WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የእግርኳሱ አለም ለንጉስ ሮናልዲንሆ እጅ ይነሳል !!!!

Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

View previous topic :: View next topic  
Author Message
አፍሪክ

ኮትኳች

Joined: 18 Feb 2005
Posts: 450
Location: united states

PostPosted: Wed Jan 11, 2006 7:44 am    Post subject: የእግርኳሱ አለም ለንጉስ ሮናልዲንሆ እጅ ይነሳል !!!! Reply with quote

እለቱ 2003/2004 ስፓኒሽ ሻምፒዮና መክፈቻ ጨዋታ የሚካሄድበት :: ቦታው ደግሞ ታላቁ ኑካምፕ ስቴዲየም -ባርሴሎና :: ተጋጣሚ ቡድኖች ባርሴሎና ሲቪያ (sevilla):: ሰአቱ ከለሊቱ 1:30 am- ጨዋታው ከተጀመረ ልክ 25 ደቂቃ :: ኳስ ደግሞ ያለችው በባርሴሎና ክልል መሀል ሜዳ አካባቢ :: ይህን ጊዜ ነው ይቺ ከሰኮንዶች ቅስበት በሗላ ተአመር ልትመዘግብ የሆነች ኳስ በባርሴሎናው 10 ቁጥር እግር ስር የምትገባው :: መለያ የሆነው ዞማ ጸጉሩን ወደሗላው ያስያዘው ይህ ወጣት በእግሩ የገባችውን ኳስ ይዞ ተወነጨፈ እግረመንገዱንም ሁለት የሲቪያ ተጫዋቾችን በሚገርም የቴክኒክ ብቃቱ አታሎ በማለፍ 30 ሜትር ርቀት አክሮ የላካት ኳስ እየበረረች ሄዳ በመጀመሪያ አግዳሚውን ገጨች ከዛም መሬት ደርሳ የጎል መስመሩ ላይ ነጥራ በመጣችበት ፍጥነት ተስፈንጥራ የመረቡ ጣራስር ስትወሸቅና ቁጥሩ 80,000 በላይ የሆነው የባርሴሎና ደጋፊ በጩህእት ስቴድየሙን ሲያናውጥ አንድ ሆነ !! ድንቅ ጎል !! አዎ ይህን ታሪክ በወርቃማ እግሮቹ በዛ ውድቅት ለሊት የጻፈው የዘመኑ የእግርኳስ ስፖርት ወርቃማ ልጅ ሮናልዶ ደአሲስ ሞሪዬራ (Ronaldo De Assis Moreira) በተለምዶ ስሙ ሮናልዲንሆ ነበር :: ካታሎናዊያኑ በአጸፋው ልባቸውን አዲስ ላስፈረሙት ብራዚላዊ ወጣት ለመስጠት የፈጀባቸው ያቺ 25 ደቂቃ ብቻ ነበረች :: አሁን ለእንግሊዙ አርሰናል የሚጫወተው ያን ቀን ግን ለሲቪያ ተሰላፊ የነበረው ሆዜ አንቶኒዮ ሬየስ ሥለሮናልዲንሆ ሲናገር "spectacular!" በሚል አንዲት ቃል ጨርሶታል :: ያን ምሽት በአስደናቂ ጎል የተጀመረው የሮናልዲንሆ ተአምራት አመቱን ሙሉ ቀጥሎ የባርሳን ቲፎዞ ከሳምንት ሳምንት አስደናቂ ክህሎቱን ከውጤታማ እንቅስቃሴ ጋር አብሮ ሲያስኮመኩመው ከረመ :: ምንም እንኳን የቡድኑ ድንቅ እንቅስቃሴ በዋንጫ ባይታጀብም አዲሱ የፍራንክ ራይካርድ ቲም በብራዚላዊ አርቲስት መሪነት ለወደፊቱ ግሩም ቡድን እንደሚሆን አመላክቶ አመቱን ጨረሰ :: የባርሳ ስኬት የማድሪድ ቅዠት እንዲሁም የማድሪድ ያማረ ጉዞ ለባርሴሎናዎች የሚጎመዝዝ ያንዳቸው ውድቀት ላንዳቸው ፈንጠዚያ መሆኑን አለም ኳስ አፍቃሪ ጠንቅቆ ያውቃል :: ያሁኑ ባርሴሎና የተቃና የመሰለ ጉዞ ግን ለሪያል ማድሪዶች ሊቀበሉት የማይቻል እጅግ መራር ጽዋ ሆነባቸው :: ታሪኩ እንዲህ ነው :: በሰመር 2003 ሁለት ተጫዋቾን የዝውውር ዜናውን ተቆጣጥረውት ነበር :: ዴቪድ ቤከም እና ሮናልዲንሆ :: ቤከም ሰር አሌክስ ፈርግሰን ጋር ያለው ግንኙነት በተለይም በአርሰናል ሲሸነፉ በንዴት የጦፉትአንጋፋው አሰልጣኝ መልበሻ ክፍል ውስጥ በፑንት የመቱት መሬት የነበረ ታኬታ ጫማ ሄዶ የቤከምን ቅንድብ ከፈነከተ ወዲህ ሻክሮ ማንቸስተርን እንደሚለቅ እርግጥ የመሆኑን ሁናቴ ያጤኑት ሪያል ማድሪዶች እንደፋሽን የያዙት ቁጥር አንድ የተመሰከራለችውን ከዋክብት ተጫዋቾች (Galacticos)* በያመቱ የማስፈረም አባዜ መሰረት ቤካምን ማስፈረም ዋነኛ አጀንዳቸው አደረጉት :: ይህ በንዲህ እንዳለ እዛው አገራቸው ያለው ባርሴሎና ቤት ውስጥ በያራት አመቱ ለሚደረገው የክለቡ ፕሬዝዳንትነት ምርጫ የሚወዳደሩት ወጣቱ የህግ ጠበቃ ዮሀን ላፖርታ የምረጡኝ ዘመቻቸውን ሲያፋፍፍሙ ለደጋፊው "ከተመረጥኩ ዴቪድ ቤካምን አስፈርማለሁ " ብለው ቃላቸውን ባደባባይ ሰጡ :: ጉዳዩ እንዲህ እያለ ቆይቶ በመጨረሻም ሪያልማድሪዶች የቀድሞውን የማንችስተር 7 ቁጥር (ቤካም )በጃቸው አስገቡ ::ይህ ሁሉ ሲሆን ቤካም ኦልድትራፎርድን እንደሚለቅ ያወቁት ማንችስተሮች ደህና ገንዘብ መድበው ሁነኛ ተተኪ ፍለጋ አይናቸውን እያማተሩ ነበር :: አማትረውም አይናቸውን ወደ ፓሪስ በመወርወር በፓሪስ ቆይታው ብልጭ ድርግም ከሚል አስደናቂ እንቅስቃሴው ውጭ እምብዛም ያልተሳካለትን ግን 2002 ኮሪያ /ጃፓን አለም ዋንጫ ያለውን ፖቴንሻል ያሳየው ሮናልዲንሆን እንዲሸጡለት ፓሪስ ሳን ዠርመ ክለብ ጥያቄ አቀረቡ :: ፓሪሶች ባህሪው ያስቸገራቸውን ብራዚላዊ ወጣት ለመሽጥ ፍላጎቱ ቢኖራቸውም ጉዳዩን በርጋታ ለመያዝ ወደዱ :: ይህን ጊዜ ነው እንግዲ ቀዳሚ ምርጫቸውን በባላንጣቸው ማድሪድ የተቀሙት አዲሱ ተመራጭ የባርሴሎና ቡድን ፕሬዘዳንት ቃል አባይ ከመሆን ያድነኛል ብለው ያሰቡትን ሮናልዲንሆን የማስፈረም ዘመቻ የተቀላቀሉት :: ሮናልዲንሆም ወኪል /ማናጀሩ ሆኖ የሚያገለግለው ወንድሙ አማካይነት ነገሮችን እያካሄደና ብዙ የተሳከሩ መግለጫዎችን ስለእንግሊዝ ፉትቦል ; ማንችስተር ዩናይትድ እየሰጠ ፍላጎቱ ወደ ባርሴሎና ስፔን መሆኑን አመላከተ :: ቅሉ የማንችስተር ቦርድ ገንዘብ ላይ መንቀጥቀጥና የዛኔው (አሁን ቼልሲ ) ቼር ማን የነበሩት ፒተር ኬንየን የመደራደር ብቃት ደካማነት ተጨማመሮ ባርሴሎና ሮናልዲንሆን አስፈረመ :: አዲሱ 2003/04 የውድድር ዘመን ሊጀመር ቀናቶች ሲቀሩ የሪያል ማድሪድ አመራር ቦታ ካሉት አንዱ የሆነው " ሮናልዲንሆን ለማስፈረም ያልፈለግንበት ምክኒያቱ ሮናልዲንሆ መልኩ አስቀያሚ በመሆኑ ቡድኑ ኢሜጅ ጥሩ ስለማይሆን ብለን ነው ..." ብለው እየተሳለቁ ሲናገሩ ተሰምቶ ወሬው ለአደባባይ በቃ :: እግርኳስም ፋሽንሾው መስሏቸው የተሸወዱት ማድሪዶች ከታላቁ ሮናልዲንሆ መልክ በስተጀርባ ምን አይነት ድንቅ ችሎታ እንዳለ ላያዩት ግብዝ ጅልነታቸው ጋረደባቸው ::

///////////// ክፍል 2 ይቀጥላል //////////////////

*Galactiocs ይህ ቃል በስፓኒሽ ቀጥታ ትርጉሙ ከሌላ ፕላኔት የመጡ ፍጡራን ማለት ሲሆን በሪያል ማድሪድ ቡድን ውስጥ ቃሉ የሚያገለግለው ግሩም ችሎታ ያላቸው የወቅቱ ቁጥር አንድ ተቻዋቾችን ነው :: እናም በያመቱ የክለቡ ፕሬዝደንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ ከተመረጡበት አመት አንስቶ እንደፈሊጥ የያዙት አንድ ጋላክቲኮ በያመቱ ማስፈረምን ነበር :: ፊጎ ፈረመ በቀጣይ አመት ዚዳን ተከተለ በሶስተኛው አመት ደግሞ ሮናልዶ መጣ ከዚያም 2003 ባለተራው ዴቪድ ቤካም ሆነ ::

Last edited by አፍሪክ on Sun Jan 29, 2006 10:33 pm; edited 2 times in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አክየ

ዋና አለቃ

Joined: 28 Jul 2005
Posts: 2591

PostPosted: Thu Jan 12, 2006 8:36 pm    Post subject: Reply with quote

ቀጥለው እንጅ ምነው ጠፋህ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አፍሪክ

ኮትኳች

Joined: 18 Feb 2005
Posts: 450
Location: united states

PostPosted: Wed Jan 18, 2006 11:50 am    Post subject: Reply with quote

ፋንታሲ ፉትቦል

የእግርኳስ ጨዋታን ቅድሚያ ለደስታው ይጫወተዋል :: ተመልካች ፈንጥዞ መሄድ አለበት የሚል አመለካከት እንዳለው አጨዋወቱ በሜዳ የሚሰራቸው ነገሮች ያሳብቁበታል :: እንደዛም ቢሆን ግን ሮናልዲንሆ እራስወዳድ አይነት ተጭዋች አይደለም :: ጎልን ከማግባት ይልቅ ያማሩ ያለቀላቸው ኳሶችን ለቡድኑ አጥቂዎች ማሳለፍ ያረካዋል :: እነኛ ተጋጣሚ ቡድን ተቻዋቾችን ሞኝ አስመስለው የሚያስጡ ትሪኮቹ (አብዶዎቹ ) ልክ እንደሙዚቃ ቀመር ቦታቸውን የጠበቁ በመሆናቸው አይሰለቹም :: ሲያሻው በተረከዙ ያቀብላል ከፈለገም ወደሌላ አቅጣጫ ዞሮ ምንም ሳያይ ኳሲቷን ወደተቃራኒ አቅጣጫ ያቀብላል :: ይህንን ጋዜጠኞቹ No look pass ብለው ይሉታል :: ሲያሻው በጀርባኡ ሁሉ ያቀብላል :: እደግመዋለው ሮናልዲንሆ የተሰጠውን ኳስ አየር ላይ እየመጣች ፊቱን አዙሮ በጀርባው በመምታት በትክክሉ በማቀበል አጀብ ሲያሰኝ እኔን ጨምሮ ብዙዎች በቀጥታ በቲቪ አይተነዋል :: ወይ ደሞ በተከላካዩ ጨንቅላት አሳልፎ እራሱ ሄዶ ኳሷን አየር ላይ ይቀበላት እና ያነኑ ተከላካይ መልሶ በጭንቅላቱ ወደቀድሞው ቦታ ያሻግርበትና ዘወር ብሎበት ውብ በሆነ ሁናቴ ይቆጣጠራታል :: ለዛ ተከላካይ ውርደት ቢሆንም ለእግርኳስ ወዳጆች ግን ንጹህ አስደማሚ ችሎታ ሆኖብን አፋችንን ባድናቆት ያስከፍተናል :: ስፓኒሾቹ የላም ጭራ ብለው ያወጡለትን ትሪኩንስ ያውቁታል ? ኳሱዋ በእግሩአውራጣት ላይ እንደተሰፋች 360 ዲግሪ ይሽከረከራል ተቃራኒ ተጭዋቾች እዛው ፈዘው እንዳለ :: ያንን ነው እንግዲህ The Cow's Tail የሚሉት ::
ሮናልዲንሆ በወርቃማው የብራዚል ማሊያም ይሁን ባርሰሎና ቡድን ውስጥ የሚያረጋቸው ጨዋታዎች እንደብዙ ሌሎች ስታር ተጭዋቾች አራምባና ቆቦ ሳይሆን ሁለቱም ቤት ስሙን ዝናውን የጠበቀ ውጤታማ እንቅስቃሴ ያደርጋል :: ብራዚል በእርሱ ብዙ የምትተማመነውን ያህል ባርሴሎናዎችም ባደባባይ አይበሉት እንጂ ካለሮናልዲንሆ መንገዱ ሁሉ ጨርቅ በጨርቅ እንዳልሆነ ልባቸው ያውቀዋል ::

ድንቅ ጎሎች

የሮናልዶ ውጤታማነት በግሩም ጎሎቹ የታጀቡም ናቸው :: በክፍል አንድ ጽሁፌን የከፈትኩባት የባርሳን ማሊያ አድርጎ የመጀመሪያ የነጥብ ጨዋታ ሲያደርግ ያገባት አስደናቂ ጎል ብቻዋን እንድትደነቅ ሮናልዲንሆ አልፈቀደላትም :: ብዙ ተከታይ ምርጥ ጎሎችን በየጊዜው እያከለባት ይገኛል :: ባርሳ የገባበትበመጀመሪያው ሲዝን በመጀመሪያው ሱፐርክላሲኮ ደርቢ (ሪያልማድሪድ ጋር ግጥሚያ ) ጎል ባያገባም 2-1 ሲረቱ ሀቪ (Xavi) ማንም ባልጠበቀው አስገራሚ ሁኔታ ሰቅስቆ ያቀበለው ሀቪ ወደግብ ሲቀይራት ከግቡ በላይ የሮናልዲንሆ አሰጣጥን ያለም ሚድያዎች ጉድ ጉድ ሲሉ አንድ ሰሞን ከርመውባታል :: ምን እሱ ብቻ ባለፈው አመት በቻምፒየንስ ሊጉ ሚላንን ሲያሸንፉ ከኳሷ ጋር ወደዛና ወደዚ ደንሶ በግራ እግሩ የላካት መብረቅ ምት ያገሩ ልጅ የሚላን በረኛ ዲዳ ከአይኑ ፈጥናበት መረቡ ላይ የተሰካቸው :: ከቼልሲ ሲጫወቱ ደሞ ቅጣት ምት እዛው ኳሷ ቆሞ አንድ ስንዝር ሳይርቅ የተደረደሩት ተከላካዮችና ግብጠባቂው ፒተር ቼክ እንደፈዘዙ ያገባት ለዘላለም የማይረሱ በራሳቸው ጥበብ የሆኑ ግቦች ናቸው ::

ሽልማቶች ሲጎርፉ

ክፍል አንድ ላይ የተጠቀሱት ሁለቱ ሽልማቶችን ተከትለው በዘንድሮውም ምርጫ ሁሉንም ታላላቅ ሽልማቶች ማለትም ያለም ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞችና አምበሎች የሚመርጡበት የፊፋን ምርጫ አንቱ የተባሉ የአውሮፓ እግርኳስ ጋዜጠኞች የሚመርጡበት ፍራንስ ፉትቦል መጽሄት የሚያዘጋጀው ያውሮፓ ኮከብነትን ምርጫ እናም እንደኔና እንደናንተ ያሉ አንባቢያን የሚመርጡበት የወርልድ ሶከር መጽሄት ከከብነት ጠቅለሎ ባንደኝነት ጨርሷል :: ይህ በግል ሲሆ በቡድን ደሞ 2002 አለም ዋንጫ ባለድል , 2004/05 ስፓኒሽ ሊግ ከባርሰሎና ጋር ሻምፒዮን , 2005 ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ባለቤት (ብራዚል ) የሆነ ሲሆን ባሁኑ ወቅት ደሞ ቡድኑ ባርሴሎና በሊጉ ሰንጥረዥ በከፍተኛ ነጥብ ልዩነት እየመራ ነው :: በቻምፒየንስ ሊጉም የስፖርቱ ተንታኞች በአንደኝነት ያሸንፋሉ ብለው እየተናገሩ ነው :: ከሁሉም በላይ ደሞ መጪው የጀርመኑን አለም ዋንጫ ከብራዚል ጋር ባለድል እንደሚሆኑ የቅድሚያ ግምት ተሰቷቸዋል :: እነኚን ድሎች አሁን ያለው ላይ ከጨመረባቸው ገና 25 አመት ወጣት የሆነው ሮናልዲንሆ ካለምንም ጥርጥር በጣት ከሚቆጠሩ የምንጊዜም ታላላቅ ተጫዋቾች ተርታ ያስመድበዋል ::

የአድናቆት ክብር ከጠላት መንደር

ሪያልማድሪድ ከባርሴሎና ያላቸውን ፉክክርና መጠላላት እኔ እራሴ ደጋግሜ ያልኩት ነገር ነው :: ለሁለቱም ቡድን ደጋፊዎችና ተጭዋቾች ከምንም በላይ ደስታን የሚሰጣቸው ባላንጣቸዋን ሲያሸንፉ ነው :: በጨዋታ ባይገናኙ እንኳን ያንዱ ሽንፈት ለሌላው ፈንጠዚያን ይፈጥራል :: ለዚህ ጥሩ ምሳሌው 2003/04 የውድድር ዘመን ባርሴሎናዎች በዝናብ ምክኒያት በይደር የተላለፈባቸውን ለሊጉ ባለድልነት እጅግ ወሳኝጨዋታ ሪያል ቤቲስ ጋር ተጫውተው ተሸንፈውና ዋንጫውን ለቫሌንሺያ አሳልፈው ሲሰጡ ሁሉም ደብቶዋቸው ወደአገራቸው ሲመለሱአውሮፕላን ውስጥ በብስጨት ተክዘው ሳለ ድንገት ሮናልዲንሆ ማይኩን አንስቶ PA " ሰዎች ምን ነካቹ አዎ ልክ ነው ዋንጫውን ለቫሌንሺያ አሳልፈን መስጠታችን ያሳዝናል ግን ዋናው ቁም ነገሩ በዛሬው እለት ሪያል ማድሪድም ክፉኛ በሜዳው ስለተሸነፈ በዛ ደስ ይበለን እንጂ " ብሎ አስቆዋቸው ሀዘናቸውን ረስተው ካርታቸውን እየቀጠቀጡ ባርሴሎና ኤርፖርት ደርሰዋል :: የማድሪድ ሽንፈት ዋንጫን ያሳጣ የራስን ሽንፈት ሲያብስ !! አስገራሚ ከማለት ውጭ ምን ይባላል :: የዘንድሮ ሱፐርክላሲኮ ከሁለቱ የመጀመሪያው የሆነው በታላቁ የማድሪድ ሜዳ ኢልሳንትያጎ ቤርንበ ስታዲየም ተድርጎ የሮናልዲንሆ ካታሎኛ ጦር የነዚዳንና ሮናልዶን በጋላክቲኮ የተጨናነቀውን ሪያል ማድሪድ እንዳይሆኑ አድርጎ በገዛ ሜዳው 3-0 ሲታደባየው ከሶስቱ ሁለቱን ያገባው የህጻን አይነት ከልብ የመነጨ ፍልቅልቅ ፈገግታ የማይለየው ጂንየሱ ሮናልዲንሆ ነበር :: ከግራ ክንፍ እየተቀበለ እንደንፋስ ወደጎል ገስግሶ ሁለት ሶስት ተጫዋቾችን አታሎ ሁለቱንም ጎሎች ተቀራራቢ በሆነ ሁናቴ ከመረብ ዶሏቸዋል :: በተለይም ለቡድኑ ሶስተኛ ለራሱ ሁለተኛይቱን ጎል በግል ጥረቱ አርበድብዶ ሲያገባ እስታዲየሙ የሞላው የማድሪድ ደጋፊ ለባርሴሎና ተጭዋቾ የማይታሰብ በሆነ መልኩ ባንድነት ከመቀመጫው ተነስቶ ለረጅም ደቂቃ አጨብጭቦለታል ::የባርሴሎናን ማሊያ አጥልቆ እንዲህ ያለ ከመቀመጫ ያስነሳን ያድናቆት ጭብጨባን በማድሪድ ሜዳ ከማድሪድ ቲፎዞ ከሮናልዲንሆ በፊት የተቀበለ አንድ ተጫዋች ብቻ ነበር >>>>DIEGO ARMANDO MARADONA!!!!!

ጨርሻለሁ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ላህ

ኮትኳች

Joined: 29 Oct 2004
Posts: 171
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Jan 19, 2006 9:46 am    Post subject: Reply with quote

አፍሪክ
ዉብ አቀራረብ በጣም የሚጥም አቀራረብ ነበር ልክ ጨዋታውን ያየሁት ያህል ይመችህ ሮናልዲንሆንም አንተ እንደተመኘህለት ድል በድል ሆኖ ለማየት ያብቃን ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሰምፔር

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 20 Jun 2005
Posts: 64
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Jan 23, 2006 3:16 pm    Post subject: Reply with quote

በጣም ድንቅ አቀራረብ ነው ! ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ያነበብኩት ! በጣም አድናቂው ነኝ ::እሱ ሲጫወት ማየት በጣም ያዝናናኛል
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ለእኔም

አዲስ

Joined: 19 Jan 2006
Posts: 33

PostPosted: Fri Feb 03, 2006 8:30 am    Post subject: Reply with quote

ይመችህ አቦ ! እኔ ግን እንዳው ቀላቤ ፍሰሀ ተገኝ እንደሆንክ ነግሮኛል :: ተሳሳትኩ ?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አፍሪክ

ኮትኳች

Joined: 18 Feb 2005
Posts: 450
Location: united states

PostPosted: Sat Feb 04, 2006 4:50 am    Post subject: Reply with quote

ለእኔም ተሳስተሐል
እኔ ከሀገር የወጣሁት ፍስሀ ገና እውቅና ሳያገኝ ኤፍኤም ሬዲዮ መስራት እንደጀመረ ሰሞን ነው :: ካጫጭር ስፖርት ዜናዎች ውጭ ሰፊ ዘገባ ሲያቀርብ ስለማላቀው ባጻጻፍ ስታይላችን ምን መመሳሰል እንዳለን ለማየት ያዳግተኛል ::ለስፖርቱ ጥሩ ፍቅር የነበረው ልጅ እንደነበር ግን አስታውሳለሁ
*** በተጨማሪ ከላይ አድናቆትና ማበረታቻ ላቀረባቹ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia