WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የቦሬ ልጆች በዋርካ ጥላ ስር :
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 63, 64, 65, 66  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Sun Aug 17, 2008 8:15 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

ራስ ብሩ አንተን ተከትዬ ድሉን ለማብሰር ብገባ ቀማኛው ዋርካ ሰለቀጠብኝ ::

የዛሬው ታሪካዊ ድል ልዩ ነበር :;ሀይሌን በምን ቃላት ማሞካሸት እንደምችል አላውቅም ::
ትልቅነቱንና ችሎታውን ነው አሁንም ያስመሰከረው :;ኤርትራዊያኖቹና ኬንያዎቹ በቀነኒሳ ላይ ሲፈራረቁበት ያስተዋለው ሀይሌ ከመሀል
በመውጣት እነሱን ያዳከመለት ሲሆን እስከመጨረሻው ድረስ አንገላቷቸው ድሉን እንደተለመደው
ዘውዱን ላስረከበው ለቀነኒሳና ለስለሺ በመተው መንገዱን
በርግዶላቸዋል !!!!!::በጣም በጣም ነው ያደነኩት ::
አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ የሀይሌን
ስም እየጠራና እያሞካሸ ሲጨፍሩ መመልከት በራሱ እንዴት ስሜ ++++++++9 ውስጥ እንደሚከት ማውራት ይከብዳል ::
እነ አዶቆርሳስ እንደት ሆነው ይሆን ????
የሚቀጥለውን ድላችንን በናፍቆት እንተብቃለን ::

ሌላው ያስደሰተኝ ነገር ራስ ብሩ እንዳበሰርከን አንፈራራም እንደ ቀነኒሳ ሮጦ የጨረሰውን መጻፉን
መስማት ሲሆን ለማንበብ መጓጓቴንም ቀድመህ አሳውቅልኝ ::

ቸር እንሰንብት !!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Mon Aug 18, 2008 8:35 pm    Post subject: Reply with quote

የአንፈራራችን አዲሱ ልጅ ተወለደ !_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ትርንጎ 123

ኮትኳች

Joined: 03 Feb 2008
Posts: 190

PostPosted: Mon Aug 18, 2008 9:55 pm    Post subject: Reply with quote

ራስብሩ ...ለምስራቹ ምስር ብላ ብያለሁ :: እስካነበው ቸኩያለሁ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Report post
አደቆርሳ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Aug 2005
Posts: 754
Location: ethiopia

PostPosted: Mon Aug 18, 2008 10:25 pm    Post subject: Reply with quote

የሰሞኑ ጉዳይ አነጋጋሪና አስደሳች ስለነበረ አዶላ ራስብሩ ቤት ቆይቼ ሳበቃ እዚህም የኔን የደስታ ስሜትና አጋጣሚውን ከስፖርት ወዳዶቹ ሞፊቲና ወቤ ጋር ሀሳብ ለመለዋወጥ ደስታዬንም ለማካፈል መጣሁ ::
እንኳን ደስ አላችሁ !

የዘንድሮውን የቤጂንግ የስፖርት ውድድር በተመለከተ ትናንት በመላው ሀገሪቱ ውስጥ ታላቅ የደስታ ቀን ሆኖ ነበር ያመሸው ::
ኢትዮጵያ ከጥግ እስከጥግ በደስታ ታመሰች በአዲስ አበባው የመስቀል አደባባይ ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ የነበረ ህዝብ በጣም ትልቅ ሆኖ በተሠራው Publik Screen ውድድሩን በቀጥታ ሲመለከት የቆየው ስፖርት ወዳድ ህዝብ ያሳይ የነበረው ጨዋነትና ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ስሜት ደስታውን ሲገልጽ ክፍለሀገር ለነበርነውም እጅግ አስገራሚ ነበር ::
በአንድ ሰፋ ባለ የመኖሪያ ቤት ሳሎን ውስጥ ከባለቤቱ መቀመጫ የሶፋ ወንበር ውጪ ትልቁ ሳሎን የተሞላው በሚያማምሩ ምንጣፎች ነው ::
በግድግዳው ጥግ በሶስቱም ማዕዘን በተነጠፈው ፍራሽ ላይ በየቅርብ ተጠጋግተው የተቀመጡት ፍራሾች ገና ሲያዩዋቸው ምቾትን ይናገራሉ ውድድሩን ለመከታተል ወደሳሎኑ ገብቶ ተመቻችቶ ለመቀመጥ የነበረው መተጣጠብና መንጎራደድ ስፖርት ለማየት አይመስልም ::
ከመኪና ስንወርድ ለአለቃ ቦታ መልቀቅ ስላለ ከላይ ተጭነን የነበርነውን ማን ማን እንደሆንን ለመለየት የተሸከምነውን አዋራ ካላራገን በውነት ያስቸግራል ::
ሌላ ሰዎች ነው የምንመስለው :: አንዱ ጓደኛዬን አይቼ የሳቅኩት ሳቅ እኔን እንዳይበት ስላደረገኝ ሽርጤን አናቴ ላይ ጠምጠም አደረኩና ወደ መታጠቢያ ቤት ዘለቅኩ ::
ወረፋዬን ጠብቄ የለበስኳትን እዛው ትቼ ሰው መስዬ ከመታጠቢያው ስወጣ ሰዓቱ ሰባት ሠዓት ሆኗል ::
ጥሩ የምሳ ሰዓት ነው :: ምሳችንን አስነካነውና ወደተንጣለለው ሳሎን ከቲቪው ፊት ለመደቀን ሁላችንም ቸኩለናል ::
እዚህ ቤት ምርጫው ሰፊ ነው በኢቲቪ አልያም በፈረንጆቹ ቻናል ::
አይ የእንግሊዙን ታዋቂ ኮሜንታተር ለመስማት የኢትዮጵያን ቲቪ መረጥንና ከተዘጋጀው ምቹ ፍራሽ ላይ አንዷን ጥግ ይዤ ተፈደልኩ ::
አወዳይ ታስሮ ታስሮ በየፊታችን ቀረበ ትልቁ የቡና ረከቦት ከተነጠፈው እርጥብ ሳር በላይ ጉብ ብሎ አጠገቡ ቡል ቡልል ከሚለው ሉባንጃ ጋር የበርጫውን ሙድ ልዩ አድርጎታል ::
እኔ እንጃ ብቻ ደስ ደስ ይለኛል የምርቃናው አፈጣጠን ደሞ አይወራ ሁለት ሁለት ትኩስ ቡና ስንልክበት አሮጌ አወዳይ ቱግ አድርጎኝ ቁጭ ::
ለአስራ ሁለት ሩብ ጉዳይ ውድድሩ ሲጀመር ምርቃናዬ ሌላ ስሜት ውስጥ ከተተኝ ከዚህ ቀደም የማላውቀው ስሜት ::
የአስመራዎቹ ሁለት አዳዲስ አትሌቶች የመጀመሪያዎቹን አሥር ገደማ ዙሮች አላስቀምስ ከማለታቸውም ባሻገር ዙሩን ከኖርማል ውጪ ከረር ማድረጋቸው ከፍተኛ ልምድ የሌላቸውን ሯጮች በግዜ ወደኍላ ማስቀረት ችለዋል ::
ይህ አይነቱ ሁኔታ አንዳንዴ በሳል አትሌቶችንም ከግምት ውጪ ያደረገበት አጋጣሚ እንደመኖሩ እነዚያኑ በሳል አትሌቶችን ለተሻለ የውድድር ሠዓት ማብቃቱም ከዚህ ቀደም በተገኘ ልምድ ታይቷል ::
እንደኔ እምነት ግን ለእነዚህ ልጆች ይህንን አሰላለፍ ያደረገ አሠልጣኝ ተሳስቷል ::
የዛሬ አራት አመቱ የግሪክ ኦሊምፒክ ለዚህ ለዛሬው ስህተት ምስክር ነው ::
እነዚህ ልጆች ተራቸውን ለኬንያውያኑ ሲለቁ ውድድሩ በጣም አስጨናቂ መሆኑ አልቀረም :: ምክንያቱም በዚህ አጋጣሚ ኬንያውያኑም ከፍተኛ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል ::
ኃይሌ የመሪነቱን ስፍራ ተረክቦ ቀዳሚውን ቦታ ሲይዝ የኔ የልብ ምታት በእጥፍ ጨመረች :: ዙሩ ሀያ ሁለተኛውን ሲይዝ የነበርንበት ቤት ስታዲየም እንጂ ቅድም በክብር የነበርንበት ቤት አይመስልም ::
ኬንያውያኑ ዙሩን ለመጨረስ የነበራቸው ጉልበት ከቀነኒሳ በልጦ ባያስታውቅም በኛ ላይ የፈጠረው ስጋት የህመም ያህል ነበር :: ቀነኒ ኬኛ የመጨረሻውን ዙር ለመገላገል ሲወነጨፍ ቡና ልታፈላ ጀበናውን ጨብጣ የነበረችው ልጅ ጀበናውን እንደያዘች ቴሌቪዥኑ ሥር ሄዳ ታዋን ታስነካዋለች :: አንዷ የቤቱ ቆንጅዬ መስኮቱ ላይ ማን እንዳወጣት አይታወቅም ወጥታ ቂጢጥ ብላለች እቤቱ ውስጥ ያለነው በሙሉ ሳናስበው ተያይዘናል ::
የስለሺ ስህንን ተከትሎ መግባት ለመግለጽ አሁን ቃላት አይገኝም ::
እያንዷንዷን አጋጣሚና ሁኔታ ለመጻፍ ግዜም አይበቃኝም ዋርካም እሺ አይለኝም ::
ከመስኮቱ ላይ ያለችው ልጅ ራሷ የወጣችውን ራሷ መውረድ አለመቻሏ የስፖርትን ስሜታዊነት ከመመዘን ጋር አስደንቆኛል ::
በኦሊምፒክ ታሪክ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ለሶስተኛ ግዜ 10,000 ሜትር የኦሊምፒክን ሪኮርድ ሰባበሩት ::
ይህንንም ታሪክ በአምስቱ ሺህ ሜትር ተደግሞ እናየዋለን !
ድል ለጀግኖቹ አትሌቶቻችን !

_________________

kibremengist
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወቤ (ጃሎ )

ኮትኳች

Joined: 28 Jul 2004
Posts: 201

PostPosted: Tue Aug 19, 2008 12:36 am    Post subject: Reply with quote

ሁላችንንም እንኳን ደስ አለን !
እኔ ምንም የምለው የለኝም ሩጫዉን አስመልክቶ , ሁሉንም ነገር በዝርዝር ገልጻችሁታል ; ቀጣዩን ዉድድርም የድል ሆኖ ለመደሰት ያብቃን !
አዶቆርሳ ግን ሆን ብለህ ሰዉን ለማስቀናት እንቁልልጭ እያልክ ሩጫዉን እንዴት እያየህ የጻፍከው በእዉነቱ ግፍ ነው :ማግኘት ለማንችለዉና እሩቅ ላለን ማለቴ ነው ::
ወንድማችን ራስ ብሩ የአንፈራራን መጽሀፍ ስለአስተዋወከን በጣም እናመሰግናለን :; አንፈራራም በዚሁ አጋጣሚ እንኳን ደስ አለህ !
በቅርቡ ሁላችንም እጃችን እንደሚገባ ነው :: በጣም በተጨማሪ ደስ ያለኝ ደግሞ መጽሀፉ < አዶላ ማተሚያ ቤት >መታተሙ ነው ::
ሰላምታዬ ለሁላችሁም ይድረስ ;
ቸር ያቆየን !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Thu Aug 21, 2008 12:58 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

ውድ የሀገር ልጆች እንዴት ሰንብታችሁልኛል ?
የመጪውን አርብና ቅዳሜ ድል የሚያበስር የማጣርያ ውድድር ተደርጎ አትሌቶቻችን በሙሉ
አልፈዋል :: እርግጠኝነት በሁለቱም ጾታ 5000 ውድድር ከጃችን እንደማይወጣ ስናገር በድፍረት ነው ::

በሴቶቹ ማራቶን የተገኘውን ሁጤት በተመለከተ በተለይ በሀገር ውስጥ ብዙ ሲተች ከርሟል ::
ይህም ያለምክንያት አይመስልም ::ዛሬ የወጣውን ሪፖርተር የስፖርት አምድ መመልከቱ ይበልጥ
ያለውን ችግር የሚያስረዳ መስሎ ይታየኛል ::

በሴቶች ማራቶን በኦሎምፒክ ያለን ሁጤት ከዛሬ አስራሁለት አመት በፊት በአትላንታ
በጀግናዋ ፋጡማ ሮባ የተገኘው የወርቅ ሜዳልያ ነው ::ይህን ወቅት ዛሬ በዚህ አጋጣሚ ላስታውስ ወደድኩ ::
ኢትዮጵያ ሬድዮ እሁድ ፕሮግራም የሚያበቃው በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር አስራአንድ ላይ ነበር ::
ፋጡማ ሮባ አስር ሰአት ከአርባ አምስት አካካባቢ የማራቶን ድሏን ተጎናጸፈች ::ደምሴ ዳምጤ ምጥ ያዘው ::ይህን ብስራት ኢትዮጵያ ህዝብ ሬድዮን ስርጭት ከማቆሙ በፊት ማድረስ አለበት ::እጁ ላይ ስልክ ይለም ::ከስቴድዮም ወቶ ቢደውል ሰአቱ ያልቃል ::ወድያው አንድ አበሻ
ያገኝና እጁን ስልክ ይቀበለዋል ::አስር ሰአት ከሀምሳ ሆኗል ::አምስቷ ደቂቃ ደግሞ የዜና ማጠቃለያ ናት :;ወድያው የፕሮግራሙ መሪ አዲስ የደረሰን የድል ዜና አለ :;ደምሴ ዳምጤ ከአትላንታ መስመር ላይ ነውና ተከታተሉ አለ ::
ወድያው ደምሴ ሲቃ እየተናነቀው የፋጡማን የድል ብስራት አበሰረ !!!!!!!!

ይህን ሁኔታ የተመለከተው አለምነህ ዋሴም በነገታው የደምሴን ዜና ይዞ እንዲህ አቀነባበረው :;
አደራ ስታነቡ እንደ አለምነህ ሆናችሁ ይሁን ::

እንዲህ ከወደ አዋሽ አንዲት ሬንጅሮቨር መኪና ከቁሉቢ ገብሬል በአል የተመለሱ አራት ሰዎችን ጪና
በሰአት መቶሀያ ትንገጫገጫለች :;
በመንገዱ ዳርና ዳር የነበሩት ግመለቹ ቀና እያሉ ቅጠል ይቀነጥሳሉ ::ወዲያ ወዲህ
የሚሉት ገመሬ ዝንጀሮዎች ኩራታቸው ለብቻ ነው ::በዚህ መሀል ሹፌሩ ሬድዮውን ከፍ አድርጎ ከፈተ :;ወድያው አንድ ነገር ተሰማ :-
ደምሴ ዳምጤ =አትላንታ =ፋጡማ ሮባ =ማራቶን =ወርቅ ለአፍሪካ =ወርቅ ለኢትዮጵያ :-

ወደላይ ቀና ብለው ቅጠል ይበጥሱ የነበሩት ግመሎች እስክስታ መምታት ጀመሩ ; ገመሬዎቹ
ዝንጀሮዎች ቦረቁ ; ኮሮኮንች የነበረው መንገድ ወድያው አስፓልት ሆነ ; በሰአት መቶ ሀያ ስትከንፍ የነበረችው መኪናም ወደላይ መዝለል ጀመረች ቀና ብሎ ወደሰማይ የተመለከተው ሹፌር
በቀስተደመና ታጅበው ንግሴ ሮባና አበበ ቢቂላ ብቅ ሲሉ ተመለከተ ......

ሙዚቃው ቀጠለ ..
ፋጡማ ፋጡማ ፋጡማ
እንደለምለም ቄጤማ
እንደአበቦች አውድማ
እንደወለላ ደማ
ነይ ነይ የኔ ፋጡማማማማም !!

ከዚያም አለምነህ ግጥሙን አዝጎደገደው ......
ከዚያም ሙዚቃውን ከዚያም ሀተታውን
ሮባ = ሮባ ማለት ዝናብ ማለት ነው
ፋጡማ ሮባ
ንጉሴ ሮባ .....ቀጠለ አለምነህ .......
እንዲህ እንዲህ ብሎ ነበር በሚጣፍጥ ድምጹና ቃሉ ለሀያ አምስት ደቂቃ የፋጡማን ድል የሰራው ::

ቸር እንሰንብት !!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቺኮኩባኖ

ኮትኳች

Joined: 14 Sep 2006
Posts: 259
Location: usa

PostPosted: Sat Aug 23, 2008 4:50 am    Post subject: Reply with quote

እንኩዋን ደስስስስስስስስስስስስ ያለን
ጥሩዬ ዳግም ድል ተጎናፅፋ ሀገራችንን በማስጠራትዋ
መሰረትም ለትንሽ አብየ ለገሰ ተቀድማ ሶስተኛ ብትወጣም
በጣም የሚያጉዋጋ ውድድር ነበር ያቺ ምስኪን ቱርክ ግን ባንዲራ እንኩዋን የሚያቀብላት አጥታ አሳዘነችኝ የት ገቡ ቱርኮቹ እስቲ ሞፊቲ እንዳለምነኽ ዋሴ አድርግና ዘግበው
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Sat Aug 23, 2008 11:36 am    Post subject: Reply with quote

እንደምን አላችሁ ኢጆሌ ቦሬ

ትርንጎ በጣም አመሰግናለሁ :: ላንቺም ለሁላችንም መጽሀፉን የምናገኝበትን መንገድ በኢንተርኔት ሲሆን የትና እንዴት ሊገኝ እንደሚችል በቅርቡ ቶሎ አሳውቃለሁ ::
ይህንንም መጽሀፍ ስታነቡት የበለጠ ደስተኞች እንደምትሆኑና ብዙ እንደምንነጋገርበት አምናለሁ ::

ዛሬ ከሁለት ሠዓት በኍላ በሚካሄደው የወንዶች 5000 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያዊያኑ ድል እንደሚቀናቸው አምናለሁ :: በተለይም የወርቅ ሜዳሊያው እጃችን እንደሚገባ እርግጠኛ ነኝ :: ሞፊቲ ታስታውሳለህ የዛሬ አራት አመት በግሪክ ኦሎምፒክ ቀነኒሳ በቀለ በአምስት ሺህ ሜትር በሞሮኳዊው ሂሻም ኤልጉራዥ በትንሽ ስህተት ወርቅ መነጠቁ እስካሁን ይቆጨኛል :: እኔ እንደማምነው ዛሬ ቀነኒሳ ያቺን እልሁን ተወጥቶ ያመለጠውን ወርቅ መልሶ እንደሚወስድ አልጠራጠርም ::
ዛሬ አራተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ ቀኒ ሲያመጣ የሜዳሊያ ሠንጠረዡ ከፍ ብሎ በአለም ጥሩ ደረጃ ላይ ያደርሰናል ::
ድል ለአትሌቶቻችን ::

ራስብሩ
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Sat Aug 23, 2008 11:37 am    Post subject: Reply with quote

PostPosted: Sun Aug 24, 2008 10:11 am    Post subject: Reply with quote

ለውድድሩ በቂ ዝግጅት አድርጌ በመግባቴ ውጤቱ በእጄ ሊገባ ችሏል ::

በጣም ፈጣንና ኃይለኛ አትሌቶች እንደነበሩ አውቃለሁ ውድድሩም ፈታኝ ነበር ነገር ግን ለዚህም ጥሩ ልምምድና ዝግጅት ስለነበረኝ ላሸንፍ ችያለሁ ::

አዎን የቤጂንግ አየር ምንም አይነት ተጽዕኖ አላሳደረብኝም ::

ውድድሩ ከተካሄደ ከአምስት ደቂቃ በኍላ ጋዜጠኛ ዓለሙ መኮንን በቤጂንግ ብሄራዊ ስታዲየም ላቀረበለት ጥያቄ በስልክ የሰጠው መልስ ነበር ::

ሲጠበቅና ከኢትዮጵያውያን አልፎ በአለም የስፖርት ቤተሰቦች ዘንድ ታላቅ ጉጉትን ያሳደረው ውድድር ተጠናቆ አንበሳው ኢትዮጵያዊ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ ከአዲስ የኦሊምፒክ ሪከርድ ጋር ለሀገሩ አስገኝቷል ::
እስካሁንም አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን አንድ የብርና ሁለት የነሀስ ሜዳሊያዎችን በማግኘት ኢትዮጵያ በአለም 18 ደረጃ ላይ ትገኛለች :: ከአፍሪካ ሁለተኛ መሆኑ ነው ::
ከአንበሳው ቀነኒሳ በቀለ ድል በኍላ በቤጂንግ ብሄራዊ ስቴዲየም አትሌቶቻችን እና የቡድን መሪዎቹ እጅ ለእጅ ተያይዘው ሠለሜ ሠለሜ አያ ሠለሜ ሲጨፍሩ አምሽተዋል ::
እንዴት እንደሆነ አላውቅም ዓለም ለኢትዮጵያውያን አትሌቶች የተለየ ክብር አለው ::
ጀግናው ኃይሌ ገብረስላሴ ይህንን አይነት ውድድር አድርጎ ለቡድኑ መከታ መሆን መቻሉ እስካሁን ድረስ ያለውን ትልቅ ጥንካሬ አስመልክቷል :: ኃይሌ በሚቀጥለው የሎንዶን ኦሊምፒክ በማራቶን ተካፋይ እንደሚሆን እና በቂ ዝግጅትም እንደሚያደርግ ከወዲሁ ትልቅ ተስፋ ሰጥቶናል :: ጀግናው ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ በዘንድሮው የቤጂንግ ኦሊምፒክ ላይ ባደረገው ጠንካራ የቡድን ሥራ ባሻገር ከረዥም ግዜ ልምድ እንደምናየው ኬንያውያኑን የማሸነፍ ልዩ ጥበብ አንበሳው ቀነኒሳ በቀለ ከኃይሌ የተረከበውን ጀግንነት በግብር አሳይቷል :: ስለዚህም አልጋወራሽ የሚል ስያሜን አትርፏል ::

ከሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ ስምንት የሜልቦርን ኦሊምፒክ ጀምሮ ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ የተካፈለች ሲሆን ባጠቃላይ 38 ሜዳሊያዎች ባለቤት መሆን ችላለች ::
ከነዚህም ውስጥ ከፍተኛውን ብዛት የያዘው 18 የወርቅ ሜዳሊያ ሲሆን ስድስቱ የብር 14 የነሀስ ሜዳሊያ ናቸው ::
አበበ ቢቂላ አለም በማይረሳውና አሁንም ድረስ ትኩስ በሆነው የማራቶን ታሪኩ የመጀመሪያውን የኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ያጠለቀው በአዲስ የኦሊምፒክ ሪከርድ ነበር :: ጀግናው ኃይሌ ገብረስላሴ በሞንትሪያል ኦሊምፒክ 10000 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ሲያጠልቅ በአዲስ የኦሊምፒክ ሪከርድ ነው ::
ይህንን አዲስ ሪከርድ በግሪክ ኦሊምፒክ የሰበረው አንበሳው ኢትዮጵያዊ ቀነኒሳ በቀለ ሲሆን ቀነኒሳ ዘንድሮም በቤጂንግ ኦሊምፒክ በራሱ ተይዞ የነበረውን የኦሊምፒክ ሪከርድ ሰብሯል ::
አስገራሚው ነገር ቀነኒሳ በተሰለፈባቸው የሁለት ርቀቶች በሁለቱም አዳዲስ ሪከርዶች በማስመዝገቡ ዓለም ታላቅ አድናቆትን ቸሮታል ::
በሴቶች 10000 ሜትር እንደወንጭፍ ስትወረወር የቤጂንጉን ብሄራዊ ስታዲየም ቀልብ የሳበችው አትሌት ጥሩነሽ ዲባባም አዲስ የኦሊምፒክ ሪከርድ በመስበር አይበገሬነቷን አስመስክራለች ::
ለሁለተኛ ግዜ የኦሊምፒክ 10000 ሜትር የብር ሜዳሊያ ባለቤት የሆነው ስለሺ ስህን (ካንጋሩ ) ወደ ሀገሩ እንደተመለሰ ከባለቤቱ ከጥሩነሽ ጋር ጋብቻቸውን እንደሚፈጽሙ ይጠበቃል :: ከድል በኍላ ጋብቻ በጣም ደስ የሚል ነው የሚሆነው :: ጀግናው ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ እና የሲድኔው ኦሊምፒክ የማራቶኑ ጀግና ገዛኸኝ አበራ ጋብቻቸውን የፈጸሙት ከድል መልስ እንደነበር ሁላችንም የምንረሳው አይደለም ::
ኢትዮጵያይውያኑ አትሌቶች ከሀገራቸው ወጥተው ለባእዳን ሀገራት እየተሸጡ በስፖርቱ አደባባይ ብቅ ብቅ ማለታቸው ጎላ እያለ መታየት ጀምሯል ::
ከዚህ በፊት በክለብ ለመታቀፍና የውድድር መድረኮችን ለማግኘት በጣም ጠባብ ከመሆኑም በላይ መሰናክሎች የመኖራቸውን ያህል አሁን ደሞ ማንም ችሎታ ያለው አትሌት መድረኩን በቀላሉ ማግኘት የሚችልበት የፕራይቬት ስፖርት ክለቦች መመስረታቸው ይህን አይነቱን ችግር ያቃልላል የሚል ትልቅ ተስፋ አለ ::
ከውድድር አሸናፊነት በኍላ ደስታቸውን መግለጽ ሳይችሉ መቅረት የባዕድን /ያልተወለዱበትን ሀገር ) ባንዲራ ይዞ መሮጥ ...... ከሞራልም አኳያ ምን ያህል ስሜት ሊፈጥር እንደሚችል መገመት አይቸግርም :: ለውድድር መሸጥ ከተቻለ ከጥቅም አኳያ ጥሩ ነው ብሄራዊነት ግን የሚሆን አይመስለኝም ::
ዛሬ ከቀኑ 10 ሠዐት ጀምሮ በሚደረገው የቤጂንጉ ኦሊምፒክ የመዝጊያ ሥነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያን ቡድን በመምራት ሠንደቅ አላማችንን ይዞ ከፊት የሚሰለፈው አንበሳው ቀነኒሳ በቀለ ነው ::
ይሄው የኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ቡድን ረቡዕ እለት ከጠዋቱ 12 ሠዓት አዲስ አበባ ቦሌ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ እጅግ ከፍተኛ አቀባበል እንደሚደረግ ተገልጿል ከሶስት ሠዓት ጀምሮ በብሄራዊ ስቴዲየም የሚደረገውን የአቀባበል ሥነ ሥርዓት በቦታው ተገኝተን ለመመልከት አደቆርሳም ደፋ ቀና እያለ ነው ::
_________________

kibremengist
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Sun Aug 24, 2008 10:29 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

አዶቆርሳ = ሰፊ ስለነበረው የአትሌቶቻችን ድል ዘገባህ ከልብ አመሰግናለሁ ::
ይበልጡን ደግሞ እሮብ ጀግኖቹን ለመቀበል መሰናዳትህን ስትገልጽልኝ በጣም አስቀናኧኝ ::
የሲዲኒ ኦሎምፒክ ግዜ ከወቤ ጃሎ ኤርፖርት ሄደን የነበረውን አቀባበል ሳስበው ይሄ ደግሞ ምን
ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል ::
የትላንቱ የማራቶን ድል እኔንም እንደራስ ብሩ አስደስቶኛል ::ሶስቱም ሯጮች እስከመጨረሻው ያሳዩት
ትግል አስደንቆኛል :: እውነት ለመናገር የጠበኩት አልነበረም ::እንደሴቶቹ ይከብዳቸው ይሆናል የሚል ግምት ነበረኝ ::በጣም ተደስቻለው ::
ያም ሆነ ይህ ግን አራቱንም ወርቅ ያገኘነው በሁለት ጀግና አትሌቶች ብቻ መሆንን ሳስብ ደግሞ ወደፊት ምን እንደሚውጠን ያሰጨንቀኝ ጀምሯል ::
ጎሮቤቶቻችን ኬኒያውያን በተሰለፉበት ውድድር ሁሉ የሜዳልያ ባለቤት ነበሩ :;እናም ሁጤታማ ሆነዋል ::ከነሱ ምን ልንማር እንደምንችል የቤት ስራውን ለባለሙያዎቹ ለግዜው መተው ይሻላል ::
የሚቀጥለው የለንደን ኦሎምፒክ ቀነኒሳ 30አመት ስለሚሆነው እንደዚሁ በጥንካሬ ላናገኘው እንችላለን ::
ሀይሌን የተካልን እሱ ቢሆንም እስካሁን ድረስ እሱን እየመሰለ የመጣ አትሌት ያለማየታችን
እጅግ በጣም አሳሳቢ ነው ::

ለማንኛውም እንኳን ደስ ያለን ::

ቸር እንሰንብት !!!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወቤ (ጃሎ )

ኮትኳች

Joined: 28 Jul 2004
Posts: 201

PostPosted: Tue Aug 26, 2008 12:56 am    Post subject: Reply with quote

ወገኖቼ እንኳን ደስ አላችሁ ! በድጋሚ ;
ቺኮ , ራስ ብሩ ሞፊቲ እንዲሁም አዶቆርሳ የቤጂንጉን ድል አስመልክቶ ያቀረባችሁት ዘገባ በጣም ድንቅ ነበር ::
እኔ ኮምፒዩተሬ ትንሽ እክል ገጥሞት በወቅቱ ደስታዬን ዋርካ ላይ መግለጽ አልቻልኩም ሆኖም ማንበቡን እችል ስለነበር የሁላችሁንም በሚገባ ተከታትያለሁ ::
ሞፊቲ - ቀነኒሳ ቅዳሜ እለት ዳግመኛ ወርቁን ካገኘና ወዲያዉኑ አንተ ደዉለህልኝ እንደጨረስን ከአገር ቤት ማን ደወለልኝ መሰለህ ?
ልጅ አመሀ ወልዴ ከአዲስ አበባ ! ታዲያ ላንተ የከበረ ሰላምታ አቅርቦልሀል ; ስለ ኬኒያው ካማቲ ሁሉ አንስቶ በጣም ስቀናል :;ከአንድ ወር በህዋላ እኔ ያለሁበት አገር ለጥቂት ቀናት እንደሚመጣ ነው : በተረፈ ቀሪዉን በስልክ አብራራልሀለሁ ::
ሌላው አትሌቶቻችንን ከሲድኒ ኦሎምፒክ መልስ ለመቀበል እኔና አንተ ቦሌ አየር ማረፊያ ሆነን ስንጠባበቅ ግቢው ዉስጥ የነበረ አንድ ትልቅ ዛፍ ላይ ወጥተው የነበሩ ልጆች የዛፉ ቅርንጫፍ ተገንጥሎ ከነልጆቹ መሬት ላይ የፈረጡት ትዝ ይለኛል ; ልዩ አቀባበል ነበር እሮብ እለትስ ? እንዴት ይሆን ?
ሰላም ሁኑ ! ሰላምታዬ ለሁላችሁም ይድረስ !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ወቤ (ጃሎ )

ኮትኳች

Joined: 28 Jul 2004
Posts: 201

PostPosted: Tue Aug 26, 2008 12:58 am    Post subject: Reply with quote

በስህተት ተደግሞ የተሰረዘ :
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Wed Aug 27, 2008 3:15 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

ወቤ = የልጅ አመሀ መደወል አስደንቆኛል ::እሱ መቼም የሀገሩ ባንዲራ ነገር አይሆንለት ?
ሎንዶን ሲመጣ ቃል የምትገባለት ነገር ከአራት አመት በኌላ አንተ ባለህበት ሀገር የሚዘጋጀውን
ኦሎምፒክ በአይኑ እንዲመለከት የምትጋብዘው መሆኑን ነው :: ወይ አመሀ ?እሱ በቃ ትዝ የሚለኝ
እንዳልከው በካማቲ ነገርና ያቺ ላሊበላ ሆቴል ጠብቄ የተቀበልኩት ሶስት ሺህ ብር ናት ::
የዛኔ እኮ ነው ለመጀመርያ ግዜ ሜዞ እያላችሁ የምታዙትን ውስኪ የጠጣሁት ::እኔ በመለኪያ ለዚያውም የሻኪሶዎቹ
ሀብታሞች ሲመጡ (ቺኮ እንዳይሰማ ) የምቀምሳትን ውስኪ እኮ ነው እናንተ ስትጫወቱበት ያየኌችሁ ::
ለማንኛውም ደግመህ ከተገናኛችሁ የከበረ ሰላምታዬን አቅርብልኝ ::

ውድ ራስ ብሩ ምነው ቁምነገር የያዘውን መልክቴን የዳቦ ቅርጫት አረካት ?ባይስማማህ እንኳ ሚሴጅህ
ደርሶኛል አይባልም እንዴ !?

ቸር እንሰንብት !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ራስብሩ

ዋና ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2005
Posts: 607

PostPosted: Wed Aug 27, 2008 10:04 am    Post subject: Reply with quote

Quote:
ውድ ራስ ብሩ ምነው ቁምነገር የያዘውን መልክቴን የዳቦ ቅርጫት አረካት ?ባይስማማህ እንኳ ሚሴጅህ
ደርሶኛል አይባልም እንዴ !?

ያንተ መልክት የደረሰኝ ትናንት ምሽት ነው ዛሬ ደሞ ገና መንጋቱ ነው :: ከፍ ካለ ምስጋና ጋር ተቀብዬሀለሁ :: መልሱን በጣም በቅርቡ አሳውቅሀለሁ ::
እስከዚያው የላኩልህን መልክት ተመልከተው ::
_________________
This is Ras Biru Woldegebriel.......................!!

http://www.oyla22.de/userdaten/406/65542/bilder/Ras_Biru.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 63, 64, 65, 66  Next
Page 64 of 66

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia