WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home | About us | Advertise with us | Contact us
__________///__________
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ብራንጎናትርን

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Dec 2006
Posts: 608

PostPosted: Fri Oct 03, 2008 9:06 am    Post subject: Reply with quote

ኦኬ ዋርካን በኔ ኮመንቶች ሳላጥለቀልቅ የመጨረሻዋን ኮሜንቴን ለዋኒቾ ላስረክብና መጬ ልበል ...

ወይ አንተ መደራገም አልከው ??? Laughing

መደራገም ግን ምንድነው ?? Embarassed

ቆይ እስኪ ቆም ብለን እናስብና ...

ህልም የሚባል ነገር እውነት አለ ?

እውነታዊ ወይም ሪል የምንለው ህልም ሆኖ ህልም የምንለው ደግሞ እወነታዊ ቢሆንስ ?? Shocked ህልም ካለኮ በህልም ውስጥ ነው እየኖርን ያለነው ማለት ነው ??? Laughing በለው ድንቄም ተፈላሰፍኩት .... Mad
_________________
"The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Mon Nov 03, 2008 2:57 am    Post subject: Reply with quote

ሣሉቴ ... አልኩኝ ለመግባቴ

በቀደም ከሸራየ ጋር ሆኜ ዝም ብዬ ስቀድ ዋልኩኝ እሱ በብሩሽ ያጎረስኩት ቀለም ላይ ሙድ ይዞ ሲያገጥብኝ እነም ምናባ እያልኩኝ ስደግመው በቃ አለ አይደል እንደድሮ ጓደኞች ሆነን እያወራን የሆነ ሠኣት ላይ ቢራዬን ልጎነጭ አፍት ያህል ቆም ብዬ ሳየው ድብልቅ ያለ ፔንቲንግ ሆኗል ... እንዲህ እየተሳሳቅን በመላመድ ምሠራቸው ምስሎች ብዙም አይስቡኝም ነበር :: አለ አይደል ዝምብሎ የተለምደ ሕሳቦችን በቄንጥ ቀለምኛ ጥበቦች እየጎነጎኑ ቀባ ቀባ ሚደረጉ ...የቴክኒሻን ዓይነት ስራ ነው ሚመስሉኝ .... ዛሬ ዘኪን ሆኜ የመጣዉት ምናቦች ሲወለዱ የነዛ ውስጠ -ፅነሣቸው መንስሄ ምንድነው ብዬ ከራሴ ጋር ልጨቃጨቅም ነው አንዳንዴ አለ አይደል የሆነ ቦታ ዝምታ ...በራሱ ሲያፈጥ ጨዋታ ለማምጣት በመሳሣቅ ሚጀመረው ዓይነት የሐሳብ ፅንስ ሳይሆን ነርቮችን ቆንጥጠው ሕዋሳቶቹን ታክከው ብቅ ሚሉ ሕሳቤ -ፅነሣዎች አሉ አይደል .... የነዛስ መነሾነት ምንድነው ነው ? የስሜት ማዳመጥ አንድምታ ተርታ ናቸው ዓይነት ውስጤ ቢያቃጭልም እሺ ልለው ውስጤ እምቢ ይለኛል :: ወይም ነገርን ነገር ያነሠዋል ዓይነት .....

በዛች ብሽክሊሊት ልሦምሡምማ .....ወደዛኚያው ማዶ ካቻምናዎች .... አንድ ሌሊት ሠርቫይቪንግ ፒካሶን ያነበብኩበት ወቅት ነው .... እኔ ከሚስቴ አልተጣላሁም ልጆቼንም ተቆጥቼ አላማረርኩም 'ምክኒያቱም ምሽትም ልጆችም የሉኝምና .... ታዲያ ከሸራ ጋር ስፋጠጥ ሁለታችንም ተኳረፍን ሠኣታትም ነጎዱ .......ሌሊት ሲሆን ጫማዬን ተጫምቼ በእግሬ ወክ እያደረግኩኝ ወደፒያሳ አቀናው ካፊያው አዱገነትን ያበሳጫት ይመስል ነበር በዛ ብርቱካናም መብራት ጭልንጭል ያለው የምሽት ትዕይንት ምናብ የተራበው ውስጤን መገበው ሠንሻይን ባር ዲጄ ዳኒ የከፈተልኝን ሮክ ሙዚቃ ሠምቼ ውስጤን በጅን ካኮማተርኩት በኌላ ስወጣ ቁልቁለቱ ላይ አንዲት ጥቁር ውሻ አፏን ወደሠማይ ቀስራ ታላዝናለች አራስ ስለመሆኗ የጡቶቿ ግት መንጠልጠል ያስታውቅ ነበረ አንዲት ቡችላዋ በመኪና ተገጭታ ነበረ አጯጯዋ አንጀትን ይበላል ሢጋራዋና ይዛ በማዘን ምታያት የምሽት ሥሜት አዳኝ እንስት እንደኔው ልቧ እንደተነካ ያስታውቅ ነበረ ::
እናም ይህንን ሥዕል ውስጤ ጭርስ አድርጌው ቤቴ ገባው :: ለማግስቱ ዕንቅልፍ ካጠራቀምኩኝ በኌላ እኔና የተኳረፍነው ሸራ መተቃቀፋችን አይረሣኝም ....
ልምጣማ ወደዚህ ወደአሁኑ ዘኪዮስነቴ አሁን ዕይታ ጠኔ ነው ግና ሸራ ቀለም ልሶ ምስል ጎርሶ ያድራል እነኚህ የዛሬ ውልደተ -ምናቦች ፅንሣቸው ኬት ነው ? ነገ (በኔ ነገ ) ዋንቾን ሆኜ እመልሠው ይሆን ?

በነገና በዛሬ መዐል ምናለ ፈጣሪ ለእንግዳ ብሎ ያኖረው ትርፍ ጊዜ ቢኖር ....
ሄድኩኝ ::ብዬ ነበር ....

ይሄንን ጥያቄ ራሴን ከጠየቅኩት ዓመት ሊሞላኝ ምን ቀረኝ ጊዜው ተንቀዥቅዦ ነው ወይስ .....????

ተመሣሣይ ሕሣብ ሠሞናቱን ውስጤ ሲተራመሱ ነበር .... አሁን አሁን የሱስ ያህል አቅበጥብጦ ፊደል ለማስዘራት ብሕር ሚያስጨብጥ ...ተቅበዝብዞ ኪቦርድ ሚያስቀበቅብና ፓሌት አስደግኖ ብሩሽ ሚያሲዝ አባዜ ምንኛ ምክኒያት እንደሚያነሳሳቸው ሳስብ ጭውውውው ያለ ኦና ሆኖ እያስቸገረኝ መጥቷል :: በሽታ ሆኖ ጊንጎኛ ሚያጥመዘምዙኝን ለጊዜው ጎኔ ላስቀምጠዉና ወደ ዕለት ውጫዊና ውስጣዊ ዕይታዎቼ ልሂድ ...
ቀለማት በራሳቸው የማኩረፋቸው ምክኒያት የሆነው ሥሥታም ብረሐን ስሜትን ለመግለፅ ሚፀነስን ዕይታ ቁብ ሊሠጥ ቀርቶ የግዱ የሆነዉን ፍጡራንን የመምራት አላፊነቱን እንኳን የዘነጋ ይመስላል : ግን እዛ ውስጥ ሁላሁሉም በአንድ ክቡድ ዕይታ ተጀቡኖ በሚያስጠላ ስብጥር ዓይንን ሊወጋ ደርሶ ጊዜን ልክፍት ሆኖት ይታያል : ይሄ ውጪያዊ መሆኑ ነው
ውስጣዊው ደግሞ የነኚያ ዕይታዎች ነፀብራቅ በስሱ ተበርዞበታል .... ልብረር ሚለው ምናብ ከጥልቁ ሩቅ ትዝታዎች ላለመስጠም የመፍራትም እሾህ ሆነው ሚወጉት አዉኖችን በመሸሽም ሆኖ ያደባ ይመስላል :: ግን እሱም ሙሉ ነው : በሽታው በበሽታው ሙሉ ያደረገዉና ሆኖ የመገኘቱ ግዴታ እውን ያደረገው ዓይነት ::
በነኚህ ባልተመቹ ጣምራ ዕይታዎች መሀል በሽታዬ ባልኩት የማንነት ግዴታዬ ምስል አለያም ፊደል የማነፁ ምተዐት ግርም ይለኛል :: እናም ሁሉም ምናቦች የየራሳቸው ምክኒያት አሏቸው :: የራስ ተመክሮ .... የዕለት ዥንጉርጉር ማሕደር ..... የነገን መናፍቅና ሕልምን ማስተናገድ ማሕተብ ሆነው ዛሬን ዘክረው የማለፋቸው ጉዳይ መቀጠሉ ከምንም በላይ ደስ ይላል :: መደብዘዙም የውበት ነው ብሎ በቀና ማሰብ ይሻላል ...

ጭራሽኑ ቢጠፋስ .... ብላቹ እንዳታስፈራሩኝ እንጂ
ለራሴ መለስኩኝ ለበል ..... እስቲ ....? አዎ :: ራሴ አዎ ብሎኛል :

እስቲ የዛፍ ቅጠሎች መንትፎ ሚሮጠዉን የኦቶም ነፋስ አልጋዬ ውስጥ ሆኜ ላዳምጠው ::

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Sat Nov 08, 2008 2:14 am    Post subject: Reply with quote

ጥሎብኝ እቺን ቤቴን በጣም ነው ምወዳት እናም ሠላቢ ሲጎበኝብኝ ቤቷ አሳዘነችኝ
_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ሞዛርት

አዲስ

Joined: 08 Nov 2008
Posts: 39

PostPosted: Sat Nov 08, 2008 3:34 am    Post subject: Reply with quote

ዘቡልቄው ለምን ቅጥ ታጣላቹ ? ራሳቹ የከፈታቹት ላይ http://habeshabid.blogspot.com/ ሂዱና ተጫወቱ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Sun Nov 09, 2008 3:45 pm    Post subject: Reply with quote

ከላይ ለለጠፋችሁብኝ ገፀ -ነውር ምስጋናዬ ይድረሳቹ : ለጊዜው ማመስገን ብቻ ስላለብን ማለቴ ነው :

ግን ምን አድርጌ ይሆን ???
ደብዚቾ እስቲ መጥተሽ አበስኩህ ገበርኩህ በዪልኝ እኔ ደከመኝ

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዉቃው

ዋና ኮትኳች

Joined: 07 Jan 2007
Posts: 970

PostPosted: Mon Nov 10, 2008 8:52 pm    Post subject: Reply with quote

ይህች ብላንክ ዌብ -ወረቀት የአንጋፋው ቀባጣሪ ዞን ብትሆንም : ራሴን የነፈግኩትን ቅብጠራ ብጽፍ ማን ከልካይ
አለኝ አልኩና እቸከችከው ገባሁ :: በፊደላቱ ቀለምና አጣጣል አንጋፋው ቀባጣሪን ማስመሰል መቻሌ : ጥሩ አስመሳይ
እንደሚወጣኝም ከወዲሁ ገምቻለሁ :: ከበላይ የተንሰራፋውውብ ሸንተረር ቅብጠራዬን እየዘረጠጠ እንድሚያስቸግረኝ
አውቄያለሁና ኢንተር ኪይን ቶሎቶሎ መጫን እንዳለብኝ አልረሳሁም :: ስክሮል አደረኩና በድጋሚ ሸንተረሩን በተመስጦ አየሁት ::
ማን ይሆን ፎቶውን ያነሳው ?አላውቀውም ::
ግን የሆነ ስሜቱን የመሰጠ ነገር አግኝቶበታል :: ለኔም እንዲሁ :: ግን ደግሞ ህዝበ አዳምና ሄዋን ይህንን ፎቶ እስኪያቅለሸልሸው አይቶታል ::
ታዲያ ባለካፒራይቱ ፎቶግራፈር : አስደናቂ ብሎ ያነሳው ሸንተረር የተደጋገመና አሰልቺ ምስል
ሆኖ በአንድ የህብረተሰብ ክፍል ሊታወቅለት በቅቷል ::
ፎቶውን በድጋሚ ላለማየት ወሰንኩ :: አላስቻለኝም :: ፎቶውን እንደገና ማየት ጀመርኩ :: ለካ ካሜራዎች ተጃጅለው ያጃጅላሉና ::
ፎቶው ሳየው አሁንም ውብ ነው :: ግን ደግሞ ሰልችቶኛል ::ፎቶው እየኝ እየኝ ሲል :: እኔ ደግሞ በቃኸኝ በቃኸኝ እለዋለሁ :: አይገባውም አይገባኝም :: ብቻ መነታረክ !
ለውቡ ግን ለጠላሁት ፎቶ ...እሱንም ሆነ የሱን ዓይነት የተሰለቹ ፎቶዎች :
እሱንም ሆነ እሱን እንበልጣለን የሚሉ ሌሎች ተደጋጋሚ እና የተሰለቹ ፎቶዎች :
እሱንም ሆነ ከሱ አናንስምም አንበልጠምም የሚሉ ተራ ተወዳዳሪ ፎቶዎችን :
ላለማየት የመወሰን አቅሙ እንዳለኝ በትህትና አስረዳሁትና ተለያየን ::
አልገባውም :: በበነጋው ስመለስ እንደበፊቱ እየኝ እየኝ ይላል ::
የጫማ መስፊያ ወስፍዬን አነሳሁና አንድ ዓይኔን ወግቼ አፈሰስኩለት ::
ደግሞ በበነጋው ስመለስ እሱ አሁንም ባንድ ዓይህም ቢሆን እየኝ እየኝ ይላል ::
ባንድ ዓይኔ ውቡን ፎቶ አየሁት :: አሁንም ውብ ነው : ግን ደግሞ ሰልችቶኛል :: ትቸው ሄድኩ ::
አሁንም በበነጋው በድጋሚ ስመለስ አሁንም ፎቶው እየኝ እየኝ ይላል ::
ማስረዳትም መከራከርም አላስፈለገኝም :: ሳላመነታ ወስፌውን አንስቼ የቀረውን ዓይኔን
አፈሰስኩለት :: በበነጋው ተመለስኩ :: ፎቶው አሁንም እየኝ እየኝ
እንደሚል አንድ አንድ ዓይናቸውን ያፈሰሱቱ ነገሩኝ :: ጊዜ አላጠፋሁም
ዓይናቸውን ያፈሰሱበትን ወስፌ ተቀብዬ : የሁለቱንም ጆሮዎቼን ታንቡር በፍጥነት ቦረቀስኩት ::
መሸቶ ነጋ :: ሌሊቱን ግን ስለ ሰለቸሁት ፎቶ : ስለሰለቸኋቸው ተወዳዳሪና ጓደኛ ፎቶዎች : ማለሜ አልቀረም ::
በኋላ ላይከጣሪያ በላይ በረጅሙ መሳቅ ጀመርኩ :: ፎቶዎቹ መታየትን ሲፈልጉ :
እኔ ግን ህልም አድርጌያቸዋለሁ ::
ፎቶዎቹ ግን አሁንም ወደፊትም እነሱን የማይ ሰለነሱ የምሰማ ይመስላቸዋል ::
የሆነ ነገር ትዝ ብሎኝ ድንገት ከወንበሬ ተፈናጥሬ ተነሳሁ :: አሁን ዓይኖቼ አያዩም ጆሮዎቼም አይሰሙም ::
ፎቶውና ፎቶዎቹ ላይ የሆነ የጎደለ ነገር መኖሩ ውል አለኝ :: ለካ ፎቶውና ፎቶዎቹ :
ነፍስያ የሚባል ነገር ያልተፈጠረባቸው ግዑዛን ነበሩና ! ይህ ሁሉ ለግዑዛን !
ኤዲያ ! ዓኖቼ ጠፍተው : ጆሮየ ደንቁሮ : ይህንን ሁሉ ጊዜ አጥፍቼ ......

አዲዮስ
ዘኪዮስ !
_________________
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Debzi

ዋና አለቃ

Joined: 02 May 2004
Posts: 2790
Location: Los Angeles, CA

PostPosted: Mon Nov 10, 2008 11:03 pm    Post subject: Reply with quote

ዋናው እንደጻፈ(ች)ው:

ደብዚቾ እስቲ መጥተሽ አበስኩህ ገበርኩህ በዪልኝ እኔ ደከመኝ

አበስኩ ገበርኩ !

የውቃውን ስም አይቸ ነበር የገባሁት :: ከየት ጠፍቶ ብቅ አለ ?
ዘይገርም ላምባቶራ እሚል ሰው ነበር አንዴ ....ውነትም ዘይገርም ላምባቶራ !!
_________________
Ke akbrot selamta gar!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Thu Nov 13, 2008 3:09 am    Post subject: Reply with quote

ሣይበር ኢትዮጵያዎች ከልብ አመሰግናለሁ ..... ወይም ምስሎን የሰረዘው አካል

ከዋርካ ፍቅር እስከ ዋርካ ፖለቲካ ሚደርስ ግድንግድ ምስል ተለጥፎብኝ ትንፋሽ አጥሮኝ ነበር ::

በድጋሚ እግዚያብሔር ያክብራቹ

ከብዙ ብዙ ማክበር ጋር

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Thu Nov 13, 2008 4:08 am    Post subject: Reply with quote

ዉቃው እንደጻፈ(ች)ው:
ይህች ብላንክ ዌብ -ወረቀት የአንጋፋው ቀባጣሪ ዞን ብትሆንም : ራሴን የነፈግኩትን ቅብጠራ ብጽፍ ማን ከልካይ
አለኝ አልኩና እቸከችከው ገባሁ :: በፊደላቱ ቀለምና አጣጣል አንጋፋው ቀባጣሪን ማስመሰል መቻሌ : ጥሩ አስመሳይ
እንደሚወጣኝም ከወዲሁ ገምቻለሁ :: ከበላይ የተንሰራፋውውብ ሸንተረር ቅብጠራዬን እየዘረጠጠ እንድሚያስቸግረኝ
አውቄያለሁና ኢንተር ኪይን ቶሎቶሎ መጫን እንዳለብኝ አልረሳሁም :: ስክሮል አደረኩና በድጋሚ ሸንተረሩን በተመስጦ አየሁት ::
ማን ይሆን ፎቶውን ያነሳው ?አላውቀውም ::
ግን የሆነ ስሜቱን የመሰጠ ነገር አግኝቶበታል :: ለኔም እንዲሁ :: ግን ደግሞ ህዝበ አዳምና ሄዋን ይህንን ፎቶ እስኪያቅለሸልሸው አይቶታል ::
ታዲያ ባለካፒራይቱ ፎቶግራፈር : አስደናቂ ብሎ ያነሳው ሸንተረር የተደጋገመና አሰልቺ ምስል
ሆኖ በአንድ የህብረተሰብ ክፍል ሊታወቅለት በቅቷል ::
ፎቶውን በድጋሚ ላለማየት ወሰንኩ :: አላስቻለኝም :: ፎቶውን እንደገና ማየት ጀመርኩ :: ለካ ካሜራዎች ተጃጅለው ያጃጅላሉና ::
ፎቶው ሳየው አሁንም ውብ ነው :: ግን ደግሞ ሰልችቶኛል ::ፎቶው እየኝ እየኝ ሲል :: እኔ ደግሞ በቃኸኝ በቃኸኝ እለዋለሁ :: አይገባውም አይገባኝም :: ብቻ መነታረክ !
ለውቡ ግን ለጠላሁት ፎቶ ...እሱንም ሆነ የሱን ዓይነት የተሰለቹ ፎቶዎች :
እሱንም ሆነ እሱን እንበልጣለን የሚሉ ሌሎች ተደጋጋሚ እና የተሰለቹ ፎቶዎች :
እሱንም ሆነ ከሱ አናንስምም አንበልጠምም የሚሉ ተራ ተወዳዳሪ ፎቶዎችን :
ላለማየት የመወሰን አቅሙ እንዳለኝ በትህትና አስረዳሁትና ተለያየን ::
አልገባውም :: በበነጋው ስመለስ እንደበፊቱ እየኝ እየኝ ይላል ::
የጫማ መስፊያ ወስፍዬን አነሳሁና አንድ ዓይኔን ወግቼ አፈሰስኩለት ::
ደግሞ በበነጋው ስመለስ እሱ አሁንም ባንድ ዓይህም ቢሆን እየኝ እየኝ ይላል ::
ባንድ ዓይኔ ውቡን ፎቶ አየሁት :: አሁንም ውብ ነው : ግን ደግሞ ሰልችቶኛል :: ትቸው ሄድኩ ::
አሁንም በበነጋው በድጋሚ ስመለስ አሁንም ፎቶው እየኝ እየኝ ይላል ::
ማስረዳትም መከራከርም አላስፈለገኝም :: ሳላመነታ ወስፌውን አንስቼ የቀረውን ዓይኔን
አፈሰስኩለት :: በበነጋው ተመለስኩ :: ፎቶው አሁንም እየኝ እየኝ
እንደሚል አንድ አንድ ዓይናቸውን ያፈሰሱቱ ነገሩኝ :: ጊዜ አላጠፋሁም
ዓይናቸውን ያፈሰሱበትን ወስፌ ተቀብዬ : የሁለቱንም ጆሮዎቼን ታንቡር በፍጥነት ቦረቀስኩት ::
መሸቶ ነጋ :: ሌሊቱን ግን ስለ ሰለቸሁት ፎቶ : ስለሰለቸኋቸው ተወዳዳሪና ጓደኛ ፎቶዎች : ማለሜ አልቀረም ::
በኋላ ላይከጣሪያ በላይ በረጅሙ መሳቅ ጀመርኩ :: ፎቶዎቹ መታየትን ሲፈልጉ :
እኔ ግን ህልም አድርጌያቸዋለሁ ::
ፎቶዎቹ ግን አሁንም ወደፊትም እነሱን የማይ ሰለነሱ የምሰማ ይመስላቸዋል ::
የሆነ ነገር ትዝ ብሎኝ ድንገት ከወንበሬ ተፈናጥሬ ተነሳሁ :: አሁን ዓይኖቼ አያዩም ጆሮዎቼም አይሰሙም ::
ፎቶውና ፎቶዎቹ ላይ የሆነ የጎደለ ነገር መኖሩ ውል አለኝ :: ለካ ፎቶውና ፎቶዎቹ :
ነፍስያ የሚባል ነገር ያልተፈጠረባቸው ግዑዛን ነበሩና ! ይህ ሁሉ ለግዑዛን !
ኤዲያ ! ዓኖቼ ጠፍተው : ጆሮየ ደንቁሮ : ይህንን ሁሉ ጊዜ አጥፍቼ ......

አዲዮስ
ዘኪዮስ !
令人惊奇的

አንድ ነገር ደስ ሲለኝ ቻይንኛ ማውራት ያምረኛል .... ወንደርፉል ለማለት ነው :: ውቅሽ እኛን ያስተዋወቀን ይሄ ግዑዝ ነገር አይደል ?
እስቲ የመቀባጠር ሙዴ ሲመጣ እመለሳለው ይሄንን ነገር ቦርቀቅ ለማድረግ .... መቦርቀቅ ሲባል እነዛ መጥተው ደግሞ በስንት መከራ ያነሱልኝን የተንቦረቀቀ ተራራ እንዳይለጥፉብኝ ....በለፈለፉ .... ብላ ትተርት ነበር ሞኒካ ያኔ ቡና ቤት ከፍታ ብዙ ስታወራ .

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Mon Nov 24, 2008 5:39 pm    Post subject: Reply with quote

ኮኒቺዋ ብያለው በጃፓን አፍ

ዛሬ ብርዱ ልክ ዕዳ እንደሚያበስር ትኬት ጭምድድ አድርጎ ቢጥለኝ ሠውነቴን 'ማፍታታበት አንዳች ነገር ውስጤ ሲሻ ያቺ የናፈቀችኝ ብሽክሊሊቴን ካኖርኩባት አነሳው :: 'ላይዋላይ ያሉትን ድሮች ጠራርጌ ፔዷላን በጊንጎኛ ዘወርኳት የውኃሊት ፈረጠጥኩባት ... የትዝታኛ ሶመሰኦምኩባት ... አሌ ተብለውንም ፎሪ የተለጉትንም ጊዚያት ሳይቀር እያጮላለቅኩኝ በማይፈገገዉም እየገለፈጥኩኝ እርሌ ....
አሁን ሄጄ ገጭ ያልኩበትን ጊዜ ቅስፈቱ አላስታውሰዉም ቀን የመቁጠር የእድሜ ስስት እዚች መዘውሬ ውስጥ ድርሻዋ ከግርጌ ነውና .... እሣት ሚነድ ይመስለኛል አሆ አየሩ እየቀዘቀዘ እኔ ግን ሞቆኛል ስለዚህ እሣት እየነደደ ነበር : የያዝኩት መጠጥ ውስጤን አኮማትሮ ስሜቴን ሲኮረኩር አቅሙ በብርጭቆ ሊይዘው ምችል መሆኑ ገርሞኛል : ከጎኔ አንድ ጓደኛዬ አለ እሱም ሰክሯል : መስከር ፈልጎ ነው የሰከረው ደስ እያለው ነው የጠጣው ስለዚህ ስካሩ ቆንጅቶ ነበር :: እያወራን ነው ማውራት ... ማውራት ... ታዲያ ስለሚያገባን ነገር ብቻ ነው ምናወራው ውስጡ ቅዥ .... ቅዥ .... እያለ ሚያስቸግረዉን ምናብ በቀለም አስምጦ የተገላገለው ዛሬ ቀን ነው : አለ አይደል አራስ ልጁን ቤቱ አስቀምጦ ለእልልታ ጥዋዉን ሊያነሳ ነው የመጣው : ሲያወራኝ ስለመኖር ትርጉም ደጋግሞ ይነግረኝ ነበር :: መላ አካላትህን በራስህ የማንቀሳቀስ መብት ኖሮህ ... ምታስበዉን የማድረግ መብት ኖሮህ እንዴት አንተ ውስጥህ ያልፈቀደዉን ኑሮ ልትኖር ትሞክራለህ ...? ይለኛል እየኖሮ አይቶት ሳይሆን ታይቶት ...
ሥዕሎቹን ዛሬ ቀን ሳያቸው አሁን እሱ ውስጥ 'ማየዉን ስሜት ፍንትው አድርጎ አሳየኝ : ሽፍን ነገሮች ነበር ርዕሱ መኪኖች በነጫጭ ጨርቅ ተሸፍነው ቆነጃጅት እንስቶች ደግሞ እራቃናቸዉን ቆመው ... በእሱነቱ የመኖር ሕግ ውስጥ ያስፈራል .... ስለምን ብለን ግን 'ሚያስፈራንን ነገር እናስባለን ስለምን ብለን ምንሰጋበትን ነገር የፍራቻ እናስባለን ? ይሄ በርግጥ ጓደኛዬ ማንነት ውስጥ ሳስበው እንቆቅልሽ ነው :: ነገን በመልካም የመኖር መሻት ጉዳይ አይደለም ወይም አምኖ የመቀበል ጉዳይ ... ተንጠራርቶ ነገን የማየት መሻት ሊሆን ይችላል ...
''እየጠጣህ ''
እንባባላለን ስለሩል ኦፍ ዲስቶርሽን ያነሳነው ዘመናዊ ሥዕልኛ ወጋችን እየተንቦረቀቀ ግዑዙን ውላውሉ እየዘለለ ነፍስን መሸለም እያማረው የእሽክርክሮሽ እሙሽ ገለባ እያልን ወደውስጣችን ደግሞ እንሰጥማለን ... የስዕልኛው ዲስቶርሽንን እኛ ውስጥ ልንሞክረ እንደፍራለን ስእተቶቻችን ውበት የሆኑበትን ጊዜ ለምሳሌ እያስታወስን እንስቃለን : የመማሪያ ትክክልነታቸው ሳይሆን በራሳቸው አቅም ልክ የሆኑበትን 'ውነታ እንፈለፍላለን : ....
አሁን ያንን ቅስፈት ሳስበው ጓደኛዬ ውስጥ የነበረ የተቀበረ አንዳች ነገርን ቀድሜ የመመርመር አቅም ቢኖረኝና ከእሆነው ነገር በታገልኩት ... እሱ ዛሬ የአሁን ቅብጥርጥሬን የማስታወስ ወየም የመስማት አንዳችን ድርሻ የለዉም ምክኒያቱም ቡዝዝ ብሎ ይታየኝ የነበረው ማንነቶቹ በራሳቸው መግነጢሳዊ ኃይል ተሳስበው አንዳች ጉልህ ስሜት ሆነው ከዚች ምድር ሸኝተዉታል ወይም አብረዉት ተቀብረዋሉ : እራሱን እንዳጠፋ እርፈቱን ስሰማ ዳግም ከሱ ጋር ሚጣፍጥ ወሬ ማውራት ባለመቻሌ .... እና እስትንፋሱን በማቋረጡ ሀዘንኩ እንጂ ....ለምን ? ብዬ አልጠየቅኩም ::

አሁን እዛ ጊዜ ውስጥ በምናብ ሄጄ ብርጭቆዋችንን እያጋጨን ነው : ስለዚች ከንቱ ምድር እየሳቀ ይነግረኛል : ስለቀለማት እያወራን ነው ስለመስመሮች ክፋት እና ደግነት እያወራን ነው : ዛሬም ምናልባት ሚተራመሱ ወይም የሌሉ ጥቂት ሰዎች በስካር ቆንጅተው ከፊታችን ይወላከፋሉ : እነሱም ያወራሉ ደስ ስላላቸው ነገር ያወራሉ ግን ደግሞ ስለማያገባቸው ነገር ያወራሉ .... ይሄኔም እያወሩ ይሆናል ... ስለቪክቶሪያ ቤካም ክሳት እያወሩ ይሆናል .... ስለፓሪስ ሂልተን ሞልቃቃነት እያወሩ ይሆናል ... ባያገባቸእዉም ደስ ስለሚላቸው

እስቲ ልመለስ ደግሞ .... አቤት እዚ ግን እንዴት ይበርዳል ?
ብሽኪሌቴ ወደአንድ የረሳዉት ሠፈር ካልወሰድኩ እያለችኝ ነው : ታይም አውት ብያት ነው
አሁን ግን እንዲበርደኝ ፈልጊያለሁ : ዛሬን መሆን ግዴታ ስላለብኝ :

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Wed Dec 10, 2008 4:57 am    Post subject: Reply with quote

ከመይ ....... ብያለው
ቴሌቭዢን ያለማቋረጥ ያወራል ... ሰው ተገደለ ... ስፍራ ተቃጠለ ... ባንክ ከሠረ .... ባቡር ተገለበጠ ... ሕዝብ አመፀ .... ሕዝብ ተራበ ....ያወራል ያወራል ... ጉድ ጉዳንጉድ ... ከዛም ያሟርታል ... ይሄን ያህል በዚህ ጊዜው ውስጥ ኪሳራ ይደርሳል ... በዚህ ከቀጠለ በዚህ ዓመት ይሄን ያህል ሠው ይሞታል ... ይሄን ያህል ይራባል ...... ሟርት ቴሌቭዢን ጥቁር ምላሳ አለው በማግስቱ የአምናው ትንበያ ይነገራል ....
አንዳንዴ ስናስበው ኑሮዋችን ልክ እንደሰኞ ማክሠኞ የልጅነት ጨዋታ እንጣጥ እያልን መርጠን ምንረግጠው ዓይነት ይሆንብኛል
ቲቪዉን ዘጋውት ኢንተርኔት ከፈትኩኝ አገርኛ ዜና ፍለጋ በድረገፆች ላይ እንደኢሊኮፍተር መዞር ጀመርኩኝ ... የደቡብ ሕዝብ ይሄን ያህል ቁጥሩ ካልደረሱለት በረሐብ እንደሚያልቅ ... የሚያትት .... የቴዲ አፍሮ መታሰር ሕዝቡን ምንኛ እንዳስቆጣው ....
ቢቀርስ አልኩና -ትቦ ከፈትኩኝ አዲስ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ፈለግኩኝ አንዲት አሰልቺ ሜዳ ላይ በንፋስ ብቻዋን ሆና ''ባታስቸግረኝስ '' እያለች ታንቧርቃለች
ኤጭ ! አዲስ የኢትዮጵያ ቀልድ አልኩና ፈለግኩኝ አንድ ቁንጮ ሰውዬ ክራባት በከናቴራ አስሮ ሁለት ሚሪንዳ ይዞ ይሟዘዛል እጁን ሲያወናጭፍብኝ ''ሁለተኛ ኮሜዲ ብለህ ተፍልግና '' የሚለኝ መሰለኝ
ትቼው ቀን ከባቡር ላይ ያመጣዉትን ጋዜጣ ማንበብ ጀመርኩኝ አንድ የእንግሊዝ ትንሽ መንደር ውስጥ 4 ሠዎች ገሎ ስጋቸዉን ስለቆራረጠ ግፈኛ ሠው አነበብኩኝ ድጋሚ ሌላ ቴረር .... ጋዜጣዉን ወረወርኩት
ጃኬቴን ደራርቤ ድራፍት ቢጤ ለመጠጣት ልወጣ ስል ብርዱ በረዶ እየተፋ ገፍትሮ አስገባኝ ... ጫማና ጃከቴን አወላለቅኩና ቲቪዉን ድጋሚ ከፈትኩት ጆርዳን ጡቷን ለቀዳጆች ዘርግታ ቡቱቶ ስታስወትፍ ባሏ ፒተር ትኩር ብሎ ያያል ቀየርኩት ቻናሉን .... ሸዋንግዛው በሞተርሳይክል እሣት ውስጥ እየበረረ አንድ እንደ ብረት እየቀለጠ ሚረጋን ሠው ያባርራል ... ቀየርኩት .... አንዲት የውሻ አሰልጣኝ የባለቤቷን እግር ሚሰርረዉን ወሲባም ውሻ እየተቆጣች ነው .... ቀየርኩት .... ጎርደን ራምሲ የወጥ ቤቶቹ ሰራተኞች ላይ እየጮኸ ከአሣማ ስጋ ጋር ይታገላል .... ሌላ ቻናል ... አንዲት ዘረጦ ለመክሳት ፈልጋ ፍዳዋን ስታይ ጋዜጠኛው እያስለፈለፋት ነው .... አሁንም አዞርኩት ቻናሉን ... ትኩስ ዜና ብሎ አንድ ወጣት አንዱን 17 ዓመት ልጅ በቢላ ዘልዝሎ ገደለው :: ኡፍፍፍፍፍፍፍፍ ዘጋዉት ......
ቀን ባስ ስጠብቅ አንዲት ቻይናዊ ተሳቃ የሸጠችልኝን የዲቪዲ ፊልም ከፈትኩት ..... የፊልም ተዋናዩ ብራድ ፒት መሆኑን ያወቅኩት ቆይቼ በድምፁ ነው ፊልሙ ጥቁርቁር ከማለቱ የወንዱን እና የሴቱን መልክ መለየት አይቻልም : በዚህ ላይ ሠውች ብድግ ሲሉና ሲያስሉ ይታያል ይሰማል ... አውጥቼ የቡና ሲኖ ማስቀመጫ ደረግኩት ...
ኮምፒውተሩ አዲስ -ሜይል እንዳለኝ ነገረኝ አነበብኩት አንዱ ከሀገር ቤት ''ያንን ብር እንዴት አደረግክልኝ '' የሚል መልዕክት ነው ::
መርዶ ... ዕዳ ... ሟርት ....
እቺን ዓለም ግን ከዝባዝንኬዋ ውጪ አድርጎ ለብቻዋ እንደፈለገው ሚኖራት ጥበበኛ ይኖር ይሆን ?....

እስቲ ልተኛ የረባ ነገር ይዞ ላይመጣ የሌቱ ምንቀዥቀዥ ይገርመኛል

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዉቃው

ዋና ኮትኳች

Joined: 07 Jan 2007
Posts: 970

PostPosted: Sun Jan 11, 2009 7:15 pm    Post subject: Reply with quote

Wha the *** wong wi me ?

ሰላምታዬን ጲው ጲው ብያለሁ : በልማድ :: የነበረ ያለ የሚኖር የለም :: ...ሁሉም ይለዋወጣል :: እርግጠኛ ነኝ በብዙ ነገሮች ተለውጫለሁ :: በአስተሳሰብ : በአመለካከት ....በቃ በሁሉም ነገር ..ተለውጬ ተሻሽያለሁ ብዬ አምናለሁ :: ማመን ብቻ አይደለም እርግጠኛም ነኝ ::እናም ያለፈችውን እሁዲት በደስታ ልዞራት ወሰንኩ :: ፕላኔ ብዙ ነው :: ብቻ ጌታ ይባርከኝና ዝንጥ ብዬ ወደ ቅዱስ ፓፓሲኖስ ቤተክስቲያን ተፈተለኩ :: ፓርኪንጉ ጢም ብሏል :: ቅዳሴው እየተካሄደ ነው :: አቤት ሰዉ ደስ ሲል ......ውስጤ ቂም የለ ...ምቁ የለ ..... የለ .....እዝጋቤርን አመስግኜ .....ሽው :: ቆይቶ ቅዳሴው አለቀና በቤተክርስቲያናችን ዙሪያ ማሳሳቢያ ስለሚኖር ቆዩ ተባልንና ቆየን :: ሰገነቱ ላይ ያሉ ወጣቶች መጮህ ጀመሩ :: ታች ያሉት የመርቆርዮስ ነን እያሉ ወደላይ ይጮሀሉ : ላይ ያሉት ደግሞ በተዘበራረቀ ሁነታ እኛ የጳውሎስ እያሉ ወድታች እሪ ይላሉ .... እኔም ከየትኛው ወገን እንደሆንኩ በማላውቀው ሁነታ ከነሱ በላይ እጮሃለሁ :: ቤተክርስቲያን የመጣሁበት ምክንያት ትዝ አለኝ :: ለካ ምንም ምክንያት የለኝም :: ብቻ ሳምንቱን ሙሉ ....የሰበሰብኩትን ብሶት ምቁ ......እና .ቂም እዚያ አስተነፍስኩ :: ወይኔ ዉቃው ለካ አልተለወጥኩም :: ግን ዋት * ሮንግ ዊዝ ? ተንደርድሬ ቤተክርስቲያኑ ወጣሁ :: ....... ! ዊች ዋን ኢዝ ማይ ካር ? ደረጃው ላይ ቁጭ አልኩ :: ሚልዮን ጊዚልዮን ካምሪዎች በየባለቤቶቻችው ተወሰዱ :: ቦይ ! ሂር ኢዝ ማይን ..ፊት ለፊቴ ነበረች :: አይ ቶውት ማይን ኢዝ ዲፍረንት ...ለረጅም ጊዜ እንደዛ ነበራ የማስበው .......ግን @ THE F*** WROG WI ME ? ቤቴ ተጣድፌ ደረስኩና ምሳዬን ባፌአድረጌ ራሴን በመስታወት አየሁ :: ኡፕስ ! ሽበቶቼ ብቅ ብቅ ብለዋል :: ቀባ ቀባ አደረኩና ወደኮምዩኒቲው ስብሰባ ተፈተለኩ :: ስለስብሰባው የደረሰኝ ጥሪ የሚለው "ለልጆቻችን አማርኛ አስተማሪነት ሚስተር ዚያንግ ፉን ስለመቅጠር " ይላል :: ኬርስ ? ባለፈው ሌላ ስብስባ ላይ የፐፒፓ ድጋፊዎች ሲርብሹ አንጀቴ አሯል :: ከዛ በፊት ደግሞ የአያኔ ደጋፊዎች እንዲሁ ረብሸው እርር ኩምትር ብያለሁ :: ከዛ ከዛ በፊት ደግሞ የጂጃጅት ደጋፊዎች አጭሰውኛል :: ናዊ ኢት ' ተርን ......ስብሰባውን እንዳሰብኩት በጥብጨ ተለያየን :: ግን ግን ጋይስ ....... ካን ቴል ዋት * ሮንግ ዊዝ ?

አልጨረስኩም
_________________
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዉቃው

ዋና ኮትኳች

Joined: 07 Jan 2007
Posts: 970

PostPosted: Sun Jan 11, 2009 9:11 pm    Post subject: Reply with quote

አይ ቤች , ዜር ሹድ ሳምሲንግ ሮንግ ዊዝ . ታዲያ መቸስ በጤናዬ ......
ግን ሳሰልስለው የሆነ በጥብጥ በጥብጥ አትስማማ የሚል ምናምን ካያቴ በደም ሳይተላለፍብኝ አልቀረም : እንጂ አሜሪካ ኖሬ ሰርቼ ከነሱ ጋር ውዬ ከየት አመጣኸው ልትሉ ነው ? ፓሲቲቭ ዲስከሽን : አግሪ ዲሳግሪ ...ጂኒ ቁልቋል ብሎ ነገር ፍጹም አይመቸኝም :: ዲስከስ ካድረኩኝም ቤቴ ስመለስ ቂም ቋጥሬ መሆኑን አልሸሽግም :: በውነት የምላችሁ ተለውጫለሁ ተሻሽያለሁ ግን .....ዜር ጋታ ሳም ሲንግ ሮንግ ዊዝ . .......ስታር በክስ ሄድኩና ላቴዬን ይዤ ውዝፍ አልኩ :: አየት ያደረጉኝን ግልምጥ : ሰላም ያሉኝን ዝግት ...ፊቴን ጥምዝዝ አረጋለሁ :: የሆነ ኔገቲቭ ፓወር ውስጤን ይተናነቀዋል ...መሰለኝ :: ነጩን ሳይ ዘረኛ ክፉ : ጥቁሩ ሳይ ሰነፍ : ሜክሲካኑን ከኔ ያነሰ ምናምንቴ : ቻይኒዙን ሰልፊሽ : ህንዱን ከይሲ .....በቃ ለሁሉም ስም እሰጣለሁ :: ኮዝ አም ዲፍረንት :: ሴቶቹ ጥሩ ባል አይሆንም ይሉኛል እልና እኔም እበቀላለሁ ...ጥሩ ሚስት አይሆኑም እያልኩ :: ስታር በክሱ ውስጥ ያሉት አበሾች ደበሩኝና ወደ አበሻ ረስቶራንት መረሽኩ :: አስተናጋጇ ሳላዛት በሞተ ፊት ቤክስ አምጥታ ከፈተች :: ግን ለምንድን ነው ቤክስ ብቻ የምጠጣው ? ለምን ሌላ አልሞክርም ? በቃ ቡናየ ከስታር በክስ : ቢራዬ ቤክስ : ዳንሴ ስክስ ስክስ ...........ኑሮዬ ምሬትና ክስ ......ኤዲያ !!!! ቦርጨን አዘቅዝቄ አየህዋት :: የሌሎቹንም አየሁ :: ተመሳሳይ ነን :: ኤክሰርሳይስ አያስፈልገኝም ...ተመሳሳይ ነና !!! አመሻሸሁና ቤቴ ተመለስኩ :: ዋርካን ከፈተኩ :: ማንም የጻፈ የለም :: አናደዱኝ :: አያቁኝም አላቃቸውም :: ግን ለምን አይጽፉም ? በአዲስ ስም ተመዘግብኩና ይጠሉኛል ብየ የምጠረጥራቸውን ሁሉ በስድብ እስከ አፍንጫቸው አስታጥኳቸው :: ነገ ደግሞ በቀድሞው ስሜ ስድብ መጥፎ ነገር ነው አያልኩ ሰስብክ እውላለሁ :: ግን ግን WHAT THE F*** WRONG WITH ME ?

_________________
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዉቃው

ዋና ኮትኳች

Joined: 07 Jan 2007
Posts: 970

PostPosted: Wed Mar 04, 2009 2:44 am    Post subject: Reply with quote

አባ ነብሶ ......ይቺን ቤት አቤት ስወዳት ......አንዳንዴ የራሴም ያንተም ሳይገባኝ አንብቤ /ጥፌ ውልቅ የምልባት ቤት :: ቆይኝማ ሰሞኑን እዘምትባታለሁ ! ለማንኛውም ወደፊት ብቅ ትበል !
_________________
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2637
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Mon Mar 09, 2009 1:59 am    Post subject: Reply with quote

ውጪ እግር 'ሚያጭድ ጆሮ 'ሚቆለምም ብርድ አለ .. ኬፍ ለማለትም አገጬ እየተርገበገበ ነው .... የፒንክ ፍሎይድን ዲቪዥን ቤል እያዳመጥኩኝ ነው ጥሎብኝ እሑድ ማታን አልወደዉም ልጅም እያለው እጠላው ነበር ...
ያልሠራዋቸው የቤትስራዎች ትዝ ይሉኝ ነበረ ....

ውቅሽ አቺን ቤት ሣሎን ጎትተህ ባያት ደስ አለኝ ዋርካ ውስጥ ስለቀልቅ ከኖርኩት በርካታ ቤቶቼ ሁሉ እቺን በጣም ነው 'ምወዳት እራሴን ስለምትሸተኝ ' ነው ዳሩ ራስ ወዳድ አይደለን ... እስቲ ባክህ አንተም ውስጥህ በል ! በል ! ሲልህ እየመጣህ ቀባጥርባት እቺህ ዓለም እንደሆነ የቀባጣሪዎች መድረክ ናት ያው ሁሉም ነገር መቀባጠር ነው

ውስጤ የተሻሸ የእርሳስ ንድፍ ይታየኛል ግን ቡዝዝ ብሏል አይታይም ምናልባት በአንድ ወቅት ለአንድ የረሳዉት ነገር የነደፍኩት ይሆናል ባዶ ነጭ ወረቀት ከፊቴ ቅስት ላይ በመቆንጠጫ ሰቅዬ በሾለ እርሳስ አስፈራራዉት እርሳሴ ግን አቅም አልነበረዉም ያንን ነጭ ወረቀት አስፈራርቶ ያንን ንድፍ ሊያናዝዘው የሚችል ; አቅም ቀርቶ ለራሱም የረባ መስመር መትፋት እንኳን አልቻለም
ዕይታ ምንድነው ? ይሄንን ግድንግድ ቀመር መፍታት ፈለኩኝ የትላንት ንድፌንም ሆነ የዛሬን ቀሽም እርሳሴን ግብግብ ትቼ ዕይታን መመርመር ፈለኩኝ
በጊንጎኛ መጥመልመል የድግግሞሽን ፈዛዛ ንሑስ ዕይታዎች ፎሪ 'ሚያወጣ አንዳች ድብቅ ኃይሌን ፈለግኩት ይደበቅ እንደሆን እንጂ ከውስጤ እንደማይጠፋ እርገጣኛ ነኝ : አሁን ግን ዕይታ ምንድነው ውደሚለው ጥያቄዬ ያለምንም ጥቃቅን ፕሪዲክሽኖች መመለስ ፈለግኩኝ .... ቀለም እና ብረሐን ዕይታ የተሠሩበርት መሠረታዊ ቀመሮች ስለሆኑ በነርሱ ጊዜዬን ማጥፋት አልፈለግኩም ዕይታ የነኚህ ብቻ ስሌት ቢሆንማ ኖሮ ዋርካዊያን እና ዋርከኞችን ያለገፅና ምስል ማየት ባልቻልኩኝ ኖሮ .... ስለዚህ ይሄ ዕይታ 'ምንለው ነገር አንዳች የገዘፈ እና የተወሳሰብ ምስጢር እንዳለው ተረዳው ስሜቴን አዳመጥኩት ዕይታዬ ውስጥ አለ ዕይታዬም ቢሆን ስሜቴ ውስጥ ነበረ ... ከዚህ ምሕዋር ውስጥ እየሠፋው ስሔድ ነው ሠዋዊ ምንነት ውስጥ ተንቀዥቅዤ ዘው 'ምለው ምክኒያቱም የከበቡኝ ዕይታዎች የመደጋገማቸው ምክኒያት በራሳቸው አንዳች ኃይል ፈጥረው መምጣታቸው ግድ ነው ::

እቺን ለመፃፍ .ቦርድ ከመቀብቀቤ በፊት አንድ የተለየ ዲዛይን ለመፍጠር ሳስብ ነበር ያቺ ፌድ ያደረገች የእርሳስ ንድፍ የታየችኝ አድምቄ ካላየዋት 'ሚያመልጠኝ ነገር እንዳለ ይታወቀኛል ለማድመቅ ደግሞ ዕይታዬን ማባበል ይኖርብኛል ዛሬ አንዳች ጥበባዊ ኃይል ውስጣችንን ሲያንኳኳ በሩን መክፈት አለብን በጥበብ ሂደት ውስጥ ዛሬና ነገ ከተጣሉ ጥበብ ጥበብነቷ ቀርቶ ሣይንስ አለያም ሂሣብ በሆነች እነርሱ ሁለቱ ደግሞ ሞት ናቸው ... ስጋ ሲደመር ሴል ብለው ሞት ላይ ያበቃሉ :: ጥበብ ግን ሞት ውስጥ የመኖር ሁሉ ጉረኛ መብት አላት ::

እስቲ እኔ እራሴን በድምብ ለመጠየቅ ልሂድ ''ዕይታ '' ምንድነው ?

ካምሣሚዳ ብዬ ልውጣ ?

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8  Next
Page 5 of 8

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia