WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ከእግር ኳስ ዓለም -ስፖርት ለፓስፖርት ኤርትራ ስታይል
Goto page Previous  1, 2
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Jun 29, 2012 2:29 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች :-

ቴዎድሮስ ገብረሥላሤ የጀርመኑ ቬርደር ብሬመን ክለብ ተጨዋች ሆኗል :: ከትላንት ወዲያ ወደዚያ ጎራ ብሎ ከክለቡ ማናጀርና ባለሥልጣኖች ጋር የመጀመሪያ ትውውቅ እንዲሁም የጤና ምርመራ አድርጓል :: ትልቁ ሕልሙ ከቬርደር ብሬመን ጋር የአውሮፓን የሻምፒዮናዎች ሊግ ውድድር ዋንጫ ማንሣት እንደሆነ ይፋ አድርጓል :: ይቅናው ::

ምንጭ :- Werder Bremen, 26 June 2012. Theo Gebre Selassie introduced.

Quote:
Things were hectic on the first day at Werder Bremen for Theodor Gebre Selassie, who will be called Theo in the future. At 10:20 a.m., he landed at Airport Bremen from Munich and headed to Sporthep Werder for the medical check-up and then in the afternoon he met at the business offices for a chat with manager Klaus Allofs that ended in the official presentation at Weser Stadium.

"I am happy to be here even though naturally I would rather be still playing at the Euro. Of the city, I actually only know the doctor, but today I will deal intensively with the tradition of this club and my new teammates. I will ask the head coach for a couple days to recover," said Gebre Selassie.

Head coach Thomas Schaaf immediately granted his wish. "He had a week off now without really being able to recover. So starting today he can take two weeks off," said the head coach, who has plenty of expectations for his new acquisition. "We want to experience him just like at the European Championship, where he showcased himself very well. He ran a lot, was active and regularly pushed forward. He will enrich our game from the defender position."

The outside defender also has high expectations on himself. "The Bundesliga is one of the best leagues in the world. I came here to persevere. After the offer from Werder, I knew that I didn't have to look around any more. It was my first offer and my first choice," said the Czech, who wants to excel. "Werder will have a young team, but the Champions League is without question a goal for which we should play."

And the Czech had to make clear on his first Werder day that he has no relation to the Ethiopian world class star runner Haile Gebreselassie and that he was not named after him. "There is nothing to those stories. I was born in the Czech Republic. Gebre Selassie is my surname from birth on. Other than a distant uncle, I don't have any connection to Ethiopia and haven't been there since I was three years old. And I don't have any recollections of that visit," said Gebre Selassie. It was not the first time he was asked about it.
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Jun 29, 2012 7:09 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም :-

ለትዝታ ያህል የሚከተለውን የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ውድድር ተመልከቱት :: ዘመኑ 42 ዓመታት በፊት ሰኔ 14 ቀን 1962 .. (June 21, 1970) ነበር :: ብራዚልና ጣሊያን 10ኛው የዓለም ዋንጫ ተፋላሚዎች ነበሩ :: በብራዚል በኩል ተሠላፊዎቹ :-
  1 ..... ፌሊክስ (በረኛ )
  2 ..... ብሪቶ
  3 ..... ፒያዛ
  4 ..... ካርሎስ አልቤርቶ (አምበል )
  5 ..... ክሎዶአልዶ
  16 ..... ኢቬራልዶ
  7 ..... ጃርዚኖ
  8 ..... ጀርሠን
  9 ..... ቶስታዖ
  10 ..... ፔሌ
  11 ..... ረቨሊኖ
ሲሆኑ በጣሊያን በኩል ደግሞ :-
  1 ..... አልቤርቶዚ
  2 ..... ቡሪኚች
  3 ..... ፋቼቲ
  13 ..... ዶሜኒጊኒ
  5 ..... ቼራ
  15 ..... ማዞላ
  16 ..... -ሲስቲ
  8 ..... ሮዛቶ
  2 ..... ቦኒንሴኛ
  10 ..... በርቲኒ
  11 ..... ሪቫ
ነበሩ :: በዚያ ውድድር ብራዚል በፔሌ (በጭንቅላት ገጭቶ 18ኛው ደቂቃ ) : ጀርሠን (66ኛው ደቂቃ ከርቀት መትቶ ያስቆጠራት ) : ጃርዞኖ (70ኛው ደቂቃ ) እና ካርሎስ አልቤርቶ (86ኛው ደቂቃ ) ባስቆጠሯቸው አራት ጎሎች አሸንፎ የጁሊዬት ሪሜትስን ዋንጫ የግሉ አድርጓል (ሌቦች ከብራዚል ፌዴሬሽንን ጽሕፈት ቤት በታኅሣሥ 9 ቀን 1976 .. [December 19, 1983] ባይሠርቁት ኖሮ ):: ጣሊያንን ከባዶ ከመሸነፍ ያዳናትን ጎል በመጀመሪያው ግማሽ 37ኛው ደቂቃ ቦኒንሴኛ ያስቆጠረው ነበር ::

ጨዋታውን ስትመለከቱ ብዙ የሚያዝናኑና የሚያስቁ ነገሮችን ትታዘባላችሁ :-
  # ..... ያኔ ጨዋታ የሚካሄደው በአንድ ኳስ ብቻ ነበር :: ኳስ ወደ ውጪ ከወጣች ኳሷ እስክትመለስ ድረስ መጠበቅ የግድ ነበር (ጥሩ ምሣሌ የሚሆነው ጨዋታው ሊጠናቀቅ 1 ደቂቃ ያህል ሲቀር ኳስ ወደ ተመልካች ተመታችና ተመልካቹ ቶሎ አልመልሣት ስላለ ተለዋጭ ኳስ እስኪመጣ ጥቂት ተጠበቀ ):: ነገር ግን የባከነ ጊዜ ተብሎ አይያዝም ነበር ::

  # ..... የተጨዋቾች ቁመና እንዳሁኑ ሣይሆኑ ከባታቸው ቀጠን : ጭናቸው ፈርጣማና ትከሻቸው ሠፋፊ ነበር :: ሲሮጡ ያስቃሉ ::

  # ..... ተጨዋች ተጎድቶ ወጌሻ ሲጠራ : በተለይ የብራዚሉ ወጌሻ ይዞ ወደ ሜዳ የሚመጣው በባልዲ ውሃ እና ፎጣ ነበር ::

  # ..... ፔሌ ጨዋታ ማቆሚያው ዘመን ላይ ተቃርቦ ስለነበረ ዋና ተግባሩ ገና ኳስ እንደያዘ አንድ የጣሊያን ተከላካይ እስኪመጣ ጠብቆ 'ተጠለፍኩ ' ብሎ መንከባለል ነበር ::

  # ..... ከብራዚል ቡድን ዋና አብዶኛ 11 ቁጥሩ ረቪሊኖ ሲሆን ጃርዞኖ ደግሞ ከአብዶ ጋር ፈጣን አጥቂ ነበር :: ሌሎቹ የብራዚል ተጨዋቾች አንዳንዴ ሲጫወቱ ፊልሙ 'slow motion camera' የተነሣ ይመስላል :: በተለይ የዚያ ዘመን ተከላካዮች ቀርፋፎችና ጅሎች ይመስላሉ Laughing

  # ..... ቅጣት ምት መምታት ምን ያህል እንደተሻሻለ ያኔ ከሚደነቁት ከእነ ፔሌ የቅጣት ምት አመታት ቀሽምነት ጋር እያነፃፀሩ ማዬት ይቻላል ::

  # ..... ጣሊያኖች ያኔ የሚታወቁበትን የካቴና አጨዋወታቸውን እና በተንኮል አጥቂን መጥለፍና መተናኮሉን በአሁንም ዘመን አልተውትም : ብራዚል ግን በቀላሉ በአጭር ቅብብል ይፈታባቸዋል ::

  # ..... ጎል ሲገባና ተጨዋቾች ሲጨፍሩ ፎቶግራፍ አንሺዎች ሜዳ ውስት ገብተው ፎቶግራፍ ያነሡ ነበር ::
ቀሪውን ለእናንተ ትቻለሁ ::

ምንጭ :- videocannelli, Published on Mar 28, 2012. Italia - Brasile (messico 70) Versione integrale completa a colori (10ኛው የዓለም ዋንጫ : ሰኔ 14 ቀን 1962 .. [June 21, 1970] : ሜክሲኮ -ሲቲ [ሜክሲኮ ] : ብራዚልና ጣሊያን )::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መጽናናት

ውሃ አጠጪ

Joined: 20 Aug 2004
Posts: 1354
Location: united states

PostPosted: Fri Jun 29, 2012 11:28 pm    Post subject: Reply with quote

ሁሉ ነገር የሚያምረው በጊዜው ለነበረው ነው በዝአም አለ በዚህ ብራዚል የአለማችን ቀጥር አንድ ቡድን ነው ወደ ስምንት ጊዜ ለፍጻሜ የደረሰ 5ቱን ፈስ በፈስ አድርጎ የወሰደ ቡድን ነው ;;እንደ አርጅቲና በገንዘብና በድራግ አደለም ለዚህ የበቁት በችሎታ እንጂ ;;
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu Jul 12, 2012 1:04 am    Post subject: Reply with quote

ሲያልቅ አያምር ::

በብራዚል እግር ኳስ አመራር ታሪክ ሁለት ሰዎች ለረዥም ጊዜያት ታላቅ ተፅዕኖ ማሣደር ችለዋል :- ጃኦ ሀቫላንጅ እና ሪካርዶ ቴክሢዮራ :: ሀቫላንጅ ከብራዚልም አልፈው የፊፋ ፕሬዘዳንት በመሆን 24 ዓመታት አገልግለዋል (... 1974 - 1998):: ከዚያ በፊት ሀቫላንጅ 16 ዓመታት ያህል (... 1958 - 1973) የብራዚል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ነበሩ :: ሀቫላንጅ ፊፋን የመሩበት ዘመን ለማኅበሩ ''ወርቃማ ዘመን " ተብሎ ተወድሷል :: በስፖርቱ ፈጣን እና መሠረታዊ የሆኑ ዓለም አቀፍ ለውጦች እንዲገኙ ጥሩ አመራር መሥጠታቸው ይመሠከርላቸዋል :: ለምሣሌ :-
  @ ..... የፊፋ ተግባር በየ 4 ዓመቱ የዓለም ዋንጫን ብቻ ማስተናገድ ሣይሆን የወጣቶችን (17 ዓመት በታች : 20 ዓመት በታች እና 23 ዓመት በታች ) የዓለም ዋንጫ : የሴቶችን የዓለም ዋንጫ እንዲሁም የዓለም የቤት ውስጥ እግር ኳስ ውድድርን በማስጀመር :

  @ ..... ፊፋን እንደ አንድ የንግድ ተቋም በመምራት በድህነት ከሚቸገር ድርጅት ወደ አትራፊ ኩባንያነት ቀይረውታል ::

  @ ..... በዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ውድድር የሚሣተፉ ቡድኖችን ቁጥር 16 ወደ 24 ከዚያም ወደ 32 እንዲያድግ አድርገዋል ::

  @ ..... ለዳኞች : ለአሠልጣኞች : ለእግር ኳስ ስፖርት አመራር ሠጪዎች ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ሥልጠናዎችን እንዲያገኙ በማድረግ :

  @ ..... 'የኮካ ኮላ ፕሮጀክት ' በሚባለው አማካይነት በተለይ የእግር ኳስ ስፖርት በደንብ ባልተደራጀባቸው አዳጊ አገሮች ለአዳጊ ሕፃናትና ለወጣቶች የእግር ኳስ ሥልጠናዎችን በማዘጋጀት :

  @ ..... ሌሎችም ...
እውን እንዲሆኑ አድርገዋል ::
ምንጭ :- FIFA.com, Friday 24 April 1998. Joã o Havelange steered FIFA into the golden age of football

የልጃቸው ባል የሆነው ቴክሢዮራ ግን የብራዚልን እግር ኳስ ሲመራ እምብዛም ተወዳጅነት የነበረው ሰው አልነበረም :: ይባስ ብሎ አማቱን በሙሥና ቅሌት አነካክቷቸዋል :: ታዲያ ዛሬ ስዊትዘርላንድ በሚገኝ ፍርድ ቤት ሁለቱ የብራዚል ዜጎች ቀደም ብሎ ለፊፋ የማስታወቂያ ሥራ ሲሠራ ከነበረ 'International Sports Media and Marketing (ISMM) Group (ISL)' ኩባንያ አግባብ ያልሆነ ጥቅም (ወደ 14 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ) ተቀብለዋል በሚል ክሥ ቀርቦባቸዋል ::

ምንጭ :- Canton of Zug Prosecutors Office. Translation of the Order on the Dismissal of the Criminal Proceedings of May 11, 2010 with the Public Prosecutors own Anonymisation.

መጨረሻቸው ምን ይሆን Question Question Question

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Aug 14, 2012 8:41 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች :-

ባለፈው ወር ትኩረታችንን ስቦ የነበረው የኢትዮጵያዊ ደም ያለው የእግር ኳስ ተጨዋጭ ቴዎድሮስ (ቴዶር ) ገብረሥላሤ ነበር :: ሠሞኑን ደግሞ አንድ ተጨምሮልናል :- ጌድዮን ዘለዓለም ይባላል :: ጌድዮን ጀርመን አገር ተወልዶ አድጎ ወደ አሜሪካን የተሻገረ ወጣት ሲሆን ለአሜሪካ የአዳጊ ወጣቶች ብሔራዊ ቡድን ተሠላፊ መሆን የቻለ ነው :: በጥረቱ ላይ ዕድል ተጨምሮበት ለእንግሊዙ ታላቅ የእግር ኳስ ክለብ ለአርሤናል ለመጫወት ፈርሟል :: አሁን አሁን ኢትዮጵያውያን በእግር ኳሱ ዓለም ታዋቂ መሆን እየጀመሩልን ነው ::

ምንጭ :- Posted by Meron, Sodere Blog, August 14, 2012 at 6:30am. Ethiopian Descent Gedion Zelalem Recruited by English Premier League club Arsenal.

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Sep 21, 2012 3:54 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

በዚህ ዓምድ ሥር አስተያዬት ካሠፈርኩ ሠንበትበት አልኩ ::

ቴዎድሮስ ገብረሥላሤ በዚህ የውድድር ዓመት ለተቀላቀለው የቬርደር ብሬመን ክለብ ወሣኝ ተጨዋች ለመሆን ጊዜ አልወሠደበትም :: ባለፈው ወር 'August 24, 2012' የእርሱ ክለብ ከአምናው የቡንደስሊጋ ሻምፒዮና ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ ጋር ባደረገው ግጥሚያ አንድ ግሩም ጎል በጭንቅላቱ ገጭቶ አስቆጥሯል ::

ምንጭ :- Soccer Highlights, 24 Aug 2012. Borusia Dortmund Vs. Werder Bremen.

ቴዲን እንዲቀናው ምኞቴ ነው ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon Dec 03, 2012 6:32 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

በዛሬው የስፖርት ዜና አስደማሚ የሆኑ ሁለት ርዕሰ -ጉዳዮችን አንብቤአለሁ :- ድሮ ድሮ 'ስፖርት ለፓስፖርት ' በሚባልበት ዘመን ውጪ አገር ሄዶ መጥፋት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾች ትልቁ ሕልማቸው ነበር :: አሁን አሁን ይህ የቀረ ቢመስልም የእኛን የቀድሞ የእግር ኳስ ተጨዋቾች የወደቀ አርማ የሚያነሱ አልጠፉም :- ከቀድሞዋ 14 ክፍለ -ሀገራችን ከኤርትራ :: ሰው ጥሩ ነገር ይኮርጃል እንጂ አገር ጥሎ ሽሽት እንደ ፋሽን ይኮርጃል እንዴት ?

ሌላው ደግሞ ወያኔ እና ሻቢያ የእግር ኳስ ተጫዋቾቻቸው በአሥመራ ሣባ ስቴድዬም እንዲጫወቱ የማይፈቅዱ ከሆነ ለተጫዋቾች የነፍስ -ወከፍ ጠመንጃ ይስጧቸውና ባድመ ላይ ይታኮሱ :: ያን ውጊያ ያሸነፈ ለሚቀጥለው ውድድር ይለፍ Cool ምክንያቱም ሁለቱም ዘረኛ አምባገነኖች ምንጫቸው ከኤርትራ ሆኖ እያለ አንዱ በኢትዮጵያ ገዢነት አዲስ አበባ የተቀመጠው ልክ ከሻቢያ ጋር ጥል እንደሆነ ያስመስላል :: ጦርነት ሲባል ግን 120,000 የድሃ ልጆችን ለሥልጣናቸው ዘመን ማራዘሚያ ጭዳ ያደርጋሉ Evil or Very Mad

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወርቅነች

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Oct 2010
Posts: 968

PostPosted: Tue Dec 04, 2012 7:07 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ዘነገድ - ዘረኛ ፈዛዝው ዘገምተኛው ተድላ Laughing

Quote:
ድሮ ድሮ 'ስፖርት ለፓስፖርት ' በሚባልበት ዘመን ውጪ አገር ሄዶ መጥፋት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾች ትልቁ ሕልማቸው ነበር ::

ድሮ ድሮ እንዳንተ ያለ ዝንጀሮ ሀገር ሲገዛ እውንትም ስፖርት ለፓስፖርት ነበር አሁን ግን በኛ በወያኔዎቹ ዘመን እስፖርት ለጤንነት ሆኗል Laughing Laughing ግን ለናንተ በርሜል ገፊ አደረጋችሁ ግን ትግሬ እንዳይንፋችሁ ትላለች ጀሚላ ከቸርችል ጎዳና Laughing Laughing

Quote:
ሌላው ደግሞ ወያኔ እና ሻቢያ የእግር ኳስ ተጫዋቾቻቸው በአሥመራ ሣባ ስቴድዬም እንዲጫወቱ የማይፈቅዱ ከሆነ ለተጫዋቾች የነፍስ -ወከፍ ጠመንጃ ይስጧቸውና ባድመ ላይ ይታኮሱ :: ያን ውጊያ ያሸነፈ ለሚቀጥለው ውድድር ይለፍ ምክንያቱም ሁለቱም ዘረኛ አምባገነኖች ምንጫቸው ከኤርትራ ሆኖ እያለ አንዱ በኢትዮጵያ ገዢነት አዲስ አበባ የተቀመጠው ልክ ከሻቢያ ጋር ጥል እንደሆነ ያስመስላል :: ጦርነት ሲባል ግን 120,000 የድሃ ልጆችን ለሥልጣናቸው ዘመን ማራዘሚያ ጭዳ ያደርጋሉ

አንተሰ ምን ቤት ነህ ....ፊሸካ ነፊ ነህ ወይሰ አጭብጫቢ ነህ አቃጣሪ መሆንህን አላጣንህም .... ሰንበቴ ቤት ሀሸር በሼር ነው እንዴ የበላሀው ....አፍህ እንዲህ የተኮላተፈው ትላለች ጀሚላ ከቸርች ጎዳና Laughingተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም የእግር ኳስ ስፖርት አፍቃሪዎች :-

በዛሬው የስፖርት ዜና አስደማሚ የሆኑ ሁለት ርዕሰ -ጉዳዮችን አንብቤአለሁ :- ድሮ ድሮ 'ስፖርት ለፓስፖርት ' በሚባልበት ዘመን ውጪ አገር ሄዶ መጥፋት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጨዋቾች ትልቁ ሕልማቸው ነበር :: አሁን አሁን ይህ የቀረ ቢመስልም የእኛን የቀድሞ የእግር ኳስ ተጨዋቾች የወደቀ አርማ የሚያነሱ አልጠፉም :- ከቀድሞዋ 14 ክፍለ -ሀገራችን ከኤርትራ :: ሰው ጥሩ ነገር ይኮርጃል እንጂ አገር ጥሎ ሽሽት እንደ ፋሽን ይኮርጃል እንዴት ?

ሌላው ደግሞ ወያኔ እና ሻቢያ የእግር ኳስ ተጫዋቾቻቸው በአሥመራ ሣባ ስቴድዬም እንዲጫወቱ የማይፈቅዱ ከሆነ ለተጫዋቾች የነፍስ -ወከፍ ጠመንጃ ይስጧቸውና ባድመ ላይ ይታኮሱ :: ያን ውጊያ ያሸነፈ ለሚቀጥለው ውድድር ይለፍ Cool ምክንያቱም ሁለቱም ዘረኛ አምባገነኖች ምንጫቸው ከኤርትራ ሆኖ እያለ አንዱ በኢትዮጵያ ገዢነት አዲስ አበባ የተቀመጠው ልክ ከሻቢያ ጋር ጥል እንደሆነ ያስመስላል :: ጦርነት ሲባል ግን 120,000 የድሃ ልጆችን ለሥልጣናቸው ዘመን ማራዘሚያ ጭዳ ያደርጋሉ Evil or Very Mad

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2
Page 2 of 2

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia