WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
all conquering Barcelona

 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት


 
View previous topic :: View next topic  
Author Message
አፍሪክ

ኮትኳች


Joined: 18 Feb 2005
Posts: 450
Location: united states

PostPosted: Thu Dec 22, 2005 12:57 am    Post subject: all conquering Barcelona Reply with quote

በትናንትናው እለት ባርሳ ከሴልታቪጎ በታላቁ ኑካምፕ ስቴድየም ከመጫወቱ በፊት ቡድኑ ያለውን የችሎታ ክምችት ለአለም ያሳዩበት አጋጣሚ ተፈጥሮ ነበር :: ሮናልዲንሆ ለሁለተኛ ጊዜ በተከታታይ የፊፋ ያለማችን አንደኛ ተጫዋች ተብሎ የተሸለመውን የወርቅ ኳስ ለደጋፊው ሲያሳይ ሳሙየል ኢቶ ደግሞ በሶስተኝነት የተሸለመበትን ሽልማት እንዲሁ ከፍ አድርገው አሳይተዋል :: ምን ይህ ብቻ በያመቱ በጣሊያኑ የስፖርት መጽሄት ቱቶ ስፖርት አማካይነት የሚደረገውን የአመቱ ወጣት ተጫዋች በኮከብነት የተመረጠው አርጀንቲናዊው 18 አመት ወጣት ሊዮኔል ሜሲ እሱም ሽልማቱን ከነሮናልዲኖ ጋር አሳይቷል :: ምን አይነት ቡድን ነው የአለማችን ቁጥር አንድና ቁጥር ሶስት ኮከቦችን እንዲሁም ያለማችን አንደኛ ወጣት ተጫዋችን በውስጡ ያካተተ ? ይህ የሚቻለው በታላቁ ባርሴሎና ቤት ብቻ ነው !!በሜዳው ላይ እንቅስቃሲያቸውም ቢሆን ያገኙትን ተጋጣሚ እደርማመሱ ሪኮርድ በሪኮርድ እየሰበሩ የራይካርድ ልጆች እየገሰገሱ ነው :: በተለይማ የካሜሩኑ አጥቂ ኢቶ ብቃት ከማስገረምም አልፎ እያስፈራ ያለ ነገር ነው :: ጎል ማግባት ሸሚዝ የመልበስ ያህል እየቀለለው የመጣ መርዘኛ አጥቂ መሆኑን ትናንት እራሱ ሴልታ ቪጎን ሁለት ለባዶ ሲረቱ ሁለቱንም ከመረብ በማሳረፍ አስመስክሯል :: ከተከላካዩ አንስቶ ኳስን መስርተው እየተቀባበሉ ተአመር ማየት ሲያስፈልግ አሊያም ነእግሮች ከበድ ሲሉ ምንም ለማይሳነው ለሮናልዲንሆ ይሰጡታል እሱም አያሳፍራቸውም ለአይን የማይታመኑ ምትሀቶችን ሰራ ሰራ አድርጎ ለኢቶ ወይም ላርሰን ይለቃል ...ዋው ባርሳሳሳ
I LOVE BARCELONA
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

 
Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum


Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia