WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ያኔ ............
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ክርስትያን 06

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Sep 2006
Posts: 501

PostPosted: Wed Oct 18, 2006 3:53 pm    Post subject: Reply with quote

በዳበሳ እጄን ዘርግቸ አጠገቤ ያለውን የብርጭቆ ውህ ጅው አድርጌ የተቃጠለውን ጉሮሮየን አለሳልሸ እየተደናበርኩ ወደ መታጠቢያ ቤት ልሂድ ስነሳ ነበር በላየ ላይ ምንም ልብስ አለመኖሩን የተገንዘብኩት ;; ሰአቱን ሳይ ከንጋቱ 5ፒም ነው ;; ቆንጂት እንደተለመደው ተንዘራፍጣ ያልጋውን ግማሽ ይዛ ተንጋላለች ;; ላተኛኘትዋ ግድ የላትም ;; ብዙ ስለተላመድን ነው መስለኝ ቤት አብረን ካለን ልብስ የሚባል ነገር ላያችን ላይ አይቆይም ;; ገና ቤት እንደገባች ውልቅልቅ አርጋ ያለልብስ መቆየትን ትወዳለች ;; ነጻነትን የመሰለ ምን አለ ? የሚል አባባል አላት ;; ብቻዋን ስለምትኖር ይህንን ነጻነትዋን አጥብቃ ትወደዋለች ;; የሰው ልጅ በራሱ ህግ የተተበተበ ፍጡር ነው ;; እንደራሱነቱ የማይኖር ፍጡር ነው ትላለች ;; በቀን ውስጥ አብዛኛውን ስንዋሽ እንደምንውልና ያልሆነውን ሆነን ስለምንገኝ ነጻነቴን የማገኘው ቤቴ ስለሆነ ማንም እንዲነጥቀኝ አልፈልግም የሚል አባባል አላት ;; በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ጊዜ ተመሳሳይ እምነት ቢኖረኝም አንዳንዴ የምታሳየው ግድየለሽነት ስለሚበዛብኝ ሳልወድ በግድ እከራከራታለሁ ;;ራስሽን ከመጠን በላይ ከመውደድ የተነሳ የመጣ እምነት ነው ;; ስለራስሽ እንጅ ስለ ማህበረሰቡ ደንታ የለሽም ;; ሁላችንም የዚህ ማህበረሰብ ውጤት ነን ;; የምንወደውን እየተንከባከብን የምንጠላውን ማሻሻል የኛ ግዴታ ነው ;; ;ለመጭው ትውልድ ምንነት ማንነት የኛ የዛሬ ስራችን ወሳኝ ነው ;; ክርክራችን አያልቅም ;; ግን አንዳንዴ እወደዋለሁ ;; የዚህ አይነቱን ጠለቅ ያለ የማህበራዊ ጉዳዮችን ችግሮችን ከርሱዋ ካልሆነ ከማንም ጋር አላወራም ;;

ትናንት ማታም ይህንኑና ሌሎችንም ማህበራዊ ጉዳዮችን አንስተን ማውራታችንና ከሞላ ጎደል ትዝ ይለኛል ;; ከሴክስ ውጭ በሚያስማሙንም ሆነ በማያስማሙን ብዙ ጉዳዮች ላይ ማውራታችን መከራከራችን መስለኝ ለግንኙነታችን መዝለቅ ምክንያት የሆነው ;; ግንኙነታችንን በጣም ትወደዋለች ;; ግዳጅ የሌለበት በነጻ አእምሮ ላይ የተገነባ የሚል አባባል አላት ;; ባካቢያችን ከምትገኘው ትንች ፐብ ነበር ያመሸነው ;; የሰውነትዋን ቅርጽ አጉልቶ የሚያሳይ ጂንስ ለብሳለች ;; እንደተለመደው ጸጉርዋን ለቃው በጀርባዋ ተንፈላሶ ቀሪውን ደግሞ ከግራ ወደቀኝ ከቀኝ ወደ ግራ ታተራምሰዋለች ;; አብረን ስናመሽ በተለይ የዳንስ ምሽት ካለ ትልቁ ችግራችን መጨረሻ ላይ መፈላለጉ ነበር ;; ለዳንስ የማያስነሳት የለም ;; እኔም ዞረን ተመልሰን እንደምንገናኝ ስለማውቅ ብዙም ግድ የለኝም ;; ራስዋን ነጻ ማድረግ እጅግ የምትወደውን ያህል ለራስዋ ትልቅ ክብር እንዳላት በሚገባ አውቃለሁ ;;

እለቱ እሁድ ስለነበር ቁርስ ከተኛችበት ላቀርብላት ለማዘገጃጀት ኪችን ስንጎዳጎድ ነበር ሳላውቀው ከህዋላየ ጀርባየ ላይ ፊጥጥ ብላ የተሳፈረችው ;; ሁለታችንም አምላክ በገነት ውስጥ ያኖረን ይመስል በላያችን ምንም ሳንለብስ ተያይዘን ከኪችን ወለል ላይ ተዘረፈጥን ;; ያዘጋጀሁት እንቁላል አንድ ባንድ እተሰበረ በላያችን ላይ መፍሰሱን እንክዋን አላስተዋልንም ;; ከንፈርዋ በከንፈሬ ውስጥ ቀልጠ ;; እንደተራበ እንሰሳ መላው ሰውነቴን አዳረስችው ;; ስልታዊ በሆነ መንገድ ዝቅ ባለች ቁጥር የኔም የርስዋ ስሚታዊ ሲቃ እየጨመረ ........... ወደማይታውሰው ነጥብ ላይ ደረስን ;; ቆይተንም በወለሉ ላይ ተንጋለን ሳቃችንን ለቀቅነው ;;
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Debzi

ዋና አለቃ

Joined: 02 May 2004
Posts: 2790
Location: Los Angeles, CA

PostPosted: Wed Oct 18, 2006 5:33 pm    Post subject: Reply with quote

ክርስቲያን 06.....ታሪኩንም አተራረክህንም ወድጀልሀለሁ :: አጠር አጠር ብሎ first person የሚነገር ጽሁፍ ደስ ይለኛል በተለይ ::
ይቅርታ ጣልቃ ስለገባሁ ::
_________________
Ke akbrot selamta gar!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አክየ

ዋና አለቃ

Joined: 28 Jul 2005
Posts: 2591

PostPosted: Wed Oct 18, 2006 6:03 pm    Post subject: Reply with quote

መጀመሪያ ሳታስፈቅጅ ማን ጣልቃ ግቢ አለሽ ይቅርታ ከመደርደር
_________________
"Say what you have to say in the fewest possible words"
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሂሩትዬ

አዲስ

Joined: 07 Aug 2006
Posts: 21
Location: italy

PostPosted: Wed Oct 18, 2006 7:15 pm    Post subject: Reply with quote

የተደበቁ ችሎታዎች እየወጡ ነው እሰየው ያሰኛል ያልተንዛዛና ልብ የሚያንጠለጥል ሀሪፍ ድርሰት ነው በርታ እና ደሞ ቶሎ ቶሎ ጻፍ ልባችንን አታንጠልጥለው
አክባሪህ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክርስትያን 06

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Sep 2006
Posts: 501

PostPosted: Wed Oct 18, 2006 8:19 pm    Post subject: Reply with quote

ደብዚ አመሰግናለሁ ..... አክየ በጣም ነው ያሳቅህኝ ....

ቶሮንቶ ጭፍግግ ብሎዋታል ;; ትናንት ማታ የጣለው በረዶ ተዝቆ የሚያልቅ አይመስልም ;; ዛፎች ጭምር ሆን ተብሎ በነጭ ጥጥ ያጌጡ ይመስል ቅጠላቸው በበረዶ ተሸፍኖአል ;; በሰመር ሁሉ ሳር የበቀለበትና በካናቴራ የወጣንበት አገር አይመስልም ;; አሻግሬ ሳይ የቤት ባለቤቶች በወፍራም ልብስ ተጀቡነው በረዶ ይጠርጋሉ ;; አሁን ምን ቸግሯቸው ነው በክረምት በረዶ ለመጥረግ በበጋ ሳር ለማጨድ ቤት የሚገዙት እያልኩ በመገረም አያቸዋለሁ ;; በራስ ላይ ስራ ማብዛት ...... ድንገት ስልኩ አንጫረረ ..... እህቴ ስላም ነበረች ;; ምሳ አብረን ቤት እንድንበላና በዚያውም ልጆቹንም እንዳያቸው ነበር አደዋወልዋ ;; ሰላም እህት ብቻ ሳትሆን ለኔ እንደ ግዋደኛም ናት ;; ሁሉንም ነገሬን ታውቃለች ;; የምደብቃት ነገር የለም ;; እንዳገባ የምታደርገው ጥረት ሁሉ አልሳካ ብልዋት ተስፋ የቆረጠች ይመስላል መስለኝ ብዙም አታነሳብኝም ;; ለነገሩ በጨቀጨቀችኝ መጠን የምሸሻት ስለመሰላት እንደሆነ ገብቶኛል ;;

ስልኩን ዘግቸ ላንድ አፍታ በህሳብ ጭልጥ ብየ አገር ቤት ገባሁ ;; ብዙ ዘመዶቼንና የሰፈር ልጆች ከዛም አልፌ የት /ቤት ግዋደኞቸ ልክ እንደ ፊልም እየተቀነባበሩ ከፊቴ አያቸው ጀመር ;; የት እንዳለ አላውቅም ;; ከማውቃቸው የልጅነት ግዋደኞች የማገኘው ቆንጂትን ብቻ ነው ;; ገዛህኝ ግን አልፎ አልፎ ይጽፍልኝ ነበር ;; የቆንጂትን አድራሻ እንድሰጠው ጠይቆኝ ቆንጂት ተቆጥታ እንዳልሰጠው ካስጠነቀቀችኝ በህዋላ ግኑኘነታችን እየቀዘቀዘ እንደመጣ አስታውሳለሁ ;; በቅርቡ ግን አሜሪካ መምጣቱን ስለሰማሁ አንድ ቀን እንገናኝ ይሆናል በሚል ተስፋ ትቸዋለሁ ;; የቆንጂትና የገዛሕኝ ንኪኪ አልፎም ቆንጂት ለርሱ ያላት የመረረ ስሜት ግን ሁሌ የሚቆረቁረኝ ጉዳይ ነበር ;; ትዝ ይለኛል አንድ ቀን ቆንጂትን ስለገዛህኝ ጠይቂያት ፊትዋ ሲለዋወጥና እንባ ስያቅራት ካየሁ ወዲህ በድጋሜ እንደማላነሳባት ቃል ገብቼላት ስለነበር የውሾን ሥም ያነሳ ብየ ትቸዋለሁ ;;

የፈረንጆቹ ገና መድረሱ ግርም እያለኝ በመስሪያቤት በተለይም በዲፓርትመንታችን ስለተዘጋጀው አመታዊ የምሽት ፕሮግራም እያሰላሰልኩ ወደ እህቴ ቤት ማዝገሙን ተያያዝኩት ;; የሰሞኑ የሩፒ ድፍረት , የአንድሪያ ዝንባሌ የቆንጂት ለበአሉ ሰሞን ፕሮግራም እንዳይኖረኝ የነብረውን ውትወታ እንዴት እንደማስታርቃቸው እያሰላሰልኩ እህቴ ቤት ደረስኩ ;;
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክርስትያን 06

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Sep 2006
Posts: 501

PostPosted: Wed Oct 18, 2006 10:06 pm    Post subject: Reply with quote

በብዙ መስሪያቤቶች የበአል ሰሞን ስራ እንደነገሩ ነው ;; በዲፓርትመንታችን ግን ስራ የሚበዛው በዲሴምበር ወር ላይ ነው ;; አምሽቶ መስራት የተለመደ ነው ;; አመት ማለቂያ ላይ የሚዘጉ ብዙ ጉዳዮች ስላሉ ትርፍ ሰአት መስራት የተለመደ ነው ;; በግምት ወደ 30 የምንጠጋ ሰዎች በተከታታይ ለአስራአምስት ቀናት በጊዜ ቤታችን አንገባም ;; አንዳንዶቹማ እስከ አዲስ አመት መባቻ የማይገቡ አሉ ;; ባለፈው አመት ስራ አላልቅ ብሎ ሆቴል ሁሉ ተከራይተውልን ስንሰራ ማምሸታችን ትዝ ይለኛል ;; ይህ በያመቱ ስለሚሆን ለሁላችን አዲስ አልነበረም ;; አለቆቹ ሪፖርት ካዲስ አመት በፊት ስለሚፈልጉት ማድረሱ የግድ ነበር ;; አንድሪያ አዲስ እንደመሆንዋ መጠን ስራዋም በአለቆችዋ አካባቢ የሚለካበት አጋጣሚም ስለሆነ የሁላችንንም እርዳታና ትብብር ደጋግማ በስብሰባ ላይ ጠይቃናለች ;; እኛም የምንችለውን ሁሉ እንደምናደርግ አረጋግጠንላታል ;;

ዛሬ የመስሪያቤታችን የክሪስማስ ምሽት በአል ነው ;; ቆንጂትን አዲስ አመትን አብረን እንደምንሆን ቃል ስለገባሁላት የገናን አዋዋሌን ለማንኛውም በማለት ክፍት አድርጌዋለሁ ;; በዚህ ምሽት ቢቻል ሁሉም የራሱን ሚስት ወይም ግዋደኛ ይዞ መምጣት ስለሚፈቀድ ከጥቂቶቻችን በስተቀር በጥንድ ነበር የተገኘው ;; ያልተጠበቀው የአንድሪያ ነበር ;; እጮኛየ ነው ብላ ያስተዋወቀችን ሰው በግምት 30ዎቹ የሆነና በሁኒታው ወግ አጥባቂ ባህርይ እንዳለው መገመት ይቻላል ;; ቁጥብ ነገር ይመስላል ;; ሩፒ እንደተለመደው ብቻዋን ነበረች ;; ከዚያ ምሽት ወዲህ ከሩፒ ጋር ያለን ወዳጅነት እንደመጀመሪያው ወቅት ሞቅ ያለ አልነበረም ;; የኔ ዝግመታዊ ሪአክሽን ይመስለኛል በድርጊትዋ ቁጭት ውስጥ የገባች ይመስላል ;; ከዚያ ምሽት ወዲህ እንድንወጣ ወይም አብረን ለቡና እንድናመሽ ጠይቂያት አላውቅም ;; ሁሉነገር የተምታታብኝ ስለሆነ ምን ማድረግ እንዳለብኝ እንክዋን በቅጡ አላውቅም ;; አይናችን ሲገጣጠም ሁለታችንም ከምናሳየው የፊት ቅላት ውጭ በድርጊት ያደረግነው ምንም ተግባር የለም ;; ይህን ምሽት ብቻዋን ለመምጣት መወሰንዋ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለብኝ እንደምትጠብቅ አልተጠራጠርኩም ;; ካንድ ዲፓርትመንት የሚለው እምነቴ ደግሞ ራሴን ይበጠብጠኛል ;; መልሱ ቀላል ነው መጠጣት ..... ራስን መሳት ... ከዚያ የፈለገው ይሁን ......

ከአንድሪያ እጮኛ ጋር አብረን የቆጡን የባጡን በማውራት መቀራረባችንን ለኔም ለርስዋ ለሩፒም ወይም ለሚጠራጠሩት ሁሉ እንደ እፎይታ ወስጀዋለሁ ;; አንድሪያ አልፎ አልፎ ስታወራ ከምታሳየኝ የጥቅሻ ምልክት በስተቀር የሰላም ምሽት ነበር ያሳለፍነው ;; ጥቅሻውንም ቢሆን አጉል ልምድ ብየ አልፌዋለሁ ;; በዳንስ ላይም ቢሆን ብዙውን ጊዜ በግሩፕ ወይም አልፎ አልፎ ከሩፒ ጋር መደነሴ ከማንም ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንደሌለኝ እንዲያውቁልኝ ሞክሪያለሁ ;; ባንድ ወቅት ከሩፒ ጋር ስደንስ በሩቅ አንድሪያ ትከታተል ስለነበር በቀጥታ መጥታ ተቀላቅላን መጫወትዋን ፋይልዋን አልዘጋች ይሆን የሚል መጠነኛ ጥርጣሬ ውስጥ ከቶኛል ;; ከሩፒ ጋር ስንደንስ በርግጥ ልንደብቅ ያልቻልነው አንዳንድ ሁኒታዎች አሉ ;; ቀና ብላ አይኔን ለረጅም ጊዜ ውስጡን ስታየኝ , ሳናውቀው የምናደርገው መጠጋጋት ከፊታችን ላይ የሚታየው ቅላት ወደ መቀመጫዋ ስትመለስ የምታሳየው መደነባበር ተዳምሮ ጥርጣሬ ውስጥ እንደሚጥል አላጣሁትም ;; በምሽቱ ማለቂያ ላይ ቃል በገባሁት መሰረት ሩፒን ጨምሮ ሶስት ስዎች ወየቤታቸው ላደርስ ጉዞ ጀመርን ;; ሁለቱን አድርሸ መጨረሻ የቀረችው ሩፒ ነበረቸ ;; ዛሬ ቡና መጠየቅ ተራየ ነው ብየ አስቀድሜ ወስኛለሁ ;; ከዚያች ከንፈሬን ላይ ሳም ካደረገችኝ ምሽት በፊት በጣም የምንቀላለደውና የምንበሻሸቀው እኔና ሩፒ አንመስልም ;; ጭራሽ ሁለታችንም ትናንት እንደተገናኘ ሁሉ ከንግግራችንና ከድርጊታችን መቆጠብን መርጠናል ;; ይህንኑ ደመና መግፈፍ እንዳለብኝ ወስኝ ቡና ልጋብሽ ብየ ጠየክዋት ;; ሳታቅማማ እሽ አለችኝ ;;
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክርስትያን 06

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Sep 2006
Posts: 501

PostPosted: Thu Oct 19, 2006 3:07 pm    Post subject: Reply with quote

ሩፒን ማስቀየም አለፈለግሁም ;; አብረን እንሰራለን ይህ ደግሞ በስራችን ላይ መጥፎ ጥላ እንዲያጠላበት አልፈልግም ;; ከምጠላው ነገር ቢኖር ወስብስብ ህይወት መኖርን ነው ;; ችግርን ውስጥ እያወቁ ገብቶ ያንን ለመፍታት ደግሞ እንደገና መባዘን ..... ፍጹም የማይዋጥልኝ ነገር ነው ;; የሚሰራ ነገር ጠፍቶ ;; አንዳንድ ሰዎች ያስቁኛል ;; ችግርን አውቀው ይፈጥሩና ከዚያ ደግሞ ለመፍታት ላይ ታች ሲባዝኑ .... ይህንን ሲያደርጉ ደግሞ ሁሉ ሰው እንዲያውቅላቸው ጠብ እርግፍ ሲሉ ... እግዜር ጥናቱን ይስጣቸው ;; በሰው ስስቅ እኔም ላይ ሊደርስ ይሆን ብየ መፍራቴ ግን አልቀረም ;; እያወቅሁ የምገባበት ጉዳይ ውሎ አድሮ ችግር ላይ እንደሚጥለኝ አሰላስየዋለሁ ;; የሩፒና የአንድርያ ባንድ ቢሮ አካባቢ መኖር ከተፈጠረው አዲስ ስሜት ጋር በራሱ በዘለቂታ በስራየ ላይ የሚፈጥረውን ጫና ልሸከመው የምችለው አይደለም ;; ሁለቱንም ከዚህ አይነቱ ስሜት ማስወገድ እንዳለብኝ ሳስስብበት ቆይቼአለሁ ;; እና በዛሬው ምሽት ሩፒን በጣም ሳይከፋት ሳላስቀይማት በወንድምነት ብቻ እንድትመለከተኝ ወደ ቀድሞ ሁኒታችን እንድንመለስ በምን ዘዴ እንደምነግራት አስቀድሜ ተዘጋጅቸበታለሁ ;; ውሳኔየ የሚያመጣውን ሪአክሽን ባለማወቅ ውስጤን ቢያስፈራኝም ባንድ በኩል ራሴን አደፋፍሬ እዚህ ውሳኔ ላይ መድረሴ ደግሞ አጽናንቶኛል ;;
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክርስትያን 06

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Sep 2006
Posts: 501

PostPosted: Thu Oct 19, 2006 3:34 pm    Post subject: Reply with quote

ለቆንጂት ባዲስ አመት እንደምንገናኝ ቃል በገባሁላት የስልክ ጭውውታችን ምሽት ይህንን ጉዳይ አንስቸባት ከት ባል እንደሳቀችብኝ አልረሳውም ;; ለረጅም ደቂቃዎች ያለማቅዋረጥ የመሳቅዋ ምክንያት ገብቶኛል ;;

ሁለታችንም ምንም አይነትን ችግር ሲገጥመን ምክር መጠያየቅ የተለመደ ነው ;; አንዴ በዜግነቱ ዩክሬን የሆነ ሰው አፍቅራ የደረሰባትን ውጣ ውረድና ራስዋን ተቆጣጠራ ወደ ኖርማል ህይወትዋ ለመመለስ የፈጀባትን ጊዜ አልረሳውም ;; ""ብዙ ተምሪያለሁ ከዚያ መናጢ ግን እንዳንተ በቢሮ አካባቢ አልተንጎዳጎድኩም "" ብላ ሳቅዋን ለቀቀችው ;; ረጅም ሳቅዋ ቢያናድደኝም የምትለው እውነት እንዳለው አውቃለሁ ;; በውነትም ቆንጂት ከዚያ ""መናጢ "" ከምትለው ሰው ወዲህ ብዙም አልተበለጠችም ;; ራስዋን ከመጠን በላይ መውደድዋ ሳይረዳት አልቀረም ;; ሰዎች የማታገባው ራስክን ስለምትወድ ነው ሲሉኝ ቆንጂትን ያላየ ብየ በውስጤ እተርትባቸዋለሁ ;; ለማንም ለምንም ግድ የላትም ;; የኔ አይነቱ ችግር ቢገጥማት በቀላሉ እንደምትወጣው አውቃለሁ ;; የኔና የርስዋ ልዩነት እዚህ ላይ ነው ;; ለሰዎች ያለን ስሜት አቀራረብ ይለያያል ;; ሰዎች ሳይጎዱ ስሜታቸውን ጠብቆ የሚደረግ ነገር በርግጥ በራስ ላይ የሚያመጣው መጠነኛ ጉዳት አለ ;; አንዳንዴም የሰው ስሜት እንዳይጎዳ በሚል የማንፈልገው ውል ውስጥ ሁሉ እንገባለን ;; ይህ ሁሉ ለቆንጂት ተረት ተረት ነው ;; ለኔ ደግሞ ይህ አይነቱ አክሄድ የድክመት ሳይሆን የተፈጥሮ የሰው ልጅ ባህርይ አድርጌው ነው የምወስደው ;; ቆንጂት ደግሞ ባጭሩ ""የራስ ድክመት "" ትለዋለች ;; ሆነም ቀረ ለዛሬው ምሽት ውሳኔየ የቆንጂት ምክር ብርታት እንደሰጠኝ አልክድም ;;
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
yammi

ኮትኳች

Joined: 28 Jul 2006
Posts: 436

PostPosted: Thu Oct 19, 2006 4:34 pm    Post subject: Reply with quote

ክሪዬ ..........ታሪኩን እየተከታተልኩት ነው :: በጣም ቆንጆ ጅምር ነው ::

በርታልኝ ::

ያሚ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክርስትያን 06

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Sep 2006
Posts: 501

PostPosted: Thu Oct 19, 2006 5:48 pm    Post subject: Reply with quote

የሰሞኑ ስራ ካለፈው አመት አይተናነስም ;; አምሽቶ መስራት የተለመደ ሆንዋል ;; ለበአሉም የሚሆን መጠነኛ ገቢም ስለሚጨምርልን ባይከፋንም ከምሽቱ 10 11 ፒም ላይ ቤት ተሄዶ እንደገና ጠዋት 8ኤም ተመልሶ መግባት እንደገና የቀኑ የስራ ጥድፊያ ይህ ሁሉ ተዳምሮ የሚያሳድረው ውጥረት ቀላል አልነበረም ;;

አንድሪያ ዲሴምበር 22 23 ሁለቱን ቀናቶች እስከ ሚድናይት እንድንሰራና ቤት ለመሄድ መቸገር እንደሌለብን ባካባቢያችን ካለው ሆቴል እንደተያዘልን ኤሜይል አደረገችልን ;; ሰሞኑን ምሳ እንክዋን የምንበላው ዴስካችን ላይ ሆንዋል ;; የግል ንግግርና ጨዋታ ለማድረግ ያለው ጊዜ ኤሊቨተር ውስጥ ወይም ማታ ስንወጣ ብቻ ነበር ;;

ሩፒ እንዳልከፋት ለመሆን የምታረገው ጥረት በግልጽ ለኔ ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም ድብቅ አልነበረም ;; አብረን ካመሸንበት ያች ማታ ወዲህ ከስራ ጋር በተያያዘ ጉዳይ ውጭ ምንም አላወራንም ;; ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ በማስመሰል ሁኒታዎችን ለመለዋወጥ ብሞክርም አልተሳካልኝም ;; ያለወትሯችን የቀዘቀዘ መስሎ የሚታየው ቅርርባችን ለሁሉም ግራ ያጋባው ይመስላል ;; በቂ ምክንያት እንደሌለኝና አስቀድማ ርምጃ በመሰድዋ ያደረብኝ የወንድ መኩራራት ኤጎ አንደሆነ ሲቃ እየተናነቃት ነግራኛለች ;; ለርምጃዋም ራስዋን ደጋግማ ረግማለች ;; ደግሜ ደጋግሜ ባስተባብልም ተቀባይነት አላገኘሁም ;; ""ማን የማያቅ አለና ነው እንዲህ የምትለው "" አንድሪያን ፈርተህት ነው አይደል ?"" አለችኝ ;; አብዛኛው ሰው መጠርጠሩን እንጅ ያለቀለት ነገር አድርገው መውሰዳቸውን ያልጠበኩት ዱብ እዳ ነበር ;; ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው ይባል የለ ?
በዚያ ምሽት ለማንኛውም ሩፒን አባብዬ ከእምነቴ ጋር የሚጋጭ እንደሆነ ነግሪያት ባጭሩ ጉዳዩን ቀጭቸ ወደ ቤትዋ አደረስክዋት ;;

ዲሴምበር 23 እንደትናንቱ ግርግር ሆኖ ነው የዋለው ;; ሆኖም የመጨረሻ ሆቴል የምናድርበት ; ስራው የሚጠናቀቅበት ; በማግስቱ ኡፎፎፎይ ብየ ወደራሴ ግል ህይወቴ የምመለስበት ስለሆነ መጠነኛ ደስታ ውስጤን ተሰምቶኛል ;; በማግስቱ አንተያይም ;; ላዲስ አመት ነው የምንገናኘው ;; ትልቅ ሸክም ከላየ ላይ እንደተነሳ ኡፎፎፎፍይ ብየ እንደተለመደው ልብሴን አውላልቄ ገንዳየን ውህ ሞልቼ ልዘፈዘፍ እየተዘጋጀሁ እያለሁ የሆቴል ስልኩ አንጫረረ ;; አንድሪያ ነበረች ;; ጠዋት ስለማንገናኝ የተጠናቀረውን ሪፖርት ኮፒ እንድሰጣት ነበር የደወለችው ;; እየተነጫነጭኩ ያወላለቅሁትን ልብሴን እንደገና ለብሸ ወደአለችበት ሩም ሪፖርቱን ይዥ የበርዋን ደውል አንጫረርኩት ;; በሩን በትንሹ ከፍታ አጮልቃ አይታ እኔ መሆኔን አረጋጣ ከፈተችልኝ ;; ሪፖርቱን በጅዋ ሰጥቸ ተሰናብቸ ልወጣ ስል የሚጠጣ ነገር የምፈልግ መሆኔን ጠየቀችኝ ;; ባዝ ለመዘፍዘፍ ገንዳ እየሞላሁ መሆኔንና ብዙም እንደማልቆይ ግን በቁሜ አንድ ባገኝ እንደማይከፋኝ ነግሪያት አንድ ብርጭቆ ውስኪ ከበረዶ ጋር ይዛ ልትመጣ ወደ አነስተኛ ፍሪጅዋ ሄደች ;; በላይዋ ላይ የነሰነስችው ስስ ሽቶ በውድ ዋጋ የተገዛ ለመሆኑ ከሚያሳድረው ልዩ ስሜት መገመት አያዳግትም ;; የለበሰችው ስስ አጭር ፒጃማ ተክለ ሰውነትዋን በጉልህ ያሳያል ;; ገዋን ለመደረብ የተጨነቀችበት አይመስልም ;; ፍሪጁን ለመክፈት ጎንበስ ስትል ቸኮሌት የሚመስለው ጭኖችዋ ከህዋላ በጉልህ ያታያሉ ;; ጡቶችዋ ባየር ላይ ተንጠልጥለው የድጋፍ ያለህ የሚሉ ይመስሉ ነበር ;; ጸጉሮችዋን ሆን ብላ ለቃው በላይዋ ላይ ተደፍቶ ይርመሰመሳል ;; በረዶውን ይዛ ቀና ስትል የሚርመሰምሰውን ጸጉርዋን ከፊትዋ ላይ ዞር ዞር አድርጋ ዊስኪውን ቀድታ ከቆምኩበት ይዛ ስትመጣ ነበር በማፈር መልክ አይኔን ከላይዋ ላይ ለመንቀል የተገደድኩት ;; መልሴን ለመጠበቅ ሳትጨነቅ እጄን ይዛ ወደ ሶፋው እንድቀመጥ መራችኝ ;; ከፊት ለፊትዋ ካለው ሶፋ ተዘርፍጨ ውስኪውን ባንድ ትንፋሽ ጭልጥ አርጌ ትኩር አርጌ አያት ጀመር ;; እግሮችዋን አነባብራ ጭኖችዋ ከሞላ ጎደል ተጋልጠዋል ;; ከላይ ከፈት ያለው ስስ ፒጃማዋ በጡት ማያዣ ያልተሰነገውን የጡቶችዋን ጫፍ እንዲታይ ሆን ተብሉ የተቀመረ መሆኑ ያስታውቃል ;; ከንፈሮችዋን ስስ ደብዘዝ ያለ ፒንክ መሳይ ቀለም በጥንቃቄ ተቀብተዋል ;; ""ልድገምህ አለችኝ "" ፈገግ ብላ አንድ ለመንገድ አይከፋም አልክዋት ;; ዊስኪውን ቀድታ በቀጥታ መጥታ ቺርስ ለማለት ስትጠጋኝ የሽቶዋ መአዛ ጠረንዋ በመላው ሰውነቴ ሲሰራጭ ይሰማኛል ;; ተጠጋግተን በቆምንበት ባንድ ትንፍሽ ጭልጥ አድርጋ ጨርሳ ከቆመችበት ሳትንቀሳቀስ እንደ ልዩ ፍጡር እስዋ እኔን እኔም እርስዋን አይናችንን ሳንሰብር ለጥቂት ደቂቃዎች ያህል ባለንበት ቆምን ;; ጠጋ ብየ እጅዋን ይዥ ካንገትዋ ቀና ሳደርጋት ከንፈርዋ ወዝቶ ፊትዋ ቀልቶ ባይንዋ እንባ አቀርዝዞ ከንፈሬን ፍለጋ ስትቃትት ...... በድንገት የበሩ ደወል አንጫረረ ;;
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክርስትያን 06

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Sep 2006
Posts: 501

PostPosted: Fri Oct 20, 2006 2:42 pm    Post subject: Reply with quote

ያሚቲ እንክን በደህና ተመለሽ .... ከጠፋሽበት .. ይህው ቤትሽን በሞኖፕል ይዥዋለሁ ... ቅር አለመሰኘትሽን በአበረታች ቃልሽ ስለገለጽሽልኝ .... ታላቅ ምስጋና .......

ታሪኩ ይቀጥላል
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክርስትያን 06

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Sep 2006
Posts: 501

PostPosted: Fri Oct 20, 2006 3:15 pm    Post subject: Reply with quote

በሩን በጥንቃቄ ቀስ ብላ ስትከፍት የሉሲን የሩፒን ድምጽ የሰማሁ መሰለኝ ;; እንቅልፍ እንቢ ሲላቸው ለመጫወት እንደመጡ እኔ ያለሁበት ክፍል ቢደውሉ ስልኩን እንደማላነሳ ሲነግርዋት ይሰማኛል ;; አንድርያም አሁን ከእጮኛዋ ጋር ስልክ ላይ እንደሆነችና ስልክዋን ስትጨርስ የሚጠጣ ይዛ ሉሲ ክፍል እንደምትመጣ ነግራቸው በሩን ዘጋች ;;

የት ላይ ነበርን አለችኝ ? .....እምምምምም ....አስቲ አስታውሽኝ ... አዎን ... ......... ብየ አንገትዋን ቀና ሳደርጋት እጄን ገፋ አድርጋ ... የሸሚዜን ቁልፍ አንድ ባንድ መፍታት ጀመረች ;; ወረድ ብላ ቀበቶየን አላልታ ሱሪየን ዝቅ አርጋ ከተወጠረው ፓንቴ እጅዋን ቀስ ብላ ሰደደችው ;; ፓንቴን ወጥሮ የያዘውን አካል በሁለት እጅዋ ግጥም አድርጋ ይዛው በጉንጮችዋ , ባይንዋ በግንባርዋ አካባቢ ስታሻሽው ቆይታ ቀስ ብላ የሰውነቴን አካሎች አንድ ባንድ እየሳመች ተነሳች ;; እንደነገሩ ከላይ የለበሰችውን ልብስ በጥንቃቄ አወለቅሁት ;; ጦቶችዋ ተገትረው ተወጥረው አፍጥጠውብኝ ምን ትጠብቃለህ የሚሉኝ ይመስላል ;; ወደ ደረቴ ጠጋ አድርጊያት አንገትዋን አገጭዋን አይንዋን ግንባርዋን አንድ ባንድ ሳምኩዋት ... በስስት አይን ቀና ብላ አይታኝ ከንፈሬን በከንፈርዋ አላተምችው ....እንዳለ ጎረሰችው ...ሁለታችንም በትኩስ እንፋሎት ሰምጠን እያቃተትን ከሰፊው ሶፋ ላይ ተገነደስን ..........;;
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክርስትያን 06

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Sep 2006
Posts: 501

PostPosted: Tue Oct 24, 2006 7:33 pm    Post subject: Reply with quote

ሰማዩ ለሰአታት ያረገዘውን የበረዶ ብናኝ ያወርደዋል ;; ማለቂያ ያለው አይመስልም ;; ቆይቶ ይህ ሁሉ ከመንገድ ከበራፍ ላይ ይዛቃል ;; እንደገና ብዙ ሳይቆይ ይነሰንሰዋል ;; እንደገና ይዛቃል ;; በአዋጅ ማንንም እንዳይወጣ የተከለከል ይመስል መንገዱ ሁላ ጭር ብሏል ;; እኔም በክሪስማስ እለት ከቤት መውጣቱን አልወደውም ;; ለእህቴ ልጆች ስጦታ ለመስጠት ትናንት ማታ ወጥቸ ከተመለስኩ ወዲህ ተከትቻለሁ ;; ክሪስማስ ለኔ የቁዘማ ቀን ናት ;; ማንም እንዲመጣ አልፈልግም የትም መሄድንም አልወድም ;; የህይወት ፊልሜን አጠንጥኜ የራሴን ፊልም ማየቱን እመርጣለሁ ;; በየቀኑ ልጎዋም በሌለው በሩጫ ኑሮ ፈረስ ላይ ስጋልብ የማይታዩኝን የራሴን እወነታዎች የምዳስስበት ጊዜ ቢኖር እንደዛሬው አይነቱ ነው ;; አቻምና ካምናው በምን ተለየ ? የዘንድሮስ ምን ልዩነት ነበረው ? ..መጪውስ ? ላውጠንጥነው ላውርደው ላውጣው እንጂ ምንም መልስ የለኝም ;; ማውጠንጠኑ በህሳብ መባዘኑ ግን በመጠኑ እፎይታ ያስገኝልኛል ;;

ካሁኑ ህይወቴ ይልቅ ይበልጥ ደስ የሚለኝ ርቄ ወደህዋላ ተጉዥ የልጅነትና የአፍላ ጉርምስና ጊዜየን ስቃኝ ነው ;; አሁን ምንም ማድረግ ሲያቅተኝ ባለፈው ህይወቴ የምደሰትና የምጽናና መሆኔን ሳየው ደግሞ ""ጅላጅል ነህ ከነባራዊ ህይወትህ ጋር ከመፋጠጥ ይልቅ በትዝታ ፈረስ ተደባብሰህ ተድበስብሰህ ማለፉን የምትመርጥ የሆንክ ግብዝ ነህ "" ብየ ራሴን እወቅሳለሁ ;; እንደዚሁ እራሴን ስወቅስና ሳወድስ አመታት ያልፋሉ ;; ኑሮን ራሱን እንደመኖር ይልቅ በፍልስፍና መልክ ማየት ሲጀመር ነው የኑሮ መልኩ መዛባቱ የሚጀምረው ;; ፍልስፍናው ሲራቀቅ ለምናደርገው በጎም ሆነ ክፉ ድርጊት ፍልስፍናውን እንደ ዋና ምክንያት (justification) አርገን እንወስዳለን ;; በሱም እንጽናናለን ;; ለጊዜው ከፊታችን የሚደቀነውን የህይወት ዋና ዋና ጥያቄ ገለል ያረግልናል ;; ግርግሩ ተመልሶ እስኪመጣ በዚሁ የትዝታ የፍልስፍና ጋሪ ተሳፍረን እንጋልባለን ;; ህይወት ተመልሳ በግርግሩ ማእበል ትዋጣለች ;; የህይወት ኡደት ይቀጥላል ;;

ላለፈው ህይወቴ ድምቀት ከሰጡኝ በትዝታ ከሚነዱኝ ዋናውን ክፍል የምትይዘው ትእግስት ናት ;; በተለይ 10 ክፍልን ትእግስትን ፍጹም ለይቸ አላያቸውም ;; በያመቱ የምዘክራት ይመስለኛል ;; ዛሬ የልጆች እናት ሆና ሳያት ሳቅ ፍርፍር ያረገኛል ;; ካምስት አመት በፊት ከሁለት ልጆችዋ ጋር የተሳቸውን ፎቶ ልካልኝ ""አበደች ግላሱ "" የሚል መጠሪያ የነበራት ትእግስት አትመስልም ;; አዎን በጊዜው አብዳ አሳብዳኝ ነበር ;; ለመጀመሪያ ጊዜ በወጉ ከሴት ጋር የሴክስ ግኑኝነት ያደረግሁት ከርስዋ ጋር ነበር ;; ከዚያ በፊት ከሴተኛ አዳሪዎች ጋር በትንሽ ደቂቃ ውስጥ የምትጠናቀቅ ግልቢያ አይሉት ሩጫ ካልሆነ በስተቀር በተለምዶ ""ከቤት ልጅ "" ጋር ምንም አይነት የሮማንቲክ አይነት ግንኙነት አልነበረኝም ;; ትእግስት በነበራት ድፍረትና የተሻለ ልምድ አለማምዳኛለች ; አስተምራኛለች ;; ብዙም ባለዋወቄ የተሻለ መሆንዋን ለማሳየት በምታደርጋቸው ጥረቶች ከእፍረት ነጻ የሆኑ ግኑኝንቶችን እናደርግ ነበር ;; ለዛሬው ያለምንም እፍረት ከቆንጂት ጋር ያለምንም ልብስ ለመንጀላጀሌ ትልቅ አስተዋጾኦ ሳይኖረው አይቀርም ;; እኔሥ ከትእግስት ተማርኩ አንቺ ይህንን መንዘላዘሉን ከየት አመጣሽው ብየ ቆንጂትን ስጠይቃት ከት ብላ ስቃ ከፈረንጅ ትለኛለች ;;
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክርስትያን 06

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Sep 2006
Posts: 501

PostPosted: Tue Oct 24, 2006 10:08 pm    Post subject: Reply with quote

ከአንድርያ ጋር ያሳለፍነው ምሽት በላዬ ላይ የፈጠረው ዝብርቅርቅ ስሜት አሁንም አለቀቀኝም ;; ከሁለት ወራት በህዋላ እንደምታገባ ነግራኛለች ;; ድርጊትዋ ሁሉ ""የነጻነቴን የመጨረሻ ጽዋ ልጎንጭ "" አይነት የምትል ይመስላል ;; በመጪው አመት ሊሆን የሚችለውን ነገር እያሰላሰልኩ ብጨነቅም ከመለያየታችን በፊት አንድርያ ይህ ያሁኑ አይነት ግኑኝነታችን የመጀመሪያና የመጨረሻ እንደሆነ ፈርጠም አርጋ ስለነገረችኝ በይበልጥ በፍሬንድሺፕነት እንድንቀጥል የምትመርጥ መሆንዋን መንገርዋ መጠነኛ መረጋጋት አሳድሮብኛል ;; የኔም ምርጫ ይህ እንደሆነ ጠበቅ አርጌ ነግሪያታለሁ ;; ከሩፒ ጋር ያለኝን ምስጢራዊ ያይን ጨዋታ እንደምታውቅና በሁለታችንም መህከል ለመግባት ሆን ብላ የወጠነችው እንዳልሆነ አስረድታኛለች ;; አንድርያ በጠባይዋ በህይወትዋ የምትፈልገውን ከማግኘት ምንም የሚያቆማት ነገር የለም ;; የኔ የመኩራራት ባህርይ ይበልጥ እንደሳባትና እልህ ውስጥ እንደከተታት በሌላ ቀን አጫውታኛለች ;; ውስብስብስ ህይወት የምጠላውን ያህል በይሉኝታ ይሁን በራስ ድክመት ራሴን ከዘፈቅሁበት ጭንቀት ለመውጣት በምውተረተርበት ሰአት የአንድርያ መልስ መጽናኛ ሆኖኛል ;; ሩፒም ዲፓርትመንት ለመቀየር ማመልክቻ አስገብታ ፕሮሰሱን መጨረስዋን ከአንድርያ መስማቴ አልገረመኝም ;; አንድሪያ ""ለሁላችንም ጥሩ ነው "" አለችኝ በሌላ ቀን ኤሊቨተር ላይ ተገናኝተን ;; ""ልክ ነሽ "" በማለት እያቅማማሁ ወደ መቀመጫየ እየቆዘምኩ ሄድኩ ;; ከሩፒ ጋር አይን ላይን ላለመገጫጨት ብሞክርም አልሆነልኝም ;; ትልቅ በደል እንደሰራባት ሰው አቀርቅሬ ከመቀጫየ ሄጀ ተዘረገፍኩ ;;
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክርስትያን 06

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Sep 2006
Posts: 501

PostPosted: Wed Oct 25, 2006 1:28 am    Post subject: Reply with quote

ተፈጸመ ...............................................................................................

ታሪኩን በትእግስት በማንበብ ድጋፋችሁን በመስጠት ላብረታታችሁኝ ሁሉ የጠለቀ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ;;

በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ስሞች ሁሉ ከማንም ከምንም ጋር ንኪኪ የላቸውም
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5  Next
Page 3 of 5

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia