WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የአዲስከተማ ሰዎች ካላቹ
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 17, 18, 19, 20, 21  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ሀምሳለ

ኮትኳች

Joined: 13 Oct 2006
Posts: 238
Location: America

PostPosted: Mon Mar 09, 2009 5:08 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የሰፈር ልጆች

በጣም አሳዛኝ ዜና ሰምቼ ማመን ስላቃተኝ እናንተ ሰምታችሁ ከሆነ ለማጣራት ብቅ አልኩ .
ቀበሌ 39 እና 49 Crying or Very sad ሊታረስ ነው አሉ ከልደታ ቤተክርስቲያን እስከ የድሮው ኮካኮላ Crying or Very sad እውነት ነው ????????????????????????
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Wed Mar 11, 2009 12:17 am    Post subject: Reply with quote

50 ይሄንን ዜና ያባቱ ልጅ ሲመጣ ቦርቅቆ ያስረዳናል እሱ ነው ሠሞኑይን የሠፈሩን አዋራ ቀምሶ የመጣው .... ግን ምን ሊዘሩበት ይሆን ያረሱት ?
_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዮሀንስ ተክለ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 12 Dec 2007
Posts: 80

PostPosted: Tue Apr 21, 2009 4:59 pm    Post subject: Reply with quote

ዋናው እንደጻፈ(ች)ው:
50 ይሄንን ዜና ያባቱ ልጅ ሲመጣ ቦርቅቆ ያስረዳናል እሱ ነው ሠሞኑይን የሠፈሩን አዋራ ቀምሶ የመጣው .... ግን ምን ሊዘሩበት ይሆን ያረሱት ?

ባጋጣሚ ያገኘሁት የአዲስ ከተማ ዌብ ሳይት ተመልከት
http://myaddisketema.weebly.com/songs-and-videos.html
_________________
http://news.bbc.co.uk/olmedia/1930000/images/_1931617_shoe150.jpg
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቶድ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 04 May 2007
Posts: 80

PostPosted: Tue Oct 06, 2009 12:42 am    Post subject: Reply with quote

ለውድ የአዲስ ከተማ ልጆች !!!!!!!!!!
በቅድሚያ እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ !!!!!!
ጎበዝ ምነው ተደባበርን ????????? ዋናው (ዋንቾ ) እንደሆን እንደመንግስት ባለስልጣን ለምርጫ ሰሞን ብቻ ነው ወደዚህ ዓምድ ብቅ ብሎ ...... ወዳጆቼ , ወገኖቼ .... ምናምን የሚያበዛው :: ቕቕቕቕቕቕቕ ኧረ ለመሆኑ ምነው ተጠፋፋንሳ ????? ዮሀንስ ተክለ ...... ያንተ ከሁሉም ይሻል ነበር ዳሩ ግን የአዲስ ከተማ ዌብሳይት እያልክ የምትለጥፈው ነገር ምንም ሊታየኝ ስላልቻለ እባክህ በሰቀቀን አትግደለን :: ከለጠፍክም በደንብ እንደፀሐይዬ ጎሚስታ የሚታይ ነገር ለጥፍ !!!!!!!!!!!!! ቅቅቅቅቅ
ለማንኛውም ለብቻዋ የምትለጥፋት ያቺ ልዩ ምልክትህ ጫማ (ሸበጥ ) ብዙ ነገር እያነጋገረች ነውና ......... ቅቅቅቅቅ ....... ከፖለቲካ ውጪ ነው ግን ....... የአዲስ ከተማ ዌብሳይት እያልክ ከምትለጥፍ ዙሪያዋን የሆነ ነገር ብታስለጥፍባት መልካም ነው :: ውድ ያራዳ ልጅ ወንድም ዮሀንስ ..... ለጫወታ ብቻ ብዬ ነውና እንደ ወቀሳ እንዳትውሰደው አደራ !!!!!! የመርኬ ዓምላክ እንደገና እንድንሰባሰብ ያድርገን ..... ከከበረ ሰላምታ ጋር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቶድ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 04 May 2007
Posts: 80

PostPosted: Tue Nov 10, 2009 11:39 pm    Post subject: Reply with quote

የአዲስ ከቴ ልጆች ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Tue Nov 17, 2009 1:52 pm    Post subject: Reply with quote

የሠፈር ልጆች ሠላም ብያለሁ :: ተጠፋፋን ነው ሚባለው ተረሳሳን እስቲ በቅርቡ ሄዳችሁ የመጣችሁ ቢቻላችሁ ፎቶ ካልሆነም ወሬዎችን በፅሑፍ አስነብቡን ካልሆነም እዚህ ሀይ እንባባልና ስለጥንቱ እናውራ መቼም የሠፈር ትዝታን አውርቶ መጨረስ አባይን እንደመጨለፍ ነው ::
ቶድ እንዴት ነህ ? ድምፅህ እንዴት ያስተጋባል ባክህ ከባሕልና ስነፅሑፍ ሠፈር ሰምቼህ ' ነው ብቅ ያልኩት ... የቀበሌ ስብሰባ ድምፅ ማጉያ ሚለፍፈው አለማር ትዝ አለኝ ጥሩ ድምፅ ነበረው እሱ ሰውዬ ግን ሁለቱም እግሮቹ ግራ ናቸው ሚባለው እውነት ነው ??? ጫማ ሲገዛ ደብል ደብል ነው እያሉ ሲነግሩኝ ትዝ ይለኛል አረማምዱ ግን አውንም ድረስ ዓይኔ ላይ አለ ::
እስቲ አትጥፉ ፕሊስ

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ቶድ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 04 May 2007
Posts: 80

PostPosted: Fri Dec 25, 2009 8:12 pm    Post subject: Reply with quote

እንኳን ለፈረንጆቹ ገና በሰላም አደረሳችሁ !!!!...... እንዲሁም ለፈረንጆቹ አዲስ ዓመት እና ለመጪው እውነትኛው የሀገራችን ገና በዓል በሰላም ያድርሳችሁ !!!

የዛሬን አያድርገውና መርካቶን በዓመት በዓል ሰሞን ያላትን ድምቀት ሳስበው ..........

ላለው ...... በእጥፍ ሰጥቶ
የሌለውም ደግሞ ...... ካለው ላይ ቀምቶ
ማን ነበር የሚውል ...... በሀዘን ተከፍቶ
ያኔ ባገራችን ...... ውሎ በመርካቶ ::

ግና ግና የዛሬን አያድርገውና ይኽው የመርኬን ቤት ጭር አደረግናት .......... ለማንኛውም የአንድ ሰው ምላሽ ካለ ትዝታዋን አዥጎደጉደዋለሁ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ግግሌ 3

ኮትኳች

Joined: 03 Jan 2010
Posts: 113
Location: atlanta

PostPosted: Wed Jan 06, 2010 8:28 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ሰላም የአዲስ ከቴ ልጆች እንዴት ናቹ መልካም የክርስቶስ ልደት ያድርግልን ብያለው ግግሌ 26 ቀበ Very Happy
_________________
fan of the ethiopian renaisance
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ግግሌ 3

ኮትኳች

Joined: 03 Jan 2010
Posts: 113
Location: atlanta

PostPosted: Mon Jan 11, 2010 1:58 am    Post subject: Reply with quote

አዲስ ከተማ ስማር በጣም ከምወዳቸው አስተማሪዎቼ መካከል ሁለቱ አሌክሶች ይገኙበታል አንደኛው አሌክስ ዘጠነኛና አስራአንደኛ ክፍል ኬሚስትሪ ያስተማረኝ ረጅሙ ቀዩ አሌክስ ነው እና ሲያስረዳን የማይረሳኝ ነገር መጽሀፍ ሳይዝ በቃሉ ነበር ኬሚስትሪ ፍትፍት አርጎ ያጠጣን ምን ዋጋ አለው ማትሪክ ላይ ውለታውን ሳንከፍል ቀረን እን Sad Sad አሁን ታድያ ስሰማ የትምህርት ቤቱ ዩኒት ሊደር አደረጉት አሉ እንደሱ አይነቱን ጂኒየስና ሃምብል የሆነ ሰው ዩኒት ሊደር ማድረግ ተማሪውን መጉዳት ነው እሱ ጊፍትድ የሆነ አስተማሪ ነበር አስራአንደኛ ክፍል እያለን አዋጥተን የወርቅ ሃብል እንደሸለምነው አስታውሳለው ሁለተኛው አሌክስ የአስራሁለተኛ ክፍል እንግሊዘኛ አስተማሪያችን የነበሩት እንግሊዘኛን እንዳንፈራው ያደረጉን ናቸው በራሳቸው የአስተማመር ዘዴ እየቀለዱና ምሳሌ እየሰጡን እንግሊዘኛን ቀለል አድርገን እንድንይዘውና ከመጽሄት እስከ ትልልቅ መጽሀፍ እንድንዳፈር ያደረጉን አስተማሪያችን ነበሩ
_________________
fan of the ethiopian renaisance
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Ironman

መንገደኛ

Joined: 10 Jan 2010
Posts: 7

PostPosted: Thu Jan 14, 2010 2:15 pm    Post subject: የመርካቶው ነኝ Reply with quote

የመርካቶው ነኝ ሀሳቡ ጡሩ ነው መሰባሰቡ ለክፉም ለደጉም
ትውልዴም እደገቴም ከፍተኛ 6 ቀበሌ 04 ነው
የአሁኑ አውቶብስ ተራ የኔ ታላላቆች ደግሞ ጠቅላይ ቤሮ በሚለው መጠሪያ የበለጠ ያውቁታል
ሰለጠቅላይ ቢሮ ስያሜ ከኔ የበለጠ የሚያውቁ
ሰለሚኖሩ ፈቃደኛ የሆኑ ካሉ ትንሽ ቢዘክሩን አይከፍም
አለበለዚያ መሰባሰቡን እንቀጥል ብዙ ትዝታ ይኖርናል
አዲስከተማ ብዙ ነገር የሆናባታ የነቻይና ግሩፕ የነበሩባት
በዘምነ ደርግ ደግሞ ጌዜ የኢሀፓ ትልቁ የከተማችን ሕዋስ
የነበረበት አባዛኛው ወጣት በቀይ ሽብር ያለቀበት በወያኔ
ዘመነ ደግሞ ብዙ ወጣት ባጋዚ ቅልብ ግምባሩን እየተመታ
የወደቀበት ነው ብዙ ማለት ይቻላል ሌላው

በይደር ይቆይልኝ

ብቸር ያቆየን የናንተው አይረን ንኝ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ማሉሜ

አዲስ

Joined: 28 Jan 2010
Posts: 19
Location: ZULU LAND

PostPosted: Thu Jan 28, 2010 10:52 am    Post subject: Reply with quote

ውዴት ! ውዴት ! እኔ ልመጣ ስል ነው እንዴ የምትጠፉት ? በሉ ሰብሰብ በሉ !! ዋናው !! ቶድ !! አንቆጲ !! ሐምሳል .....ላሊ ገየት ....ታቲ ገየት ...እር ሁላችሁም ተመለሱ ......
_________________
I am who I am!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Getsh

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 09 Aug 2003
Posts: 94

PostPosted: Fri Jan 29, 2010 5:16 am    Post subject: Getsh Reply with quote

የቆየ የዋርካ እንግዳ ትቀበላላችሁ ?

በቅድምያ ሰላም ለሰፈሬ ልጆች !

አንዳንድ የማያቸው ስሞችን በደንብ አስታውሳቸዋለው ማለቴ እዚሁ ዋርካ ውስጥ : ስለአዲስ ከተማ የሚነሱት ግን ብዙ ትዝታ ጭረውብኛል እርግጠኛ ነኝ ብዙዎቻችን ያንድ ቦኖ ውሀ ነው የጠጣነው : ውሀው ቢቀር ያለሙ ሜዳን ቀይ አፈር ቀምሰናል ::

ለትውውቅ ይህን ታህል ካልኩኝ ይበቃኛል

ቸር ሰንብቱ
ጌትሽ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቶድ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 04 May 2007
Posts: 80

PostPosted: Sat Jan 30, 2010 1:28 am    Post subject: Reply with quote

ሀይ መርኬዎች እንዴት ሰነበታችሁ !!!!! Getsh,,, ማሉሜ ,,,, Ironman እና ግግሌ 3 እንኳን ወደ ውድ ሰፈራችን ወደመርካቶ ዓምድ በሰላም መጣችሁ !!!!!!!!

Getsh ....... አቦ ቃላቶችህ በጣም በትንሹ እንኳን ሆነው እንዴት ያምራሉ ......... የዓለሙ ሜዳን ቀይ አፈር ቀምሰን አልክ ??????? አቦ ይመችህ ወዳጄ !!!!! እዛ ዓለሙ ሜዳ ኳስ ስጫወት በሳንባዬ ያጠራቀምኩትን አፈር አንድ ቀን ዶክተር በራጅ ከተመለከተው በኌላ ጎረቤቱ በጭቃ ቤት ወድሚያሰሩ ወዳጆቹ ሄጄ አዋራዬን እንዳራግፍ የታዘዝኩትን አስታወስከኝ :: ቅቅቅቅቅቅ እስኪ ከትዝታዎችህ ጀባ በለንና እንሰባሰብበት እንጨዋውትበት እባክህ ....... አትጥፋ !!!!

ማሉሜ ያራዳ ልጅ !!!! መምጣትህ /ሽን ሳታሳውቀን ሁሉ እንደምትመጣ / በደንብ እናውቅ ነበረና እባክህ ከትዝታዎችህ / ጀባ ጀባ ....... አብሽር እኛማ አለን !!!!!

በእንግሊዝ Ironman ...... በኛ ብረቱ ሰው
ፀባዩ ምቹ ነው ...... ለፈረንጅ ላበሻው
በደንብ ያስታውቃል ....... የትውልዱ ቦታው
እንዳትገረሙ ..... የመርካቶ ልጅ ነው ::
ፈረንጅኛ ስምክን ...... ሳስብ ስፈትሸው
ያበሻነት መንፈስ ........ ምንም ስለሌለው
መርኬ አደዋውዬ ..... ብዙ አጣርቻለው
በዚህ አያውቁህም ..... ባበሻ ስምህ ነው
እነሱም ባይነግሩኝ .... ቢሉኝም አናውቀው
የድሮ መጠሪያህ ..... መች የሚጠፋኝ ነው

Ironman አይደለም ...... ጠንክር አብሬ ነው ::
Razz Razz

ቅቅቅቅቅ ለጫወታ ነው ወዳጄ !!!!!!!! እንኳን ደህና መጣህ ... 6 04 በተለይ አዲስ ከተማ የተማር ሰው ብዙ ትዝታ አለው :: አንተው እንዳልከው ደግሞ በጠቅላላው የመርካቶ ወጣት ለውድ ሐገራችን በሚደረግ ገንቢ ትግል በግንባር ቀደምነት በመሰለፍ መስዋት እየሆነ ያለፈ አንቱ የተባለ ትውልድ የፈራበት ሰፈር ነው :: አሁንም እስከመጨረሻው ለሀገሩ ሟች ነው :: አቦ መርኬ ......
ወዳጄ አንተ ጋር ብዙ ትዝታዎች አሉንና እስኪ አዥጎድጉደው እባክህ ....

ግግሌ 3 አንተም በተለያዩ ቦታዎች የምትጽፋቸውን መጣጥፎች ስመለከት በሰፈራችን ያለህ ተሳትፎ ማነሱ ተገቢ አይደለምና እባክህ እንኳን ደህና መጣህ ...... እስኪ ያለሙ ሜዳን ትዝታና በጥቅሉ የመርኬን መንፈስ በዚህ ቤት እናርከፍክፈው :: ቸር ይግጠመን !!!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Getsh

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 09 Aug 2003
Posts: 94

PostPosted: Tue Feb 02, 2010 12:11 am    Post subject: Getsh Reply with quote

ሰላም ለሁላችሁም !!!

ቶድ ቀለም የነካ ብዕርህ ሳይደርቅ ሌሎቹንም የቤቱ እድምተኞች ከያሉበት ቀባ ቀባ አድርግልን እስቲ : ባይሆን ለማፈላለጉ እተባበራለው : ለነገሩ ያሉበት ይጠፋሀል የሚል ዕምነት ኖሮኝ ሳይሆን ጊዜህን ለመቆጠብ ታህል ብዬ ነው ::

ባቲንና ዋናውን - ብሌን ብትገባ ከሁለት ኮረዶች ጋር ድራፍታቸውን ሲኮመኩሙ ታገኛቸዋለህ ብዬ ተስፋ አደርጋለው
ዲጎኔን - ልደታ ካለው ቁርጥ ስጋ ቤት ሞክር እዚያ ከሌለ ካምቦዲያ አካባቢ አፈላልገው
ዮሀንስን - ጥሩ ፓርክ ወይም ዋርካ እንደምታገኘው ጥርጥር የለኝም : ችግሩ ግን የያዛትን Girl ጀንጅኖ ከጎጆ እስኪወጣ መጠበቅ ሊኖርብህ ነው ማለት ነው
ሉህን ደግሞ ገብረመስቀል ግሮሰሪ ወይም 21 ክበብ ቼክ አርገው
ሀምሳለን - ዌናሞ ሳላያት የቀረሁኝ አይመስለኝም ማኪያቶዋን ጠጥታ ወደ ሁለተኛ ፎቅ ወጥታለች : e-mail check ልታደርግ ወይም ዋርካ ላይ post የምታደርገው አዲስ ነገር ሳይኖራት አልቀረም ብዬ አስባለው
የጦምኔው አድራሻ አንተም ካወቅክ ብትነግረኝ ደስ ይለኛል
ባለሱቁን - ዱቤ ከሌለብህ እዛ አውቶብስ ተራ አካባቢ አታጣውም
ጌታን - ለጊዜው ከአዲስ ከተማ ወጣ ስላለ የምታገኘው አይመስለኝም : ፋሲካ እየቀረበ ስለሆነ ከገበሬዎች ዶሮ ለመግዛት ክፍለሀገሩን እያዳረሰው እንደሆን መረጃዎቼ ጠቁመውኛል
መልካም ዜና እንደምታሰማን እምነቴ ነው ::

ሰላም ሰንብቱ
Getsh
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቶድ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 04 May 2007
Posts: 80

PostPosted: Fri Feb 05, 2010 3:08 am    Post subject: Reply with quote

Getsh !!!!! መች እኔ አንተን አጣሁህ ..... ገና በፊደል አጣጣልህ እርድናህን ሙልጭ አድርጌ ነው ያወኩት :: በነገርከኝ መሰረት እያንዳንዳቸውን የመርኬ ልጆች በጠቆምከኝ ቦታ በትክክል አግኝቻቸኌለሁ :: ግን ባቲና ዋናውን ብሌን ሆቴል ላገኛቸው ስገባ የተለመደውን ሄልሜት (የወታደር የብረት ኮፍያ ) ባላደርግ ኖሮ .... ጭንቅላቴ ተበርቅሶ ነበር :: አቦ እዛ ብሌን ሆቴል መቼ ነው ድብድብ የሚቆመው :: ታዲያ የጸቡ ዋናው መነሻ ''ዋናው '' ሆኖ ነበር ያገኘሁት :: ምንም እንኳ ዋናው ጸብ ባያነሳም ሁለት የብሌን ኮረዶች ወደውት ሲደባደቡ እገላግላለሁ ብሎ ነገሩን አባብሶት ........ ጉዳዩ እንዴት እንደተቋጨ ባላየውም በአልጀዚራ መተላልፉን ሰምቻለሁ :: ቅቅቅቅቅቅቅ

ወንድም ዲጎኔን ግን ማግኘት እጅግ በጣም ነበር የከበደኝ .... ምክንያቱም እሱ እንደምታውቀው የድሮ ጉልቤ ከነበሩት ከእነ መስፍን ታመነና አየለ ጅቦ ውስጥ አንዱ ስለነበር እስካሁን ወኔ አልከዳውምና .... ሲያሻው የፍንዳታዎች ቤት ሲያሻው ደግሞ የሽሜዎች ቤት ሲስተሙን እየቀያየረ በመዘዋወር ስለሚዝናና እሱን ማግኝት ከባድ ሆኖብኝ ነበር :: እንደተመለከትኩትም በድሮ ስሙ ብዙ ሰዎች ያከብሩታል :: ...... ምንአልባትም ?????? ..... በቃ ትቼዋለሁ !!!!!!

በነገራችን ላይ ስለ ዲጎኔ የሰማሁት ...... በኢሕአፓ ጊዜ ውድ ሀገራቸውን ከወታደራዊ አገዛዝ ለማላቀቅ የህይወት መስዋትነት ከፍለው ካለፉት እጅግ በጣም የተማሩና .... ያልተማሩም ቢኖሩ እንኳን በወገንና በሀገር ፍቅር አንቱ የተባሉና የተመረቁ ብርቅና ድንቅ ወንድምና እህቶቻችን መሐከል በህይወት ከተረፉት ውስጥ አንዱ እንደሆነ በተነገረኝ ጊዜ የተሰማኝን ስሜት እንዳትጠይቀኝ !!!!!! በእዛ ታላቅ ትውልድ ውስጥ የነበረው ወኔና ሀገር ፍቅር በእውነት አስደሳች እና አስገራሚ ነበረ :: አሁን ያለውም ትውልድ ቢሆን .... በተለይ በሰፈራችን አካባቢ ያለው ትውልድ የሚያሳየው የወገንና የሐገር ፍቅር እጅግ በጣም አስደሳችና ምናልባትም ሐገራቸውን ለውጪ ገዢ ጠላት አሳልፈን አንሰጥም ብለው በወደቁ በእነዛ በታላቅና በከበረ ማዕረግ በተሸለሙ ብርቅና ድንቅ ሰመዓታት አያትና ቅድም አያቶቻችን እንዲሆም ባለፈው ስርዓት በግፍ የተሰዉት ወንድምና እህቶቻችን መልካም መንፈስ በውስጡ አድሮበት ይሆን እንዴ ???? ያስብላል :: በተለይ አሁን ባለፈው የምርጫ ውድድር ወቅት ..... የሕዝቡን መብት ለማስከበርና ሕዝብ ያልፈለገውን ፓርቲ ለመጣል ያደረገው ትግልና የከፈለው መስዋትነት አስገራሚ .. አስደሳች .... አልፎ ተርፎም እጅግ በጣምም አሳዛኝ ነበር :: እስከመቼ ይሆን በሐገራችን መንግስት በጦር መሳሪያ ስልጣን እየያዘ ..... ወገናችንን በመረሸን መጨረስ የሚያቆሙት ??????
እዚህ ጋር ግን አንድ ነገር ተረዱልኝ ...... ከላይ ስለ ኢሕአፓ ስናገር ከዕርዮተ ዓላማ አኳያ ስለ ኢሕአፓ የማውቅ ሰው አይደለሁም :: አላማቸውም ትክክል ነበር /አልነበረም ለማለት ብዙ የማውቀው ነገር የለኝም ........ ነገር ግን ያደረጉት ትግልና የከፈሉት መስዋትነትን ..... በትክክል ለሐገርና ለወገን በሚጠቅም ራዪ ተነሳሽነት ከነበረና የሕዝባችንም ትክክለኛ የልብ ትርታን ባዳመጠ መልኩ ከሆነ .... እጅግ በጣም የተከበረና .... በታሪክ ማሕደር .. "በከበረ እንቁና በአማረ የአልማዝ ልባስ በተጠረዘ መፅሀፍ ውስጥ በሚያብረቀርቅ የወርቃማ ቀለማት ተፅፎ አብቦና አሸብርቆ ከትውልድ ትውልድ ይተላለፋል :: ሐገራችንም በወታደራዊ አገዛዝ ሳይሆን መገዛት ያለባት .... ወይንም ከውጪ መንግስታት ..... መሪ እየተመረጠላት ..... የውጪ አለቆቹን የስልክ ጥሪ እየጠበቀ የሚያስተዳድረን መሪ የሚሾምባት ሀገር መሆን ሳይሆን ያለባት ...... በታሪኳና በባህሏ የኮራች ...... በጠላት ያልተገዛችና ከበዓድ ገዢ ኃይል ጋር ያልጎለመተች በመሆኗ ......ሊያስተዳድራት የሚገባውም ....... በቀለም ትምህርቱ የላቀ ጠቢብ ..... በአፈጣጠሩም እሩህሩህና ፈርሀ እግዚሕአብሔር ያለው ኢትዮጵያዊነት መንፈስ ያደረበት ሀገር ወዳድ ሊሆን ሲገባው ..... ነገር ግን ካልተማረም እንኳን ባህላችንንና ታሪካችንን የሚያከብር የሓገራችንን የህዝብ ትርታ የሚያዳምጥ አስተዋይ .... ህዝቡ ወዶትና መርጦት ለስልጣን በሚበቃ ምርጥ ዜጋ ነው መመራት ያለባት :: ይህም እውን ከሆነ አመራሩ ፍጹም ይሆናል !!!! ... ባይሆን እንኳ አደጋው አነስተኛ ነው የሚሆነው ::

በእነ ዲጎኔ ጊዜም ተማሪው በባዶ እጁ መሳሪያ ከታጠቁ ወታደሮች ጋር ያደረገውን ትግልና የከፈለውን መስዋትነት በዚህ መልኩ ከነበረ ...... እጅግ በጣም አስደናቂ ነበር :: አሁንም ያለው ትውልድ ..... ሀገራችንን በዘር በጎሳና በቋንቋ ለመከፋፈል የሚደረገውን ትግል በመቃወምና ... እውነተኛ ዲሞክራሲ በሀገራችን እንዲሰፍን ..... ነፃ የመገናኛ ብዙሐን (media) አገልግሎት እንዲኖር ...... እንዲሁም ህዝቡ የፈለገውን ለመምረጥና እንዲሁም ለስልጣን የወደደውን ለማብቃት ... ብረት ከታጠቁ ወታደራዊ አገዛዝ ጋር ያደረገው ትግል እንዲሁ አንቱ የሚያስብልና ወደፊትም ታፍኖ የማይቀር ራዪ እንደሆን በሙሉ ልቤ የምመሰክርለት ነው :: አቦ መርኬ ......... ደግሞ ዛሬ የማን ፖለቲከኛ ሆኜ ነው የቀበጣጠርኩት ጎበዝ ??????? እኔስ ለመሆኑ የማን መስካሪ ነኝ ???? የመርኬ ቤታችን ከፖለቲካ የፀዳ እንዲሆን በሚቀጥለው ፅሁፌ በሰፈር ትዝታዎቻችን ላይ በማተኮር እመለሳለሁ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 17, 18, 19, 20, 21  Next
Page 18 of 21

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia