WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ሡልጣን ውይይቱ ተጀምሯል !
Goto page Previous  1, 2, 3
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ሱልጣን

ኮትኳች

Joined: 03 Sep 2003
Posts: 465

PostPosted: Mon Jun 18, 2012 3:34 pm    Post subject: መርሀባ Reply with quote

ዘርዐይ ደረስ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም በድጋሚ ሱልጣን :- ወደ ውይይታችን እንኳን በደህና መጣህ እያልኩ ለዛሬ መንደርደርያ እንዲሆን አንዳንድ ነጥቦችን አነሳለሁ ::

Arrow ይህን ርእስ ከዓመት በኋላ ተመልሼ ሳየው ያቋረጥኩት እኔ መሆኔን ተረድቻለሁና በቅድሚያ ይቅርታ እጠይቃለሁ ::በተረፈ ለመልሱ አልዘገየህም እንዲያውም እንዲህ ትፈጥናለህ ብዬ አልጠበቅኩም ነበር ::

ምንም አይደለም ለትህትናህ አመሰግናለሁ ሁላችንም ቢዚ ስለሆንን በማንም መፍረድ አይቻልም ለማንኛውም እንኳን ደህና መጣህ

እኔም ዋርካን አልፎ አልፎ በቅርቡ እጎበኛታለሁ የምፈልጋቸውን ጉዳዮች እመለከታለሁ ::

Arrow
Quote:
እኔ በበኩሌ በተለይ ባለፉት ወራት paltalk እከታተል ስለነበር የሃይማኖት ውይይቶችንም በሰፊው ተከታትያለሁ ::ካንተ ጋር የተነጋገርንባቸውም ጉዳዮች በሰፊው ሲብራሩ ሰምቻለሁ ::ሆኖም ግን የተለያዩ ሰዎች ሲያስተምሩ አንዳንድ ጉዳዮች ላይ እንደማይስማሙ ለመረዳት ችያለሁ ::

በነገራችን ላይ ያኔ የጠየቅሁህን ጥያቄዎች ሁሉንም ላላስታውስ ስለምችል ደግሜ ላለመጠየቅ ስል 70ውንም ጥያቄዎች እንደገና ማየት ስላለብኝ እስከዚያው ድረስ እንዳላነሳኋቸው እርግጠኛ የምላቸውን ጥያቄዎች ለዛሬ አቀርባለሁ ::

መርሀባ

Quote:
71)paltalk ውስጥ የሚያስተምሩ ሙስሊም ሴቶች አጋጥመውኛል ::ባንተ አመለካከትይህ አካሄድ ትክክል ነው ወይ ?

የሚያስተምሩት ሴቶች ሩም ውስጥ ወይስ ወንዶች ?ከሴቶች ሩም ከሆነ ምንም ችግር የለም ::ከወንዶች ሩም ከሆነ ደግሞ
ወንዶች ማስተማር እስካልቻሉ ድረስ ሴቶች ቢያስተምሩ ችግር የለውም ::ነገር ግን ብዙ ጊዜ እርስ እርሳቸው ለመማማር ካልሆነ በስተቀር ለወንዶች በቂ አስተማሪ ስላለ አስፈላጊነቱ አይታየኝም :: ያልገባቸውን ጥያቄ ግን በማይክ በድምጽ ለወንዶች ቢጠይቁ ችግር የለም :Sadየግሌን አስተያየት ነው የጠየቅከኝ )

Quote:
72)ኡስታዝ የሚባሉት አስተማሪዎች ለዚህ 'ሥልጣን ' ያበቃቸው መመዘኛ ምንድነው ?

እኛ ኡስታዝ የምንላቸው በተለምዶ በማስተማር ስራ የተሰማሩትን ነው ::ነገር ግን ትክክለኛ ትርጉሙ ፕሮፌሰር ማለት ነው ::እና ኡስታዝ ብሎ መጥራት ተለምዶን እንጅ ማእረግን አይጠቁምም የሚጥጠሩትም ሰዎች ባለስልጣንነት አይሰማቸውም ወንድማዊነትን እና ይበልጥ ቅርብነትን ለመግለጽም እንጠቀምበታለን (በኢትዮጵያ ሁኔታ )ማለት ነው ::

Quote:
73) መጅሊስ የሚባለው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች አመራር አካል የተቋቋመው በደርግ ዘመን ነው ሲባል ሰምቼአለሁ ::ይህ አባባል ትክክል ከሆነ ከዚያ በፊት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንዴት ነበር የሚተዳደሩት ?

መጅሊስ ሙስሊሙን እያስተዳደረ ነው ሊባል አይችልም ::ከደርግ በፊትም ሆነ በኍላ ሙስሊሙ ራሱን ነው የሚያስተዳድረው ::የሀጅ ጸሎት ስነ ስርአት በመጅሊስ በኩል ማለፍ አለበት ስለተባለ እንጅ የመጅሊስን ስም ስንጠራ የምትሰማው ሙስሊሙ ከመጅሊሱ የሚፈልገው ነገር የለም :: ምክንያቱም ለሙስሊሙ በሚጠቅም መልኩ ስላልተዋቀረ ሙስሊሙ በተቋሙ ላይ ሳይሆን በተቋሙ ውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ አመኔታ ስለሌለው ከነሱ ምንም አይነት ጉዳይ አልነበረውም ::ስለዚህ መኖር እና አለመኖሩ አንድ ነው ::ከተመሰረተ ጊዜ እስከ አሁን ይህ ነው የሚባል ስራ ወይም ልማት ለሀገርም ይሁን ለሙስሊሙ መስራቱ አይታወቅም ሹመኞች ግን የግል ኪሳቸውን አሙቀውበታል :ያም በትንሳኤ ቀን ቅጣቱ ይጠብቃቸዋል ::ሙስሊሙን የሚወክሉ ሰዎች በሰላማዊ እና በትክክለኛ ምርጫ እስካልተቀመጡ ድረስ ሁሉም ነገር ትርጉም የለሽ ነው የሚሆነው !እስከ አሁን ግን ከሀይማኖት ድርጅትነቱ ይበልጥ ተጠሪነቱ ለመንግስት የሆነ አንድ የፖለቲካ ድርጅት መሳይ ነገር ሆኖ ይስተዋላል ሹመኞችም የመስጅድ ሸሆች ሳይሆኑ ካድሬዎች ማለቱ ለአገላለጽ ይመቻል ምክንያቱም ሀይማኖታዊ እውቀታቸው እዚህ ግባ የሚባል አይደለም እና !ይህን ሀሳቤን አብዛኛው ሙስሊም ይጋራኛል ብየ አምናለሁ (ሆኖም ግን ይህ የግሌ ምልከታ ነው ትክክል ላይሆንም ይችላል )

Quote:
74)ከወራት በፊት የተጀመረው የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እንቅስቃሴ ሁሉንም ሙስሊም ያካትታል ወይስ እነ መለስ እንደሚሉት ጥቂቶች የሚያካሂዱት ነው ?

በጣም አንገብጋቢ ጥያቄ ነው እንደ እኔ ብቻ ሳይሆን እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም እምነት ጥያቄው ሁሉንም ሙስሊም ያካትታል እነ አቶ መለስ እንደሚሉት አይደለም ::ከአንድ ሚሊዮን ህዝብ በላይ በአዲስ አበባ ብቻ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ እየተሰለፈ የጥቂቶች ጥያቄ ነው ማለት ደስ የማይል ቀልድ ነው ::በተለይ ከአንድ ጠቅላይ ሚኒስትር አይጠበቅም ::የልብ ጆሮ ተሰጥቶት ሊደመጥ የሚገባው ጥያቄ እየቀረበ ነው ::መጅሊስ አይወክለንም -አህባሽ እንደ እምነት መስፋፋት ይችላል ነገር ግን በመንግስት አስገዳጅነት መሆን የለበትም -ብቸኛው የሙስሊሞች ተቋም አወሊያ ለሙስሊሞች ይመለስ እንጅ መጅሊስ ሊያስተዳድረው አይገባም (በሙስና የተዘፈቀ በህዝብ ያልተመረጠ ተቃም ነውና ) የሚሉ መሰረታዊ የህዝብ ብሶት የወለዳቸው ጥያቄዎች ናቸው እንጅ የጥቂቶች ጥያቄ አይደሉም --40 ሚልዮን ክርስቲያን በሚኖርበት ሀገር ''ጥቂቶች የሸሪአ መንግስት የማቋቋም ፍላጎት ያላቸው '' ተብሎ መቅረቡ በራሱ በጣም ስህተት እና አሳዛኝ ተአማኝነት የጎደለው ከአንድ ታላቅ ባለስልጣን ይቅር እና ከቀበሌ ሊቀመንበር የማይጠበቅ ንግግር ነው ::
እናም የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መሰረታዊ ጥያቄ መሆኑን በጽኑ አምናለሁ Exclamation Exclamation Exclamation

Quote:
75)አል ሐባሾች ሙስሊሞች ናቸው ማለት ይቻላል ?

አዎ !ሙስሊሞች ናቸው ነገር ግን ከትክክለኛው እስልምና አስተምሮ ያፈነገጡ ስሜታቸውን የሚከተሉ ናቸው :: ውስጣቸውን በደንብ ለሚፈትሸው በጣም የሚገርም አይዲዮሎጅ አላቸው ከነዚህ ውስጥ ከክርስትና ሀይማኖት ተከታይ መስረቅ እና ቁማር መሻወት ይበቃል ይላሉ (ኢስላም ግን ስርቆትን ወይም ቁማርን ከማንም ጋር እርም አድርጓል )::

Quote:
76)ራሱን ዋሃቢያ እያለ የሚጠራ ድርጅት በዓለም ላይም ሆነ በአገራችን አለ ?ካለስ የዋሃቢያና የሰለፊያ ልዩነት ምንድነው ?

Arrow እጅግ በጣም ምርጥ ጥያቄ ነው Idea

እራሱን ወሀብያ ብሎ የሚጠራ ድርጅት ወይም ግለሰብ እስከ አሁን አላጋጠመኝም ::ሰዎች ግን ይህን ስያሜ ለተለያየ ነገር ይጠቀሙበታል ::የስያሜው አመጣጥ ሳኡዲ አረቢያ ይኖር ከነበረ እና አንድ አምላክን ብቻ ማምለክ የማይፈልጉ ጠንቋዮች እና ፎግረህ ብላዎች በበዙበት ዘመን ሙሀመድ አብዱል ወሀብ በመባል የሚታወቅ ሰው ተወለደ ::ይህን ከፈጣሪ ጋር ሌላን ማምለክ እና የሟርት እና የጥንቆላ ስራ ስለተቃወመ ከሱ ጎን የቆሙ ሙስሊሞች ሁሉ ወሀብይ ተባሉ እሱ አባት አብዱል ወሀብ ስለሆነ (በነገራችን ላይ ወሀብ የአላህ ስም ነው አብዱል ወሀብ ማለት የወሀብ አገልጋይ ወይም ባሪያ ማለት ነው ::
ከዚያ ጀምሮ የሸሁን መሰረታዊ ሀሳብ የሚጋሩ ሰዎችን ወሀብይ ብሎ መጥራት እንደተጀመረ አንብቤያለሁ ::እኔ ወሀብይ ነኝ ብሎ እራሱን የሰየመ ድርጅት ወይም የጠራ ግለሰብ አላየሁም ::
ሰለፊ ማለት የነብዩ ሙሀመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ፈለግ ተከታይ (በነሱ መንገድ የተተኩ ማለት ነው ) ስለዚህ ሰለፍ በቋንቋ ደረጃ ምትክ እንደማለት ነው (እንደኔ አረዳድ ) በመሰረቱ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሁላችንም ሱኒ ሙስሊሞች ነን ስለዚህ ሰለፊ ብንባልም ነብያቸውን የሚከተሉ ከሚለው አባባል ውጭ ምንም አይነት ትርጉም የለውም !!አንዳንድ ጸጉር ሰንጣቂዎች ግን የተለያየ ቦታ ላይ እንደፈለጉት ቃላቱን ያሽሞነሙኑታል ::እኔ ግን ሰለፊ ነኝ ከምል ሙስሊም ነኝ ማለቱን እመርጣለሁ (አላህ ያወጣልን ስም ሙስሊም ስለሆነ )ለዚያም ነው (ሁዎ ሰማኩሙል ሙስሊሚነ )የሚለው ቁርአን ::አላህ ሙስሊም ብሎ ሰይሟችኍል እንደማለት ነው (አላህ የበለጠ ትርጉሙን ያውቀዋል )

በተረፈ ለሰለፊ ፓርላማ ውስጥ የተሰጠው ትርጓሜ አራምባ እና ቆቦ ነው ::::አንዳንድ ታላላቅ ባለስልጣኖች ወሀብይ የሚባል አነጋገር ስህተት ነው ይላሉ ::ጀሌዎቻቸው ደግሞ በየአደባባዩ ወሀብይ የሚባለውን ነገር ከምላሳቸው አልጠፋ ብሏቸዋል ::
እናም የሰለፊ እና የወሀብይ ትርጓሜ እንዳስቀመጥኩልህ ሲሆን ከዚህ ውጭ ከሙስሊሞች በበለጠ ትርጉሙን እናውቀዋለን ብለው ምናባዊ ጭራቅ አድርገው በመሳል የኢትዮጵያን ህዝብ ለማስፈራራት የሚጠቀሙበት ሰዎችም አይጠፉም ::አክራሪ ከሚለው ወደ አሸባሪ አሸጋግረው ከሁለት አንዱን ስም የሚጠቀሙበትም አይጠፉም ::
እንደ ኢትዮጵያዊነቴ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ የከረረም የተሸበረም ነገር የለም አይኖርም ::ለፖለቲካ ጥቅም አንዱን በአንዱ ላይ ለማነሳሳት ታቅዶ በሙስሊሞች የተሳበቡ ነገሮች ሁሉ ይዋል ይደር እንጅ ከጀርባቸው ማን እንዳለ ይታወቃል ::ስለዚህ የኢትዮጵያ ሙስሊም በጣም ሰላም ያለው ሙስሊም ነው :Sadበኔ አመለካከት )

Quote:
77)የነቢያችሁ ሙሐመድ አሟሟት በሕመም ነው ወይስ የሰው እጅ አለበት ?

አባቴ እና እናቴ እኔ እና ቤተሰቦቼ በሳቸው ምትክ እንሰዋላቸው እና ነብዩ ሙሀመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም በህመም ምክንያት እንደሞቱ በታሪክ አንብቤያለሁ ይሁን እንጅ በአንድ ወቅት ግብዣ በተጠሩበት ሁኔታ አይሁዶች በስጋ ውስጥ መርዝ በማድረግ ሲሰጧቸው አንዴ ስጋውን በጥርሳቸው እንደያዙት (ተመርዣለሁ እና አትብላኝ ) ብሎ ስጋው ነገራቸው ::ያን ስጋ አልበሉትም ነገር ግን መርዙ በተወሰነ መልኩ አግኝቷቸው ስለነበር ለመጨረሻ ጊዜ ለመሞታቸው የራሱን አስተዋጽኦ አድርጓል ይባላል (እርግጠኛ ለመሆን መጽሀፍትን ማንገላበጥ እሻለሁ )

Quote:
7Coolሙስሊሞች ከበሉ በኋላ ጣቶቻቸውን የሚልሱበት ምክንያት ሃይማኖታዊ መሠረት አለው ?

አዎ !ሱና ነው (የነብያችን ትእዛዝ ነው )የምግቡ በረከት እዚያ ይኖራል ተብሎም ይታመናል :በመሰረቱ ሙስሊም ማለት ፍጹም ታዛዥ ማለት ነው ::ሰው እጆቹን ካጸዳ በኍላ ነው ወደ ማእድ የሚቀርበው ::በአንዳንዶች እይታ አስነዋሪ ቢመስልም ሙስሊሞች ግን የነብያችን ትእዛዝ እና ስራ ስለነበር እንኮራበታለን ::በረከት አለው ብለንም እናምናለን !በዚህ አጋጣሚ በቀኝ እጃችን ብቻ እንድንበላም ነብያችን አስተምሮናል ::ስለዚህ ሙስሊሞች ሲበሉም ሆነ ሲጠጡ በቀኝ እጃቸው ነው ::ከንጽህና አንጻርም ስታየው ሎጅኩ ትክክል ሆኖ ታገኘዋለህ ::

~~~~~~~
Quote:
79)ክርስቲያን ዓረቦች አላህን እንደ አምላክ ሥም መጠቀማቸው በሙስሊሙ ላይ ቅሬታ አሳድሯል ?

እንደዚህ አስቤ አላውቅም ::የግብጽ ክርስቲያኖች እና የሊባኖስ ክርስቲያን አረቦች ሲቀድሱ አላህ ነው የሚሉት : አላሁ አክበርም ይላሉ ::ቋንቋ ስለሆነ ለምን አሉ ብሎ ቅር የሚሰኝ ወገን አላጋጠመኝም ::

Quote:
80)ከመካና ከመዲና በክብር ማን ይበልጣል ?ወይስ በሙስሊሙ እኩል ነው የሚታዩት ?

የጠቀስካቸው ሁለት የተለያዩ ከተሞች ናቸው :;እኔም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ መካ መዲና ሲባል አንድ ከተማ ይመስሉኝ ነበር ነገር ግን መካ ከጅዳ 75 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ የተቀደሰው እና ነብዩሏህ ኢብራሂም እና ልጃቸው የተገነባ (የአብርሀምም ግንብ )የሚባለው የአላህ ቤት ያለበት ከተማ ነው ::
መዲና ከጅዳ 400 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ያለች ከተማ ስትሆን የነብዩ ሙሀመድ መስጅድ ያለበት ከተማ ነው መቃብራቸውም መዲና ውስጥ ነው ያለው ::
አሁን በከተማ ደረጃ ሳይሆን በውስጣቸው ያዙት ቅዱስ ስፍራ አንጻር ሲሆን የምነግርህ በመካ ካእባ ተብሎ በሚጠራው ቤት ውስጥ መስገድ ሌላ ቦታ ከመስገድ 1መቶሽ ጊዜ ይበልጣል በመዲና በነብዩ መስጂድ ውስጥ መስገድ ደግሞ ሌላ ቦታ ከመስገድ 1 ጊዜ በደረጃ ይበልጣል :;ይህ በሁለቱ ከተሞች ውስጥ ስላሉት መስጅዶች ውስጥ ስለሚደረግ ሰላት ደረጃ መበላለጥ ነው በእየሩሳሌም መስጂደል ቁድስ ውስጥ መስገድ ሌላ ቦታ ካለ መስጅድ 5መቶ ደረጃ ይበልጣል ::
ወደ ማጠቃለያው ስመጣ ይህን ያክል ካልኩህ በአንተ በኩል ካልተመለሰልህ ጥያቄውን ይበልጥ ማብራራት እንድትችል ሂንት ሰጥቸሀለሁ ::በአላም ላይ ለኑሮ ምቹ እና በረከት ያለበት ሀገር ''እዚያ ኖሬ ብሞት '' ተብሎ የሚመኙበት ከተማ ግን መዲነቱል ሙነወራ (መዲና ነው )
በትንሳኤ ቀንም የመጨረሻ አማኞች የሚገኙ በዚህ ከተማ እንደሆነ ነብያዊ ሀዲስ ያረጋግጣል ::
ያልጠየቅከኝን መልሸ ከሆነ ይቅርታ !
ከምስጋና ጋር
_________________
HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1087
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Jun 18, 2012 11:20 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም በድጋሚ እያልኩ :-

ለጥያቄዎቼ በቂ ማብራርያ ሰጥተኸኛል አመሰግናለሁ ::ሆኖም ግን በኋላ የምመለስባቸው አንዳንድ ነጥቦች ይኖራሉ ::በተረፈ ከላይ እንዳልኩህ paltalk በምከታተልበት ወቅት ከተለያዩ ግለሰቦች የሚሰጠው ማብራርያ በጣም ብዙ ጥያቄዎች እንዳነሳ አድርጎኛል ::በወቅቱ ማስታወሻ ስላልያዝኩ አሁን ካንተ ጋር ውይይቱን ስጀምር ለማስታወስ እየተቸገርኩ ነው ::ለዛሬ የሚከተሉትን እያቀረብኩ በተመቸህ ጊዜ ልትመልስልኝ ትችላለህ ::አንተም ጥያቄዎች ካሉህ መጠየቁን አትርሳ ::ለማብራርያዎችህ እንደተለመደው አመሰግናለሁ ::

81)ነቢዩ ሙሀመድ ያደጉበትን እምነት (አምልኮ ) የሚከተሉ ሰዎች በእኛም ዘመን አሉ ?

82)በኢስላም እምነት መሠረት አላህ አካል አለው ?

83) በመፅሐፍ ቅዱስ የተጠቀሱት ነቢያት ሃይማኖታቸው ኢስላም እንደነበረ እንደምታምኑ ተረድቻለሁ ::የነሱ ተከታዮች የነበሩትስ ?

84)በኢስላም አዳም (አደም ) ከተፈጠረ ምን ያህል ጊዜ ሆኖታል ተብሎ ይታመናል ?

85)ሙስሊም ካልሆኑ ሰዎች (ሐዲስ እናውቃለን የሚሉ ) እንደሰማሁት ከሆነ ከነቢዩ ሙሐመድ ሞት በኋላ በአንዳንድ ነገሮች ላይ የሚለያዩ ቁርአኖች ስለነበሩ በወቅቱ የነበሩ ሊቃውንት ተስማምተው አንዱን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን አቃጥለዋቸዋል ::ይህ ነገር እውነትነት አለው ?

86)ነቢዩ በህይወት እያሉ ሴቶችና ወንዶች አንድ ላይ የሰገዱበት ጊዜ ነበር የሚባለውስ ?

87)ወደ ኢትዮጵያ ከተሰደዱት የነቢዩ ተከታዮች መካከል እስልምናን ትተው ክርስትያን የሆኑ ነበሩ ሲባልም ሰምቻለሁ ::የምታውቀው ነገር አለ ?ከነበሩስ ከዚህ በፊት እንዳልከኝ እስልምናን የለቀቀ ይገደላል የሚለው ሕግ ያኔ አይሰራም ነበር ?

8Coolከዚህ በፊት የግድ ካልሆነ ፎቶ መነሳት በኢስላም እንደማይፈቀድ ነግረኸኛል ::ከዚያ የባሰ ቴሌቪዥን ቪዲዮ ፊልም እንዴት አልተከለከለም ?

89) ቁርአንና ሀዲስ እንደማይጋጩ እንደነገርከኝ አስታውሳለሁ ::እንደሰማሁት ከሆነ ግን አስተማማኝ ያልሆኑ ሐዲሶች እንዳሉ ነው ::እኔ አንዳንድ ነገሮችን ማመሳከር ስለምፈልግ በመላው ዓለም በሚገኙ ሙስሊሞች ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው ሐዲሶች የትኞቹ እንደሆኑ ከቻልክ ብትነግረኝ ::

90)ለሙስሊም ሴቶች ሒጃብ ግዳጅ እንደሆነ ሁሉ ለወንዶችስ ኮፍያው የግድ መደረግ አለበት ?
_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ሱልጣን

ኮትኳች

Joined: 03 Sep 2003
Posts: 465

PostPosted: Tue Jun 19, 2012 7:26 am    Post subject: Reply with quote

ዘርዐይ ደረስ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም በድጋሚ እያልኩ :-

ለጥያቄዎቼ በቂ ማብራርያ ሰጥተኸኛል አመሰግናለሁ ::ሆኖም ግን በኋላ የምመለስባቸው አንዳንድ ነጥቦች ይኖራሉ ::በተረፈ ከላይ እንዳልኩህ paltalk በምከታተልበት ወቅት ከተለያዩ ግለሰቦች የሚሰጠው ማብራርያ በጣም ብዙ ጥያቄዎች እንዳነሳ አድርጎኛል ::በወቅቱ ማስታወሻ ስላልያዝኩ አሁን ካንተ ጋር ውይይቱን ስጀምር ለማስታወስ እየተቸገርኩ ነው ::ለዛሬ የሚከተሉትን እያቀረብኩ በተመቸህ ጊዜ ልትመልስልኝ ትችላለህ ::አንተም ጥያቄዎች ካሉህ መጠየቁን አትርሳ ::ለማብራርያዎችህ እንደተለመደው አመሰግናለሁ ::

መርሀባ ስለተመቸህ ተመችቶኛል ::

Quote:
81)ነቢዩ ሙሀመድ ያደጉበትን እምነት (አምልኮ ) የሚከተሉ ሰዎች በእኛም ዘመን አሉ ?

ነብዩ ሙሀመድ (..) ነብይ ሆነው ከመላካቸው በፊት
እንደሌሎች የአረብ ሰዎች ጣኦት አያመልኩም ነበር ::
በጣም ትህትና እና ጨዋ ታማኝ ከመሆናቸው ተጨማሪ የዚህ ታላቅ ዩኒቨርስ ባለቤት አንድ አምላክ እንጅ በመካ አካባቢ የነበሩ ሰዎች በየቀኑ የሚያመልኳቸው 360(ለአንድ አመት )ያክል ጣኦቶች አምላክ እንዳልነበሩ ስለሚያውቁ ብቻቸውን ሄራ ወደሚባለው ዋሻ እየሄዱ በራሳቸው ስታይል አንድን አምላክ ብቻ ያመልኩ ነበር ::በዚህ ጊዜ ነበር በተወለዱ 40 አመታቸው በዚሁ ዋሻ ኢቅራእ (አንብብ )የሚለው የቁርአን አንቀጽ በመልአኩ ጂብሪል አማካኝነት በወህይ የተገለጸላቸው ስለዚህ ነብይ ሆነው ከመላካቸው በፊትም አንድን አምላክ ብቻ ያመልኩ ነበር ::
በነገራችን ላይ ኢስላም ከአባታችን አደም ከነብዩሏህ ኖህ (ኑህ )ጀምሮ የነበረ እምነት እንጅ በነብዩ ሙሀመድ (..)የተጀመረ እምነት አይደለም እሳቸው የሰውን ልጅ አላህን ብቻ እንዲያመልክ የተላኩ የመጨረሻ ነብይ ናቸው ::

Quote:
82)በኢስላም እምነት መሠረት አላህ አካል አለው ?

አዎ !ነገር ግን ይህን ይመስላል ብለን በህሊናችን ልንመስለው አንችልም :: ጌታችን ያያል ይሰማል ::ይህ ሲባል እኔ እና አንተ እንደምናየው እና እንደምንሰማው አይደለም ::እኔ እና አንተ በክፍል ውስጥ ቁጭ ብለን ከግድግዳ ውጭ ያለውን ማየት እንችላለን ?አንችልም ::አላህ ደግሞ ከምንም አይነት መመሳሰል የጠራ ታላቅ ሀያል ጌታ ነው ለክብሩ እና ለልቅናው በሚገባ ሁኔታ ያያል ይሰማል እና በቁርአኑ በተገለጸው መሰረት እናምናለን ::ለአላህ እጅ አለው :;ምን አይነት አናውቅም :;አላህ ብቻ ነው የሚያውቀው ::የሰው ልጅ አእምሮ በፍጹም ይህን ይመስላል ብሎ በአእምሮውም ሆነ በልቡ ጭራሽ ማሰብ አይችልም (ወሊላሂል መሰሉል አእላ )

Quote:
83) በመፅሐፍ ቅዱስ የተጠቀሱት ነቢያት ሃይማኖታቸው ኢስላም እንደነበረ እንደምታምኑ ተረድቻለሁ ::የነሱ ተከታዮች የነበሩትስ ?

አዎ ብዙ ተከታይ የነበራቸው እና 950 አመታት ጥሪ አድርገው በጣት የሚቆጠሩ ብቻ አማኞች የነበሯቸው ነብያት ነበሩ ::የነብያት ሁሉ እምነት ኢስላም ነው :;ኢስላም የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ እምነት እንደሆነ እና የሰው ልጅ ከተወለደ በኍላ ቤተሰበቹ ወደ ሌላ እምነት እንደሚቀይሩት ኢስላም ያስረዳል ::ነብያት አይመለኩም ::ከራሳቸው ምንም ነገር ማድረግ አይችሉም ::የፈጣሪን መልእክት ብቻ ነው የሚያደርሱ :;ነብይ ለመሆናቸው ግን በአላህ ፈቃድ የተለያየ ተአምር ተሰጥቷቸዋል ::

Quote:
84)በኢስላም አዳም (አደም ) ከተፈጠረ ምን ያህል ጊዜ ሆኖታል ተብሎ ይታመናል ?

የዚህን መልስ አላውቀውም :;አንገብጋቢ ጥያቄ መስሎ ከታየህ አዋቂዎችን ጠይቄ እመለሳለሁ

[quote]85)ሙስሊም ካልሆኑ ሰዎች (ሐዲስ እናውቃለን የሚሉ ) እንደሰማሁት ከሆነ ከነቢዩ ሙሐመድ ሞት በኋላ በአንዳንድ ነገሮች ላይ የሚለያዩ ቁርአኖች ስለነበሩ በወቅቱ የነበሩ ሊቃውንት ተስማምተው አንዱን ብቻ
_________________
HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ሱልጣን

ኮትኳች

Joined: 03 Sep 2003
Posts: 465

PostPosted: Tue Jun 19, 2012 7:52 am    Post subject: Reply with quote

Quote:
85)ሙስሊም ካልሆኑ ሰዎች (ሐዲስ እናውቃለን የሚሉ ) እንደሰማሁት ከሆነ ከነቢዩ ሙሐመድ ሞት በኋላ በአንዳንድ ነገሮች ላይ የሚለያዩ ቁርአኖች ስለነበሩ በወቅቱ የነበሩ ሊቃውንት ተስማምተው አንዱን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን አቃጥለዋቸዋል ::ይህ ነገር እውነትነት አለው ?

በጣም ጊዜ ወስጀ የጻፍኩትን ዋርካ ስለበላብኝ ነው ከዚህ በታች ያለውን ደግሜ እየጻፍኩ ያለሁት
ወደ መልሱ ስመጣ ቁርአን 7 በላይ አነባብ ሂደት አለው በወቅቱ አረበኛ ተናጋሪ ያልሆኑ ወገኖች በአነባበቡ በመቸገራቸው ዉሎ ሲያድር ችግር ይፈጠራል በማለት ነው በአንድ አይነት አነባብ ይቀራ ዘንድ ሌሎች ቅጅዎች የተቃጠሉት ::እኔ የማውቀው ይህንን ነው ::

Quote:
86)ነቢዩ በህይወት እያሉ ሴቶችና ወንዶች አንድ ላይ የሰገዱበት ጊዜ ነበር የሚባለውስ ?

አንድ ላይ መስገድ ሲባል በአሰላለፍ ከወንዶች ሰልፍ ኍላ ከሆነ አሁንም ድረስ በቲቪ እንደምታየው መካ እየተሰገደ ነው ::ምንም ችግር የለም ::ዋናው አሰላለፉን ስር አት መጠበቅ ነው :;
በቤት ውስጥ ደግሞ ሚስት ከባሏ እና ከወንድሟ ኍላ ተከትላ መስገድ ትችላለች ::

Quote:
87)ወደ ኢትዮጵያ ከተሰደዱት የነቢዩ ተከታዮች መካከል እስልምናን ትተው ክርስትያን የሆኑ ነበሩ ሲባልም ሰምቻለሁ ::የምታውቀው ነገር አለ ?ከነበሩስ ከዚህ በፊት እንዳልከኝ እስልምናን የለቀቀ ይገደላል የሚለው ሕግ ያኔ አይሰራም ነበር ?

የሰማኸው ነገር ትክክል ነው :;ኡበይዱሏህ ኢብን ጀህሽ አሰዲ የሚባለው የኡም ሀቢባ ቢንት ሱፍያን ባለቤት ወደ ክህደት ተመልሷል :: የሞት ፍርድ ይፈረድበታል የተባለ በሸሪአ ህግ ሙሉ በሙሉ በሚተዳደሩ ሀገሮች የሰረቀ እጁ በሚቆረጥበት እና ለሌላው ህብረተሰብ እሱን በማየት ትምህርት በሚወስድበት የተመቻቸ አቶሞስፌር ውስጥ ነው እንጅ የትም ቅጣቱ ይፈጸምበታል ማለት አይደለም ::
በነገራችን ላይ በኢስላም ህግ መሰረት በሀይማኖት ማስገደድ የለም አንድ ሰው የግድ ሙስሊም ካልሆንክ ተብሎ አይገደድም ::ሙስሊም ከሆነ በኍላ ግን እስልምናን አልፈልግም ቢሎ ከሄደ ያኔ በሸሪአ ህግ በሚተዳደሩ ሀገሮች ውስጥ ከሆነ ወደ እስልምና እንዲመለስ ይጠየቃል
እምቢ ካለ ቅጣቱ ይፈጸምበታል ::ይህ የአላህ ህግ ነው ::ለምን እንደደነገገው እሱ ያውቃል ::አንድ ነገር ግን ላስቀምጥልህ ::ያንን ሰው የፈጠረው አላህ ብቻውን መሆኑን አትዘንጋ ስለዚህ በፍጡራን ላይ የፈለገውን ህግ ማውጣት መብቱ ነው ::ፍርዱም ሚዛናዊ ነው ::የሰርቀ ይቆረጥ ሲባል እኮ ለሌሎችም መማሪያ እንዲሆን ማስፈራሪያ እንዲሆን እንጅ ለሌላ አይደለም ::ያለ አግባብ ሰው የገደለ የሚገደል ከሆነ የተከበረውን የሰው ልጅ ነፍስ በቀላሉ ለመቅጠፍ የሚሞክር አይኖርም ::

Quote:
8Coolከዚህ በፊት የግድ ካልሆነ ፎቶ መነሳት በኢስላም እንደማይፈቀድ ነግረኸኛል ::ከዚያ የባሰ ቴሌቪዥን ቪዲዮ ፊልም እንዴት አልተከለከለም ?

ይህን ማለቴን አስታውሳለሁ ::በጠይቅከኝ ጉዳይ የምሁራን የአስተያየት ልዩነት እንዳለ አንብቤያለሁ ይቻላል ወይስ አይቻልም የሚል :;አንዳንዶች ጠቃሚ ነገር መመልከት ከተቻለ ችግር የለም ይላሉ ሌሎች ደግሞ መልካም ስነምግባርን የሚያጎድፍ ነገር ለመመልከት በር ሲለሚከፍት ባይሆን ይመረጣል ይላሉ :;ፎቶ ተነስቶ ግድግዳ ላይ መስቀል እና ለመታወቂያ መነሳት የተለያዩ ነገሮች እንደሆኑ
ስገልጽልህ ግድግዳ ላይ ያለ ፎቶ ከጊዜ ብዛት ለአምልኮ ይጋለጣል :;የደጋግ አበው ፎቶ አሁንም ድረስ በሌሎች እምነቶች ሳይቀር የሚመለክበት ሁኔታ ስላለ ለዚያ መከልከሉን አንብቤያለሁ ነገርግ መልሱ በአጭሩ በምሁራን መካከል የሀሳብ ልዩነት አለ (ይቻላል አይቻልም በሚለው ሁሉም የራሱን ማስረጃ ያቀርባል )

Quote:
89) ቁርአንና ሀዲስ እንደማይጋጩ እንደነገርከኝ አስታውሳለሁ ::እንደሰማሁት ከሆነ ግን አስተማማኝ ያልሆኑ ሐዲሶች እንዳሉ ነው ::እኔ አንዳንድ ነገሮችን ማመሳከር ስለምፈልግ በመላው ዓለም በሚገኙ ሙስሊሞች ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው ሐዲሶች የትኞቹ እንደሆኑ ከቻልክ ብትነግረኝ ::

ቁር አን እና ሀዲስ አይጋጩም እኛ አእምሮ እውነታውን በጊዜው ካለመረዳት በመነጨ ሁኔታ እንጅ ::
በአሁኑ ሰአት ቡሀሪ እና ሙስሊም በሚባሉ ሸኾች የተዘጋጁት የሀዲስ መጽሀፎች እጅግ አስተማማኝ ናቸው ሌሎችም አሉ :;የኢስላም ጠላቶችም አንዳንድ አሉቧልታዎችን ሀዲስ ናቸው በማለት ሲያወሩ ይስተዋላል :;ደካማ የሚባል ሀዲስም አለ (ዶኢፍ )ከአዘጋገቡ ሰነድ የሚቆራረጥ ተአማኝነት የጎደለው አይነት ነገር ስለዚህ ቡኻሪ እና ሙስሊም ትክክለኛ ናቸው :;

Quote:
90)ለሙስሊም ሴቶች ሒጃብ ግዳጅ እንደሆነ ሁሉ ለወንዶችስ ኮፍያው የግድ መደረግ አለበት ?

ኮፍያ ባህል ይመስለኛል ልክ እንደ አረብ ቀይ ወይም ነጭ ቁድራ (ጥምጣም )
በነገራችን ላይ ሂጃብ በሁሉም እምነት ተከታዮች ዘንድ አለ አንድ የአውሮፓ ሀገር መሪ ሂጃብ እንዲከለከል ፈርም ሲሉት (ማርያም በሁሉም ፎቶግራፎቿ ሂጃብ ለብሳ [/quote] ተነስታ እንዴት መከልከል እችላለሁ ያለውን አባባል አስታወስከኝ )

ያልተብራራ ካለ ጠይቄ አብራራለሁ
_________________
HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1087
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Jun 20, 2012 9:10 pm    Post subject: Reply with quote

በድጋሚ ሰላም እያልኩ :-

በነገራችን ላይ ዋርካ ጽሑፉን ያልበላችበት ይኖራል ብለህ ነው ? በተለይ ረዘም ያለ ነገር ከተጻፈ ለጊዜውም ቢሆን ቅስም ይሰብራል ::እኔ በበኩሌ አንድን ጽሑፍ (በተለይ ረዘም ያለ ከሆነ ) submit በፊት copy ማድረግ ከጀመርኩ ወዲህ ይህ ችግር ተቃሎልኛል ::

ወደ ጉዳያችን ስመጣ ለዛሬ እነዚህን ጥያቄዎች አቀርብና በሚቀጥለው እስካሁን የተወያየንባቸውን ጉዳዮች እንደገና አያቸውና ተጨማሪ ማብራርያ ያስፈልጓቸዋል ብዬ ያሰብኳቸውን እንመለስባቸዋለን ::

91)በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ያለው ኢስላማዊ ሥርዓት በመላው ዓለም ላሉ ሙስሊሞች እንደ አርአያ (role model) ይችላል ወይ ?

92) 5 የኢስላም 'ምሶሶዎች ' ውስጥ ቁርአን ላይ የማይገኝ አለ ?

93)አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ተለይተው የሚታተሙበት ጊዜ አለ ::ለምሳሌ መዝሙረ ዳዊት ወንጌል . . . ቁርአንስ የተወሰኑ ሱራዎች ለየብቻ ሊታተሙ ይችላሉ ?

94)ሲባል እንደሰማሁት ከሆነ ቁርአን በአሁኑ ጊዜ በበርካታ የዓለም ቋንቋዎች ቢተረጎምም ሁሉም ትርጉሞች ተቀባይነት የላቸውም ::ትክክለኛው እንዴት ነው የሚታወቀው ?

95) 'satanic verses' ደራሲ ሞት የፈረዱበት ሺዓዎች (ኢራኖች ) ናቸው ::ይህ ውሳኔ በሱኒዎች ዘንድ ተቀባይነት አለው ?

96)አንዲት ሴት ባሏ ከሞተባት የባሏ ወንድም እንደሚያገባት ሰምቻለሁ ::ይህ ሥርዓት ግዴታ ነው ወይስ ሁለቱም ፈቃደኞች ከሆኑ ?

97)በበርካታ ሙስሊም አገሮች ባንዲራቸው ላይ ጨረቃና ኮከብ እናያለን ::ነቢዩ ሙሐመድ በህይወት እያሉ ተከታዮቻቸው ይጠቀሙበት ነበር ?

9አንድ ሰው ሃይማኖትን ነክ በሆነ ምክንያት ቢሞት በህመም ወይም በአደጋ ከሞተ ሰው የተሻለ ነው ተብሎ ይታመናል ?

99)ዘፈን ጨርሶ አንሰማም የሚሉ ሙስሊሞች አጋጥመውኛል ::የግል ውሳኔያቸው ነው ወይስ ክልክል ስለሆነ ነው ?

100) መጽሐፍ ቅዱሳችን እግዚአብሔር በመጀመርያ ሰማይንና ምድርን እንደፈጠረ ይነግረናል በቁርአን መሠረት አላህ መጀመርያ የፈጠረው ምንድነው ?
_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ሱልጣን

ኮትኳች

Joined: 03 Sep 2003
Posts: 465

PostPosted: Fri Jun 22, 2012 5:23 am    Post subject: Reply with quote

[quote="ዘርዐይ ደረስ "]በድጋሚ ሰላም እያልኩ :-

በነገራችን ላይ ዋርካ ጽሑፉን ያልበላችበት ይኖራል ብለህ ነው ? በተለይ ረዘም ያለ ነገር ከተጻፈ ለጊዜውም ቢሆን ቅስም ይሰብራል ::እኔ በበኩሌ አንድን ጽሑፍ (በተለይ ረዘም ያለ ከሆነ ) submit በፊት copy ማድረግ ከጀመርኩ ወዲህ ይህ ችግር ተቃሎልኛል ::

ወደ ጉዳያችን ስመጣ ለዛሬ እነዚህን ጥያቄዎች አቀርብና በሚቀጥለው እስካሁን የተወያየንባቸውን ጉዳዮች እንደገና አያቸውና ተጨማሪ ማብራርያ ያስፈልጓቸዋል ብዬ ያሰብኳቸውን እንመለስባቸዋለን ::
Quote:

እንደዚያ እያደረግኩ ነበር ሀይላይት አድርጌ ኮፒ ላደርግ ስል የት እንደሄደ ጠፋብኝ Laughing

Quote:
91)በሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ያለው ኢስላማዊ ሥርዓት በመላው ዓለም ላሉ ሙስሊሞች እንደ አርአያ (role model) ይችላል ወይ ?

በትክክል 100% አርአያ ይሆናል ::ምክንያቱም መመሪያችን ይሆን ዘንድ የተሰጠን ቁርአን በመካ እና መዲና (ሳኡዲ በሚገኙ ከተሞች ነው )በጅብሪል አማካኝነት ለነብዩ ሙሀመድ በወህይ መልክ እንዲነገራቸው የተደረገው ::ከአረበኛ ቋንቋ ይዘትም አንጻር እስልምናን ከትክክለኛ ምንጩ መረዳት የሚቻለው ከዚህ ሀገር ከሚፈልቀው አመለካከት ነው ::ይህ ማለት ግን አረቦች ወይም የሳኡዲ ህዝብ ኢስላምን ይወክላል ማለቴ አይደለም ::ኢስላም በሀገር ወይም በግለሰብ ይልለካል ማለት አይቻልም ::ከአረባዊነት ጋር ተያይዟል ማለትም አይቻልም ::
አላዋቂዎች በሚያጠፉ ጊዜ የራሳቸውን እምነት ደካማነት እንጅ ኢስላምን አይወክሉም ::ለምሳሌ እኔ አጽረቅ ተብየ ብሰርቅ እና አታመንዝር ወይም ዝሙትን አትቅረብ ተብየ በዚህ ኢሞራላዊ ስራ ላይ ብገኝ ሱልጣን ይህን ነገር አጠፋ እንጅ ኢስላም እንደዚህ ያዝዛል አይባልም ::ለዚህም ነው ኢስላም ሙሉ የህይወት ቀመር ይዟል ::ለምድራዊ ህይወትም ሆነ ከትንሳኤ በኍላ ላለው ለወዲያኛው አለም የሚያዋጣ ብቸኛ መንገድ ነው የምንለው ::የሰዎች ጥፋት ወደ ኢስላም እስካልተላከከ ድረስ ::

Quote:
92) 5 የኢስላም 'ምሶሶዎች ' ውስጥ ቁርአን ላይ የማይገኝ አለ ?

ቁርአን ላይ የማይገኝ ምንም ነገር የለም :: በጅምላ የተጠቀሰ እና በሀዲስ የተብራራ ቢሆን እንጅ ::

Quote:
93)አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ተለይተው የሚታተሙበት ጊዜ አለ ::ለምሳሌ መዝሙረ ዳዊት ወንጌል . . . ቁርአንስ የተወሰኑ ሱራዎች ለየብቻ ሊታተሙ ይችላሉ ?

ለአነባበብ (ለመቅራት እንዲመች ) 1ጁዝ ( እራፍ ) ለብቻ እየተደረገ 30 ጁዝ 30 እትም ማውጣት ይቻላል ::ችግር የለውም :;

Quote:
94)ሲባል እንደሰማሁት ከሆነ ቁርአን በአሁኑ ጊዜ በበርካታ የዓለም ቋንቋዎች ቢተረጎምም ሁሉም ትርጉሞች ተቀባይነት የላቸውም ::ትክክለኛው እንዴት ነው የሚታወቀው ?

ትርጉሞች ተቀባይነት የላቸውም ማለት አይደለም ::ማንኛውምንም ትርጉም ብታየው እንደ አረበኛው የሚመስጥ እና ልብን የሚያረካ ሴንስ አታገኝበትም ማለት ነው እንጅ ሲተረጎም በጥንቃቄ በራሳቸው ቋንቋ የታወቁ ምሁራን ሲለሚተረጉሙት ትርጉሙ ተቀባይነት የለውም ማለት አይቻልም ::

Quote:
95) 'satanic verses' ደራሲ ሞት የፈረዱበት ሺዓዎች (ኢራኖች ) ናቸው ::ይህ ውሳኔ በሱኒዎች ዘንድ ተቀባይነት አለው ?

እጅግ በጣም !!!!

Quote:
96)አንዲት ሴት ባሏ ከሞተባት የባሏ ወንድም እንደሚያገባት ሰምቻለሁ ::ይህ ሥርዓት ግዴታ ነው ወይስ ሁለቱም ፈቃደኞች ከሆኑ ?

ሁለቱም ፈቃደኛ ከሆኑ ነው እንጅ ኢስላም አዝዞ አይደለም ::ባህል ነው ነገር ግን መልካም ባህል ነው ምክንያቱም ወንድሙ ካገባት የወንድሙን ልጆች እንደራሱ አድርጎ ያሳድጋቸዋል ተብሎ ስለሚታመን ነው ::አልፈልግም ካለች ግዴታ የለባትም ::

Quote:
97)በበርካታ ሙስሊም አገሮች ባንዲራቸው ላይ ጨረቃና ኮከብ እናያለን ::ነቢዩ ሙሐመድ በህይወት እያሉ ተከታዮቻቸው ይጠቀሙበት ነበር ?

የዚህን መልስ አላውቀውም ጠይቄ እመጣለሁ ኢንሻአላህ

Quote:
9አንድ ሰው ሃይማኖትን ነክ በሆነ ምክንያት ቢሞት በህመም ወይም በአደጋ ከሞተ ሰው የተሻለ ነው ተብሎ ይታመናል ?

ለምሳሌ የአላህ ቃል ከፍ ቢሎ እንዲውል ሲል የተሰዋ ኢስላም እና ሙስሊሞችን ለመታደግ የተሰዋ ደረጃው በህመም ከሞተው በጣም የላቀ ነው :: ነገር ግን ንያው (ኢንቴንሽኑ ) ለይዩልኝ ወይም ጀግና እንዲባል ሰው እንዲያሞግሰው ከሆነ ከሁሉም ሰው የከሰረ ማለት ይህ ነው ::ቢሞት እንኳ ለኢስላም መስዋእት የሆነ ተብሎ አይመዘገብም :;ስለዚህ ልቡ ላይ ያለው ንያ (ለአላህ ብሎ በጥራት ያደረገው መሆን አለበት ከይዩልኝ እና ከይስሙልኝ ያልጠራ ማንኛውም ስራ በኢስላም ተቀባይነት የለውም !ይባስ ብሎም ያስቀጣል :;ለሰው ቸር እንዲባል ብሎ የሚመጸውት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ነው የሚያመዝን :;
ለአላህ ውዴታ ተብሎ እንጅ ለጉራ የሚሰራ ሲራ ሁሉ ተቀባይነት የለውም :::ለዚያም ነው ቁርአን (ኢንነማ ኑጥዒሙኩም ሊወጂሂላህ ላኑሪዱ ሚንኩም ጀዛአን ወላ ሹኩራ )እኛ የምንመግባችሁ (የምናበላችሁ )ለአላህ ውዴታ ብለን ነው :: እናንተ ያበላንባችሁን ውለታ እንድትመልሱልን ወይም ወይም እናመሰግናለን እንድትሉንም አንፈልግም (ብድር እንድትከፍሉ ወይም እንድታመሰግኑን አይደለም ያበላናችሁ ) ትርጉሙን የበለጠ አላህ ያውቀዋል ::
ስለዚህ ለአላህ ውዴታ ተብሎ የሚሰራ ስራ ነገ የትንሳኤ ቀን ከመልካም ስራዎች ተርታ ተሰልፎ ምንዳየን ከአላህ አገኘዋለሁ ተብሎ የታሰበለት ስራ ብቻ ነው የሚጠቅም ::

Quote:
99)ዘፈን ጨርሶ አንሰማም የሚሉ ሙስሊሞች አጋጥመውኛል ::የግል ውሳኔያቸው ነው ወይስ ክልክል ስለሆነ ነው ?

በመሰረቱ ዘፈን ክልክል ነው የሚለው ማስረጃ እጅግ በጣም ጠንካራ ማስረጃ አለው ::ዘፈን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል (ምንም እንኳ እየተዝናናንበት ነው ቢባልም )ነገር ግን በምሁራን መካከል ይቻላል አይቻልም የሚል አስተያየት አለ ::አይቻልም የሚሉት በቁጥር ይበልጣሉ ::ማስረጃቸውን ጠንካራ ነው : ስለዚህ አንሰማም የሚሉት ይበልጥ እውነታው የቀረቡ ናቸው ለዚህም ቁርአን ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል

Quote:
100) መጽሐፍ ቅዱሳችን እግዚአብሔር በመጀመርያ ሰማይንና ምድርን እንደፈጠረ ይነግረናል በቁርአን መሠረት አላህ መጀመርያ የፈጠረው ምንድነው ?

አላህ መጀመሪያ የፈጠረው ቀለምን ነው

ጥያቄዎች አሉህ ብየ ዋርካ ጄኔራልን በቀን ሳልጎበኘው አልውልም ::ጊዜ ካለህ
አንተም ፈጠን ፈጠን በል Laughing
_________________
HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1087
Location: ethiopia

PostPosted: Fri Jun 22, 2012 10:19 pm    Post subject: Reply with quote

ሱልጣን እንደጻፈ(ች)ው:

ጥያቄዎች አሉህ ብየ ዋርካ ጄኔራልን በቀን ሳልጎበኘው አልውልም ::ጊዜ ካለህ አንተም ፈጠን ፈጠን በል Laughing

አሁንማ እንደ አምናው አይደለም ::ወዲያውኑ እየተመላለስን ነው እኮ ::ለማንኛውም ባለፈው እንዳልኩህ ለጊዜው አዲስ ጥያቄዎች ከማቅረብ ካለፉት ግልጽ ያልሆኑልኝንና ያልመለስካቸውን እንደገና ብናያቸው ይሻላል ::

በዚህም መሠረት መጀመርያ ጨርሶ መልስ ያልሰጠህባቸውን አስቀድማለሁ ::

)የዓለም ፍፃሜ (የውመል ቂያማ ) ሲደርስ የሚታዩት ምልክቶች ምንድናቸው ?

)አንድ መስማትና መናገር የተሳነው ሰው መስለም ቢፈልግ ሥርዓቱ እንዴት ነው የሚካሄደው ?

)አንድ ካፊር የሙስሊም ሚዜ ሊሆን ይችላል /ትችላለች ?ሙስሊምስ የካፊር ሚዜ መሆን ይፈቀድለታል ?
)ሙስሊሞች የሚያምኑባቸው ተውራት ዘቡር ኢንጂል (ያልተበረዙት ) ባሁኑ ዘመን አሉ ተብሎ ይታመናል ?

)አንድ ሙስሊም ሙስሊም አይደለሁም ብሎ ሃይማኖቱን እንዲክድ የሚፈቀድለት ሁኔታዎች ምን ዓይነት ናቸው ?

)በኢስላም ነቢዩ ሙሐመድ በጀነት መርየምን (የዒሳን እናት ) ያገባሉ ተብሎ ይታመናል ?

)አንድ ሙስሊም ውሻ ለማሳደግ ወይም ለማሳደር የሚፈቀድለት ሁኔታዎች አሉ ?

)ከኢስላም በፊት የነበሩት ሰዎች (ከአይሁድና ክርስትያን ውጭ ) በምን መመዘኛ ነው የሚፈረድባቸው ?

)በኢስላም ከአሳማ ሌላ የማይበሉት እንስሶች የትኞቹ ናቸው ?(ብዙ ከሆኑ አንዳንዱን ለምሳሌ ያህል )

)የተለየ ክብር ያለው እንስሳስ አለ ?

)አንድ ሙስሊም ሲሞት በሬሳ ሳጥን መቅበር የሚቻልበት ሁኔታ አለ ?

)በኢስላም አዳም (አደም ) ከተፈጠረ ምን ያህል ጊዜ ሆኖታል ተብሎ ይታመናል ?

)በበርካታ ሙስሊም አገሮች ባንዲራቸው ላይ ጨረቃና ኮከብ እናያለን ::ነቢዩ ሙሐመድ በህይወት እያሉ ተከታዮቻቸው ይጠቀሙበት ነበር ?

)ሲባል እንደሰማሁት ከሆነ ቁርአን በአሁኑ ጊዜ በበርካታ የዓለም ቋንቋዎች ቢተረጎምም ሁሉም ትርጉሞች ተቀባይነት የላቸውም ::ትክክለኛው እንዴት ነው የሚታወቀው ? (እዚህ ላይ ባለፈው ጥያቄውን ግልጽ አላደረግኩልህም መሰለኝ ::ለማለት የፈለግሁት እንደሰማሁት ከሆነ የቁርአን ትርጉሞች ሳዑዲ አረቢያ ባለው ሳንሱር ክፍል ማረጋገጫ ማግኘት አለባቸው ::ይህም ማረጋገጫ የቁርአኑ መግብያ ላይ መጠቀስ አለበት ሲባል ስለሰማሁ ነው :Smile
_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ሱልጣን

ኮትኳች

Joined: 03 Sep 2003
Posts: 465

PostPosted: Sat Jun 23, 2012 4:02 pm    Post subject: Reply with quote

[quote="ዘርዐይ ደረስ "]
ሱልጣን እንደጻፈ(ች)ው:

ጥያቄዎች አሉህ ብየ ዋርካ ጄኔራልን በቀን ሳልጎበኘው አልውልም ::ጊዜ ካለህ አንተም ፈጠን ፈጠን በል Laughing

አሁንማ እንደ አምናው አይደለም ::ወዲያውኑ እየተመላለስን ነው እኮ ::ለማንኛውም ባለፈው እንዳልኩህ ለጊዜው አዲስ ጥያቄዎች ከማቅረብ ካለፉት ግልጽ ያልሆኑልኝንና ያልመለስካቸውን እንደገና ብናያቸው ይሻላል ::

በዚህም መሠረት መጀመርያ ጨርሶ መልስ ያልሰጠህባቸውን አስቀድማለሁ ::

Quote:
)የዓለም ፍፃሜ (የውመል ቂያማ ) ሲደርስ የሚታዩት ምልክቶች ምንድናቸው ?

የውመል ቂያማ (የትንሳኤ ቀን )ሊደርስ ሲቃረብ የሚታዩ ምልክቶች በሁለት ይከፈላሉ ታላላቅ እና ታናናሽ በመባል
ታናናሾች በተደጋጋሚ የተከሰቱ እና በመከሰት ላይ ያሉም አሉ ወደ 28 ከሚሆኑት ውስጥ ቲቆቶችን እነሆ
1/የንብዩ ሙሐመድ በነብይነት መላክ እና ከዚያም መል እክታቸውን ካደረሱ በኍላ መሞት
2/ከሳቸው ሞት በኍላ የሀሰት ነብይ መእነሳት (ሙሰይሊመቱል ከዛብ ) የሚባል ተነስቶ ነበር ተግባራዊ ሆኗል
3/አሚረል ሙእሚን ኡመር በነበረበት ጊዜ የተከሰተ የወረርሽኝ በሽታ
4/በነብዩ ባልደረባዎች መካከል ፈተና መፈጠር እና እርስ እርሳቸው መጋደል
5/ እሳት ነበልባ በሂጅዛ መታየት ( 654 ሂጅራ ተከስቷል
6/የአማና አለመኖር ወይም አላዋቂውን አዋቂዎች ቦታ ማስቀመጥ መሾም
7/የኡለማዎች (የአዋቂዎች መሞት እና የጃሂሎች (የማይማን )መበራከት
8/የዚና (ልቅ የሆነ ወሲብ )አመንዝራነት ካለምንም ይሉኝታ መስፋፋት
9/ ወለድ መስፋፋት የአስካሪ መጠጥ እና ጠጭ መብዛት የሙዚቃ መሳሪያ መብዛት
10/እራቁታቸውን የሚሄዱ ሰዎች መብዛት
11/ የከብት እረኛ የነበሩ አሁን ሰማይ ጠቀስ ህንጻ በመስራት መፎካከር
12/የመሬት መንቀትቀትጥ የጸሀይ ግርዶሽ መብዛት
13/የሞት መብዛት
14/ በውሸት መመስከት እና እውነትን መደበቅ መብዛት
15/የሴቶች መብዛት
16/እንስሳዎች እኛ በምናውቀው ቋንቋ መናገር
17/ የቱርክ መከፈት እና የመሳሰሉት ናቸው
ታላላቅ ምልክቶች
1/ጸሀይ በመግቢያዋ መውጣት
2/የደጃል መከሰት
3/የኢሳ መምጣት
4/አንተ አማኝ ነህ አንተ ከሀዲ ነህ የምትል ግመል መምጣት
5/ ሰዎችን የምታባርር እሳት መውጣት
6/3ጊዜ የጸሀይ ግርዶሽ
7/ ጭስ መውጣት
በነገራችን ላይ ታላላቆች መታየት ከጀመሩ እየተከታተሉ ይፈጸሙና በጣም አስችጋሪ እና አመጸኛ በሆኑ ሰዎች ላይ ትንሳኤ ይቆማል ::

Quote:
)አንድ መስማትና መናገር የተሳነው ሰው መስለም ቢፈልግ ሥርዓቱ እንዴት ነው የሚካሄደው ?

የዚህን መልስ በጣም አላውቀውም ጠይቄ መመለስ እችላለሁ

Quote:
)አንድ ካፊር የሙስሊም ሚዜ ሊሆን ይችላል /ትችላለች ?ሙስሊምስ የካፊር ሚዜ መሆን ይፈቀድለታል
?

እዚህ የራሴን አስተያየት ነው የምሰጥህ
ሚዜ መሆን እና ያለመሆን እንደ ሀይማኖታዊ ግዴታ እና ክልከላ ተመልክቸው ወይም ሰምቼው አላውቅም
ነገር ግን ወንድ እና ሴት የተቀላቀለበት በሙዚቃ የታጀበ አስካሪ መጠጥ የሚጠጣበት ቪዲዮ እና ፎቶግራፍ ያለበት ሰርግ ላይ ሙስሊሞች ቢጠሩ እንኳ መገኘት የለባቸውም ::
በነገራችን ላይ ጥሪን ማክበር ሙስሊም በሙስሊሙ ላይ ያለበት ግዴታ ነው ሆኖም ግን ከላይ የጠቀስኳቸው ነገሮች ካሉ አለማክበሩ የግድ ይሆንላ
ስለዚህ ሙስሊም የክርስቲያን ሚዜ ወይም ክርስቲያን የሙስሊም ሚዜ የሚለውን ከላይ ካለው ቅድመ ሁኔኤታ ጋር ካየነው መልሱ ከዚያ ውስጥ አለ ማለት ይቻላል ::
ካልተብራራ ጥያቄውን ቀለል አድርገህ አቅርብልኝ (አልተረዳሁትም ማለት ነው እና )

Quote:
)ሙስሊሞች የሚያምኑባቸው ተውራት ዘቡር ኢንጂል (ያልተበረዙት ) ባሁኑ ዘመን አሉ ተብሎ ይታመናል ?

ሙስሊሞች ባበረዙም አሁን ባሉት ተውራት ያምናሉ እና ስራ ላይ ይውላሉ ማለት አይደለም ::በነዚህ መጽሀፎች ማመን ማለት እነዚህ ኦሪት ዘቡር ወንጌል እና ዳዊት በወቅቱ ለነበሩ ህዝቦች ፈጣሪ ለመመሪያነት ሰጥቷቸው ነበር ቢሎ ማመን እንጅ አሁን ባይበረዙም ስራ ላይ ይውላሉ ማለት አይደለም ::ከመበረዝ የዳነ እና ስራ ላይ የሚውል የመጨረሻ ለሰው ልጆች ሁሉ የተሰጠ ቁርአን ሲሆን የመጨረሻ ነብይም ነብዩ ሙሀመድ ለሰው ልጆች ሁሉ ተልከዋል ::ለዚያም ነው እውነተኛ ነብይ አይኖርም የተባለው ::

Quote:
)አንድ ሙስሊም ሙስሊም አይደለሁም ብሎ ሃይማኖቱን እንዲክድ የሚፈቀድለት ሁኔታዎች ምን ዓይነት ናቸው ?

የዚህን ጥያቄ መልስ አላውቀው ::
አላውቀውም ያልኩህን ሁሉ በፈለግከው ሰአት ሰብሰብ አድርገህ ብትጠይቀኝ እኔም ጠይቄ መልስ አንድ ላይ እሰጥሀለሁ ኢንሻአላህ

Quote:
)በኢስላም ነቢዩ ሙሐመድ በጀነት መርየምን (የዒሳን እናት ) ያገባሉ ተብሎ ይታመናል ?

ይህን ጥያቄ ለመመለስ 15 ደቂቃ በኔት ላይ ፈልጌ ያገኘሁትን መልስ ላስቀምጥልህ ::
አዎ መርየምን እና አስያን ያገባሉ ማስረጃውም ከዚህ በታች ያለው ሊንክ ነው
http://www.islamweb.net/fatwa/index.php?page=showfatwa&Option=FatwaId&Id=37869

Quote:
)አንድ ሙስሊም ውሻ ለማሳደግ ወይም ለማሳደር የሚፈቀድለት ሁኔታዎች አሉ ?

ለማሳደግ ለአደን ከሆነ ነው ለማሳደር ግን አላውቅም ጠይቄ እመለሳለሁ

Quote:
)ከኢስላም በፊት የነበሩት ሰዎች (ከአይሁድና ክርስትያን ውጭ ) በምን መመዘኛ ነው የሚፈረድባቸው ?

ልሞክር ነበር አላውቅም ማለቱ ይሻላል እና ጠይቄ እመለሳለሁ

Quote:
)በኢስላም ከአሳማ ሌላ የማይበሉት እንስሶች የትኞቹ ናቸው ?(ብዙ ከሆኑ አንዳንዱን ለምሳሌ ያህል )

በሙስሊም ምሁራን መካከል በሚበሉ እና በማይበሉ እንስሳዎች መካከል ልዩነት አለ
ይህን ጥያቄ ለመመለስ 10ደቂቃ ሰርች አድርጌ ያገኘሁት ቁርጥ ያለ መልስ የለም ምክንያቱም አላህ ክልክል ያላደረገውን ክልክል ነው ቢሎ መናገር ወይም አላህ የከለከለውን ተፈቅዷል ብሎ መናገር ወንጀል ሲለሆነ ነው ::
Quote:
)የተለየ ክብር ያለው እንስሳስ አለ ?

አልሰማሁም :አላነበብኩም

Quote:
)አንድ ሙስሊም ሲሞት በሬሳ ሳጥን መቅበር የሚቻልበት ሁኔታ አለ ?
[quote]

ይህን ሁኔታ አልሰማሁም አላየሁም ከኔጋ የሚሰራ ጓደኛየን ጠይቄ ፍጹም አይቻልም የሚል መልስ ሰጥቶኛል በዚህ መደምደም ግን አልችልም እንደተለመደው ጠይቄ እመለሳለሁ

[quote] )በኢስላም አዳም (አደም ) ከተፈጠረ ምን ያህል ጊዜ ሆኖታል ተብሎ ይታመናል ?[quote]

Quote:
)በበርካታ ሙስሊም አገሮች ባንዲራቸው ላይ ጨረቃና ኮከብ እናያለን ::ነቢዩ ሙሐመድ በህይወት እያሉ ተከታዮቻቸው ይጠቀሙበት ነበር ?

በጥንት ጊዜ ይይዙት የነበረው ባንዲራ ልሙጥ ጥቁር እንደነበር ያነበብኩ ይመስለኛል እስኪ ይህንም ለመጠየቅ ጊዜ ስጠኝ .......ምክንያቱም እለታዊ ህይወታችን ጋር ያልተዛመደ ብናውቀው የማይጠቅመን ብንተወው ደግሞ የማይጎዳንን እውቀት ትኩረት አንሰጠውም ::
ለምሳሌ አደም ከተፈጠረ ጀምሮ ምን ያክል እድሜ እንዳስቆጠረ ማወቁ ወይም አለማወቁ ለውጥ አያመጣም

Quote:
)ሲባል እንደሰማሁት ከሆነ ቁርአን በአሁኑ ጊዜ በበርካታ የዓለም ቋንቋዎች ቢተረጎምም ሁሉም ትርጉሞች ተቀባይነት የላቸውም ::ትክክለኛው እንዴት ነው የሚታወቀው ? (እዚህ ላይ ባለፈው ጥያቄውን ግልጽ አላደረግኩልህም መሰለኝ ::ለማለት የፈለግሁት እንደሰማሁት ከሆነ የቁርአን ትርጉሞች ሳዑዲ አረቢያ ባለው ሳንሱር ክፍል ማረጋገጫ ማግኘት አለባቸው ::ይህም ማረጋገጫ የቁርአኑ መግብያ ላይ መጠቀስ አለበት ሲባል ስለሰማሁ ነው :Smile

ቁር አንን በዘፈቀደ የሚተረጉም ሀገር የለም ::ብዙ ጊዜ በተለያዩ ቋንቋዎች የሚተረጎመው ሳኡዲ አረቢያ ውስጥ ሲሆን የሚተረጎምበት ሀገር ሊቃውንት ወይም ምሁራን የእውቀት ደረጃቸው ከታወቀ በኍላ ነው ትርጉሙ ዋጋ የሚሰጠው :;ማንም ደግሞ ብቃት ሳይኖረው ልተርጉም ቢሎ የሚነሳ ሰው የለም ስለዚህ ሳንሱር ያልከው ነገር ትክክል ሊሆን ይችላል ::
_________________
HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1087
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Jun 25, 2012 12:19 pm    Post subject: Reply with quote

Quote:
እለታዊ ህይወታችን ጋር ያልተዛመደ ብናውቀው የማይጠቅመን ብንተወው ደግሞ የማይጎዳንን እውቀት ትኩረት አንሰጠውም ::
ለምሳሌ አደም ከተፈጠረ ጀምሮ ምን ያክል እድሜ እንዳስቆጠረ ማወቁ ወይም አለማወቁ ለውጥ አያመጣም

በዚህ ጉዳይ ላይ በክርስቲያኖች ዘንድም ተመሳሳይ ሁኔታ አለ ::ለማንኛውም ግን ለጊዜው ጠቃሚ ባይመስለንም የቻልነውን ያህል ስለ ሃይማኖታችን ለማወቅ ከመጣር መቆጠብ የለብንም ብዬ አምናለሁ ::በተረፈ ለጊዜው መመለስ ያልቻልካቸውን ጥያቄዎች ሲመችህ ትመልሳቸዋለህ ::የሚያስቸኩልና የሚያጨናንቅ ነገር የለም ::እኔም እንዳልከው ያልመለስካቸውንና ግልጽ ያልሆኑልኝን ነገሮች ሌላ ጊዜ ሰብሰብ አድርጌ ላቀርብልህ እሞክራለሁ ::እስከዚያው ሌሎች ጥያቄዎችን ላስከትል ::

101)በክርስትና ሃይማኖት መሠረት ከኃጢአት ሁሉ የከፋው የትኛው እንደሆነ ጠይቀኸኝ መልስ ሰጥቼአለሁ ::በኢስላምስ ?

102)ኢትዮጵያ ያለው የሸሪዓ ፍርድ ቤት ከጋብቻ ውጭ የሚያያቸው ጉዳዮች አሉ ?

103) ነቢያችሁ ሙሐመድ ተከታዮቻቸው በኢትዮጵያ (ሐበሻ ) ላይ ጂሃድ እንዳያውጁ ትእዛዝ ሰጥተዋል ይባላል ::በታሪካችን እንደምናየው ግን ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘመናት የጂሃድ ጦርነት ተካሂዶባታል ::ታዲያ እነዚህ ጂሃድ ያካሄዱት ኃይሎች የነቢዩን ትእዛዝ አልጣሱም ትላለህ ?

104)ነቢያችሁ ሙሐመድ በእርግጠኝነት ጀነት እንደሚገቡ የተናገሩላቸው ሰዎች አሉ ይባላል ::ምን ያህል እውነት ነው ?

105)በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት አጋንንት መላእክት የነበሩ ናቸው ::ከሰው ልጆች ሴቶች ጋር ግንኙነት አድርገው ሲመለሱ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የተጣሉ ናቸው ::ቁርአንስ ስለ ጂኒዎች አመጣጥ ምን ይላል ?

106)አንድ ሰው ክርስትያን ለመባል ከክርስቲያን ቤተሰብ ቢወለድም መጠመቅ አለበት :: አንድ ከሙስሊም ቤተሰብ የተወለደ ልጅ ኢስላምን መቀበል (ሸዓዳ ማድረግ ነው የሚባለው መሰለኝ ) አለበት ወይስ አስፈላጊ አይደለም ?

107) አንድ ካፊር ከሙስሊም ጋር ውይይት ሲያደርግ ነቢያችሁን በስማቸው ብቻ ቢጠራ ውይይቱ መቀጠል ይችላል ?

108)ነቢያችሁ በህይወት እያሉ የተሰራና አሁንም ያለ መስጊድ አለ ?

109)ነቢያችሁ ሙሐመድ ከሰሩት ተአምራት አንዳንዶቹን ብትጠቅስልኝ ::

110)መጽሐፍ ቅዱስ ሄኖክና ኤልያስ ጨርሶ እንዳልሞቱ ያስተምረናል :: በኢስላም ያልሞተ ሰው አለ ተብሎ ይታመናል ?

111) በቁርአን መሠረት አንድ ሙስሊም ኢንዲያገባ የሚፈቀድለት 4 ሚስቶች 'ብቻ ' ነው ::ነቢያችሁ ግን ከዚያ በላይ እንዳገቡ ይነገራል ::ምን ያህል እውነት ነው ?

112)ከነቢያችሁ ቤተሰቦች ወይም ዘመዶች መካከል ክርስትያን የነበረ ሰው አለ ?

113) ነቢያችሁ ሲወለዱ አንዳንድ ለየት ያሉ ነገሮች ታይተውባቸዋል ይባላል ::ለምሳሌ ተገርዘው እንደተወለዱ ሰምቻለሁ ::ሌሎችስ ከሌላው ሰው የተለየ የሚያደርጓቸው ነገሮች አሉ ?

114)አንዳንድ የዓለማችን ክፍሎች ቀኑ በጣም የሚረዝምበት ጊዜ አለ ::እዚያ አካባቢ የሚኖር ሙስሊም በረመዳን ወቅት ለማፍጠር የግድ የፀሐይን መጥለቅ መጠበቅ አለበት ?

115)በቁርአን መሠረት መሬት ሳትሆን ፀሐይ ነች የምትዞረው ሲባል ሰምቻለሁ ::እውነት ነው ?

116)የቁርአን ሱራዎች እያንዳንዳቸው የተለየ መጠርያዎች አላቸው ::አንዳንዶቹም የእንሳሳት ሥም የያዙ ናቸው :: ቁርአን ከነዚህ መጠርያዎችና ከአያቶቹ መለያ ቁጥሮች ጭምር ነው የወረደው ነው የሚባለው ወይስ በኋላ የተጨመሩ ናቸው ?

117) ኖህ ከልጆቹ አንዱን (ከንዓን ) እንደረገመው ከመጽሐፍ ቅዱስ እንረዳለን ::ቁርአን ውስጥ የተረገመ ሰው ወይም ህዝብ አለ ?

118)በኢስላም አንድ ሰው ከሞተ በኋላ እንደ ተዝካር ሙት ዓመት ወዘተ . ይደረጋል ?

119)የታዋቂ ሙስሊሞችን መቃብር መጎብኘት (ለምሳሌ የኛ አገር ሙስሊሞች የባሌው ሽከናው ሑሤን የተቀበሩበት ቦታ እንደሚሄዱት ) የተከለከለ ነው የሚሉ አጋጥመውኛል ::አንተስ ምን ትላለህ ?

120)አንድ ከሙስሊምና ከካፊር የተወለደ ልጅ አባቱ ሙስሊም ከሆነ ብቻ ነው ሙስሊም ሊባል የሚችለው ::እናቱ ከሆነች ግን ሙስሊም ሊባል አይችልም ሲባል ሰምቻለሁ ::ምን ያህል እውነት ነው ?

P.S.: እኔ በምጽፋቸው ጽሑፎች ላይ emoctions(ከዚህኛ Arrow በስተቀር ) አልጠቀምም ::አንዳንድ ቦታ ላይ ግን ሊታዩ ይችላሉና የዋርካ እንጂ የእኔ አይደሉም ::

ባለፈው ጽሑፍህ ላይ የእኔን ጽሑፍ quote ስታደርግ ያንተንም አብረህ አድርገኸው ትንሽ ግር ብሎኝ ነበርና submit ከማድረግህ በፊት ብታየው አይከፋም ::
[/quote]
_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ሱልጣን

ኮትኳች

Joined: 03 Sep 2003
Posts: 465

PostPosted: Fri Jun 29, 2012 3:47 pm    Post subject: Reply with quote

[quote="ዘርዐይ ደረስ "]
Quote:
እለታዊ ህይወታችን ጋር ያልተዛመደ ብናውቀው የማይጠቅመን ብንተወው ደግሞ የማይጎዳንን እውቀት ትኩረት አንሰጠውም ::
ለምሳሌ አደም ከተፈጠረ ጀምሮ ምን ያክል እድሜ እንዳስቆጠረ ማወቁ ወይም አለማወቁ ለውጥ አያመጣምበዚህ ጉዳይ ላይ በክርስቲያኖች ዘንድም ተመሳሳይ ሁኔታ አለ ::ለማንኛውም ግን ለጊዜው ጠቃሚ ባይመስለንም የቻልነውን ያህል ስለ ሃይማኖታችን ለማወቅ ከመጣር መቆጠብ የለብንም ብዬ አምናለሁ ::በተረፈ ለጊዜው መመለስ ያልቻልካቸውን ጥያቄዎች ሲመችህ ትመልሳቸዋለህ ::የሚያስቸኩልና የሚያጨናንቅ ነገር የለም ::እኔም እንዳልከው ያልመለስካቸውንና ግልጽ ያልሆኑልኝን ነገሮች ሌላ ጊዜ ሰብሰብ አድርጌ ላቀርብልህ እሞክራለሁ ::እስከዚያው ሌሎች ጥያቄዎችን ላስከትል ::

Quote:
101)በክርስትና ሃይማኖት መሠረት ከኃጢአት ሁሉ የከፋው የትኛው እንደሆነ ጠይቀኸኝ መልስ ሰጥቼአለሁ ::በኢስላምስ ?

እስልምና ታላቁ ወንጀል ሽርክ ነው ::ርክ ማለት ከፈጣሪ ሌላ ወይም ከፈጣሪ ጋር የሆነን አካል አብሮ ማምለክ ማለት ነው ::ከፈጣሪ ውጭ ያለ አካል ይጠቅመኛል ወይም ይጎዳኛል በሚል እምነት ፍጹም አምልኮት የሚገባው ጌታ አላህ ሆኖ ሳለ ይህን ተግባር ለሌላ አካል መስጠት ታላቅ ወንጀል ነው ::ከዚያ በኍላ ንጹህ የሆነችን ነፍስ ማጥፋት /መግደል /የየቲምን ገንዘብ ካለ አግባብ መብላት /አራጣ መብላት /ጥንቆላ እና ሟርት /ዝሙት እና ተዛማጅ ወንጀሎች የመሳሰሉ ከባድ ወንጀል ይባላሉ ::

Quote:
102)ኢትዮጵያ ያለው የሸሪዓ ፍርድ ቤት ከጋብቻ ውጭ የሚያያቸው ጉዳዮች አሉ ?

ኢትዮጵያ ውስጥ የሸሪአ ፍርድ ቤት አለ እንዲባል ለይስሙላ የተቋቋመ እንጅ ሁሉንም ሸሪአዊ ጉዳዮች ያያል ማለት አይደለም ::በውስጡ ያሉ ሰራተኞች አብዛኞቹ ደግሞ ሙስሊሞች አይደሉም ::ስለዚህ ጋብቻ እና ፍችን እያስተናገደ ነው ቢባልም ለይስሙላ የተቋቋመ እንጅ እውነት ሙስሊሞችን እምነታቸው መሰረት እያገለገለ ነው ለማለት አልደፍርም ::

Quote:
103) ነቢያችሁ ሙሐመድ ተከታዮቻቸው በኢትዮጵያ (ሐበሻ ) ላይ ጂሃድ እንዳያውጁ ትእዛዝ ሰጥተዋል ይባላል ::በታሪካችን እንደምናየው ግን ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘመናት የጂሃድ ጦርነት ተካሂዶባታል ::ታዲያ እነዚህ ጂሃድ ያካሄዱት ኃይሎች የነቢዩን ትእዛዝ አልጣሱም ትላለህ ?

ሀበሾችን ካልወጓችሁ አትውጓቸው የሚል ሀዲስ እንዳለ አስታውሳለሁ :ነገር ግን በኢትዮጵያ ላይ የታወጀ የጅሀድ ጦርነት መኖሩን አላስታውስም ::ብትጠቅስልኝ ይበልጥ ለውይይት ይረዳናል

Quote:
104)ነቢያችሁ ሙሐመድ በእርግጠኝነት ጀነት እንደሚገቡ የተናገሩላቸው ሰዎች አሉ ይባላል ::ምን ያህል እውነት ነው ?

እጅግ በጣም እውነት ነው ::10 በጀነት የተበሰሩ (ጀነት እንደሚገቡ የተመሰከረላቸው ሰዎች አሉ )
ከነዚህም ውስጥ አራቱ ኸሊፋዎች (አቡበከር ኡመር ኡስማን አልይ ) እና ጠለሀ ዙበይር ሰእድ ሌሎችም ይገኙበታል ::

Quote:
105)በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት አጋንንት መላእክት የነበሩ ናቸው ::ከሰው ልጆች ሴቶች ጋር ግንኙነት አድርገው ሲመለሱ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የተጣሉ ናቸው ::ቁርአንስ ስለ ጂኒዎች አመጣጥ ምን ይላል ?

ጅኖች ሙስሊም እና ካፊር በመባል ይታወቃሉ ::ልክ እንደሰው ልጅ የፈጣሪን ትእዛዝ የሚፈጽሙ እና የሚያምጹ አሉ ቁር አንን ሲነበብ በሰሙ ጊዜ በጌታችንን አምነናል የሚል የምስክርነት ቃል መስጠታቸው እና ሱረቱል ጅን በሚል በነሱ ስያሜ የተሰየመ አንቀጽ አለ ::

Quote:
106)አንድ ሰው ክርስትያን ለመባል ከክርስቲያን ቤተሰብ ቢወለድም መጠመቅ አለበት :: አንድ ከሙስሊም ቤተሰብ የተወለደ ልጅ ኢስላምን መቀበል (ሸዓዳ ማድረግ ነው የሚባለው መሰለኝ ) አለበት ወይስ አስፈላጊ አይደለም ?

በመሰረቱ ሁሉም ሰው ሲፈጠር ሙስሊም ሆኖ ነው የሚፈጠር ::ከዚያም ቤተሰቦቹ ናቸው ሌላ እምነት እንዲከተል የሚያደርጉት ::ከሙስሊም ቤተሰብ የተወለደ ሸሀዳ እንዲያደርግ አይጠየቅም :;አንዴ ሙስሊም ሆኗልና !አዲሱ ከሊባኖች በመንግስት ድጋፍ ኢምፖርት የተደረግው አህባሽ ግን እንደ አዲስ ሸሀዳ አድርጉ ይላል ::

Quote:
107) አንድ ካፊር ከሙስሊም ጋር ውይይት ሲያደርግ ነቢያችሁን በስማቸው ብቻ ቢጠራ ውይይቱ መቀጠል ይችላል ?

ምንም ችግር የለውም ::

Quote:
108)ነቢያችሁ በህይወት እያሉ የተሰራና አሁንም ያለ መስጊድ አለ ?

አዎ !የቁባ መስጅድ እና መስጀደል ነበዊ (የነብዩ መስጅድ ተብሎ )የሚታውቀው መዲና ያለው መስጅድ ::

Quote:
109)ነቢያችሁ ሙሐመድ ከሰሩት ተአምራት አንዳንዶቹን ብትጠቅስልኝ ::

ለቁጥር የሚታክቱ ተአምራቶች አሉ !ሙስሊሞች ግን እንደዚህ አይነት ነገሮችን አያካብዱም ::ነብያቸውንም እንደፈጣሪ አድርገው አያመልኩም ::ይህን ተአምር እንዲሰሩ የፈቀደላቸውን አላህ ብቻ ነው የሚያመልኩ ::
ከተአምራቶች በጥቂቱ ለአንድ ሰው የማይበቃ ምግብ በሳቸው ጸሎት አብረው የነበሩ ባልደረባዎች እስኪጠግቡ ድረስ መመገባቸው ::እሳቸውን ለመግደል ሲያሴሩ የነበሩ ጠላቶቻቸው ሁለት ብቻ ሆነው ያወሩትን ወሬ አላህ ለሳቸው አሳውቋቸው ለበላጉዳዮች ተናግረው አንዱ መስለሙ (ምክንያቱም ሌላ ሰው ይህን ሚስጥር አያውቅም ነበር እና አላህ ነግሯቸው ነው በማለት ስላመነ :: እርግጥም አላህ ነግሯቸው ነበር ) የኸንደቅ ዘመቻ ጊዜ ጉድጓድ ሲቆፍሩ አንድ ቋጥኝ አስቸግሯቸው እሳቸው በያዙት መዶሻ ሲመቱት እሳቱ ብልጭ ሲል አሏሁ አከበር
እነዚህ አገሮች ላይ ድል እንደማገኝ ተገለጸልኝ እያሉ የተናገሩት እውነት መሆኑ /ለአንድ ሰሀባ የኪስራ ንጉስን የራስ ዘውድ አንተ ትለብሳለህ ብለው ትንቢት ነግረውት እሳቸው ከሞቱ በኍላ ኡመር ጊዜ ትንቢቱ እንድተፈጸመ /የተኙበት ምንጣፍ ሙቀቱ ሳይቀዘቅዝ ወደ ሰማይ ከጅብሪል ጋር ሄደው ብዙ ነገሮችን አይተው እንደተመለሱ (በዚህ አጋጣሚ በይተል መቅዲስን አየሁ ብለው ነበር ሰዎች በንግድ እንካ 2 ወር ስለሚወስድባቸው እንዴት በተወሰነ ሰአት ይህን ሊያዩ ቻሉ በማለት መስጅዱ ስንት በራፍ እንዳለው ሲጠየቁ በትክክል እንደመለሱ /እና ሌሎችም (ከትቀመጡበት አካባቢ ዳመናው እየተከተለ እንደሚያስጠልላቸው ::እና ቁር አን በራሱ እሳቸው ነብይነት ማረጋገጫ የተሰጠ ማንም ቻሌንጅ ሊያደርገው የማይችል ጅኖች እና ሰዎች ቢሰበሰቡ እንኳ አንድ አንቀጽ ቢጤውን ማምጣት እንደማይችሉ የተወሳበት ሁኔታ እና ሌሎችም ....

Quote:
110)መጽሐፍ ቅዱስ ሄኖክና ኤልያስ ጨርሶ እንዳልሞቱ ያስተምረናል :: በኢስላም ያልሞተ ሰው አለ ተብሎ ይታመናል ?

እስካሁን እንዳልሞተ እርግጠይነት ኢስላም የሚያስተምረው ነብዩሏህ ኢሳን ነው ::

Quote:
111) በቁርአን መሠረት አንድ ሙስሊም ኢንዲያገባ የሚፈቀድለት 4 ሚስቶች 'ብቻ ' ነው ::ነቢያችሁ ግን ከዚያ በላይ እንዳገቡ ይነገራል ::ምን ያህል እውነት ነው ?

በጣም እውነት ነው ::ነብዩ ሙሀመድ ሴቶችን ለተለያየ አላማ ነበር የሚያገቡት :: ኢስላም ጠላቶች እንደሚሉት ለስሜት ቢሆን ኖሮ ኸድጃ የመጀመሪያ ባለቤታቸው 40 አመት ሆኗት ባላገቧት ነበር ::የኢስላምን አስተምሮ በቀላሉ ለማስፋፋት /በየጎሳ በቀላሉ ለማስረጽ ባላቸው የሞቱባቸውን ሴቶች ሞራል ለመጠበቅ እና በሌሎችም ምክንያት አላህ እንዲያገቡ የፈቀደላቸውን አግብተዋል ::
ለሌላ ሰው እስከ 4 ይፈቀዳል ( በፍትህ ማስተዳደርን ብትፈሩ አንዷን መያዙ በላጭ እንደሆነ ያስተምራል ::
ኢስላም የሴቶችን መብት የጠበቀበት አጋጣሚም እዚህ ላይ ይስተዋላል ::ሰው ልቅ በሆነ ግንኙነት ቅምጦችን (ውሽሞችን ) በሚስጥር አስቀምቶ በሰው ህይወት ከመቀለድ ህጋዊ ሚስት ሆነው ሊወልዱ ሊወርሱ ይችሉ ዘንድ እስከ አራት ሚስት በህጋዊነት አግባብ ባለው ሁኔታ ሲደነገግ የወንዶችን ከማያልቅ ፍላጎትም ከግምት ውስጥ ያገባ ነው ::ስለዚህ ክልክል በሆነ መልኩ የአለም ህዝብ የሚሰራውን ጸያፍ ስራ ኢስላም ህግ ተጠሪነት እና ተጠያቂነትን ያማከለ በሆነ መልኩ 4 ሚስት ፈቅዷል ::

Quote:
112)ከነቢያችሁ ቤተሰቦች ወይም ዘመዶች መካከል ክርስትያን የነበረ ሰው አለ ?

ክርስቲያን ነበሩ ከማለት ጣኦት አምላኪ ነበሩ የሚለው ያስኬዳል ምክንያቱ ነብዩ ወደ ህዝብ ነብይ ሆነው ሲላኩ የአረብ ነገዶች ጣኦት አምላኪ ነበሩ በዚህም መሰረት አባታቸው እንዲሁም አጎቶቻቸው አቡለሀብ እና አቡ ጀህል ጣኦት አምላኪ ነበሩ ኢስላምን ሳይቀበሉ ነው የሞቱት ::

Quote:
113) ነቢያችሁ ሲወለዱ አንዳንድ ለየት ያሉ ነገሮች ታይተውባቸዋል ይባላል ::ለምሳሌ ተገርዘው እንደተወለዱ ሰምቻለሁ ::ሌሎችስ ከሌላው ሰው የተለየ የሚያደርጓቸው ነገሮች አሉ ?

ተገርዘው ነው የተወለዱ የሚለውን ማረጋገጥ አለብኝ ነገር ግን እናታቸው አሚና እንደምትለው በጽንስ ጊዜ በጣም እንዳልከበዳት እና ሁሉ ነገር ቀላል እንደነበር / በህልሟታላቅ ሰው እንዳረገዘች የተነገራት እሳቸው ሲወለዱ እሳት አምላኪዎች የሚያመኩት እሳቱ ጠፍቶ የማያውቅ እሳት መጥፋቱ /በልጅነታቸው ለጣኦት አለመስገዳቸው እና ጨዋ እና ታማኝ ትሁት መሆናቸው ::/መል አኮች መጥተው ልባቸውን ከፍተው አጽድተው እንደገና እንደነበር እንደመለሱላቸው /በህጻንነታቸው ልታሳድጋቸው ገጸር የወሰደቻቸው ሴትዮ ስትመጣ ይዛው የነበረው እንስሳ ስነብዩን ይዛ ስትመለስ ሁሉንም ሰው ቀድሞ ጠንክሮ እንደተጓዘ እቤት ሲገቡ ደግሞ ቤቱ በበረከት እንደተሞላ ደረቅ እና ከሴታ የነበሩ ፍየሎች በወተት ተሞልተው ቤት ውስጥ ያለው ሁሉ ነገር በረከት እንደጨመረ /ሌሎችም ነገሮች አሉ

Quote:
114)አንዳንድ የዓለማችን ክፍሎች ቀኑ በጣም የሚረዝምበት ጊዜ አለ ::እዚያ አካባቢ የሚኖር ሙስሊም በረመዳን ወቅት ለማፍጠር የግድ የፀሐይን መጥለቅ መጠበቅ አለበት ?

የዚህን ጥያቄ እና ቀሪዎችን እመለስባቸዋልሁ ::ይህን ሰሞን ትንሽ ቢዚ ነገር ነኝ ::ባለፈው ትያቄውን በጻፍከው 30 ደቂቃ ውስጥ መልስ ሰትቼህ ፖስት አድርግልኝ ስለው የት እንደወሰደው አላውቅም ::
ቀሪዎችን እመለስባቸዋለሁ ኢንሻአላህ ::
_________________
HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ቆቁ

ዋና አለቃ

Joined: 21 Sep 2003
Posts: 4564
Location: united states

PostPosted: Fri Jul 27, 2012 6:03 pm    Post subject: Reply with quote

ልዩ ደብዳቤ ለሱልጣን ለጥንቱ ወዳጄ

ጽሁፌ የናንተን አምድ አይመለከትም

ሱልጣንን ወደ ፖለቲካው የዋርካ መድረክ ብቅ በማለት ስለ ኢማም አህመድ ቢን ኢብራሂም ( ግራኝ መሐመድ ) አስተያየቱን እንዲሰጥ ነው

ታዲያ ሱልጣን ወዳጄ የጥንቱ ሐገር የጋራ ነው ሐይማኖት የግል ነው የሚለውን መመሪያ ሳንረሳ

ይቅርታ ለዚህ ዓምድ ተካፋዮች በሙሉ
እንደ እርጎ ዝንብ ጥልቅ በማለቴ

ቻው ቻው ከዚህ አምድ ፈላስፋው ቆቁ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሱልጣን

ኮትኳች

Joined: 03 Sep 2003
Posts: 465

PostPosted: Mon Jul 30, 2012 8:55 am    Post subject: Reply with quote

ውድ ዘርአይ ሰሞኑን ትንሽ ቢዚ መሆኔን ጠቅሼልህ ነበር አሁንም ኤክስቴንድ ለማድረግ ነው የመጣሁ /በወዳጅነታችን እንሰንብት ::
ውድ ቆቁ ስለ ግብዣህ አመሰግናለሁ
የጥንቱ መመሪያ እንደተጠበቀ ነው ወዳጀ
_________________
HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1087
Location: ethiopia

PostPosted: Sun Nov 11, 2012 8:46 pm    Post subject: Reply with quote

ሱልጣን እንደጻፈ(ች)ው:
ውድ ዘርአይ ሰሞኑን ትንሽ ቢዚ መሆኔን ጠቅሼልህ ነበር አሁንም ኤክስቴንድ ለማድረግ ነው የመጣሁ /በወዳጅነታችን እንሰንብት ::
ውድ ቆቁ ስለ ግብዣህ አመሰግናለሁ
የጥንቱ መመሪያ እንደተጠበቀ ነው ወዳጀ

ሰላም ሱልጣን እንዴት ከርመሃል ?መቼም የጠፋኸው በደህና እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ ::እኔ እንኳ እንደበፊቱም ባይሆን አልፎ አልፎ ዋርካን መጎብኘቴ አይቀርም ::ይህንን ቤታችንም ረስቼው ሳይሆን ያው ያንተን መልስ እየጠበቅኩ ስለነበር ነው ::እንግዲህ አንተ መቼ እንደምትመለስ ስለማላውቅ እንዳልረሳቸው በማለት ዛሬ ተጨማሪ ጥያቄዎች ላስከትል ነው ::በተመቸህ ጊዜ መልስ ትሰጥባቸዋለህ ::እስካሁን ብዙ ጉዳዮች ላይ ስለተወያየንና ጊዘውም ስለረዘመ አንዳንድ ጥያቄዎች የተደገሙ መስሎ ከተሰማህ ዝለላቸው ::ከይቅርታ ጋር ::

121)ሙስሊሞች ሁሉ የሚጠቀሙበት ቁርአን አንድ ዓይነት ነው ?ለምሳሌ ክርስትናን ብንወስድ ሁሉም 66ቱን ቢቀበሉም ኦርቶዶክስ 15 ካቶሊኮች 7(ትክክለኛውን ቁጥር እርግጠኛ አይደለሁም ) ተጨማሪ መጻሕፍትን ይቀበላሉ ::ተመሳሳይ ልዩነት በሙስሊሞች ዘንድ አለ ወይ ለማለት ያህል ነው ::

122)በኢስላም እምነት አንድ ሰው ሲሞት ነፍሱ ወድያውኑ ነው ወደ ጀሐነም ወይም ጀነት የምትገባው ?

123) ያልተቀበረ ሰው ነፍስ እረፍት የላትም የሚባለውስ ምን ያህል እውነት ነው ?

124)አንዳንድ ጊዜ በተለይ የሙስሊሞች መቃብር በሌለበት ቦታ በክርስትያን ወይም በሌሎች እምነት ተከታዮች የመቃብር ቦታ የሚቀበሩ ሙስሊሞች ይኖራሉ ::በሁለቱ መካከል ልዩነት አለ ወይ ?

125)በኢስላም አንድ ሰው ጠላቴ በሚለው ሰው ሞት መደሰት ይፈቀድለታል ?

126)በህፃንነታቸው የሚሞቱ ልጆች በሙሉ ጀነት ይገባሉ ሲባል ሰምቼ ነበር እውነት ነው ?

127)አንድ ሰው ሙስሊም ነኝ ካለ የራሱ ምስክርነት በቂ ነው ወይስ ሌሎች ሁኔታውን አይተው ይህ ሰው ሙስሊም አይደለም የማለት መብት አላቸው ?

128)አንድ ሰው እስልምናን ሳቀበል ቢሞት ሌላ እድል ይሰጠዋል ?በተለይ እንኳን ስለኢስላም ሊነገራቸው የእስልምናን መኖር ሳያውቁ የሞቱት

129)ሴቶች ሃይማኖታዊ ያልሆነ ሥልጣን ይፈቀድላቸዋል ?

130)የአንድ ወንድ ምስክርነት ከሁለት ሴቶች ምስክርነት ጋር እኩል ነው የሚባለውስ ?

131)ባልና ሚስት ከተፋቱ በኋላ በድጋሚ ለመጋባት ቢፈልጉ በመሐሉ ሚስትዬው ሌላ ሰው ካላገባች አይቻልም ሲባል ሰምቼ ነበር ::ምን ያህል እውነት ነው ?

132)ከዚህ በፊት ነቢያችሁ ሙሐመድ ጀነት እንደሚገቡ የመሰከሩላቸው ግለሰቦች እንዳሉ ነግረኸኝ ነበር ::በእርግጠኝነት ጀሐነም ይገባሉ ያሏቸው ሰዎችስ አሉ ?

133)መስቀል የቤተ ክርስትያኖች መለያ እንደሆነ ሁሉ ጨረቃና ኮከብ ደግሞ የመስጊዶች መለያ ናቸው ::በክርስታና መስቀልን ግለሰቦችም ይጠቀሙበታል (በሐብል ላይ በቀለበት ቤታቸው ግድግዳ ላይ ወዘተ ) ሙስሊሞችስ ?

134)በኢስላም ለህክምና ጉዳይ ደም መስጠት ወይም መቀበል እንዲሁም የሰውነት ብልቶችን (ጉበት ኩላሊት ወዘተ )ማስቀየር ይፈቀዳል ?

135)ከዚህ በፊት ቁራን ላይ ያሉ ብዙ ነገሮች በሳይንስ ተረጋግጠዋል ያልከኝ መሰለኝ ::ቁርአን ላይ ፀሐይ መሬትን እንደምትዞር ተጽፏል የሚባለው እውነት ነው ?

136)በአሁኑ ዘመን የማይሰሩ የቁርአን አንቀፆች አሉ ?

137)በአገራችን በርካታ ወራት ያስቆጠረ የሙስሊሞች የመብት ጥያቄ እንቅስቃሴ አለ ::ከጥያቄዎቹ አንዱ የመጅሊስ ምርጫ ነው ::በነቢዩ ዘመንና ከሳቸው ሞት በኋላ መጅሊስ የሚባል ተቋም ነበረ ?ምርጫውስ የሚካሄደው የት ነበር ?

138)ዓለም አቀፍ መጅሊስስ አለ ?

139)በኢስላም ሰው ሲሞት ወይም የሞተ ሰው ሥም ሲነሳ ነፍስ ይማር ይባላል ወይ ?

140)አንድ ሙስሊም የሌላ እምነት ተከታዮች በዓላቸውን ሲያከብሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት ማቅረብ ይችላል ?ወይስ እንደ በዓላቱ ዓይነት የሚወሰን ጉዳይ ነው ?
_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ሱልጣን

ኮትኳች

Joined: 03 Sep 2003
Posts: 465

PostPosted: Sun Nov 18, 2012 11:46 am    Post subject: Reply with quote

Quote:
ውድ
ሰላም ሱልጣን እንዴት ከርመሃል ?መቼም የጠፋኸው በደህና እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ ::እኔ እንኳ እንደበፊቱም ባይሆን አልፎ አልፎ ዋርካን መጎብኘቴ አይቀርም ::ይህንን ቤታችንም ረስቼው ሳይሆን ያው ያንተን መልስ እየጠበቅኩ ስለነበር ነው ::እንግዲህ አንተ መቼ እንደምትመለስ
ስለማላውቅ እንዳልረሳቸው በማለት ዛሬ ተጨማሪ ጥያቄዎች ላስከትል ነው ::በተመቸህ ጊዜ መልስ ትሰጥባቸዋለህ ::እስካሁን ብዙ ጉዳዮች ላይ ስለተወያየንና ጊዘውም ስለረዘመ አንዳንድ ጥያቄዎች የተደገሙ መስሎ ከተሰማህ ዝለላቸው ::ከይቅርታ ጋር :: [/quote]
አዎ በሰላም ነው ማለት ይቻላል በጣም ቢዚ የሚያደርግ ጉዳይ ገጥሞኝ ነው ቢሆንም እስኪ ወደ ጥያቄዎጭ ላምራ ከምስጋና ጋር

[/quote]
Quote:
121)ሙስሊሞች ሁሉ የሚጠቀሙበት ቁርአን አንድ ዓይነት ነው ?ለምሳሌ ክርስትናን ብንወስድ ሁሉም 66ቱን ቢቀበሉም ኦርቶዶክስ 15 ካቶሊኮች 7(ትክክለኛውን ቁጥር እርግጠኛ አይደለሁም ) ተጨማሪ መጻሕፍትን ይቀበላሉ ::ተመሳሳይ ልዩነት በሙስሊሞች ዘንድ አለ ወይ ለማለት ያህል ነው ::

ቁርአን አንድ ብቻ ነው ::ሁሉም የሚጠቀምበት በዚሁ ሲሆን ከብረዛ እንደሚጠብቀው አላህ ቃል ስለገባለት እስከ ትንሳኤ ቀን እንደተጠበቀ ይቆያል ::

Quote:
122)በኢስላም እምነት አንድ ሰው ሲሞት ነፍሱ ወድያውኑ ነው ወደ ጀሐነም ወይም ጀነት የምትገባው ?

አንድ ሰው ሲሞት ነፍሱ የምትቆይበት ቦታ አለ እንደ ትራንዚሽን ፔረድ ይህ አለም በርዘህ ይባላል እናም እንደሰውየም መልካም ስራ እና እኩይ ተግባር ድሎት እና ቅጣት በቀብር ውስጥ አለ ::

Quote:
123) ያልተቀበረ ሰው ነፍስ እረፍት የላትም የሚባለውስ ምን ያህል እውነት ነው ?
ይህን አላውቅም ቶሎ መቀበር እንዳለበት ግን ሰምቻለሁ ::

Quote:
124)አንዳንድ ጊዜ በተለይ የሙስሊሞች መቃብር በሌለበት ቦታ በክርስትያን ወይም በሌሎች እምነት ተከታዮች የመቃብር ቦታ የሚቀበሩ ሙስሊሞች ይኖራሉ ::በሁለቱ መካከል ልዩነት አለ ወይ ?

ልዩነት ይኖራል ብየ አልገምትም ::ቀብር ለሙስሊሙም ለክርስቲያኑም እኩል የሚያድረግ ሀብታም እና ደሀ እኩል የሚያደርግ መሆኑን እናውቃለን ነገር ግን ወንጀለኛ የሆነ እና ያልሆነ አብረው ተጠጋግተው ሲቀበሩ ምን ያህል ሳይድ ኢፌክት ሊኖረው እንደሚችል አላውቅም ልክ እንደ መጥፎ ጎረቤት ማለት ነው ይህ የግሌ አስተያየት እንጅ በጉዳዩ ላይ ኢስላማዊ እውቀት የለኝም ::

Quote:
125)በኢስላም አንድ ሰው ጠላቴ በሚለው ሰው ሞት መደሰት ይፈቀድለታል ?

ጠላት ማለት ብዙ ትርጉም አለው በሞቱ የምትደሰትበት እና የማትደሰትበት ጠላት አለ ::ለምሳሌ ፊርአውን ታላቅ ጠላት ነበር እሱ ሞት መደሰት አስፈላጊ ነው ምክንያቱም እኔ ጌታ ነኝ ከማለቱም በተጨማሪ ብዙ አማኞችን ያሰቃይ ነበር ::ነገር ግን ይህም የግሌ አስተያየት እንጅ ኢስላም ምን ይላል የሚለው እውቀቱ የለኝም ::ጥያቄዎችህ ትንሽ ከበድ እያሉ መጡ :ብዙ ጊዜ እኔ ትኩረት አድርጌ የምማረው ማንኛውም ሙኡስሊም ሊያውቀው አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ነው ::በመጠየቅህ ግን ደስ ብሎኛል ::

Quote:
126)በህፃንነታቸው የሚሞቱ ልጆች በሙሉ ጀነት ይገባሉ ሲባል ሰምቼ ነበር እውነት ነው ?

እኔም ሰምቻለሁ ::

Quote:
127)አንድ ሰው ሙስሊም ነኝ ካለ የራሱ ምስክርነት በቂ ነው ወይስ ሌሎች ሁኔታውን አይተው ይህ ሰው ሙስሊም አይደለም የማለት መብት አላቸው ?

በኢስላም አንድ ሰው ሙስሊም ነው አይደለም ማለት አደጋ አለው ሙስሊም ካልነበረ እና ወደ ኢስላም ሲመጣ እውነት የሚያመልኩት ጌታ ከላህ በስተቀር የለም ሙሀመድ እና ኢሳ የአላህ ሰላም ይውረድላቸው እና መላክተኛ ናቸው ብሎ የመሰከረ ሰው ሙስሊም ነው እንለዋለን (የልቡን አላህ ነው የሚመረምረው )ከዚ ውሽ ያለን ካፊር የሆነን ሰው ካፊር ማለት ወንጀል አይደለም እኔ ሙስሊም ነኝ እያለ ያን የምስክርነት ቃል እየተናገረ እኛ ግን ካፊር ልንለው አንችልም ::ወንጀልም ነው ::

Quote:
128)አንድ ሰው እስልምናን ሳቀበል ቢሞት ሌላ እድል ይሰጠዋል ?በተለይ እንኳን ስለኢስላም ሊነገራቸው የእስልምናን መኖር ሳያውቁ የሞቱት

ኢስላም መኖሩን እያወቁ ሳይሰልሙ የሞቱ ሌላ እድል ፈጽሞ አይሰጣቸውም ::ሳያውቁ የሞቱ ፍጹም ያልሰሙ ግን ይሰጣቸው አይሰጣቸው እንደሆነ አላውቅም ::

Quote:
129)ሴቶች ሃይማኖታዊ ያልሆነ ሥልጣን ይፈቀድላቸዋል ?

ለሴቶች ስልጣን መስጠት ችግር የለውም ነገር ግን እይሀገር መሪነት የመሰለ ቁልፍ ቦታዎችን ለሴቶች የሚሰጡ ህዝቦች ከችግር ነፃ እንደማይሆኑ አንብቤያለሁ ምክንያቱም ሴቶች ከምክንያት ይልቅ በሀዘኔታ ስሜት ስለሚበለጡ እናም ጸባያቸው የሚቀያየርበት የተፈጥሮ ምክንያት ስላላቸው ሀገርን ቀጥ አድርጎ ለመምራት ይቸገራሉ ::በዚህም ጉዳይ በቂ እውቀት የለኝም
Quote:
130)የአንድ ወንድ ምስክርነት ከሁለት ሴቶች ምስክርነት ጋር እኩል ነው የሚባለውስ ?

በጣም እውነት ነው ::

Quote:
131)ባልና ሚስት ከተፋቱ በኋላ በድጋሚ ለመጋባት ቢፈልጉ በመሐሉ ሚስትዬው ሌላ ሰው ካላገባች አይቻልም ሲባል ሰምቼ ነበር ::ምን ያህል እውነት ነው ?

3 ፍች ከተፈታች አዎ !ይህ ማለት ሲኖሩ አልተስማሙም አንዴ ፈታት እና ተመለሰች ታረቁ እንደገናም ተጣሉ ለሁለተኛ ጊዜ ፈታት እና ታረቁ ለመሸረሻ ጊዜ ተጣልተው ከፈታት 3 ስለሚሆን መመለስ ቢፈልጉ ቢስማሙ እንኳ ሌላ ባል አግብታ ካልተፈታች በስተቀር እሱ ሊያገባት አይችልም ::ይህ ማለት ግን ገንዘብ ከፍሎ ድሮ በል ፍታልኝ ብሎ ማስፈታት ይችላል ማለት ግን አይደለም ::ኢስላም አንድን ነገር ሲፈቅድ ወይም ሲከለክል የራሱ ሎጅክ ምክንያት አለው ለሰው ልጆች ጥቅም ::እኛ ባናውቀው እንኳ የምናውቅበት ጊዜ ይመጣል ::

Quote:
132)ከዚህ በፊት ነቢያችሁ ሙሐመድ ጀነት እንደሚገቡ የመሰከሩላቸው ግለሰቦች እንዳሉ ነግረኸኝ ነበር ::በእርግጠኝነት ጀሐነም ይገባሉ ያሏቸው ሰዎችስ አሉ ?

አዎ !

Quote:
133)መስቀል የቤተ ክርስትያኖች መለያ እንደሆነ ሁሉ ጨረቃና ኮከብ ደግሞ የመስጊዶች መለያ ናቸው ::በክርስታና መስቀልን ግለሰቦችም ይጠቀሙበታል (በሐብል ላይ በቀለበት ቤታቸው ግድግዳ ላይ ወዘተ ) ሙስሊሞችስ ?

አይጠቀሙበትም :ሙስሊም ወንድ በተለይ አንገቱ ላይ ምንም ማንጠልጠል የለበትም ሴቶች ግን እንደጌጥ ሊጠቀሙበት ይችላሉ ::በተረፈ ጨረቃን አላህ ሲፈጥራት በወር መጀመሪያ የመወለድ እና 15 ቀን ላይ ሙሉ የመሆን ከዚያ እየጎደለች የመሄድ ፀባይ ስላላት ጾም ለመግባት እንደምልክትነት እንጠቀምባታል እንጅ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች ለመስቀል እንደሚሰጡት ክብር እና እና አምልኮ ለጨረቃም ይሁን ለኮከብ በኢስላም 0.00001% ግምት አንሰጥም ::አናመልካቸውም ::በተለምዶ ይሆናል እንጅ እንደሙስሊሞች መለያ በኢስላም ይታያሉ የሚል አላነበኩም ::

Quote:
134)በኢስላም ለህክምና ጉዳይ ደም መስጠት ወይም መቀበል እንዲሁም የሰውነት ብልቶችን (ጉበት ኩላሊት ወዘተ )ማስቀየር ይፈቀዳል ?

አዎ ይፈቅዳል ::ቅድመ ሁኔኤታዎች ግን ይኖሩታል ::

Quote:
135)ከዚህ በፊት ቁራን ላይ ያሉ ብዙ ነገሮች በሳይንስ ተረጋግጠዋል ያልከኝ መሰለኝ ::ቁርአን ላይ ፀሐይ መሬትን እንደምትዞር ተጽፏል የሚባለው እውነት ነው ?

ለነብዩ ሙሐመድ (..)ከተሰጡዘለአለማዊ ተአምራት ውስጥ አንዱ ቁር አን ነው ያልተሳፈበት ነገር የለም :በተለይ እጅግ በጣም የሚገርመኝ ሁለት ባህሮች እንዳይገናኙ በመካከል ላይ መጋረጃ አልለ ስለዚህ አይደባለቁም የሚለው እና ሮም ትሸነፋለች ከተሸነፈች በኍላ ግን እሱዋ እንደገና ታሸንፋለች የሚለው የቁር አን ቃል በጣም ይገርመኛል ተፈጽሟል ::ሌላው ፈር ኦንን ዛሬ አንተ ነጻ የምትወጣው እሬሳ ሆነህ ነው እናም ለተአምር እናስቀምጥሀለን የሚለው አንቀጽ እስከ አሁን ፈሮ ኦን ያለ ኬሚካል በዚህ ይዘቱ ለመቆየቱ ቁር አን ተአምር ነው እጅግ ብዙ ተአምሮች አሉ ያልከውም ነገር ተጠቅሷል ይህ ዩኒቨርስ በፍንዳታ እና ጭስ መሰል ነገር ከተከሰተ በሁዋላ እንደተፈጠረ የተናገረው እውነታም ሳይንስ ዛሬ ላይ አረጋጦታል ::ስለ ሰው ልጅ የጽንስ አቀማመጥ ቁር አን በትክክል እንደገለሠው ሳይንስም ዛሬ አረጋጦል ::ጉንዳን በነብዩ ስለሞን ጊዜ የሰለሞን ወታደር እንዳይሰባብራጩ ብላ ስትናገር እንዴት ጉንዳን እንደ መሳወት ሰበራለች በማለት የተሳለቁ ሰዎች በሩ ሳይንስ አረጋግጧል ::ብዙ መጥቀስ ይቻላል

Quote:
136)በአሁኑ ዘመን የማይሰሩ የቁርአን አንቀፆች አሉ ?

ቁር አን ለሁሉም ዘመን ነው የወረደ ::በአሁን ዘመን የማይሰሩ የሚባል ነገር የለም ::ለሁሉም ዘመን እንዲስማማ ተደርጎ ነው የተላከ ::ነገር ግን አንዱ አንዱን እየሻረ የተከለከለው እየተፈቀደ የተፈቀደው እየተከለከለ በህግነት የሰደቀው በዚያው መሰረት ይተገበራል ለምስሌ አስካሮኢ መጠጥ ያልተከለከለበት ጊዜ ነበር በኍላ ግን ተከለከለ ለዚህም እጅግ ውብ እና ማራኪ የሆነ ምክንያት አለው ::ከዚህ ውጭ ግን ቁር አን ኤክስፓየሪ ዴት የለውም !!!

Quote:
137)በአገራችን በርካታ ወራት ያስቆጠረ የሙስሊሞች የመብት ጥያቄ እንቅስቃሴ አለ ::ከጥያቄዎቹ አንዱ የመጅሊስ ምርጫ ነው ::በነቢዩ ዘመንና ከሳቸው ሞት በኋላ መጅሊስ የሚባል ተቋም ነበረ ?ምርጫውስ የሚካሄደው የት ነበር ?

መጅሊስ ማለት የሙስሊሞችን ጉዳይ የሚመራ ተቃም መሆኑ ይታወቃል :: ነብዩ ጊዜ ተመሳሳይ በሆነ መልኩ የምክክር አባላት እንዳሉ እና በሙስሊሙ ጉዳይ እንደሚመካከሩ አውቃለሁ መዋቅሩ ግን ተመሳሳይ ይሁን አይሁን አላውቅም ::

Quote:
138)ዓለም አቀፍ መጅሊስስ አለ ?
የሙስሊሞች የምሁሮች ምክር ቤት አለ

Quote:
139)በኢስላም ሰው ሲሞት ወይም የሞተ ሰው ሥም ሲነሳ ነፍስ ይማር ይባላል ወይ
? የሞተው ሙስሊም ከሆነ አዎ !!

Quote:
140)አንድ ሙስሊም የሌላ እምነት ተከታዮች በዓላቸውን ሲያከብሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት ማቅረብ ይችላል ?ወይስ እንደ በዓላቱ ዓይነት የሚወሰን ጉዳይ ነው ?

እንደ በአል አይነቱ ይወሰናል ለምሳሌ ስቅለትን ውሰድ በመሰቀሉ የማናምነውን እንኳን አደረሳችሁ አንልም ..
ዘርአይ የሙስሊሙን ህብረተሰብ ጥያቄ እንዴት ታየዋለህ ? የጥቂቶች ነው ብለህ ታምናለህ
ወይስ የመላው ሙስሊም ህብረተሰብ ?
ከብዙ ምስጋና ጋር
_________________
HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1087
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Nov 19, 2012 8:21 pm    Post subject: Reply with quote

ሱልጣን እንደጻፈ(ች)ው:

ዘርአይ የሙስሊሙን ህብረተሰብ ጥያቄ እንዴት ታየዋለህ ? የጥቂቶች ነው ብለህ ታምናለህ
ወይስ የመላው ሙስሊም ህብረተሰብ ?
ከብዙ ምስጋና ጋር

በድጋሚ ሰላም እያልኩ መልሱ ላይ ሌላ ጊዘ አስተያየት እስከምሰጥ ለጊዜው ከላይ ለጠየቅከኝ አንተ አላገጠመህ ይሆናል እንጂ ከዚህ በፊት አንድ ሁለት ቦታ ላይ አስተያየት ሰጥቼበት ነበር :: አንደኛውን በቅርብ ስላገኘሁት ሊንኩን ተመልከት ::

http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=49289
_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3
Page 3 of 3

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia