WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
***የየጁ ኩማንዳ ጠባ ልጆች ***
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 13, 14, 15
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

View previous topic :: View next topic  
Author Message
እሪኩም

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Apr 2005
Posts: 981
Location: ወሎ

PostPosted: Thu Aug 06, 2009 11:05 pm    Post subject: ሠላም ! Reply with quote

ሠላም ለቤቱ !

ታሪክን ታሪክ ሲያነሳው ወንድም የጁ ባስታወስከኝ መሰረት ይኽው ወደ ቤታችን ጐራ ብዬ እህታችንን ለማሥፈር ተገድጃለሁ :: በጣም አመሰግናለሁ :: ብቅ ብለህ ሃሳብህን ሰንዝር በለው ጃል ::

የራያ ልጅ (ብርሃኔ ገብረ ሚካኤል )

http://www.youtube.com/mertoabet#play/favorites/3/T167FSZLeNs

............>>>>>>

ሳይነኩት አይነካም እንደ ነብር ልጅ :
እንኳንሥ ለራሡ ለሰው የሚበጅ ::

ለወደደው ማር ነው ለጠላው ሬት :
ወገኑን አክባሪ የአዝመራው አባት ::

............>>>>>>>

መልካም ጁማ
እሪኩም ከቦሩ ሜዳ

_________________

መሸፈት ያለ ነው ይጠየቅ ልብሽ :
ሥንድድ እና ድንብል አሸን ክታብሽ ::

http://www.cyberethiopia.com/warka5/viewtopic.php?t=23129
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሀራ

መንገደኛ

Joined: 12 Aug 2009
Posts: 0
Location: non

PostPosted: Tue Aug 18, 2009 1:21 pm    Post subject: የየጁ ልጆች ብቅ ብቅ በሉ Reply with quote

ሰላም ለየጁ ታዳሚዎች ሁሉ
ለዚህ በቱ እግዳ ነኝ ግን ይህንን አምድ ሳይ በታም ነው ያስደሰተኝ ምክንያቱም ስለ የጁ የምተይቀው ሰው አጥቸ ነበር
አጋታሚ ሆኖ ግን ይህንን ሳይት ስመለከት በታም አስደሰተኝ ምስጋና ለናተ ይሁን እነ የጁን ከተለየሁ በታም ብዙ ጊዘ ሆነኝ እናም ስለ ወልድያ ዶሮግብር መርሳ ሲወራ ከሰማሁ በታም ቆየሁ
አሁንም የማስችሀግራችሁ ቢኖር ስለ ወልዲያ እና ሃራ ሁነታ በቅርብ የሚያቅ ካለ ብታሳውቁኝ እላለሁ
ለምታደርጉልኝ ትብብር ሁሉ

ምስጋናየ ይድረስ [/url][/list][/list][/code][/quote]
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ሀራ

መንገደኛ

Joined: 12 Aug 2009
Posts: 0
Location: non

PostPosted: Fri Sep 04, 2009 12:51 am    Post subject: Reply with quote

የጁ እንደጻፈ(ች)ው:
ሠላም ያገር ልጆች ! ውድ እለፈው አብሽር አንተን ማዳመጥ እንዳይሰለችህ እንጅ ስለወሎስ ተወርቶም አያልቅ Wink

ወዳጄ ጦሳው እንደምናለህ ? ተራራ ላይ ሰፍረው የነበሩት ሼህ ታዬ (የአሩሲው ሼህ ) በመባል ይታወቁ ነበር የነበሩበትም ቦታ ውድመን ይባል ነበር ::

ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ::

ፖሰት የተደረገ : ማክሰ Aug 18, 2009 3:21 pm ርዕስ ፖሰት ያድርጉ : የየጁ ልጆች ብቅ ብቅ በሉ

--------------------------------------------------------------------------------

ሰላም ለየጁ ታዳሚዎች ሁሉ
ለዚህ በቱ እግዳ ነኝ ግን ይህንን አምድ ሳይ በታም ነው ያስደሰተኝ ምክንያቱም ስለ የጁ የምተይቀው ሰው አጥቸ ነበር
አጋታሚ ሆኖ ግን ይህንን ሳይት ስመለከት በታም አስደሰተኝ ምስጋና ለናተ ይሁን እነ የጁን ከተለየሁ በታም ብዙ ጊዘ ሆነኝ እናም ስለ ወልድያ ዶሮግብር መርሳ ሲወራ ከሰማሁ በታም ቆየሁ
አሁንም የማስችሀግራችሁ ቢኖር ስለ ወልዲያ እና ሃራ ሁነታ በቅርብ የሚያቅ ካለ ብታሳውቁኝ እላለሁ
ለምታደርጉልኝ ትብብር ሁሉ
_________________
////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message AIM Address Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ወልዲያ

ዋና ኮትኳች

Joined: 17 Apr 2007
Posts: 596
Location: የጁ - ወሎ

PostPosted: Wed Sep 09, 2009 5:32 pm    Post subject: አርብ መስከረም 1, 2002 Reply with quote

ሠላም ለየጁ ልጆች እና ታዳሚዎች !

ታደስ ዓለሙ (አውድ ዓመት )

http://www.youtube.com/mertoabet#play/all/favorites-all/0/A4DozMF7taI

መስከረም 11, 2009 (መስከረም 01, 2002) አርብ ዕለት የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ይከበራል :: እንኳን ለኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በሠላም እና በጤና አደረሳችሁ ::

ፍቅር ጀባ
ወልዲያ - የጁ

_________________

አንድ ኢትዮጵያ
http://www.cyberethiopia.com/warka5/viewtopic.php?t=28757
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እሪኩም

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Apr 2005
Posts: 981
Location: ወሎ

PostPosted: Sat Nov 07, 2009 1:15 pm    Post subject: የጁ Reply with quote

ሠላም !

የጁ ለመሆኑ አለህ ወይ ?

ፍቅር ጀባ
እሪኩም ከቦሩ ሜዳ

_________________

መሸፈት ያለ ነው ይጠየቅ ልብሽ :
ሥንድድ እና ድንብል አሸን ክታብሽ ::

http://www.cyberethiopia.com/warka5/viewtopic.php?t=23129
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የጁ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 28 Sep 2006
Posts: 66

PostPosted: Sat Nov 07, 2009 3:03 pm    Post subject: Reply with quote

ሠላም ሠላም ለቤቱ !!

እሪኩሜ አማን ነህ ዎይ ? አለንለት ይኸው ክብሩ ይስፋ :: ይህንን የተዳፈነ ቤት ወደዚህ ስላመጣኸው ምስጋናየ ይድረስህ ........ እኔም አንድ ብየ ልውጣ

ፈተና !

ይመስለኝ ነበረ የችሎታ መለኪያ

ጠንክሮ የሰራውን ከሰነፋ መለያ

አመት ወይም መንፈቅ የተማረውን

ማሳያ ነበረ የዕውቀት ልኩን

እንዳሁኑ ሳይሆን የቀድሞው ፈተና

ጎበዝ ለመለየት ነበር ለምዘና

ዛሬ ግን በምድር ላይ ፈተና ተዘርቶ

ጎተራው እስኪጠብ አለቅጥ ተሞልቶ

ሞሰቡም ሰፌዱም በፈተና ሞልቶ

ለረሃብ ማስታገሻ ፈተና ተበልቶ

ገበያ ቢወጡ ፈተና ሼምቶ

ሰማይ ቢያንጋጥጡ ተስፋ የለው መና

አራት አምስት ደርዘን ይወርዳል ፈተና

እንግ ቢመጣም ማን ያፈላል ቡና

የተለመደውን ማቅረብ ነው ፈተና

ምን አርገው ሊያመልጡ ከፈተና ከቶ

ቅቤ ተራ ቢሆን እሱ መቸ ጠፍቶ

ሙዝ እና ቅቤውን በአንድ አዋህዶ

ሲሸጥ ያገኙታል ዋጋውን አዋዶ

አንድ ላይ ደባልቆ ሼክላና በርበሬ

ይሼጥልዎት የለ ፈተና አጅሬ

አሼዋና ጤፍም አንድ ላይ ሆኑና

ጭነውልዎት መጡ አሁንም ፈተና

የበቀለ ከሥር ከላይ ትንሽ ደህና

ሽንኩርት ተራም ቢሆን አለዎት ፈተና

ወገቡ እማይሰፋ ቁመቱ እማያጥር

ይችን ይሼምቱ ከያዙ ጥሩ ብር

ውሸቴን አይደለም እግዚያብሄር ይመስክር

እያለ ሰብኮዎት የገዙት አልባሳት

ከፊት አርገው ሲያዩት ባይሆን እንዳሰቡት

ልክ አልሆንም ብሎ በጣም ቢቸገሩ

ቢበሽቁ ቢነዱ ቢገርምዎት ነገሩ

ፈተና ከማለት ምንም አይጨምሩ

ለክፉም ለበጎም ብለው ያኖሩት

ለቤት ጣጣም ሆነ ለልጆች ትምርት

ጠቃሚ ያሉትን አስበው ለመግዛት

ደፋ ቀና ሲሉ ቶሎ ቢመለሱ

መሃል ዘልቀው ገብተው ወደ ትርምሱ

ዘወር ብለው ሲይዩ ኪስዎ ተገልብጦ

ማመን እያቃተዎት አይንዎ ብቻ ፈጦ

ቦርሳዎ ቢጠፋ ለብዙ ያሰቡት

ከፈተና በቀር ምን ሥም ሊያገኙለት

ወደ ተጠሩበት ሠርግ ቤት ለመድረስ

የክት ልብስዎን ለብሰው ጀምረው መገስገስ

ጥቂት እንደሄዱ ከኋላዎ መጥቶ

የተበተ ሾፌር ጭቃውን ረጭቶ

የለበሱትን ልብስ በጭቃ ቢያበላሽ

ፈተና ከማለት ሌላ አለዎት ምላሽ ?

የተዘራው ሰብል ክው ብሎ እንዳይደርቅ

መሬትዎን ሊያርሱ ዝናቡ ሲጠበቅ

ጓል ጓል የሚያካክል በረዶ ቢወድቅ

ፈተና ነው እንጅ አይባልም ድንቅ

አልለቅ ቢልዎት ቆሻሻ ሲያጥቡት በሳሙና

ማለትዎ አይቀርም አሁንም ፈተና

ድንገት ከዚህ ዐለም ሲለዩ በሞት

ቄሱ አልተገኙም ለማድረግ ፍታት

ተብሎ ቢዘገይ የቀብርዎ ሥራት

ከፈተና በቀር ምን ሥም ሊያወጡለት

እባክህ አምላኬ ወይ ፈተና ቀንስ ወይም ጥራኝ ቶሎ

ሚሊዮን ፈተና ሳይወጣ ገንፍሎ

አልፋለሁ ባልልም ውድቅቴ እንኳን እንዲያምር

አቅል ፈተናውን እባክህ እግዚያብሔር ::
_________________
Diqaw Ke Kumandateba
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ማን

መንገደኛ

Joined: 20 Mar 2004
Posts: 2

PostPosted: Mon Nov 30, 2009 5:01 am    Post subject: Reply with quote

የየጁ ልጆች ስማቺሁ ብቻ አስደሳች አሁንስ የት አላቺሁ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የጁ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 28 Sep 2006
Posts: 66

PostPosted: Mon Dec 14, 2009 7:11 am    Post subject: Reply with quote

ያውም ለሞተ ሠው !

ያውም ለሞተ ሠው ለተገላገለ

ስንቄን ማቄን ጨርቄን አምጡልኝ ላላለ

የምን ደረት መምታት የምን ዕምባ ማፍሰስ

የምን አንገት መድፋት ለምን ከል መልበስ

ማልቀስስ በቁሙ ግራ ለገባው ሰው

ኑሮውን መከራ ችግር ላቃወሰው

እሪ ይበል እንጅ ጸጉሩንም ተላጭቶ

በውኑ ለሞተ አስታዋሽ አጥቶ

በገዛ ሀገሩ ለሆነ አገር አልባ

ሙሾውም ይደርደር እምባውም ይነባ

ግን እንዳቅሙ ኑሮ ፈጣሪ እንዳደለው

የሞተ ሠውማ ምንም ሃጥያት የለው

ማልቀስ በምድር ላይ ሳይሞት ሳትቀበር

እያለ ለሌለው በሆነ ውብ ነበር

ሃገሩ ላይ ሆኖ ሃገር ለናፈቀው

ከሚሊዮን ወገን አንዱም ላልጠየቀው

በጨለማ ጉዞ ጨለማ ለገባ

እና እናፍስስለት መራራውን እምባ

_________________
Diqaw Ke Kumandateba
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እሪኩም

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Apr 2005
Posts: 981
Location: ወሎ

PostPosted: Thu Dec 24, 2009 4:36 pm    Post subject: መልካም ገና Reply with quote

ሠላም ለሁሉም !

ናፈቀኝ ሃገሬ ጨዋታ እና ለዛው :
ብቸኝነት ጥሎ አብሮ ሚቋደሰው ::

____________________________________
ይቅር የሰው ሀገር (ሰማሃኝ በለው )
http://www.youtube.com/watch?v=qaRSWDAp35A
____________________________________

ውጭ መኖር ማለት ደልቶን ስላልሆነ :
አዙረን እንዬው ወፈረም ቀጠነ ::

አንድነት ኃይል ነው አብረን እንጓዝ :
አሜኬላ መጥፎ እናጥፋ ነቀዝ ::

እንኳን ለአውሮፓውያን አዲስ ዓመት (2010) እና ለኢትዮጵያ ገና በፍቅር እና በሠላም አደረሳችሁ ::

እሪኩም ከቦሩ ሜዳ

_________________

መሸፈት ያለ ነው ይጠየቅ ልብሽ :
ሥንድድ እና ድንብል አሸን ክታብሽ ::

http://www.cyberethiopia.com/warka5/viewtopic.php?t=23129
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
belew70

አዲስ

Joined: 18 Dec 2009
Posts: 40

PostPosted: Fri Dec 25, 2009 5:37 am    Post subject: Reply with quote

አሰፋ አባተ ጎበዝ ድምጠኛ ነበር :: I'm surprise nobody mentioned his name here. I believe he was one of the founding member of Hager Feker, born in Woldia. የማትበላ ዎፍ was one of his famous hits in 1950's EC calendar. He died before the revolution.

http://www.youtube.com/watch?v=UfMJZpXz2XQ
played by Dereb Zenebe.
_________________
http://korokonch-sefer.blogspot.com/

Old forgotten articles, excerpts, interviews comes to life
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
እሪኩም

ዋና ኮትኳች

Joined: 01 Apr 2005
Posts: 981
Location: ወሎ

PostPosted: Mon Jan 03, 2011 5:40 pm    Post subject: መልካም ገና Reply with quote

ሠላም ለቤቱ !

እንዴምናችሁ ?
መልካም ገና ለሁሉም !

ከሰሜን እስከ ደቡብ ያላችሁ እሕቶች፣
ከሰሜን እስከ ደቡብ ያላችሁ ወንድሞች፣
ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ ያላችሁ እሕቶች፣
ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ ያላችሁ ወንድሞች፤

ሠላም፣ ፍቅር እና ጤና እግዛብሔር ይስጣችሁ፣
ሠላም፣ ፍቅር እና ጤና አላሕ ይስጣችሁ፣
ልዩነት አጥፉና አንድ ይሁን ልባችሁ፣
የፊታችን ገናም በር ይክፈትላችሁ፣
ሠብሠብ በሉና ይመር ጨዋታችሁ፣
ተንኰል እና ሤራን ያምዘግዝግላችሁ።

ፍቅር ጀባ
እሪኩም ከቦሩ ሜዳ

_________________

መሸፈት ያለ ነው ይጠየቅ ልብሽ :
ሥንድድ እና ድንብል አሸን ክታብሽ ::

http://www.cyberethiopia.com/warka5/viewtopic.php?t=23129
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሾተል

ዋና አለቃ

Joined: 13 Jan 2005
Posts: 6811
Location: Vienna-Austria

PostPosted: Tue Jan 04, 2011 12:57 pm    Post subject: Re: መልካም ገና Reply with quote

እሪኩም እንደጻፈ(ች)ው:
ሠላም ለቤቱ !

እንዴምናችሁ ?
መልካም ገና ለሁሉም !

ከሰሜን እስከ ደቡብ ያላችሁ እሕቶች፣
ከሰሜን እስከ ደቡብ ያላችሁ ወንድሞች፣
ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ ያላችሁ እሕቶች፣
ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ ያላችሁ ወንድሞች፤

ሠላም፣ ፍቅር እና ጤና እግዛብሔር ይስጣችሁ፣
ሠላም፣ ፍቅር እና ጤና አላሕ ይስጣችሁ፣
ልዩነት አጥፉና አንድ ይሁን ልባችሁ፣
የፊታችን ገናም በር ይክፈትላችሁ፣
ሠብሠብ በሉና ይመር ጨዋታችሁ፣
ተንኰል እና ሤራን ያምዘግዝግላችሁ።

ፍቅር ጀባ
እሪኩም ከቦሩ ሜዳ

ማነኽ አንተ አሽቃባጭ ...ከሴቶች የወሬ እድር የማትጠፋው እሪኩም የሚሉህ ሉዘር ....አሁንም በህይወት ተስፋ ሳትቆርጥ አለኽ ?ከላይ የጻፍከው ግጥም ነው ስድ ንባብ ነው ወይስ የባለጌ ንባብኛ ነው ?ግጥም በኛ ጊዜ ቀረ ....አንተን እንደው እዛ ሳንቃ ዘወር ጎተራ ሚካኤል ወስዶ ጉዋያ ሆድህ እስኪተረተር አብልቶ አችመድምዶ ያያቴን እርሻ ወፍ ጠባቂ ማድረግ ነበር ::

እረ ቆይ ሁሉ ዋርካን በሞኖፖል ይዞ ማጨመላለቁ የት ቀረ ?እናንተ ጊንጦች ባጠቃላይ ምን በላችሁ ? ሁሉ እዩኝ እዩኝን የት ከተታችሁት ?በህይወቴ በግሩፕ ሆኖ እዩኝ እዩኝ ብሎ የሾተል ሾተል ሲሸልታቸው ባንድ ላይ ደብቁኝ ብለው የጠፉ ሰዎችን ሳይ ለመጀመርያ ጊዜዬ ነው ::እንግዲህ እንዳንተ ከላይ እንደጻፍከው ግጥም ይሁን ምን የማይታወቅ ጽሁፍ እየጻፋችሁ ነበር አድናቆት በባዶ ስትቸሩ የነበራችሁት ::በሉ ውጡ ....አሁንማ በእውቀት ገንትረናል ...የናንተን ጽሁፍ አያሳየኝ እንጂ መተልተል አይደለም ብትንትኑን አውጥቼ በመገምገም ወይ አስተምራችሁዋለሁ ወይ እንደሰው ክሪቲክ መቀበል ምን እንደሆነ አሳያችሁዋለሁ ...ወይ ለሱሳይድነት እዳርጋችሁዋለሁ ::አያገናኘን ብለኽ ጸልይ ...

እንደገና ስትሞጋገሱበት የነበረው ፓልቶካችሁ እንደ ጧት ጤዛ ወዴት ግድም መከነ ?

ወለዬዎች እንዳንተ የሳር ውስጥ እባብ መሰሪዎች አይደሉም ::ገር የዋሆች እንካችሁ በሞቴ የሆኑ መልከ መልካሞች ናቸው ::አንተ ከየት ሲኦል እንደመጣኽ አይታወቅም ....እባብ አመሉን አይቶ እግር ነሳው እንደተባለው አንተንም ክፋትህን አይቶ ከወሬኞች ሸረኞች ነገረኞች ጎራ አዋለኽ ....ወንድነትኽን የሸጥክ ....ወለዬዎች ባሉበት ወለዬ ለመምሰል እራስኽን አታላልጥ ...የገና የፈላ ውሀ ያገንትርህና ...ሳይኽ ታስጠላኝ ጀመር .....ድንባዣም ::

ምርቃና የሚሉት አንተን ጀለብያ ውስጥ ከቶ ከወሸመህ ጊዜ ጀምሮ ጾታህን አለማስቀየርኽ ድንቅ ይለኛል ....የሆንክ የቼክ አገር አዛባ ....

ይኽ የአዲስ አመት ላንተ ስጦታዬ ነው ::

በወሎ ስም አትነግድ ::አንተ እንኩዋን ወለዬ አይደለም ኢትዮዽያዊም አይደለኽም ...ክፉ ...የሂትለር ሰገራ ::

ባክህ ይብቃኝ ..ይኼን ያህል ሰላምታ ካቀረብኩልኽ ይብቃኝ ::

ለቤቱ ይቅርታ ::በወለዬዎች ሲነግድ አግኝቼው ነው ይኼንን አዡዛም ::

ሾተል ነን .......ከጠዶት ማርያም ....የሳንቃን ሸንኮራ ባይነ ህሊናችን እያየን ...ካፋፉ ሆነን አይዋን እየጠራን
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
www.shottel.webs.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቦሮቦጭ

ኮትኳች

Joined: 25 Jul 2005
Posts: 168
Location: ethiopia

PostPosted: Wed Jan 05, 2011 8:47 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም አቶ እሪኩም እና አቶ ሾተል ...... የወጋ ቢረሳ ቂም አለባችሁ እንዴ ?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የጁ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 28 Sep 2006
Posts: 66

PostPosted: Tue Apr 10, 2012 7:01 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ያገር ልጆች Smile
_________________
Diqaw Ke Kumandateba
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የጁ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 28 Sep 2006
Posts: 66

PostPosted: Wed May 16, 2012 6:55 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም አረዳው !

ዎይ ወልድያ አይ ዘመን ...... ሃያ ሳንቲም ምን የመሰለ ቁርስ የሚበላበት ዘመን ላይመለስ ኮበለለ ... ጣፋጭ ሚስቶ ሲያምረን ወደ ዘራይ ደረስ ምግብ ቤት ጎራ ስንል በመልካም መስተንግዶ ይቀበሉን ነበር ወይዘሮ ንግስቲ እንደ ጣሊያኖች ስፓጌቲ ሲያምረን ደግሞ ወደ መብራት ብስራት ብቅ እንላለን ታዲያ ሁልጊዜ እዛ የማይጠፋው ሲኛር አሌኖን ነበር በቅድሚያ የምናገኘው ::

ጠንከር ጠጅ ሲያምረን ደግሞ አዳነ ካህሳይ ወይንም ደጃች ጎበና ቡና ቤት ደርደር ማለት ነው .... ይህንን ስል እነ ጄሪካንና ምን ጨገረኝን ሳልዘነጋ ነው :: በቅመም የተጥለቀለቀ ጥብስ ሲያስፈልገን ደግሞ አንድነት የእስላም ምግብ ቤት እነ ሮመዳን መሀመድ ቤት መሄድ ነበር :: ታዲያ አባ ሸሁ ቤት አንድ ፈታ ስታዝዝ በክቡር ዘበኛ ብርጭቆ ሙሉ ቅቤና እርጎ ይሰጥህ ነበር እናም ለዚህ ሁሉ ሐያ ሳንቲም ብቻ ነበር የሚከፈለው ...ታዲያ ላህያ ማር አይጥማትም ሆነ እና በላተኛው አባ ሸሁ ምነው ልብሳችን እስኪበላሽ ቅቤውን አበዙብን ብለው ያጉረመርሙ ነበር አይ አሁንማ ሽታውም እርቆናል አሉ እማማ አማከል Smile ጥሩ አናጺ ሲፈልጉ ወደ በላይ አንዳሩ ወይንም በርሄ ወደ እነ መዝገቡ አበጋዝ ቤት ጎረቤት ወደ ሆኑት ብቅ ማለት ነበር አሁን እነዚህ ሰዎች በርግጥ ግማሽ የሚሆነው አልፏል ያለውም ተሰዷል በጊዜ መለኪያ ወርቅ መባል ከተቻለ ወርቁ ጊዜ ላይመለስ ኮብልሏል ::

ቸር እንሰንብት

_________________
Diqaw Ke Kumandateba
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 13, 14, 15
Page 15 of 15

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia