View previous topic :: View next topic
Author
Message
ስህን Joined: 20 Jul 2004 Posts: 40
Posted: Wed Jun 20, 2012 4:05 pm Post subject: What is happening in Ethiopia?
While visiting Ethiopia I was listening to FM Sheger Radio and watching ETV , at cinema ,airport etc anywhere I go I noticed that nowdays speaking in pure Amharic is considered not fashionable and sprinkling english is considered a sign of Siltane . . I meet some freinds ,family etc even the old people are not using the amharic I used to know it !!!!!!!!!!!!! Have you noticed this?
PS I am using English because I could not find Amharic font good enough to express myself sorry
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ዳጨው Joined: 19 Apr 2004 Posts: 212
Posted: Wed Jun 20, 2012 6:48 pm Post subject:
ቂቂቂ አንተ ሀሳብህ ለመግለፅ አማርኛ ካጠረህ እዴት ስዎች እንግሊዝኛ ቀላቀሉ ብለህ ትኮንናለህ ለማንኛውም የተናገርከው ጉዳይ ትክክል ነህ :: አብዛኛው ሰው እንግሊዝኛን መቀላቀል የስልጣኔና የመማር ምልክት ከሆነ ስንበት ብሏል :: ግን በጣም የሚያሳዝነው በማይገባ ቦታ ላይ የማይሆን ቃል እየከተቱ ከሚንጣጡት ዘመናዊ ሰዎች ነን ባዮች አንዱን አቁመህ በእንግሊዝኛ ብታፋጥጠው አንድ ሙሉ አርፍተ ነገር መስራት አለመቻሉ ነው :: እኔ ትምህርቴን የጨረስኩት በወያኔ ግዜ ሲሆን ባልገፋበትም የመጀመሪያ አመት የዩንቨርስቲ ተማሪ ነበርኩኝ :: በውጭ አለም ግን ስመጣ ገና ምንም የማላውቅና ብዙ መማር እንዳለብኝ ነበር የተረዳውት :: አቤት ታዲያ ትምህርታቸው እንዴት ደስ ይላል :: ሁሉ በጀህ ሁሉ በደጅህ ያንተ የመማር ችሎታ ብቻ ነው የሚወስነው ::
እኛ አገር ግን የትምህርት ደረጃው መሞቱ ብቻ ሳይሆን ተማሪው በእጥፍ ጨምሮ ዛሬ ኮሌጅና ዩንቨርስቲ መግባት በጣም ቀላል ሆኗል :: እነዚህ ልጆች ግን ምንም አይነት እውቀት የሌላቸውና ለባህላቸውና ለአገራችው ትንሽ እንኩዋን ክብር ያልፈጠረባቸው የጠፉ ትውልዶችን ልናፈራ ችለናል :: መንግስት እንደቁም ነገር የያዘው ነገር ቢኖር በገፍ የተማረ ሀይልን ማምረት ሲሆን እነዚህ ሀይሎች ደግሞ ከውጭው አለም ጋር ሊወዳደሩ አይደለም ከህንድ የአምስተኛ ክፍል ተማሪ ያነስ እውቀት ያላቸው ሆነው አግቻቸዋለው :: ሌላው የታዘብከው ምንድነ ነው ብትለኝ መንግስት እራሱ የዚህ ችግር ሰለባ ስለሆነ ወይም ደግሞ ቋንቋ ቢጠፋ ግድ ስለማይሰጠው ቋንቋንና ባህልን ለማሳደግ ምንም ጥረት ሲያደርግ አይታይም :: ለዚህ ጥሩ ምሳሌ እንዲሆነን አንዳንድ የንግድ ቤቶችንና ድርጅቶችን መመልከቱ ይበቃል :: በአፋን ኦሮሞም ሆነ በአማርኛ ከእንግሊዝኛ እንደ ወረደ ነው የሚፅፉት :: ለምሳሌ "ዳን ቴክኖክራፍት " "ሜጋ አንፊቲያትር " "ሎንደን ካፌ " ምኑ ቅጡ ሰካራም የሚመራው አገር መስለናል :: _________________http://ayyaantuu.com/wp-content/uploads/2012/04/OromoPoliticalPrisoners2012.jpg
http://gadaa.com/KabadaJagama2009.JPG
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ዘርዐይ ደረስ Joined: 23 Oct 2004 Posts: 1081 Location: ethiopia
Posted: Wed Jun 20, 2012 9:21 pm Post subject:
ዳጨው እንደጻፈ(ች)ው : ቂቂቂ አንተ ሀሳብህ ለመግለፅ አማርኛ ካጠረህ እዴት ስዎች እንግሊዝኛ ቀላቀሉ ብለህ ትኮንናለህ ::
ሰላም ዳጨው :-
ስህን ሃሳቤን በአማርኛ የመግለጽ ችግር አለብኝ ያለ /ች አልመሰለኝም ::በ amharic font መጻፍ ስለማይመቸኝ ነው እንግሊዝኛ የተጠቅምኩት ነው መሰለኝ የግርጌ ማስታወሻው መልእክት ::እንግሊዝኛና ሕልም እንደፈቺው ነው እንዳትለኝ እንጂ ! _________________ ''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
recho Joined: 20 Sep 2004 Posts: 2992 Location: Earth
Posted: Wed Jun 20, 2012 9:25 pm Post subject: Re: What is happening in Ethiopia?
ስህን እንደጻፈ(ች)ው : Amharic font good enough to express myself sorry
ሶሪ ፒኪ ለመሆን ብዬ አይደለም ግን ፎንት ማለት እኔ እስከሚገባኝ ድረስ አልፋቤቱ ራሱ ነው እና ፎንቱ አስቸገረኝ ለመጻፈ ብትይ ይገባኛል .. ካለመዱት አስቸጋሪ ነው .. ግን ፎንቱ ስሜቴን ለመግለጽ አስቸገረኝ ግን አለገባኝም ... በአማርኛ ቁዋንቁዋ ስሜቴን ለመግለጽ አስቸገርኝ ያስኬዳል .. ፎንት ግን ኢዝ ጀስት ካራክተር እስከገባኝ ድረስ ... _________________ ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ዳጨው Joined: 19 Apr 2004 Posts: 212
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ዘርዐይ ደረስ Joined: 23 Oct 2004 Posts: 1081 Location: ethiopia
Posted: Wed Jun 20, 2012 10:17 pm Post subject:
ዳጨው እንደጻፈ(ች)ው : ዘርዐይ ደረስ
ሰላምታዬ ይድረስህ :: ጥሩ ስም ነው ያለህ ጃል እንደው ብትችል ስለ ዘርዐይ ደረስ አንድ ሩም ከፍተህ ብታጫውተን እወድ ነበር :: ወደ ጉዳያችን ስንገባ , ልጁ አማርኛ ፊደል ሀሳቤን ለመግለፅ በቂ አይደለም ማለቱ በአማርኛ እንደፈለኩኝ ሀሳቤን መግለፅ ያስቸግረኛል በሚለው ነው የወሰድኩለት እንጂ ልጁ ያለውማ ሴንስ አይሰጥም ::
ሰላም በድጋሚ :-
ልክ ነህ አባባሉ አሻሚ ነው ::እኔ ከ ዐውዱ (context) የተረዳሁት ያንን ስለሆነ ነው ::ለማንኛውም 'ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው ' እንደሚባለው እሱን /እሷን እንጠብቅ ::በተረፈ ዘርዐይ ደረስን በተመለከተ አንተ የማታውቀውን ነገር ልነግርህ የምችል አይመስለኝም ::ለማንኛውም አስብበታለሁ ::ዳጨው የራስ ጎበና አባት ነበሩ መሰለኝ ባልሳሳት ::ስህን ግን ምን ማለት ይሆን ወይስ ስኂን መሆኑ ነው ? _________________ ''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ናፖሊዮን ዳኘ Joined: 18 Apr 2008 Posts: 1874
Posted: Thu Jun 21, 2012 10:25 pm Post subject:
'ትክክል የተማረ ኃይል ማምረት ' የተማረ ከተባለ ነው እንግዲህ ህንፃ ተገንብቶ መግቢያው በር ላይ ወይ ወሎ ወይ ዲላ ወይ ምናምንትሴ ዮኒቨርሲቲ የሚል ከተፃፈበት በህወሀት ቤት ዮኒቨርሲቲ ነው ! ከዛ የሚወጡት ተማሪዎች ግን እንዳልከው የህንድ አምስተኛ ጁኒየር ተማሪዎች ሊበልጡአቸው ይችላሉ :: አንዳንዶቹ የሳይበር ቋንቋ ለቃቃሚ ስለሆኑ ብዙ ያወቁ የሚመስላቸውም አሉ ::
_________________
ባጠቃላይ ግን ለማብራራት የሞከርከው ሀሳብ ሊሰመርበት የሚገባ ጉዳይ ነው :: ባህል የሀገር ጉዳይ እንዳልሆነ እንዳልባሌ ነገር እየታየ ነው :: ስግብግብነቱ ለሀገር ግዴለሽ ከመሆን አልፎ እንደ ህወሀት ያለ ዘረኛ ቡድን ጋር መቧደኑ ትልልቅ ሰዎችን ከፍ ዝቅ ማድረጉ ...ሌላውም ሌላውም ከባህላችን መፈራረስ ጋር ተያይዞ እደመጣ ብዙ የገባን አይመስልም :: ይህን የምልበት ምክንያት ደሞ በባህል አንፃር እየደረሰ ያለውን ጥፋት ለመቀነስም ሆነ ለመዋጋት የሚደረግ ጥረት ባለማየቴ ነው ! ይሄ የባህል መፈረረስ ታዲያ ባህል ላይ የሚያቆም ሳይሆን የኢኮኖሚም የፖለቲካም አንድምታ አለው !
ራሱን ለአሜሪካኖቹ አገልጋይነት አሳልፎ የሰጠ 'ኢትዮጵያዊ ነኝ ' የሚል ልጂ በቦብ ማርሌ ዘፈን " emanicipate yourself from mental slavery' እያለ ሲወዘወዝ ልትሰማው ትችላለህ እየቀለድኩ እንዳይመስልህ ::
እንደገና ወደ መሰረታዊ ነገር ስንመጣ በጣም ግራ የተጋባ ትውልድ ላይ ነው የደረስነው :: የስልጣኔ ምንነት እና ፋይዳ የገባው አይመስልም ::
ሰሞኑን አዳም ረታ የሚባለውን ፀሀፊ ሁለት ስራዎች እግኝቼ እያነበብኩ ነው :: ""እቴሜቴ የሎሚ ሽታ "" በሚለው ድርሰቱ ላይ አርታኢ ካለው አንድ ግለሰብ (ዓለማየሁ ሌንጮ ) ጋር የተደረገ ቃለ (በ 1970አካባቢ ) ምልልስ በህዳግ ማስታወሻው ላይ ጠቅሶታል :: (በነገራችን ላይ በልቦለድ ስራ የጥናታዊ ፅሁፍ ባህሪ ያለው አይነት የህዳግ ማስታወሻ ሳይ የመጀመሪያ የው :
በተጠቀሰው ማስታወሻ ውስጥ ያለው ነገር በሙሉ ልብ ሊባል የሚገባው ነጥብ ነው :: የመረጥኩትን ሀይለ ቃል ግን ላካፍል :-
"" አብረው ተቀምጠው ሲበሉ የማይጎራረሱ ሀበሾች ቁጥራቸው ከበዛ ኢትዮጵያ የምትባል እንደሌለች ወይ በመለወጥ ላይ እንዳለች ምልክት ነው :: ...እዚህ አዲስአባ ውስጥ አንዳንድ ቦታ እንጀራ በቢላዋ ሲቆረስ እናያለን :: ይሔን በቢላ የመቁረስ ባህል የጀመረው ማን ነው ?ለምን ጀመሩ ? እንጀራን በቢላ መቁረስ እንጀራን ወደ ዳቦ ለማውረድ መጣር እንደሆነ አልተረዱም ? የእኛ ትልቁ ችግራችን ዕውር ኮፒ አድራጊዎች መሆናችን ነው :: ፈረንጂ ዳቦ በቢላ ሲቆርስ አይተን ከዛ ያን በጭፍን ያለ ጥየቃ ያለ ትንታኔ ተበደርን :: የዚህ ችግር በራሳችን ማመን አለመቻላችን ነው :: በራሱ የማያምን ህዝብ ወደ ባርነት የሚጓዝ ነው ::"" ገጽ 16.
ከላይ ከጠቀስኩት መገመት እንደሚቻለው ኢንተርቪውን ሰጠ የተባለው ሰውየ የተብከነከነው እንዲህ ነገሮች እንዳልነበሩ ሳይሆኑ በፊት ነው ! ዛሬ ከህሊና ከይሉኝታ ከክብር እና ከሀገር ፍቅር በላይ ገንዘብ እና አስረሽ ምቺው ማለት እንደተለመደ አይቶ ቢሆንስ ?? ዛሬ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (ዪኒቨርሲቲ እና ኮሌጆች ) ኢትዮጵያውያን ወጣት ሴቶች እንኵንስ የቤተሰብ እና የሀገር ክብር ሊገባቸው ቀርቶ የራሳቸውንም ክብር እየቸረቸሩ በወሲብ ንግድ ውስጥ ገብተው ኢትዮጵያን በነፃነት ትግሏ የሚያውቋት ፈረንጆቹ ዛሬ ወሲብ የሚሸጥባት ሀገር እንደሆነች በማመን ሲተሙ ---የህወሀት መንግስት የቱሪዝም ገቢያችን ጨምሯል የትግላችን ውጤት ነው እያለ ሲያላግጥ እና ትውልዱም (አብዛኛው ማለቴ ነው ) እውነት ነው ብሎ ለህወሀት ሲያጨበጭብ ቢያይ ኖሮ ምን ይል ይሆነ ነበር ?? ዛሬ ከላይ እንዳልከው ትውልዱ የሚያውቀውን እና የሚያቀላጥፈውን የሀገሩን ቋንቋ እየተጠየፈ የማያቀውን የፈረንጂ ቋንቋ በሀገር ውስጥ በማያስፈልግ ሁኔታ ለመናገር ሲሞክር ቢያ ኖሮ ምን ይል ይሆን ነገር ??
""በራሱ የማያምን ሕዝብ ወደ ባርነት የሚጓዝ ነው ::"" !!
ናፖሊዮን ዳኘ ::
ዳጨው እንደጻፈ(ች)ው : ቂቂቂ አንተ ሀሳብህ ለመግለፅ አማርኛ ካጠረህ እዴት ስዎች እንግሊዝኛ ቀላቀሉ ብለህ ትኮንናለህ ለማንኛውም የተናገርከው ጉዳይ ትክክል ነህ :: አብዛኛው ሰው እንግሊዝኛን መቀላቀል የስልጣኔና የመማር ምልክት ከሆነ ስንበት ብሏል :: ግን በጣም የሚያሳዝነው በማይገባ ቦታ ላይ የማይሆን ቃል እየከተቱ ከሚንጣጡት ዘመናዊ ሰዎች ነን ባዮች አንዱን አቁመህ በእንግሊዝኛ ብታፋጥጠው አንድ ሙሉ አርፍተ ነገር መስራት አለመቻሉ ነው :: እኔ ትምህርቴን የጨረስኩት በወያኔ ግዜ ሲሆን ባልገፋበትም የመጀመሪያ አመት የዩንቨርስቲ ተማሪ ነበርኩኝ :: በውጭ አለም ግን ስመጣ ገና ምንም የማላውቅና ብዙ መማር እንዳለብኝ ነበር የተረዳውት :: አቤት ታዲያ ትምህርታቸው እንዴት ደስ ይላል :: ሁሉ በጀህ ሁሉ በደጅህ ያንተ የመማር ችሎታ ብቻ ነው የሚወስነው ::
እኛ አገር ግን የትምህርት ደረጃው መሞቱ ብቻ ሳይሆን ተማሪው በእጥፍ ጨምሮ ዛሬ ኮሌጅና ዩንቨርስቲ መግባት በጣም ቀላል ሆኗል :: እነዚህ ልጆች ግን ምንም አይነት እውቀት የሌላቸውና ለባህላቸውና ለአገራችው ትንሽ እንኩዋን ክብር ያልፈጠረባቸው የጠፉ ትውልዶችን ልናፈራ ችለናል :: መንግስት እንደቁም ነገር የያዘው ነገር ቢኖር በገፍ የተማረ ሀይልን ማምረት ሲሆን እነዚህ ሀይሎች ደግሞ ከውጭው አለም ጋር ሊወዳደሩ አይደለም ከህንድ የአምስተኛ ክፍል ተማሪ ያነስ እውቀት ያላቸው ሆነው አግቻቸዋለው :: ሌላው የታዘብከው ምንድነ ነው ብትለኝ መንግስት እራሱ የዚህ ችግር ሰለባ ስለሆነ ወይም ደግሞ ቋንቋ ቢጠፋ ግድ ስለማይሰጠው ቋንቋንና ባህልን ለማሳደግ ምንም ጥረት ሲያደርግ አይታይም :: ለዚህ ጥሩ ምሳሌ እንዲሆነን አንዳንድ የንግድ ቤቶችንና ድርጅቶችን መመልከቱ ይበቃል :: በአፋን ኦሮሞም ሆነ በአማርኛ ከእንግሊዝኛ እንደ ወረደ ነው የሚፅፉት :: ለምሳሌ "ዳን ቴክኖክራፍት " "ሜጋ አንፊቲያትር " "ሎንደን ካፌ " ምኑ ቅጡ ሰካራም የሚመራው አገር መስለናል ::
_________________ ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ዳጨው Joined: 19 Apr 2004 Posts: 212
Posted: Sat Jun 23, 2012 6:10 am Post subject:
ሰላም ለሁላችን
ናፖሊዮን ዳኘ የኛ ችግር ዋንኛ ምንጩ ችግራችን ነው :: እድሜዎቹ ወደ አርባዎቹ መጨረሻ የሚጠጋ አንድ እንግሊዛዊ እኔ የምሰራበት ቦታ ተቀይሮ መጣና ከሰው ሁሉ ጋር ሲተዋወቅ እኔም ስሜን ነግሬው ተዋወቅን :: እረፍት ሰአት ላይ ስንጫወት ከየት ነህ አለኝ ኢትዮጵያ ስለው ፊቱ በደስታ ፈካና በየሰመሩ እንደሚሄድና ለኢትዮጵያ ትልቅ ፍቅር እንዳለው ነገረኝ :: ነገሩ ከንክኖኝ ኢትዮጵያ ከሌላው አፍሪካ አገር በምን ትለያለች እዛ ለምን በየሰመሩ መሄድ አስፈለገህ ብዬ አፋጠጥኩት :: እሱም ደንገጥ ብሎ ሰው ጥሩ ነው ምናምን እያለ መቀባጠር ሲጀምር ምናልባት በደንብ እንግሊዝኛ የሚያወሩት ኬንያውያን አይሻሉህም ነበር አልኩት :: መልስ ሳይሰጠኝ ትንሽ ሲቆይ ሴቶቹ ቆንጆዎች ናቸው አይደል አልኩት ላበረታታው :: አጅሬው ታዲያ የአልጋ ላይ ጨዋታውን ገድልና የሴቶቹን እንቢ አለማለት እየደጋገመ ሲያወራ አብረውኝ የሚሰሩት ሰዎች እሱን ሳይሆን እኔን ነበር የሚመለከቱት ምንም አልተናገርኩም አንገቴን ደፍቼ ከራሴ ጋር ሙግት ያዝኩኝ ::
እንግዲህ የሞት ስንቅ አቀባይ የመሰለ መልከ ጥፉ ነጭ ያገሬ ቆንጆ ላይ እንደዚ የሚፈነጨው ድክነታችንና አስጠቂ መንግስት ስላለን አይደለም :: ሌላው ደግሞ መንግስት ሴተኛ አዳሪነትን ለመቆጣጠር ምንም አለማድረጉ ነው :: ይባስ ብሎ እራቁት የሚደነስበት ቤት እንዳለና እዛ ደግሞ በ vip passes ካልሆነ እንደማይገባ አጫውቶኛል :: ምነው መንግስት ከልክሎ ዘግቶት አልነበረም እንዴ ስለው ይገርምሀል አብዛኛው የመንግስት ባለስልጣንና ሀብታም ነጋዴዎች ናቸው የሚገኙት ብሎኝ አረፈው :: ፈጣሪ የሚመለክበት ግዜ እየጠፋ ብር የሚመለክበት ዘመንና ብርን የሚያመልክ ትውልድ እየተፈጠረ ይገኛል :: አገር , ባንዲራ , ወኔ ይሄ ሁሉ በሀብታሞችና ዘመናይ ነኝ ባዮች ዘንድ ቦታ የለውም :: ለጥቁር ህዝብ አለኝታ አልገዛም ባይ የነበረችው አገራችን ዛሬ ልጆቿን ማንም በገንዘቡ ያሻውን እያደረጋቸው ባርነትን እጇቿን ዘርግታ እየለመነች ስትታይ በእውነት ታሳዝናለች :: ነፃነት ይሄ አይደለም የአስራ ስድስትና የአስራ ሰባት አመት ወጣቶች በ hiv እየተቀሰፉ ማለቅ ስልጣኔ አይደለም :: ልጆቻችንን ለባእድ ሰዎች መሸጥ ስልጣኔ አይደለም :: እስቲ ይሄን ታዋቂ የአሜሪካ ካርቱን ስለ ኢትዮጵያ የቀለደውን እንመልከተው ::
http://www.youtube.com/watch?v=YRkWGNV8hNc&feature=related _________________http://ayyaantuu.com/wp-content/uploads/2012/04/OromoPoliticalPrisoners2012.jpg
http://gadaa.com/KabadaJagama2009.JPG
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ናፖሊዮን ዳኘ Joined: 18 Apr 2008 Posts: 1874
Posted: Tue Jun 26, 2012 6:04 am Post subject:
ሰሞኑን በሆነ አጋጣሚ ያገኘኍት የውጪ ዜጋ እጽኖት ሰጥታ ካነሳቻቸው ሀሳቦች አንዱ 'ኢትዮጵያ ትልቅ የቱሪዝም ፓቴንሺያል አላት ' ...አዲስ ነገር የነገረችኝ ይመስል :: የትኛውን ፓቴንሺያል ማለቷ እንደሆነ ሴትዮዋ ከምታወራቸው ሌሎች ነገሮች ለመገመት ችያለሁ ::
በዚህ አላበቃም ማህበረሰቡ 'ዲስፔየር ይታይበታል '? አለችን --- እኔ ሳውቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ (እንደህዝብ )እና ዲስፔየር አይተዋወቁም ! የመስተዳድሩን አስተዋጾዎ ስጠቁማት ደሞ ነገሩን ወደ ኢኮኖሚ ትወስደዋለች ---እንግዲህ በአፍሪካም ታሪክ ጭምር እንደ ህወሀት አይነት ግዙፍ ርዳታ የተቀበለ አመራር አልነበረም ::
እስኪ ለማንኛውም እመለሳለሁ :: አሁን እንቅልፍ ነገር ሳለለብኝ መቀጠል የምችል አይመስለኝም ::
ናፖሊዮን ዳኘ ::
ዳጨው እንደጻፈ(ች)ው : ሰላም ለሁላችን
ናፖሊዮን ዳኘ የኛ ችግር ዋንኛ ምንጩ ችግራችን ነው :: እድሜዎቹ ወደ አርባዎቹ መጨረሻ የሚጠጋ አንድ እንግሊዛዊ እኔ የምሰራበት ቦታ ተቀይሮ መጣና ከሰው ሁሉ ጋር ሲተዋወቅ እኔም ስሜን ነግሬው ተዋወቅን :: እረፍት ሰአት ላይ ስንጫወት ከየት ነህ አለኝ ኢትዮጵያ ስለው ፊቱ በደስታ ፈካና በየሰመሩ እንደሚሄድና ለኢትዮጵያ ትልቅ ፍቅር እንዳለው ነገረኝ :: ነገሩ ከንክኖኝ ኢትዮጵያ ከሌላው አፍሪካ አገር በምን ትለያለች እዛ ለምን በየሰመሩ መሄድ አስፈለገህ ብዬ አፋጠጥኩት :: እሱም ደንገጥ ብሎ ሰው ጥሩ ነው ምናምን እያለ መቀባጠር ሲጀምር ምናልባት በደንብ እንግሊዝኛ የሚያወሩት ኬንያውያን አይሻሉህም ነበር አልኩት :: መልስ ሳይሰጠኝ ትንሽ ሲቆይ ሴቶቹ ቆንጆዎች ናቸው አይደል አልኩት ላበረታታው :: አጅሬው ታዲያ የአልጋ ላይ ጨዋታውን ገድልና የሴቶቹን እንቢ አለማለት እየደጋገመ ሲያወራ አብረውኝ የሚሰሩት ሰዎች እሱን ሳይሆን እኔን ነበር የሚመለከቱት ምንም አልተናገርኩም አንገቴን ደፍቼ ከራሴ ጋር ሙግት ያዝኩኝ ::
እንግዲህ የሞት ስንቅ አቀባይ የመሰለ መልከ ጥፉ ነጭ ያገሬ ቆንጆ ላይ እንደዚ የሚፈነጨው ድክነታችንና አስጠቂ መንግስት ስላለን አይደለም :: ሌላው ደግሞ መንግስት ሴተኛ አዳሪነትን ለመቆጣጠር ምንም አለማድረጉ ነው :: ይባስ ብሎ እራቁት የሚደነስበት ቤት እንዳለና እዛ ደግሞ በ vip passes ካልሆነ እንደማይገባ አጫውቶኛል :: ምነው መንግስት ከልክሎ ዘግቶት አልነበረም እንዴ ስለው ይገርምሀል አብዛኛው የመንግስት ባለስልጣንና ሀብታም ነጋዴዎች ናቸው የሚገኙት ብሎኝ አረፈው :: ፈጣሪ የሚመለክበት ግዜ እየጠፋ ብር የሚመለክበት ዘመንና ብርን የሚያመልክ ትውልድ እየተፈጠረ ይገኛል :: አገር , ባንዲራ , ወኔ ይሄ ሁሉ በሀብታሞችና ዘመናይ ነኝ ባዮች ዘንድ ቦታ የለውም :: ለጥቁር ህዝብ አለኝታ አልገዛም ባይ የነበረችው አገራችን ዛሬ ልጆቿን ማንም በገንዘቡ ያሻውን እያደረጋቸው ባርነትን እጇቿን ዘርግታ እየለመነች ስትታይ በእውነት ታሳዝናለች :: ነፃነት ይሄ አይደለም የአስራ ስድስትና የአስራ ሰባት አመት ወጣቶች በ hiv እየተቀሰፉ ማለቅ ስልጣኔ አይደለም :: ልጆቻችንን ለባእድ ሰዎች መሸጥ ስልጣኔ አይደለም :: እስቲ ይሄን ታዋቂ የአሜሪካ ካርቱን ስለ ኢትዮጵያ የቀለደውን እንመልከተው ::
http://www.youtube.com/watch?v=YRkWGNV8hNc&feature=related