WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home | About us | Advertise with us | Contact us
__________///__________
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
አቡቲ

ኮትኳች

Joined: 09 Mar 2005
Posts: 113
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu Feb 28, 2008 5:58 pm    Post subject: Reply with quote

...ነጥብ ይኑርህ ወይም ነጥብ አብጅ እንጂ እንዲያው ተነስተህ ከዚህ እዚያ አትበል (አትቀዥብር ) ቢለኝ ደርሶ ...ያው በውስጤ ካለው የሀሳብ ነዶ አንዱን መዘዝ አድርጌ ለፍሬ ባላበቃውም ለወዳጄ ፍላጎት መሳካት አዎን ...ለእርሱ የሚስማማ ነጥብ ለማበጀት በሐሳቤ ምሕዋር ዙሪያ ስዞር ቆይቼ ሙሻዙሬ ዞሮ ግና የሐሳቤ እስከ እንዲሁም ለማያበቃ ጊዜ እንዲሁ ስነዳ ስኳትን ነጥብን ፍለጋ መቆየቴ ሳይሆን በአንፃሩ ያለፍላጎቱ ያለፍቃዱ ሐሳቤን በሁለት ብሎም አራት ነቁጥ ከፍፃሜ ማድረሴ ነበር ...

Smile
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋኖስ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Nov 2004
Posts: 1571
Location: Mars

PostPosted: Thu Feb 28, 2008 6:28 pm    Post subject: አዎ Reply with quote

[quote="አቡቲ "]...ነጥብ ይኑርህ ወይም ነጥብ አብጅ እንጂ እንዲያው ተነስተህ ከዚህ እዚያ አትበል (አትቀዥብር ) ቢለኝ ደርሶ ...ያው በውስጤ ካለው የሀሳብ ነዶ አንዱን መዘዝ አድርጌ ለፍሬ ባላበቃውም ለወዳጄ ፍላጎት መሳካት አዎን ...ለእርሱ የሚስማማ ነጥብ ለማበጀት በሐሳቤ ምሕዋር ዙሪያ ስዞር ቆይቼ ሙሻዙሬ ዞሮ ግና የሐሳቤ እስከ እንዲሁም ለማያበቃ ጊዜ እንዲሁ ስነዳ ስኳትን ነጥብን ፍለጋ መቆየቴ ሳይሆን በአንፃሩ ያለፍላጎቱ ያለፍቃዱ ሐሳቤን በሁለት ብሎም አራት ነቁጥ ከፍፃሜ ማድረሴ ነበር ...

የሀሳብ ነዶ ! አሉ ! ህምምም ...ግና "ነዶ " ካነሱ ዘንድ ለነዶዉም ማሰሪያ ከሌለው በነፋስ ኃይል ከነዶነት ወደ መላ -ቅጥ ወደጠፋዉ ዝብርቅርቅ ሰርዶ ዉስጥ እንደሚቀላቀል አዉቀዉ ለነዶዉ ማሰሪያ በራሱ ይጠቀሙ ዘንድ አነቁጠዉት ይለፉ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
አቡቲ

ኮትኳች

Joined: 09 Mar 2005
Posts: 113
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu Feb 28, 2008 6:55 pm    Post subject: Reply with quote

...አንዳንድ ጊዜ የነቁጥ የሥራ ድርሻ እስከማይታወቅ ድረስ ነዶዎቹን ሰብሰብ አድርጎ ያሰሩበት ውሉ ይጠፋና ...ታዲያ ፍፃሜ ማኅለቅት እንደሌለው የክረምት ወጀብ ወዲያ ወዲህ የሚያማታ አንዳች እንደ ክረምት -አግቢ የሚፈላ የዕወቁልኝ ጥሪ ያደርግ ይመስል ደርሶ ላይ በላዩ ተነባብሮ የቱን ይዘው የቱን እንዳይተውት ምርጫ ነስቶ አንዱን ጥሎ አንዱን አንጠልጥሎ ጉዞ ማነኝ እኔ ተብዬው ንክች የሚያደርጋት ....እኅ
እህ ...ስጀምረው ያለፈቃዴ ያኔ እንደምፈልገው ጀምሬ እንደማልወደው ስነዳ ...

ይለጥቃል ..

Smile
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Thu Feb 28, 2008 10:55 pm    Post subject: Reply with quote

የኔታ ከዚች የወናበደች ደጄ ባገኝህ ምናቤ ፈገግ አለ ልበል ? ዳሩ በድቅድቁ ቅብጣሬያችን ቅፅበት ምናብ ያንተ ንብረት አይደለም ብለህ ሹክ ስተልኝ ነበር ልበል ...እስቲ ይበሉ ከጀማው ይሠየሙና ነጥብም ካሻዎም ተነስተው ሚመለሡበት የግስጋሴ መንደርደር ... ብቻ ውስጥዎ ይበሉ ያልዎትን የብሉ ::

ነገርን ስፅፍ ከሣድስ ጥግ እቺን የተውሦ ' አፖስትሮፊ መጠቀሜ ቋንቋ ያድጋል ሢሉ ሠምቼ ለማሳደግ ፈልጌ ብቻ ሳይሆን አለ አይደል ሠዉ ሲያነብልኝ ምላሡ ስር 'ሚያላውሳትን ቃል ምን ስል ኪሣራ አስገብቶ አስፃፈኝ ብዬ ' ነው :: ''ወጪ ያዘዘባት ጥቁር ሤት አንገቷን ትነቀሣለች '' ብለው እንዳይተርቡኝ <== ውስጠ ምናቦቼ
በተረፈ አቡቲ አሁን አሁን ተሻሽዬ አግኝተህኝ 'ንጂ ለፊደል ግድፈትማ ቁጥር አንድ ነበርኩ ''ኮልታፋዋ ደራሲ '' ብለው ተቀፅላ ስም እነመሪጌታ አውጥትዉልኝም አልነበር : እስቲ እየመጣህ ጥቆማህን ስጠኝ ግሳፄህንም አቀብለኝ : ከዋርካዊያን ተደራሲናን አንባቢያን ጋር ሳልተባበር የፃፍኳቸው ጽሆፎች በጣም ጥቂት ናቸውና ::

እቺ ቤት ግብሯ ጥራዝ የነጠቀ ... የቋንቋ ክህሎት ያልጠበቀ ነውና አርጩሜ ይዞ በህገ -ቃላት ሚገዝት ስለሌለ እንደማትፈልገው መነዳትህን ውበት አድርጌ ነው ምወስደው

ምናቦች ይርቡልህ ብያለው ::

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::

Last edited by ዋናው on Wed Sep 22, 2010 1:42 am; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Sat Mar 08, 2008 1:58 am    Post subject: Reply with quote

ዘኪዮስን ሆኜ እየመጣው ራሴን ምጠይቀዉን ቀልቤን የቦከመኝ ማነው ግን ....?

ያክሺማሽ

ዛሬ ምንኛ በስማም ተብሎ ሚማተብበት ሕሣቤ ውስጤ ተላወሠ ደግሞ ... ዳሩ ሃሣብን ለምን ያንን ሀሠብክ ብሎ በሃሣብ መክሰስ አይቻልም አይደል ...የተቻለም ቀን ''ሠው ራሡን ሢፃረር '' ተብሎ ሣይንሥኛ ትንቅንቅ ውስጥ ገብተን ወደ አንደኛ ደረጃ የእብደት ጅማሬ ልንገባ እንዳይሆን ብዬ ተውኩት ...

አሁን አሁን ሆሊዉድን ያጥለቀለቁት የሣይንሣዊ ልቦለድ አስፈሪ ፊልሞችን ሳስተዉል የፊልሞቹ መነሻ ሃሣቦችን ልጅ ሆኜ አስቢያቸው ማውቃቸው እንደሆኑ መሠለኝ ልበል ...? በቀደም ከናቲ ጋር መፃፍ ኖረባቸው ስላልተፃፉ የሕፃናት መፀሐፍት ለከነገወዲያ ቀጠሮዎቼ አጀንዳ ውስጥ የዘበትም ይሁን የአልቀረብሕም ዓይነት መዘገብኳቸዉም :: ብዙዎቹ ተረቶቹ እንጂ ተረቶቹን ማን እንደነገረኝ አላስታውሣቸዉም

አራት ዓይኖች ያሉት ጭራቅ

ለረጅም ጊዜ ውስጤ ምስሎ በደማቁ ተስሎ እስከጉርምስናዬ የሸኘኝ ነገር ነው :: ሳስበው በቃ ሚጥሚጣ ይዞ ሚዞር ይመስለኛል .... ቀን ቀን ሻሽ እና ኮፍያ ያደርጋል ከውኃላው ያሉት ሁለቱ ዓይኖች እንዳይታዩበት ነው አሉ .... ከቀበቶው ስር ቢላ አይጠፋም ሠው ይይዝና መብላት ሚጀምረው ከቂጥ ነው ጭራቅ ለምን የቂጥ ሥጋ እንደሚጣፍጠው ትልቅ ሆኜ ለአቅመ -ቂጥ ማድነቅ ሁሉ ደርሼ ይገርመኝ ነበር ... ታዲያ አንድ ቦታ ብቻዬን በማታ ስላክ ሁሌም ዞር እያልኩኝ ይህንን ጭራቅ እፈልገዋለሁ ድንገት ደርሶ ቂጤን ሚቦጭቅብኝ እየመሠለኝ ... ፀጕሩ ሉጫ ሆኖ ብትንትን ያለ ነው የፈረንጅ ድብልብል አገጭ አለው የውኃላ ዓይኖቹ ከፊተኛው የተለዩ ናቸው በማታ እንደድመት ዓይኖች ያበራሉ :: ከቢላው ጋር ቀበቶው ውስጥ ቀን ቀን ሚደብቀው ጭራው እንደቀትር እባብ ሚያደርገዉን ነው ሚያሳጣው ... ይሄ ጭራቅ የጊቢያችን በር ጋር ካለው ትልቅ ዛፍ ስር ሆኖ ከሁሉም እኔን ብቻ ሚጠብቀኝ ይመስለኛል ... ወጣ ብዬ ሣየው የቆመ ይመስለኛል ጉልበቶቹ ቆልመም ብለው ቁጭ ብድግ ሊሠራ እንደተዘጋጀ ሠው ሆነዋሉ ያፈጥብኛል እኔ ላይ ብቻ .... መፍራቴን ሲያይ ይስቃል ጥርሦቹ እንደአጥንት ስንጣሪ ሾለው በደም የተነካኩ ይመስለኛል ... ምናልባት አንድ ሁለት ሠው በሚጥሚጣ እያጠቀሠ ሠልቅጦ መጥቶ ይሆን ....? ፍራቻዬን ለትርታዬ እየነገርኩኝ ትርታዬም እያቃሠተ ...ድጋሚ በሩን ገርበብ ሳደርግ የዛፎቹ ቅጠል ሁሉ እንደሱ ጭራቅ ሆነው አያቸዋለሁ :: ከዛፎቹ ቅጠሎች አንደናው ሚስቅብኝ ይመስለኛል ፈርቼ እገባና ወደመኝታዬ ስሄድ ደግሞ እጅም እግርም የሌለው ሠው ሚበላው ሠውዬ እየተነከባለለ ሚመጣ ይመስለኛል ... እግርና እጅ ከማጣቱ በፊት የነበረችዉን ቆንጆ ሚስቱን አሉ ስለከዳቸው ቆጥ ላይ ተደብቃ ስታለቅስ እንባዋ ፊቱ ላይ ጠብ ይላል ቀምሶት የድሮ ሚስቱ እንባ መሆኑን አውቆ እየተደበለበለ ቆጥ ላይ ይወጣትና ብላት : ቅርጥፍ አድርጎ :: ታዲያ ይሄ ድብልብል ሠውዬ እኔንም እራቱ ሊያደርገኝ ወደኔ ሚመጣ ይመስለኛል .... ወደውጪ ስወጣ ጭራቁ ወደውኃላም ወደኔም እያፈጠጠ ጭራዉን እያወናጨፈ ጥርሡን እያፋጨ ያየኛል : ወደሕልሞቼ እንዳልገባ ያኔ ሕልሞች አልነበሩኝም ::

ታዲያ ዛሬ እነኚያን ምስሎች ሳስባቸው መልካቸው ቁልጭ ብሎ ይታየኛል ሠፊ መሬት ላይ የተከሉት ተክል ለዘላለሙም ይኖራል እንዲሉ .... ያኔ እነኚያን ምስል ሚያጣብብ ውስጤ ምንም አልነበረም ....
ሌላው ሠው ሲሞት እሬሳ ለመመርመር አባዲና ይመጣሉ ሲባል እኚህን አባዲና እንዴት እፈራቸው እንደነበር ከሬሣዎች ጋር ጥልቅ ግኑኝነት ያላቸው ነፍሠ -በላ ይመስሉኝ ነበር አጭር ሆነው መላጣ ዓይኖቻቸው ድፍርስ ... የእጅ ጣቶቻቸው አንጓ እንደዝንጅብል ዱልዱም ያለ መዳፋቸው አሕያ በጥፊ ሚያንፈራፍር ዓይነት .... ሠው ሠፈራችን ሞቶ አባዲና ይመጣሉ ሲባል እኚህ ሠውዬ እግረመንገዳቸዉን እኔን ሚያስጠሩኝና ከሬሶቹ ጋር ሚመረምሩኝ እየመሠለኝ በጣም ነበር ምፈራቸው : ልክ እንደ ባለአራት ዓይኑ ጭራቅ ልክ እንደዛ ሚስቱን ቆጥ ላይ ወጥቶ እንደበላው ድብልብል ነፍሠበላ ....
ዛሬ ዛሬ ምናልባት ፊልሞች ማያስፈሩኝ በነኚህ የጨቅላ ፊልሞቼ ተገርቼ ይሆን እንዴ ? እላለው ግን ' እነኚያ አፈ -ተረቶች ውስጤ ገብተው ራሣቸው ግድግዳ ላይ ሊለጠፉ አንድ ምክኒያት አላቸው : ውስጠቴ => ካየው ውጪ በምናብ ሚቀርፀዉን ምስል በራሱ እየቀያየረና ሥሜቶቼን እያዳመጠ ያኖረዋል : ማን ያውቃል እነኚህ ሁሉ በራሣቸው ጊዜ ለመጨበጥም ላለመጨበጥም ተረግዘው የተወለዱት ገጾች ምናልባት ከጣምራ ሕይወት ስንቃሬ ወይም ከስጋ ነፍስ ትንግርታት ስር ዳግም ይከሠቱ ይሆናል : ጊዜ በራሱ ሙሐር ሢሽከረከር ሚደግማቸው ነገሮች ይኖራሉ ፎሪ ሚጠለዙም ይኖራሉ የፎሪዉና የድግምጋሞሹ ሥብጣሬ በአወሊያዎቼ ወይም ባንዳች ክስተት ተጋጭተው አይ ይሆናል :: አይቼ ብመሰክርም ''በጨ '' ሚባል ሹመት ባገኝበትም ወይም በጭጬ ትዕንቢቴን ባደንቅበትም ::

ዛሬ ባለ አራት ዓይኑ ጭራቅ ቢላዉን አያፏጭብኝም ምክኒያቱም በገዐዱ ዓለም የቆነጁ ጭራቆች ስር እንደምኖር ያውቃልና ....

እስቲ ከቻልኩኝ የካርሎስን መላምት ላንቀርቅብና ያንን ጭራቅ ያንን ድብልብል ሠውበላ ... በሕልሜ ልፍራቸው በቅዠት ሥጋዬን አክብጄ እስትንፋሤን ላንሣፍባቸው ከቻልኩኝ ነው ግን ....

በቃ ሄድኩኝ ::

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Sun Mar 23, 2008 5:30 pm    Post subject: Reply with quote

ሣውቦና አልኩኝ (በዙሉኛ )

የሁለት ዓያላን ቀለማት መቃረን ያለነጭ አስታራቂነት ሚፈጥረው ቀለም ብረሐንን ሚያስኮርፍ ገፅታ አለው : ለምሳሌ የወይንጠጅና የቢጫ ወይም ያረንጓዴና የቀይ ... ፍልሚያ ... ታዲያ እነኚያ ቡዝዝ ያሉ ቀለማት ዛሬ ጠዋቱን ጀምሮ በሚተነፍሠው ቀዝቃዛ ነፋስ ታጅቦ ቢታየኝ ያገሬን ክረምት አስታወስኩኝ : በዛች ብሽክሊሊት የውኃሊዮሽ ልፈረጥጥም አይደል : ሄድኩኝ እንግዴ በልግን ,በጋን እና ፀደይን ሦምስሜ ክረምቱ ላይ ገጭ አልኩኝ ልክ አደራዉን እንደተወጣ ፈረስ እያጓራች ብሽክሊሊቴ .... ይሄንን ያስወሳኝ አንድም የማታው የልጅነት ጭውውታችን ከጆሮዬና ቢራ ካነቃው ስሜቴ ስር መለጠፉ አልፎ ዛሬን አብሮኝ ቢያድር ላልጨብጠው እጄን ሚያዘረጋኝ አንዳች የለጋ ዕድመዎቼን መናፈቅም ሆነና ነው .....
የጭቃ ብይ ሠርተን በእርሳስ አቅልመነው በፀሐይ ክርር አድገን አድርቀነው ሦስት ጉድጓድ ቆፋፍረን ጉልበታችን እስኪሻክር የመዳፋችን ጀርባ አንጓዎች እስኪጠነክሩ በእጅ ፎቅ እየሠራን በአራት ጣቶቻችን እየቆጠርን ...በአውራ ጣቶቻችን በመፈንቀል ምንጨዋወታቸው ጨዋታዎች ትዝ አሉኝ :: ታዲያ ' የጭቃ ብዬ መበላላታችንን የነዉር ተደርጎ ቁማር ነው ተብለን ምንሞዠለቅበት ጊዜ ሁሉ ነበር እነኚህን ነው ኦርጋኒክ ቶይ ብለን ምንጠራቸው ዛሬ : ክረምት ላይ ሁሉም ነገር ደስ ይል ነበር : የሠፈር የዝናብ ውኃዎችን ትንንሽ ንሑስ ጎርፎች በአፈር ደልድለን ምንሠራው ግድብ ልክ አባይን እንደገደብን ዓይነት ነበር ሚሠማን ደስታ ምናለበት አሁን እንደመጠናችን ጥረታችንም አድጎ አባይን መገደብ በቻልን ::
አንዳንዴ ልጅነት ጊዚያን ውስጥ ምናያቸው ግዑዝ ነገሮች ሁሉ በዛን ጊዜ በጣም ትልቅ ነገሮች ይመስሉን ነበር ታዲያ ከረጅም ጊዜ ትልቅ ሆነን እነዚያን ነገሮች ሁሉ ስናያቸው ትንንሽ የመሆናቸው ነገር በጣም ይጎላብኛል እይታ ራሡ መጠናዊ እድገቱ አለው :: ከሁሉም ደስ ሚለኝ የክረምት ኃይለኛ ዶፍ ዝናብ ጣሪያን ሲያስጮህ የነበረው ስሜት ነው በጣም ደስ ይላል :: ቤት ውስጥ የከሠል ፍም ሙቀት ፈጥሮ ! ! እያለ ሚጮኸው በቆሎ እሸት የከሠሉን አመድ እያቦነነ ከመብረቁ ጋር ሲፎካከር .... ድንገት በዝናቡ በስብሶ የውጪውን በር ሲያንኳኳ ሚሠማው አጥትቶ የተናደደ አንዱ ወንድማችን ሲገባ ምንስቅበት ሳቅ .... ታዲያ እነኚህ የክረምት ውበቶች ዛሬ ሩቡ እንኳን ለምን እንደሌለ ይገርመኛል ::
እዚህ የዛፍ ቅጠል ሚያራቁት ውርጭ እንደእሣት ሚለበልብ ብርድ አለ ለዛዉም ሁለት ወር ብቻ አይደለም ፀሐይቱ እስክትናፍቀን ድረስ : አንዳንዴ ቤቴ ስገባ ከላዬ ላይ እየገፈፍኩኝ ማወልቀው ለልብስ ክምርን እያየው ያንን ሁሉ ተሸክሜ መሄዴ የእርግማን ሁሉ ይመስለኛል :: እነኚህ ያኮረፉ ቅጽበታት ናቸው ለኮንትራስት ፍለጋ እነኚያን የቆነጁ ጊዚያት ሚያስወሡኝ :
እስቲ ቢያንስ ዓይኔን ሚሞላ የፀሐይ ብረሐን እንዲበረክትልኝ 'ንኳን ልመኝ ዝናቡ ከፈለገ ይዝነብ ባይሆን እንደልጅነታችን ጅብ ወለደ እላለሁ ከዛም አውራ ጣቴን እቀስራለሁ የጅብ ክርስትና እዳላነሣ <== የልጅነት አወለያ ነው ይሄ እንግዲህ እስቲ ልመለሠው ደግሞ መጣው እግሬ ፔዳሎቹ ላይ እየተፈራገጡ ነው

ይህንን ላስወሳኝ በደርሶ መልስ ውስጠ ፍካት ላስፈገገኝ ካምሣሚዳ ልበልና ላብቃ ?

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::

Last edited by ዋናው on Tue Sep 14, 2010 12:03 am; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Tue Apr 08, 2008 1:01 am    Post subject: Reply with quote

እኔና ዝባዝንኬዬ ሠሞናቱን በዚች ሜታሊክ የግል .... የራሴ ብቻ .... ክፍል ውስጥ እንዘባዘባለን እና የሚሚ ኮበሌ ፀበሉን ካመጣ ለመረጨቱ እጣው እንዲደርሠን ተፊት እናፍጥ ቆለጨ ሆነን <== ነን '::

ኃሙስ ለመምጣት መንደርደሬ ነው ::

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Tue May 27, 2008 12:20 am    Post subject: Reply with quote

ሳሉቴ .....

ዘለላዋን የቅዳሜ ሠንበት እዛች ያዋቂ ወግ ምናወራባት ፓልቶክ ውስጥ ድቅድቁ ሌሊት ከረፈደ በኌላ ውስጣችን ብቅል ሚሻበትን ምስጢር መጎልጎል አምሮን ስለስካር ብናወራ ወጋችን እየተንሻፈፈ ምልከታችን እንደሁሌም እየተንቦረቀቀ ስንቱን ትዝታቶች ተለዋወጥን እውነትም ያዋቂ ወግ ኤጭ ::
ታዲያ ዛሬን በዛ ጠፈጠፍ ውስጥ ሆኜ ባላባራ ስሜት በብሽክሊሊትኛዬ ሳስገመግም ባንድ ወቅት ካንድ አንጋፋ የበቃ የጥበብ ሠው የሠማዉት ትዝ አለኝ :: የጥበብ ሠው የራሱ ገዳም ያስፈልገዋል ያለን ... እቺን ቅኔያዊ ምክር ለመተግበር ሁሉም ወደውስጡ ገብቶ ያልማሰው ያላሠሠው ነገር አልነበረም ... ዓይኖቻችን ብረሐናትና ቀለማት ተሸልመው ውስጠ እይታችን ግን የግል የራሳችን የማንነታችን ይሆን ዘንዳ እንደ መዳፍ አሻራ ዕኔያዊ ጥበብ ለማተም የግስጋሴው መንደርደርን .... ገዳም ተብሎ የተሠበከነው ነገር እዚጋ ደማቅ ድርሻ ነበረው በርግጥም ነበረው ::
አህምሮን ከወትሮው ለማንቃት የራስ ገዳም ያስፈልግም ነበር .... መደዴ ወይም የዕለት ተዕለት ኑባሬን ችክ ላለማለት ያልታዩ ጥቃቅን ዕይታዎችን ለማየት ... አንዳች የተጋረደን ሚገልጥ የራስ ገዳም ያስፈልጋል ....::

ሢያልፍ ሁሉም የሕይወት ዱካዎች ይሆናሉ ውኃ አቁረው የጎደጎዱ ዱካዎችና ..... እንዲያው በቀላሉ የታተሙ የሕይወት ዱካዎች ... ግን እነኚያ ዱካዎች ሁሉ ለዛሬ አንዳች ድርሻዎች አላቸው :: በነበረበት ቅጽበት ያለምክኒያታዊ የሆነ አንዳችም ነገር አልነበረም ::

ዛሬ ብቅል ሥጋን ለማሞቅ ይጠቅማል .... አኩራፊዉን ዕይታ የማስፈገግ ኃይል 'ንኳን ባይኖረው ..... ለአንዳች ክስተትም መለኪያን ለማጋጨት ይጠቅማል እንደ ክብ ጠረጴዛም ሠዎችን ይሠበስባል ::

እስቲ እኔም ቺርስ ልበልና እጀ -መንገዴን ብቅ ያልኩበትን መንደር ልቀላቀል ::
_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::

Last edited by ዋናው on Tue Sep 14, 2010 12:09 am; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Sat Jul 12, 2008 12:46 am    Post subject: Reply with quote

ደረን ደረን
እንል ነበር ዱሮ ሸፍተን ስንመጣ ..... የዋርካ ልደቴን ቆጥሬ ከስሯ ምጠፋበትን ጊዜያት መልሼ ስቃኝ ነበር የመፈረጠጥ እና ያለ መድረስ ልዩነቶችን በመሀል እየሠነቃቀርኩኝ .... በእርግጥም ይናፈቃል እጅግ ይናፈቃል ውስጣችን ተግባብቶና ተዋውቆ ዓመታትን ጠፋህ ጠፍሽ ተባብለን ስንጠያየቅ ቋንቋ በራሱ አዚም በቤተሠባዊነት ስሜት እንዳስተሳሰረን አስባለሁ ::
አንዳንዴ ዋርካዊያን ሁሉ ሕልሞቼ ሆነው የተቸሩኝ ያህል ደፋር ሃሳብ ይዳዳኛል ወይም እኔ እራሴ ዋርካዊያን /ያት ውስጥ የበቀልኩኝ ትንሽዬ ድንክ ሕልም የሆንኩኝ ይመስለኛል ምክኒያቱም ሁላችንም ሃሣብ ነን ትላንትናን ኖረን ዛሬን ያስበን ምናልባት ነገን መከሠት ማንችል ነን :: ታዲያ አንዳንዴ በእንደዚህ ሕሣቦቼ ጣልቃ በጣቶች ቀብቅበን በምንግባባው እኛነታችን ውስጥ ፍቅርን ስናጣ ግድንግድ ጅሎች የሆንን ዓይነት ይሠማኛል በእርግጥም ጅሎች ነን ::
ይህንን ሁሉ የዘበዘብኩት በናፍቆቴ ግርጌ የመናፈቄን 'ማያጨበጥ ነገር እየፈገግኩኝ ሳስበው ነው በእርግጥ የዋርካ መስኮት እጅ አሾልካ ያጨባበጠችን ስለመኖሯ ከራሴም ገጠመኝ ጨምሬ እመሰክራለሁ :: ዘመን የወለደው የመረጃ መረብ የመሠይጠን ሹመት ቢሠጠዉም ሠይጥነን እንቀበለዋለን ::
በወግ ጣልቃ ገዐዱ ዓለም ውስጥ ማገኛቸውን ሠዎች ስለዋርካዊያን እና ስለዋርክነት ሳወጋቸው አንዳንዴ እንደእብድ ሁሉ ይገላምጡኛል ሕልም ዓለም ውስጥ ምዋዥቅም ይመስላቸዋል :: በፊደል ወይም በቡርሽ የፈጠርኩት ዓልምን ምስብካቸው ይመስላቸዋል ልክ እኔም ሎግ አውት አድርጌ ስነሣ እንደሚሠማኝ

እናም እናንተ ትልቅ ሕልሞቼ ናችሁ :: ሕልም ደግሞ እውዳለሁ እቺ ዓለም ብቻዋን ስለምትፈዝ ሕልም ያስፈልጋታል ከሞት በኋላ ካለው ተላላ ሕልም ውጪ

እስቲ ሚጢጢ ሕልሜን የዛለ ስጋዬ ሚያባብለው እንቅልፌ ውስጥ ልፈልገው ::

ቸር ቆዩልኝ

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Tue Sep 16, 2008 3:26 am    Post subject: Reply with quote

እቺን ሀርድ ሮክ ጓዳዬ የት ሠፈር ወስደዋት በስንት ድብድብ እዚህ አመጣዋት ምን ያህል እንደመውዳት ' የግሌ ስለሆነች ምን ፃፍክ ለምን ፃፍክ ስለማልባልባት :

ቆይ መጣው

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Mon Sep 22, 2008 4:04 am    Post subject: Reply with quote

ሻሎም ብያለው

አሁን ይህንን ስፅፍ ውጪው ጨለማ ነው : ግብግብ ያለ ጨለማ የጀምበርን ጊዜ ሳይቀር በስሱ ላፍ ሚያደርግ ጨለማ ምስጢራዊ ግዝፈት አለው ይባላል : ብዙ ጥቋቁር ነገሮች በምስጢር ይመሰላሉ ይሄ የቀለም ዓይነተኛ መላ ምት በየራሳችን ሲውጠነጠን ጦር እስከማማዘዝ ሚያደርስ ጭብጥ ይኖረው ይሆናል : ግን የሁላሁሉ መነሾዎች ኃሣብ ብቻ ነበሩ .... ከፍጥረታት በፊት ቃል ብቻ እንደነበሩ ሁሉ ::
ሌቱን ኪቦርድ ሚያስደነቁለኝ የጨለማ አባዜ ነው ? በእርግጥ አይደለም : ቀለማት በዓይኖቻችን ሠርፀው ለህዝለ -ሕሊናችን በል ሚሉት ስሜታት የመፀነሳቸው ምስጢር ሁሌም ስለሚገርመኝ ነው : ቅጠል አስቀጥፎ ቀለማትን የፈጠሩ ምን አዝዋቸው ነው ? አንድ ኃይል ይኖራል .... ከብረሀን ጋር የተዛመደ ምስጥሪር አላቸው ::
ነጭን የንፅሑ ተምሰሌት ጥቁርን የሰይጣን ያለው ማነው ? ያው መላ ምት ነው ቢጫና ጥቁርን ለአደጋ ማስጠንቀቅያ ሠማያዊን እና ነጭን ለማስገንዘቢያ ብሎ የጀመረውም ያው አንድ ለራሱ የታየው ኃሣብ ነው ::

ትላንትና ሌቱን ሙሉ ቀለም የበዛበት ሕልም አይሉት ቅዠት ብቻ ዓይኖቼ ብዥ እንዳሉብኝ ነጋ እነኚያ ቀለማት ከሕፃንነቴ ጀምሮ ውስጤ የነበሩ ናቸው አሁን እይታ በሚደበዝዝበት ስፍራ ሆኜ ውስጤ የገቡ ስለ አለመሆናቸው የመማል ያህል እርግጠኛ ነኝ : የዛሬው ገገማ ጨለማ ላይ እነኚያን የልጅነቴን ቀለሞች አምጥቼ የመርጨት አንዳች አስማት ቢኖረኝ ደስ ባለኝ ....ልክ ኤኒያ ፔንት ስታር ኦን ስካይ ብላ እንዳዜመችው ... ዳሩ የርሱዋስ ቢሆን ምኞት አይደል ልክ ድሮ ዳመና ጉማጅ ላይ ሆነን ጅራፍ መተኮስ እንደሚያምረን ዓይነት መሆኑ ' ነው

አሁን እዚህ ጨለማ ሌሊት ውስጥ ልዋጥ ልሄድ ነው ከቻልኩኝ በምናቤም ቢሆን ቀለም እያጠቀስኩኝ ላፈካው እሞክራለሁ ካልሆነ ግን ጀምበሯ ማልዳ በስልጣንዋ ታቀልመዋለች

ሄድኩ

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ብራንጎናትርን

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Dec 2006
Posts: 608

PostPosted: Mon Sep 22, 2008 5:43 am    Post subject: Reply with quote

ዋንሽ ... ስለ ህልም ስታነሳ ዋርካ ውስጥ ህልም ፈቺ ይኖር ይሆን ስል አሰብኩ :: Smile ለምን ? እኔም ትናትና ህልም ስላየሁ ወይንስ ቅዠት ? እርግጠኛ ነኝ ህልም ነው :: እንዴት እርግጠኛ ሆንኩ ? ይሄ ራሱን የቻለ ጥያቄ ስለሆነ አልፈዋለሁ :: Smile አሁን እኔ ማውራት የምፈልገው ራሱን ስላልቻለ ነገር ነው -- የትናንትናው ህልሜ :: እንዴት ህልም ራሱን አይችልም ? እንዴትስ ራሱን ይችላል ? ይሄስ አላስፈላጊ መቀባጠር ነው ::

ግን ዋርካ ላይ ህልም ፈቺ አለ ? ወይንስ ኢንተርፕሪቴሽን ኦፍ ድሪምስን ማንበብ ሊጠበቅብኝ ነው ? Twisted Evil ወይ አበሳ !

ህልሜ :-

እንደ ዋናው ከቀለሞች ጋር ሳይሆን ከቀጭኑ ሽቦ ከስልክ ጋር ይያያዛል :: ማን ነበር ስልኩ ላይ ? ለምን ተደወለ ? የማይመለሱ ጥያቄዎች ናቸው :: የኔ ጥያቄ ታዲያ :-

ሰው በስልክ ከሩቅ ሀገር ሲያናግር ምንን ያመላክታል ? በመኪና መጉዋዝ ሞት ነው ሲባል ሰምቻለሁ :: በሉ እንግዲህ ፈቺዎች ፈታ ፈታ አርጉልኝማ ::

አፌን በዳቦ አብሻለሁ :: ዋናው በሩን ዘግቶ ስላልተኛ እንደልቤ የሰው ቤት ገብቼ እቀበጣጥራለሁ ... አረ ከንቅልፍ እንዳልቀሰቅሰው ... አቤት ... እንዴት ያንኮራፋል ... በስማም ... Laughing
_________________
"The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Wed Sep 24, 2008 11:19 pm    Post subject: Reply with quote

ብራንጎናትርን� እንደጻፈ(ች)ው:
ዋናው በሩን ዘግቶ ስላልተኛ እንደልቤ የሰው ቤት ገብቼ እቀበጣጥራለሁ ... አረ ከንቅልፍ እንዳልቀሰቅሰው ... አቤት ... እንዴት ያንኮራፋል ... በስማም ... Laughing

ባላንኮራፋኮ ነው ሚገርመው ብራንጎ ሰው ኣገር አየተኛው ዳሩ ኣይመቸኝ ፤ቢመቸኝማ ሙት ሆኜ ነበር ምተኛው ሕልምህን ለፈቺ ኣስተላልፌዋለሁ ዋጋዉን ኣብሬ ከፍቺው ጋር አልክልህና ትከፍላለህ ሕልም ግን ' ራሱን ይችላል ይልቅስ የቀን መወላገዳችን አና የሥጋችን መዝልፈለፍ ነው ራሱን ያልቻለ ሕልምማ ቀመሯ ምስጢር የሆነች የነትጽፃነት ኣለም ናት በቀን ውዥንብርህ ውስጥ የተሳነህን የማከናወን ኣቅምህን ምታይባት ኣለም በዚች ኣለም ውስጥ ምታገኘው ሁሉ ልዩ ነው በተረፈ የሕልምን ካልኩሌሽን ፍለጋ የግድ የነካርሎስን መላምት ማገላበጥ ኣይኖርብህ ይሆናል ምክንያቱም ሕልምኛ አስከሆነ ድረስ ኣንተ የራስህ ቀመር ኣለህና።

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ብራንጎናትርን

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Dec 2006
Posts: 608

PostPosted: Wed Sep 24, 2008 11:42 pm    Post subject: Reply with quote

እንዴት ነው ህልም ራሱን የሚችለው ጃል ? Laughing ምንም ግልጥ አልሆንልህ አለኝ :: ራሱን እንዲችል መክሬ መክሬ አቃተኝና ነው ::

ይኸውልህ ትናንት እቺን ልጅ ቁርጥ በህልሜ አየሁልህ :: ዛሬ እንዳጋጣሚ የሳይበር ዐለም ውስጥ እንደ እብድ ስሯሯጥ የሆን ጥግ ላይ ፎቶዋ ተሰቅሎ አገኘሁት :: ህልሜ ራሱን ቢችል ኖሮ ይችን ልጅ እንዴት የሳይበር ዐለም ውስጥ ዳግም ላያት ቻልኩ ? Laughing ቆይ ፎቶዋን እታች እለጥፍና አንተም እያት :: የዛኛውን ህልሜን ትርጉም ባክህ ላክ አርገው :: ሰሞኑን ኪሴ ተቀዶብኛል :: Cool

አሁን ወደ ልጅቱ ፎቶ ...

_________________
"The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Thu Oct 02, 2008 9:57 pm    Post subject: Reply with quote

ብራንጎናትርን� እንደጻፈ(ች)ው:
እንዴት ነው ህልም ራሱን የሚችለው ጃል ? Laughing ምንም ግልጥ አልሆንልህ አለኝ :: ራሱን እንዲችል መክሬ መክሬ አቃተኝና ነው ::ብራንጎ ይሄ የአሁኑ የኔና ያንተ መደራገም ነው እንጂ የሕልምዓለም ' ራሱን ከመቻልም ራሱን ገሎ ዳግም የመነሳት አቅም አለው ::

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8  Next
Page 4 of 8

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia