WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ዊኪሊክስ 2.4 ሚልዮን የሶርያ ፋይሎችን እየለቀቀ ነው

 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ


 
View previous topic :: View next topic  
Author Message
ዊኪሊክስ

አዲስ


Joined: 09 Mar 2012
Posts: 41

PostPosted: Thu Jul 05, 2012 7:18 pm    Post subject: ዊኪሊክስ 2.4 ሚልዮን የሶርያ ፋይሎችን እየለቀቀ ነው Reply with quote

ዛሬ ጁላይ 5 , 2012 ዊኪሊክስ ሶርያን የሚመለከቱ 2.4 ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ሚስጥራዊ ኢሜሎችን መልቀቅ እንደጀመረ አስታውቋል :: እነዚህ ኢሜሎች 2006 እስከ 2012 ያለውን ጊዜ የሚሸፍኑ ሲሆን ለሶርያ መንግስት እንዲሁም ለሶርያ መንግስት ተቃዋሚ ነን ባዮች ትልቅ እፍረትን ሊያስከትል እንደሚችል ጁልያን አሳንጅ እስካሁን ተጠልሎ ከሚገኝበት በለንደን የኤክዋዶር ኤምባሲ ሆኖ ተናግሯል :: ዊኪሊክስ እነዚህን ኢሜሎች ለህዝብ ሊለቅ የወሰነው ሶርያ ውስጥ ትልቅ የእርስ በርስ ጦርነት ባለበት ሰዐት ሲሆን 2011 መግብያ ጀምሮ ብቻ 10 በላይ የሚሆን ህዝብ አልቋል :: ዊኪሊክስ ከዚህ በፊት የአለም መንግስታትን በአደባባይ የሚያሳፍሩ ሚስጥሮችን ለህዝብ በማውጣት የሚታወቅ ሲሆን ከአሜሪካው AFP, ከፈረንሳዩ owni, ከጣልያኑ Espresso, ከሊባኖሱ al akbhar እንዲሁም ከግብጹ al masry ጋዜጣዎችጋ በትብብር መስራቱን ቀጥሏል ::
የዊኪሊክሱ ዋና አለቃ ጁልያን አሳንጅ አሜሪካን ወደ አገሯ አስመጥታ የሞት ፍርድ ልታስፈርድበት እንደምትችል በመፍራት በለንደን የኤክዋዶር ኤምባሲ ውስጥ ጥገኝነትን በመጠየቅ ላይ ይገኛል :: የለንደን ፖሊሶች ከኤምባሲው ውጪ ጁልያንን ወደ እስር ቤት ለመክተት አሰፍስፈው በመጠበቅ ላይ ናቸው ::
_________________
"If journalism is good, it is controversial, by its nature." Julian Assange
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዊኪሊክስ

አዲስ


Joined: 09 Mar 2012
Posts: 41

PostPosted: Sat Jul 14, 2012 3:45 am    Post subject: Reply with quote

ዊኪሊክስ ላለፈው አንድ አመት ተኩል ህዝቡ እርዳታ እንዳያደርግለት ከአሜሪካ መንግስት በመጣ ግፊት የክሬዲት ካርድ ካምፓኒዎች visa እና master card ካርድ እንዲሁም የኦንላይኑ ገንዘብ አስተላላፊ paypal, የአሜሪካ ትልቁ ባንክ bank of america ማንኛውም ሰው በእነሱ በኩል ለዊኪሊክስ ገንዘብ በቀላሉ እንዳያስተላልፍ ከልክለው ቆይተዋል :: ይህም ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ህገ ወጥ የሆነና ነጻ በሆነው የምዕራቡ አለም አንድ ሰው ለፈለገው ካምፓኒ የገዛ ገንዘቡን እንዳይለግስ የሚከለክል ነው :: በዚህም ምክንያት ዊኪሊክስ 90 ፐርሰንት በላይ የሚሆነውን ገቢውን አጥቶ ቆይቷል :: ዊኪሊክስን በነጻ የሚያገለግሉ በአለማችን አሉ የተባሉ ምርጥ ጠበቃዎች ይህንን በየፍርድ ቤቱ ሲከራከሩ ቢቆዩም የአሜሪካ መንግስት ሆን ብሎ የፍርዱን ሁኔታ ሲያስተጓጉለው ቆይቶ በትላንትናው እለት ዊኪሊክስ የመጀመሪያውን ድሉን visa ላይ ፍርድ ቤት ውስጥ ተቀናጅቷል :: ይህ ፍርድ ሙሉ ለሙሉ visa የህዝቡን እርዳታ ተቀብሎ ፕሮሰስ አርጎ ለዊኪሊክስ እንዲሰጥ ግን አያደርግም ምክንያቱም በፕሮሰሱ ላይ ከአንድ በላይ የሚሆኑ የክሬዲት ካርድ ካምፓኒዎች ወይም ባንኮች የሚያስፈልጉ ሲሆን ፍርዱ ግን የተፈረደው ለጊዜው visa ላይ ብቻ ነው :: ሆኖም ከዛሬ ጀምሮ visa ፍርዱን ሳያከብር ቀርቶ እርዳታ መቀበል እምቢ ቢል በየቀኑ 6200 ዶላር ይቀጣል ::
_________________
"If journalism is good, it is controversial, by its nature." Julian Assange
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

 
Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum


Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia