WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
........መደበሪያ
Goto page 1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8, 9  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ጦምኔው

ውሃ አጠጪ

Joined: 14 Jan 2007
Posts: 1433
Location: Right here

PostPosted: Sun Apr 15, 2012 8:48 pm    Post subject: ........መደበሪያ Reply with quote

አቦ በትንሳዔው ጥግረራ በርትቶብናል :: እስኪ እንደኔ የደበራቹ ብቅ በሉና ለጥቂት ሰዓታት እናላግጥ :: Who's up??
_________________
http://www.youtube.com/watch?v=_jIwsS_eT5w

http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=22540&start=105
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጦምኔው

ውሃ አጠጪ

Joined: 14 Jan 2007
Posts: 1433
Location: Right here

PostPosted: Sun Apr 15, 2012 9:20 pm    Post subject: Reply with quote

Luks layik ay am gona hav tu tok tu mayself!!

ሁለት ወር ተጾመለት :: እነ መንፌው እና እነ ውቅሽ እሙሙን ሲያሳድዱ (ውቅሽ የእሙሙ ነገር በቅቶኛል ቢልም እስኪጣራ ደረስ ተዐማኒነቱ አልተረጋገጠም Laughing ) እኛ ዓለም በቃን ብለን ፊታችንን እርሱ ከደረሰበት አርቀን ሰነበትን :: ሁለት ወር እንደዚህ ረጅጅጅም ነው እንዴ ጃል ? ቢሆንም ዎርዝ ያደርገዋል :: አንዳንዴም ከፈጣሪ ጋር መቀራረብ ሙድ አለው :: ያስፈልጋል ::

ይቀጥላል .....
_________________
http://www.youtube.com/watch?v=_jIwsS_eT5w

http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=22540&start=105
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጦምኔው

ውሃ አጠጪ

Joined: 14 Jan 2007
Posts: 1433
Location: Right here

PostPosted: Sun Apr 15, 2012 9:45 pm    Post subject: Reply with quote

አይ ፋሲካ ....ድሮ ቀረ !! ይሄ ድሮ ቀረ የሚል አባባል በቃ ለመደብን አይደል ? ምኑ ይሆን ድሮ የቀረው ? ምን ያልቀረ አለና ?.....ፈላ እያለን ያው እኛ ሰፈር ያደገ ሰው ያውቀዋል :: ልጅነት በጭቁን መንደር ሙድ አለው :: አንዴ ትዝ ይለኛል ለእኔና ለፈላው ብራዘር (ያው ታናሽ ነው ) ፋዘር ኮምፕለተ ነው የገዛልን -የካሽሚር :: የኔ አረንጌአዴ ነበር (መስከረም 2 ነው ያስመሰልኩት ) ለብራዘር ደሞ ኔቪ ብሉ (ደማቅ ሰማያዊ ? ).....በጣም የሚያምረው ኮምፕሊቱ (2 ፒስ ) የሚሰፋው ሸራ ተራ ነው :: ገበሩ የሻማ ነው (እዚህ ጋር "ያሻማ ቡሬ ቲያን " ያስታውሷል ) እና የኔ ገበሩ ወይን ጠጅ ነበር :: ያው ሸሚዝ ተሸመተለት ተክልዬ (ትሪፍት ስቶር ዘኢቲዮ ):: ሾዳው አይነሳ :: Laughing አንድ ሰሞን መጥቶ የነበረ ጫማ ትዝ ካላቹ ...ለነገሩ አሁንም ከማርኬት አልጠፋም መሰለኝ :: የፕላስቲክ ሾዳ ነው በቆዳ ጫማ ሙድ የተሰራ ማሰሪያ ሁሉ አለው :: ያው ማች አይደል የኔ አረንጓዴ የታናሽ ደሞ ቢጫ ነበር : እናማ በቃ ያው the night before አልነጋ ሁሉ ብሎን ለብሰነው ነው ያደርነው :: Laughing አይ እሱ ጫማ :: ከወራት በኋላ መርገጫው አላልቆ Moon Walk ነበር የምንሄደው :: መጨረሻ ላይ በጠዋት ጤዛ በረጠበ ድንጋይ ታግዞ አፍርጦ ሰበረን እንጂ :: true story! true story).

አቦ ፋሲካ በና ልጅነት ዘመን ቀረ :: ምሳ ከተበላለት በኋላ ትልቁ ብራዘር እኔን : ታናሼን እና የመጨረቻውን ብራዘር ይዞን ያዝናናን ነበር :: ብሔርው ጽጌ ...ሐምሌ 19.....ምን ያልሄድንበት መናፈሻ :: ታላቅ ብራዘርም ድሮ ቀርቷል በቃ !!!

ይቀጥል ይሆናል ........
_________________
http://www.youtube.com/watch?v=_jIwsS_eT5w

http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=22540&start=105
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጦምኔው

ውሃ አጠጪ

Joined: 14 Jan 2007
Posts: 1433
Location: Right here

PostPosted: Sun Apr 15, 2012 10:06 pm    Post subject: Reply with quote

እኔ እና ስጋ .....

ይድረስ ከልጅነቴ እና ዕድገቴ ወራት እጅጉን ትናፍቀኝ ለነበርከው የቅርብ ሩቅ ሆነህ ለሰነበትከው ስጋ :: ለጤናህ እንደምን አለህ ? አንተማ የናን ጤንነት ትነሳለህ እንኢ ጤናህ ምን ይሆናልና ነው ? ቅላትህ ከስባትህ ጋር ተቀላልቅሎ በልጅነት ዓይነ ሕሊናዬ ከነ ሳምሪ ቤት የሳምሪ አባት ግራ እጅ ጣቶች መካከል በቀኝ እጃቸው በተጨበጠ ቢላዋ ስትመተር እና በአዋዜ ተጠቅሰህ ከአፋቸው ስትገባ በጉጉት ካየሁህ ያች የፋሲካ ዕለት ጀምሮ በልቡናዬ ስዬህ ሰንብቼ ነበር :: አንድ ቀን አገኝህ ይሆናል ....እንዲህማ እንዳየሁህ አትቀርም ብዬ ዝቼም እንደነበር የምታስታውሰው ክስተት ነው :: ታዲያ ስጋ ሆይ ....እንዲሁ አንተም በሳምሪ አባት በየፋሲካው ስትመተር ...እኔም ለብዙ ፋሲካዎች ቆሜ ስጓጓ እና ስመለከትህ ብዬም ስዝትብህ ዓመታት ነጎዱ ..ነጓጎዱ እንጂ :: የሳምሪ እና የአንተ ከአንድ ቤት ሆኖ ስጋዬን እና መንፈሴን ማጓጓቱ ቀጠለ :: አይ ስጋ :: ስጋት ሆንክብኝ እንጂ ::

አሁን ታዲያ ከግዛትህ ገብቻለሁ :: ይኸው ከፊት ለፊቴ አጋድሜህ በቁርጥ በጥብስ በክትፎ በወጥ ደርድሬህ እንደዛትክብኝ እየዛትኩብህ ነው :: ምን ትሆን ? አሁን ሀገርህ ገብቼ መጥፎነትህ እየተነገረኝ ነው :: ኮሌስትሮል , ሊቨር ዳሜጅ ቅብርጥሶ ታመጣለህ እያሉኝ ነው :: እንደዛትኩብህ እንዳልበላህ ስጋቱ እንዳልተውህ ዛቻው መንታ መንገድ ላይ ጥለውናል :: ምን ይሻላል ትላለህ ታዲያ ጋሽ ስጋ ??

......
_________________
http://www.youtube.com/watch?v=_jIwsS_eT5w

http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=22540&start=105
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጦምኔው

ውሃ አጠጪ

Joined: 14 Jan 2007
Posts: 1433
Location: Right here

PostPosted: Sun Apr 15, 2012 10:32 pm    Post subject: Reply with quote

አይ ሳምሪ ......

አባትሽ ኮሎኔል XX ከራሺያ ባመጡልሽ የእንጨት ዔሊ እንጫወት ብልሽ እምቢ ብለሽ ከከለከልሽኝ ዕለት አንስቶ ምንም ነገር ለእኔ ለመስጠት ፍቃደኛ አልነበርሽም :: ሌላው ነገር ቢቀር እንኳ ያኔ ትዝ ካለሽ በትምህርት ቤት በተዘጋጀው እንጦጦ ሙዚየም ጉብኝት የጋራ ጉዞ ላይ "ሽንቴ መጥቶብኛል እባክህን በሹራብ ከልለህ አሸናኝ " ብለሽኝ ተስማምቼ ነበር :: እኔም ሚጢጢሽን ከሌሎቹ ተማሪዎች አምቺም ሚጣሽን ከእኔ ለመሸፈን በተቻለን መጠን ስንጥር ህግ አፍርሼ በጨረፍታ አይቼ ቆንጥረሽ እንድጸጪኝ ብለምንሽ ብለምንሽ እምቢየው አለሽኝ :: ከጉዞው ከተመለስንም በኋላ በአካልም በደብዳቤን ብጠይቅሽ ከለከልሽኝ :: መጨረሻ ላይ ግን እሱ አያውቅም ብለሽ ለቦቸራ አሻርሽው :: እኔ ከቦቸራ በምን አንሳለሁ ??

ባለፈው ደሞ ከዚህ ካለሁበት ከአሜርካ (ያው ያለሁበትን ካላወቅሽ ላቅራራብሽ ብዬ ነው Laughing) ለእረፍት የመጣሁ ጊዜ ሰፈር ውስጥ በእጅች : በጀርባሽ እና በሆድሽ ልጅ በጉንጭሽ ደሞ ዳማከሴ ይዘሽ (ለጥርሴ ነው ያልሽኝ ጊዜ ) አይቼሽ አዘንኩ :: ድሮ በውስጠ ከሳልኳት ሳምሪ ጋር ፍጹም አልጣጣም አልችኝ :: እነኛ የብር ኳስ የመሳሰሉት ዓይኖችሽ ደም ለብሰው እና ከጉድጓዳቸው ላለመውጣት እንደሚሳሱ እባቦች ተደብቀው : ሀጫ በረዶ የመሰለው ጥርስሽ ይስነ እማማ በሻዱን አጥር መስሎ እና ዛዝጎ : እነኛ ለመሳም ያጓጉ የነበሩ ከናፍሮችሽ እንደ ኩበት ደርቀው በመካከላቸው ያለው ስንጥቅ ስምጥ ሸለቆን መስሎ : ደሞ ስል ደረትሽ ላይ በኩራት ቀጥ ብለው አርፈው የነበሩ መንታ ጦቶችኝ ከዉበትነው ወደ ምግብነት ተቀይረው : ወደ ዳውን ታውን ሙቭ አድርገው ከእምብርትሽ በታች ካበጠው ሆድሽ ጋር ግብ ግብ ይዘው አይቼ አዘንኩ :: አየሽ የዛኔ ያንን ለቦቸራ የሰጠሽውን ለእኔ ሰጥተሽኝ ቢሆን ኖሮ ዛሬ አሜሪካን ሀገር ጎዳና ላይ ልጆችሽን በሚገፋ ጋሪ እየገፋሽ ትሄጂ ነበር :: ለማንኛውም ያው ሳምሪ እያልኩ አንዳንድ ቀን ቅዳሜ ማታ ማታ ብቻዬን ስሆን ከራሴ ጋር እጫወትበት የነበረው ውበትሽ በአዲሱ አቋምሽ ስለተበላሸብኝ ለመጫወቻ የሚሆን መጽሀፍ በየወሩ ሰብስችራይብ አስደርጌያለሁ ::

በይ ይመችሽ ......መልካም በዓል ::
_________________
http://www.youtube.com/watch?v=_jIwsS_eT5w

http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=22540&start=105
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ከምካሚው

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 23 Mar 2008
Posts: 66

PostPosted: Mon Apr 16, 2012 1:00 am    Post subject: Reply with quote

Laughing ግሩም : ትዝብት : ነው : ቀጥል እባክህ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዘጌ _ዘጋንባው

ኮትኳች

Joined: 18 Aug 2010
Posts: 166

PostPosted: Wed Apr 18, 2012 6:31 pm    Post subject: Reply with quote

ጦምኔው እንደጻፈ(ች)ው:
Luks layik ay am gona hav tu tok tu mayself!!

ሁለት ወር ተጾመለት :: እነ መንፌው እና እነ ውቅሽ እሙሙን ሲያሳድዱ (ውቅሽ የእሙሙ ነገር በቅቶኛል ቢልም እስኪጣራ ደረስ ተዐማኒነቱ አልተረጋገጠም Laughing ) እኛ ዓለም በቃን ብለን ፊታችንን እርሱ ከደረሰበት አርቀን ሰነበትን :: ሁለት ወር እንደዚህ ረጅጅጅም ነው እንዴ ጃል ? ቢሆንም ዎርዝ ያደርገዋል :: አንዳንዴም ከፈጣሪ ጋር መቀራረብ ሙድ አለው :: ያስፈልጋል ::

ይቀጥላል .....

ጦሜ x...ጦማሩ ....
በቅድምያ እንክዋን አብጽኢኩም እልሻለሁ ዋናው ስቱዲዮዬ ....

አንቺ ሰውዬ ግን እንደ አሜሪካን ኢምባሲ ሰፈር ሰዎች እሁድን ( ለዛውም ባመትባሉ ? ) ተጠግርረሽ ሰኞን ብቻሽን ያለከልካይ አራኪሎን ታምሽዋለሽ ....ስድስት ሚሪንዳ ባንዴ አዘሽለት ምናምን ....

ስማ የሳምሪ ባለዳማከሴ -ተግዚናዋ ታሪክ ከምር አንጀት ያላውሳል .....

ደሞ ለጨዋታ መጽሄት ሰብስክራይብ አርግያለሁ ስትዪ አንድ ጭውቴ ትዝ አለኝ .....

አንዱ ነው ወጉ አይቀርምና ትዳር ጋማ ይልልሻል ....
እና በቃ ከተወሰኑ ግዝያቲች በዋላ በእምነቱ መሰረት ሊናዘዝ አባ ይሄድና .....
አባ ከበድ ያለ ሀጥያት ፈጽምያለው .....
እረ ...ምንድነው ልጄ ....

አይ በቃ ሚስቴ ላይ ቺት አረኩ ይላቸዋል ....

እረ ...በስማምምምም ....ምነው ልጄ ..ምን ነካህ እንዲህ የከፋ ሀጥያት ውስጥ መዘፈቅክ ?.... ለመሆኑ ከማንን ከምትባል ነው ያመነዘርከው ?

ሰውየው ..... ሳሙና ! ብሎ አይመልስልሽም ?

በል ቻው
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ገልብጤ

ውሃ አጠጪ

Joined: 26 Jun 2010
Posts: 1334

PostPosted: Thu Apr 19, 2012 5:06 pm    Post subject: Reply with quote

Quote:
ሰውየው ..... ሳሙና ! ብሎ አይመልስልሽም ?

ቅቅቅቅቅ ..ሳሙና ባለትዳሮች የማይደርሱበት ቦታ ይቀመጥ ተብሎ እንዲጻፍበት ነው እንዴ Wink
_________________
SEX IS NOT THE ANSWIER, SEX IS THE QUESTION '* YES* IS THE ANSWIER
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ጦምኔው

ውሃ አጠጪ

Joined: 14 Jan 2007
Posts: 1433
Location: Right here

PostPosted: Fri Apr 20, 2012 1:49 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ሰላም ዘጌው እና ጀለሶች :: አማን ነው ? በቀደም ባክሽ የበዓሉ ቀን ሲደብረኝ ለፈለፍኩለት ሎል ::

ጀለሴ በሰንበቱ መስራት አላቆምኩም ይኸውልሽ ....የቢደና ነገር ግድ ይላል ባክሽ ::....አንቺማ በቃ ዕሁድ ስራ ያቆምሽው ቸርች ለመሄድ ነው አይደል ?? ..ያንቺን መላ መች አጣሁት አባ .....አሁን ቺኮቹ ቢጸድቁበት ምን አለ ብለሽ ነው ? Very Happy

የሳሙናው ያምራል ......የጃንሆይን አልሰማሽም ?.....የጉለሌ 555 ሳሙና ፋብሪካ ሲቋቋም (ሲበረገድ ) እንዲመርቁ ተጠርተው ንግግር ምናምን ሲያደርጉ "የሳሙናን ጥቅም በወጉ ያየነው እቴጌ ከሞቱ በሗላ ነው " ያሉትን ? Very Happy

ስማ መንፌው ግን ከምር ....በልጅነትሽ የመጨረሻ ነብስ ያላቸው ችኮች የነበሩ አሁን የደካከሙ የሉም እናንተ ሰፈር ?? እኛ ሰፈር እንደ አፈር ናቸው ...በተለይ የወላለዱት ......

አቦ አትጥፊለት አባ .....እስኪ እኛም ሰሞኑን ያው ዋርካ ላይ ብቅ ብለናል ....ያው ይቀባጠርለታል .....

ሰላምከ አባ

_________________
http://www.youtube.com/watch?v=_jIwsS_eT5w

http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=22540&start=105
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጦምኔው

ውሃ አጠጪ

Joined: 14 Jan 2007
Posts: 1433
Location: Right here

PostPosted: Fri Apr 20, 2012 2:08 am    Post subject: Reply with quote

የታመመን ሰው "በሕይወት " ማቆየት ያለብን እስከመቼ ነው ???

መኖር ማለት ምንድነው ባክህ ለነኚህ አሜሪካኖች ? ሰሞኑን ሆስፒታል የማየው ነገር በጣም ሰላም የለውም .....እረ ቱቦ በቱቦ .....

ዕድሜያቸው የገፋ አዛውንቶች ICU ውስጥ Life Support እየተሰጣቸው "እየኖሩ " ነው :: ግራ ያጋባኝ ነገር የታመመቱ ሰዎች እየኖሩ ነው ማለት በጣም ይከብዳል :: የሚተነፍሱት ሜካኒካሊ ነው .....የሚመገቡት TPN (በቱቦ )....ፈሳሽ ያው IV ነው :: ሸኖ ድሬኔጅ ሲተም ነው (ካተተር ).....ካካም ያው ነው :: አንዱ በሽተኛማ ያው ኩላሊቱ ስራ አቁሞ ዳያለሲስ ሁሉ አለው በሳምንት ሶስት ቀን :: ...ታዲያ እንዲህ ሆነው ከአንድ ወር በላይ የቆዩ በሽተኞች አሉ :: ብቸኛው ምክንያት ሆስፒታሉ እዚያ የሚያቆያቸው ቤተሰቦቻቸው እንዲያ ሆነው እንዲቆዩ በመፈለጋቸው ነው ::

ቤተሰብ እስከመቼ ነው አንድን የቤተሰብ አባል በዚህ ሁኔታ "በሕይወት " ማቆየት ያለበት ? የቱ ጋር ነው "በቃ " የሚለው ? ወይንስ "በቃ "ማለቱ ጭካኔ ነው ? እውነት እነኚህ ልሳን የሌላቸው በሽተኞች በዚህ ሁኔታ መኖር ይፈልጉ ይሆን ?? ስቃይ ላይ ናቸው ወይንስ የመዳን ፍላጎቱ እና ተስፋው አላቸው ?

አንድ ሀበሻ በሽተኛ የማየቱ አጋጣሚ አጋጥሞኝ ነበር በዚሁ ሁኔታ ላይ ያሉ :: ወደ 17 ቀናቸው ነው እንግዲህ ሆስፒታል ከገቡ :: ባለቤታቸው እና ሁለቱ ልጆቻቸው እያስታመም Oአቸው ነው :: ከአነጋገራቸው ግን ባለቤትየውም ሆኑ ልጆቹ "ተስፋ እንደቆረጡ " ይነበባል :: ነገር ግን አፍ አውጥተው የሚሉት "የመጨረሹ እስትንፋሹ እስካለች ድረስ የተቻለንን ሁሉ እንጥራለን " ነው ::

እኔ የራሴን አባት በቦታው አስቀምጬ ለማየት ሞከርኩ :: እጅጉን የሚዘገንን ሀሳብ ነው ነገር ግን ምንድነው ማድረግ ያለብኝ ? አልኩና የልጆቹን ሀሳብ ደገፍኩ :: እስከመጨረሻው እስትንፋስ ድረስ መታገል እና ከጸጸት መዳን :: መልሼ ደጎ የዚህን የአሜሪካን ሀገርን የጤና ጥበቃ አሰራር (Health Care System) ሳስበው እኝህ አባት ሕይወታቸው ካለፈ በሗላ ለቀሪው ቤተሰብ የሚቀረውን "ቢል " አሰብኩት እና ደግሞ ሀበሻው ጎኔ "ራሴን ተሰበው ":: እንዴት ስለገንዘብ አስባለሁ አንድ የታመመ አባቴ ሆስፒታል ተኝቶ እያለ ::

እስኪ አስተያየት ስጡበት :: የዘመኑን እና የሀገሪቱ ሁኔታ ባካተተ ሁኔታ :: ያው ከሪያሊቲው በመነሳት ::

ሰላም ::

_________________
http://www.youtube.com/watch?v=_jIwsS_eT5w

http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=22540&start=105
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጦምኔው

ውሃ አጠጪ

Joined: 14 Jan 2007
Posts: 1433
Location: Right here

PostPosted: Fri Apr 27, 2012 1:29 am    Post subject: Reply with quote

ሰሞኑን ወጣ ወጣ ማለቱን አብዝቻለሁ :: ያው ነው ወጣ ወጣ ቢሉም ባይሉም ያው ኮይኑ እንደሆነ ይከሳል :: እዚህ ሀገር የመታሁ ሰሞን ሳቢ አጠራቅማለሁ ብዬ ሞክሬ ሞክሬ ምንም ሊሳካ አልቻለም :: ያው ነው .....የወሩ ስቴትመት ከች ሲል ዜሮውቹ የሚበዙት ከነጥብ በሗላ ሲሆንብኝ ያው በቃ ተስፋ ቆርጬ ማጠራቀሙን ትቼ ማባከኑን ተያያዝኩት :: በጣም የገረመኝ ነገር የኔ ሳቢ አያያዝ ይሁን የሳቢው እኔን አያያዝ በፍጹም ልንግባባ አልቻልንም :: ልክ እንደመጀመሪያዋ ቺኬ :: እኔ ከላይ (ከሰው በላይ ) ላርግሽ ስላት እሷ መሬት ላይ እየሆነች ስታሽቸግረኝ እንደፈታሗት ቺኬ ::

ይሄንን ከቤንጃሚን ጋር ያለኝን ግንኙነት ማስተካከል ይኖርብኛል :: እስከመቼ የባንክ ስቴትመኔ በመጣ ቁጥር ስቅቅ ብዬ እችለዋለሁ ? ያው ጥግረራው እንደጉድ አለ ሲያጉላላን :: ይከፍሉናል (ያው 17 እያባዛን ነው እንጂ የምንጽናናው ):: እንደዚህ ብዬ በጣም አሰብኩና ከዶላር ስቶር የአሳማ ባንክ ገዛሁ :: እና እዚያ ባንክ ውስጥ ማታ ማታ ወደ ቤት ስገባ ኪሴ ውስጥ የቀረውን ካሽ (ሳንቲምም ሆነ ብር ) እዚያ ውስጥ ለማጠራቀም ወሰንኩ :: መቼም በቀን 3 ብር ባስቀምጥ ወይም 4 ብር ያው ሳምንት 21-28 ብር ይሆናል :: በወር ደሞ እስከ 100 ዶላር ይደርሳል አልኩና በዓመት ያው ካልኩሌት ሳላደርገው የትዬለሌ (ነፍ ) እንደሚሆን ገምቼ ተስፋ ታየኝ :: ያቺን ያጠራቀምኳትን ሳቢ ያው ቫኬሽን እወጣበታለሁ አልኩና ሆዋይ ወይም ደሞ ሆኖሉሉ ለመሄድ ወስኜ የትኛውን ቺክ ይዤ እንደምሄድ ቅየሳ ጀመርኩ :: ቺኮቹን ሁሉ በቁመት : በዕድሜ : በመልክ : በቁመና : ካሰልፍኳቸው በኋላ ግምገማዬን ጀመርኩለት :: የትኛዋ ቺክ ነች ቢች ዳርቻ በዋና ልብስ ስትታይ የምታኮራው አልኩኝ :: እነ ፐርሰናሊቲ : ቪዥን : ማንነት : ማንምን የሚባሉትን ዕንቅፋቶች ከመስፈርቱ ውስጥ አስወገድኩና ምርጫዬን ተያያዝኩት :: ለተወዳዳሪዎቹ ልዩ ምልክት ሁሉ ሰጠሗቸው ስልህ :: እና የምርጫው ሂደት በጣም ዴሞክራሲያዊ ነበር :: ያሸነፈችው ችክ ራሷ ለዚህ ምስክር ትሆናለች :: ቺኳ ግድንግድ ዲጌ ሉጌ አላት :: ጋቢናዋ የሰጠ ነው :: ጥያቄ አታበዛም በቃ ዝም ብላ ማዳመጥ እና መስማማት ነው :: ታዲያ ከዚህ በላይ ዴሚክራሲ አለ ?? አሁን አንድ 4 ቀን ሆኖኛል ማጠራቀሙን ከጀመርኩ :: ያው የዛሬ ዐመት ውጤቱን አሳውቃለሁ ::

እናልህ ትላንትና ማታ ከጀለሶች ጋር ወጣ ተባለለት እና አንድ የዐረቦች እና ሀበሾች መሰብሰቢያ ቤት ተኬደለት :: አንዷ ሀበሻ ቺክ ይህንን ሺሻ ትምገዋለች እንደጉድ :: ጀለሴ አያትና "ይሄ ሀገር ቤት በቢልቦርድ ተደርጎ እናት ጡት ማስታወቂያ ቢሰራበት ውጤት ተኮር ይሆናል " አላለም Very Happy

ፒስ

_________________
http://www.youtube.com/watch?v=_jIwsS_eT5w

http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=22540&start=105
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዘጌ _ዘጋንባው

ኮትኳች

Joined: 18 Aug 2010
Posts: 166

PostPosted: Sat Apr 28, 2012 5:56 pm    Post subject: Reply with quote

ጦሜው ... ሰላም

ምን የሰፈራችን ችኮች ነገርማ ተይኝ .... ጥንት እሷን ኢምፕረስ ለማረግ ብዬ እጄ ላይ የራምቦን ባለክርክሩን ሲኪኒ የተነቀስኩላት ልጅ .... ላስት ታይም ሄጄ ሳያት ... ነፍ ልጆች ወላልዳ ምናምን ደሞ በዛ ላይ በየ 6 ወሩ ነው ጡብ ጡብ የምታደርገው መሰለኝ እኩያ ነገር ናቸው ....ባንዴ አምስቱንም ነው እንደውሻ ጥላ ስር ምናምን ጋደም ብላ የምታጠባቸው ስልክ ... Laughing

ስለ ንቅሳቱ ነገር ካልነሳሁልኝ አይቀር ..... ይገርምሻል እንደምታቂው አሙካ ተገብቶለት ፒዛ ይገመጥለታል :: ፒዛ ከገመጥክ ደሞ ያው ትከሻዎች መሰፋፋት ይጀምራሉ :: እናልሽ ድሮ የራምቦ ጩቤ ብዬ ያካበድኩባት አሁን ብታያት እጄ ላይ ጭረቷ አልማዝ ባለ ጭራ መስላልካለች ....

የውሀ ዳር ሽርሽሩን ጥሩ አይዲያ ነው ...ግን ምነው ያበትሻት ችክ ዱዳ ናት እንዴ ? ዝም ዝም ብቻ ? ቅቅቅቅ .... ለነገሩ ዱዳ ችክ ቀምጭያለው ከዚ በፊት በጣም ሀት ናቸው በተለይ ሞን ሲያረጉ ቅቅቅቅ ...ግን ተተንቀቅ መዳፋቸው ጠንካራ ስለሆነ ከያዘችክ ማምለጫ የለክም ...አንተ አልመጣ ቢልክ እንኳን ጨምድዳ ፊው ፊው ታስደርግካለች ....

ማነው ደሞ አላዲን ነው ቢንላዲን የሚሉት ሺሻ መንፊያ ቤት ክስቶ ማረግ ጀመረሽ ? ይገርምካል ... የአበሻ ችኮች ሺሻ አጫጫስማ ... አይናቸው ፈጤ ብሎ አንገታቸው ደምስር ግትርትር ሲል ... በዛ ላይ ተርዚናውን ወጥረውት ምናምን ... ዴይ ኦፍ ዴድ ሙቪን ነው የሚያስታውስክ ....
ምናለ ያንንም ነገር እንደዚ በጥሞና ቢመገምጉልን ?

እያልኩ ያዛሬውን ስርጭቴን ከጊዜያዊ ስቱዲዮዬ በዚሁ አበቃለሁ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ገላጋይ -1

ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2006
Posts: 493

PostPosted: Sat Apr 28, 2012 10:15 pm    Post subject: Reply with quote

ጫወታችሁ ጥሞኛል ......

ጦምኔው ... ባንክህ ስንት ደረሰች አሁን ? Razz
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እህምም

አለቃ

Joined: 19 Dec 2005
Posts: 2400
Location: on a small rock; between an ocean and a sea.

PostPosted: Wed May 09, 2012 7:21 pm    Post subject: Reply with quote

Laughing ጦምንሻ you just made my day. የዋርካ አዲክሽኔን ልታስመልሰው ነው መሰለኝ .
_________________
Homage to darkness : http://yekolotemari.blog.com/2010/02/09/homage-to-darkness/

"Is it stealing
if I take
the pains of others

and make it my healing?"
http://elicitbeauty.blogspot.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
recho

ዋና አለቃ

Joined: 20 Sep 2004
Posts: 3059
Location: Earth

PostPosted: Wed May 09, 2012 7:27 pm    Post subject: Reply with quote

እህምም እንደጻፈ(ች)ው:
Laughing ጦምንሻ you just made my day. የዋርካ አዲክሽኔን ልታስመልሰው ነው መሰለኝ .
ማይ ጋድ !!! Arrow Arrow !
_________________
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8, 9  Next
Page 1 of 9

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia