WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ይድረስ ለነገደ አርበኛ !!
Goto page Previous  1, 2, 3  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ዓለማየሁ

አለቃ

Joined: 15 Dec 2003
Posts: 2315

PostPosted: Sun May 06, 2012 4:28 am    Post subject: Reply with quote

Quote:

ግዛቸው እንደጻፈ(ች)ው:

ወራሪዎችና ወያኔወች እኛ ከማንም በላይ የምንኮራበትንና አለም ሁል የተገረመመበት አንጸባሪቂውን ታሪካችን ላማጥፋጥ ቀን ከሌት እየሰራ ቢኖንም ወያኔና ባንዳው እራሱ ይጠፋል እንጅ ምን ግዜም የምንኮራበት ታሪካችን ለዘላለም እንዳንጸባረቀ ይኖራል ::

ሞት ታሪክ ለሌላቸውና የታሪክ ጠላቶች ለሆኑት ወያኔዎች ሁሉ ::
ነጻነት ድልና ጥንካሬ ወያኔን እየተፋለሙል ላለው ጀግናው የኢትዮጵያ ህዝብ ::

በለው Exclamation .That's what I'm talking about Exclamation Exclamation Thank you ግዛቸው :: እንክዋን አብሮ አደረሰን ወንድሜ :: ላንተም አንድ ግብዣ ልጋብዝህ ግዛቸው -ነገደ አርበኛ
ሁሉ ማየት የሚገባው ቪዲዮ ነው ::አደራ እስከመጨረሻው
ይሄንን ቪዲዮ ተመልከትልኝ .. የአራዳ ልጅ .. የታገለ ሰይፉ ግጥም ነው :: Enjoy
http://youtu.be/RPOhBeaPZZQ

_________________
http://img28.imageshack.us/img28/3931/etho.jpg
http://img33.imageshack.us/img33/9715/alemayehu.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ayantu

አዲስ

Joined: 09 Mar 2012
Posts: 32
Location: addis ababa

PostPosted: Sun May 06, 2012 4:34 am    Post subject: Reply with quote

ውድ ዳግማዊ ! ምክንያታዊ ሰው ትመስለኝ ነበር ! የሆነ የህጻናት ብሽሽቅ አደረከው :: ላለፉት ጥቂት የማይባሉ አመታት የምትለውን ስከታተል ቆይቻለሁ :: ካንተ ጋር የምስማማበትም የማልስማማብትም ሀሳብ እና አመለካከት ቢኖርም አቁዋምህን አከብራለሁ ::
የምትደግፈውን ኢሀዲግ ለማወደስ ደርግን በመስደብ መጀመር የአስተሳሰብ ድህነት :እደግፈዋልሁ በሚሉት ድርጅት እምነት ማጣት እንዲሁም የስብእና ዝቅጠት ምልክት ነው :: የመለስ ዜናዊን ግዝፈት ለማሳየት ንጉስ ሀይለ ስላሴን ማንኳሰስ ከምቀኝነት እና ከበታችነት ሰሜት ካልመነጨ ምን ሊባል ነው !? የአምስቱ አመት የአርበኞች ተጋድሎ እንዲሁም በሗላ ለተገኘው ድል ጣፈጠህም መረረህም የመሪው የንጉስ ሀይለ ስላሴ ፖለቴካዊም ሆነ ዲፕሎማሳዊ ትግል ወሳኝ ነበር :: እንግሊዝም ቢሆን ለራሱ ብሎ እንጂ የኢትዮጵያን አርበኞች የረዳው ለመጽደቅ ብሎ እንዳልሆነ ይታወቅ !! ለማንኛውም ስለ ሀይለስላሴ ጥቂት ነገሮች ይዤ መምጣቴ አይቀርም ! እመነኝ ግን ......ስለ ንጉስ ሀይለ ስላሴ ጥሩነት ለማውራት የሀይለ ስላሴ ጉግሳን ባንዳነት በማውራት አልጀምረም !! ምክንያቱም የንጉሱን ታሪክ ያኮስስብኛል !!
መልካም ምሽት !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
መቅደላዊ

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Dec 2009
Posts: 599
Location: Ethiopia

PostPosted: Sun May 06, 2012 4:47 am    Post subject: Reply with quote

ሚያዝያ 27 መታሰበያ መደረግ አለበት :: ውጭ አገር ያለው የኢትዮጲያ ተወላጅ ሁሉ ቀኑን እንዲያስታውስ ቢደረግ ጥሩ ነው :: በሰሜን አመሪካና በአውሮጳ ያላችሁት ሚያዝያ 27 በአለም አቀፍ ደረጃ ታስቦ እንዲውልና የኢትዮጲያ አረበኞች እንዲታወሱ እንዲደርግ ማደረግ ይገባል ::

ኢትዮጲያ ለዘለአለም ትኑር !
_________________
United we stand, divided we fall!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አንፌቃ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 08 Dec 2004
Posts: 1920
Location: united states

PostPosted: Sun May 06, 2012 4:54 am    Post subject: Re: ይድረስ ለነገደ አርበኛ !! Reply with quote

ሰላም አለማየሁ እህቴ ...ትልቕ ምስጋና ስለማስታወሻሽ ..እንኳን በሰላም አብሮ አደረሰን Exclamation Exclamation

ዓለማየሁ እንደጻፈ(ች)ው:
የኢትዮጵያ አርበኛ ልጅ የልጅ ልጅ ልጆች የሆናቹ (ዘረማን ዘረ ባንዳ የባንዳ ልጅ ያልሆናቹ ) የዋርካ ኢትዮጵያኖች ሆይ Exclamation እንክዋን ለዚህ ለአባቶቻችን ድል መታሰቢያ ቀን በሰላም አደረሳቹህ :: ይህ ቀን ወያኔን የሚያፈራ ኢትዮጵያዊን የሚያስኮራ ቀን ነው :: ክብረ በዓሉ እንዳይደምቅ ከታሪክ እንዲደለዝ ወራሪው ባንዳ ወያኔ በከንቱ ቢለፉም ነጻነት ናፋቂው የኢትዮጵያ ህዝብ ዛሬ ከመቼውም በላይ ቀኑን እየቆጠረ ያስታውሰዋል :: መላው የአለም ጥቁር ህዝብ ሚያዚያ 27 ያስታውሳል Exclamation
http://img233.imageshack.us/img233/6643/miazia27.jpg
Dear CyberEthiopia Warka patriots, the flame of our forefathers' sacred sacrifice can never be extinguished.Their triumph over the facists and their banda footsoldiers is eternal. Their victory is ours. Until the end of time the victory of good over evil is guaranteed. እንክዋን አብሮ ደስ አለን Exclamation
http://www.youtube.com/watch?v=50YO68g_Zb4

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች ::

_________________
Article-39: The poison of peace, unity, and brotherhood in Ethiopia !!
አንፌቃ ዘብሄረ ኢትዮጲያ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ችበሀ

ኮትኳች

Joined: 09 Nov 2003
Posts: 272

PostPosted: Sun May 06, 2012 5:03 am    Post subject: Reply with quote

አባት አያት ቅድም አያቶቻችሁ ያገራችንን አንድነት ለማስጠበቅ ሲዋደቁ ለኖሩ የጀግኖች ኢትዮጵያውያን አርበኞች ዝርያዎች እንኳን ለዚህ ቀን አደረሳችሁ

ዛሬ በሄድንበት ሁሉ አንገታችንን አቅንተን ቅኝ ገዥዎችን ባንበረከከው ታሪካችን እንድንኮራ በነጻነት የኖርን ሕዝቦች መሆናችን እንዲታውቅ ለማድረግ ደማቸውን አፍሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ታላቅ አገር ላስተላለፉልን ጀግኖቻችን ምስጋና ይግባቸው

ሕያዋን አርበኞቻችን ሆይ !
ጠላትማ ጠላት ምንግዜም ጠላት ነው
አስቅድሞ መግደል አሾክሻኪውን ነው በማለት
ባንዳንና ከሀዲን በተግቢው ብትቀጡም ይኸው አሁን ትንንሽ የበታችነት ስሜት ያኮሰሳቸው የባንዳ ትላትሎች አገራችንን አድምተው ህዝቡን ከፋፍለው ጮቤ እየረገጡ አጽማችሁን እረፍት ነሱብን

ታሪክ አልባዎችና ማፈሪያዎች በናንተ ባርበኞቹ ልጆች ኩራት እየቀኑና አይናቸው ደም እየለበሰ ላንድነቱ ስትሉ የተዋድቃችሁለትን ታጋሹንና ልበሙሉውን ኢትዮጵያዊ ተሳለቁበት

ዳግማዊ ባንዳዎች ተፈልፍለው አገሪቷን ለጠላቶቿ አሳልፈው በብር እየቸበቸቡ ነው
ስለዚህ እነዚህ የእበት ትሎች ፍቅርና ትዕግሥት የማይገባቸው ደናቁርት በመሆናቸው ለባንዳ የሚገባውን ምስ መቀበያ ጊዚያቸው ተቃርቧል

ይህ የኢትዮጵያውያን ቃል አያልፍም
ባንዳና ወያኔ ግን ከነተሳቢያቸው ያልፋሉ

ሰላም እንሰንብት
ችበሀ ነኝ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ዓለማየሁ

አለቃ

Joined: 15 Dec 2003
Posts: 2315

PostPosted: Sun May 06, 2012 5:42 am    Post subject: Re: ይድረስ ለነገደ አርበኛ !! Reply with quote

ሰላም አንፌቃ ቢሄረ ኢትዮጵያ ነገደ አርበኛ ! እንክዋን ደህና መጣህ ! እንክዋንም አብሮ አደረሰን :: በዚህ በታሪካዊ ቀን ላንተ የምጋብዘው ዘፈንም አይደለም ግጥምም አይደለም !! ታሪክ ነው Exclamation ታሪኩ ደሞ ስለ ኢትዮጵያ አርበኞች ብቻ ሳይሆን የጃፓን ንጉስና ህዝብ ለኢትዮጵያኖች የነጻነት ትግል ..በተለይ ለኢትዮጵያ አርበኞች ስለሰጡት ድጋፍ ነው Shocked ምናልባት አንተ already ታውቀው ይሆናል ግን ለካስ የኛ የነገደ አርበኛ ድል ..የጥቁር ህዝብ ድል ብቻ ሳይሆን የቢጫ ህዝብም ድል ነው ለካስ ..WOW Exclamation Shocked የዚህ አስገራሚ ታሪክ ዘገባ THE SUGIMURA AFFAIR OF JULY 1935 ይባላል ከታች ያለው ጥቅስ ከዛና አንድ ሌላ ዘገባ የተቀንጨበ ነው :: በመጨረሻ የጃፓን ምንግስት .. በተለይ ሱጊሙራ የተባለው ከሀዲ የጃፓን በለስጣን ከኢትዮጵያ ይልቅ ከጣልያኖች ጋር መቆሙን መረጠ እንጂ የጃፓን ንጉስና የጃፓን ህዝብ እስከመጨረሻው ከኢትዮጵያኖች ጎን ነበረ ::
የኢትዮጵያ አምላክም ኢትዮጵያን አልካዳትም ::
ENJOY THE READING አንፌቃ !
Quote:
In the first half of the 1930s, the nations of Japan and Ethiopia drew closer together to the acute concern of all of Africa's colonial powers, most especially Italy. Much came to trouble Rome about Japanese activities including their economic and political encroachments into Northeast Africa. Rumors exaggerated the extent of the threat. Particularly vexing were reports of increasing Japanese military influence in Ethiopia. The threat of Japanese political, commercial, and military intrusions into Ethiopia to statesmen in London, Paris, Moscow, and elsewhere seemed sufficient to justify Italy's military preparations against Ethiopia from 1934 on. One issue for many came to symbolize Japan's expanding influence in Ethiopia, that is, the proposed marriage between Araya Abeba of Ethiopia and Kuroda Masako of Japan.

As Italy's dispute with Ethiopia grew during 1934 and 1935, Japan's leading nationalists, especially "Pan-Asianists," promoted a "solidarity movement" with Ethiopia. A most urgent supporter of Ethiopia was one of the ultranationalist groups, the Amur River Society [Kokuryu Kai, often misnamed the "Black Dragon Society" in English]. In June, the Kokuryu Kai organized Ethiopian Crisis Committee [Echiopia Mondai Iinkai]. Its membership saw the conflict between Italy and Ethiopia as pitting white and colored peoples against one another. Further, Japan was obligated to support Ethiopia, which admired, praised, and respected Japan. (5) Similarly, members of the Japanese-Ethiopian Society [Nihon Echiopia Kyokai] and the Great Japanese Turan Youth League [Dai Nihon Turan Seinen Renmei] prayed: "We wish the wrong-doings of the whites to be punished, and our friend Ethiopia achieve victory."(6)

ምንጭ
THE SUGIMURA AFFAIR OF JULY 1935
MARRIAGE ALLIANCE: THE UNION OF TWO IMPERIUMS, JAPAN AND ETHIOPIA
_________________
http://img28.imageshack.us/img28/3931/etho.jpg
http://img33.imageshack.us/img33/9715/alemayehu.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዓለማየሁ

አለቃ

Joined: 15 Dec 2003
Posts: 2315

PostPosted: Sun May 06, 2012 6:46 am    Post subject: Reply with quote

ጤና ይስጥልኝ ወፌ .....ታዲያ ያንን ጀግና ማን ወለደው ? የጀግንነት ትርጉምንስ ማን አስተማርው Question እናቱ የሰላሌ አንበሳዋ አይድለችምን ? የኢትዮጵያ ሴቶች ጀግና ስለሆኑ ነው እኮ ኢትዮጵያኖች ጀግና የሆኑት :: የወያኔ ውሸት ያንገሸገሻቸው የሰላሌ ሴቶች ብዙ ይሸልላሉ ይፎክራሉ :: የወያኔዎች ሚሌኒየም ፕርፓጋንዳ የሰለቻት አንዲት የሰላሌ ሴትዮ እንዲህ ብላ ስትዘፍን ተደምጣለች - yaa Bar-kumee tiyyaaBar-kumumaa!shraa bitadhu surreet na jalaa dhumaadandae ka hundumaa Exclamation Shocked THAT IS WHAT THE SELALE OROMO WOMENS SONG OF RESISTANCE SAY Exclamation ነገደ አርበኛው ወፌ ለዘፈኑ እናመሰግናለን እንክዋን ደህና መጡ Exclamation ይችን ያዳምጡ ..
ENJOY!

http://www.youtube.com/watch?v=HnjmgHmqMQk
OUR LEGENDS ARE STILL LIVING! AND ETHIOPIAN MOTHERS ARE MAKING MORE EVERYDAY!! እንክዋን ደስ ያለን ! እንክዋን አብሮ አደረሰን ::
_________________
http://img28.imageshack.us/img28/3931/etho.jpg
http://img33.imageshack.us/img33/9715/alemayehu.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
SAY-NO-TO-HATRED

ውሃ አጠጪ

Joined: 12 Mar 2005
Posts: 1339
Location: united states

PostPosted: Sun May 06, 2012 7:18 am    Post subject: Reply with quote

ክህደት :.......እና :....ውሸት :......ሳይሆን :....ነገር :ግን :....እውነት ::...እና :....
............ጀግንነት :.....እንደ :ቅርስ :...በደማችሁ :....
ከአባቶቻችሁ :....ከእናቶቻችሁና :...ከአያቶቻችሁ :.....የወረሳችሁ :....እንቁ :ኢትዮጲያውያን :
ወገኖቼ :ሁሉ :......እንኩዋን :ለዚህ :ታላቅ :..የታሪክ :ቀን :አብሮ :አደረሰን !....

ይህ :ታላቅ :የኢትዮጲያ :አርበኞች :ቀን :.....እጅግ :በጣም :በቅርብ :ጊዜ :ውስጥ :...
በአለም :ነጻነትን :አፍቃሪ :አገሮችና :......ህዝቦች :ሁሉ :.....ተከብሮና :ታስቦ :...
እንደሚውል :....ፈጽሞ :አልጠራጠርም ::......በዉጭ :አለም :...ተወልደውና :...
እያደጉ :ያሉ :....ኢትዮጲያውያን :ልጆችና :ወጣቶች :.....ምን :ያህል :...
ልዩ :የሆነውን :.....የኢትዮጲያዊነትን :ትኩሳት :.....እንክዋን :በአንደበታቸው :...
ብቻ :ሳይሆን :......በፊታቸው :ገጽታ :..ብቻ :እንኩዋን :...እያስተላለፉ :...
እንዳሉ :.....ያልተረዳ :ካለ :......ሊነቃና :ሊታዘብ :ይገባዋል ::....

የኢትዮጲያዊነት :ልዩ :ትኩሳት :......ሊበርድ :አይችልም !!.....
ታላቁ :መጽሀፍ :እንደመሰከረው :.......ኢትዮጲያዊነትን :ማንም :
.....ማንም :......ሊቀንሰውም :....ሊበርዘውም :....ሊያሻሽለውም :...አይችልም !...

አሁንም :በድጋሜ :እንኩዋን :አብሮ :አደረሰን !!

እንበርታ !!.......የብርታት :ምንጭ :የሆነው :የኢትዮጵያ :አምላክችን :....
......አርበኞቻችንን :ይባርክልን !....ውለታቸውን :ይክፈልልን !!.....

ዘወትር :አክባሪ :እህታችሁ :

እምቢ :ለጥላቻ :

ነኝ .......
_________________
WE ARE NOW AMBASSADORS FOR OUR BELOVED COUNTRY AND ONE DAY WE WILL BE CITIZENS IN ETHIOPIA, ONCE AGAIN!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዓለማየሁ

አለቃ

Joined: 15 Dec 2003
Posts: 2315

PostPosted: Sun May 06, 2012 3:48 pm    Post subject: Reply with quote

SAY-NO-TO-HATRED እንደጻፈ(ች)ው:

ሰላም ውድ እህቴ አንበሲት SAY-NO-TO-HATRED, creme-de-la-creme of the House of Freedom-ነገደ አርበኛ Exclamation እንክዋን አብሮ አደረሰን :: My dearerst sister, ወያኔ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ሀይ አመት ታከተ :: በዘር በሀይማኖት ከፋፍሎ አንዱን ከአንዱ ማጋጨት ቢያቅተው አሁን ደሞ በደጀ ሰላም እና በመስጊድ በመጅሊሱ እየገባ መጨማለቅ .. የመጨረሻውን የመከፋፈል ሙከራ ሲያደርግ ይታያል :: Desperate acts in final days. እነዚህ ባንዳ ወያኔዎች ባንዳ ቅድማያቶቻቸው እምቢ እንደተባሉት ሁሉ ዛሬ ሁሉም ኢትዮጵዮጵያዊው እምቢ እያላቸው ነው :: ወያኔ የሚያቅዱው እና የሚሰራው ሁሉ እምቢ ብሎታል :: የወያኔ ክፋትና ጭካኔ ይህ -ኢትዮጵያና -ኢትዮጵዊነት አረመኔነቱ አንቺ እንዳልሸው ጠላት ያቃጠለው ትኩሳትን .. የአርብኞቹን እንቢታን ይበልጥ ጨመረው እንጂ ሌላ ምንም ውጤት አላስገኘም :: ኢትዮጵያዊነትን ሊያጠፋት አልቻሉም :: እንክዋን እኛ ከኢትዮጵያ ውስጥም ውጭም ያለነው ነፍስ ገዝተን የወያኔን ጉድና ግፍ የምንገነዘበው አይደለንም ትንሹ ህጻን እንክዋን ኢትዮጵያዊነት ምን ማለት እንደሆነ ተገንዝቦ ኢትዮጵያና እትዮጵያዊነቱ እንዲጠፋበት አይፈልግም :: አዜብና እነሀዱሽ ህለፎም ለፈረንጆች የሸጠብን ልጆቻችን ሳይቀሩ ኢትዮጵያዊነታቸውን ይፈልጋሉ ..አልተለወጡም አይለወጡምም Exclamation አንቺ እንዳልሽው ኢትዮጵያዊነት አይሸጥም አይለወጥም Exclamation Exclamation በጣም የሚገርም ነገር እኮ ነው እታለም :: የባንዳው መለስ ዜናዊና ሌሎች የባንዳ ወያኔዎች ባንዳ አያቶች በጣሊያ ቂጣቸውን እየተረገጡ ጫማ ሳሙ :: ዛሬም ለሆዳቸው ብለው ባንዳ ወያኔ ኢትዮጵያዊነቱን ክዶ ያጎነበሳል :: በተቃራኒው ግን ፈረነጅ አሳዳጊ ያላቸው ወያኔ ለፈረንጅ በአዶፕሽን የሸታቸው ልጆቻችን በስንት እንክባኬ በፍቅር ቢያዙም Arrow እኛ ፈረንጅ አይደለንም Exclamation ነገደ አርበኛ ነን ኢትዮጵያዊ ነን Exclamation ይላሉ :: Shocked
ቪዲዮን ልጋብዝሽ እታለም ::

http://www.youtube.com/watch?v=ondBEbb7Wu0

You are so right my conciousness raising sister!! ነቅተን ነገሮችን ብንታዝብ ይሻለናል :: Ethiopians are making clear that their freedom, their country is non negotiable. It can never be replaced by Woyanes articial life and limitless lies. Another Victory day is coming. እንበል ነቃ ነቃ
እንበርታታታታታታ !
አክባሪሽ
ዓለማየሁ
_________________
http://img28.imageshack.us/img28/3931/etho.jpg
http://img33.imageshack.us/img33/9715/alemayehu.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዓለማየሁ

አለቃ

Joined: 15 Dec 2003
Posts: 2315

PostPosted: Sun May 06, 2012 4:03 pm    Post subject: Reply with quote

መቅደላዊ እንደጻፈ(ች)ው:
ሚያዝያ 27 መታሰበያ መደረግ አለበት :: ውጭ አገር ያለው የኢትዮጲያ ተወላጅ ሁሉ ቀኑን እንዲያስታውስ ቢደረግ ጥሩ ነው :: በሰሜን አመሪካና በአውሮጳ ያላችሁት ሚያዝያ 27 በአለም አቀፍ ደረጃ ታስቦ እንዲውልና የኢትዮጲያ አረበኞች እንዲታወሱ እንዲደርግ ማደረግ ይገባል ::

ኢትዮጲያ ለዘለአለም ትኑር !

ሰላም መቅደላዊ :: ትክክል ብለሀል :: እንዳንተ የሚያስቡ ኢትዮጵያኖች ዛሬ ከሰዓት ብህዋላ የሚያዚያ 27 ድል መታሰቢያ ቀንን ለማክበር SUNDAY MAY 6 at 4 p.m.
ዋሽንግተን ዲሲ አንድ ዝግጅት ያደርጋሉ :: ዝግጅቱ የሚያስታውሰው የኢትዮጵያኖችን ድል እና መስዋትነት ብቻ ሳይሆን ጣልያንና ባንዳ ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ ከኢትዮጵያኖች ጎን ለመዋጋት ዝግጁ ሆነው ለኢትዮጵያ በውትድርና ለማገልገል የተመዘገቡት 17,000 ጥቁር አሜሪካኖችንም ለማስታወስና ለማክበር ነው :: ዝርዝሩን ከታች ባለው የአዘጋጆች PRESS RELEASE ሊንክ ታገኘዋለህ ::

http://img233.imageshack.us/img233/6643/miazia27.jpg

_________________
http://img28.imageshack.us/img28/3931/etho.jpg
http://img33.imageshack.us/img33/9715/alemayehu.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ደብረብርሀን 33

ኮትኳች

Joined: 17 Aug 2011
Posts: 262

PostPosted: Mon May 07, 2012 2:46 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወገኖች ,

ዋርካ ከተከፈተው ብዙ እርባና ከሌለው ብዙ ቤቶች ውስጥ ይኸኛው ቤት ሚዛን ይደፋል :: ለማንኛውም እንኳን ለድል በአላችን አደረሰን Exclamation ጀግኖች አያቶቻችን ጣሊያንን በዱር በገደሉ ተዋግተውና . ብዙ ውድ መስዋእትነትን ከፍለው ኢትዮጵያን ነጻ አድርገዋል :: ይህን የታሪክ ገድል አሁን ጊዜው ረዝሞና ተረሳ እንጂ ቀላል እንዳልነበረ ታሪክ ያስተምረናል :: ብዙውን ነገር ከላይ በጥሩ ምሁራዊ አጻጻፋችሁ ገልጻችሁታል :: እኔ ትንሽ ለማለት የፈለግሁት ስለ አጼ ኃይለስላሴ ሚና ነው ::
ኃይለስላሴ ጣሊያን ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ እርሳቸው በጅቡቲ አድርገው እንደወጡ ይታወቃል :: ሲወጡም ዋና አላማ ብለው የወጡት ጉዳዩን ለተባበሩት መንግሥታት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ አቤቱታ ለማቅረብ ነበር :: ይህን እርምጃቸውን አገር ውስጥ የጣሊያንን ጦር በዱር በገደል ይዋጉ የነበሩት አልወደዱትም ነበር ::እንዲያውም በቁጥር ትንሽ የማይባሉት እንደ ክህደት ቆጥረውት ነበር :: እንዲያውም በኃላ ከእንግሊዝ እርዳታና ከድል በኃላ . ኃይለስላሴ በሱዳን ጠረፍ አድርገው ሊገቡ ሲል . በዚህ በእኛ ባድማ አሳልፈን አንሰድም ብለው ያመጹ አርበኞች ሁሉ ነበሩ :: በተለይ በጎጃም እነ በላይ ዘለቀና በጎንደር እነ ራስ አሞራው ውብነህ አይነት ሰመ -ጥር አርበኞች አይነት :: ይህን የአምስት አመት ከቀኝ ግዛት ለመውጣት የተደረገውን ትግል በጥሩ መረጃ የጻፈ "" ቀኝ አንበሳ "" በሚል ርእስ የጻፈ ድሮ እንግሊዝ ይኖር የነበረ የኩባ ተወላጅ በጥሩ ሁኔታ ጽፎታል :: ይህ መጽሐፍ አሁን ከእጄ የለም እንጂ ያኔ ኃይለስላሴ በጅቡቲ ሲወጡ እራሱ አግኝቶቸው ....."" ለምን ይሸሻሉ Question ለምን ከዚህ ሆነው አርበኛውን አያዋጉም "" ብዬ ጠይቂያቸው ነበር ይላል :: እርሳቸውም በውጭ ለተባበሩት መንግሥታት አቤት ለማለት እና ዲፕሎማሲያዊ ትግል ለማድርግ እንደሆነ ገልጽውልኝ ነበር ይላል :: እናም ውሳኔያቸው ምንም እንኳ ለአብዛኞቻችን መጀመሪያ አልዋጥ ቢለንም . ጣሊያን ከነበራት የሀይል ሚዛንና ወገን ከነበረው የመሳሪያ የሰውና የጦር ደካማናት አንጻር እራሳቸው ለመቆየት ቢሞክሩ አላስፈላጊ መስዋእትነት ብቻ ሳይሆን . የሚያዚያን ድል አናይም ነበር :: በማንኛውም ጦርነት መሪ ከሞተና ከተማረከ የወገን ጦር ከማያገግምበት ሽንፈት ይገባ ነበር :: ይህ በኩባው ተወላጅ የተጻፈች "ቀኝ አንበሳ " መጽሐፍ ስለ አምስት አመቱ የአርበኝነትና የትግል ታሪክ . ጥሩ የምታስተምር መጽሐፍ ስለሆነች . ማግኘት የምትችሉ ጥሩ ነበር :: አርበኞች ሲቆስሉና በዱር በገደሉ ሲዋደቁ ምን አይነት ታክቲክና የቆሰለውን እንዴት እንደሚያክሙ , ጋቢውንና ብርድ ልብስ ከወገባቸው በማዞርና . ጦር እንዳይወጋቸው እንዴት እንደሚታጠቁ የምትገልጽ ነች ::
እንደገና መልካም ሚያዚያ ድል . የአያቶቻችንን የትግል ጀግንነት እኛም በወያኔ አምባገነኖች ላይ እንደግማለን Exclamation
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዲጎኔ

ዋና አለቃ

Joined: 19 Aug 2005
Posts: 4208
Location: united states

PostPosted: Mon May 07, 2012 6:05 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችን ይሁን
ውድ አለማየሁ ስለመልካም ምኞቱ ምስጋና ብያለሁ የአመለካከት ልዩነት ቢኖረንም ሀገራችን ከወራሪ በህዝቦቿ ነጻ የወጣችበት ማክበር በጋራ መቆም በጎ ነው ::
ብስራተወንጌልና ሚሽኑ ስያስተምሩን ዋና ክፉ ጅብ ሰይጣንን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዴት ማባረር ስለነበር ጅቡ ከቶ አያገኘንም :ሞረቴዎቹ ጅብ ብንባልም የምንበላው ሰውን ሳይሆን ክፉ ስራ ጠል የስንፍና ባህልናግፍን ለመሆኑ በአጼው ዘመን የመጀመሪያውን ለስላሳ ፋብሪካ የከፈተ ሞረቴው ተፈሪ ሻረውና የደርግን ግፍ መጀመሪያ ጊዜ በነፍጥ የተፋለመ ሞረቴው ጸሀይ እንቁስላሴ ምስክሮች ናቸው ::
የነጻነት በአል ቀናት መጋቢት 28 ወይም ሚያዝያ 27 ለእኔ ለውጥ የለውም ድሉ የገዥዎች ባለመሆኑ ብዙሀኑ ህዝቦች ድል ያስቆጠሩበት ተመዝኖ ቢጸና ደስ ይለኛል ::
የጠላትን ጦር ለመፋለም ማይጨው የዘመተችው አያቴና የውስጥ አርበኛ የነበረው ወንዱ አያቴ የሚያኮሩኝ ናቸው ::አጼ በዚህ ደህና ሰርተዋል ሴቷ አያቴ ኢሉአባቦራ አንድ ጋሻ መሬት ወንዱ አያቴ በግራዝማችነት ጋሞጎፋ የወረዳ ሹመት አግኝቶ በህመም የቀረ ሲሆን በጥብቅና እንዲሰራ ጠቅል እያለ የሚወዳቸው አጼው እድል ሰተውት መላ ዘመኑን በዚያ አሳልፏል ::ሆኖም ግን ሁለቱም አያቶቼ አጼውን በጣም የሚወዱና የሚያከብሩ ቢሆኑም በሞረቴነትና በከፊቾነት ያገኙት መገለልና መናቅን ዲጎኔ በለጋነቱ ስላየና እኒያ የዛ ትውልድ ታጋዮች ስለቀሰቀሱት የፊውዳሉ አገዛዝ ተቃዋሚ ሆኖ ቀጣዮቹንም ግፈኞች ደርግንም ወያኔንም እየተፋለም ከዚህ ደርሷል ::
ለማጠቃላል ሀገርኛ የብሄር /ጭቆና ቢኖርም ወራሪን ባማስወገድ ነጻነትን መጠበቁን የአያቶቼን ቅርስ በሚቻለኝ እጠብቃለሁ ይህንንም ለመጭው ትውልድ አስተምራለሁ ::

ዓለማየሁ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ዳጎኒ በአጼ ሀይለስላሴ ጊዜ ...ሚሽነሪ ሲያስተምርህ እና ብስራተ ወንጌል ስትስራ ..እንክዋን ጅብ አለብላህ ብቻ :: እግዜር የተመሰገነ ይሁን :: እንክዋን ለዚህ በዓል አብሮ አደረሰን ::
አንተንም አንድ የአርብኞች ዜማ ልጋብዝህ :: ደሞ የድሮ እንዳይመስልህ ....አዲስ ቀረርቶ ነው :: አዳምጠው ::
ፋኖ ፋኖ by Abebaw Asrat. God Bless Him!

http://www.youtube.com/watch?v=6pIilZLOkZk
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዓለማየሁ

አለቃ

Joined: 15 Dec 2003
Posts: 2315

PostPosted: Tue May 08, 2012 2:02 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ዲጎኔ ..ለመልስህ አመሰግናለሁ :: እኔ ከላይ ለማለት የፈልኩትን ግን የተረዳ ስላልመሰለኝ ላብራራልህ :: ወንድሜ ዲጎኔ አንተ በምትሰድባቸው ንጉስ ዘመን ጥሩ ስራና ኑሮ እንደነበርህ ራስህ ትናገራለህ :: ስለተማርክና ሰርተህ በሰላም ስለኖርክ ነው እኮ ጅብ አልበላህም ያልኩህ Exclamation Exclamation I was trying to say that despite the claimed hyena you constantly complain about in fact you lived in tolerant society. Tolerance ነው የኢትዮጵያኖች ታሪክ :: Tolerance የኢትዮጵያ ባህል ነው :: ይሄንን ሀቅ የሚሸመጥጥ ሁሉ የሴይጣንን ስራ ነው እየሰራ ያልው :: ኢትዮጵያኖች ከጥንት ጀምሮ በሀይማኖት ምክኒያት ፍርድና ፍትህን መብትን እንደማይነፍጉ የሚመሰክሩ ሞልተዋልና በዚህ ቪዲዮ የሚናግረውን የሙስሊም ወንድማችን ስለኢትዮጵያኖች የሰጠውን ልብ የሚነካና ሀቀኛ ምስክርነት አዳምጥ :: (18 ደቂቃ ጀምር )
http://www.youtube.com/watch?v=-yVftEVYcnk
በተጨማሪ ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረሩ ጊዜ (እንድየውም ከዛም በፊት ) ጴንጠዎችና አጼ ሀይለሳልሴ ስለነበራቸው ጠንካራ ፍቅር እና ግዋደኝነት ይሄንን ዌብሳይት አባክህ አንብብ :: እንደ ኢንጊሊዝ መንግስት ...ለራሳቸው ጥቅም ብለው ማለት ነው ...
Quote:

One of the first intercessions that came upon the College as a body was in 1936 when Mussolini intended to invade Ethiopia. The College saw what lay behind this scheme of the enemy. Ethiopia, through the influence of the Emperor, was opening in a new way to Evangelical Missions and there was a prospect of widespread evangelisation in many areas.If the country was captured it could be the end of the Protestant Evangelical witness there.
http://www.byfaith.co.uk/paulreeshowells.htmደብረብርሀን 33... ስለከፈትኩት አምድ እየተነጫነጭንክም ቢሆን አንተ ጥሩ ነገር አካፍለህናል :: አመሰግናለሁ :: ግን ያቀረብክልን ጥቅስ ምንጩን ከየት ላግኘው ? መጸሀፉን ወይንም በአርቲክል መልክ እንዲገኝ ጽሁፍን ማን እንደጻፈው ባክህ አሳውቀን :: Thank you.

አክባሪያቹህ
ዓለማየሁ
_________________
http://img28.imageshack.us/img28/3931/etho.jpg
http://img33.imageshack.us/img33/9715/alemayehu.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
SAY-NO-TO-HATRED

ውሃ አጠጪ

Joined: 12 Mar 2005
Posts: 1339
Location: united states

PostPosted: Tue May 08, 2012 3:48 am    Post subject: Reply with quote

እጅጉን :የምወድሽ :የማከብርሽ :የምመካብሽና :የማደንቅሽ :.....ውዲቷ :
እህቴ :አለማየሁ .......እንደምን :አለሽልኝ ...!..ሊባል :የሚገባውን :ሁሉ :...
....በድንቅ :ሁኔታ :እንደወትሮው :...አስቀምጠሽዋል ::...ውዲቷ :አለማየሁ :...
....ከሀሳብሽ :ጋር :....አስታከሽ :እንድናይ :የምትጋብዥን :ቪድዮዎች ...
እጅግ :ጥልቅ :መልእክት :ያላቸውና :...ትምህርት :የሚሰጡም :ናቸው :....
...እጅጉን :የኢትዮጲያ :አምላክ :አብዝቶ :.....በሁሉም :በኩል :ይባርክሽ !..

የማይጠፋው :የኢትዮጲያዊነት :ትኩሳት :.....ውጭ :አለም :እያደጉ :..
...ያሉ :ልጆቻችን :....በአንደበታቸውም :.....በፊታቸውም :ገጽታ :....
እንዲህ :እያሉ :...... Exclamation ልዩ :የኢትዮጲያዊነትን :.....ባህርይ :...
.....ያስተላልፋሉ :.....

2:44.....ጀምሮ :ያለውን :በመመልከት :....ታዘቡ ....!
============
http://www.youtube.com/watch?v=xhnHDTnsSyQ&feature=related
=============

......ልጆቻችን :......"". Exclamation ..in my home country... Exclamation ..""....
እያሉ :....የማይጠፋውን :የኢትዮጲያዊነትን :ትኩሳት :......ያስተላልፋሉ :...
......."..ከቶ :ማነው :ኢትዮጲያዊነትን :ሊቀይር :የሚችለው ?....".....እንዳለው :
ታላቁ :መጽሀፍ :....አዶፕሽን :....አይቀይረውም :.......የባእድ :የዜግነት :ወረቀትም :አይቀይረውም :...
ባንዳዎችም :አይቀይሩትም :.....!

................እንበርታ !!.........

ዘወትር :አክባሪ :....አድናቂ :....እህትሽ :

እምቢ :ለጥላቻ

ነኝ .........
_________________
WE ARE NOW AMBASSADORS FOR OUR BELOVED COUNTRY AND ONE DAY WE WILL BE CITIZENS IN ETHIOPIA, ONCE AGAIN!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዓለማየሁ

አለቃ

Joined: 15 Dec 2003
Posts: 2315

PostPosted: Tue May 08, 2012 3:23 pm    Post subject: Reply with quote

Thank you very much SAY-NO-TO-HATRED. It is always good to see you here again! ሁሌም በዋርካ ስናይሽ እንበረታለን !! በርቺ !My dear sister, እንዲሁም በዚህ አምድ የተገኛቹህ ሌልችም
Arrow ነገደ አርበኞች ሆይ Exclamation Exclamation እህድ ለት በዋሽንግተን ዲሲ የተከበረው የሚያዚያ 27 መታሰቢያ ቀን ፎተግራፎችን ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ተመልከቱና ተደሰቱ Exclamation ትላንትም ሆነ ዛሬ ነገንም ጨምሮ ..
የኛ ... የነገደ አርበኛ ነው ድሉ Exclamation ::
Quote:
MIAZIA 27 COMMEMORATION OF THE ETHIOPIAN VICTORY. HISTORICAL PRESENTATION OF WREATH.

http://img254.imageshack.us/img254/360/miyazia27memorial1.jpg

http://img685.imageshack.us/img685/3162/miyazia27memorial2.jpg

http://img804.imageshack.us/img804/9273/miyazia27memorial3.jpg

http://img690.imageshack.us/img690/9696/miyazia27memorial4.jpg

_________________
http://img28.imageshack.us/img28/3931/etho.jpg
http://img33.imageshack.us/img33/9715/alemayehu.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3  Next
Page 2 of 3

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia