WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ክተት ለእግዚአብሔር

Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ደቂቀ ያሬድ

ኮትኳች

Joined: 27 Nov 2005
Posts: 150

PostPosted: Sun May 27, 2012 6:37 pm    Post subject: ክተት ለእግዚአብሔር Reply with quote

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አኃዱ አምላክ አሜን ::

አባቶች የሠሩትን የቀድሞውን ድንበር አታፍርስ [መጽሐፈ ምሳሌ 22 28]

እነሆ ከአባቶቻችን የቆየውን መድኃኒዓለም ክርስቶስ የመሠረተውን የዋልድባ ገዳም የኢህአዴግ መንግሥት በማፍረስ ላይ ይገኛልና እንሰብሰብ አባቶቻችን እንደሚያደርጉት እኛም ለእግዚአብሔር እንክተት ::

ክተት ለእግዚአብሔር ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ : በሎሳንጀለስ : በኒዮርክ : በካናዳና በመላው አለም በሙሉ :: ግንቦት 27 ቀን 2004 ዓም የመድኃኒዓለም እለት በፈረንጆች አንጋገር June 4, 2012

አድራ እንደ አባቶቻችሁ ለእግዚአብሔር አለን በሉ ::

http://www.savewaldba.blogspot.com/2012/05/blog-post_17.html

ወስብሃት ለእግዚአብሔር

Last edited by ደቂቀ ያሬድ on Sun May 27, 2012 7:16 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ደቂቀ ያሬድ

ኮትኳች

Joined: 27 Nov 2005
Posts: 150

PostPosted: Sun May 27, 2012 6:44 pm    Post subject: Reply with quote

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አኃዱ አምላክ አሜን ::

ኢህአዴግ በዋልድባ እያደረሰ ስላለው ጥፋት ማስረጃ ለምትፈልጉ እነሆ :-

https://docs.google.com/file/d/0B08ihe6dWn9Hcm96Q1p2c2VoWGc/edit?pli=1

ወስብሃት ለእግዚአብሔር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ደቂቀ ያሬድ

ኮትኳች

Joined: 27 Nov 2005
Posts: 150

PostPosted: Mon May 28, 2012 12:46 am    Post subject: Reply with quote

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አኃዱ አምላክ አሜን።

በዋሺንግተን ዲሲ የጉልበተኛ አገሮች መሪዎች በተሰበሰቡበት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በመናገር ላይ እያሉ አቶ አበበ ገላው የሳቸውን ንግግር በማጨናገፍ “አንባገነን ናቸው” እያለ ሲጮህ ሁሉም ሰማ። በቅድሚያ የሚያፍሩት ፕሬዘዳንት ኦባማ ናቸው ምክንያቱም “ረሃብን ለማጥፋት” በሚል አርእስት በተደረገው ስብሰባ ተሰብሳቢዎቹም ሆኑ ቴሌቪዢን ተመልካቾች የጨበጡት ግንዛቤ በፕሬዚዳንት ኦባማ ግብዣ ከኢትዮጵያ የመጡት መሪ የኢትዮጵያን ህዝብ ለእጦትና ለረሃብተኛነት የዳረጉና መብትም የነፈጉ ናቸው የሚል ነውና። ይህ የአቶ አበበ ጩኸት አቶ መለስን ብቻ ሳይሆን በዋነኛነት ያጋለጠው የፕሬዚደንት ኦባማ የትብብር ጥሪ (partnership initiative) የፌዝ ጥሪ መሆኑን ነው። ይህ ሃፍረት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ላይ የመጣው ዋልድባን ደፍረው ብዙም ሳይውል ሳያድር ነው። በእግዚአብሔር ላይ ትእቢት ያዋጣልን ?

የኢህአዴግ መኳንንቶችና ሹማምንት በሰማይ ጌታ ላይ ተተበዩ፣ ያባቶቻቸውን አምላክም አላከበሩትም። የእግዚአብሔርን ርስት ቆረሱ፣ የመቅደሶቹን እቃዎችም አረከሱ፣ እግዚአብሔርን በመናቅ የማያውቁትንና የማይገባቸውን የውጭ ፍልስፍና አመለኩ፣ የእግዚአብሔርን ርስትም ለነዚህ ለጣኦታት አሳልፈው ሰጡ። ስለዚህም እግዚአብሔር የኢህአዴግን መንግሥት በሚዛን መዘነው። ቀሎም አገኜው። እግዚአብሔርም የኢህአዴግን መንግሥት ቆጠረው፣ ፈጸመውም።

ወስብሃት ለእግዚአብሔር።
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዲጎኔ

ዋና አለቃ

Joined: 19 Aug 2005
Posts: 4216
Location: united states

PostPosted: Mon May 28, 2012 6:50 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችን ይሁን
ወገን ደቂቀ ያሬድ
ይህ ማሳሳቢያህ ለተዋህዶ ማህበረተኞችህ ብቻ ከሆነ ይህን አስተያየቴን እርሳው ካልሆነ ግን ጥቂት ልበል ::
መንፈሳዊያን ክርስቲያኖች ለሀገርና ለህዝቦች ነጻነት ካለፉት ለድል ከበቁት ከነአቡነ ዴዝሞንድ ቱቱ ምን እንማራለን ? የህዝቡ ግፍ እንዲያበቃ የትግሉ ይዘት ይጥራ በሀገራችው ሰርተው ራሳቸውና ቤተሰብ መደገፍ ያልቻሉት ወገኖቻችን መብት ተጥሶ የወያኔ አገዛዝ የሚያጠፋው አዲሱ መቅደስ የሰዎች ተክለሰውነት ይበልጣልና እስኪ ክተት ሰራዊቱ መንፈሳዊ የምለው ወደሰዎች መብት ይዙር !በፍልሚያው ጌታ እንዳለው ከልብስ መብል ከመብል ነፍስ ይበልጣልና ከድሮ መቅደስ ዋልድባ ይልቅ ለአዲስ ኪዳን መቅደስ ለሰው ቅድሚያ እንስጥ :: ቅዱስ ቃሉ እንዲል እኛ ሀገራችን በሰማይ ሲሆን ለተገፋው ለመበለቷ መጮህ ሀላፊነታችን መጀመሪያ ህዝቡ መብቱ እንዲጠበቅ እንትጋ ::ይህን ስል መንፈሳዊ የህዝቦች ቅርስ መደፈር እንደማወግዝ ይታወቅልኝ ::ይህንንም ውጤት ባለው መንገድ ለመፈጸም የወያኔ አፓርታይድ የግፍ አገዛዝ ላይ የሚካሄድ ትግልን በሁሉ ዘርፍ እናድርገው ::እንደቃሉም ሰልፉ የጌታ ነው !
http://www.youtube.com/watch?feature=fvwpANR=1&v=y47coaKXCd8
ደቂቀ ያሬድ እንደጻፈ(ች)ው:
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አኃዱ አምላክ አሜን።

በዋሺንግተን ዲሲ የጉልበተኛ አገሮች መሪዎች በተሰበሰቡበት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በመናገር ላይ እያሉ አቶ አበበ ገላው የሳቸውን ንግግር በማጨናገፍ “አንባገነን ናቸው” እያለ ሲጮህ ሁሉም ሰማ። በቅድሚያ የሚያፍሩት ፕሬዘዳንት ኦባማ ናቸው ምክንያቱም “ረሃብን ለማጥፋት” በሚል አርእስት በተደረገው ስብሰባ ተሰብሳቢዎቹም ሆኑ ቴሌቪዢን ተመልካቾች የጨበጡት ግንዛቤ በፕሬዚዳንት ኦባማ ግብዣ ከኢትዮጵያ የመጡት መሪ የኢትዮጵያን ህዝብ ለእጦትና ለረሃብተኛነት የዳረጉና መብትም የነፈጉ ናቸው የሚል ነውና። ይህ የአቶ አበበ ጩኸት አቶ መለስን ብቻ ሳይሆን በዋነኛነት ያጋለጠው የፕሬዚደንት ኦባማ የትብብር ጥሪ (partnership initiative) የፌዝ ጥሪ መሆኑን ነው። ይህ ሃፍረት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ላይ የመጣው ዋልድባን ደፍረው ብዙም ሳይውል ሳያድር ነው። በእግዚአብሔር ላይ ትእቢት ያዋጣልን ?

የኢህአዴግ መኳንንቶችና ሹማምንት በሰማይ ጌታ ላይ ተተበዩ፣ ያባቶቻቸውን አምላክም አላከበሩትም። የእግዚአብሔርን ርስት ቆረሱ፣ የመቅደሶቹን እቃዎችም አረከሱ፣ እግዚአብሔርን በመናቅ የማያውቁትንና የማይገባቸውን የውጭ ፍልስፍና አመለኩ፣ የእግዚአብሔርን ርስትም ለነዚህ ለጣኦታት አሳልፈው ሰጡ። ስለዚህም እግዚአብሔር የኢህአዴግን መንግሥት በሚዛን መዘነው። ቀሎም አገኜው። እግዚአብሔርም የኢህአዴግን መንግሥት ቆጠረው፣ ፈጸመውም።

ወስብሃት ለእግዚአብሔር።
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወርቅነች

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Oct 2010
Posts: 968

PostPosted: Sat Jun 09, 2012 7:20 am    Post subject: Reply with quote

ለመሆኑ አቶ ተድላ ሀይሉ (ፈዛዛው ቄሰ ) እዚህ ክተት ላይ ተሳትፏል ... መቼም የቄሰ ጀግና የለውም ..እኛም እኮ ተናግረናል ፈዛዛው ከደረሰ ቤተ ክርስቲያኑ ይፈንዳል ብለናል ..አይኑ ክፉ ነው ቁም ነገር አይውልም ... አረ እንኳን በዚህም ተረፈ ..መሬቷ ሳትሰነጠቅ ነበር ...እባካችሁን ፈዛዛውን ውሰዱና እዚያው እረዱት ቤተ ክርስቲያኑ እንዲሰራ ..እሱ ካልታረደ ቤተ ክርስቲያኑ አይሰራም ትላለች ጀሚላ ከቸርችል ጎዳ Laughing Laughing Laughing
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ደቂቀ ያሬድ

ኮትኳች

Joined: 27 Nov 2005
Posts: 150

PostPosted: Mon Jul 16, 2012 9:24 pm    Post subject: Reply with quote

ደቂቀ ያሬድ እንደጻፈ(ች)ው:
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አኃዱ አምላክ አሜን።

በዋሺንግተን ዲሲ የጉልበተኛ አገሮች መሪዎች በተሰበሰቡበት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በመናገር ላይ እያሉ አቶ አበበ ገላው የሳቸውን ንግግር በማጨናገፍ “አንባገነን ናቸው” እያለ ሲጮህ ሁሉም ሰማ። በቅድሚያ የሚያፍሩት ፕሬዘዳንት ኦባማ ናቸው ምክንያቱም “ረሃብን ለማጥፋት” በሚል አርእስት በተደረገው ስብሰባ ተሰብሳቢዎቹም ሆኑ ቴሌቪዢን ተመልካቾች የጨበጡት ግንዛቤ በፕሬዚዳንት ኦባማ ግብዣ ከኢትዮጵያ የመጡት መሪ የኢትዮጵያን ህዝብ ለእጦትና ለረሃብተኛነት የዳረጉና መብትም የነፈጉ ናቸው የሚል ነውና። ይህ የአቶ አበበ ጩኸት አቶ መለስን ብቻ ሳይሆን በዋነኛነት ያጋለጠው የፕሬዚደንት ኦባማ የትብብር ጥሪ (partnership initiative) የፌዝ ጥሪ መሆኑን ነው። ይህ ሃፍረት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ላይ የመጣው ዋልድባን ደፍረው ብዙም ሳይውል ሳያድር ነው። በእግዚአብሔር ላይ ትእቢት ያዋጣልን ?

የኢህአዴግ መኳንንቶችና ሹማምንት በሰማይ ጌታ ላይ ተተበዩ፣ ያባቶቻቸውን አምላክም አላከበሩትም። የእግዚአብሔርን ርስት ቆረሱ፣ የመቅደሶቹን እቃዎችም አረከሱ፣ እግዚአብሔርን በመናቅ የማያውቁትንና የማይገባቸውን የውጭ ፍልስፍና አመለኩ፣ የእግዚአብሔርን ርስትም ለነዚህ ለጣኦታት አሳልፈው ሰጡ። ስለዚህም እግዚአብሔር የኢህአዴግን መንግሥት በሚዛን መዘነው። ቀሎም አገኜው። እግዚአብሔርም የኢህአዴግን መንግሥት ቆጠረው፣ ፈጸመውም።

ወስብሃት ለእግዚአብሔር።
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አኃዱ አምላክ አሜን ::

ለኢትዮጵያውያን በሙሉ ::

እነሆ የእግዚአብሔርን ተዓምር እያያችሁ ነው :: ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ልጓም የሌለው ትእቢት በእግዚአብሔር ላይ አሳዩ :: ደካማ ናቸው ብለው የዋልድባ መነኮሳትን እሮሮ ሊሰሙ አልፈለጉም :: በትእቢትና በስንፍናም ተናገሩ :: እኛ ኢትዮጵያውያን በእግዚአብሔር ላይ የፈጸምነው በደል ስለበዛ እንቀጣ ዘንድ እግዚአብሔር አቶ መለስንና ባቢሎንን በላያችን ላይ ጫነ :: በጉልበትና በፈረስ የሚመካ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ቅጣቱን አቶ መለስን ለማውረድ ጦር ሰበቀ : የተሳለውን ጎራዴውንም መዘዘ :: አንድም የቻለ የለም :: እንዲያውም የሞከረ ሁሉ ተዋረደ ::

ይሁንና ከጊዜ በኍላ ብዙ ሰዎች በተለይም ወጣቶችና ልጃገረዶች ፊታቸውን ወደ እግዚአብሔር አዞሩ :: የአባቶቻችን እምነት ጠብቀን በተዋህዶ መንገድ እንሄዳለን ብለው እግዚአብሔር አገራቸውን ኢትዮጵያን እንዲታረቃት አለቀሱ :: በትእቢት የተነፋፋው የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አስተዳደርም እነዚህን ሥራቸው ወደ እግዚአብሔር ማልቀስ ብቻ የሆኑ ወጣቶችን ሽብርተኛ ናቸው ብሎ በሀሰት ወነጀለ :: እነሱንም ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ታጥቆ ተነሳ :: እግዚአብሔር እራሱ የመሠረተውን የዋልድባ ገዳምም ከፊሉን መሬት ወስጀ የስኳር ፋብሪካ እሰራለሁ , ከስኳሩም ዶላር አገኛለሁ ብሎ የተቀደሰውን ገዳም የዋልድባን መሬት አረሰ :: መነኮሳቱም አቤቱታ ሊያሰሙ አዲስ አበባ ቢመጡ አንከሳክሶ መለሳቸው :: እነሱም ወደ እግዚአብሔር አለቀሱ : እግዚአብሔርም ጆሮውን አዘንብሎ የወጣቶቹንና የመነኮሳቱን ለቅሶ አዳመጠ :: የተቀላጠፈ መልስም ሰጠ :: እግዚአብሔር አምላክም የኢህአዴግን አስተዳደር ፈጸመው ::

ይህን ተአምር አይታችሁ ወደ እግዚአብሔር የማትመለሱ ወዮ : ወዮ : ወዮ :: ለዚህ ለእግዚአብሔር ተአምር ሌላ አለማዊ ገለጻ የምትሰጡ እናንተም ታለቅሳላችሁ ::

ከአሁን በኋላ የኢትዮጵያ አስተዳደር የእግዚአብሔር ነው :: የባቢሎን ፍልስፍና : የባቢሎንም ቀንበር በኢትዮጵያ ቦታ የለውም ::

ወስብሃት ለእግዚአብሔር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon Jul 16, 2012 10:15 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ደቂቀ ያሬድ :-

የጻፍከው መልዕክት አንድም ሥህተት የለበትም ::

ልዑል እግዚአብሔር ለእኛ ለኢትዮጵያውያን እርሱን ፈጣሪያችንን የሚፈራ : የሚያምንና የሚያከብር መሪ ይስጠን ::

ወስብሐተ እግዚአብሔር ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ደቂቀ ያሬድ

ኮትኳች

Joined: 27 Nov 2005
Posts: 150

PostPosted: Mon Sep 03, 2012 4:37 am    Post subject: Reply with quote

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አኃዱ አምላክ አሜን ::

በአራተኛ ሰንበት በእለተ መድኃኒዓለም።

እግዚአብሔር የበቀል አምላክ ነው። የበቀል አምላክ ተገለጠ።
የምድር ፈራጅ ሆይ፥ ከፍ ከፍ በል፤ ለትዕቢተኞች ፍዳቸውን ክፈላቸው።
አቤቱ፥ ኃጢአተኞች እስከ መቼ ? ኃጢአተኞች እስከ መቼ ይጓደዳሉ ?
ይከራከራሉ፥ ዓመፃንም ይናገራሉ፤ ዓመፃንም የሚያደርጉ ሁሉ ይናገራሉ።
አቤቱ፥ ሕዝብን አዋረዱ፥ ርስትህንም አስቸገሩ።
ባልቴቲቱንና ድሀ አደጉን ገደሉ፥ ስደተኛውንም ገደሉ።
እግዚአብሔር አያይም፥ የያዕቆብ አምላክ አያስተውልም አሉ።
የሕዝብ ደንቆሮች ሆይ፥ አስተውሉ፤ ሰነፎችማ መቼ ይጠበባሉ ?
ጆሮን የተከለው አይሰማምን ? ዓይንን የሠራው አያይምን ?
አሕዛብንስ የሚገሥጸው፥ ለሰውም እውቀት የሚያስተምረው እርሱ አይዘልፍምን ?
የሰዎች አሳብ ከንቱ እንደ ሆነ እግዚአብሔር ያውቃል።
ለኃጢአተኛ ጕድጓድ እስኪቈፈር ድረስ ከክፉዎች ዘመናት ይወገድ ዘንድ፥ አቤቱ፥ አንተ የገሠጽኸው ሕግህንም ያስተማርኸው ሰው ምስጉን ነው።
እግዚአብሔር ሕዝቡን አይጥልምና፥ ርስቱንም አይተውምና
ፍርድ ወደ ጽድቅ እስኪመልስ ድረስ ልበ ቅኖችም ሁሉ ይከተሉአታል።
በክፉዎች ላይ ለእኔ የሚቆም ማን ነው ? ዓመፃንስ በሚያደርጉ ላይ ለእኔ የሚከራከር ማን ነው ?በእለተ መድኃኒዓለም ጽዮንን ለአርባ አመታት ያመሰው የቄዳርና የባቢሎን ጥምር ቀንበር፣ እራስን በራስ የማጥፋት ፍልስፍና፣ አንዲቷን የቀደመች ሐይማኖት የማጥፋት ፍልስፍና፣ የእግዚአብሔርን አገር የመገነጣጠል ፍልስፍና፣ የእግዚአብሔርን መንበር የማርከስና የመንጠቅ ፍልስፍና፣ ጽዮንን ለባቢሎንና ለቄዳር ቅኝ የማስገዛት ፍልስፍና ግብአተ መሬት ተፈጸመ።

እግዚአብሔር ሆይ አንተ ከኛ ጋር ባትሆን ኖሮ የቄዳርና የባቢሎን ፈረሰኞች ዘንዶ ግልገልን እንደሚውጥ ይውጡን ነበርኮ ! አንተ ከኛ ጋር ስለሆንክ ያቀዱልንን ተንኮል አጨናገፍክ። ፈጣሪ ሆይ ምስጋና ላንተ ይሁን።

እነሆ የባቢሎን ሰዎች የሬኔሰንስና የሉተራዊ ፈርጀ -ብዙ ደባዎቻቸውን በመጠቀም በጽዮን ዙፋንህን ለመጥለፍ ይነሳሉ። ጉድጓድ እስኪውጣቸው ድረስ ይከራከራሉ። የቄዳር ምርኮኞችም በቄዳር እየተደገፉ ጽዮንን ለመጥለፍ የቄዳርን መረብ በጽዮን ዙርያ ወረወሩ። መረቡ እራሳቸውን አዙሮ ይጠልፋቸዋል። ይወድቁማል። እግዚአብሔር ሕዝቡን አይጥልምና፥ ርስቱንም አይተውምና። ፍርድ ወደ ጽድቅ እስኪመልስ ድረስ ልበ ቅኖችም ሁሉ ይከተሏታል።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ደቂቀ ያሬድ እንደጻፈ(ች)ው:
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አኃዱ አምላክ አሜን።

በዋሺንግተን ዲሲ የጉልበተኛ አገሮች መሪዎች በተሰበሰቡበት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በመናገር ላይ እያሉ አቶ አበበ ገላው የሳቸውን ንግግር በማጨናገፍ “አንባገነን ናቸው” እያለ ሲጮህ ሁሉም ሰማ። በቅድሚያ የሚያፍሩት ፕሬዘዳንት ኦባማ ናቸው ምክንያቱም “ረሃብን ለማጥፋት” በሚል አርእስት በተደረገው ስብሰባ ተሰብሳቢዎቹም ሆኑ ቴሌቪዢን ተመልካቾች የጨበጡት ግንዛቤ በፕሬዚዳንት ኦባማ ግብዣ ከኢትዮጵያ የመጡት መሪ የኢትዮጵያን ህዝብ ለእጦትና ለረሃብተኛነት የዳረጉና መብትም የነፈጉ ናቸው የሚል ነውና። ይህ የአቶ አበበ ጩኸት አቶ መለስን ብቻ ሳይሆን በዋነኛነት ያጋለጠው የፕሬዚደንት ኦባማ የትብብር ጥሪ (partnership initiative) የፌዝ ጥሪ መሆኑን ነው። ይህ ሃፍረት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ላይ የመጣው ዋልድባን ደፍረው ብዙም ሳይውል ሳያድር ነው። በእግዚአብሔር ላይ ትእቢት ያዋጣልን ?

የኢህአዴግ መኳንንቶችና ሹማምንት በሰማይ ጌታ ላይ ተተበዩ፣ ያባቶቻቸውን አምላክም አላከበሩትም። የእግዚአብሔርን ርስት ቆረሱ፣ የመቅደሶቹን እቃዎችም አረከሱ፣ እግዚአብሔርን በመናቅ የማያውቁትንና የማይገባቸውን የውጭ ፍልስፍና አመለኩ፣ የእግዚአብሔርን ርስትም ለነዚህ ለጣኦታት አሳልፈው ሰጡ። ስለዚህም እግዚአብሔር የኢህአዴግን መንግሥት በሚዛን መዘነው። ቀሎም አገኜው። እግዚአብሔርም የኢህአዴግን መንግሥት ቆጠረው፣ ፈጸመውም።

ወስብሃት ለእግዚአብሔር።

Last edited by ደቂቀ ያሬድ on Wed Sep 26, 2012 8:19 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዲጎኔ

ዋና አለቃ

Joined: 19 Aug 2005
Posts: 4216
Location: united states

PostPosted: Tue Sep 04, 2012 5:05 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችን ይሁን /ሰላምወኩልክሙ
ወገን ደቂቀ ያሬድ ዘእግዚእነ በከፈተው ስለወያኔው መሪ በሚያወሳ አምድ ሚዛናዊ ብዬህ ሳልቆይ እዚህ የምድራችን መንፈሳዊና ስጋዊ ለውጥና በረከት መንገዶችን ሬኔሳንስና ተሀድሶን ስታወግዝ ሳይ አፈርኩ ::ሬኔሳንስ The rebirth of learning የዘመናዊ ጥበብ ይህ የምንጻጻፍበትን መተየቢያ ሳይቀር ያመጣ ምን በደለ ?ተሀድሶ እንቅስቃሴ ከነሉተር በፊት በኛ ሀገር በነደቅ እስጢፎ የተጀመረ ዘማዊ ንጉስ ዘረያቆብን ያጋለጠ ለቅዱሳን ለመላክት ስግደት አይገባም ያለ ምን በደለ ?በአውሮፓ ከላቲን ውጭ ጌታ ይሰማል ፍትሀት ለሞቱ ሰዎች እየተከፈለ የሮማ ጳጳስና ንጉስ እየተጋሩ ሙታን መንግስተ ሰማይ ይገባሉ ኢመጽሀፍ ቅዱሳዊ አሰራርን ፕሮቴስት ማድረግ /መቃወም ወደመጽሀፍ ቅዱስ እንመለስ ለምን እዚህ ትኮንናለህ ? አስተዋል ይልቅስ ከአጼ እስከ ወያኔ ሺአመት ይንገሱ ያሉትን ምንደኛ ጳጳሳትን ብትገስጽ እንዴት ባማረበህ !

ደቂቀ ያሬድ እንደጻፈ(ች)ው:
በአራተኛ ሰንበት በእለተ መድኃኒዓለም።

እግዚአብሔር የበቀል አምላክ ነው። የበቀል አምላክ ተገለጠ።
የምድር ፈራጅ ሆይ፥ ከፍ ከፍ በል፤ ለትዕቢተኞች ፍዳቸውን ክፈላቸው።
አቤቱ፥ ኃጢአተኞች እስከ መቼ ? ኃጢአተኞች እስከ መቼ ይጓደዳሉ ?
ይከራከራሉ፥ ዓመፃንም ይናገራሉ፤ ዓመፃንም የሚያደርጉ ሁሉ ይናገራሉ።
አቤቱ፥ ሕዝብን አዋረዱ፥ ርስትህንም አስቸገሩ።
ባልቴቲቱንና ድሀ አደጉን ገደሉ፥ ስደተኛውንም ገደሉ።
እግዚአብሔር አያይም፥ የያዕቆብ አምላክ አያስተውልም አሉ።
የሕዝብ ደንቆሮች ሆይ፥ አስተውሉ፤ ሰነፎችማ መቼ ይጠበባሉ ?
ጆሮን የተከለው አይሰማምን ? ዓይንን የሠራው አያይምን ?
አሕዛብንስ የሚገሥጸው፥ ለሰውም እውቀት የሚያስተምረው እርሱ አይዘልፍምን ?
የሰዎች አሳብ ከንቱ እንደ ሆነ እግዚአብሔር ያውቃል።
ለኃጢአተኛ ጕድጓድ እስኪቈፈር ድረስ ከክፉዎች ዘመናት ይወገድ ዘንድ፥ አቤቱ፥ አንተ የገሠጽኸው ሕግህንም ያስተማርኸው ሰው ምስጉን ነው።
እግዚአብሔር ሕዝቡን አይጥልምና፥ ርስቱንም አይተውምና
ፍርድ ወደ ጽድቅ እስኪመልስ ድረስ ልበ ቅኖችም ሁሉ ይከተሉአታል።
በክፉዎች ላይ ለእኔ የሚቆም ማን ነው ? ዓመፃንስ በሚያደርጉ ላይ ለእኔ የሚከራከር ማን ነው ?በእለተ መድኃኒዓለም ጽዮንን ለአርባ አመታት ያመሰው የቄዳርና የባቢሎን ጥምር ቀንበር፣ እራስን በራስ የማጥፋት ፍልስፍና፣ አንዲቷን የቀደመች ሐይማኖት የማጥፋት ፍልስፍና፣ የእግዚአብሔርን አገር የመገነጣጠል ፍልስፍና፣ የእግዚአብሔርን መንበር የማርከስና የመንጠቅ ፍልስፍና፣ ጽዮንን ለባቢሎንና ለቄዳር ቅኝ የማስገዛት ፍልስፍና ግብአተ መሬት ተፈጸመ።

እግዚአብሔር ሆይ አንተ ከኛ ጋር ባትሆን ኖሮ የቄዳርና የባቢሎን ፈረሰኞች ዘንዶ ግልገልን እንደሚውጥ ይውጡን ነበርኮ ! አንተ ከኛ ጋር ስለሆንክ ያቀዱልንን ተንኮል አጨናገፍክ። ፈጣሪ ሆይ ምስጋና ላንተ ይሁን።

እነሆ የባቢሎን ሰዎች የሬኔሰንስና የሉተራዊ ፈርጀ -ብዙ ደባዎቻቸውን በመጠቀም በጽዮን ዙፋንህን ለመጥለፍ ይነሳሉ። ጉድጓድ እስኪውጣቸው ድረስ ይከራከራሉ። የቄዳር ምርኮኞችም በቄዳር እየተደገፉ ጽዮንን ለመጥለፍ የቄዳርን መረብ በጽዮን ዙርያ ወረወሩ። መረቡ እራሳቸውን አዙሮ ይጠልፋቸዋል። ይወድቁማል። እግዚአብሔር ሕዝቡን አይጥልምና፥ ርስቱንም አይተውምና። ፍርድ ወደ ጽድቅ እስኪመልስ ድረስ ልበ ቅኖችም ሁሉ ይከተሏታል።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ደቂቀ ያሬድ እንደጻፈ(ች)ው:
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አኃዱ አምላክ አሜን።

በዋሺንግተን ዲሲ የጉልበተኛ አገሮች መሪዎች በተሰበሰቡበት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በመናገር ላይ እያሉ አቶ አበበ ገላው የሳቸውን ንግግር በማጨናገፍ “አንባገነን ናቸው” እያለ ሲጮህ ሁሉም ሰማ። በቅድሚያ የሚያፍሩት ፕሬዘዳንት ኦባማ ናቸው ምክንያቱም “ረሃብን ለማጥፋት” በሚል አርእስት በተደረገው ስብሰባ ተሰብሳቢዎቹም ሆኑ ቴሌቪዢን ተመልካቾች የጨበጡት ግንዛቤ በፕሬዚዳንት ኦባማ ግብዣ ከኢትዮጵያ የመጡት መሪ የኢትዮጵያን ህዝብ ለእጦትና ለረሃብተኛነት የዳረጉና መብትም የነፈጉ ናቸው የሚል ነውና። ይህ የአቶ አበበ ጩኸት አቶ መለስን ብቻ ሳይሆን በዋነኛነት ያጋለጠው የፕሬዚደንት ኦባማ የትብብር ጥሪ (partnership initiative) የፌዝ ጥሪ መሆኑን ነው። ይህ ሃፍረት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ላይ የመጣው ዋልድባን ደፍረው ብዙም ሳይውል ሳያድር ነው። በእግዚአብሔር ላይ ትእቢት ያዋጣልን ?

የኢህአዴግ መኳንንቶችና ሹማምንት በሰማይ ጌታ ላይ ተተበዩ፣ ያባቶቻቸውን አምላክም አላከበሩትም። የእግዚአብሔርን ርስት ቆረሱ፣ የመቅደሶቹን እቃዎችም አረከሱ፣ እግዚአብሔርን በመናቅ የማያውቁትንና የማይገባቸውን የውጭ ፍልስፍና አመለኩ፣ የእግዚአብሔርን ርስትም ለነዚህ ለጣኦታት አሳልፈው ሰጡ። ስለዚህም እግዚአብሔር የኢህአዴግን መንግሥት በሚዛን መዘነው። ቀሎም አገኜው። እግዚአብሔርም የኢህአዴግን መንግሥት ቆጠረው፣ ፈጸመውም።

ወስብሃት ለእግዚአብሔር።
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ደቂቀ ያሬድ

ኮትኳች

Joined: 27 Nov 2005
Posts: 150

PostPosted: Sat Dec 08, 2012 12:42 am    Post subject: Reply with quote

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አኃዱ አምላክ አሜን ::

http://oftsion.org/Messengers.html

ወስብሃት ለእግዚአብሔር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia