WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ትዝታዬ : ናፍቆቴና ግርምቴ ! እናቴ !
Goto page 1, 2, 3 ... 14, 15, 16  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ዉቃው

ዋና ኮትኳች

Joined: 07 Jan 2007
Posts: 969

PostPosted: Sun Mar 25, 2007 4:02 pm    Post subject: ትዝታዬ : ናፍቆቴና ግርምቴ ! እናቴ ! Reply with quote

ሰላም ዋርከኞች

ነገሩ እያነሳህ ጣለው ነውና የባጥ የቆጡን አብረን እያነሳን እንጥላለን :: በቅድሚያ ወንድማችን ሀሪከን <ልጅ እያለሁ > በሚለው ርዕሱ ወደኋላ ሄደን ትዝታችንን እንድናወጋና : ለዚህች ርዕስም መነሻ እንዲሆነኝ ስላሳሰበኝ አመሰግነዋለሁ ::

ይጀመራ ቀደዳው !

እንግዲህ ጊዜ በጣሙን እያለፈ በመጣ ቁጥር አንዳንዶቹን ሳሰባቸው ምናለ ተመልሰው አሁን ቢሆኑ : ያስብሉኛል :: አንዳንዶቹ ግርም ሲሉኝ ቀሪዎቹ ደግሞ እንደጉድ ይናፍቁኛል ::

ከግርምቴ ልጀምር ::
በልጅነቴ እጅግ በጣም ሲበዛ ቅማላም ነበርኩ :: ቅማሎቹ እንዴት ከምን ለምን በማን አናቴ ላይ ተፈጠረው ሲርመሰመሱ እንደሚውሉ አሁንም አይገባኝም :: በቃ የቅማል ሰራዊት ደሜን ሲመጥ ይውላል ያድራል :: በወላጆቼ ቅማሎቹን ለማጥፋት : ያልተደረገ ጥረት : ያልተቀባሁት እምነት : ያልጠጣሁት የጸበል ዓይነት አልነበረም :: ወደ ኋላ ላይም ጸጉሩ ሉጫ ቢጤ ሰለሆነ የሰው ዓይን ነው ተብሎ የተቆጣጠሩ ነገሮች ለዓመታት አንገቴ ላይ አንጠልጥያለሁ ::

እነ ቅማል ግን : ወይ ፍንክች !

የናቴ ተጨማሪ ስራ ቀን በእናት ቅማሎች ሲዘሩ የዋሉትን ቅጫሞች ማታ ሲያላቀቁ ማምሸት ነው :: ቅጫሞቹ ብዙውን ጊዜ ከጸጉሬ ጋር በጣም ሰለሚጣብቁ : እናቴ ቅጫሞቹን በጥፍሮቿ ለማላቀቅ በምታደረገው ጥረት : በአሰቃቂ ሁኔታ መነጨቴ አይቀሬ ነው :: በቅማል ሲፈተፈት የዋለ ቆሮቆራም ጭንቅላት በናቴ ጥፍር ደግሞ ሌላ ተጨማሪና ሰልታዊ ጥቃት ይደርሰበታል ::

በቃ ቅማሎች ቢራገፉ : ምደረ ቅጫም ሲመዘዝ ቢያድር : ጭንቅላቴ በማላውቀው ኬሚካል ሲታጠብ ቢያመሽ : አንድም ለውጥ የለውም :: በበነጋው ማታ የዉቃው አናት ቀድሞ ከነበሩት ቅማሎች በእጥፍ ይሞላል :: ባጠቋቸው ቁጥር ራሳቸውን የሚያባዙበት አንዳች ዓይነት ምትሃት ሳይኖራቸው አልቀረም :: አሁን አሁን ለድድብናዬ ዋነኛ ተጠያቂዎች ለዘመናት ሲመጠመጡኝ የኖሩት ቅማሎች መሆናቸውን ተገንዝቤያለሁ ::

መጣሁማ ! የውጭ በር ተንኳኳ መሰለኝ

Last edited by ዉቃው on Tue Aug 14, 2012 2:17 am; edited 5 times in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዉቃው

ዋና ኮትኳች

Joined: 07 Jan 2007
Posts: 969

PostPosted: Sun Mar 25, 2007 11:36 pm    Post subject: Reply with quote

ተመለስኩኝ :;

አንድ ቀለብላባ ነጭ በር አንኳኩቶ ፔፐሮኒ ፒትዛ ኦርደር አርገሃል ወይ ይለኛል :: ትናንት የገዛኋትን በበርበሬና በዘይት የታሸች አነባበሮ አላየ !

ወደ ግርምቴ ሰመለስ : ያው እንግዲህ የሆነ ዕድሜ ላይ ሰደርስ ቅማል የሚባል አናቴ ላይ የለም :: እንዴት በምን ለምን በማን እንደጠፉ የማውቀውም የሰማሁትም ነገር የለም :: በቃ ብን ብለው ጠፉ !

ሌላው የሚገርመኝ ደግሞ የሾዳ ጉዳይ ነው :: አይ ሸራ ጫማ ! ለምንድን ነው ግን ሸራ ጫማ ትናንት ተገዝታ ከአንድ ሁለት ሞቅ ያለ እግር ኳስ ጨዋታ በኋላ ቡን የምትለው ? በፍጠነት ከመቀዳደዷ ይልቅ ይገርመኝ የነበረው ግን ለየት ያለው ቁናሷ ! አቤት ቁናስ ! አሁን ላይ ሆኘ ወደኋላ ሳሰበው ያኔ በልጅነቴ : እግሮቼ ሞተው ነበር እንዴ ? እያልኩ ራሴን እጠይቃለሁ :: ሞተው ቢሆን እንጂማ ነፍስ ያለው እግር እንዴት እንደዚያ ይሸታል ! በኔ ሰሌት በዓመት ሀያ ጊዜ ጉንፋን ይይዘኝ እንደሆን : ለአስራ ዘጠኙ ተጠያቂ ሸራ ጫማዎቼ ናቸው :: እርግጥ ነው ሸራ ጫማውም ሆነ እኔ ውሃ የሚያገኘን በሳምንት አንዴ ነበር :: ያውም በዕለተ ቅዳሜ ! ሸራዋ እሁድ ታጥባማ ለሰኞ /ቤት አትደርቅማ ! ሰለዚህም ሸራዬ በቅዳሜ መታጠቧ ግድ ነው :: አቤት ያቺ ብረት ግን ምጣድ ምን ያላየችው አለ ! እኔ እታጠብባታለሁ : እነቦጌም ይታጠቡባታል : ቁናሳሟ ሸራዬ : የቤቱ : የሴቱ : የከብቱ ጣጣ ይታጠብባታል :: ከዚያ ከተረፈች ደግሞ በርበሬ ይሰጣባታል :: በዚህ ቢበቃት እሺ :: ደሞ የቶታአው እናት ይመጡና : "የዉቃው እናት ብረትምጣዶን ያውሱኛል " ተብሎላት : የነሱን ቤት ደግሞ ስታገለገል ትውላለች :: ብረት ምጣዶች እኮ ባለውለታዎቻችን ናቸው :: ከነ ጆግና ማስታጠቢያ ተደምረው ጋር ሆነው በገጣሚያኑ ሊገጠምባቸው ይገባል ::
_________________
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ማይ ኔም

ኮትኳች

Joined: 17 Mar 2005
Posts: 165
Location: united states

PostPosted: Mon Mar 26, 2007 2:19 pm    Post subject: Reply with quote

Quote:
ዉቃዉ በሳቅ ገደልከኝ
Laughing Laughing Laughing
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቅራሪ

ኮትኳች

Joined: 10 May 2006
Posts: 236
Location: adiss abeba

PostPosted: Tue Mar 27, 2007 5:10 pm    Post subject: Reply with quote

ወይ ውቃው ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ በጣም ነው በሳቅ የገደልከኝ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ጌታ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Apr 2005
Posts: 3229
Location: ዶሮ ተራ

PostPosted: Tue Mar 27, 2007 5:29 pm    Post subject: Reply with quote

ዋርካ አንድ ጥሩ አጫዋች አግኝታለች :: ይመችህ አቦ !!!!

ነገረ ሥራህ ሁሉ ግን ያን የምወደውን ጓደኛዬን ጉዱን ትመስላለህ :: ትንሽ ልዩነታችሁ እሱ ሸራ ጫማ ሳይሆን በረባሶ ነበር የሚገዛለት ::
_________________
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ቅራሪ

ኮትኳች

Joined: 10 May 2006
Posts: 236
Location: adiss abeba

PostPosted: Tue Mar 27, 2007 5:33 pm    Post subject: Reply with quote

ጌታ ምነው እኛ አንወደድም እንዴ ???? ምነው ለጉዱ አደላህ ? ጉዱ ቢሰማህ ደስ አይለውም ...
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ጉዱ ካሳ

ኮትኳች

Joined: 22 Oct 2003
Posts: 431

PostPosted: Tue Mar 27, 2007 5:58 pm    Post subject: Reply with quote

አይይይይ ጌታ ! አሁን አንተም ከኔ የተሻልክ አትመስልም ? የምትበልጠኝ በባለሰደርያው ካልሲ በረባሶህን ስለምታደርግ ብቻ ነው :: ግን የቶታው ነገር ሳስበው ግርም አለኝ ! ለካ እንደዚያ አመዳም የሚመስለው ከነ ውቃው በተዋሰው ብረት ምጣድ የአሻሮ -ሻወር እየወሰደ ነው ! ታጥቦ ማይጠራ ሽንፍላ ብቻ ይመስለኝ ነበር ! ቱፍ ! ቱፍ ! አበስኩ ገብርኩ ! በጾሙ ምድር ስለሽንፍላ አወራሁ ::
ቅራሪነት አይዞሽ አንቺንም እንደሚወድሽ ሸውራራ አይኑ ያሳብቅበታል :: በል ውቃው ወንድማችን እስቲ ለጥቅልን ! ወግ መጠረቁን ተክነህበታል አቦ ! በርታልን !

ጉዱ ካሳ
ከፒያሳ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጌታ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Apr 2005
Posts: 3229
Location: ዶሮ ተራ

PostPosted: Tue Mar 27, 2007 6:31 pm    Post subject: Reply with quote

ቅራሪ እንደጻፈ(ች)ው:
ጌታ ምነው እኛ አንወደድም እንዴ ???? ምነው ለጉዱ አደላህ ? ጉዱ ቢሰማህ ደስ አይለውም ...

መጀመሪያ እስቲ እኛ የሚለውን አብራሪው :: አንቺን ግን በጣም ትወደጃለሽ ::
_________________
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
የመንደራው

ኮትኳች

Joined: 05 Oct 2006
Posts: 189

PostPosted: Tue Mar 27, 2007 6:56 pm    Post subject: Reply with quote

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ውቃው ፍንድት ልልህ ነው በሳቅ በተለይ በበርበሬና በዘይት የታሸች አነባበሮ ፒትዛ መሆኗ ነው አየ አንተ ሰው እዴት መጣልህ አቦ ይመችህ ቀጥልበት

የመንደራው
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቅራሪ

ኮትኳች

Joined: 10 May 2006
Posts: 236
Location: adiss abeba

PostPosted: Tue Mar 27, 2007 7:29 pm    Post subject: Reply with quote

ጌታ ጌታጠንበለል ሰላም ነህ በምጀመሪያ ሰላምታ ላስቀድም ብዬ ነው "'እኛስ "" ብዬ የጠቀስኩት እኔ አንተን ጉዱን እና እምናውቃትን ለማለት ያህል ነው ግን ዋናው ቁምነገር ለጥያቄዬ መልስ ስለሰጠህኝ አመሰግናለሁ በኛም በኩል እንደዛው ነው

ጉዱ ቅቅቅ ሸውራራ ለሸውራራ ተያይዞ ገደል ነው በለኝ ቅቅቅ አትጥፋ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ጌታ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Apr 2005
Posts: 3229
Location: ዶሮ ተራ

PostPosted: Tue Mar 27, 2007 7:32 pm    Post subject: Reply with quote

ቅራሪ እንደጻፈ(ች)ው:
ጌታ ጌታጠንበለል ሰላም ነህ በምጀመሪያ ሰላምታ ላስቀድም ብዬ ነው "'እኛስ "" ብዬ የጠቀስኩት እኔ አንተን ጉዱን እና እምናውቃትን ለማለት ያህል ነው ግን ዋናው ቁምነገር ለጥያቄዬ መልስ ስለሰጠህኝ አመሰግናለሁ በኛም በኩል እንደዛው ነው

ጉዱ ቅቅቅ ሸውራራ ለሸውራራ ተያይዞ ገደል ነው በለኝ ቅቅቅ አትጥፋ

ኧረ ተይ አንቺ ልጅ እምናውቃትን እያልሽ እየሸፋፈንሽ ሌላ ነገር አታስመስያት !!! ስም ካላት ተናገሪና እንደምትወደድና እንደማትወደድ እነግርሻለሁ ::
_________________
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
በቃል

አዲስ

Joined: 11 Feb 2005
Posts: 13

PostPosted: Tue Mar 27, 2007 8:40 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለቤቱ እና ለባለቤቱ

አቶ ጌታ ሰላም ኖት ወንድማችን ውቃው የኛኑ ታሪክ ከሽኖ ያወጋናል :: መቼስ ማንነትን በቃል በዚች መስኮት መግለጽ ባይቻልም እንደውቃው አሳምሮ ማቅረቡ ትልቅ ችሎታ ነው ::
ውቅነት እስቲ ለጥቅበት .....

ቸር እንሰንብት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ShyBoy

ዋና ኮትኳች

Joined: 04 Apr 2006
Posts: 904
Location: Gojjam

PostPosted: Tue Mar 27, 2007 10:14 pm    Post subject: Reply with quote

እኔም እንደውቃው ጽሁፍ የሚያዝናናኝ የለም !!! ዋርካ ውስጥ ብዙ Stars አሉ .........ማዝናናትን በተመለከተ ደግሞ ውቃው Super-Star ነው !!!!!!!!!

እስቲ እባክህ ቀጥልበት !!!!!!!!!!!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ቅራሪ

ኮትኳች

Joined: 10 May 2006
Posts: 236
Location: adiss abeba

PostPosted: Mon Apr 02, 2007 9:36 pm    Post subject: Reply with quote

ውድ ውቃው ምነው የት ነው እልም ብለህ የጠፋህው ? አረ ብቅ በልልን ናፍቆት ሲበዛ እኮ ሆስፒታል ያስተኛል ብለዋል ስለዚህ አትጥፋብን
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
ማያዬ

ኮትኳች

Joined: 29 Jan 2007
Posts: 208

PostPosted: Mon Apr 02, 2007 11:20 pm    Post subject: Reply with quote

ዉቃው እንደጻፈ(ች)ው:

አሁን ላይ ሆኘ ወደኋላ ሳሰበው ያኔ በልጅነቴ : እግሮቼ ሞተው ነበር እንዴ ? እያልኩ ራሴን እጠይቃለሁ :: ሞተው ቢሆን እንጂማ ነፍስ ያለው እግር እንዴት እንደዚያ ይሸታል ! በኔ ሰሌት በዓመት ሀያ ጊዜ ጉንፋን ይይዘኝ እንደሆን : ለአስራ ዘጠኙ ተጠያቂ ሸራ ጫማዎቼ ናቸው :: እርግጥ ነው ሸራ ጫማውም ሆነ እኔ ውሃ የሚያገኘን በሳምንት አንዴ ነበር :: ያውም በዕለተ ቅዳሜ ! ሸራዋ እሁድ ታጥባማ ለሰኞ /ቤት አትደርቅማ ! ሰለዚህም ሸራዬ በቅዳሜ
መታጠቧ ግድ ነው :: አቤት ያቺ ብረት ግን ምጣድ ምን ያላየችው አለ ! እኔ እታጠብባታለሁ : እነቦጌም ይታጠቡባታል : ቁናሳሟ ሸራዬ : የቤቱ : የሴቱ : የከብቱ ጣጣ ይታጠብባታል :: ከዚያ ከተረፈች ደግሞ በርበሬ ይሰጣባታል :: በዚህ ቢበቃት እሺ :: ደሞ የቶታአው እናት ይመጡና : "የዉቃው እናት ብረትምጣዶን ያውሱኛል " ተብሎላት : የነሱን ቤት ደግሞ ስታገለገል ትውላለች :: ብረት ምጣዶች እኮ ባለውለታዎቻችን ናቸው :: ከነ ጆግና ማስታጠቢያ ተደምረው ጋር ሆነው በገጣሚያኑ ሊገጠምባቸው ይገባል ::

ውቃው ..... በናትህ ሆዴን ነው ያሳመምከኝ በሳቅ ሂሂሂሂሂሂ
ነፍስህ አይማርም የብረት ምጣዱ ነገር ምን እንዳስታወሰኝ ታውቃለህ ...አንዲት ልጅ እዚህ ምንም አልመች ይላትና ወደ ሀገርቤት በጣም መመለስ እንደምትፈልግ እያማረረች ስትናገር የሰማት ልጅ ...ተዋት ትሂድ በብረት ምጣድ መታጠብ ናፍቓት ነው አለ ....ሂሂሂ ሂሂሂሂ እስኪያመኝ ድረስ .......አንተ ድግሞ የባስክ ነህ አትጥፋ እባክህ ትንሽ አስነብበን
አክባሪህ
_________________
''''ሁሉም ነገር ለበጎ ነው ''''
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2, 3 ... 14, 15, 16  Next
Page 1 of 16

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia