WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የአፍሪቃ ሕብረት :- ደቡብ ሱዳን ወዴት እያመራች ነው ?
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 11, 12, 13, 14  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Jun 03, 2012 4:09 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም የተወደዳችሁ ወገኖቼ :-

በእኒህ ሁለት ሣምንታት በአፍሪቃ አህጉር ሁለት የቀድሞ የአፍሪቃ አምባገነን ገዢዎች ለወደፊቱ ወደተዘጋጀላቸው የእሥር ኑሮ ተሸጋግረዋል :- የቀድሞው የላይቤሪያ ጨፍጫፊ ቻርለሥ ቴይለር እና የግብፁ አምባገነን ገዢ የነበረው ሆሲኒ ሙባረክ :: ቻርለሥ ቴይለር 50 ዓመት ሲከናነብ ሙባረክ ደግሞ ዕድሜ ይፍታህ ተፈርዶበታል :: እኒህ አምባገነኖች በሥልጣን ዘመናቸው የሰውን ልጅ ሕይወት ማጥፋት ትንኝ እንደመግደል የሚቆጥሩ ሰው -ጤፉዎች ነበሩ :: በሠፈሩት ቁና መሠፈር አይቀርምና ቀሪ ዕድሜያቸውን ባለ 5 ኮከብ ደረጃ ባላቸው እሥር ቤቶች ውስጥ ያሣልፋሉ ::

በነገራችን ላይ ግብፅ የማምሉክ ገዢዎች አገር ለመሆን የቀራት ጊዜ ጥቂት ሣምንታት ብቻ ነው Rolling Eyes

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu Jun 21, 2012 2:39 am    Post subject: Reply with quote

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

ጥንታዊቷ ምሥር (ግብፅ ) ረዥም ታሪኳ የሚያሣየው በአብዛኛው በየዘመኑ በተነሡ የተለያዩ የዓላም ኃያላን ቅኝ ተገዢነት ማሣለፏን ነው :: የምሥርን ሰዎች ግሪኮች : ሮማውያን : ፋርሶች : መሐመዳውያን አረቦች : ቱርኮች እና እንግሊዞች እየተፈራረቁ ገዝተዋቸዋል :: ይህም ሆኖ 1940 መጀመሪያ ጀምሮ የምሥር ሰዎች የራሣቸው የሚሉት ብሔራዊ ማንነት አዳብረው ፖለቲከኞቻቸውም የሌላውንም የዓረብ ሕዝብ የፖለቲካ አቅጣጫ ተላሚ ለመሆን የሚያስችላቸውን አቅም ማዳበር ችለዋል :: ካለፈው ዓመት ጀምሮ በምሥር ምድር የሚታየው ለውጥ ደግሞ 'መጨረሻው ምን ይሆን ?' የሚያሠኝ ነው ::

1942 .. (... ጁላይ 1952) ጀምሮ ምሥር ስትገዛ የኖረቸው በወታደራዊ አምባገነን ገዢዎች ነው :: ዛሬም በሕዝባዊ አብዮት ጄኔራል ሙባረክ ከሥልጣን ቢወገድም የዕድሜ ልክ ታማኝ ወዳጆቹና ጓደኞቹ አነ ማርሻል ታንታዊ በእርሱ እግር ተተክተው ፈላጭ ቆራጭ የምሥር ገዢዎች ሆነዋል :: ሠሞኑን የምሥር ሕዝብ በእኒህ ወታደራዊ አምባገነኖች ላይ ቁጣውን በአደባባይ እየገለፀ ነው :: የዚህ ሕዝባዊ ቁጣ ግፊት ምናልባትም ምሥርን ከሚከተሉት ወደ አንዱ አቅጣጫ ይመራት ይሆናል :-

1 ..... የግብፅ ወታደራዊ ደርግ ይበልጥ ሥልጣኑን የሙጥኝ ብሎ ካሁኑ በከፋ አገዛዝ ለመቀጠል ይወስናል ::

2 ..... አመቺ ጊዜ ሲጠብቁ የኖሩት 'የእስላማዊ ወንድማማቾች ' እንቅስቃሴ በምርጫ ሽፋን ግብፅን አዲስ የከሊፋ እስላማዊ አገዛዝ ግዛት ያደርጓታል ::

3 ..... የምሥር ምድር ሰዎች ለረዥም ዘመናት ልክ በሊባኖስ እንደተከሠተው በማያባራ የእርስ በእርስ ጦርነት ይታመሣሉ ::

እናንተስ ምን ይታያችኋል ?

ተድላ

ከሰባት ወራት በፊት ይህንን አስተያዬት አሥፍሬ ነበር :: እስካሁን በምሥር ምድር የእርስ -በእርስ ጦርነት አልተነሣም :: ነገር ግን በተራ ቁጥር 1 እና 2 ያሉት ከሞላ ጎደል ዕውን ሆነዋል :: በዚህም ምክንያት የግብፅ ወታደራዊ ደርግ በእሥላማዊ ወንድማማቾች የተሞላውን አዲሱን ፓርላማ በትኗል : የእሥላማዊ ወንድማማቾች እጩ የሆነው መሐመድ ሙርሲ አሸነፍኩት የሚለውን "የፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ትክክለኛነት ለማጣራት " በሚል ምክንያት ውጤቱ ይፋ እንዳይደረግ አግዷል :: ስለዚህ በመጪዎቹ ሣምንታት ከሁለት አንዱ ይለይለታል የሚል ግምጋሜ አለኝ :- ወይ እሥላማውያኑ በሕዝባዊ አመፅ የወታደራዊውን ደርግ አገዛዝ አንበርክከው ሥልጣን ይጠቀልላሉ : ያለበለዚያም በምሥር 'የፓኪስታን ዓይነት ' ወታደራዊ አገዛዝ ዳግም ይንሠራፋል :: ወጣም ወረደ ምሥር የአመፅ አገርነቷ ይቀጥላል ::

የምሥር ፖለቲካ ያለመረጋጋት በተለይ በምሥራቅ በኩል ላለችዋ ጎረቤቷ እሥራኤል አስጊ ነው :: በደቡብ በኩል ያሉት የሰሜን ሱዳን እሥላማዊ አገዛዝን ያሠፈኑት እነ አል -በሽር ደግሞ ይበልጥ ውጥረት ውስጥ ይወድቃሉ :: ምክንያቱም የግብፅ ወታደራዊ ደርግ አገዛዝ በሥልጣን ላይ ለመቆዬት ሲል ዞሮ ዞሮ በሰሜን ሱዳን ተመሣሣይ ርዕዮት ያለው አገዛዝ ወደ ሥልጣን እንዲመጣ ግፊት ማድረጉ ስለማይቀር ነው ::

ይህ ሁሉ ለወያኔ ትልቅ የራስ ምታት መሆኑ አይቀርም ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Jul 11, 2012 3:53 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ነገደ -አርበኛ ዘዋርካ :-

የምሥር ምድር ለማያባራ የፖለቲካ ትኩሣት የተዳረገች ይመስላል :: በዚያች አገር ከቀን : ቀን የሚከሠቱት ክንውኖች ገና ብዙ የፖለቲካ ትርምስ እንደሚኖር ጠቋሚ ናቸው :: ባለፈው ወር ሰኔ 8 ቀን 2004 .. ወታደራዊው አገዛዝ ዐይን ያወጣ የሕዝብ ድምፅ ግልበጣ አካሂዶ ፓርላማውን በትኖ ነበር :: ይባስ ብሎም የአገሪቱን ሕግ በመቀየር የወታደሩ ክፍል ከሲቪሉ አስተዳደር ቁጥጥር ውጪ የሚሆንበትን ሕግም ደንግጎ ነበር :: የእሥላማዊ ወንድማማቾች ዕጩ የነበሩት ዶክተር ሙርሲ መሐመድ ፕሬዘዳንት ሆነው ከመመረጣቸው እኒህን የወታደሩን የሥልጣን ማደላደያ አዳዲስ ድንጋጌዎች በአደባባይ መዘንጠሉን ተያያዙት ::
    # ..... ከመነሻው ለፕሬዘዳንታዊ መሃላ አንድ ቀን ሲቀራቸው በዋና ከተማው በካይሮ የሚኖሩትን ደጋፊዎቻችውን ልብ ለመያዝ በጣህሪር አደባባይ 'በሕዝብ የተመረጡ መሪ በመሆናቸው ተጠሪነታቸው ለመረጣቸው የአገራቸው ሕዝብ ብቻ እንደሆነ ' አወጁ ::

    # ..... በበነጋው መሃላ የፈፀሙት በወታደሮቹ ካምፕ ሣይሆን በአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተገኝተው ነበር ::

    # ..... ከዚያም በወታደሮቹ የተበተነው ፓርላማ ከትላንትናው ዕለት ጀምሮ የተመረጠበትን ሥራ እንዲቀጥል አወጁ : ፓርላማውም ዛሬ ሥራውን በይፋ ጀምሯል ::

    # ..... እዚህ ላይ ወታደሮቹ እንዳይቀናቀኗቸው ከአንድ ቀን በፊት በዕጩ መኮንኖች ምረቃ ሥነ -ሥርዓት ላይ ተገኝተው አዲሶቹን መኮንኖች መርቀዋል ::

ሰውዬው የፖለቲካ ብሥለት ያላቸው ይመስላል :: ነገር ግን 50 ዓመታት ለበለጠ ጊዜ ተጠያቂነት የሌለበት ብዙ ጥቅማ ጥቅም ያለው ሥልጣን የለመዱት ቅምጥል ወታደሮች እንዲህ በቀላሉ ለሰውየው የፖለቲካ ጅምናስቲክ የሚንበረከኩ ይሆናሉ ተብሎ አይገመትም :: እንዲያውም በመጪው ቅዳሜና እሑድ ዶክተር ሙርሲ ለአፍሪቃ ሕብረት ሥብሰባ ወደ አዲስ አበባ ጎራ ሲሉ እኒህ ወታደሮች ጉድ እንዳይሠሯቸው ወይም አንድ አዲስ ወጥመድ እንዳይዘረጉባቸው ያሠጋል :: ወጣም ወረደ የምሥር ምድር ገና ብዙ : እጅግ ብዙ ውጣ ውረድ ይጠብቃታል : ዜጎቿም እንዲሁ ::

ለመረጃ ያህል እስኪ እኒህን ወቅታዊ ትንታኔዎች አንብቧቸው ::

ምንጮች :-
1 ..... Hamza Hendawi, Associated Press, Tue Jul 10, 2012. Egypt's legislature convenes despite court ruling.

2 ..... BBC, Tue July 10, 2012, Last updated at 12:47 ET. Egypt: Who holds the power?

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Jul 31, 2012 11:03 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ነገደ -አርበኛ ዘዋርካ :-

የለገሠ [መለስ ] ምሥጢራዊ ፍፃሜ በአፍሪቃ አኅጉር በሥልጣን ላይ ፊጥ ብለው ያለገደብ ሲገዙና ሲረግጡ ከኖሩ አምባገነኖች ፍፃሜ የተለየ አይደለም :: 1950 መጀመሪያ ጀምሮ ከቅኝ አገዛዝ ነፃ የወጡትን የአፍሪቃን አገሮች አምባገነን ገዢዎች ፍፃሜዎ -መንበር ብንመለከት ወይ በመንግሥት ግልበጣ : ወይ ሆን ተብሎ በመመረዝ : ያለበለዚያም በሤራ በተቀነባበረ ግድያ ከሥልጣን የተወገዱት የአፍሪቃ አምባገነን ገዢዎች ቁጥር በምርጫም ሆነ በፈቃዳቸው ሥልጣን ከለቀቁት ቁጥር በእጅጉ ይልቃል :: ለናሙና ያህል ባለፉት አምሥት ዓመታት ከአፍሪቃ አኅጉር አገሮች ገዢዎች መካከል አሟሟታቸው አጠራጣሪ እና ሚሥጢራዊ የነበረውን እንመልከት ::

1 ..... የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዘዳንት ኡማሩ ያራ -ዱዋ (ነሐሴ 10/1943 - ሚያዝያ 28/2002 .. [16 August 1951 5 May 2010])
እኒህ የናይጄሪያ ፕሬዘዳንት የነበሩ ሰው በፅኑ ሕመም መሠቃየት የጀመሩት ገና ወደ ሥልጣን ሣይወጡ እንደነበረ ይታወቃል :: እንዲያም ሆኖ ከኅዳር 13/2002 ጀምሮ ለሕክምና ወደ ሣዑዲ አረቢያ አቀኑና ሕመማቸው ምን እንደሆነ ሣይገለጥ እዚያው ከረሙ :: በመጨረሻም ፐሪካርዲየም በሚባል የልብ ሽፋን ጡንቻ ሕመም ምክንያት ሕክምና ሲከታተሉ እንደነበረ ተገለፀ :: ይህንን መረጃ ላለመሥጠት እርስ -በእርሱ የሚጋጭ ወሬ ሲያናፍሡ የከረሙት የአገራቸው ባለሥልጣኖች ብቻ ሣይሆኑ የዓለም አቀፉም ሚዲያ (በተለይ የምዕራባውያኑ ) ጭምር ነበሩ :: በመጨረሻም አገራቸው ተመልሠው የማይቀረውን አፈር ቀመሡ :: ምንጭ :- Wikipedia (Accessed July 31, 2012). Umaru Musa Yar'Adua.

2 ..... የቀድሞው የጊኒ ፕሬዘዳንት ላንሣና ኮንቴ (ኅዳር 20/1926 - ታኅሣሥ 13/2001 .. [November 30, 1934 - December 22, 2008])
የእኒህ አረጋዊ አሟሟትም ምሥጢራዊ ነበር :: ሕመማቸው ለረዥም ጊዜ ተደብቆ ኖሮ ሲሞቱ ድንገት ለጊኒ ሕዝብ መርዶው ሲነገር አስደንጋጭ ዜና መሆኑ የማይታበል ነበር :: ቢሆንም መርዶው በሞቱ በበነጋታው በመነገሩ የጊኒ ሕዝብ ከተጨማሪ ውዥንብር ተገላግሏል ::
ምንጭ :- Wikipedia, Accessed Tue Jul 31, 2012. Lansana Conté .

3 ..... የቀድሞው የዛምቢያ ፕሬዘዳንት ሌቪ ፓትሪክ ሙዋንዋሣ ነሐሴ 28/1940 - ነሐሴ 13/2000 .. [September 3, 1948 August 19, 2008])
ሦሥተኛው የዛምቢያ ፕሬዘዳንት ነበሩ :: የፕሬዘዳንትነት ሥልጣን ላይ ከመውጣታቸው 10 ዓመታት በፊት በደረሠባቸው የመኪና አደጋ በቀሪ የሕይወት ዘመናቸው ጤንነት ላይ ጉልህ ተፅዕኖ የነበረውን ደዌ አፍርተው ነበር :: ለሞታቸው ምክንያት የነበረው አጋጣሚ የተከሠተው ለአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ በሻርም -አል -ሼክ (ሢናይ ግዛት : ግብፅ ) ባጋጠማቸው የጤና መቃወስ ነበር :: እዚያው ሻርም -አል -ሼክ በስብሠባው ላይ እያሉ ድንገተኛ በሆነ ሁኔታ ጭንቅላት ውስጥ ደም ሲፈስ በሚከሠት ራስን የመሣት (stroke) አደጋ ያጋጠማቸውና የግብፅ ሐኪሞች ሊረዷቸው ይሞክራሉ : ሕመሙ ፅኑ ስለነበረ በዓለም አቀፍ 'SOS' የአየር አምቡላንስ ወደ ፓሪስ (ፈረንሣይ ) ተወሠዱ :: ከዚያ በኋላ ስለጤንነታቸው የሚሠራጩት ዜናዎች እርስ -በርሣቸው የተምታቱና ግልፅ ያልሆኑ ነበሩ :: ብሎ : ብሎ ግን ሞታቸው ባረፉ በማግሥቱ መሠማቱ አልቀረም ::
ምንጭ :- Wikipedia, Accessed Jul 31, 2012. Levy Patrick Mwanawasa.

4 ..... የቀድሞው የማላዊ ፕሬዘዳንት ቡንጉ - ሙታሪካ የካቲት 16/1926 -መጋቢት 27/2004 . . ([February 24, 1934 - April 5, 2012])
የእኒህ ፕሬዘዳንት አሟሟታቸው ሣይሆን ከሞቱ በኋላ መርዶውን ለመደበቅ የተደረገው ሙከራ የሚያስገርም ነበር :: በዘንድሮው ዓመት መጋቢት 27 ቀን 2004 .. በአገራቸው ያሉ በሁለተኛዋ ትልቋ የማላዊ ከተማ በሊሎንግዌ በልብ ድካም ያርፋሉ :: ይህንን ዜና ለመደበቅ ሲባል አሥከሬናቸው ተጭኖ ወደ ጆሃንስ በርግ (ደቡብ አፍሪቃ ) ይወሠዳል :: ከዚያ ከብዙ የተምታታ ዜና ሲሠራጭ ቆይቶ የማላዊ ባለሥልጣኖች ከሁለት ቀናት ሞታቸውን ለአገሬው ሕዝብ አረዱት :: ነገር ግን ቀደም ብሎ መሞታቸውን የዘገቡት የአገሬው ጋዜጠኞች ሣይቀር ያዩት ማዋከብ ቀላል አልነበረም ::
ምንጭ :- Wikipedia, Accessed Jul31, 2012. Bingu wa Mutharika.

በዚህ በመገባደድ ላይ በሚገኘው የሐምሌ ወር አፍሪቃ ውስጥ ሁለት ገዢዎችና አንድ በሕዝብ የተመረጡ መሪዎች አርፈዋል :: ሙባረክ ከሥልጣን ሊወገድ ሲል ምክትል ፕሬዘዳንት አድርጓቸው የነበሩት የኦማር ሱሌይማን እና የለገሠ [መለስ ] አሟሟት እጅግ ሚሥጢራዊ ነው :: ቢያንስ ቢያንስ የጋናው ፕሬዘዳንት ጆን አታ ሚልስ ሕመምና ሞታቸው ሣይደበቅ በወቅቱ ይፋ በመደረጉ ምክንያት የአገራቸው ሕዝብ አዝኖ ቀብሯቸዋል :: ከሁሉም የሚገርመው ግን የለገሠ ሞት ሚሥጢር ሆኖ ለዘለዓለም ሊዘልቅ እንደማይችል እየታወቀ መርዶውን ለሮቦት ተከታዮቹ ሣይገልፁላቸው እስከመቼ ሊቆዩ ይሆን ?

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Aug 01, 2012 9:56 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ነገደ -አርበኛ ዘዋርካ :-

'DAILYMAVERICK' የሚባል የደቡብ አፍሪቃ የድረ -ገፅ ጋዜጣ ስለቅርብ ዘመኑ የአፍሪቃ አምባገነኖች አሟሟት አንድ አጠር ያለች ትንታኔ አቅርቧል :- ለአፍሪቃ አምባገነኖች የሠጠው ምክር "አፍሪቃ ውስጥ መሪ መሆን አደገኛ ነው : ለሕይወት ያሠጋልና " የሚል ነው ::

ምንጭ :-DAILYMAVERICK, Wed Aug 1, 2012. Africa: Why Do African Presidents Keep Dying?

Quote:
Being an African president is a risky business. It can be fatal. We're already three down this year alone, and critically-ill Meles Zenawi looks like he'll make it four. Other continents, by and large, seem to do a better job of hanging on to their leaders. SIMON ALLISON examines Africa's strangely high presidential mortality rate.

The curse of the African president strikes again. This time, its victim was Ghana's John Atta Mills, who complained of pains on Monday last week and was dead by Tuesday afternoon. Mills was the latest in a disturbingly long line of African presidents to be unexpectedly and unceremoniously despatched to the Great Presidential Palace in Sky while still firmly ensconced in a real one.

Mills is the third this year alone. Before him was Malawi's Bingu wa Mutharika, who had a heart attack in April after over-exerting himself in an illicit sexual encounter with a female MP (according to this scandalous report, which, as much as I want it to be true, does strain the definition of credibility).

And in January, Guinea-Bissau's Malam Bacai Sanha succumbed in Paris after spending most of his two years in office in hospitals. Not Guinea Bissau hospitals, of course. As a rule, African presidents don't leave themselves at the mercy of their own health systems, not even in Guinea Bissau, which has the continent's best drug supplies (a fringe benefit of being a narco-state).

Go back just a little bit further and the list of dead sitting African presidents gets alarmingly longer. Libya's Muammar Gaddafi last year, although his circumstances were rather unusual (as, of course, was he).

In 2010, it was Nigeria's Umaru Musa Yar'Adua. In 2009, Omar Bongo of Gabon. In 2008, Zambia's Levy Mwanawasa and Guinea's Lansana Conté .

Maybe it's a presidential thing. It's a stressful job. But other continents aren't affected in the same way. Since 2008, Africa has lost eight heads of state. There are only 54 states. That's a presidential mortality rate of nearly 15%; slightly higher than the infant mortality rate of Sierra Leone, which is the second highest in the world. In other words, a baby in Sierra Leone has more chance of surviving its first five years than African presidents do of getting through a few terms in office.

Contrast this with other continents. In the same time period, there was just the one presidential fatality each from Asia (the Dear Leader from North Korea), Europe (Poland's Lech Kaczy?ski, in a plane crash), and North America (David Thomson of Barbados, from cancer). South America's leaders all somehow managed to keep themselves alive, an impressive feat especially considering Hugo Chavez's increasingly shaky public appearances. Same for Australasia.

So what's happening in Africa - why do our presidents keep dying on us?

It's tempting to resort to the old cliché about death being the only thing that can separate African leaders from their grip on power. But the facts don't support this analysis. It's certainly true of Bongo, Conte and Gaddafi, all of whom were old-school dictators who were never going to stop.

But the other five were all within their constitutional term limits. And they hadn't even fiddled with those limits yet. Mutharika looked like he was about to, but never got the chance. Mills, Sanha and Yar'Adua hadn't even made it to a second term.

So the problem must lie somewhere else. Perhaps it's something to do with age. Political success tends to come later to African leaders, a function perhaps of some holding on to it for too long and a long tradition of veneration for one's elders. The average age of African heads of state is 62.5. That's pension time, or nearing it, in most countries. To give you a bit of context, the European equivalent is just 55. This is also the average age of American presidents at the time of their inauguration. Barack Obama is 50. David Cameron is 45.

Given that 62.5 is just an average, and the continent does have a few young leaders - the DRC's Joseph Kabila is just a pipsqueak at 41, while Swaziland's King Mswati III is 44 and still virile (he needs to be with all those wives) - it follows that there are also some very old leaders.

Plenty of Zimbabweans have questioned why Robert Mugabe is still alive and kicking at 89 when so many younger presidents have fallen before him. Mwai Kibaki of Kenya is 80, and rumours abound that he's exactly as alert as 80-year-olds are expected to be: that is, not very.

Age is certainly a factor in Africa's high presidential mortality rate, probably the main factor. It's a truism that the longer you live, the more chances you have to die. Life is really just one long countdown to death; you don't know when it's coming, but it's always getting closer.

Going by the averages, African presidents are more than seven years closer to their deaths than their European counterparts. The recent record seems to confirms this.

But it's not just about age. Bear in mind too that basic health indicators in Africa are, on the whole, lower than any other continent.

You might think this has nothing to do with presidents, especially when they seek treatment in exclusive foreign hospitals. But healthcare is about more than just immediate treatment. Lifestyle plays a role, and, more pertinently here, so does one's health history. Growing up without access to decent healthcare while quite probably living through some form of rebellion, civil war or chaotic independence movement is bound to have long term implications.

Whatever the reason, it's a disturbing phenomenon. Sudden deaths create power vacuums, and power vacuums can cause huge instability. Sanha's death led almost directly to the coup in Guinea Bissau and the messy transitional arrangement that doesn't look like it's working.

Mutharika's passing also prompted a few tense moments, with members of his party wanting to ignore the consitutional succession process. In the end, everything worked out well, with Mutharika's replacement, Joyce Banda, proving far more effective than he ever was.

But Banda had better look after herself. Being an African president is a dangerous business, after all.
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Nov 14, 2012 5:47 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ነገደ -አርበኛ ዘዋርካ :-

ከአንድ ዓመት በፊት የወያኔ ቅጥር -ነፍሰ ገዳዮች አቤዪ ወደተባለችዋና በሰሜን ሱዳን እስላማዊ አገዛዝና በደቡብ ሱዳን ሪፑብሊክ መንግሥታት መካከል የግዛት -ይገባኛል ውዝግብ መንስዔ ወደሆነችዋ ግዛት ሲያመሩ ለገሠ [መለስ ] ዜናዊ በሕይወት ይገኝ ነበር :: ያኔ እርሱ የቀመረው ከሁለቱም ሱዳኖች ወዳጅነትን አፍርቶ ዘላቂ የሆነ የወያኔን ጥቅም ማስከበር ሊሆን እንደሚችል ለመገመት አይከብድም :: ቀናት አልፈው በወራትና ዓመት ጊዜ ሲለኩ የአቤዪ ችግር እያመረቀዘና ይበልጥ እየተወሣሠበ በመሄዱ ምናልባትም ቅጥር ነፈሰ -ገዳዮቹ የወያኔ ጀሌዎች በቁማቸው በአቤዪ ሕዝብ በእሣት የሚጋዩበት ወይም በጅምላ የሚጨፈጨፉበት ዕለት ሩቅ አይሆንም :: ለዚህም ጠቋሚ የሆነ ግጭት ዛሬ ረቡዕ በአቤዪ ከተማ ተክስቶ ነበር :: ጉዳዩም እንዲህ ነው :- ከሰሜን ሱዳን የመጡትና 'ሚሴሪያ ' በመባል የሚጠሩት ልውጥ የአረብ ጎሣ አባሎች ለደቡብ ሱዳን አካል የሆኑትና በአቤዪ ግዛት ባለቤትነታቸው የሚመኩትን የዲንቃ -ጎቅ ጎሣ መሪዎችን ሣያሣውቁ ወደ አቤዪ ግዛት በመግባታቸው የዲንቃ -ጎቅ ጎሣ አባሎች በሚሴሪያዎች መስጊድ ዙሪያ የተቃውሞ ሠልፍ ያደርጋሉ :: የወያኔ ቅጥር ነፍሰ -ገዳዮች ግን ይህንን የሕዝብ ተቃውሞ ለመበተን በኢትዮጵያውያን ላይ በተደጋጋሚ እንደሚያደርጉት ወደ ሕዝቡ ይተኩሱና አንድ ሰው አነጣጥረው ተኩሰው ደረቱ ላይ በጥይት መትተው ይገድሉና ሌሎችን ያቆስላሉ :: በዚህ የወያኔዎች አረመኔያዊ ድርጊት የተቆጡት የዲንቃ -ጎቅ ጎሣ አባሎች የወያኔዎችን የጦር ካምፕ ከብበው ተቃውሟቸውን ቀጥለዋል :: እንግዲህ ሠሞኑን ወያኔዎች አቤዪ ግዛት ውስጥ የሚገጥማቸውን የሕዝብ የአፀፋ -እርምጃ አብረን የምናየው ይሆናል ::

ምንጭ :- Radio Tamazuj, Wed 14 Nov 2012. UN troops clash with Abyei protesters, 1 dead.

Quote:
One person was killed and three others wounded yesterday in a clash between Ethiopian troops and citizens of Abyei at the city market.

Witnesses told Radio Tamazuj that a group of Abyei youth tried yesterday afternoon to raid a mosque in the town after learning that a group of Misseriya from the native administration had come to the region to meet with leaders of the Dinka Ngok.

But Ethiopian peacekeeping troops refused them and evacuated the native administration leaders to the headquarters of UNISFA, the UN Interim Security Force for Abyei.

The youth returned to storm the mosque for a second time which led to a clash between the Ethiopian troops and the citizens. Witnesses claimed that the Ethiopian troops fired at the demonstraters, killing a man named Majik Kuol, who was hit in the chest.

Three others were wounded, one of them critically, who was transferred to the UNISFA hospital for treatment.

Sultan Kuol, a Dinka Ngok leader, condemned the Misseriya native administration leaders for coming to the region without prior notice, a move which he called provocative and caused the young people to demonstrate.

UNISFA in a security report yesterday stated that A group of women and children held a gathering in-front of UNISFA Main Gate on this date at around 0645H demanding a stoppage of violations on their land based on what was written on some papers being carried. The crowd dispersed at around 0925H and proceeded to Abyei town.

Crowd was also reportedly grouped in Abyei town particularly at the mosque where a group of Misseriya Chiefs are staying. Situation in Abyei town is still tense as of this report, it added.

The report was apparently prepared before the shooting incident and did not mention any violence at the mosque.

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Jan 22, 2013 3:32 pm    Post subject: Reply with quote

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
4 ..... የኢሣያስ በሞትም ሆነ በሌላ መንገድ ከሥልጣን መወገድ በአካባቢው የኃይል አሠላለፍ ላይ ምን ዓይነት ተፅዕኖ ይኖረዋል ?

ጥያቄዎችን መጨመር ይቻላል :: እስኪ ኃሣቦቻችንን እንለዋወጥ ::

ተድላ

ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ላይ ኢሡ ወፈፌው "ሞቷል " ተብሎ ትንሽ ግርግር ተፈጥሮ ነበር :: ትላንት ደግሞ 'መፈንቅለ አገዛዝ ተሞከረበት ' ተብለናል :: 'ፅንስ ከሆነ ይገፋል ዐይነ -ምድር ከሆነ ይጎላል ' ነውና ውሎ ሲያድር ሃቁ ፍንትው ብሎ መውጣቱ አይቀርም :: እስከዚያው ግን መጠዬቅ ያለበት አንድ ጥያቄ አለ :-

በኢሣያስ ወፈፌው ላይ መፈንቅለ አገዛዝ ለማድረግ የተዳፈሩት ወታደሮች የዕድሜ ክልል ምን ያህል ነው ? ወጣቶች ናቸው ወይስ ከእርሱ ጋር አብረው ከናቅፋ የመጡት አውሬዎች ?

ለዚህ ጥያቄዬ አጥጋቢ መረጃዎች ሣገኝ በርዕሱ ሥር ተጨማሪ አስተያዬት ይኖረኛል ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Jan 23, 2013 9:35 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ነገደ -አርበኛ ዘዋርካ :-

ትላንት በአሜሪካን ድምፅ ሬድዮ የአማርኛው መርኃግብር ስለ ሠሞኑ የአሥመራው ድራማ ሠፋ ያለ ዘገባ ቀርቦ ነበር ::
ምንጭ :- Voice of America, Tue Jan 22, 2013. VOA discussion on military mutiny in Eritrea.

ዋናውን ቃለ -መጠይቅ ያደረጉት ጋዜጠኞች (ፒተር ኃይንላይን እና ሊኦናርድ ቪንሠንት ) የተወያዩት በእንግሊዘኛ ቋንቋ ነበር :: በእንግሊዘኛ ቋንቋ ከተወያዩት መካከል ቅንጫቢው የሚከተለውን ይመስላል ::
ምንጭ :- Peter Heinlein, January 22, 2013.Eritrean Siege Stalemate Sheds Light on an Opaque Society.

Quote:
A day-long siege at Eritrea's information ministry Monday ended in a stalemate, with disgruntled soldiers retreating to a strategic location outside the capital, Asmara. That the incident provides rare insight into the inner workings of one of the world's most opaque societies.

International observers are wondering what happened Monday after a group of soldiers drove to Eritrea's information ministry and demanded that a statement be read out over state-run television. The statement asking for the release of political prisoners and for respect of the constitution was being read when the station suddenly went off the air.

Nearly 12 hours later, the station resumed broadcasting with no mention of the cause of the disruption. The troops that had occupied the ministry simply climbed back into their armored personnel carriers and drove off.

Information gathered from a variety of sources indicates the operation was led by Colonel Saleh Osman, a legendary figure of the Eritrea-Ethiopia war from 1998 to 2000. A usually authoritative opposition website reports that Colonel Osman and several dozen supporters retreated to the suburbs of Asmara, where they are in talks with President Isaias Afewerki's government.

Information is tightly controlled in Eritrea. The watchdog group Reporters Without Borders ranks the Red Sea nation last out of 179 countries in press freedom, below North Korea.

Former Reporters Without Borders Africa director Leonard Vincent is the author of a book titled The Eritreans, and a close follower of the country. In a telephone interview, Vincent said Monday's siege appears to have been a show of force, and not an attempt to seize power.

"Yesterday's operation was not aimed at overthrowing by violence the government, but still it's a standoff with the government," said Vincent. "It's an operation aimed at showing defiance toward them. So this shows the level of frustration in the army is very high."

Vincent says the standoff at the information ministry suggests Colonel Osman has broad support within the military.

"If this was an isolated operation led by a rebel colonel, this kind of move should have been met by violence and severe repression," he said. "This hasn't happened, so there might be negotiations going on, and this unit might not be so isolated as we thought yesterday."

Vincent believes it is too early to tell whether the operation was successful.

"We cannot say if it has succeeded or failed," said Vincent. "What we can say is a faction of the army is showing its strength and is talking with the government on the basis of what they are capable of doing in terms of taking control of parts of the country."

Vincent says the dissidents' demand of freedom for political prisoners, particularly those jailed in a 2001 purge, has deep resonance among ordinary Eritreans.

"It's the sine qua non [essential] condition for change in Eritrea," he said. "The situation of political prisoners is awful. Reformists and journalists who were jailed in 2001 have vanished. According to sketchy reports, they are detained in high security prison in the far northeast of the country, and the majority have died from disease or by suicide. This is a method the government uses against any dissent or criticism."

Human rights groups have long criticized Eritrea's record of jailing government critics. The United Nations last year estimated there are as many as 10,000 political prisoners in a country of six million people.

ለመሆኑ የወታደሮቹ አዛዥ ኮሎኔል ኦስማን ሣሌህ ማን ነው ? ከሻቢያ መስራቾች አንዱ የሆነው የኦስማን ሣላህ ሣቤ ልጅ ወይም ዘመድ ይሆን ?

ሌላው ጉዳይ የወታደሮቹ የዕድሜ ክልል ነው :: እኒህ 'አመፁ ' የሚባሉት ወታደሮች ወጣቶች ናቸው :: ስለዚህ በብሔራዊ አገልግሎት የተማረረው የማኅበረሰብ አካል ናቸው ማለት ነው :: ስለዚህ ....

ብዙ ጊዜ የተሣኩ ወታደራዊ መፈንቅለ -አገዛዞች የሚከናወኑት በአዛዥነት ደረጃ ካሉት በጣም ጥቂቶቹ ብቻ በሚያውቁት ሤራ የበታች መኮንኖችን እና ተራ ወታደሮችን በመጠቀም ነው :: ስለዚህ ሠሞኑን በኤርትራ ተከሠተ የተባለው ሙከራ የዚህ 'ዘመን የማይሽረው ዕውነታ ' የሚያንፀባርቅ ሆኖ እናገኘዋለን ::

ስለሆነም በአሁኑ ሙከራ ባይሣካም ሌላ ሙከራ የሚያደርግ የጦር መሪ ዳግም ግልበጣ እንዳይሞክር የሚያግደው ኃይል እንደሌለ በእኒህ 100 በማይልቅ ቁጥር ባላቸው ወታደሮች እርምጃ ታይቷል ::

'ሃፊንግተን ፖስት ' የኢንተርኔት ቴሌቪዥን የሚከተለው ዘገባ አለው :: እነ ሔርማን ኮኼን እና ሌሎችም የተሣተፉበት ጥሩ : ጥሩ የሆኑ አስተያዬቶች ስላሉት ተከታተሉት ::
ምንጭ :- HuffPost Live, Wed Jan 23, 2013. Unrest In Eritrea.

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Jan 25, 2013 4:49 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ነገደ -አርበኛ ዘዋርካ :-

ከለገሠ [መለስ ] መሞት አስቀድሞ ድምፁ የጠፋው ወፈፌው ኢሣያስ ዘንድሮ ጉድ ፈልቶበታል ::

ምንጭ :- EthVid, Thu Jan 24, 2013. Protesters occupy Eritrean embassy in London - Jan. 24, 2013.

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon Jan 28, 2013 1:10 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ሀለቃ :-

እስኪ የሚከተለውን ዜና ወደ አማርኛ ተርጉምልን ::
ምንጭ :- Aseye Asena, Saturday January 26, 2013. 21 ጥሪ ዝተኻየደ ናይ ሓይልታት ምክልኻል ምንቅስቓስ ንለውጢ ዝተቐትለ ኮለኔል ስባህትለኣብ ጽገ ( ወዲ ጽገ ) ተቐቢሩ።

'እኔ እንደገባኝ ከሆነ ኮሎኔል ሰብሐትለአብ ጽገ የተባለ የአንድ ብርጌድ አዛዥ በጥር 13 ቀን 2005 .. ፎርቶ አካባቢ በነበረው ግጭት ቆስሎ ሞቷል : ቀብሩም በደቀመሐረ ተፈፅሟል ::' የሚል መሠለኝ :: ይህ ኮሎኔል በእርግጥ ሞቷል ? ከሞተስ ለሕይወቱ መጥፋት ምክንያት የነበረው ፎርቶ አካባቢ የነበረው ግጭት ነበር ?

እንዲያው በእኛ በኢትዮጵያውያን ጉዳይ ጣልቃ እየገባችሁ አስተያዬት እንደምትሠጡት ሁሉ የሠሞኑን የአገራችሁን ድራማ ለምንከታተል ጎረቤቶቻችሁ የምታውቁትን ዕውነት አካፍሉን ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Jan 30, 2013 11:21 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ነገደ -አርበኛ ዘዋርካ :-

በሐሰት የተመሠረተ ታሪክ በድቡሽት ላይ እንደተገነባ ቤት ነው :: ጀብሃ : ሻቢያ እና መሠሎቻችው "ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ስለሆነች ከኢትዮጵያ አገዛዝ ነፃ መውጣት አለባት ::" ብለው 30 ዓመታት ላላነሠ ጊዜ የደም መፋሰስ እንዲሠፍን ያደረጉ ነበሩ :: ሆኖም ጊዜው ሲደርስ ሁሉ በሐሰት የገነቡት ሥርዓት እንደ እንቧይ ካብ ሊናድ ሣምንታት : ቢበዛ ወራት የቀሩት ይመስላል :: በየቀኑ ከኤርትራ እስከ ውጪ አገር ስለዚያች አገር ገዢዎች የሚሠማው ወሬ ሁሉ ይህንን አመልካች ነው ::

ምንጭ :- Ethiopian Review, Wed Jan 30, 2013. Protesters occupy Eritrean embassy in Rome, Italy.

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Jan 30, 2013 11:35 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ሀለቃ :-

ከዚህ በኋላ የውስጥ ፍርሃትህን አስወግደህ ዕውነቱን እንደምታጋራን እና የሚከተለውንም ዜና ከምንጩ ጋር አመሣክረህ እንደምታቀርብልን ተስፋ አደርጋለሁ :: እስከዚያው ድረስ 'Ethiopian Review' የቀረበው ትርጉም እነሆ :-

ምንጭ :- Ethiopian Review, Wed Jan 30, 2013. Eritrean Information Minister Ali Abdu gives interview; confirms his defection.

Quote:
Posted by Adam » Wed Jan 30, 2013 7:42 am
Translated from Swedish newspaper Expressen

BEIRUT (Jan. 30, 2013) -- Eritrean dictator Isaias Afewerki's Information Minister Ali Abdu Ahmed has fled the country and is living today in a secret location.

He confirm his defection himself today in an exclusive interview with Expressen's reporter Kassem Hamade.

Ali Abdu says he is surprised that the Swedish authorities did not seek him for information about what happened to the imprisoned journalist Dawit Isaak. But he dare not give any hope to Isaaks family in Sweden.

Eritreas information minister, Ali Abdu, 47, disappeared without a trace during a business trip to Germany in November.

Since then, not a sign of life heard from the Minister, who has been one of dictator Isaias Afewerki's closest men for many years.

He dares not speak on the phone with journalists, so he responds to Expressen questions via his brother Saleh Younis, who lives in the U.S..

Ali Abdu says that he very well knows who Dawit Isaak is.

"No one from the Swedish government or authorities have been trying to contact me about Dawit Isaak, Ali Abdu told Expressen."

For Dawit Isaaks family in Sweden and among the thousands who are working for his release, Ali Abdu defection brought hope that they will finally get an answer if Dawit Isaak still alive.

But Ali Abdu says he and the other ministers do not know anything about what happened Dawit and other imprisoned journalists and politicians.

"Neither I nor any other minister dared to ask what happened to Dawit Isaak. It is taboo to ask about things that are not related to ones job. There is an old guerrilla culture in the country. You carry out orders without asking why," he says.

Ali Abdu says it is routine for suspected dissidents to be arrested without court papers, without any documentation.

"It is done by oral orders. Sometimes, it is over the phone and in coded language. They are afraid of being intercepted by Western intelligence services, he says.

Ali Abdu says he is sorry about what happened to Dawit Isaak and other journalists.

"But it is only the president himself and his closest security that has information about Isaak. Not even the police chief knows anything about it," he says.

Ali Abdu lives under great pressure. Immediately after his defection in November, his father, his 15 year old daughter and his brother were arrested by the Security Service. He says he does not know where they are kept today.

He does not want to answer questions about what prompted him to defect or how he lives today.

"My brother is in shock right now. He is sad and feeling disappointed at how an entire generation in Eritrea has been lost," says the former minister's brother Saleh Younis.

አንድ አምባገነን መውደቂያው ጊዜ ሲቃረብ በቅርቡ ያሉት ታማኞቹ ከሁሉም ቀድመው ይከዱታል :: አሊ አብዱ ለኢሣያስ አፈወርቂ እጅግ ቅርብ እና ታማኝ ከሚባሉት ባለሟሎች አንዱ ነው :: እርሱ ኢሣያስን ጥሎ ለመሄድ ከወሠነ ማን ከኢሣያስ ጋር አብሮ ይቆያል ?

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ደብረብርሀን 33

ኮትኳች

Joined: 17 Aug 2011
Posts: 262

PostPosted: Thu Jan 31, 2013 2:27 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም አቶ ተድላ ,

እንዴ ትግሬኛው ስትረጉም ጎበዝ ነህ እባክህ Laughing Laughingቅቅቅቅ ልክ ነው ቁልፍ ቃሉ "" ምቕታል "" ነው .... እንደዚህ ትግሬኛ የምትችል አይመሰኝም ነበር :: እነሱ ከሚተረጉሙልን የአንተን የበለጠ እናምናለን :: ፎርቶ አካባቢ የሞተው ብዙ ነው ይባላል ... ዘንድሮ ኢሳያስ እራሱ ፎርቶ ሳይቀበር ይቀራል ብለህ ነው Question ውቃቤየ ነግሮኛል ግድየለህም .... የኢትዮጵያ አምላክ ገና ብዙ ያሳየናል Exclamation Exclamation

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ሀለቃ :-

እስኪ የሚከተለውን ዜና ወደ አማርኛ ተርጉምልን ::
ምንጭ :- Aseye Asena, Saturday January 26, 2013. 21 ጥሪ ዝተኻየደ ናይ ሓይልታት ምክልኻል ምንቅስቓስ ንለውጢ ዝተቐትለ ኮለኔል ስባህትለኣብ ጽገ ( ወዲ ጽገ ) ተቐቢሩ።

'እኔ እንደገባኝ ከሆነ ኮሎኔል ሰብሐትለአብ ጽገ የተባለ የአንድ ብርጌድ አዛዥ በጥር 13 ቀን 2005 .. ፎርቶ አካባቢ በነበረው ግጭት ቆስሎ ሞቷል : ቀብሩም በደቀመሐረ ተፈፅሟል ::' የሚል መሠለኝ :: ይህ ኮሎኔል በእርግጥ ሞቷል ? ከሞተስ ለሕይወቱ መጥፋት ምክንያት የነበረው ፎርቶ አካባቢ የነበረው ግጭት ነበር ?

እንዲያው በእኛ በኢትዮጵያውያን ጉዳይ ጣልቃ እየገባችሁ አስተያዬት እንደምትሠጡት ሁሉ የሠሞኑን የአገራችሁን ድራማ ለምንከታተል ጎረቤቶቻችሁ የምታውቁትን ዕውነት አካፍሉን ::

ተድላ

_________________
Only two defining forces have ever offered to die for you : Jesus Christ and the American Army . One died for your soul the other died for your freedom ! May God bless the USA !!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Dec 18, 2013 2:06 am    Post subject: Reply with quote

ስለ ደቡብ ሱዳን የወደፊት ዕጣ ፋንታ ምን ብዬ ነበር ?

ተድላ

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

የደቡብ ሱዳን ውሣኔ ሕዝብ ዛሬ እሁድ ጥር 8 ቀን 2003 .. በተጀመረ በሣምንቱ ተጠናቋል :: እስካሁን ድምፅ መስጠት ካለብት ሕዝብ በደቡብ ሱዳን ከሚኖሩት 80% በላይ : በሰሜን ሱዳን ነዋሪ ከሆኑት 53% እንዲሁም በውጭ አገሮች ነዋሪ ከሆኑት 91% ያህሉ ድምፃቸውን ሠጥተዋል :: በአመዛኙ የውሣኔ ሕዝቡ አዝማሚያ ነፃነትን የሚደግፍ እንደሆነ የዜና ዘገባዎች ያመለክታሉ ::
ምንጭ :- APA-Dakar (Senegal), Released on: 2011-01-17 00:41:00 . Early results of south Sudan referendum show vote for split

ስለ ደቡብ ሱዳን የማቀርበውን ትንተና በዚህ በአራተኛው ክፍል አጠናቅቃለሁ :: ነገር ግን ወደፊት አስፈላጊ ሁኔታዎች ሲኖሩ እንደገና ጉዳዩን ማንሣቴ አይቀርም ::

4 ..... የወደፊቱ የደቡብ ሱዳን ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል ?
የደቡብ ሱዳንን የወደፊት ዕጣ ለመገመት በቅድሚያ የደቡብ ሱዳንን ፖለቲካ በጥልቀት ማወቅ ይጠይቃል :: ይህ ደግሞ በደቡብ ሱዳን ላይ ለረዥም ጊዜ ጥናት ማድረግን እና በአካባቢው በመኖር ከሕይወት ልምድ መቅሰምን የሚጠይቅ ነው :: ስለዚህ በእኔ በኩል የሚቀርበው ትንታኔ በወሬ -ጠገብ መረጃ ላይ የተመሠረተ እና አጠቃላይ ሁኔታዎችን የሚያለመክት ውሱን የሆነ ነፀብራቅ ነው ::

በደቡብ ሱዳን ለረዥም ጊዜ ለዘለቀው እና ለወደፊቱም ሊያገረሽ የሚችለው የፖለቲካ ችግር መንስዔዎቹን ከውስጥ እና ከውጭ ብለን ልንከፋፍላቸው እንችላለን ::

...... ውስጣዊ ሁኔታ
ቀደም ባሉት ክፍሎች ለመጥቀስ እንደሞከርኩት የደቡብ ሱዳን ግዛት በሱዳን ግዛት ሥር ሙሉ በሙሉ ተጠቃሎ መገዛት የጀመረው እንግሊዞች በግብፆች እና የሰሜን ሱዳን ልውጥ አረቦች ድጋፍ 1890 .. (... 1898) ሙሉ በሙሉ ከተቆጣጠሩት በኋላ ነበር :: ቀደም ብሎ ግን ቱርኮች በግብፆች እና የሰሜን ሱዳን ልውጥ አረቦች ድጋፍ 1813 .. (... 1821) በደቡብ ሱዳን ላይ ወረራ አካሂደው ለተወሰነ ጊዜ የደቡብ ሱዳን ከፊል አውራጃዎች መቆጣጠር ችለው ነበር :: ከቱርኮችም ሆነ ከእንግሊዞች ወረራዎች በፊት ግን የደቡብ ሱዳን ጎሣዎች በየራሣቸው የአካባቢ ጎሣ መሪዎች የሚገዙ ሆነው በመካከላቸው ለተጨማሪ የግጦች መሬት እና የባሪያ ፍንገላ ሽኩቻ ነበራቸው ::
ምንጭ :- Dr. Riek Machar Teny-Dhurgon, Chairman and Commander-in-Chief, SSIM/A. 19 Nov 95. South Sudan: A History of Political Domination - A Case of Self-Determination

በደቡብ ሱዳን ውስጥ በዛ ያሉ ጎሣዎች አሉ :: ከእነዚህ መካከል ዋና ዋና የሚባሉት 24 ጎሣዎች :- ዲንቃ : ኑዌር : ባሪ : ሎቱኮ : ኩኩ : ዛንዴ : ሙንዳሪ : ካክዋ : ፖጁሉ : ሺሉክ : ሞሩ : አቾሊ : ማዲ : ሉሉቦ : ሎኮያ : ቶፖሣ : ላንጎ : ዲዲኛ : ሙርሌ : አኝዋ () : ማካራካ : ሙንዱ : ጁር እና ካሊኮ የሚጠቀሱ ናቸው :: እንዲህ በዛ ያሉ ጎሣዎች ያሉበት አገር በፖለቲካ እንቅስቃሴ በፖለቲካ ልሂቃን ፍላጎት ምክንያት ለጎሣ ፀብ እና ሽኩቻ የተጋለጠ ይሆናል :: እንዲህም ሆኖ የሰሜኖቹን ጨቋኝ እና ዘረኛ አገዛዝ በአንድ ላይ ሆነው ታግለው ለመጣል ስለበቁ ተዋጊዎቻቸው በትግላቸው ወቅት ያዳበሩት ጓዳዊ ስሜት ከጎሣ ፖለቲካ ጋር በተያያዘ በከፊልም ቢሆን ሊፈጠሩ የሚችሉ ውጥረቶችን ሊያረግበው ይችላል ::
ምንጭ :- Wikipedia. Southern Sudan

ደቡብ ሱዳን ከዓለም ሁኔታ ጋር ሲነፃፀር በኢኮኖሚ እና ማኅበራዊ ዕድገት እጅግ የተጎዳ አካባቢ ነው :: 5 ዓመት በፊት የደቡብ ሱዳን ነፃነት ግንባር ዋና ከተማውን ጁባን ሲቆጣጠር በአገሪቱ ውስጥ የነበረው የአስፋልት መንገድ ርዝመት 1.2 .. የነበረ ሲሆን ያም የሚገኘው በጁባ አውሮፕላን ማረፊያ የአውሮፕላኖች ማኮብኮቢያ ሆኖ የሚያገለግለው መሥመር ነበር :: ትምህርት ቤቶች : ሆስፒታሎች : ልዩ ልዩ የንግድ እና አገልግሎት መስጫ ተቋሞች ያለመኖር ብቻ ሣይሆን ድሮ በእንግሊዞች ቅኝ ግዛት ዘመን የነበሩትም በእርስ በእርሱ ጦርነት ወቅት ቀደም ብሎ ሰው የማይኖርበት እስኪመስል ድረስ በሰሜን ሱዳን ገዢዎች እንዲወድሙ ተደርገዋል ::

ደቡብ ሱዳን አሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ትኩረት ያገኘቸው በቅርብ በተገኘው የነዳጅ ሃብቷ ምክንያት ነው :: ይህ ሃብት በረከትም : እርግማንም ሊሆንባቸው ይችላል :- እንደአጠቃቀማቸው ይወሰናል :: በዚህም ሃብት ምክንያት በደቡብ ሱዳን ጎሣዎች መካከል ቅራኔ ሊፈጠር ይችላል ::

ስለዚህ ደቡብ ሱዳን ያላት የውስጣዊ ቅራኔዎች መንስዔዎች :- በፖለቲካ ልሂቃን መካከል በጎሣ ልዩነት ምክንያት ሊፈጠሩ የሚችሉ ሽኩቻዎች : ደካማ የኢኮኖሚ እና ማኅበራዊ ተቋሞች : አዲስ መንግሥት ሲመሠርቱ ከዜሮ ስለሚሆን ደካማ የመንግሥት አስተዳደር መዋቅር እንዲሁም ከነዳጅ ሃብት ክፍፍል አንፃር በውስጥ የጎሣዎች የይበልጥ ይገባኛል ሽኩቻዎች ይሆናሉ ::

ተድላ

_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወርቅነች

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Oct 2010
Posts: 968

PostPosted: Wed Dec 18, 2013 5:41 am    Post subject: Reply with quote

Quote:
ስለ ደቡብ ሱዳን የወደፊት ዕጣ ፋንታ ምን ብዬ ነበር

ፈዛዛው ...ደግሞ ምን ብለህ ነበር አንት ምቀኛ ፈልፈላ ቡዳ ...ደቡብ ሱዳኖችም ካንተ ገደቢሰነት አልተረፉም ...እነሱ እንዳንተ የሞቱት ጆን ቀረንቅን የገደሉ ለት ነው ...ደግሞ አታፍርም የሰው ልጅ ሲሞት ምን ብዮ ነበር ብለህ አፍህን ትከፍታለህ ...አንት ክፍት አፍ ትላለች ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና Laughing Laughing
ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ስለ ደቡብ ሱዳን የወደፊት ዕጣ ፋንታ ምን ብዬ ነበር ?

ተድላ

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

የደቡብ ሱዳን ውሣኔ ሕዝብ ዛሬ እሁድ ጥር 8 ቀን 2003 .. በተጀመረ በሣምንቱ ተጠናቋል :: እስካሁን ድምፅ መስጠት ካለብት ሕዝብ በደቡብ ሱዳን ከሚኖሩት 80% በላይ : በሰሜን ሱዳን ነዋሪ ከሆኑት 53% እንዲሁም በውጭ አገሮች ነዋሪ ከሆኑት 91% ያህሉ ድምፃቸውን ሠጥተዋል :: በአመዛኙ የውሣኔ ሕዝቡ አዝማሚያ ነፃነትን የሚደግፍ እንደሆነ የዜና ዘገባዎች ያመለክታሉ ::
ምንጭ :- APA-Dakar (Senegal), Released on: 2011-01-17 00:41:00 . Early results of south Sudan referendum show vote for split

ስለ ደቡብ ሱዳን የማቀርበውን ትንተና በዚህ በአራተኛው ክፍል አጠናቅቃለሁ :: ነገር ግን ወደፊት አስፈላጊ ሁኔታዎች ሲኖሩ እንደገና ጉዳዩን ማንሣቴ አይቀርም ::

4 ..... የወደፊቱ የደቡብ ሱዳን ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል ?
የደቡብ ሱዳንን የወደፊት ዕጣ ለመገመት በቅድሚያ የደቡብ ሱዳንን ፖለቲካ በጥልቀት ማወቅ ይጠይቃል :: ይህ ደግሞ በደቡብ ሱዳን ላይ ለረዥም ጊዜ ጥናት ማድረግን እና በአካባቢው በመኖር ከሕይወት ልምድ መቅሰምን የሚጠይቅ ነው :: ስለዚህ በእኔ በኩል የሚቀርበው ትንታኔ በወሬ -ጠገብ መረጃ ላይ የተመሠረተ እና አጠቃላይ ሁኔታዎችን የሚያለመክት ውሱን የሆነ ነፀብራቅ ነው ::

በደቡብ ሱዳን ለረዥም ጊዜ ለዘለቀው እና ለወደፊቱም ሊያገረሽ የሚችለው የፖለቲካ ችግር መንስዔዎቹን ከውስጥ እና ከውጭ ብለን ልንከፋፍላቸው እንችላለን ::

...... ውስጣዊ ሁኔታ
ቀደም ባሉት ክፍሎች ለመጥቀስ እንደሞከርኩት የደቡብ ሱዳን ግዛት በሱዳን ግዛት ሥር ሙሉ በሙሉ ተጠቃሎ መገዛት የጀመረው እንግሊዞች በግብፆች እና የሰሜን ሱዳን ልውጥ አረቦች ድጋፍ 1890 .. (... 1898) ሙሉ በሙሉ ከተቆጣጠሩት በኋላ ነበር :: ቀደም ብሎ ግን ቱርኮች በግብፆች እና የሰሜን ሱዳን ልውጥ አረቦች ድጋፍ 1813 .. (... 1821) በደቡብ ሱዳን ላይ ወረራ አካሂደው ለተወሰነ ጊዜ የደቡብ ሱዳን ከፊል አውራጃዎች መቆጣጠር ችለው ነበር :: ከቱርኮችም ሆነ ከእንግሊዞች ወረራዎች በፊት ግን የደቡብ ሱዳን ጎሣዎች በየራሣቸው የአካባቢ ጎሣ መሪዎች የሚገዙ ሆነው በመካከላቸው ለተጨማሪ የግጦች መሬት እና የባሪያ ፍንገላ ሽኩቻ ነበራቸው ::
ምንጭ :- Dr. Riek Machar Teny-Dhurgon, Chairman and Commander-in-Chief, SSIM/A. 19 Nov 95. South Sudan: A History of Political Domination - A Case of Self-Determination

በደቡብ ሱዳን ውስጥ በዛ ያሉ ጎሣዎች አሉ :: ከእነዚህ መካከል ዋና ዋና የሚባሉት 24 ጎሣዎች :- ዲንቃ : ኑዌር : ባሪ : ሎቱኮ : ኩኩ : ዛንዴ : ሙንዳሪ : ካክዋ : ፖጁሉ : ሺሉክ : ሞሩ : አቾሊ : ማዲ : ሉሉቦ : ሎኮያ : ቶፖሣ : ላንጎ : ዲዲኛ : ሙርሌ : አኝዋ () : ማካራካ : ሙንዱ : ጁር እና ካሊኮ የሚጠቀሱ ናቸው :: እንዲህ በዛ ያሉ ጎሣዎች ያሉበት አገር በፖለቲካ እንቅስቃሴ በፖለቲካ ልሂቃን ፍላጎት ምክንያት ለጎሣ ፀብ እና ሽኩቻ የተጋለጠ ይሆናል :: እንዲህም ሆኖ የሰሜኖቹን ጨቋኝ እና ዘረኛ አገዛዝ በአንድ ላይ ሆነው ታግለው ለመጣል ስለበቁ ተዋጊዎቻቸው በትግላቸው ወቅት ያዳበሩት ጓዳዊ ስሜት ከጎሣ ፖለቲካ ጋር በተያያዘ በከፊልም ቢሆን ሊፈጠሩ የሚችሉ ውጥረቶችን ሊያረግበው ይችላል ::
ምንጭ :- Wikipedia. Southern Sudan

ደቡብ ሱዳን ከዓለም ሁኔታ ጋር ሲነፃፀር በኢኮኖሚ እና ማኅበራዊ ዕድገት እጅግ የተጎዳ አካባቢ ነው :: 5 ዓመት በፊት የደቡብ ሱዳን ነፃነት ግንባር ዋና ከተማውን ጁባን ሲቆጣጠር በአገሪቱ ውስጥ የነበረው የአስፋልት መንገድ ርዝመት 1.2 .. የነበረ ሲሆን ያም የሚገኘው በጁባ አውሮፕላን ማረፊያ የአውሮፕላኖች ማኮብኮቢያ ሆኖ የሚያገለግለው መሥመር ነበር :: ትምህርት ቤቶች : ሆስፒታሎች : ልዩ ልዩ የንግድ እና አገልግሎት መስጫ ተቋሞች ያለመኖር ብቻ ሣይሆን ድሮ በእንግሊዞች ቅኝ ግዛት ዘመን የነበሩትም በእርስ በእርሱ ጦርነት ወቅት ቀደም ብሎ ሰው የማይኖርበት እስኪመስል ድረስ በሰሜን ሱዳን ገዢዎች እንዲወድሙ ተደርገዋል ::

ደቡብ ሱዳን አሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ትኩረት ያገኘቸው በቅርብ በተገኘው የነዳጅ ሃብቷ ምክንያት ነው :: ይህ ሃብት በረከትም : እርግማንም ሊሆንባቸው ይችላል :- እንደአጠቃቀማቸው ይወሰናል :: በዚህም ሃብት ምክንያት በደቡብ ሱዳን ጎሣዎች መካከል ቅራኔ ሊፈጠር ይችላል ::

ስለዚህ ደቡብ ሱዳን ያላት የውስጣዊ ቅራኔዎች መንስዔዎች :- በፖለቲካ ልሂቃን መካከል በጎሣ ልዩነት ምክንያት ሊፈጠሩ የሚችሉ ሽኩቻዎች : ደካማ የኢኮኖሚ እና ማኅበራዊ ተቋሞች : አዲስ መንግሥት ሲመሠርቱ ከዜሮ ስለሚሆን ደካማ የመንግሥት አስተዳደር መዋቅር እንዲሁም ከነዳጅ ሃብት ክፍፍል አንፃር በውስጥ የጎሣዎች የይበልጥ ይገባኛል ሽኩቻዎች ይሆናሉ ::

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 11, 12, 13, 14  Next
Page 12 of 14

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia