WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የእናት ፍቅር
Goto page Previous  1, 2, 3, 4
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ፎንቃው

ኮትኳች

Joined: 20 Oct 2005
Posts: 220
Location: jamaica

PostPosted: Mon Feb 20, 2006 6:10 pm    Post subject: Reply with quote

ቀብራራው እንደጻፈ(ች)ው:
ስለ እናት ስታወሩ አስቀናቹኝ ....ተሰምቶኝም አዘንኩኝ :: እኔ እናቴ 4 አመት ልጅ እያለሁ ነው ታማ የሞተችው :: በጣም ጭላንጭል ትዝታዎች /ብልጭታዎች ብቻ ነው ያሉኝ ...... ልትወጣ ስትል በመስተዋት እያየች ጸጉሯን የምታስተካክለውን ...እና ....ታናሼ ምን እንዳለ ትጠይቀኝ የነበረውን (የሱን ቋንቋ የምረዳው እኔ ብቻ ነበርኩ ):: ብቻ ሁሌም በጣም እየናፈቀችኝ እንዳደኩ ትዝዝዝዝ ይለኛል :: በልጅነት አእምሮዬ "ሰው ለምን ይሞታል ...እንደብረት ቢጠነክር ኖሮ እኮ አይሞትም ነበር " እያልኩ ለብቻዬ አወራ ነበር :: እናቴን ስለነጠቀኝም ሞትን በጣም ነበር የምጠላው :: አንዳንዴ በጣም ስትናፍቀኝ ድንገት ካገኘኃት እያልኩ ለብቻዬ መቃብሯ ጋር እሄድ ነበር ::

ብቻ እናት ስላልነበረኝ ...አንደኛ ደረጃ ስማር በእኩዮቼ ምን ያህል እቀናና እተክዝ እንደነበር አትጠይቁኝ :: ይባስ ብሎ ... የአንደኛና የሁለተኛ ክፍል መዝሙሮች ሁሉ ደግሞ ስለእናት ብቻ ስለነበሩ በደንብ እችላቸው ነበር ...ስዘምርም አለቅስ ነበር በሀዘን :: ከጊዜ በኃላማ ያው በቃ እየለመድኩት መጣሁ ...ተቀበልኩትም :: እስካሁንም ግን እናቴን አለማወቄን ሳስበው በጣም አዝናለሁ -- እለሰልሳለሁም :: ይሄን ስጽፍላቹ ራሱ እምባዬ እየወረደ ነው :: እጅግ በጣም ደግና ሩህሩህ እናት እንደነበረኝ ሁሉም ሲያወራ ይቆጨኛል ... ቆንጅዬና በሰፈር ውስጥ ሁሉም እንደሚወዳትም ይነግሩኝ ነበር ::

ሌላው በልጅነቴ ያሳዝነኝ የነበረው አባቴ ነው ...ከራሱ
በላይ የሚወዳት ሚስቱን ሲያጣ ብዙ ነገር ደርሶበታል ::

አንዳንዴ የምገባባቸውን ገጾች አንብቤ ብቻ ከማለፍ ይልቅ አንድ ነገር ብል ብዬ አስብና .... እተወዋለሁ :: ይህን በእናት ስም የተጀመረውን አርእስት ግን እንዲሁ ስሸሸውና አይመለከተኝም ስል ደግሞስ ከፍቼው የኔን ቁስል የሚነካ ነገር ባገኝበት በሚል ስዘለው ብከርምም ዋርካን ላስጎበኘው የከፈትኩለት ወዳጄ ማንበብ ፈለገና አንተን ቀብራራውን አነበብንህ ::
የሁለታችን ችግር አንድ ነበር የኔና የአብሮ አደግ ጉዋደኛዬ ... አሁን ' ያንተ ..ሶስታችንም የናት ድሀ ነን ... እኔ እንኩዋ የናቴን አሁንም ቃሉ ይመረኛል ... መቀበል ያስቸግረኛል .. እሱ ሰው ስለእናቱ ካወራ ሆድ ይብሰዋል .. የወንድ እምባ ወደ ውስጥ ነው እሱዘንድ አይሰራም ... ሳለቅስ ይሻለኛል ይላል .. ይህው 3 አመቱ ... . እኔም ስሸሽ የከረምኩትን ርእስ በሱ ምክንያት ብከፍተውም ምንም ሳልልህ ለመውጣት ስላልቻልኩ አይዞህ ለማለት ብቻ ይህን መልእክት አሰፈርኩ :: እስቲ ጉዋደኛዬን ላዋራው ... አንተና ሌሎች እኛን መሰሎች በዚህ ስፍራ ካሉ ለሁላችንም እግዚአብሄር መጽናናቱን ይስጠን እላለሁ ::
_________________
Don't let yesterday use up too much of today.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ማህቡብ

ኮትኳች

Joined: 18 Aug 2005
Posts: 253

PostPosted: Tue Mar 21, 2006 7:55 am    Post subject: Reply with quote

A MOTHER'S LOVE

A little boy came up to his mother in the kitchen one evening while she was fixing supper,and handed her a piece of paper that he had been writing on.
After his Mom dried her hands on an apron,she read it,and this is what it said:
For cutting the grass: $5.00
For cleaning up my room this week: $1.00
For going to the store for you: $.50
Baby-sitting my kid brother while you went shopping: $.25
Taking out the garbage: $1.00
For getting a good report card: $5.00
For cleaning up and raking the yard: $2.00
Total owed: $14.75
Well,his mother looked at him standing there,& the boy could see the memories flashing through her mind.
She picked up the pen,turned over the paper he'd written on,and this is what she wrote:
For the nine months i carried you while you were growing inside me: No Charge
For all the nights that i've sat up with you,doctored and prayed for you: No Charge
For all the trying times,and all tears that you've caused through the years No Charge
For all the nights that were filled with dread,and for the worries i knew were ahead: No Charge
For the toys,food,and even wiping your nose: No Charge
Son,when you add it up,the cost of my love is No Charge.
When the boy finished reading what his mother written,there were big tears,and he looked straight at his mother and said, ''Mom I sure do love you.''
And then he took the pen and in great big letters he wrote: ''PAID IN FULL.''

Lessons:
You will never know how much your parents worth till you become a parent.
Be a giver not an asker,especially with your parents. there is a lot of give,besides money.

Advice:
If your mom is alive and close to you,give her a big kiss and ask her for forgiveness.
If she is far away-call her. if she passed away-pray for her.

Related Quote:
''God bless mu mother,all that i am or ever hope to be I owe to her.''
Abraham Lincoln

ከአክብሮት ጋር
_________________
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሳተርን

ኮትኳች

Joined: 28 Dec 2005
Posts: 359

PostPosted: Tue Mar 21, 2006 6:42 pm    Post subject: Reply with quote

አንድ አባባል አለ እስካሁን ትዝ የሚለኝ

"ፍቅር ሁሊ ቁልቁል ነው " የሚል ነው ;;

አባባሉ : ወላጅ ስንሆን ሁሊ ፍቅራችን ወደ ልጆቻችን ያመዝናል ;; ከልጆች በፊት የምናፈቅራቸው ሁሉ እናትም አባትም በልጆች ፍቅር ይተካል ;; እነዛም ልጆች አድገው ልጆች ሲኖርዋቸው ሂደቱ ይቀጥላል ;; የተፈጥሮ ሂደት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የዘመኑ አፄ

ኮትኳች

Joined: 19 Jan 2005
Posts: 248
Location: fiji

PostPosted: Thu Mar 23, 2006 7:26 am    Post subject: Reply with quote

አሪፍ ነው ሁሌም ቢሆን ለእናት ያለን ፍቅር መግለፅ ::
_________________
url=http://www.usersigs.com][/url]
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Jan 22, 2012 2:20 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም የሩቅም ሆነ የቅርብ ዘመን ተሣታፊዎች :-

ሰላም ማህቡብ :-

ይህ ሁሉ ስለ እናት ሲወሣ አንድም ሰው ለእናት ከተዜሙት ዜማዎች አንዱንም ያለመምረጡ ገርሞኝ ነው Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes ለማንኛውም ቆዬት ካሉት ዜማዎች በሟቹ ጋዜጠኛ በሰለሞን ተሰማ ተደርሶ ብዙዬ ባዜመችው ዜማ ተጽናኑ ::

ብዙነሽ በቀለ : የእናት ውለታዋ ::

የእናት ውለታዋን ባወሣ እወዳለሁ :
ደግነቷ ብዙ መሆኑን አውቃለሁ :
ወላጅ እናት እኮ ፍፁም በመንፈሷ :
ልጇን ትወዳለች አብልጣ ከራሷ ::

ዘጠኝ ወር በሆድዋ :
ከዚያም በጀርባዋ :
ጡቷን እያጠባች እኔን ማሣደግዋ ::
ዘወትር ይሠማኛል የእማዬ ድካሟ
ጥራ በማሣደግ በሴትነት አቅሟ ::

የእናት ውለታዋን ባወሣ እወዳለሁ :
ደግነቷ ብዙ መሆኑን አውቃለሁ :
ወላጅ እናት እኮ ፍፁም ሣትሰለች :
ከራሷ አስበልጣ ልጇን ትወዳለች :: (2 ጊዜ )

አባቴ ሞቶብኝ በሕፃንነቴ :
ደክማ ያሣደገችኝ ብቻዋን እናቴ ::
ሣይርበኝ : ሣይጠማኝ : ወይም ሣልታረዝ :
ነው ያሣደገችኝ እማምይ ...

የእናት ውለታዋን ባወሣ እወዳለሁ :
ደግነቷ ብዙ መሆኑን አውቃለሁ :
ወላጅ እናት እኮ ፍፁም ሣትሰለች :
ከራሷ አስበልጣ ልጇን ትወዳለች ::

የእናት ውለታዋን ባወሣ እወዳለሁ :
ደግነቷ ብዙ መሆኑን አውቃለሁ :
ወላጅ እናት እኮ ፍፁም ሣትሰለች :
ከራሷ አስበልጣ ልጇን ትወዳለች ::

እናቱን የማይወድ ሰው አለ ቢሉኝ :
ሰው ነው አልለውም አውሬ ነው ባይ ነኝ :
የዋሂቷ እናቴ : እኔን ወላጂቷ :
እጅግ ይሠማኛል እውነተኛነቷ ::

የእናት ውለታዋን ባወሣ እወዳለሁ :
ደግነቷ ብዙ መሆኑን አውቃለሁ :
ወላጅ እናት እኮ ፍፁም ሣትሰለች :
ከራሷ አስበልጣ ልጇን ትወዳለች :: (2 ጊዜ )

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሱልጣን

ኮትኳች

Joined: 03 Sep 2003
Posts: 465

PostPosted: Tue Jan 24, 2012 2:04 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወገኖች
6 አመት በኍላ ይህን ርእስ በማስታወስህ አደንቃለሁ .
ማህቡብ እንደምን አለህ ?ቤትህን ዳግም እንደምትጎበኘው ተስፋ አለኝ
ቀብራራው በልጅነትህ በሞት ስለተለዩ እናትህ ያወጋኸን ነገር የብዙውን ቀልብ በሀዘን ስሜት ሰብሮታል ::ሀዘን እንደማያረጅ ተረድቻለሁ ::
በዚህ አጋጣሚ እንደተመኘኻት አይነት የትዳር ጓደኛ ማግኘትህን ማወቅ ስለጓጓሁ ይህን ገጽ በጎበኘህበት ጊዜ አብስረን !!ምክንያቱም ጣፋጭ ህይወት እንመኝልሀለን እና !!
በተረፈ ብዙዎቻችን ስለ እናት የምናስብ ስናጣት ብቻ መሆኑ ያስገርመኛል ::በህይወት እያለች የምናመናጭቃትን ያክል አንድ ቀን እንደምንፀፀት እንኳ ብዙም አንገምትም ::
ሁሉም እናቱን ይወዳል .....የኔ ግን የተለየ ነው ::ከልጅነት እስከ ጎላማነት እናትየ ብየ ነው የምጠራት ከዚያ ውጭ አልረካም ::እናም በዚህ አመት በሆነ ጉዳይ እየመከረችኝ እያለ እኔም ሁሌም ምክርሽን አነሳለሁ ::አሁንማ እድሜም እየመከረኝ ነው በምላት ጊዜ ''አንተ ለኔ ሁሌም ህፃን ነህ 'ያለችው ነገር መቸም ማብራሪያ የሚያስፈልገው አይመስለኝም ::
መቸም ለጉራ ሳይሆን ካለሁበት ቦታ ሆኜ ስልክ ስላደውልላት 3 ቀን ከቆየ በህይወት ያለሁ አይመስላትም ::
እኔም 1 ደቂቃም ቢሆን ድምጼን አሰምቸ ሌላ ጊዜ እንደምደውል እገጻለሁ ::በጣም እፎይታም አገኛለሁ ::
ወደ አርባ እድሜ ማግስት ላይ ያለን ጎልማሳ እናት እንደህጻን ስትንከባከበው ማየት መቸም ከህሊና አይጠፋም !
እናቴ ይልሻል ሁሉም እንደየአቅሙ
ውስጤን እንዳልገልጸው አይበቃም ቀለሙ

እናትየ ...........................................
ምን ብጨነቅ ምን ብሰነቅ
ላይከፈል ውለታሽ
እኔ እንዳልሽው ህጻን ነኝ
ሁሌም አይለየኝ ይቅርታሽ ................
_________________
HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
የሳጥናኤአባት

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 27 Jan 2005
Posts: 51
Location: ethiopia

PostPosted: Tue Jan 24, 2012 5:16 pm    Post subject: Reply with quote

የናት ወላታዋን ባነሳ እወዳለሁ ደግነትዋ ብዙ መሆኑን አውቃለሁ እናቴ ሆይ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Tue Jan 24, 2012 5:52 pm    Post subject: Reply with quote

ሌላ ቦታ ለናቴ የቋጠርኍትን ይሄንን ቤት ሳየው አመጣኍት :: ለእናትስ ይገጠምላት ይዜምላት ::

'እያለሁ እናትህ

ምነው ጠይም ፊትህ

የጠቆረው ጸጉርህ

እስከዚህ ገረጣ

ቅባት ወዙን አጣ ?

በል እንካ ከቅቤው

ከወተቱም ጠጣ

ወዝህ እንዲመለስ

ቆዳህ እንዳይነጣ '

ስትይኝ የነበረውን

ሆነሽ 'ጠገቤ

ምክርሽን አስቤ

ቅባቱን ወተቱን

ገዛሁ በገንዘቤ

ቅባቱን ተቀባሁ

ወተቱንም ጠጣሁ

ግን ፊቴም አልወዛ

ጸጉሬም ከረደደ

ተወ መሆን ላዛ

ሚስጥሩ ምክንያቱ

ለፊቴ ውበቱ

ለጸጉሬ ጥቁረቱ

አሁን ገባኝ ገና

የእናትነት ፍቅርሽ

ቅባቱ ወተቱ

እሱ ኖሯልና ::
ልጅ ሞንሟናው

_________________
_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Tue Jan 24, 2012 6:02 pm    Post subject: Reply with quote

ስለ ችኮቼ የፍቅር ወግ ሳወጋ ይሄንንም ብያታለሁ -እናቴን :: ይህችን ' በይን እናቴ ብዬ ' ጽፌ ፖስት እንዳደረግሁ እዚያው ሀገር ቤት ላለች ለተማሪ እህቴ ደውዬ አነበብቤላት ...አልቅሳለች ....ሩቅ ሆኜ ' በይኝ እናቴ ' ብዬ በናፈቀ ስሜት ሳነብላት ....ሆድ ባሳት እሷም እዚያው ሆና ናፈቀቻትና አለቀሰች :: ደግ እናቶቻችንን እግዚአብሄር ይጠብቃቸው እድሜም ይስጥልን ....አሜን !

በይኝ እናቴ

የትም ብዞር ብሄድ

ካንችስ በላይ ዘመድ

ካንችስ ወዲያ መውደድ

ካንችስ ወዲያ አፍቃሪ

ራስሽን ጥለሽ ለኔ ብቻ ኗሪ

የቆሸሸ ለብሰሽ እኔን አሽቀርቃሪ

አንች ጉስቁል ብለሽ እኔን አሳማሪ

ለኔ ጠበቃዬ ሟች ተከራካሪ

ካንችስ ወዲያ ሃኪም ነርስ ተንከባካቢ

የታመመ ውስጤን በእንባሽ የምታጥቢ

የፍቅርሽን ወተት ነፍሴን ምታጠቢ

ሆድሽ ባዶ ሆኖ እኔን ምታጠግቢ

ነፍሴ በፍለጋ ተንከራታ ኳትና

አንችን የሚተካ አላገኘሁኝም አላገኝምና

ጥሪኝ እናቴ በይኝ ቶሎ

ቁጭ ብለን እናውጋ ...

ሰፈሩን እንማው እንዳምና ታች -አምና ::
ልጅ ሞንሟናው [i]

_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4
Page 4 of 4

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia