WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ዋኖስን አፋልጉኝ

 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ


 
View previous topic :: View next topic  
Author Message
ወለላዬ

ዋና ኮትኳች


Joined: 26 Jan 2005
Posts: 519
Location: united states

PostPosted: Tue Jun 26, 2012 4:33 pm    Post subject: ዋኖስን አፋልጉኝ Reply with quote

የዛሬ ሰባት አመት ዋኖስ ጠፍቶብኝ ይሄንን ጽፌ ነበር አሁንም ስለጠፋ ይሄንን መለጠፍ ግድ ሆነብኝ ጥልቁስ የት ደረሰ አቤት በዛ ወርቃማ የስነጽሁፍ አመት የነበረ ጽሁፍ ለማንኛውም ዋኖስን አፋልጉኝ

ዋኖስን አፋልጉኝ

ስነጽሁፍ መንደር አጣሁት ጠፋብኝ
አረ ምን ሆኖ ነው ዋኖስን አፋልጉኝ
ተናግሮ ነበረ አስቀድሞ በፊት
አባይን ተሻግሮ ገብቶ እንዳይሆን ዳሞት
እማንኩሳ ደብር እመርጦ ለማሪያም
አመቱን ጠብቆ ሄደ ወይ ሊሳለም
እከተሞው ይሆን ወይስ ደብረማርቆስ
ስንቄን ጨርቄን ሳይል የበረረው ዋኖስ
ወይንስ ጣና ዙርያ ዘለቀ ባህር ዳር
እነዛ አዋቂዎች እደጋጎች ሀገር
ይሆን ወይ ምናልባት አለዛስ ቢቸና
ለሰው ሳያማክር ሊቀበል ቅስና
ከአለቃ ክንፉ ከየኔታ ሀብተወልድ
ፊቱኑ ሳስበው ይመስለኛል ዘመድ
መምህር ለአከ መሪጌታ ሀብቱ
አይቀሩም ሳይሆኑ አባቱና አጎቱ
አፈሊቅ እንግዳ ብላታ ይሄይስ
የቅርቦቹ ናቸው ምናልባት ለዋኖስ
እነሱን ፍለጋ ከሄደም ንገሩኝ
እስቲ ሁላችሁም ዋኖስን አፋልጉኝ
This message expresses the views and opin
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ዋኖስ

ዋና ውሃ አጠጪ


Joined: 16 Nov 2004
Posts: 1571
Location: Mars

PostPosted: Mon Jul 02, 2012 11:01 pm    Post subject: Re: ዋኖስን አፋልጉኝ Reply with quote

ግልባጭ :

ለአፍቃሬ - ኢትዮጵያዉያንና /ያትወለላዬ እንደጻፈ(ች)ው:
የዛሬ ሰባት አመት ዋኖስ ጠፍቶብኝ ይሄንን ጽፌ ነበር አሁንም ስለጠፋ ይሄንን መለጠፍ ግድ ሆነብኝ ጥልቁስ የት ደረሰ አቤት በዛ ወርቃማ የስነጽሁፍ አመት የነበረ ጽሁፍ ለማንኛውም ዋኖስን አፋልጉኝ

ዋኖስን አፋልጉኝ

ስነጽሁፍ መንደር አጣሁት ጠፋብኝ
አረ ምን ሆኖ ነው ዋኖስን አፋልጉኝ
ተናግሮ ነበረ አስቀድሞ በፊት
አባይን ተሻግሮ ገብቶ እንዳይሆን ዳሞት
እማንኩሳ ደብር እመርጦ ለማሪያም
አመቱን ጠብቆ ሄደ ወይ ሊሳለም
እከተሞው ይሆን ወይስ ደብረማርቆስ
ስንቄን ጨርቄን ሳይል የበረረው ዋኖስ
ወይንስ ጣና ዙርያ ዘለቀ ባህር ዳር
እነዛ አዋቂዎች እደጋጎች ሀገር
ይሆን ወይ ምናልባት አለዛስ ቢቸና
ለሰው ሳያማክር ሊቀበል ቅስና
ከአለቃ ክንፉ ከየኔታ ሀብተወልድ
ፊቱኑ ሳስበው ይመስለኛል ዘመድ
መምህር ለአከ መሪጌታ ሀብቱ
አይቀሩም ሳይሆኑ አባቱና አጎቱ
አፈሊቅ እንግዳ ብላታ ይሄይስ
የቅርቦቹ ናቸው ምናልባት ለዋኖስ
እነሱን ፍለጋ ከሄደም ንገሩኝ
እስቲ ሁላችሁም ዋኖስን አፋልጉኝ
This message expresses the views and opin

ከሁሉ አስቀድሜ ይድረስ ሰላምታዬ፣

ሰላምና ጤና፤ ፈንጠዝያ ሕይወት፤ ለጋሽ ወለላዬ።

ዓመታት ቢሮጡ ዘመናት ቢበዙ ለቁጥር ቢያስቸግር፣

ሃምሳና ስድሳ ዓመት ቢኖሩ ዉጭ ሃገር፣

ከቶ እንዴት ይረሳል ? ያደጉበት ሰፈር።

ወንዙ ሸንተረሩ፣ ሜዳና ዳገቱ፣

አቀበት፣ ቁልቁለት መዉረዱ መዉጣቱ፣

ከቶ እንዴት ይረሳል ? ዛፉ ምልክቱ።

እንኳን ሕይወት ያለዉ ያገር ሰው ይቅርና፣

ተፈጥሮን ስታደንቅ የተቀመጥሕበት ቀምበጡ ብሳና፣

ዉል፣ ዉል፣ ይል አይደል፤ ሱስ እንዳለበት ሰዉ የሚጠጣ ቡና።

“አለሌ አሕያና ወንድ ልጂ አንድ ነው፣

ሃገሩን አይረሳም በሕይወት እስካለ ከኖረ በጤናው”።

ያሉኝ ትዝ ይለኛል፤ የጎጃሙ ንጉስ የዋሸራዉ ጌታ፣

የቅኔዉ ባላባት፤ ጥንት ጆሮዬን ያሹኝ የኔታ ብላታ።

እረ ! ስንቱን ልበል እረ ስንቱን ላንሳ፣

የቱን ነው ምተወዉ ? ስለምን ላወሳ፣

የጥበብ አዝመራ የቅኔ ቡቃያ፣

ያፈራዉን አገር የምሥራቋን ጮራ፣ ሃገረ -ኢትዮጵያ፣

እንዲያዉ በደፈናዉ አምላክ ይጠብቃት፤ ቃል የለኝም ለኔ መግለጫ መተኪያ።


በስተመጨረጫም፤


ስንኝ መቋጠሬን ሳልገድብ እዚህ ጋ፣

ታላቁን ወዳጄን የዋርካዉን ዜጋ፣

ሊቅ -ዋናዉ ጠፍቶኛል፤ እንዲያዉ በነካ እጅህ “አፋልጉኝ” ይለጠፍ መጦም እንዲያወጋ ::
Last edited by ዋኖስ on Tue Jul 03, 2012 11:20 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ሳምራውው 33

ዋና ኮትኳች


Joined: 21 Jun 2007
Posts: 533

PostPosted: Tue Jul 03, 2012 11:34 am    Post subject: Reply with quote

ግራዋ

እኔም ከደጃፌ ግራዋ ተክዬ
ከትንሽነትዋ ያሳደክዋት ጥሬ
ከቤታችን ደጃፍ ያለችው ግራዋ
ተንዠርግጋ አድጋ በቅጠል ተውባ
ትኖር ነበር አምራ ጌታዋን ተማምና
የእህል ውሀ ነገር ሆነና ነገሩ
እዛው ትቼአት ወጣው ከአገሩ
መቼም ሰው አይኖርም ሁሌም እንዳሳቡ
ይለቃል ይተዋል የትውልድ መንደሩን
ከብዙ አመታት መለየት ቦሀላ
ተመልሼ ብሄድ ወደኌላ
ትኖር አትኑር ብሎ ልቤ እየፈራ
ነገር ተለዋውጦ ቅኔው ተለውጦ
ግራዋዋን ትልቅ ኮንዶሚንየም ውጦ
ጠበቀኝ አፍጥጦ Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes


ነገሮች ተለዋውጠው ለጠበቋችሁ ሁሉ ምሳሌ ትሁን Exclamation Exclamation Exclamation
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

 
Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum


Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia