WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የኦርቶዶክስ አማኞች የሚያመልኩትን ለይተው አያዉቁም !
Goto page 1, 2, 3 ... 17, 18, 19  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ዘለቃሽ

አዲስ

Joined: 12 Feb 2005
Posts: 49
Location: ከአዲሲቷ ኢየሩሳሌም

PostPosted: Sun Apr 24, 2005 6:24 am    Post subject: የኦርቶዶክስ አማኞች የሚያመልኩትን ለይተው አያዉቁም ! Reply with quote

ልብ ብለው ካስተዋሉ በጣም የሚያስቅ ነው :: አብዛኛው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ይጾማሉ ለምን እንደሚጾሙ አያቁም : ወደ ቤተክርስቲያን ሄደው ደጅ ላይ ይሰግዳሉ ለምንና ለማን እንደሚሰግዱ ምክንያቱን አያቁትም : ስለሀይማኖታቸው ሲጠየቁ ከአባት ከቅመአያት ሲወርስ ሲዋረድ የመጣ <የጥንቷ ሀይማኖታችን ኦርቶዶክስ > ናት :: ከማለት ሌላ የተጨበጠ ነገር አይናገሩም :: የሀይማኖት ሁሉ መሰረት ከሆነው መጽሀፍ ቅዱስ አንዲት ጥቅስ ስለኦርቶዶክስ ጥንታዊነትና ቀዳሚነት እንዲያሳዩ ቢጠየቁ በራሳቸው ተጻፈ የተባለውን የተለየ የተሸፈነ <መጻሀፈ ሰማኒያ > ምናምን የሚባል ነገር ያወራሉ :: ይህን መጽሀፍ ማን ጻፈው ? ለመሆኑ / በመጨረሻ ማሳረጊያው ላይ ምን እንዳለ ያስታዋለ አለ ? <በተጻፈው ላይ ላይ አንዳች የሚጨምር ወይም የሚቀንስ በዚህ መጻሀፍ ላይ የተጻፈ እርግማኔ ሁሉ ይጨመርበታል > ይላል ::

ባለመጽሀፈ ሰማኒያ ኦርቶዶክሶችና በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ ተቀጽላ ልቦለድ የቀጠሉ ሞርሞኖች በፍርድ ቀን ምን መልስ ይኖራቸው ይሆን ??

ኦርቶዶክሶች ስለእምነታቸው አጥብቀው ከተጠየቁ ጣታቸውን ወደ ሀይማኖት አባቶች ይጠነቁላሉ :: አሊያም ለዱላ ይገባበዛሉ የስድብ ናዳ ያወርዳሉ :: ብዙ ርቀን ሳንሄድ ከሰሞኑ አንዱ እዚ ዋርካ ላይ <የጴንጤን አፍ የሚዘጋ የሀይማኖት አዋቂ ይፈለጋል !> ብሎ ባደባባይ ፖስት ያድረገው ምን ያህል በባዶ ዕምነት በባዶ ተስፋ እንደተሞሉ ያሳያል :: ነገሩ ያስቃል : ስለነፍሳችን በምናስበበት ጊዜ ግን የሚጠፋ ነፍስ ያሳዝናል :: እንደእውነቱ ከሆነ ግን ይህ ሕዝብ የሚለቀስለት ነው ::

ተነጋግረው ካልተማመኑና አፍ የሚያዘጋ <ፕሮፌሺናል ሰዳቢ > ተጋብዞ ከመጣ ምን ይጠበቃል ? እንዲህ ከሆነ አክራሪ ኢስላሞች <ጂሀዲስት > ሆኑ ማለት ነው ::

ለነገሩ <የሀይማኖትአባቶች > ተብዬዎቹ ሲጠየቁ የሚጠየቁትና የሚናገሩት አራምባና ቆቦ ነው :: ድሮ ጥንት የተማሯትን የተወሰነች ግዕዝኛ ጥቅስ ይጠቃቅሱና ሸፋፍነው ለማለፍ ይጣደፋሉ :: ትርጉሙን ሲጠየቁ የተባሉትና የሚናገሩት ነገር አይገናኝም :: የሚከራከራቸው አዋቂ አጋጥሟቸው ስለማያቅ አዲስ ተሟጋች ሲገጥማቸው በንዴት የከዘራቸውን አያያዝ ያስተካክላሉ ::

የሚገርመውና የሚያስቀው ግን ተራው ምዕመን ከሱ ሌላ <ክርስቲያን > እንደለለ ይናገራል :; እንዲያውም ሌላውን <መናፍቃን ጴንጤ > ይላል :: ትርጉሙን ግን ከተጠየቀ ዐይን ታች ላይ ይዋትታል :: መጽሀፍ ቅዱስ አንብቦ እንደሚያቅ ሲጠየቅም <እሱማ ለቄሶች ነው እነሱ ምን ሰርተው ይብሉ > የሚል ቀልድ ይናገራል :: አንዳንዱም <ጥቃቁሮቹ እንዳያስደነግጡኝ ተንተርሼ እተኛለሁ > ይላል ::

ዛሬ በዐለማችን ላይ ያሉ የማንኛውም ሀይማኖት ተከታዮች ስለሚያመልኩበት ነገር ጠንቅቀው የሚያውቁ ሲሆን ኦርቶዶክሶች ግን ምንም ሳያውቁ በተለምዶ ማምለካቸው ልዩ ያረጋቸዋል :: ቁራን ለእስልምና ተከታዮች በአረብኛ እንደሚነበብ ሁሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሶች ደግሞ መጽሀፍ ቅዱስን በግዕዝ ይጠቅሱና መንግስተ ሰማይን የጨበጡ ያስመስላቸዋል ::

መጽሀፍ ቅዱስ በግዕዝ ስለተነበበ ብቻ ክርስቶስ ራሱ ተናገረ ማለት አይደለም :: ቁራንኛም ቢሆን እንዲሁ አረብኛ ስለሆነ ስፔሻል የሚያረገው የለም :: ቅዱስ መጽሀፍ በነገድ በቋንቋ ሳይከፋፈል ለሁሉም በሚገባው በቃሉ የተተረጎመው የነፍስ የድህንነት ጉዳይ ስለሆነ በሚገባ እንዲረዳው ነው ::

ባገራችንም ኦሮሚኛን ሲዳሚኛን ወላይትኛን በትግሪኛን ጨምሮ 18 ቋንቋዎች ቃል በቃል የተረጎሙት ዛሬ <ጴንጤ > እየተባሉ የሚወገዙ ናቸው :: ምክንያቱም በተስፋው ቃል መሰረት የምስራቹ ወንጌል እስትንፋስ ያለው ሁሉ በቋንቋው አምላኩን አውቆ እንዲያመልክ በማሰብ ነው ::

ለምንድ ነው ኦርቶዶክስ ባንድ በተወሰነ በሞተ ባፈጀና ጥቂቶቹ ብቻ የሚናገሩትን በግዕዝ ቋንቋ የሚያዋክቡት ? ይህን አባባሌን በትክክል የሚገልጸው <ማዋከብ > የሚል ቃል እንደሆነ አምንበታለሁ :: ምክንያቱም የማያውቀውን ሕዝብ በሚመቻቸው ቃል ለማጣመምና ለማሞኘት ስለሚቀል !

እዚህ ዋርካ ላይ እንክዋ አንዳንዶቹ ግዕዝኛ ጥቅስ ያመጡና ትርጉሙን ሲጠየቁ የሚነጋገሩበት አርዕስትና ፈጽሞ የማይመስል ምስራቅና መእራብ ዐይነት ሆኖ እንደሚገኝ ተሳታፊ ባልሆንም ብዙ ጊዜ አንባቢ በመሆን የተዛብኩት ነው ::

ሌላው የኦርቶዶክስ እምነት ትልቁ ባዶነት ክርስቲያን አማራ ብቻ እንደሆነና ኢትዮጵያ ማለት አማራ ብቻ እንደሆነ መስበካቸው ነው :: ቅዱስ መጽሀፍ የሰውን ልጅ በነገድ በብሄር ሳይከፋፍል ኦርቶዶክሶች ግን የአገርን ባንዲራ ከእምነት ጋር ያቆራኙታል :: የጠባብ ብሄረተኝነት ፖለቲካቸውን ከሀይማኖቱ ጋር ማዛመዳቸው ነው :: ሙስሊሙና ጴንጤው የኢትዮጵያን ባንዲራ ስላልያዙ ወይም በሀይማኖታቸው ስላላንጸባረቁ <ባንዳዎች : መጤ : ሰልባጅ ሀይማኖተኞች > ይሆናሉ ::

በነሱ ቤት ጥቁር ክር ባንገት ማንጠልጠል አርብና ሮብ ከጾሙ ጥዋትና ማታ በቀን ሁለቴ ካማተቡ በቤ /ቲያን ደጃፍ ከሰገዱ አለቀ ደቀቀ ! ግለሰብ አገር የመሰከረለት ክርስቲያን ነው :: አያሳዝንም ?????????
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዳሞት

ኮትኳች

Joined: 19 Oct 2003
Posts: 481
Location: ethiopia

PostPosted: Sun Apr 24, 2005 1:03 pm    Post subject: በሳቅ Reply with quote

Rolling Eyes በሳቅ ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
መቀስ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 17 Mar 2005
Posts: 63
Location: mexico

PostPosted: Sun Apr 24, 2005 1:42 pm    Post subject: መዝለቂያሽ ይላቀቅ ! Reply with quote

ስሚ ሥራ ከፈታሽ ጫት ላይ ነኝና ብቅ በይና ቡና አፍይልኝ :: ያወቅሽ መስሎሽ መጽሐፍ እያጠብሽ ከምታስጭብን ማለቴ ነው ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
karter

አዲስ

Joined: 14 Sep 2003
Posts: 12
Location: russia

PostPosted: Sun Apr 24, 2005 1:56 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችሁም ይሁን !
ሁሉን ቻይና ይቅር ባይ እግዚአብሄር ክብር ምስጋና ይድረሰው !
ወዲትዋ እህት አይም ውንድም ...ከሁሉም በላይ ራስህን \ሽን አዋቂ አድርግህ \ ስታቀርብ መታበይ አንደሆን መገንዘብ አለብህ \!!!""ትንሽ እውቀት አደገኛ ናት አገር ታጠፋለችና !""
ቅንተ \ ቅዱስ ሆነሽ ነው የሰውን እምነት የምትተቺው ? ሁናችንም መጽሐፍ ቅዱስን አንብበናል ...ሁላችንም ግን የምንረዳው እንደፈቀድን ስለሆነ ነው የምንለያየው ::አንቺ \ የጠቀስሽው ጥቅስ ራሱ በጽሐፍ ቅዱስ ወስጥ መጨመር ወይም መቀነስ ክልክል ነው ሰለሚለው ቃሉ የሚገኘው የዮሀንስ ራአይ ውስጥ ነው ይህም ቃል የተነገርው ዩሀንስ ራሱ ስለአየው ራአይ ስለሆነ የጽፈው ነው እንጂ በአጠቃላይ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ አይደለም ::በተጨማሪም የምመክርሽ \ ነገር ሰለ መጽሐፍ ቅዱስ አመጣጥና መነሻው ማወቁ የበለጠ ጠቀሜታ ያለው ይመስለኛል ::አለማወቅ ደግሞ ሐጢያት ወይም አስቂን አይደለም ...የማያውቀውና አዋቂው ማለው ?
እግዚአብሔር እውነቱን ይግለጽልሽ \
ደህና ሰንብቱ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጌታ ያለው .

ኮትኳች

Joined: 21 Feb 2005
Posts: 373
Location: antarctica

PostPosted: Sun Apr 24, 2005 5:00 pm    Post subject: Re: የኦርቶዶክስ አማኞች የሚያመልኩትን ለይተው አያዉቁም ! Reply with quote

ዘለቃሽ እንደጻፈ(ች)ው:
ልብ ብለው ካስተዋሉ በጣም የሚያስቅ ነው :: አብዛኛው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ይጾማሉ ለምን እንደሚጾሙ አያቁም : ወደ ቤተክርስቲያን ሄደው ደጅ ላይ ይሰግዳሉ ለምንና ለማን እንደሚሰግዱ ምክንያቱን አያቁትም : ስለሀይማኖታቸው ሲጠየቁ ከአባት ከቅመአያት ሲወርስ ሲዋረድ የመጣ <የጥንቷ ሀይማኖታችን ኦርቶዶክስ > ናት :: ከማለት ሌላ የተጨበጠ ነገር አይናገሩም :: የሀይማኖት ሁሉ መሰረት ከሆነው
መጽሀፍ ቅዱስ አንዲት ጥቅስ ስለኦርቶዶክስ ጥንታዊነትና ቀዳሚነት እንዲያሳዩ ቢጠየቁ በራሳቸው ተጻፈ የተባለውን የተለየ የተሸፈነ <መጻሀፈ ሰማኒያ > ምናምን የሚባል ነገር ያወራሉ :: ይህን መጽሀፍ ማን ጻፈው ? ለመሆኑ / በመጨረሻ ማሳረጊያው ላይ ምን እንዳለ ያስታዋለ አለ ? <በተጻፈው ላይ ላይ አንዳች የሚጨምር ወይም የሚቀንስ በዚህ መጻሀፍ ላይ የተጻፈ እርግማኔ ሁሉ ይጨመርበታል > ይላል ::

ባለመጽሀፈ ሰማኒያ ኦርቶዶክሶችና በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ ተቀጽላ ልቦለድ የቀጠሉ ሞርሞኖች በፍርድ ቀን ምን መልስ ይኖራቸው ይሆን ??

ኦርቶዶክሶች ስለእምነታቸው አጥብቀው ከተጠየቁ ጣታቸውን ወደ ሀይማኖት አባቶች ይጠነቁላሉ :: አሊያም ለዱላ ይገባበዛሉ የስድብ ናዳ ያወርዳሉ :: ብዙ ርቀን ሳንሄድ ከሰሞኑ አንዱ እዚ ዋርካ ላይ <የጴንጤን አፍ የሚዘጋ የሀይማኖት አዋቂ ይፈለጋል !> ብሎ ባደባባይ ፖስት ያድረገው ምን ያህል በባዶ ዕምነት በባዶ ተስፋ እንደተሞሉ ያሳያል :: ነገሩ ያስቃል : ስለነፍሳችን በምናስበበት ጊዜ ግን የሚጠፋ ነፍስ ያሳዝናል :: እንደእውነቱ ከሆነ ግን ይህ ሕዝብ የሚለቀስለት ነው ::

ተነጋግረው ካልተማመኑና አፍ የሚያዘጋ <ፕሮፌሺናል ሰዳቢ > ተጋብዞ ከመጣ ምን ይጠበቃል ? እንዲህ ከሆነ አክራሪ ኢስላሞች <ጂሀዲስት > ሆኑ ማለት ነው ::

ለነገሩ <የሀይማኖትአባቶች > ተብዬዎቹ ሲጠየቁ የሚጠየቁትና የሚናገሩት አራምባና ቆቦ ነው :: ድሮ ጥንት የተማሯትን የተወሰነች ግዕዝኛ ጥቅስ ይጠቃቅሱና ሸፋፍነው ለማለፍ ይጣደፋሉ :: ትርጉሙን ሲጠየቁ የተባሉትና የሚናገሩት ነገር አይገናኝም :: የሚከራከራቸው አዋቂ አጋጥሟቸው ስለማያቅ አዲስ ተሟጋች ሲገጥማቸው በንዴት የከዘራቸውን አያያዝ ያስተካክላሉ ::

የሚገርመውና የሚያስቀው ግን ተራው ምዕመን ከሱ ሌላ <ክርስቲያን > እንደለለ ይናገራል :; እንዲያውም ሌላውን <መናፍቃን ጴንጤ > ይላል :: ትርጉሙን ግን ከተጠየቀ ዐይን ታች ላይ ይዋትታል :: መጽሀፍ ቅዱስ አንብቦ እንደሚያቅ ሲጠየቅም <እሱማ ለቄሶች ነው እነሱ ምን ሰርተው ይብሉ > የሚል ቀልድ ይናገራል :: አንዳንዱም <ጥቃቁሮቹ እንዳያስደነግጡኝ ተንተርሼ እተኛለሁ > ይላል ::

ዛሬ በዐለማችን ላይ ያሉ የማንኛውም ሀይማኖት ተከታዮች ስለሚያመልኩበት ነገር ጠንቅቀው የሚያውቁ ሲሆን ኦርቶዶክሶች ግን ምንም ሳያውቁ በተለምዶ ማምለካቸው ልዩ ያረጋቸዋል :: ቁራን ለእስልምና ተከታዮች በአረብኛ እንደሚነበብ ሁሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሶች ደግሞ መጽሀፍ ቅዱስን በግዕዝ ይጠቅሱና መንግስተ ሰማይን የጨበጡ ያስመስላቸዋል ::

መጽሀፍ ቅዱስ በግዕዝ ስለተነበበ ብቻ ክርስቶስ ራሱ ተናገረ ማለት አይደለም :: ቁራንኛም ቢሆን እንዲሁ አረብኛ ስለሆነ ስፔሻል የሚያረገው የለም :: ቅዱስ መጽሀፍ በነገድ በቋንቋ ሳይከፋፈል ለሁሉም በሚገባው በቃሉ የተተረጎመው የነፍስ የድህንነት ጉዳይ ስለሆነ በሚገባ እንዲረዳው ነው ::

ባገራችንም ኦሮሚኛን ሲዳሚኛን ወላይትኛን በትግሪኛን ጨምሮ 18 ቋንቋዎች ቃል በቃል የተረጎሙት ዛሬ <ጴንጤ > እየተባሉ የሚወገዙ ናቸው :: ምክንያቱም በተስፋው ቃል መሰረት የምስራቹ ወንጌል እስትንፋስ ያለው ሁሉ በቋንቋው አምላኩን አውቆ እንዲያመልክ በማሰብ ነው ::

ለምንድ ነው ኦርቶዶክስ ባንድ በተወሰነ በሞተ ባፈጀና ጥቂቶቹ ብቻ የሚናገሩትን በግዕዝ ቋንቋ የሚያዋክቡት ? ይህን አባባሌን በትክክል የሚገልጸው <ማዋከብ > የሚል ቃል እንደሆነ አምንበታለሁ :: ምክንያቱም የማያውቀውን ሕዝብ በሚመቻቸው ቃል ለማጣመምና ለማሞኘት ስለሚቀል !

እዚህ ዋርካ ላይ እንክዋ አንዳንዶቹ ግዕዝኛ ጥቅስ ያመጡና ትርጉሙን ሲጠየቁ የሚነጋገሩበት አርዕስትና ፈጽሞ የማይመስል ምስራቅና መእራብ ዐይነት ሆኖ እንደሚገኝ ተሳታፊ ባልሆንም ብዙ ጊዜ አንባቢ በመሆን የተዛብኩት ነው ::

ሌላው የኦርቶዶክስ እምነት ትልቁ ባዶነት ክርስቲያን አማራ ብቻ እንደሆነና ኢትዮጵያ ማለት አማራ ብቻ እንደሆነ መስበካቸው ነው :: ቅዱስ መጽሀፍ የሰውን ልጅ በነገድ በብሄር ሳይከፋፍል ኦርቶዶክሶች ግን የአገርን ባንዲራ ከእምነት ጋር ያቆራኙታል :: የጠባብ ብሄረተኝነት ፖለቲካቸውን ከሀይማኖቱ ጋር ማዛመዳቸው ነው :: ሙስሊሙና ጴንጤው የኢትዮጵያን ባንዲራ ስላልያዙ ወይም በሀይማኖታቸው ስላላንጸባረቁ <ባንዳዎች : መጤ : ሰልባጅ ሀይማኖተኞች > ይሆናሉ ::

በነሱ ቤት ጥቁር ክር ባንገት ማንጠልጠል አርብና ሮብ ከጾሙ ጥዋትና ማታ በቀን ሁለቴ ካማተቡ በቤ /ቲያን ደጃፍ ከሰገዱ አለቀ ደቀቀ ! ግለሰብ አገር የመሰከረለት ክርስቲያን ነው :: አያሳዝንም ?????????

ዘልቃሽ የሰጠሽው ወይንም የሰጠህው አስተያየት በጣም ጥሩ እና እውነትነት የተሞላበት ነው ዋናው እና ትልቁ ነገር የኦርቶዶክስ የካቶሊክ የቡዲስት የእስላም የሚለው ነገር ሳይሆን መጽሀፍ ቅዱስ በዘመናት እንደሚናገረው ከሆነ እግዛብሄር አንድ ልጁን እየሱስ ክርስቶስን ወደምድር ለሰው ሁሉ መዳን ልኮል ይህንን የማዳን ጸጋ ሰው አምኖ እና ፈልጎ ከተቀበለው በምድር ላይ እያለ ሰላም , ደስታ ፍቅር እንዲሁም ሂወት በዝቶለት በሰማይ ላይ ደግሞ ከሞት በሆላ ጌታ መንግስቱን ያወርሰዋል
ይህን ህይወት የሚያገኙት ሰዎች እየሱስን የግል አዳኝ አድረገው የተቀበሉ እና መንፈስ ቅዱስ በሚሰጣቸው ዘላለማዊ ሀይል በቅድስና እና በንጽህና እርሳቸውን ለለዩ ብቻ ወይንም ልክ እንደዮሴፍ ቅድስናቸውን ይዘው እና ልብሳቸውን ጥለው ለሚሸሹ እንጂ ሀይማኖት ያላቸው ሰዎች አይደለም ይህንን ስል ሀይማኖት ቦታ የለውም ማለቴ ሳይሆን ግን ሀይማኖት ማለት ስርአት ማለት ነው , በድሮ ግዜ እነሀዋሪያ ፓውሎስ ፒተር እንዲሁም ሌሎች ቅዱሳኖች የተገለጠላቸውን እውነት ( የመዳን መንገድ እየሱስን ) በየቦታው ሲሰብኩ እርሱ ብቻ አንድ የመዳን መንገድ ለሰው ልጆች የተሰጠ እንደሆነ ሲናገሩ በዘመናቸው የዚያኔ እየሱስ የሚባል ሳይሆን ህዝበ አዳም የሚኖረው ያለመዳን ጸጋ በጣኦት አምልኮ እና በሞት ጥላ ስር ነበር ያንን እነፓውሎስ የሰበኩትን የመዳም መንገድ የተቀበሉ ለነርሱ ኮንቪዩዥን ሳይኖር በግልጽ እውነትን እየሱስን መንገድ ይዘው እነርሱን በአይናቸው ያዩትን በጀሮቸው የሰሙትን አብሮቸው የነብረውን እና የተገለጠላቸውን ሂወት በተግባር በቅድስና በንጽህና አምላካቸውን አስከበረውት ዛሬ በመንግስቱ ስር አብረውት በደስታ እና በፍቅር በሰላም በመንግስተ ሳማያት ይኖራሉ ,,, ዛሬ ግን በምድራችን ብዙ ሰው ክርስቶስ እየሱስን በታሪክ እና በማስ ሚድያ ያውቁታል ስለዚህ እንዲህ ተብሎ ስለእየሱስ ማዳን ሲነገር ሰው እንዲህ ይላል ,
እንዴ እነ ቤተሰቦቼ አባቶቼ እናቶቼ ቅድመ አያቶቼ ከጥንት ከድሮ አንስቶ ሀይማኖቶኝች ናቸው ስለዚህ እኔ ክርስቲያን ነኝ እኔ እየሱስን አውቃለሁ መጻሀፍ ቅዱስን አውቃለሁ የሚለውን ሰው የጌታ ብርሀን በመንፈስ ቅዱስ ሀይል እየሱስን እስካልገለጠልን ድረስ ልንፈራረድ አይገባም ይህንን ለበል , በማንኛውም ዘመን ቢሆን የመጽሀፍ ቅዱስን እውነት የሚገልጸው አንድ መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው
በተጨማሪም አንድ የመዳን መንገድ የሆነውን እግዛብሄር ለሰው ልጅ የገለጸለውን እውነት በትክክል ለእያንዳንዱ በምድር ላይ ለሚኖር ነፍስ የሚያሳየው እርሱ መንፈስ ቅዱስ ብቻ እንጂ ሌላ አይደለም ይህንን ጉዳይ የምለበት ሁኔታ እግዛብሄር በዘመናቱ ሁሉ የገለጸው የማዳን እውነ ዛሬ በስመ ሀይማኖት ስም ተደብቆ እና ተሰወሮ የሰውን ልጅ እየሱስ በግሉ ሳይገለጽለት ዘመናቱን ሁሉ በስጋ ህይወት ብቻ የነፍሱን ማዳን እንዳያገኝ ትልቅ እንቅፋት ሆኖበታል ይህም ሰው ሁሉ እየሱስ የተባለውን ጌታ ብዙው ሰው በኢንፎርሜሽን እንጂ በእውነት ስለማያውቁት ነው ዛሬ እግዛብሄር ለሰው ልጅ የገለጸው እውነት ሳይሆን የሚሰበከው
የኔ ሀይማኖት , የኦርቶዶክስ , የካቶሊክ የቡድስት , የእስላም ሀይማኖት ነው ይህን የሆነው እየሱስ በሀይማኖት ስም ሰዎች የርሱን እውነትነት ሳያውቁም አወቅውም ደብቀውታል አንድ ነገር ለበል እንዴት እየሱስ በድሮ ዘመን እና በአሁኑ ዘመን ለሰው ወይንም ለነፍስ

1)በድሮ ግዜ እየሱስ ማዳኑን ያዩ የዳሰሱ አንድ አምላክ አግዛብሄር ለሰው ልጅ ማዳን የገለጠው መሆኑን በዚያን ዘመን ሲኖሩ ለነበሩ ሰዎች ሲናገሩ ወይንም ሲሰብኩ የክርቶስ አዳኝነት ሲመሰከርላቸው ለነበሩ ጣኦት አምላኪ ነፍስ ሰዎች ለሰጌታ አዳኝነት ሂወት ሰጪ መሆኑን ሲነገራቸው እየሱስ የሚባል ነገር ስም እንኮን ሰምተው አያውቁም ነበር እና ታምሩም , ማዳኑን በሰው እንዲሁም በስሙ ሰውን ከሞት ማስነሳቱ በአይናቸው በማየታቸው እየሱስን የግል አዳኝ አንድረገው ይቀበሉታል ይህ ዘመን ያልኩት እየሱስ
ለመጀመሪያ ሲሰብክላቸው በነበረበት ሰአት ለነበሩ ሰዎች ነው
2)ከላይ እንደገለጽኩት በአሁኑ ዘመን ግን ስለእየሱስ አዳኝነት , ሰላም ሰጪነት , ደስታ ለጋሽነት ለነፍስ ሁሉ ሲወራ ይህ ወንጌሉን የሚሰውማው ሰው እንዲህ ይላል እንዴ እኔ እኮ ክርስቲያን ነኝ ወይንም እኔ የምድነው ወይንም ከጥፋት የምተፈው በእስልምና በሀይማኖት ነው እያሉ ይኖራሉ ነገር ግን አንድ መርዳት የሚኖርብን ነገር በምድር ላይ የሚኖረው ሰው የክርስቶስን የማዳን መንገድ በማወቅ ወይንም ባለማወቅ ቢለውጡትም ነገር ግን እየሱስ የማዳን መንገዱን አለወጠም , የትም የሀይማኖት አባል እንሁን ቡድስት , እስላም , ፔንጤ , ኦርቶዶክስ , የፈለገውን የሀይማኖት ስም ጠርተን እንኑር እያዳንዱ በምድር ላይ የሚኖረው ሰው በእግዛብሄር መንፈስ ቅዱስ እስካተዳሰሰ ድረስ እና እየሱስ አዳኝነቱን በግል እስካልተቀበለው ድረስ ማንም ሰው ወደ እግዛብሄር መድረስ አይችልም

ይህንን ምሳሌ ልስጥ ,
እየሱስን የግል አዳኝ አድርጎ መቀበል ማለት ምን ማለት ነው
አንድ ብርቱካን እንውሰድ
ብሩትካን ጣፋጪ መሆኑን ማንም ሰው ያውቀዋል ይህንንም ያወቀው ጣፋጪነቱን ቀምሶ እንጂ በወሬ ሰምቶ አይደለም ነገር ግን ስለብሩታክን ጣፋጪነት የማያውቁ ሰዎች እንኮን ቢኖሩ በምድር ላይ ብርቱካኑን ልጠው እስካልበሉ ድረስ ጣፋጪነቱን አያውቁም ብሩትካንን ጠረጸዛ ላይ ቁጭ አድርጎ ማየት እና ቀመሶ ማጣጣም 100% የተለየ ነው ብርቱካኑን የበላ እና የቀመሰ ሰው ስለብርቱካን ጣምን መናገር ይችላል ነገር ግን ጠረፔዛው ላይ ቁጭ አድርጎ ብርቱካኖን ብቻ የሚያይ ሰው ጣሙን ማወቅ አይችልም
መጽሀፍ ቅዱስ ጌታ ቸር መሆኑ ቀመሳቹህ እወቁ ይላል መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ስለእየሱስ , ሰላም ሰጭነት , ደስታ ሰጪነት , እንዲሁም እረፍት እና ሂወት ሰጭነት ይናገራል ነገር ግን የእየሱ ይህንን ነገሮች ሰጪነት ማወቅ የምንችለው እየሱስን የግል መድሀኒት አድረገን ስንቀበለው ብቻ ነው መጽሀፍ ቅዱስ ስለጌታቸን ይህንን ይላላ መዲሀኔአለም
ይህም ማለት እየሱስ የእያንዳንዱ ነፍስ ሰው አዳኝ ማለት ነው ነገር ግን ትርጉሙ ልገባን የሚችለው መጽሀፍ ቅዱስ ላይ የተገለጠው እውነት በሂወታችን
ተቀብለነው እስከተለማመድነው ድረስ ብቻ ነው ያለበለዚህ መጽሀፍ ቅዱስን እንኮን የምናውቀው በኢንፎርሜሽን ብቻ እንጂ የጌታ ቸረነቱን ቀምሰን አይተን አይደለም የትም ሀይማኖት እንሁን ባለንበት ሀይማኖት አባልነት ውስጥ ሆነን እየሱስ ጌትነቱን አዳኝነቱን በመንፈስ ቅዱስ ሀይል እውነቱን እስከለገጸለን ድረስ እያንዳንዳችን ሰዎች በእግዛብሄር መንፈስ ቅዱስ እስካልተዳሰስነ ድረስ እግዛብሄር ያዘጋጀውን የመዳን መንገድ ተቀብለናል ማለት አይደለም ይህንን መዳን መፈወስ ማወቅ የምንችለው ክርስቶስ እየሱስን የግል አዳኝ አድረገን እነደአለም መድሀኒትነቱ የጌታችንን ቸረነት ስንቀመሰው ስናውቀው ብቻ ነው ይህም ማለት እየንዳንዳችንን እስላም ቡዲስት , የፈለገ ሀይማኖት ይኑረን በመጨረሻው ዘመን የምንጠቀለለው ወደአንድ አግዛብሄር እንጂ ወይንም ወእደመንገስተ ሰማያት እንጂ ወደሌላ እግዛብሄር ወይንም ወደሌላ መገስተስማይ አንገባም ነገር ግን አንድ የምንጠየቀው ጥያቄ እንዳለ መዘንጋት የለብነም ይህም የእግዛብሄር ጥያቄ ነው ?
እኔ አንድ አዳኝ ላንተ ነፍስ መዳን በመስቀል ላይ ሞቶ በደሙ እንዲያጥብልህ ልጄን ልኬ ነበር የእርሱን የማዳን ደም እረግጠህ ነው የመጣህው ወይስ ? ያኔ መልሳችንን ለጌታ እግዛብሄር እንሰጣለን እግዛብሄር ከሞትነ በሆላ ሊፈርድብን የሚችለው
ሀጢያተኞች ስለሆነ ሳይሆን አንድ የመዳን መንገዱን እየሱስ ክርስቶስን የግል አዳኝ አድረገን ስላልተቀብለነ ብቻ ነው ምክንያቱም የሀጥያት መድሀኒት አድርጎ እርሱን ብቻ ነው የላከው ስለዚህ የሞት መድሀኒት እያለ መዳሂኒቱን አንቀበልም ብንል በራሳችንን ላይ ነው ሞትን የፈረድነው አምላክ ብርሀኑን ያብራልን እና የተቀረው ዘመናችንን ከጌታችንን ከመድሀኒታችን ከየሱስ ጋር ሆነን እንደንኖር መንፈስ ቅዱስ ይርዳን አሜን
ጌታ ያለው
አይቀር
ሰው ሀጢያትህን ሊሸፍንልህ ይችላል እየስሱ ግን ይሰርዝልሀል

ይህንን ጸሎት ከልብ እንጸልይ
If you want to accept Jesus Christ as your Savior and be born again, here is a sample prayer. Remember, saying this prayer or any other prayer will not save you. It is only trusting in Christ that can save you from sin. This prayer is simply a way to express to God your faith in Him and thank Him for providing for your salvation. "God, I know that I have sinned against you and am deserving of punishment. But Jesus Christ took the punishment that I deserve so that through faith in Him I could be forgiven. I turn away from my sin and place my trust in You for salvation. Thank You for Your wonderful grace and forgiveness - the gift of eternal life! Amen!"
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዳሞት

ኮትኳች

Joined: 19 Oct 2003
Posts: 481
Location: ethiopia

PostPosted: Sun Apr 24, 2005 7:06 pm    Post subject: ዋዉ ! Reply with quote

Rolling Eyes ዋዉ ! ፓስተር በየት መጡ !

ቅቅቅ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ማይኮል _

ኮትኳች

Joined: 10 Dec 2004
Posts: 283
Location: 102 Gerjji ave Addis Ababa

PostPosted: Sun Apr 24, 2005 7:25 pm    Post subject: Re: የኦርቶዶክስ አማኞች የሚያመልኩትን ለይተው አያዉቁም ! Reply with quote

ዘለቃሽ እንደጻፈ(ች)ው:

ለነገሩ <የሀይማኖትአባቶች > ተብዬዎቹ ሲጠየቁ የሚጠየቁትና የሚናገሩት አራምባና ቆቦ ነው :: ድሮ ጥንት የተማሯትን የተወሰነች ግዕዝኛ ጥቅስ ይጠቃቅሱና ሸፋፍነው ለማለፍ ይጣደፋሉ :: ትርጉሙን ሲጠየቁ የተባሉትና የሚናገሩት ነገር አይገናኝም :: የሚከራከራቸው አዋቂ አጋጥሟቸው ስለማያቅ አዲስ ተሟጋች ሲገጥማቸው በንዴት የከዘራቸውን አያያዝ ያስተካክላሉ ::

የሚገርመውና የሚያስቀው ግን ተራው ምዕመን ከሱ ሌላ <ክርስቲያን > እንደለለ ይናገራል :; እንዲያውም ሌላውን <መናፍቃን ጴንጤ > ይላል :: ትርጉሙን ግን ከተጠየቀ ዐይን ታች ላይ ይዋትታል :: መጽሀፍ ቅዱስ አንብቦ እንደሚያቅ ሲጠየቅም <እሱማ ለቄሶች ነው እነሱ ምን ሰርተው ይብሉ > የሚል ቀልድ ይናገራል :: አንዳንዱም <ጥቃቁሮቹ እንዳያስደነግጡኝ ተንተርሼ እተኛለሁ > ይላል ::

... በግዕዝ ይጠቅሱና መንግስተ ሰማይን የጨበጡ ያስመስላቸዋል ::

መጽሀፍ ቅዱስ በግዕዝ ስለተነበበ ብቻ ክርስቶስ ራሱ ተናገረ ማለት አይደለም :: ቁራንኛም ቢሆን እንዲሁ አረብኛ ስለሆነ ስፔሻል የሚያረገው የለም :: ቅዱስ መጽሀፍ በነገድ በቋንቋ ሳይከፋፈል ለሁሉም በሚገባው በቃሉ የተተረጎመው የነፍስ የድህንነት ጉዳይ ስለሆነ በሚገባ እንዲረዳው ነው ::

ባገራችንም ኦሮሚኛን ሲዳሚኛን ወላይትኛን በትግሪኛን ጨምሮ 18 ቋንቋዎች ቃል በቃል የተረጎሙት ዛሬ <ጴንጤ > እየተባሉ የሚወገዙ ናቸው :: ምክንያቱም በተስፋው ቃል መሰረት የምስራቹ ወንጌል እስትንፋስ ያለው ሁሉ በቋንቋው አምላኩን አውቆ እንዲያመልክ በማሰብ ነው ::

ለምንድ ነው ኦርቶዶክስ ባንድ በተወሰነ በሞተ ባፈጀና ጥቂቶቹ ብቻ የሚናገሩትን በግዕዝ ቋንቋ የሚያዋክቡት ? ይህን አባባሌን በትክክል የሚገልጸው <ማዋከብ > የሚል ቃል እንደሆነ አምንበታለሁ :: ምክንያቱም የማያውቀውን ሕዝብ በሚመቻቸው ቃል ለማጣመምና ለማሞኘት ስለሚቀል !

እዚህ ዋርካ ላይ እንክዋ አንዳንዶቹ ግዕዝኛ ጥቅስ ያመጡና ትርጉሙን ሲጠየቁ የሚነጋገሩበት አርዕስትና ፈጽሞ የማይመስል ምስራቅና መእራብ ዐይነት ሆኖ እንደሚገኝ ተሳታፊ ባልሆንም ብዙ ጊዜ አንባቢ በመሆን የተዛብኩት ነው ::

በነሱ ቤት ጥቁር ክር ባንገት ማንጠልጠል አርብና ሮብ ከጾሙ ጥዋትና ማታ በቀን ሁለቴ ካማተቡ በቤ /ቲያን ደጃፍ ከሰገዱ አለቀ ደቀቀ ! ግለሰብ አገር የመሰከረለት ክርስቲያን ነው :: አያሳዝንም ?????????

አባባሉ እውነት ስለሆነ በጣም አስቆኛል :: Laughing Laughing Laughing ኦርቶዶክሶች አለማወቃቸውን መቀበል ስለማይችሉና በደም የተወራረሰ ሀይማኖት ስለሚመስላቸው ነቄፌታን አይቀበሉም የሚገርመው ሌላውን አማኝ ሀይማኖት የለሽ ብሎ መጥራታቸው ነው :: ማነው ደብረ ዲማ ኦርቶዶክስ የሚባለው ግራ የሆነ ግዕዝኛውን አምጥቶ ሲዘፍንብን ከረመ :: ዘለቃሽ አንቺ - እንዳልሺው ግን አዙረን ስናስብ ይህ እንደበግ የሚነዳ ሕዝብ እውነትም የሚለቀስለት ነው :: Rolling Eyes

በነገራችን ላይ በዮሀንስ ራዕይ መጨረሻ ላይ የተጻፈው ጥብቅ ማሳሰቢያ ለኛ አይሰራም ያልክው ካርተር በውን አለማወቅህ ይሁን ባለራእይው ዮሀንስ ዋሽቷል ልትል ነው ወይስ ሕልሙን ቀባጠረ ልትል ነው ዮሀንስ ራዕይ ላይ የተጻፉም ሆነ በጠቅላላው በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ የተጻፉ ሁሉ ቅዱሳን በመንፈስ ተመርተው የጻፉት ነው እንጂ እንደፈቀዳቸው አልቀባጠሩም :: መጽሐፍ ቅዱስን እንደፈለግን መጽሀፈ ሰማኒያ ሰባ ስልሳ እያልን እንድንቀጥል ማን አዘዘን ! ቃል መሸቃቀጥ ውጤቱ ቅጽፈት እንደሆነ ተጽፎ ሳለ በኛ ላይ አይሰራም ብሎ ያስተማረህ ቄሲስ ጋር ሁለታችሁም የሚጠብቃችሁ የዘላለም እሳት ስለሆነ ወንድሜ ንስሀ ብትገባ ይሻልሀል ::

Last edited by ማይኮል_ም on Sun Apr 24, 2005 7:38 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አቢነት

ኮትኳች

Joined: 21 Jun 2004
Posts: 232

PostPosted: Sun Apr 24, 2005 7:31 pm    Post subject: Reply with quote

የምትገርሚ ሰው ነሽ አንቺ በክርስቶስ ክርስቲያን ተብለሽ ነው ሌላውን ሀይማኖት ይህንን ያህል ምንም እንዳልሆነ አድርገሽ የምትተቺው እምነት እንዳማኙ ነው ላመነ ደግሞ ይደረግለታል 80 አሀዱንም መጽህፍ ልክ አይደለም ብለሻል አንቺ ትክክል ነው የምትይው መጽሀፍና እምነት ግን ይህንን ነወይ ያስተማረሽ ሮብ አርብ መጾምና ቤተክርስቲያን መሄድ ጸደቅን ሲያስብላቸው አንቺ ተናገርሽ ጥሩነቱ አንቺም ከዛው እምነት መሄድሽ ለማያቅና ለተሳሳተ ለዛውም ስለሚመስልሽ ልትጸልይለት አይገባም እንደእምነታችሁ ለምንድነው ሁሌ የኦርቶዶክስ ነገር እንዲህ የሚያንገበግባችሁ የራሳችሁን ያዙ የመዳን ቀን ለሁለም አለና አንቺ እንዳልሽው ለምን እንደሚጾምና ለምን ቤተክርስቲያን እንደሚኬድ በደንብ ያቃሉ ያንቺ ቢጤውን ጠይቀሽ ካልሆነ የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅስ የግድ ማወቅ አያስፈልግም ለመዳን የናንተ ስታይል ነው ብዙ ያልተማሩ እናቶች በዚህ እምነት እንዳሉ አትርሺ መጽሀፍ ቅዱስ በአማርኛ ቋንቋ ብቻም አይደልም ስለግዕዝ ያለሽ እውቀት ሲበዛ ያነሰ ነውና ላዋቂዎቹ ተይላቸው ቢነገርሽም አይገባሽም አዳኝ አንድ አምላካችን ነውና እዚህ ቢሉት እዛ ድህነት ያለሱ የለምና ብርሀኑን ያብራልሽ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የኔጌታ

ኮትኳች

Joined: 17 Jun 2004
Posts: 112
Location: united states

PostPosted: Sun Apr 24, 2005 8:34 pm    Post subject: ኢየሱስ የግል አዳኔ ነው ማለት ምን ማለት ነው ? Reply with quote

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሜን ::
ከሁሉ አስቀድሞ / ዘለቃሽ ሌላ መድረክ ተከፍቶ
በእነዚያ ርዕሶች ስር በመወያየት ላይ እያለን ሌላ ቅርንጫፍ (ንዑስ ርዕስ ) መክፈት ከተያዘው ውይይት ፍረ ለማስለቀቅ ካልሆነ በስተቀር ጥቅሙ አይታየኝም :: ውይይቱ እንዳይቀጥል ከተፈለገም ዝም ብሎ መትው ሲቻል እዚያም እዚያም ማለቱ ትክክልኛነቱ አይታየኝምና ይኽኛው መዘጋት አለበት ባይ ነኝ :: በግዕዝ ስለመጸለይ አቃቂር ስድብ ተቀጽላ ድርሰት ወዘተ ብሎ ማለቱ አለማወቅን ያሳያል :: ካቶሊኮች በላቲን የምሥራቅ ኦርቶዶክሳውያን : ኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ጥንታዊ የቤተ ክርስቲያን ቌንቌዎች ስላሏቸው ለመጸለይ አሁንም ይጠቀሙባቸዋል :: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንም እንዲሁ የራሷን ጥንታዊ ቌንቌ በከፊል በብዛት ግን አማርኛን አሁንም ትጠቀማለች :: ምንም የሌላቸው ደግሞ ልሳን ብለው አድማጩ ቀርቶ ተናጋሪውም በማይገባው ያቃላት አነባበሮ ይደነጋገራሉ ::
ጌታ ያለው የተባልክ ጸሐፊ ካዥጎደጎደከው ሰፊ ድርሰት ውስጥ "ኢየሱስ የግል አዳኜ ነው " የሚለው ተደጋግሞ ተነቧል :: ምን ማለት እንደፈለግክ ብታብራራልን ? እኛ ኢየሱስ ክርስቶስ - መድኅኔዓለም - ማለትም የዓለም ሁሉ መድሃኒት መሆኑን እናምናለን የዓለም ቤዛ ነውና ! መነሻ ምክንያትህስ ምንድነው ? በኦሪት ዘፍጥረት .1 ቁጥር 26 ላይ "እግዚአብሔርም አለ :- ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር " ሲል ምን ማለቱ ይመስልሀል ? በጥቅስ ላይ ጥቅስ በዚያ ላይ ጥቅስ ከመከመር እነዚህ መሠረታዊ የሆኑትን እያጣራን ብናልፍ የሚሻል አይመስላችሁም ከመሳደብ በፊት ስለምን እንደሚነገርና ለምን እንደተባለ ማወቁ መልካም ስለመሰለኝ ነው ::
የሠላም ኣምላክ እውነቱን ይግለጥላችሁ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ደብረ ዲማ

ኮትኳች

Joined: 17 Mar 2005
Posts: 275
Location: united states

PostPosted: Mon Apr 25, 2005 7:06 am    Post subject: ደብረ ዲማ ለማንበብ ብቻ ዘለቃሽ ---- Reply with quote

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን ::

በመጀመርያ ደረጃ ለኦርቶዶክስ ምእመናን

ምስክርነት ስለሰጠሽልን አናመሰግንሻለን ::

1 ጾም እንደምንጾም ::

2 ቤተክርስቲያን ሄደን እንደምንሰግድ :;

3 የጥንት የመጀመርያ ስለመሆኑዋ :;

ምስክር በሶስት ነግር ስለሚጸና በሶስት ነግር ስለመሰ
ከርሽን ከልብ እና መሰግናለን ነገር ግን ኦርቶዶክስ
ሐይማኖት ስህተት ነው ካልሽ ::
ለምን ማስረጃ አቅርበሽ አንወያይም ?
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ባለማየት በጣም ተገርሜአለሁ ምናልባት ከእውንውት ወደውሽት
የተለውጥሽው ትናት ሳይሆን አይቀርም :;

ኦርቶዶክስ የሚል የለም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ
ስላልሽው ኦርቶዶክስ ማለት ቃሉ {ወይም }

ትርጉሙ ቀጥተኛ ወውነተኛ ማለት ሲሆን
የግሪክ ትርጛሜ ነው በዚህ አጋጣሚ
አንድ ልበል የግሪኩ ድክሽነሪ እንዲህ ይላል

ጤንጤ ማለት ሰይጣን ማለት ነው ይላል ?
ፈልገሽ ተመልከቸው
ደብረ ዲማ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ ;;
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞልጨው

ኮትኳች

Joined: 11 Feb 2005
Posts: 184
Location: finland

PostPosted: Mon Apr 25, 2005 7:42 am    Post subject: አይ ዛለቃሽሽሽሽሽሽሽሽሽሽሽሽሽሽ !! Reply with quote

ቅቅቅቅቅቅቅ እኔ የማውቀው ዘለቃሽ ብሎ አስለቃሽ ነበር ! ዛሬ ደግሞ ዘለቃሽ ብሎ የወንጌል ሰባኪ መጣብን ? አንቺ ጭርታም ኦርቶዶክስ እንዳንቺ ባለችው ገልቱ አፍ የምትጠራ ይመስልሻል ? ዳሩ የሴጣን የኮንትራት ታክሲ አይደለሽ አይፈረድብሽም !! ባንቺ ቤት ኦርቶዶክስን መርምረሽ የተጠና ጹሁፍ ማቅረብሽ መሆኑ ነው ? ቅቅቅቅቅቅ ጭቅቅታም ይልቅስ በግዜ በካናዳ ስንዴ የቀየርሽውን እምነትሽን ማሪኝ ብለሽ መመለሱ ነው የሚሻልሽ !! አሊያ ግን የጼንጤዎች የተስፋይቱ አገር ኬንያን እንደናፈቅሽ ወደሲዎል መውረጃሽ መድረሱን እወቂው !! አመዳም 2 ተኛ በዚህ 44 ቁጥር አፍሽ ኦርቶዶክስን ስም እንዳትጠሪ ! ቋንጣ !!
_________________
selam le sew lijoch hulu
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
NATHRATHE

ኮትኳች

Joined: 18 Apr 2005
Posts: 298
Location: united states

PostPosted: Mon Apr 25, 2005 9:06 am    Post subject: ይድረስ ለዘለቃሽ Reply with quote

በስመ እግዚያብሔር አሜን ::

ትህቢትና ውሽት ዲያብሎስ ከራሱ አመንጭቶ ከመላህክት ከተማ ወደ እንጦሮጦስ የወደቀበት ትልቁ ምክንያት ነው :: መድህነ አለም ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ለማዳን በዚህ ምድር በተመላለሰ ጊዜ 'እርሱ ...ሐሰተኛ የሐሰት አባት ነውና ::" ማለቱን በወንጌል ተጽፎ እናገኛለን ::ዮሐ 8-44 ዛሬም የግብር ልጆቹ እርሱን ቢመስሉ ምን ያስደንቃል ::ከአባታቸው የተማሩት ስለሆነ ::
Quote:
የሀይማኖት ሁሉ መሰረት ከሆነው መጽሀፍ ቅዱስ አንዲት ጥቅስ ስለኦርቶዶክስ ጥንታዊነትና ቀዳሚነት እንዲያሳዩ ቢጠየቁ በራሳቸው ተጻፈ የተባለውን የተለየ የተሸፈነ <መጻሀፈ ሰማኒያ > ምናምን የሚባል ነገር ያወራሉ ::

እኛስ እግዚያብሔር ይመስገን ሐይማኖታችን ሐዋርያት ያስተማሩት እንደሆነችና ሀገራችንም ከጥንት ጀምራ እግዚያብሔርን እንደምታመልክ በመጽሐፍ ቅዱስ ሆነ በታሪክ መጽሐፍት ተጽፋል :: ለዚህ አንድ ጥቅስ ልንገርህ ::መቼም መሸከም እንጂ ማንበብ አይሆንላሁ ::የሐዋ 8:28-40 ስንመለከት ብዙ ጥያቄዎችን ይመልስልናል ::አዚህ ላይ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጥቅሱን ካነበብክ በኅላ ራስህን ጠይቅ
1)ጃንደረባው ወደ ኢየሩሳሌም ሊሰግድ መሄዱ ?
2)ያነብ የነበረው ትንቢት ኢሳያስ መጽሐፍ ምን ያመለክታል
3)...ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚያብሔር ልጅ እንደሆነ አምናለሁ
እኛስ መጥቀስ ካስፈለገ በጣም ብዙ ስለኢትዮጵያውያንና እግዚያብሔርን ማምለካቸው በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈውን ልናስነብብህ እንችላለን ::
አረ ለመሆኑ እናንተ ስለእምነታሁ ጀማሪ ማርቲን ሉተር ውይም ሰለኖረባት ሀገር ጀርመን አንዲት ትቅስ ልትሰጠኘ ትችላለህ ?የራስህን ሳታቅ የሰውን በጥናት ያልተደገፈ የተለመደውን የመናፍቃን ዘፈን ከዚህ ከምትዘፍን :: አንዳንተ አባባል ምንም የምናመልከውን እማናውቅ ብንሆን ቤቴ ክርስትያን ሳንሄድ ያገኘነው ቦታ እንሰግድ ውይም እንሄድ ነበር ::አይ አለመታደል በመንፈሳዊው ባዶ ሐይማኖት በአለማዊ እውቅት ጥናት እንዴት ተደርጎ እንዴት conclusion እንዲት እንደሚደረግ ሌልው ቤቀር አታነቡም ::ሰው ምን ይለናል የለ ዝም ብሎ ብቻ መንጣጣት :: ሐይማኖት መችበመለፍለፍ ሆነና ::ሌላ ምን ይባላል ልቦና ይስጣሁ ብሎ ፀሎት ከማድረግ ሌላ :: እመቤታችን የዶኪማስን አስተናጋቾች ከጭንቀታቸው አንዳገላገለቻቸው አናንተንም ካላችሁበት ጭለማ በምልጃዋ ወደ ብርሀን ትመልሳችሁ ::
ይቆየን
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
NATHRATHE

ኮትኳች

Joined: 18 Apr 2005
Posts: 298
Location: united states

PostPosted: Mon Apr 25, 2005 10:23 am    Post subject: Reply with quote

በስመ ስላሴ አሜን ::
ለዲያብሎስ የግብር ልጆች ለሚናገሩት ሁሉ መልስ መስጠት ልክ ቁም ነገር እንደሚናገሩ እንደ ጨዋ ሰው መቁጠር ነው :: የሚታወቁት በጨዋ ደንብ አሳባቸውን አምጥተው ለማስረዳት ከሞመከር ይልቅ ይልቅ ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው በማያውቁት ነገር ይሳደባሉ ::አንዳንዴ ማሳፈር ይገባልን እስቲ ስለመጽሐፍ ቅዱስ ቁጥር እንመልከት ::ብዙም የጠለቀ እውቀት ባይኖረኝም ትንሽ የተማርካትን ልግለጽ ባይሆን እንተጋገዛላን ::እንደ መናፍቃን ተምረን ጨርሰናል አንልም ::
በመጽሕእፍ ቅዱስ ውስጥ ስለሚገኙ መጽሕእፍት ቁጥር የተለያዩ ድርጅቶች የየግል ሐሳባቸውን ይሰነዝራሉ ::ላቲኖች (ካቶሊክ ) 73 ግሪኮች 76 ናቸው ይላሉ ::16ኘው .. የተነሱት ፕሮቴስታንት ደግሞ 66 ነው ይላሉ ::
በመሰረቱ ቅዱሳን መጻሐፍትን ሸራርፎና ቀናንሶ ይህ ብቻ ነው ማለቱ ጌዜ ያለፈብት ይመስለኛ ::አንተ በጠቀስከው ጥቅስና እንዳንተ አተሮጋገም እንሄድ እንበል :: ባንተ ትርጉም የጨመረና የቀነሰ ብለሀል ::አንተ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ 66 እንደሆነ የሚናገር ጥቅስ ልትሰጠን ትችላለህ ::ሰውን ጨመሩ ከማለትህ በፊት ማርቲን ሉተር ለምን መጽሐፍቱን እንደቀነሳቸው ተረዳ :: መጽሐፍ ቅዱስ ግን 81 እንደሆነ ከሚከተሉት ጥቅስ እንረዳለን እንዚህን ጥቅሶች ከናንት ከቆራጣቸሁት ውስጥ ካገኘህ እንይህ ::ልቦና ካልህ የምታመዛዝን ከሆነ ትክክለኛው የቱ እንደሆን በዚህ መረዳት ትችላለህ
1)ይሁ ቁጥር 14&15 የተጠቀሰው የሄኖክ ትንቢት የት እንደሚገኘ ልትነግረን ትችላለህ ?
2)ማቲ 27:9 "በዜያን ግዜ በነብዩ ኤርምያስ የተባለው ...' የዚህንስ ?
3)ዘፍ 4 :17 'ቃየንም ሚስቱን አወቀ ጸነሰችም ...'ከዘፍጥረትን 1 ጀምረን ስናነብ እስከ ዚህ ጥቅስ ድረስ የምናገኛት ሴት ሔዋን ብቻ ነው ታድያ ቃየል ሚስት ኬት አምጥቶ አገባ ?
ብዙ ማንሳት ይቻላል ለማንኛውም ልቦን ይስጥህ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አምባሳደር

ኮትኳች

Joined: 12 Nov 2004
Posts: 107
Location: united states

PostPosted: Mon Apr 25, 2005 12:24 pm    Post subject: Reply with quote

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ የሚገርመው እስካሁን ለዘለቃሽ የመልሥ ምት የሰጠ የለም ;;

ቆይ ጠብቅኝ መምህር ዘበነን ጠርቼ መጣሁ ;;
_________________
What is next?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፋራ ልጅ

አዲስ

Joined: 12 Apr 2005
Posts: 20
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Apr 25, 2005 1:41 pm    Post subject: ሁሉም ለአግዚአቡሄር ክብር ነው :: Reply with quote

ይሄ ሁሉ bla bla ለምን አስፈለገ ? ሁሉም ዼንጤውም ሆነ ኦርቶዶክሱ የሚያደርገው ባይገባውም ለጌታ ክብር ነው :: ሁሉን የሚያየው እሱ ደሞ ያንን ያያል :: After all kindness is all it matters!

ፋራ ልጅ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2, 3 ... 17, 18, 19  Next
Page 1 of 19

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia