WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ጀርመን ቡንደስሊጋ 2012/13

 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት


 
View previous topic :: View next topic  
Author Message
ቲኪ _ታካ

አዲስ


Joined: 05 Jun 2012
Posts: 17

PostPosted: Tue Aug 21, 2012 9:39 pm    Post subject: ጀርመን ቡንደስሊጋ 2012/13 Reply with quote

ሰላም እግርኳስ አፍቃርያን

ይህችን ገጽ ከጀርመን ፉትቦል የተያያዙ ጉዳዮችን እንድንወያይበት ከፍቻለሁ :; እንግዲህ ብቅ እያላቹ እንድጻተፉ እጋብዛለሁ ::

የዘንድሮ ቡንደስሊጋ የፊታችን አርብ ይጀመራል :: በዚሁ በመክፈቻው ቀን የአምናው ባለጥንድ ድል ቦሩሽያ ዶርትመንድ በሜዳው ቬርደር ብረመንን ያስተናግዳል :: ይህ ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል :: በአባቱ ኢትዮጵያዊ የሆነው ቴዎዶር ገብረስላሴን ለመመልከትም ጥሩ አጋጣሚ ሆኖልናል :: ዶርመንድ ቁልፍ ተጭዋቹ ቺኒጂ ካጋዋን ማንቸስተር ዩናይትድ ሸጦ በምትኩ የአምና የጀርመን ፉትቦል ኮከብ ተብሎ የተመረጠውን ማርክ ሮይስ አስፈርመዋል ::

በተረፈ ቅዳሜ እለት ባየር ሙኒክ ከሜዳው ውጪ በመጓዝ ለመጀመርያ ግዜ በቡንደስሊጋው ለመሳተፍ የበቃውን spvgg greuther fü rth የተሰኘ ቡድንን ይገጥማል :: ባየርኖች በታም ተርበዋል :: ለተከታታይ ሁለት አመት በከባድ ተቀናቃኛቸው ዶርትመንድ ክፉኛ የተዋረዱበት ሁኔታን ለመቀልበስ ዘንድሮ ሲዝንን ቆርጠው ተነስተዋል ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቲኪ _ታካ

አዲስ


Joined: 05 Jun 2012
Posts: 17

PostPosted: Tue Aug 28, 2012 5:55 pm    Post subject: Reply with quote

ቡንደስሊጋው እንደተጠቀሰው ባለፈው አርብ ሲጀመር ቦሩስያ ዶርትሙንድ በሜዳው ቬርደር ብሬመንን 2-1 አሸንፏል :: ለብሬመን አንዷን ጎል ያገባው ቴዎዶር ገብረሰላሴ ነበር :; እንግዲህ ገብረስላሴ ለአዲሱ ሲዝን የመጀመርያ ጎላቸውን ቀድሶላቸዋል :: ቡድኑም ጥሩ ቡድን መሆኑን ባሳዩት ፉክክር አስመስክረዋል :: በባየርንም በኩል የመክፈቻዋን ጎል ያገባላቸው አዲሱ ተጭዋቻቸው ማርኮ ሮይስ ነበር :: ሮይስ ዶርትሙንድ ተወልዶ ያደገ ከመሆኑም በላይ ባየርን ሙኒኮች ሲፈልጉት ጥያቅያቸውን ውድቅ አድርጎ ለአደገበት ከተማ ከለብና የባየርን ሙኒክ ቀንደኛ ተቀናቃኝ ቦሩሽያ ዶርትሙድ የፈረመበት ሁኔታ ትልቅ ዜና ሆኖ እንደነበር ትዝ ይለናል :: ምክንያቱም ካላቸው የኢኮኖሚ ጥንካሬ አንጻር ባየርኖች እየፈለጉት ለሌላ የጀርመን ክለብ መፈረም እምብዛም ያልተለመደ ነገር ነበርና ነው :: የሮይስ ማርዮ ጎትዘ እና ሎዋንዶውስኪ አክሲስ በዩሮፕ በጉጉት የሚጠበቅ አስፈሪ ኮምቢኔሽን ነው :: እንግዲህ ወደተግባር ይቀይሩታል ወይ ነው ጥያቄው ::
ባየርን ሙኒክ furth የሚባልን ክለብ በቀላሉ 3-0 አሸንፏል :; ሰሞኑን ከክለቡ ተያይዞ ያለው ትልቁ ዜና ስፔናዊው ሀቪ ማርቲኔዝን ያስፈርሙታል ወይስ አያስፈርሙትም የሚለው ነው :: እንግዲ በጋው የዝውውር መስኮቱ ሊዘጋ 2 ቀን ቀርቶታል የሚሆነውን እናያለን :: በተረፈ ስዊትዘርላንዳዊው ሻቂሪን ከባዝል ብራዚላዊው ዳንቴን ሞንቻግላድባክ እና ክሮኤሽያዊው ማንድዙኪችን ከዎልፍዝበርግ አስፈርመዋል :: ማንድዙኪች በመክፈቻ ጨዋታቸው አንድ ጎል አስቆጥሮ የጎል አካውንቱን ከፍቷል :: የቡድኑ ስፖርቲግ ዳይሬክተር ዝነኛው የቀድሞ የጀርመን ተጭዋች ማቲያዝ ሳመር ነው :: ሳመር ባየርንን ባዲስ እያቀናጀና ቡድኑ ማራኪ ፉትቦል እንዲጫወት ጥርጊያ መንገዱን እያመቻቸው እንደሆነ ነው የሚሰማው ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

 
Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum


Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia