ ሜትር ወንዶችና ሴቶች የሚወክሉ አትሌቶች የሚመረጡበት ውድድር ክርክር አስነስቶ እንደነበር ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ማናጀር ጆን ሔርመንስ ቀነኒሳ ባለፈው ዓመት ባስመዘገበው የዓመቱ ምርጥ ሰዓት በለንደን ኦሊምፒክ እንዲወዳደር ያቀረበውን ጥያቄ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውድቅ አደረገው፡፡

ፌዴሬሽኑ አገሪቱን በለንደን ኦሊምፒክ 10 ሺሕ ሜትር የሚወክሉ አትሌቶች መምረጥ ይችል ዘንድ፣ ሙሉ ወጪውን በመሸፈን ግንቦት 19 ቀን 2004 .. ወንዶችን በሆላንድ ሄንግሎ፣ ሴቶችን ደግሞ በአሜሪካ ዩጂን ግንቦት 24 ቀን 2004 .. ለማወዳደር ዝግጅት ከጀመረ ቢሰነባብትም፣ በተለይ የሄንግሎውን ውድድር ያዘጋጀው ሆላንዳዊው ጆን ሄርመንስ ቀነኒሳ በቀለ ባለፈው የውድድር ዓመት ብራሰልስ ላይ በርቀቱ ያስመዘገበው የዓመቱ ምርጥ ሰዓት 26 ደቂቃ 43 ነጥብ 16 ሰከንድ ያለ ወቅታዊ ፐርፎርማንስ በቀጥታ ለንደን ኦሊምፒክ እንዲቀርብ የሄንግሎውም ውድድር እንዲያልፈው ጥያቄ አቅርቧል፡፡ ነገር ግን ፌዴሬሽኑ ቀነኒሳን ጨምሮ በርካታ አትሌቶች ለለንደን ኦሊምፒክ የሚያበቃቸው ሚኒማ ያላቸው በመሆኑ ሁሉም በውድድሩ ተሳትፈው የተሻለ ሰዓት ያላቸውን መምረጥ የግድ ስለሚል በሚል የማናጀሩ ጥያቄ ተቀባይነት እንዳላገኘ በመጨረሻም ቀነኒሳ በቀለ ግንቦት 19 ቀን 2004 .. በሚደረገው የሚኒማ ሩጫ ላይ እንዲሳተፍ መደረጉም ተገልጿል፡፡

ከቀነኒሳ በቀለ ጋር ስለሺ ስህንና ኢማና መርጊያ ለለንደን ኦሊምፒክ የሚያበቃቸውን ሚኒማ ባለፈው ዓመት በአሜሪካ በዩጂን ከተማ፣ ስለሺ 26 ደቂቃ 56 ነጥብ 84 ሰከንድ፣ ኢማና ደግሞ 26 ደቂቃ 48 ነጥብ 35 ሰከንድ በኦሊምፒክ የሚያሳትፋቸው ሰዓት ሲኖራቸው፣ ነገር ግን መሮጥ እንደሚጠበቅባቸውም ተወስኗል ተብሏል፡፡

በተመሳሳይ ሴቶች ግንቦት 24 ቀን 2004 .. በአሜሪካ ዩጂን ሁሉም ታዋቂ አትሌቶች ለተሻለ ሚኒማ ይሮጣሉ፡፡ እንደ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በርቀቱ ማንኛውም አትሌት እስከ ሰኔ 20 ቀን 2004 .. ድረስ ውድድር ባገኘበት ሮጦ የተሻለ ሰዓት ማስመዝገብ ከቻለ ለለንደን ኦሊምፒክ የሚያዝበት አሠራር እየተከተለ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሸዋ ነህ

ኮትኳች


Joined: 07 Oct 2009
Posts: 250
Location: us

PostPosted: Mon May 14, 2012 11:59 pm    Post subject: Reply with quote

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
anferara እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ተድላ

በየሳምንቱ የምትዘግበው የስፖርት ዜና ሰሞኑን የለም :: በሰላም ነው ? ሁሉ ነገር ደህና እንደሆነ ተስፋ አለኝ ::

ሰላም ወንድሜ "anferara" ደህና ነህ ወይ ? አንዳንዴ ቅዳሜ እና እሑድ ዙረት ይኬድና ጊዜ አይበቃ ይሆናል :: ደግሞም የእኛ አትሌቲክስ ስፖርት አንዳንድ ቀዳዳዎች እየታዩበትና እኒያም እየሠፉ ስለሄዱ ሥጋትም አለ :: ለማንኛውም ሠፋ ያለ ዘገባ ይኖረኛል ::

አክባሪህ ::

ተድላ


ሳጅን :- ከዋርካ ወጥቶ ፓልቶክ መወሸቅም ዙረት ከተባለ እውነትም እግርዎ እስኪነቃ ይዞራሉ ቂቂቂቂቂቂቂ
እኔ ልንከራተትለዎ ቆራጡ የእምዬ ኢትዮጵያ ልጅ !!
ይቺን ስለተናገርኩ ዜግነቴን ይቀሙኝ ይሆን ሊጋባው አቡነ ዘዋርካ ?
_________________
"REASONABLE PEOPLE ADAPT THEMSELVES TO THE WORLD. UNREASONABLE PEOPLE ADAPT THE WORLD TO THEMSELVES. ALL PROGRESS, THEREFORE, DEPENDS ON UNREASONABLE PEOPLE." -George Bernard Shaw-
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed May 16, 2012 12:19 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም የአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

ባለፈው ስለ ማራቶኑ ጀግናችን ሻምበል አበበ ቢቂላ ያነበብነው ታሪክ በቋንቋ ውበቱ የተዋጣለት ቢሆንም በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ያለው መረጃ ውሱንነት በግልጽ የሚታይ ነው :: ዛሬ ያገኘሁት ጽሑፍ ከምንጩ ስለሆነ የበለጠ የተብራራ መረጃ ይሠጠናል ብዬ አስባለሁ ::

የኢትዮጵያን ሯጮች በማሠልጠን ረገድ ታላቅ ሥራ ያከናወኑት ሟቹ ስዊድናዊ ሻለቃ ኦኒ ኒስካነን ነበሩ :: እስከ ቶኪዮ ኦሎምፒክ ድረስ በተደጋጋሚ የኦሎምፒክ ቡድኑ ዋና አሠልጣኝ እና የቴክኒክ አማካሪ ሆነው አገልግለዋል :: እኒህ ታላቅ የኢትዮጵያውያን ባለውለታ ስለ ሻምበል አበበ ቢቂላ የሠጡትን መግለጫ ለእርሣቸው መታሠቢያ ከተዘጋጀ ድረ -ገፅ ላይ አግኝቼ እዚህ እንድታነቡት ሥቤ አምጥቼዋለሁ :: ሻለቃ ኦኒ መግለጫውን የሠጡት ለአንድ የዴንማርክ ዓመታዊ መጽሔት 1952 .. (... 1960) ነበር :: በሌላ ጊዜ ስለ እርሣቸውም አስተዋፅዖ አንዳንድ ጉዳዮችን ለማቅረብ እሞክራለሁ :: ለዛሬው መልካም ንባብ ::

ምንጭ :- How to train Olympic winners (1960). (From Duvbo IK's Annual Magazine 1960: Onni Niskanen tells the story about the marathon winner in Rome).

Quote:
Abebe Bikila, the Ethiopian soldier at the Imperial Life [Body] Guards, who won the XVII Olympic marathon race, was the biggest sensation during the Rome Olympics, according to many people. Not even backed, except by me, he ran a race that astounded most people and stepped from Ethiopian local competitions straight into the world é lite. Not only did he erase Emil Zatopek's Olympic record from Helsinki by 8.47 minutes, but also the Russian Popov's "phantom time" of 2:15:17.0 was erased by the unbelievably great running Abebe.

If needed, Bikila could have pressed the time even more. He put in the real spurt only some km from the finish, when he passed the Obelisk of Axum, an Italian war trophy that they had transported from Ethiopia, with great difficulties, during the Italian occupation.

If it had not been for a small misunderstanding in planning, the record time would most certainly have been even lower. Before the race, I had very carefully drummed the starting numbers of the 5 - 6 best competitors into the head of my two runners, Abebe Bikila and Abebe Wakjira. This was to let them know where the "big guns" were during the race. They were Popov, Rhadi, O'Gorman, Magee, Vorobiev, and a few others, whom I expected would be in the first lot during the race. After a lot of repetitions, my boys knew these starting numbers by heart. However, it turned out that Rhadi had not got his starting number according to the programme, but got permission to use the same number he had in the 10,000 metres race. That confused Abebe Bikila. Morocco had three men in the marathon and Abebe did not understand that it was Radhi, who ran together with him for the main part of the race. He thought that it was one of the other Moroccans keeping up with him, so he was waiting for Radhi to show up further on. Therefore, he saved his strength the last five kilometres and did not run faster than necessary. He was prepared to put in an extra effort if the Moroccan hot favourite Radhi showed up. The Italian doctor, who examined Abebe after the race, had only one word to say: "Fantastico!" His pulse was 88, his eyes bright, no signs of tiredness and not one blister on his bare feet. On my question, how far he could have continued at the same pace, Abebe answered: 10 - 15 km "ganano" (longer).

That Abebe Bikila won was not a surprise to me. I had pre-warned some newspaper reporters, but most of them did not dare to believe my tip-off. A Danish newspaper and the Finnish "Huvudstadsbladet" had an article about the race winner that I tipped them about, a couple of days before the race.

About the training and the preparations for the race? Well, first, I would like to say that I have not often worked with a better athlete student. He has strong willpower and willingness to train. He has been into sports for a couple of years, played basketball and run 5,000 and 10,000 metres a few times. In this year's Military Championship Games, he came second in the marathon race, with the time 2 hours 37 minutes, which was his personal best when I took him on for special training.

We then started a training focused on the Olympic Games. All candidates for the Olympic Games had special training programmes and they could show their form at continuous weekly competitions. During the last two months before the Olympic Games, the best of them were in a training camp, where it was tough training with two training sessions per day.

I noticed, at an early stage, that the long distance runners were the ones with the best possibilities and I concentrated especially on their training. As for the sprinters, I had an American, Leroy Walker, to help me with the training. Two Ethiopian instructors, educated at GCI (The Gymnastics Central Institute) in Sweden, also worked focused on the sprinters and the mid-distance runners.

Cross-country running sessions of 1 to 1½ hours were part of the daily training for the long distance runners, but not some casual jogging. Pace training, pace training and more pace training. Speed running for 4-500 metres at highest speed, up rather steep slopes, varied with a bit slower running in between.

The same thing when it came to track training. Pace! Six to eight 1,500 metres races, to start with in 4 minutes 20 to 25, then they had to press the times downwards. They also ran on the track for 30 - 40 minutes, with varied pace. Sometime full speed through the bends, sometimes on the straights. Road running was done twice per week and on distances that were increased day by day. Sauna baths twice a week was included in the training, as well as massage after the road running. Below are the results and times for the marathon runners' road training:

18/6 20 km no timing
23/6 25 km no timing
28/6 32 km in 1.45,00 (3.13 min/km)
30/6 32 km in 1..46,30 (3.16 min/km)
8/7 36 km in 2.00,45 (3.32 min/km) uphill a lot
25/7 42 km in 2.21,23 (3.21 min/km) selection for Olympic Games, uphill a lot
5/8 32 km in 1.42,16 (3.10 min/km)
20/8 20 km in 1.02,15 (3.07 min/km) in Rome
26/8 20 km in 1.01,30 (3.05 min/km) in Rome
30/8 20 km in 1.01,45 (3.05 min/km) in Rome
4/9 20 km in 1.01,05 (3.03 min/km) in Rome
10/9 42.195 km (the marathon race) in 2.15,16,2 (3.12,4 min/km)

During the month before race day, when we were in Rome, my two marathon runners ran parts of the marathon track 4 - 5 times, 20 km every time. Sometimes they ran the first part of the track, later the middle part and a couple of times the last 20 kilometres. This way they came to knew the whole track, all the difficulties and they did not have to hesitate about the where the track went.

I let them run alternately with or without shoes. I myself followed behind Abebe Bikila by car and studied style, foot stance and counted step speed. My brother Arne was in another car and studied Abebe Wakjira, who was always behind from the beginning. It appeared that Abebe Bikila was 5 - 6 steps slower per minute with shoes and his running style was not as perfect as when he ran barefoot.

After a few similar trials, we decided to let both of them run barefoot in the marathon race. The race took place in the evening, so the risk of hot tarmac was completely gone. After the decision, the runners ran barefoot all the time to harden the soles of their feet. Even in the Olympic Village, they had to walk around without shoes.

Up until three days before the race, both runners trained daily. In the early stage, they trained twice per day, but during the last week, it was cut down to one training session per day, alternatively in the stadium, cross-country or on the marathon track.

During the training period in Rome, I often added speed training. They ran 400 and 1,500 metres races, with a couple of minutes rest between each race, and 5,000 metres a couple of times. Abebe Bikila did 14.36 on 5,000 metres barefoot, without exhausting himself. That is not bad for a marathon runner!

On the race day, Abebe Bikila had orders to take it rather easy the first 25 kilometres and, if you look at the times in this world leading marathon race, you can see that he followed the instructions to the letter. Below are the official intermediate times of the race.

5 km 15,35 min = 15,35
10 km 31,07 min = 15,32
15 km 48,02 min = 16,55
20 km 1.02,39 hrs = 14,37
25 km 1.20,47 hrs = 14,08
30 km 1.34,29 hrs = 15,58
35 km 1.50,27 hrs = 7,31
42,195 km 2.15,16,2 = 17,18

Most of the hot favourites were left behind, due to the high speed between 20 and 30 kilometres. Radhi was the only one who could keep up, but the speed was too much even for him. That was obvious as he let go immediately when Abebe Bikila put in a spurt on the last kilometres. He never stood a chance!

After the race, I asked the happy triumphant victor how he felt when Radhi (who he did not know it was) started to drop behind. "When I sped up, inside the city wall, I heard less and less of the clattering footsteps behind me", said Abebe, "and when I increased the speed more, they disappeared. It was not necessary to turn around and look", he continued, "for if you have heard these footsteps behind you during a whole hour, then you know what it means when they fade away. I was happy. I did not fear a spurt fight, but it felt good to get rid of the stubborn Moroccan. And thank you, Major Onni, for what you have done!"

I was overjoyed by Abebe Bikila's victory, which means so much to my continuous work within sports in Ethiopia, but I must say that my joy was just as big for Abebe Wakjira's seventh place. He is 39 years old and before we left Addis, he had 2:30:26 as his best time at marathon, which by all means is not bad, and with that time, he was second after Abebe Bikila in the qualifying race. Some people thought it unnecessary to take him with us to Rome, but I protested and insisted that he had not finished his training. "Give me another month and you will see that he will improve. He is old and needs longer time to get in shape", I said. During the training period in Rome his form chart rose, as I had predicted, and when the marathon race went off, he was at the top of his capacity. He had always had problems keeping up with fast speed in the beginning, contrary to Abebe Bikila, and he took it easy in the Rome race as well. Maybe a bit too easy! He gradually advanced towards the lead and passed several of the favourites. He also had plenty of power left after the race and confessed that he probably had been too cautious the first 20 kilometres.

Unfortunately, I had to leave two of my best runners at home, due to illness. One marathon runner, who in fact was the one who won the Military Championship Marathon Race last spring when Abebe Bikila came second, and a very good 10,000 metres runner. The marathon runner, Besha Teklu, would certainly not have done as well as Abebe Bikila, but he was considerably better than the 7th placed Wakjira.

I have to tell a story about the 10,000 metres runner. He was ready for Rome. One day, when we were at the training camp, all of them had to go in to Addis for fitting of the Olympic costume. They got bus fare for the 50 km long trip and all was well. A few days after, Wami [Biratu] Berede, the best 10,000 metres runner, came down with a severe cold that kept him in bed for over a week. That was really bad luck and meant that one of my trump cards was gone. Some time later I heard that, instead of taking the bus in to Addis for the fitting of the costume, he had run the whole way there and back, 100 kilometres! He had done it with the best of intentions and, as he thought, by this 100 km run, train his stamina even more. Instead, he ruined his chances. The training programme I had set up was very tough itself and to run 100 km in one day, Saturday, when according to the programme he should take it easier than weekdays, was pure madness. It was probably also the cause of the cold that he got. To get back to Abebe Bikila, I would like to tell you that he has invitations to compete in several places: Spain, Argentina, Japan (two invites), Belgium, Czechoslovakia, and other places. It is impossible to accept all invites, but he will participate in 3 - 4 competitions abroad during next year. Since he is good at all distances from 5.000 metres upwards, I would rather see that he takes part in some races over shorter distances and a maximum of two marathons next year. It is also possible that we will come to Sweden!

Abebe Bikila's victory has in the highest degree opened up the possibilities for the continuous work with the athletes in Ethiopia. The interest in sports and especially long distance running has increased considerably after the triumph in the Rome Olympics and it is not difficult to get the boys to train anymore. We look forward with every hope towards the big tasks - the African Olympics 1962 and Tokyo 1964.
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed May 16, 2012 8:29 pm    Post subject: Reply with quote

ኢትዮጵያን ወክለው በሎንዶን ኦሎምፒክ የሚሣተፉት የማራቶን ሯጮች ዝርዝር ይፋ ሆነ ::

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሰኞ ግንቦት 6 ቀን በሠጠው መግለጫ ኢትዮጵያን ወክለው በሎንዶን ኦሎምፒክ በማራቶን የሚወዳደሩትን ሯጮች ዝርዝር ይፋ አድርጓል :: እንደ ከዚህ ቀደሙ አሁንም የፌዴሬሽኑ ውሣኔ ውዝግብ ያልተለየው ሆኖ ተገኝቷል :: ከሴት የማራቶን ሯጮች መካከል ባስመዘገበችው ሰዓት በሁለተኛ ደረጃ ያለቸው አሠለፈች መርጊያ ፌዴሬሽኑ ራሷን እንዳገለለች አድርጎ አስወርቷል : እርሷ ግን ራሴን አላገለልኩም እያለች ነው :: ከወንዶች ደግሞ የማነ ፀጋዬ ከአንደኛው በስተቀር ከሌሎቹ ሯጮች በማራቶን የተሻለ ሰዓት ማስመዝገቡ እየታወቀ '... 2012 ከአንድ ማራቶን በላይ መሮጥ አልነበረበትም ' በሚል ምክንያት የቡድኑ አባል እንዳይሆን ተደርጓል :: እንግዲህ እንዲህ ባሉ የተለመዱ የተንኮል ምርጫዎች የተተበተበው ቡድን በኋላ በውድድር ላይ ውጤት ሲጠፋ የፌዴሬሽኑ ሹመኞች 'እገሌ ሆን ብሎ የወርቅ ሜዳሊያ አስበላን : እገሊት እንዲህ አድርጋ ነበር : ወዘተርፈ ' እየተባለ በአትሌቶቹ ላይ የማይገባ አስተያዬት ይሠጣል :: 'ያሣዝናል ፍርድ ቤቱ አሉ ' Sad

የሴት ማራቶን ሯጮች
.._ሙሉ ሥም ______________________________ ... 2012 ያስመዘገበችው ጥሩ ሰዓት

1 ..... ቲኪ ገላና (የተመረጠች ) _____________________ በሮተርዳም ማራቶን 2 ሰዓት 18 ደቂቃ 58 ሴኮንድ
2 ..... አሠለፈች መርጊያ (?ከቡድኑ እንድትገለል ተደርጓል ?) ___ በዱባይ ማራቶን 2 ሰዓት 19 ደቂቃ 32 ሴኮንድ
3 ..... ማሬ ዲባባ (የተመረጠች ) _____________________ በዱባይ ማራቶን 2 ሰዓት 19 ደቂቃ 53 ሴኮንድ
4 ..... ብዙነሽ በቀለ (ተጠባባቂ ) _____________________ በዱባይ ማራቶን 2 ሰዓት 21 ደቂቃ 30 ሴኮንድ
5 ..... ትርፌ ፀጋዬ (ተጠባባቂ ) ______________________ በፓሪስ ማራቶን 2 ሰዓት 21 ደቂቃ 28 ሴኮንድ

የወንድ ማራቶን ሯጮች
.._ ሙሉ ስም _______________ ... 2012 ያስመዘገበው ጥሩ ሰዓት

1 ..... አየለ አብሸሮ (የተመረጠ ) _____ በዱባይ ማራቶን 2 ሰዓት 4 ደቂቃ 28 ሴኮንድ
2 ..... ጌቱ ፈለቀ (የተመረጠ ) _______ በሮተርዳም ማራቶን 2 ሰዓት 4 ደቂቃ 49 ሴኮንድ
3 ..... ዲኖ ስፍር (የተመረጠ ) ________ በዱባይ ማራቶን 2 ሰዓት 4 ደቂቃ 50 ሴኮንድ
4 ..... ማርቆስ ገነቴ (በተጠባባቂነት ) ___ በዱባይ ማራቶን 2 ሰዓት 4 ደቂቃ 53 ሴኮንድ
5 ..... ታደሰ ቶላ (በተጠባባቂነት ) _____ በዱባይ ማራቶን 2 ሰዓት 5 ደቂቃ 10 ሴኮንድ

ለማስታወስ ያህል ያልተመረጠው የማነ ፀጋዬ በሮተርዳም ማራቶን ያስመዘገበው ሰዓት :- 2 ሰዓት 4 ደቂቃ 48 ሴኮንድ ነበር (ምንጭ :- Wim van Hemert (for the IAAF), Sunday, April 15, 2012. Spectacular double Ethiopian success brings home 2:04 and 2:18 victories in Rotterdam.):: እርሱ እያለ በዚያ ውድድር ሁለተኛ የወጣው ጌቱ ፈለቀ በቡድኑ እንዲካተት ተደርጓል ::


ምንጭ :- ደረጀ ጠገናው : ሪፖርተር ጋዜጣ : ረቡዕ ግንቦት 8 ቀን 2004 .. :: የለንደን ኦሊምፒክ ማራቶን አትሌቶች ዝርዝር ይፋ ሆነ ::

Quote:
አሰለፈች መርጊያ ከቡድኑ ራሴን አላገለልኩም አለች

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በለንደን ኦሊምፒክ አገሪቱን በማራቶን የሚወክሉ አትሌቶች ዝርዝር ይፋ አደረገ፡፡

መምረጫ መስፈርቱ በዓለም አቀፍ ውድድር ፈጣን ሰዓትና ወቅታዊ ብቃት እንደነበሩም ተመልክቷል፡፡ ከብሔራዊ ቡድኑ መገለሏ የተነገረላት አሰለፈች መርጊያም ራሷን እንዳገለለች ተናግራለች፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ከትናንት በስቲያ ሰኞ በብሔራዊ ሆቴል በሰጠው መግለጫ፣ ለለንደኑ 30ኛው ኦሊምፒያድ ዝግጅት ሥልጠናውን በሦስት ምዕራፍ በመክፈል በአሁኑ ወቅትም የመጀመርያው ምዕራፍ ተጠናቆ ወደ ሁለተኛው ምዕራፍ የተሸጋገረበት ወቅት ላይ ይገኛል፡፡ አሁን ባለው ሒደትም በለንደን ኦሊምፒክ አገሪቱን የሚወክሉ የማራቶን ተወዳዳሪ አትሌቶችን በሁለቱም ጾታ መርጦ ይፋ አድርጓል፡፡

ሦስት፣ ሦስት በቋሚ አሰላለፍ ሁለት ሁለት ደግሞ በተጠባባቂነት የተመረጡት ወንድ አትሌቶች ውስጥ አትሌት አየለ አብሸሮ 2012 በዱባይ ማራቶን 2 ሰዓት 04 ደቂቃ 28 ሰከንድ፣ ጌቱ ፈለቀ በሮተርዳም ማራቶን 2 ሰዓት 04 ደቂቃ 49 ሰከንድና ዲኖ ስፍር በዱባይ ማራቶን 2 ሰዓት 04 ደቂቃ 50 ሰከንድ ከወቅታዊ ብቃቸው ጭምር ሚኒማ ያላቸው ሲመረጡ፣ ተጠባባቂዎች አትሌት ማርቆስ ገነቴ በዱባይ ማራቶን 2 ሰዓት 04 ደቂቃ፣ 53 ሰከንድ እና ታደሰ ቶላ በዱባይ ማራቶን 2 ሰዓት 05 ደቂቃ 10 ሰከንድ ሰዓት ያላቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሴቶች አትሌት ቲኪ ገላና 2012 ሮተርዳም ማራቶን 2 ሰዓት 18 ደቂቃ 58 ሰከንድ የመጀመርያዋ ስትሆን፣ አትሌት አሰለፈች መርጊያ ዱባይ ማራቶን 2 ሰዓት 19 ደቂቃ 32 ሰከንድ እና ማሬ ዲባባ በዱባይ ማራቶን 2 ሰዓት 19 ደቂቃ 53 ሰከንድ ሲሆኑ፣ ተጠባባቂዎች አትሌት ብዙነሽ በቀለ ዱባይ ማራቶን 2 ሰዓት 21 ደቂቃ 30 ሰከንድና ትርፌ ፀጋዬ በፓሪስ ማራቶን 2 ሰዓት 21 ደቂቃ 28 ሰከንድ ከወቅታዊ ብቃት ጋር ሚኒማ ያላቸው ናቸው፡፡

ምርጫውን አስመልክቶ በተለይም በሮተርዳም ማራቶን የሮጠው አትሌት የማነ ፀጋዬ ከሁሉም የተሻለ ሰዓት እያለው ለምን አልተመረጠም ? የሚል ጥያቄ ተነስቶ የፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ክፍል ኃላፊ አቶ ዱቤ ጅሎ፣ የመምረጫ መስፈርቱ 2012 ‹‹በአንድ ማራቶን የተወዳዳረ›› ይላል ብለው፣ ነገር ግን አትሌት የማነ ከሮተርዳም ማራቶን በፊት በዱባይ ማራቶን መሮጡ ከደንብና መመርያው አንጻር እንዳላስመረጠው አስረድተዋል፡፡

ከመካከለኛ ርቀት እስከ አሥር ሺሕ ሜትር የየቡድኖቹ ዋና ዋና አሠልጣኞች ከመጀመርያው የሥልጠና ምዕራፍ ወደ ሁለተኛው ምዕራፍ ሲሸጋገሩ የነበሩባቸውን ጠንካራ ጐኖች ከክፍቶቻቸው ጭምር አስረድተዋል፡፡

ከክፍተቶቹ ውስጥ በየኢቨንቱ በጉዳት ላይ የሚገኙ አትሌቶች በቶሎ አገግመው ሊመለሱ አለመቻላቸው ሲጠቀስ፣ ከነዚያ ውስጥ አትሌት ኢብራሂም ጀላን፣ ቃል ኪዳን ገዛኸኝ፣ እመቤት አንተነህ፣ ደረሰ መኮንንና መሰለች መልካሙን የመሳሰሉት ተጠቅሰዋል፡፡

እንደ ዋና አሠልጣኞቹ፣ አትሌቶቹ በፌዴሬሽኑ የሕክምና ቡድን አስፈላጊው ክትትል እየተደረገላቸው ቢሆንም፣ ነገር ግን ለንደን ኦሊምፒክ ከቀረው ጊዜ አኳያ ይደርሳሉ፣ አይደርሱም የሚለው ስጋት ሆኖብናል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል፣ ከማራቶን ብሔራዊ አትሌቶች፣ ከሴቶቹ አትሌት አሰለፈች መርጊያ ከቡድኑ ራሷን እንዳገለለች መነገሩን ተከትሎ አትሌቷ በዕለቱ መግለጫ ላይ ቀርባ ዘገባው እሷን እንደማይወክል፣ እውነት ቢሆን እንኳ የጉዳዩ ባለቤት እንደመሆኑዋ ዘገባው ይፋ ከመሆኑ በፊት መጠየቅ እንደነበረባት ተናግራለች፡፡

በእርግጥ ስትል አስተያየቷን የቀጠለችው አትሌቷ፣ ‹‹በብሔራዊ አሠልጣኙ የሚሰጠው ሥልጠና ካለኝ አቅም ጋር የማይመጣጠን በመሆኑ ለውጤቴ በማሰብ ጉዳዩ በፌዴሬሽኑ በኩል እልባት እንዲያገኝ ቅሬታዬን አቅርቤያለሁ፣ ራሴን ግን አላገለልኩም፤›› ብላለች፡፡

የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሠልጣኝ አቶ መላኩ ደረሰ በበኩላቸው፣ አሰለፈችን ጨምሮ ሁሉም አትሌቶች በየግል ማናጀሮቻቸው ሲሠለጥኑ የቆዩ በመሆኑ ያንን ወደ አንድ የቡድን ስሜት ለማምጣት መጀመርያ በሥነ ልቦናው ረገድ መሥራት የነበረበትን ለመሥራትና በዕቅዱ መሠረት ለመሔድ በተደረጉ እንቅስቃሴዎች ልዩነቶች ነበሩብን፡፡ ያም ሁኔታ የመጣው አትሌቶቹ ቸኩለው ወደ ዋናው ሥልጠና ለመግባት ጉጉት ስለነበራቸው ነው፡፡ እንደዚያም ሆኖ ሥልጠናው እስከቀጠለ ድረስ ልዩነቶች ሊኖሩ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ በሥራ ላይ ከሚከሰቱ ልዩነቶች ውጪ በግል ግን ምንም ዓይነት ልዩነትም ሆነ ጠብ እንደሌላቸው ጭምር ዋና አሠልጣኙ አስረድተዋል፡፡

በመጨረሻም 30ኛው የለንደን ኦሊምፒክ የተሻለ ሰዓት የሚያመጡ አትሌቶች ለመለየት፣ በብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ሙሉ ወጪ በተዘጋጀው በሄንግሎው 10 ሺሕ ሜትር ውድድር ላይ የሚቀርቡት አትሌቶች ዝርዝር ተነግሯል፡፡

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ፣ ኢማና መርጊያ፣ ስለሺ ስህን፣ አዝመራው በቀለ፣ አፀዱ ፀጋዬ፣ ሌሊሳ ደሲሳ፣ ጥላሁን ረጋሳ፣ የትዋለ ክንዴ፣ ምሱነት ገረመው፣ መካሻው እሸቴ፣ ብርሃኑ ዴሮ፣ ታሪኩ በቀለ፣ በለጠ አሰፋ፣ አበራ ኩማ፣ ኃይሌ ገብረሥላሴና ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያም ሲሆኑ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለውድድሩ እስከ ግማሽ ሚሊዮን ማውጣቱም ታውቋል፡፡ በተመሳሳይ ሴቶች ሰኔ ወር መጀመርያ ላይ በአሜሪካ ዪጂን እንደሚሮጡ ሲታወቅ፣ የውድድሩ ወጪ በማናጀሮች እንደሚሸፈን ነው የተነገረው፡፡
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed May 16, 2012 9:03 pm    Post subject: Reply with quote

ረቡዕ ግንቦት 8 ቀን 2004 ..

የዳ -- የአትሌቲክስ ፉክክር ::


የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር ዕውቅና ከሠጣቸውና በየዓመቱ ከሚዘጋጁት ውድድሮች አንዱ የሆነው ይህ በዳ -- የተካሄደው ነው :: በዘንድሮው ውድድር መሐመድ አማን በጥሩ ሰዓት (1 ደቂቃ 43.51 ሴኮንድ ) 800 ሜትር ሩጫ አሸናፊ ሲሆን (ምንጭ ) መስከረም አሰፋ ደግሞ 1,500 ሜትር ሩጫን 4 ደቂቃ 6.52 ሴኮንድ በማጠናቀቅ ሁለተኛ ሆናለች (ምንጭ ) ::

መሐመድ አማን ገለቶ በሎንዶን ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን በርቀቱ የሜዳሊያ ባለቤት ሊያደርጋት የሚችል ተስፋ ያለው ወጣት ነው ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri May 18, 2012 11:57 pm    Post subject: Reply with quote

በቆጂ :- የሯጮች ከተማ ::

በቆጂ በአርሲ ከሚገኙት መካከለኛ ከተሞች አንዷ ናት :: ይህቺ ከተማ ኢትዮጵያን በአትሌቲክስ ስፖርት በዓለም ካሣወቋት ታላላቅ አትሌቶች የአብዛኞቹ መፍለቂያ ናት (ደራርቱ ቱሉ : እጅጋዬሁ ዲባባ : ጥሩነሽ ዲባባ : ማሬ ዲባባ : ገንዘቤ ዲባባ : ቀነኒሣ በቀለ : ታሪኩ በቀለ : ወዘተርፈ ) :: ስለዚህ ጉዳይ ባለፉት ሦሥት ዓመታት "Town of Runners" በሚል ርዕስ አንድ ጥናታዊ ዘገባ ያዘለ ፊልም "Indiegogo" በሚባል የእንግሊዝ ተቋም ተዘጋጅቶ ባለፈው ወር ሚያዝያ 12 ቀን 2004 .. (April 20, 2012) በይፋ ተመርቋል :: ተቋሙ በድረ -ገፅ ላይ ከለጠፋቸው ቅንጭብጫቢ ፊልሞች ተቋደሡ ::

ምንጮች :-

1 ..... Town of Runners.

2 ..... Discover the Town.

3 ..... Meet the Runners - Alem Tsegaye.

4 ..... Meet the Runners - Hawi Megersa.

5 ..... Chasing A Dream.

6 ..... The Town Of Runners on Facebook.


ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sat May 19, 2012 7:45 pm    Post subject: Reply with quote

ቅዳሜ ግንቦት 11 ቀን 2004 ..::

በሻንጋይ የዓለም የአልማዝ ደረጃ የአትሌቲክስ ፉክክር ገንዘቤ እና ሀጎስ ወርቅ በወርቅ ሆኑ ::


የዓመቱ የአልማዝ ደረጃ የአትሌቲክስ ፉክክር ባለፈው ሣምንት አርብ ግንቦት 3 ቀን በዶሃ (ቃጣር ) እንደተጀመረ ይታወሣል :: ዛሬ በተደረገው የሁለተኛው ዙር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አስደማሚ ውጤቶችን አስመዝግበዋል :: በታላላቅ እህቶቿ እግር የተተካቸው ገንዘቤ ዲባባ 1,500 ሜትር ሩጫ ውድድርን ስትሣተፍ እምብዛም አትታወቅም :: ሆኖም ዛሬ 3 ደቂቃ 57.77 ሴኮንድ ውድድሩን ስትፈፅም በርቀቱ የዓመቱን : የውድድሩን እና የኢትዮጵያን ሬኮርዶች ሠባብራ በአንደኝነት አሸንፋለች :: በወንዶች 5,000 ሜትር ሩጫ ሀጎስ ገብረሕይወት እነ ቀነኒሣን ቀድሞ 13 ደቂቃ 11.00 ሴኮንድ ውድድሩን ሲያጠናቅቅ የዓመቱን እና የውድድሩን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ነበር :: በሴቶች 3,000 የመሠናክል ሩጫ ሶፊያ አሰፋ ረዳት አጣች እንጂ ኬንያውያንን ያለመታከት እየተፎካከረች ትገኛለች : በዛሬውም ውድድር 2 ሆናለች :: ዝርዝር ውጤቶቹ የሚከተለውን ይመስላሉ ::

የሴቶች ምድብ

ምንጭ :- 1,500 ሜትር ሩጫ የውጤት ሠንጠረዥ ::

1 ..... ገንዘቤ ዲባባ _____ 3 ደቂቃ 57.77 ሴኮንድ (የዓመቱ : የውድድሩ እና የኢትዮጵያ ሬኮርድ )
2 ..... አበባ አረጋዊ _____ 3 ደቂቃ 59.23 ሴኮንድ (በግሏ ጥሩ ሰዓት )
9 ..... መስከረም አሰፋ ___ 4 ደቂቃ 07.96 ሴኮንድ
12 ... ሠንበሬ ተፈሪ _____ 4 ደቂቃ 10.49 ሴኮንድ (በግሏ ጥሩ ሰዓት )

ምንጭ :- 3,000 ሜትር መሠናክል ሩጫ የውጤት ሠንጠረዥ ::
2 ..... ሶፊያ አሰፋ __________ 9 ደቂቃ 16.83 ሴኮንድ
10 .. ብርቱካን አዳሙ _______ 9 ደቂቃ 41.71 ሴኮንድ
13 .. አልማዝ አያና _________ 9 ደቂቃ 59.31 ሴኮንድ
--- ... ብርቱካን ፈንቴ ዓለሙ ___ በውድድሩ አልተሣተፈችም

የወንዶች ምድብ

ምንጭ :- 5,000 ሜትር ሩጫ የውጤት ሠንጠረዥ ::

1 ..... ሀጎስ ገብረሕይወት _____ 13 ደቂቃ 11.00 ሴኮንድ (የዓመቱ እና የውድድሩ ሬኮርድ )
5 ..... ቀነኒሣ በቀለ __________ 13 ደቂቃ 13.89 ሴኮንድ
6 ..... የኔው አላምረው _______ 13 ደቂቃ 14.26 ሴኮንድ
10 ... ሞስነት ገረመው _______ 13 ደቂቃ 17.41 ሴኮንድ
13 ... ይታያል አጥናፉ ዘሪሁን __ 13 ደቂቃ 21.27 ሴኮንድ

ባለፈው ሣምንት በዶሃው ውድድር ፋንቱ ማጌሶ ማኔቦ የሴቶችን 800 ሜትር ሩጫ 1ኛነት ስታሸንፍ የኢትዮጵያን ሬኮርድ ሠብራ ነበር :: ዛሬ ደግሞ ገንዘቤ ዲባባ 1,500 ሜትር ሩጫ የኢትዮጵያን ብቻ ሣይሆን የዓመቱን እና የውድድሩንም ጭምር ሬኮርዶች ሠባብራለች :: ስለዚህ በሎንዶን ኦሎምፒክ በሴቶች 800 እና 1,500 ሜትሮች ሜዳሊያ መጠበቅ ይቻል ይሆን Rolling Eyes

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun May 20, 2012 2:03 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም በድጋሚ :-

ከሻንጋይ ውድድር ጥቂት የቪዲዮ ፊልሞች :-

ምንጮች :-

ሀጎስ ገብረሕይወት ያሸነፈበት 5,000 ሜትር ርቀት የሩጫ ውድድር ::
1 ..... Universal Sports, published on May 19, 2012. Hagos Gebrhiwet wins 5000m in Shanghai - from Universal Sports.

ገንዘቤ ዲባባ ያሸነፈችበት 1,500 ሜትር ርቀት የሩጫ ውድድር ::
2 ..... Universal Sports, published on May 19, 2012. Genzebe Dibaba wins 1500m in Shanghai DL - from Universal Sports.


ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ


Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun May 27, 2012 10:26 pm    Post subject: Reply with quote

እሑድ ግንቦት 19 ቀን 2004 ..

የሣምንቱ መጨረሻ የአትሌቲክስ ውድድር ዘገባዎች ::


ዛሬ እሑድ በሔንግሎ (ሆላንድ ) በተደረጉት የአትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን ሯጮች ለሜዳሊያ እና ለኦሎምፒክ ማጣሪያ ተወዳድረው ነበር :: በወንዶች ምድብ 10,000 ሜትር የሩጫ ውድድር የተሣተፉት 16 ራጮች በሎንዶን ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን ወክለው ለመወዳደር ያደረጉት የማጣሪያ ውድድር ነበር :: ኢትዮጵያውያን ሯጮች ለማጣሪያ ውድድር ከአገር ውጪ ሲወዳደሩ ምናልባትም በታሪክ የመጀመሪያው ሣይሆን አይቀርም :: በውድድሩም ታሪኩ በቀለ 1 ሆኗል :: በዚህ ውድድር ቀነኒሣ አልተሣተፈም :: ምናልባትም ይህ የሌላ ውዝግብ መንስዔ መሆኑ አይቀርም ::

ራባት (ሞሮኮ ) በተደረገው የአትሌቲክስ ፉክክር በታሪክ አንድ የጥሩ አቅጣጫ ጠቋሚ ታይቷል :- በወንዶችም ሆነ በሴቶች ምድቦች 3,000 ሜትር የመሠናክል ሩጫ ኢትዮጵያውያን ኬንያውያንን እያስከተሉ አሸንፈዋል :: በሴቶች ምድብ አሸናፊ የሆነችው ሕይወት አያሌው ስትሆን በወንዶች ምድብ ደግሞ ያሸነፈው ባለፉት ዓመታት በተደጋጋሚ በኬንያውያን እየተቀደመ 2ኛነትን ሲደጋግም የቆየው ሮባ ጋሪ ነው :: ምናልባት ይህ ውጤት ለወደፊቱ ኢትዮጵያውያን ሯጮች በርቀቱ ተወዳድረው ለማሸነፍ በራስ የመተማመን ስሜት ያጎለብትላቸዋል ብዬ አስባለሁ ::

በሣምንቱ መጨረሻ ከተደረጉትና ኢትዮጵያውያን በተሣተፉባቸው ውድድሮች ውጤታቸው የሚከተሉትን ይመስላል ::

የሔንግሎ ውድድር Fanny Blankers-Koen Games, Hengelo (NED) - Sunday, May 27, 2012.

ምንጭ :- የወንዶች 10,000 ሜትር ሩጫ ውድድር የውጤት ሠንጠረዥ ::

1 ታሪኩ በቀለ _________________ 27 ደቂቃ 11.70 ሴኮንድ
2 ሌሊሣ ደሢሣ ________________ 27 ደቂቃ 11.98 ሴኮንድ
3 ስለሺ ሥህን _________________ 27 ደቂቃ 12.60 ሴኮንድ
4 ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያም ___ 27 ደቂቃ 13.66 ሴኮንድ
6 ጥላሁን ረጋሣ ________________ 27 ደቂቃ 18.90 ሴኮንድ
7 ኃይሌ ገብረሥላሤ _____________ 27 ደቂቃ 20.39 ሴኮንድ
8 አበራ ኩማ __________________ 27 ደቂቃ 25.20 ሴኮንድ
9 ኢማኒ መርጋ _________________ 27 ደቂቃ 42.39 ሴኮንድ
10 አዝመራው በቀለ ______________ 27 ደቂቃ 49.16 ሴኮንድ
16 በለጠ አሰፋ _________________ 28 ደቂቃ 28.50 ሴኮንድ
19 አሊ አብዶሽ _________________ 28 ደቂቃ 54.69 ሴኮንድ
___ ብርሃኑ ዴሮ _________________ ውድድሩን አልጨረሠም
___ መካሻው እሸቴ _______________ ውድድሩን አልጨረሠም
___ ሞስነት ገረመው ______________ ውድድሩን አልጨረሠም
___ የትዋለ ክንዴ _________________ ውድድሩን አልጨረሠም
___ አፀዱ ፀጋዬ __________________ ውድድሩን አልጨረሠም

ምንጭ :- የወንዶች 1,500 ሜትር የሩጫ ውድድር የውጤት ሠንጠረዥ ::]
3 መኮንን ገብረመድህን ____ 3 ደቂቃ 31.45 ሴኮንድ
5 ዳዊት ወልዴ __________ 3 ደቂቃ 33.82 ሴኮንድ
10 ተሾመ ድሪሣ _________ 3 ደቂቃ 35.46 ሴኮንድ

ምንጭ :- የሴቶች 1,500 ሜትር የሩጫ ውድድር የውጤት ሠንጠረዥ ::
12 ትዝታ ቦጋለ ___________4 ደቂቃ 9.29 ሴኮንድ

የመሐመድ 5 መታሠቢያ የአትሌቲክስ ፉክክር : ራባት (ሞሮኮ ) Meeting International Mohammed VI d'Athlé tisme, Rabat (MAR) - Sunday, May 27, 2012

የሴቶች ምድብ


ምንጭ :- የሴቶች 3,000 ሜትር የመሠናክል ሩጫ ውድድር የውጤት ሠንጠረዥ ::

1 ሕይወት አያሌው _______ 9 ደቂቃ 16.14 ሴኮንድ
6 መቅደስ በቀለ _________ 9 ደቂቃ 37.18 ሴኮንድ
8 ብርቱካን አዳሙ ________ 9 ደቂቃ 48.98 ሴኮንድ

ምንጭ :- የሴቶች 5,000 ሜትር ሩጫ ውድድር የውጤት ሠንጠረዥ ::
4 አፈራ ጎደፋይ __________ 15 ደቂቃ 1.20 ሴኮንድ
5 አዝመራ ገብሩ __________ 15 ደቂቃ 11.91 ሴኮንድ
10 አለምነሽ በለጠ ________ 15 ደቂቃ 32.68 ሴኮንድ
12 ዋጋነሽ መካሻ __________ 15 ደቂቃ 36.64 ሴኮንድ

ምንጭ :- የሴቶች 1,500 ሜትር የሩጫ ውድድር የውጤት ሠንጠረዥ ::
6 ጉዴቶ ፈየኔ _____________ 4 ደቂቃ 10.90 ሴኮንድ
__ብርቱካን ፈይሣ ___________ ውድድሯን አላጠናቀቀችም

ምንጭ :- የሴቶች 800 ሜትር የሩጫ ውድድር የውጤት ሠንጠረዥ ::
9 ማንጠግቦሽ መለሰ ________ 2 ደቂቃ 5.08 ሴኮንድ

የወንዶች ምድብ

ምንጭ :- የወንዶች 3,000 ሜትር የመሠናክል ሩጫ የውጤት ሠንጠረዥ ::

1 ሮባ ጋሪ __________ 8 ደቂቃ 10.04 ሴኮንድ
5 ብርሃን ጌታሁን _____ 8 ደቂቃ 18.74 ሴኮንድ
__ሲሣይ ኮርሜ ________ ውድድሩን አላጠናቀቀም

ምንጭ :- የወንዶች 1,500 ሜትር የሩጫ ውድድር የውጤት ሠንጠረዥ ::
5 አማን ወቴ ______ 3 ደቂቃ 35.38 ሴኮንድ

ምንጭ :- የወንዶች 800 ሜትር የሩጫ ውድድር የውጤት ሠንጠረዥ ::
1 መሐመድ አማን ____ 1 ደቂቃ 43.58 ሴኮንድ

ምንጭ :- የወንዶች 5,000 ሜትር ሩጫ የውጤት ሠንጠረዥ ::
17 አባይነህ አየለ ___ 13 ደቂቃ 36.98 ሴኮንድ

ከእነዚህ ትልልቅ ውድድሮች ሌላ በኦታዋ ማራቶን የሺ ኢሣያስ 2 ሰዓት 28 ደቂቃ 46 ሴኮንድ 1 ስትሆን የአገሯ ልጅ ብሩክታይት ደገፋ 2 ሰዓት 27 ደቂቃ 34 ሴኮንድ 2ኛነት ተከትላት ገብታለች ::

ምንጭ :- Paul Gains (for the IAAF), Sunday, May 27, 2012. Moiben defends Ottawa Title.

በባንግሎር 10 .. የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን ብዙም አልቀናቸውም ::
ምንጭ :- Ram. Murali Krishnan (for the IAAF), Sunday, May 27, 2012. Kipsang and Kiprop lead Kenyan double podium sweep in Bangalore.

ትላንት ቅዳሜ በኦታዋ (ካናዳ ) በተደረገው 10 .. የአገር አቋራጭ የሩጫ ውድድር በወንዶች ምድብ ባለፈው የቦስተንን እና የኒው ዮርክ ማራቶኖችን ሬኮርድ በመሥበር ያሸነፈው ኬንያዊው ጆፍሬይ ሙታይ 27 ደቂቃ 42 ሴኮንድ በመጨረስ በዚህም ርቀት አይበገሬነቱን አስመስክሯል :: ኢትዮጵያዊው ታደሰ ቶላ 29 ደቂቃ 1 ሴኮንድ በመጨረስ 4 ሆኗል :: በሴቶች ምድብ ኢትዮጵያውያኑ አለሚቱ አበራ እና አለምጸሐይ ምስጋናው በአሜሪካዊቷ ሊንድሴይ ሽረፍ ተቀድመው ሁለተኛ እና ሦሥተኛ ሆነው ውድድራቸውን ጨርሠዋል ::
ምንጭ :- Paul Gains (for the IAAF), Sunday, May 27, 2012. Mutai Destroys Field on Warm Night in Ottawa.

በመጪው ሣምንት በዛ ያሉ ውድድሮች ይኖራሉ :: በተለይ ኢውጂን (ኦሬገን ግዛት : አሜሪካ ) በሚደረገው ውድድር ሴት ኢትዮጵያውያን ሯጮች 10,000 ሜትር ሩጫ ኢትዮጵያን ወክለው ለመወዳደር የማጣሪያ ውድድር የሚያደርጉበት ስለሆነ ውድድሩን በጉጉት የሚጠበቅ ያደርገዋል :: እንግዲህ እየተከታተልኩ ውጤት በትኩሱ ለማሣወቅ እጥራለሁ ::

ቸር እንሠንብት ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች


Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Mon May 28, 2012 1:15 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

ተድልሽ = የሄንግሎውን ሁጤት በጉጉት እየጠበኩ ነበር ::ኢማነ መርጊያ በዚህ ውድድር ባመጣው ሁጤት
ለሎንዶን ኦሎምፒክ የማይመረጥ ቢሆን እጅግ ሊገርመኝ ይችላል ::በዚሁ አንጻርም የታሪኩ በቀለ 1 ሆኖ መጨረስ ቢያስደንቀኝም በሱ ልጅ ላይ
ለምን እንደሆን ባላውቅም ሙሉ እምነት ኖሮኝ አያውቅም ::ስለሺ ስህንም በሩጫው አለም የመቆየቱን ያህል በሎንዶን ኦሎምፒክ
ለተተኪዎች ለቀቅ ቢያደርግ መልካም ይመስለኛል ::ይህን ስል ለስለሺ ያለኝ ክብር ፍጹም ስይቀንስ ጭምር ነው ::
የቀነኒሳ ብቃት እንደቀድሞው ያለመሆኑ ምክንያት ዘግይቶ ወደ ውድድር የመግባቱ ሁነታ ቢሆንም ኦሎምፒክ ቢመረጥ አንድ ጥሩ ነገር ይሰራል የሚል እምነት አለኝ ::
ምናልባት በቀሪው ግዜ እራሱን አሻሽሎ የመመረጫ ካርዱን ይጨብጥ ይሆናል ::

በማራቶን በቂ ሀይል ያለን እንደሆነ ቢያሳምንም ካሉት ተፎካካሪ ሀገሮች አንጻር ትልቅ ትግል ይጠብቀናል ::
ባጠቃላይ ለዘንድሮው ኦሎምፒክ ሄሮዎች ስለሌሉን በሙሉ ልብ ሁጤታችን አጣጋቢ ይሆናል ለማለት የሚከብድ ይመስላል ::

ቸር እንሰንብት !!!
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 44, 45, 46 ... 53, 54, 55  Next
Page 45 of 55

 
Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum


Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia