WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ተጋላቢ (አስራ ሰባት )
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
የሚሚ :ባል

ዋና ኮትኳች

Joined: 22 Oct 2007
Posts: 971
Location: dictation:donation: duration:information: foundation: gas station:relation: rotation:vacation

PostPosted: Fri Feb 29, 2008 5:06 pm    Post subject: Reply with quote

.

የቆሎ ተማሪ !!ይህ እውነት ትልቅ ስጦታ ነው !! ታድያ ጽሁፍክን አንብቦ ባለመረዳት የሚሰጥህ አስተያየት ብዕርህን እንዳይዝብህ ! ዝም ብለህ ግልቢያህን ቀጥል !!!

አድናቂህ :ናቲ

.

Last edited by የሚሚ:ባል on Fri Feb 29, 2008 7:57 pm; edited 2 times in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website MSN Messenger Report post
አቡቲ

ኮትኳች

Joined: 09 Mar 2005
Posts: 113
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Feb 29, 2008 6:29 pm    Post subject: Reply with quote

Rolling Eyes
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የሚሚ :ባል

ዋና ኮትኳች

Joined: 22 Oct 2007
Posts: 971
Location: dictation:donation: duration:information: foundation: gas station:relation: rotation:vacation

PostPosted: Fri Feb 29, 2008 7:12 pm    Post subject: Reply with quote

አቡቲ እንደጻፈ(ች)ው:
Rolling Eyes

አቡቲዬ ! ካንተ በታች ስለጻፍኩ አንተን መስሎህ እንዳይሆን ! ከሆነ አንተን አይደለም !! ካንተ በላይ ሌላ አስተያየት አንብቤ ነው !

Last edited by የሚሚ:ባል on Fri Feb 29, 2008 7:59 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website MSN Messenger Report post
yammi

ኮትኳች

Joined: 28 Jul 2006
Posts: 436

PostPosted: Fri Feb 29, 2008 7:48 pm    Post subject: Reply with quote

የቆሎ ተማሪው

ግጥሞችህ ጠጠር ያሉ አይነት በመሆናቸው ተደጋግሞ መነበብን ይጠይቃሉ :: መልእክቱም ለብዙዎች ግር ቢልም አይግረምህ ::

በሳል ቃላቶችህና የግጥሙ አወራረድ የሚደነቅ ነው :: ቋንቋው በብእርህ ሲሽሞነሞን እንዴት ያምራል :: በርታ ::

አድናቂህ

ያሚ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የቆሎ ተማሪው

አዲስ

Joined: 05 Feb 2008
Posts: 35

PostPosted: Sat Mar 01, 2008 6:27 pm    Post subject: Reply with quote

አቡቲ የሚሚ ባል እንዲሁም ያሚ ስለሰጣችሁኝ አስተያየት ከልብ አመሰግናለው ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
የቆሎ ተማሪው

አዲስ

Joined: 05 Feb 2008
Posts: 35

PostPosted: Sun Mar 02, 2008 12:38 am    Post subject: Reply with quote

ተጋላቢ (አስራ ሁለት )

በየፊናቸው ዳክረው ከጋጣቸው ሲታደሙ
እንቅልፍ እስኪጥላቸው እያመሰኩ ሲቆዝሙ
በሰው ምግብ የሰው አዋዋል ውለው
ከወትሮው ድካም አገግመው
ለፋሲካ የተገዛ እንዲሉ በመከሩ መኖ፣
ያልጠገገው ግብጠታቸው ያላመሉ ሰክኖ
እያመነዠጉ በጭራቸው እራሳቸውን እየገረፉ
ከቅዠት ጅረት ወርደው ወደ ማዶ ሲቀዝፉ
ቀሚስ አገልድመው ጃኖ ለብሰው ከልፍኝ ሲታደሙ
ወግ እየጠረቁ የአበሻን ልጅ ሲያስደምሙ
ከጋጣቸው ሳይወጡ የጋት ያህል ሳይርቁ
በማይዝ ትልማቸው ሲመረቁ
ከአዛባ ምርግ ግርግዳ እየታከኩ ሲያልሙ
ጭልጥ ብለው ሲተሙ
እንጉልጃቸው አይሎ ከምርጉ ግርግዳ ሲላተሙ
አቤት ሲያሳዝኑ
በሰው ምግብ የሰው አዋዋል ውለው
ከወትሮው ድካም አገግመው
ለፋሲካ የተገዛ እንዲሉ በመከሩ መኖ፣
የትናንት ድካም እንደጉም በኖ
ጭንቅላት ረሃቡ ሆዱ ይመስል
ውሎ አድሮ ያንኑ ሲያብሰለስል
ጠሎቱ ምልጃው ፋሲካ ሆነና
ራስ ሳይጠና ጉተና ...
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2633
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Tue Mar 04, 2008 1:22 am    Post subject: Reply with quote

በሠጋሩ ምናብ
-በፎለፎል ብሕርህ
እኛን በሶምሶማ
-ደፋ ቀና አስብለህ
አንተ ግን ሽምጥ አልክ
-ተጋላቢን ጋልበህ

(ግልቢያህን እጅግ ከሚያደንቁት አንዱ )

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
የቆሎ ተማሪው

አዲስ

Joined: 05 Feb 2008
Posts: 35

PostPosted: Wed Mar 05, 2008 4:57 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ሰላም ወንድሜ ዋናው ወዲህ ወደ ዋርካ መጥቼ እፅፍ ዘንድ አይኔን ስለከፈትክልኝ ምስጋናዬ የበዛ ነው ፡፡ ደሞም ስፍራው ለግልቢያ አይነተኛ ስለሆነ ካልተሰባበርኩ፤ አሊያም ድካም ካልተጫነኝ በስተቀር እያነከስኩም ቢሆን የአቅሜን እሞክራለሁ…
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
የቆሎ ተማሪው

አዲስ

Joined: 05 Feb 2008
Posts: 35

PostPosted: Wed Mar 12, 2008 3:28 am    Post subject: ጋላቢ (አንድ ) Reply with quote

ጋላቢ አንድ

እያየን እየሰማን - ማናይ ማንሰማ
እየበላን ዕየጠጣን - ምንራብ ምንጠማ
እየለበስን እየደረብን - ሚበርደን
እያለን ሳይጎለን -ሚቸግረን
ነገራችን ተምታትቶ
ቅጥ አጥቶ
ግራ ተጋብቶ
መፈልቀቁ መነደፉ -መፈተሉ መዳወሩ
በደጋን መጦዙ -በእንዝርት መንዘሩ
ልፋት መና ሆኖ
ጉልጉል ልቃቂት መስሎ
ከወግ ከማረግ ጎሎ
ጊዜም ጉልበትም ባክኖ
ከአየር ተላትሞ ከደመና ጉኖ
ሁሉ እያለን ሌላ ለሚያምረን
ጠኔ ለማሰው ለማይጠረቃው ከርሳችን
አልታመን አላንጋጥጥ ላለች ነፍሳችን
ተመልክተን እንድናይ አድምጠን እንድንሰማ
በምንዝር አይናችን በእርጉም ልባችን እንዳንታማ
ከከርስ መኖርያ ከሩህ ማደርያችን ገብቶ
እያኘከ ሚበላኝን አልሽርያለንን ተጣብቆ
ምድርን ምሶ -ስራስሩን ምናምኑን ጨቅጭቆ
ክንዳችን በጥቶ
ካልሆነም በአፋችን ግቶ
አይነጥላችንን ሚያበር
አባዜያችን ሚሽር
ነጥተን እንዳንገረጣ
በጆሮአችን ምንሰማውን ሹክሹክታ
በነፍሳችን ያለውን ቱማታ
ቅርንጥ ጥፍንግ አርጎ የያዘንን
እንደለሊት ወፍ እያማታ ሚዞረንን
አዛኝ የለሽ ጸጉራም ውሻ ያረገንን
ጥላ ቢስ ቀትረ -ቀላል ማስጠሎ
ደም የለሽ ውበት አልቦ ዘባተሎ
ደሞ ደሞ
በምልጠታችን እንጉዋጠጥ ዘንዳ ከዛፍ ሰቅሎ
በትር አስታቅፎ ክብረ -ነዋይ አክሎ
የሰው ምንነቱ ወረቱ ይመስል አጃጅሎ
በሃብት በስልጣን በክብር አቃቂሎ
ከጫው አድርሶ ከባጥ በላይ ሰቅሎ
ሳይፈጥመን ላያቆም ከራሱ ተማምሎ
እንደቅሪላ ወደላይ ላጎነን
እንደ ባሉን ሽቅብ ላሰፈፈን
ዕንደየሎስ ጥፍሩን አሹሎ - ፈጥርቆ ሊይዘን
እንደለሊት ወፍ እያደናበረ ለሚዞረን
መጣሁ ቀረው እየለ ለሚያሞርትብን
መውረድ አይቀርምና ቀኑ ደርሶ
የጣለን ለታ ቁልቁል ከስክሶ
እሳት በልቶ በቀል ጎርሶ
በድን ማኖርያችንን ምሶ
ሻሞ ሻሞ ብሎ ቁልቁል ሲለቀን
ታችኛው እንዴት ይሆን ሚቀበለን
ደሞ ደሞ
ስንጋልብም ሆነ ስንሸመጥጥ
ስናልልም ሆነ ስንማግጥ
ባልጋችን ላይ ስንቀብጥ
አይነ -ብዙው ተጋላቢ
ዶሮ ማታ ተቀላቢ
የአመረረ የቆረጠ ለታ
የኛም መታጠቂያችን ሲፈታ
ብርክ ሲይዘን ጉልበታችን ሲርድ
ቀኑ ደርሶ ከጀርባው ላይ ስንወርድ
ቁልቁል ሲለቀን
ታችኛው እንዴት ይቀበለን ?
ጎበዝ ጫንቃው ላይ ሆነን
አሱ ነው ሚያሳስበን

ይቀጥላል ...
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ቤቲ _13

ዋና ኮትኳች

Joined: 18 Sep 2006
Posts: 723
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Mar 13, 2008 10:21 pm    Post subject: Re: ጋላቢ (አንድ ) Reply with quote

የቆሎ ተማሪው እንደጻፈ(ች)ው:
ጋላቢ አንድ

እያየን እየሰማን - ማናይ ማንሰማ
እየበላን ዕየጠጣን - ምንራብ ምንጠማ
እየለበስን እየደረብን - ሚበርደን
እያለን ሳይጎለን -ሚቸግረን
ነገራችን ተምታትቶ
ቅጥ አጥቶ
ግራ ተጋብቶ
መፈልቀቁ መነደፉ -መፈተሉ መዳወሩ
በደጋን መጦዙ -በእንዝርት መንዘሩ
ልፋት መና ሆኖ
ጉልጉል ልቃቂት መስሎ
ከወግ ከማረግ ጎሎ
ጊዜም ጉልበትም ባክኖ
ከአየር ተላትሞ ከደመና ጉኖ
ሁሉ እያለን ሌላ ለሚያምረን
ጠኔ ለማሰው ለማይጠረቃው ከርሳችን
አልታመን አላንጋጥጥ ላለች ነፍሳችን
ተመልክተን እንድናይ አድምጠን እንድንሰማ
በምንዝር አይናችን በእርጉም ልባችን እንዳንታማ
ከከርስ መኖርያ ከሩህ ማደርያችን ገብቶ
እያኘከ ሚበላኝን አልሽርያለንን ተጣብቆ
ምድርን ምሶ -ስራስሩን ምናምኑን ጨቅጭቆ
ክንዳችን በጥቶ
ካልሆነም በአፋችን ግቶ
አይነጥላችንን ሚያበር
አባዜያችን ሚሽር
ነጥተን እንዳንገረጣ
በጆሮአችን ምንሰማውን ሹክሹክታ
በነፍሳችን ያለውን ቱማታ
ቅርንጥ ጥፍንግ አርጎ የያዘንን
እንደለሊት ወፍ እያማታ ሚዞረንን
አዛኝ የለሽ ጸጉራም ውሻ ያረገንን
ጥላ ቢስ ቀትረ -ቀላል ማስጠሎ
ደም የለሽ ውበት አልቦ ዘባተሎ
ደሞ ደሞ
በምልጠታችን እንጉዋጠጥ ዘንዳ ከዛፍ ሰቅሎ
በትር አስታቅፎ ክብረ -ነዋይ አክሎ
የሰው ምንነቱ ወረቱ ይመስል አጃጅሎ
በሃብት በስልጣን በክብር አቃቂሎ
ከጫው አድርሶ ከባጥ በላይ ሰቅሎ
ሳይፈጥመን ላያቆም ከራሱ ተማምሎ
እንደቅሪላ ወደላይ ላጎነን
እንደ ባሉን ሽቅብ ላሰፈፈን
ዕንደየሎስ ጥፍሩን አሹሎ - ፈጥርቆ ሊይዘን
እንደለሊት ወፍ እያደናበረ ለሚዞረን
መጣሁ ቀረው እየለ ለሚያሞርትብን
መውረድ አይቀርምና ቀኑ ደርሶ
የጣለን ለታ ቁልቁል ከስክሶ
እሳት በልቶ በቀል ጎርሶ
በድን ማኖርያችንን ምሶ
ሻሞ ሻሞ ብሎ ቁልቁል ሲለቀን
ታችኛው እንዴት ይሆን ሚቀበለን
ደሞ ደሞ
ስንጋልብም ሆነ ስንሸመጥጥ
ስናልልም ሆነ ስንማግጥ
ባልጋችን ላይ ስንቀብጥ
አይነ -ብዙው ተጋላቢ
ዶሮ ማታ ተቀላቢ
የአመረረ የቆረጠ ለታ
የኛም መታጠቂያችን ሲፈታ
ብርክ ሲይዘን ጉልበታችን ሲርድ
ቀኑ ደርሶ ከጀርባው ላይ ስንወርድ
ቁልቁል ሲለቀን
ታችኛው እንዴት ይቀበለን ?
ጎበዝ ጫንቃው ላይ ሆነን
አሱ ነው ሚያሳስበን

ይቀጥላል ...

ምኑን መርጨ ምኑን ልተወዉ ......ዉብ ዉብ ዉብ !!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website MSN Messenger Report post
ወልዲያ

ዋና ኮትኳች

Joined: 17 Apr 2007
Posts: 596
Location: የጁ - ወሎ

PostPosted: Fri Mar 14, 2008 8:27 am    Post subject: እንበል ጠንክር Reply with quote

ሠላም የቆሎ ተማሪው !

ፈረሰኛ ሁኜ መጋለብ ባልችል :
እሸመጥጣለሁ ልመለስ በድል ::

ድሉ የእኔ ሁኖ ዋርካ ስር ሳርፍ :
ለካስ ዋሸራ ነኝ ቅኔውን ልዘርፍ ::

ዋናው ቃላት ገድፎ ዋኖስ ሲያርቀው :
ዋኖስ ቃላት ገድፎ ዋናው ሲያርቀው :
YAMMI ብቻ ቀረች እንዴት ትዝለቀው ?

መዝለቁን ዘለቀች አቡቲን ይዛ :
ዳዊት ይደግማሉ አይደሉም የዋዛ ::

ባቲ በክራሩ ቆንጅት በበገና :
መደርደር ጀመሩ ስሙ በጥሞና ::

የቆሎ ተማሪው ቅኔውን ሲያሰፍር :
ለእኛ ብሎ ነው እንበል ጠንክር ::

መልካም ጁማ
ወልዲያ - የጁ

_________________

አንድ ኢትዮጵያ
http://www.cyberethiopia.com/warka5/viewtopic.php?t=28757
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የቆሎ ተማሪው

አዲስ

Joined: 05 Feb 2008
Posts: 35

PostPosted: Thu Mar 27, 2008 10:33 pm    Post subject: Reply with quote

ተጋላቢ (12)
ናጩርታም - ተሰኝቼ በአያቴ
እኝኝዋ - ተከተለች እናቴ
የሰው ነጭኛጫ - ምትለኝ እህቴ
አረ ልጄን አሳበዳት - አማቴ
ይብላኝ አቅፋው ለምተኛው ሚስቱ
ይህን ያለው ሰፈርተኛው ጎረቤቱ
ችክ ያለ ነዝናዛ
ደረቅ ሞዛዛ
ጉዋደኛዬ
አይኑን አያሳየኝ
አዲሱ አለቃዬ
አቤት ክርክር አቤት ክርክር
መለወጥ ትችላለህ ሚለኝ መምህር
ድንጋይ ተብልህ እንዳትረገጥ
ጨው ለራስህ ብለህ ጣፍጥ፡፡
ንሰሃ አባቴ
ክጄያለው - ወላጅ አባቴ
ደሞ ራሴው ለኔው ለራሴ
በአንደበቴ በምላሴ
ዝግንን እያለኝ
እየተናነቀኝ
መልሼ አያቴን ረገምኩኝ
ስም አጥፊ እያለኩኝ
ይቀጥላል ..
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
የቆሎ ተማሪው

አዲስ

Joined: 05 Feb 2008
Posts: 35

PostPosted: Sun Apr 13, 2008 3:06 pm    Post subject: Reply with quote

ተጋላቢ አስራሶስት
ሁሉን ከመከወኛዬ - አንዳች ከማይሳነኝ ቦታ
ላርግ አላርግ -ይቅር አይቅር -እያልኩ ሳመነታ
የብኩነ ሰው ድካሙ ልቤን ነክቶት ስቆዝም
ከጢስ አላባ መንደሩ ዘልቄ ሳዘግም
ሰዉን ጠኔ የሾኬ ጠልፎት
ከአፈር ከትቢያ አንጋሎት
እሱ ወንድ ሁኖ ቦላሌ ታጥቆ
ወንዱ ሁላ ደሞ ምንም ሁኖ ተሸማቆ
ገላጋይ አይጠራ ነገር ጉሩምቦውን ታንቆ
እያስደገደገ አጀቡን እያበዛ
በደሃ ቁርበት ጎኑን እያወዛ
ጉረድምድም እያረገ ሲሰለቅጥ
እየግበሰበሰ ቀፈቱን ሲለጥጥ
እልህ ገብቶኝ በቀል ወርሶኝ
ብሽቀቴ የአውሎ ያህል ነፍሶ
ውስጤ ቢያኖረው ግሳግሱን አገባብሶ
ለነፈዙ ሰው መፍትሄ ላመጣ
ሃዘኑን ላዝን ቁጣውን ልቆጣ
አንዳች መአት ከላይ ላዥጎደጉድ
ሆነብኝና ግድ
ከዛው ሁሉን ከመከወኚያ እልፍኜ ታድሜ
ምንመ ከማይሳነኝ ማማዬ ላይ ቆሜ
ይህንን ክፉ አባዜ የአበሻን ልክፍት
የተጣባንን የትውልድ ምትሃት
ጆሮውን አስይዤ ቁጭ ብድግ ላሰራው
እንደ እንጀራ እናቴ ቅጣትን ልቀጣው
አይለመደኝም እስኪል ላስለከልከው
ፍዳ አሳሩን ላበላው
ቆረጥኩና
ቁልቁል አጮልቄ
ክንዴን ሰብቄ
በሃይል አባርቄ
አብከንክን የተሰኘውን ቦንቤን ላፈነዳ
ድሜ ላስግጠው ላበላው ፍዳ
ቀውጢ ሆና ምድር
ድህነት ላንጫርር
ጠኔን ልቀብር
ወደታች ስዳክር
የቦንቤ ሙሌት ሰአተ -ፍንዳቱ
ከዋኝ መሰሪው ለግባተ - መሬቱ
ተዛብተ ኖሮ ማፈንጃ ቅኝቱ
ቦንቤ ድህነትን ትቶ
ድሃን ብቻ በልቶ
ረሃብም ጠኔው ተበራክቶ
ስልቻው ጥርስ ብቻ ሆኖ
ሰልሎ መንምኖ
እኔም የቦንቡ ቀለህ ሖኜ
ትክዝ ብዬ አዝኜ
በስራዬ ተብከንክኜ
ሳለ በተራው እሱ እልህ ገብቶት
በቀል ወርሶት
ከአካሌ ቀስ በቀስ እየበላ
በደም ወልፍ አፉን እያቀላ
ሆዴን ብቻ ትቶልኝ
ከእልፍኜ ጣለኝ
የእድሌ ጥመቱ
ህልም እንኩዋን አይዝልኝ
ይቀጥላል… .
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ቤቲ _13

ዋና ኮትኳች

Joined: 18 Sep 2006
Posts: 723
Location: ethiopia

PostPosted: Sun Apr 13, 2008 8:23 pm    Post subject: Reply with quote

አጠረብን .....አነሰብን ......ተቆጠብክብን የቆሎዉ ብዙ ብዙ ዎቻችን በጉጉት እንጠብቃለን ጽሁፍህን
አባክህን አብዛልን ...
አክባሪህ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website MSN Messenger Report post
መልከጻዲቅ

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Aug 2007
Posts: 675

PostPosted: Mon Apr 14, 2008 2:42 am    Post subject: Reply with quote

የቆሎው ተማሪ እንደምን አለህ Cool
ከግጥሞችህ ጥልቀት ባሻገር ዛሬ ፓልቶክ ላይ ስለመረጥከው ስም የሰጠሀው ማብራሪያ ራሱ በዳገት ሳይሆን ቁልቁለት እየወረድን ለሚደክመን ትልቅ ትምህርትና ማበረታቻ ነው :: መልካም የግጥም ትበያ እመኛለሁ :: Cool
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6  Next
Page 3 of 6

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia