WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home | About us | Advertise with us | Contact us
በኢትዮጵያ ገዳም ካሉ ቅዱሳን አባቶች የመጣ መለክት ለመላው ::

Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ግሸንማርያም

ኮትኳች

Joined: 15 Aug 2005
Posts: 349
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Nov 07, 2005 4:23 pm    Post subject: በኢትዮጵያ ገዳም ካሉ ቅዱሳን አባቶች የመጣ መለክት ለመላው :: Reply with quote

በስመ አብ በስመ ወልድ በስመ ወመንፈስቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን :: የተከበራችሁ ውድ ክርስትያኖች ወገኖቼ አገራችን ኢትዮጵያ አሁን የምትገኝበት ሁኔታ እጅግ አስቃቂ እና አሳዛኝ ነው :: ከትላንታ በስትያ በትንሹ 11000( አስራ አንድ ) ቁጥሩ በየቀኑ እንደሚጨርም የታወቀ ነው :: የሚሆኑ የአዲስ አበባ ወጣቶች ከቤታቸው ታፍሰው ወደ ማይታወቅ ቦታ በወያኔ ሀይሎች እየተቀጠቀጡ ተወስደዋል :: እኔ ኢትዮጵያ በተከታትያይ ደውዬ ነበር :: ሌሊት ሌሊት ወጣቱ ሱሪውንና ጫማውን አድርጎ ለማምለጥ ተዘጋጅቷል :: ምክንያቱም ወታደሮቹ የሚመጡት ማታ ላይ ነው :: ወታደሮቹ የአማርኛ ቁዋንቅዋ እንክዋን መናገር አይችሉም :: ዝም ብለው የሁሉንም ቤት እየሰበሩ እየገቡ ወጣት ሴት ወንድ የለም ሁሉንም ወደ ማጎሪያቸው እያፈኑ እየወሰዱ ነው :: ከአንድ ሳምንት በላይ ይህ አፈና ግድያ ቀጥሏል :: የሚሸምትም ሆነ የሚሸጥ የለም :: ወገኖቼ ደሀው ሕዝባችን አሁን ምን እየበላ ይሆን ? ሀብታሙስ ተዘጋጅቶበታል :: ደሀው ግን ከአንድ ሳምንት በላይ ምግብ ቀምሶ ይሆን ? እግዚአብሔር ይወቀው ::

ኢትዮጵያ በደወልኩበት ጊዜ ውስጥ የሰማዋቸው አሳዛኝ ዜናዎች በጥቂቱ ::

1. አንድ ቤት ውስጥ የወያኔ ወታደሮች ገብተው የቤቱን አዛውንት ውጣ ብለው በሰደፍ ይደበድብዋቸዋል :: በዚህን ጊዜ የሰውየው ሚስት እረ ምንም አላደረገም እሱ ሽማግሌ ነው ብለው ለወታደሮቹ ሲናገሩ :: ወታደሮቹ የሴይትየዋን ጭንቅላት በጥይት ፈረካከሱት :: ሴትየዋም እዛው ፊታቸው ተደፍተው ሞቱ :: ወጣት ልጅየውም ወይኔ እማዬ ሲል እርሱንም ደረቱን መትረየስ አከታትለው በምታት ቅድስት ሕይወቱን አሳጡት :: አሁን በዚያ ቤት ውስጥ 7 አመት ልጅ ብቻ ትገኛለች :: እናትዮውና ወንድሞዋው ተገድለዋል :: አባትየዋ ደግሞ ወዳልታወቅ ቦታ ተወስደዋል ::

2. አንድ ወጣት ልጅ ከትምህርት ቤት መጥቶ ዩኑፎርሙን ሲያወልቅ እዚያ ቤቱ ደረስ ተከታትለው ወታደሮቹ ልጁን ገደሉት በቤቱ ውስጥ ::

3. አፈሳው አሁንም ቀጥሏል :: ሰዎች እየተገደሉ ነው :: የሚያሳዝነው ደግሞ የቀበሌ ሊቀመንበሮች ለነዚህ ወታደሮች ፈታቸውን በመሸፈን ጥቆማ እያደረጉላቸው ብዙ ወጣቶችን ማስጨረሳቸው ነው ::

ወገኖቼ ሰው በአገሩ መኖር አልቻለም :: ከአምላክ የተሰጠውን ክቡር ነፍሱን በአምባገነኖች በከንቱ እያጣው ነው ::

ከኢትዮጵያ ከሚገኙ ገዳማት ቅዱሳን አባቶች የመጣ ጥብቅ ማሳሰቢያ ለሁላችንም ::

1 ከዛሬ ሰኞ እስከ ሮብ ድረስ ጠዋት ቁርሳችንን በመተው ጾም እንድንጾም ::

2. መዝሙረ ዳዊት , ወዳሴ ማርያም ... የተለያዩ የጸሎት መጸሀፍቶችን ማንበብ :: ምክንያቱም በገዳሙ ያሉት ቅዱሳን አባቶች እንደተናገሩት :: በኢትዮጵያ ውስጥ ሕዝቡ ፓትርያርኩ ጽሎት እንዲያውጁ ሲጠይቁ ፓትርያርኩ ደግሞ ምን ተነካችሁ እና ነው ጽም የሚታወጀው ብለው በሚያስገርም ሁኔታ ተናግረዋል ብለዋል ቅዱሳን አባቶች ከገዳም :: ስለዚህ እባካችሁ ቢቻለን የተጣላናቸው ሰዎች ካሉ ይቅር እየተባባልን እንደ ነነዌ ሐዝብ እንጹም እንጸልይ :: ሌሎች ዜናዎች እና ከኢትዮጵያ የሰማችሁት በደል ካለ በዚህ ጸሁፍ ውስጥ አካፍሉን ::

ቅድስት ድንግል ማርያም የቃል ኪዳን አገርሽን ኢትዮጵያን አስታውሺ :: እናታችን ሆይ እንደ እኛ ሐጢያት ሳይሆን እንደ ቸርነትሽ አገራችንን ጠብቂልን አሜን ::

ወስብሀት ለእግዚአብሔር ወለ ወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር ::

Last edited by ግሸንማርያም on Tue Nov 08, 2005 4:09 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቤንይሁዳ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 23 Apr 2005
Posts: 93
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Nov 07, 2005 8:41 pm    Post subject: አይ ግሽን ማርያም እንደው በስመአብ እያሉ መቀደደ ሆነ ስራህ !! Reply with quote

ወያኔን የሚያደርገውን ግፍና ጭካኔ ሁላችንም በአደባባይ
እያየን ነው : ያንተ ቃል አቀባይ መለኩሴ ከገዳም ሆኖ በሞባይል አዲስ አበባ የሚደረገውን ነገርኽ ይገርማል !!

ገድም ስልክ መግባቱንም እየነገርከን ነው ይገርማል !
ምነው ማሪያምንና ጥሪ ቆርጥሞ የሚያድረውን መነኩሴ ትተህ የራስህን የተለመደውን ተረት ብታወራ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ግሸንማርያም

ኮትኳች

Joined: 15 Aug 2005
Posts: 349
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Nov 08, 2005 5:28 am    Post subject: ለቤንጉዳ :: Reply with quote

በስመ አብ በስመ ወልድ በስመ ወመንፈስቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ::

ልጅ ቤንጉዳ ይህ ሁሉ ሰው ስለሞተ በዚህ አገር ያለው ሰው ይጹም የሚለ ምልእክት በመስጠቴነው የተቃጠልከው ? ልጅ ቤንጉዳ ቅዱሳን ሞባይል አይፈልጉም እኮ :: እግዚአብሔር በየቦታው የራሱ የሆኑ ቅዱሳን አባቶች አሉት :: እነዚህ ቅዱሳን በራእይ ይገናኛሉ :: ጾሙ ካልጣመክ አትጹም ምክንያቱም ሆድክን ስለ ምታመልክ ::

እኛስ ለዚህ ለደሀው ወገናችን ሰላም እንጾማለን እንፈጽማለን :: ታውቀኛለክ ለአንተ አይነቱ ሕጻን መልስም አያስፈልግም ነበር ::

የአንተን አይነቱን መናፍቅን የሚያሳፍርና አንደበታችሁን የሚዘጋው ትምህርት ይቀጥላል :: አሁን ግን ስለ ሕዝባችን እንጸልይ እንጹም :: ስለ ድርጅትህ ስብከት ለጊዜው እዚህ ላይ አቁም ::

ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አክሱምማርያም

ኮትኳች

Joined: 13 Sep 2005
Posts: 357
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Nov 08, 2005 6:15 am    Post subject: እግዚአብሄር ይፍረድ !!! Reply with quote

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱአምላክ አሜን ::

በመጀመርያ ደረጃ ህይወታቸውን ላጡት ወገኖቻችን በሙሉ እግዚአብሄር ነፍሳቸውን ከአብርሀም ከይስሀቅ ከያእቆብ ጎን ያሳርፍልን :: እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በምልጃዋ ትራዳቸው :: ለቤተሰቦቻቸውም አጽናኝ መልአክ ይላክላቸው ::ለተፈጸመው ነገር ሁሉ እግዚአብሄር ፍርዱን እርሱ ይስጥ : የእርሱ ፍርድ ሁል ጊዜ ትክክል ነውና !!!

እኛም ጥቂት ማድረግ ከምንችለው ውስጥ እውነተኞች ቅዱሳን አባቶቻችን በነገሩን መልእክት መሰረት የሶስት ቀን ሱባኤ ይዘናል :: እግዚአብሄር የምህረት ፊቱን ይመልስልን ሀገራችንንና ሀይማኖታችንን ይጠብቅልን :: እኛ ከሰይጣን ሌላ ጠላት የለንምእና እግዚአብሄር ያሳፍርልን አፉንም ይዝጋልን ::
ኢትዮጵያዊነት ለዘለአለም ይኑር አሜን ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞልጨው

ኮትኳች

Joined: 11 Feb 2005
Posts: 184
Location: finland

PostPosted: Tue Nov 08, 2005 11:42 am    Post subject: ግሸን ማሪያም Reply with quote

በጥያቄ ልጀምር ከላይ 110000 የሚሆን አዲስ አበባ ነዋሪ በወያኔ ታፍሰው መወሰዳቸውን ገልጸሻል : እንዳጻጻፍሽ አንድ መቶ አስር ወጣቶች መሆኑ ነው ? ወይስ 11 ለማለት ፈልገሽ አንድ ዜሮ በስህተት ገብቶ ይሆን ? ምንጭ ምነው የለው ?

ወደ አምላክ በህብረት መጮሁና መጾሙ ምንም አማራጭ የሌለው ዋናው መንገድ እንደሆነ አምናለሁ : ግን እንዲህ ቡራቡሬ የሆነ ልብ ይዘን ነው የምንጾመውና የምንጸልየው ? ካንቺና እኔው ብጀምር እንኳን ከላይ ምንም መረጃ ሳይኖርሽ የጻፍሽው አህዝ ሰውን ወደ ጾምና ጸሎት ሳይሆን ወደ ዊም እና በቀል የሚመራ ነው : እውነተኛ ክርስቲያን ዋሽቶ ወደ ሰላም ይመራል እንጂ ዋሽቶ ሰውን ለበቀል አያነሳሳም :: ወያኔ ዛሬ የያዘውን ብረት ተመክቶ ደሀን እንዳሻው እየነዳ እንዳለ ብናውቀውም እነሱም እንደደርግ ቀናቸው ደርሶ ፍዳቸውን የሚያዩበት ቀን እንዲመጣ ወደ አምላክ ማሳሰቡ እራሱን የቻለ ነገር ሆኖ ግን ዝም ብሎ እያጋነኑ የሰውን ቁስል በማጭድ መነካካቱ ቢቀርስ ?
_________________
selam le sew lijoch hulu
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ድራኮላ 7

ኮትኳች

Joined: 25 May 2005
Posts: 116
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Nov 08, 2005 12:32 pm    Post subject: Reply with quote

<110000 > አንድ መቶ አስር ወጣት ጉድ እኮ ነው ሰው ቁጥር ጠፍቶታል ወይስ ይሄ ስደት ናላችሁን አዙሮታል ሠላም ለኢትዮጵያ !!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ግሸንማርያም

ኮትኳች

Joined: 15 Aug 2005
Posts: 349
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Nov 08, 2005 2:22 pm    Post subject: ከቅዱሳን አባቶች ከገዳም የመጣ መልእክት :: Reply with quote

በስመ አብ በስመ ወልድ በስመ ወመንፈስቅዱስ አሀዱ አምላካ አሜን ::

የተከበራችሁ ሰዎች ከላይ እኔ ከኢትዮጵያ ገዳማት እዚህ ላሉ ንጹሀን አባቶች መልእክት ልከው ነበር :: መልእክቱም ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ሰዎች ጾምን ማወጅ ስላልቻሉ በውጪ አገር ነጻነት ያላችሁ ሰዎች ለቅድስት አገር ለኢትዮጵያ የሶስት ቀን ጾም አውጁ የሚል ነበር :: ይህንን መሰረት በማድረግ በዚህ አካባቢ የሚኖረው ሕዝብ በአገሪቱ ላይ ለደረሰው መከራና በሕዝቡ ላይ ለተቃጣው አሰቃቂ ጥቃት እግዚአብሔር ምላሽ እንዲሰጥ ጾምን አውጇል :: እኔ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ይህንን መልእክት እንደሰሙ እዚህ ላይ አቅጥቼዋለሁኝ ::

አንዳንዶቻች ግን የወገንም ፍቅር ስለሌአችሁ ጾምም የመጽም አቅም ስለሌላችሁ ስትዘባርቁ አይቻለሁኝ :: በተለይ ጴንጤው ቤንጉዳ :: ጴንጤ መቼም ለአገሩ ፍቅር እንደሌለው አውቃለሁኝ :: ጴንጤ ፍቅር ያለው ለጀርመንና ለማርቲን ሉተር ነው ::

የቁጥር ስህተት እንዳለ ግን መመልከት ችዬአለሁኝ :: በወቅቱ የታፈሰው ሰው ወደ አስራ አንድ ነበር :: ለሱ ይቅርታ :: ቤንጉዳ ግን በሐይማኖት ስላልቻልከኝ በዚህ ለመምጣት መሞከርክ እጅግ ያስቃል :: በቅርቡ ደግሞ በውስጥህ ያለውን የአውሬ መንፈስ የሚያሳፍር ትምርት ለማውጣት በዝግጀት ላይ ነኝ :: የዛኔ እንገናኝ !!

በተረፈ የቻላችሁ ለአገራችሁ ጹሙ :: ያልቻላችሁ ደግሞ አትጹሙ :: እንጂ ሌላ ነገር አትቀባጥሩ :: ያልተጻፈም አታንቡ ::

በተረፈ በዚህ ጉዳይ ላይ በናበቃስ ....
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አክሱምማርያም

ኮትኳች

Joined: 13 Sep 2005
Posts: 357
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Nov 08, 2005 3:59 pm    Post subject: ልቦና ይስጥልን :: Reply with quote

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱአምላክ አሜን ::

ልቦናው የዞረው ማነው ? ለሀገሩ በመቆርቆር እንጹም እንጸልይ ያለው ወይስ ለመከራከር ሰበብ የሚፈልገው ???
ከላይ ያላችሁት ሁሉ ከሚገባው በላይ ተሳስታሁአል :: ለምን ? ማንም ሰው እዚህ ዋርካ ላይ ሲጽፍ ስህተት ሊሰራ ይችላል ::ደግሞ የታፈሰውን የሰው ቁጥር ማንነው በትክክል የሚያውቀው ??? በገጠርም በከተማም ቤቱ ይቁጠረው እንጂ :: ግሽንማርያም ካለው ቁጥር እንደውም በልጦ ቢገኝስ ? እውነተኛ ሰዎች ብትሆኑ ኖሮ የጻፈውን ልጅ (ግሽንማርያምን ) እንዴት ነው ይህ አሀዝ እውነት ነው ወይስ ተሳስተህ ነው ወንዴሜ ተብሎ ይጠየቃል እንጂ ከዚህ በፊት ቂም ያላችሁ ይመስል አፍን ማላቀቅ ጥሩ አይደለም :: ስታስቡት አሁን እንከራከር ወይስ ለእግዚአብሄር ድምጻችንን እናሰማ ??? የክርክር ሱስ ያለበት ሰው ካልሆነ በስተቀር በአሁን ሰአት ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊ ጋር መከራከሪያው ሰአት አይደለም :: የሚያስተውል ካለ :: እና እግዚአግሄር ለሁላችንም ልቦናችንን ይግለጽልን :: ቢያንስ አሁን አንከራከር ::
የሞቱትን ነብስ ከጻድቃን አጠገብ ያኑርልን : ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ያድልልን ::

እግዚአብሄር ሀገራችንንና ሀይማኖታችንን ይጠብቅልን አሜን ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
NATHRATHE

ኮትኳች

Joined: 18 Apr 2005
Posts: 298
Location: united states

PostPosted: Tue Nov 08, 2005 8:25 pm    Post subject: Reply with quote

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ::

ሰላም ክርስቲያኖች

የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ ለጾም አዋጅ ነገሩ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ ::ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ እርሱም ከዙፋኑ ተነሥቶ መጎናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ በአመድም ላይ ተቀመጠ ::አዋጅም አስነገረ በነነዌም ውስጥ የኑጉሱን የመኳንንቱን ትእዛዝ አሳወጀ ::እንዲህም አለ ሰዎችና እንስሶች ላሞችና በጎች አንዳችን አይቅመሱ አይሰማሩም አኃም አይጠጡ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ ::እኛ እንዳንጠፋ እግዚያብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደሆነ ከጽኑ ቁጣውም ይመለስ እንደሆነ ከጹኑ ቁጣውም ይመለስ እንደሆነ ማን ያውቃል ::እግዚያብሔር ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ እግዚያብሔር ያደረግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም :: ዮና 3:5-10

የጾምና የጸሎት ሀይል ምን ያህል እንደሆነ ለማስተዋስ ነው ::ስለሆነም በሀገራችን ያለው ሰቆቃና የህዝባችን በግፍ መገደል ሁላችንም ያሳዝናል ::ስለሆነም ሰላምን የሚሰጥ የሰላም ባለቤት መድኃኒያለም ኢየሱስ ክርስቶስ ለሀገራችን ሰላምን ፍቅርን አንድነትን እንዲሰጥ በጾም በጸሎት መጠየቅ ይገባናል ::
ግሸን ማርያም ይህን ያባቶቻችንን ጥሪ ስላሰማኅን ቃለ ህይወት ያሰማን ሌሎቻችንም እስቲ በምችለው በጾም በጸሎት እንበርታ ::
እግዚያብሔር ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን ::

ይቆየን ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ትህትና 2

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 09 Jan 2005
Posts: 1696
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Nov 08, 2005 10:34 pm    Post subject: ይህ ምን ያስገረማል Reply with quote

ግሸንማርያም እንደጻፈ(ች)ው:
በኢትዮጵያ ውስጥ ሕዝቡ ፓትርያርኩ ጽሎት እንዲያውጁ ሲጠይቁ ፓትርያርኩ ደግሞ ምን ተነካችሁ እና ነው ጽም የሚታወጀው ብለው በሚያስገርም ሁኔታ ተናግረዋል ብለዋል ቅዱሳን አባቶች ከገዳም :::

የወያኔ ካድሬዎች ቲያትር መቼም በሀዘንም ሰአት ለደይቃም የአሽሙር ሳርካስቲክ ሳቅ በግድ ያስቃል . በተቀባበለ ጥይት ቤተክርስቲያን ዉስጥ ሰው ያስረሸኑ ስዎችን ጸሎት አውጁ ማለት ራሱ አንዱ እንዳለው "for those who THINK Life is a COMEDY " ነው . እንኩዋንስ ዘንቦብሽ እንዲሁም ጤዛ ነሽ አሉ .
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አዲሳባ

መንገደኛ

Joined: 23 Jan 2005
Posts: 7
Location: germany

PostPosted: Tue Nov 08, 2005 11:02 pm    Post subject: Re: ከቅዱሳን አባቶች ከገዳም የመጣ መልእክት :: Reply with quote

ግሸንማርያም እንደጻፈ(ች)ው:
በስመ አብ በስመ ወልድ በስመ ወመንፈስቅዱስ አሀዱ አምላካ አሜን ::

የተከበራችሁ ሰዎች ከላይ እኔ ከኢትዮጵያ ገዳማት እዚህ ላሉ ንጹሀን አባቶች መልእክት ልከው ነበር :: መልእክቱም ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ሰዎች ጾምን ማወጅ ስላልቻሉ በውጪ አገር ነጻነት ያላችሁ ሰዎች ለቅድስት አገር ለኢትዮጵያ የሶስት ቀን ጾም አውጁ የሚል ነበር :: ይህንን መሰረት በማድረግ በዚህ አካባቢ የሚኖረው ሕዝብ በአገሪቱ ላይ ለደረሰው መከራና በሕዝቡ ላይ ለተቃጣው አሰቃቂ ጥቃት እግዚአብሔር ምላሽ እንዲሰጥ ጾምን አውጇል :: እኔ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ይህንን መልእክት እንደሰሙ እዚህ ላይ አቅጥቼዋለሁኝ ::

አንዳንዶቻች ግን የወገንም ፍቅር ስለሌአችሁ ጾምም የመጽም አቅም ስለሌላችሁ ስትዘባርቁ አይቻለሁኝ :: በተለይ ጴንጤው ቤንጉዳ :: ጴንጤ መቼም ለአገሩ ፍቅር እንደሌለው አውቃለሁኝ :: ጴንጤ ፍቅር ያለው ለጀርመንና ለማርቲን ሉተር ነው ::

የቁጥር ስህተት እንዳለ ግን መመልከት ችዬአለሁኝ :: በወቅቱ የታፈሰው ሰው ወደ አስራ አንድ ነበር :: ለሱ ይቅርታ :: ቤንጉዳ ግን በሐይማኖት ስላልቻልከኝ በዚህ ለመምጣት መሞከርክ እጅግ ያስቃል :: በቅርቡ ደግሞ በውስጥህ ያለውን የአውሬ መንፈስ የሚያሳፍር ትምርት ለማውጣት በዝግጀት ላይ ነኝ :: የዛኔ እንገናኝ !!

በተረፈ የቻላችሁ ለአገራችሁ ጹሙ :: ያልቻላችሁ ደግሞ አትጹሙ :: እንጂ ሌላ ነገር አትቀባጥሩ :: ያልተጻፈም አታንቡ ::

በተረፈ በዚህ ጉዳይ ላይ በናበቃስ ....

ግሸን ማርያም ወቅታዊና አስፈላጊ ርዕስ ከፍተህ ስታበቃ ለተናግሮ አናጋሪዎች መልስ እሰጣለሁ ብለህ የማያስፈልግ አምባጓሮ ውስጥ ገባህ ::በአሁኑ ሠዐት ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ሁሉ መተባበር ሲገባው የአግዓዚ ጥይት ኃይማኖት ለይቶ ይገድል ይመስል ጴንጤ ላገሩ ግድ የለውም ብለህ ደመደምክ ::አንተ ያለህበትን አካባቢ አላውቅም እንጂ እኔ እንደማየውና እንደማስተውለው ውጪም ሆነ አገር ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ኃይማኖት ዘር ወይም ሌሎች ልዩነቶችን ወደ ጎን አድርገው ድምፃቸውን እያሰሙ ነው ::ስለሆነም ይህ አባብልህ መታረም አለበት እላለሁ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የጨርቆሱ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 15 Mar 2005
Posts: 90
Location: united states

PostPosted: Wed Nov 09, 2005 7:29 am    Post subject: Reply with quote

ድራኮላ 7 እንደጻፈ(ች)ው:
<110000 > አንድ መቶ አስር ወጣት ጉድ እኮ ነው ሰው ቁጥር ጠፍቶታል ወይስ ይሄ ስደት ናላችሁን አዙሮታል ሠላም ለኢትዮጵያ !!!

-----------------
በሰህተት አንድ ዜሮ መጨመሩ ግልፅ ነው :: በአጭሩ አንተ ከቁጥሮቹ ፊት ተደንቅረህ 11000 የሚለውን 110000 አስመሰልከው :: ዜሮ ! አሁን ያንተ አይነቱ አህያ እዚህ እያናፋ እነዚያ ንጹህ ወንድሞችና እህቶች ይታገቱ ?
ሞት ለወያኔ ሞት ለአጨብጫቢዎቹ !
የኢትዮጵያ ትንሣዔ ተቃርቧል !!!!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia