WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የትኛው 'ኢህአፓ ' 38 ዓመታት ባለታሪክ ?
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Mar 21, 2010 4:19 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

ይህንን ዓምድ ከተቀበረበት ጉድጓድ ያወጣሁት ያለምክንያት አይደለም -: ሠሞኑን በአቶ እያሱ አለማየሁ የሚመራው 'ኢሕአፓ ' አንጃ በሌላው ወገን የተሠለፈውን የእነ አቶ መርሻ ዮሴፍን አንጃ ውስጣዊ ጉድ ብሎ ያወጣው መረጃ ቆስቁሶኝ ነው :: ሁለቱም 'ሙሉ -በኩለሄ ' ነን ባይ ተመጻዳቂዎች ቢሆኑም ይህ አንጋፋ ድርጅት እንዴት በጥቂት ለሥልጣን ስግብግብ በሆኑ ግለሰቦች እየተገፋ አሁን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ትግል ጠርዝ እንደበቃ ከብዙ በጥቂቱ ማሥረጃ ይሆናል ብዬ ስላሰብኩ ይህንን ባለ 68 ገጽ ሠነድ ቀስ እያላችሁም ቢሆን እንድታነቡት እጠይቃችኋለሁ :: ምናልባት ይህ ሠነድ ቶሎ ከድረ -ገጹ ሊነሣ ስለሚችል በኤሌክትሮኒክ መንገድ ቅጂውን ማስቀመጡ አይከፋም ::

መልካም ንባብ ::

ደብተራው : መጋቢት 2002 ..:: ወጣ ወጣና እንደ ሸምበቆ (ተንከባለለ እንደ ሙቀጫ ) - የአንጃው መሪ የመርሻ ዮሴፍ ክህደትና ቅሌት (መርሻጌት ) ::

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቢተወደድ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 21 Jul 2009
Posts: 1762
Location: Dabra Za`Yet

PostPosted: Sun Mar 21, 2010 12:58 pm    Post subject: Reply with quote

የጥላሁን ዘፈን ጋብዤሀልሁ ለተላ

ወደሁዋላ ሄደሽ በሀሳብ ከማለም የሚለውን
_________________
When we do it right No-one remembers,
When we do it wrong No-one forgets.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu Jan 19, 2012 10:39 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

የደብተራው ድረ -ገፅ በማን እንደሚተዳደር አላውቅም :: ነገር ግን ከሚያወጣቸው ጽሑፎች የኢሕአፓን አንዱን አንጃ (በአቶ እያሱ ዓለማየሁ የሚመራውን ) እንደሚወግን ግልፅ ነው :: 6 ዓመት በፊት የቅንጅት መሪዎች በእሥር በሚማቅቁበት ጊዜ አንድ አጠያያቂ የሆነ የቅንጅት መሪዎችን የሚወነጅል ጽሑፍ ለጥፎ ነበር :: በዚያ ጽሑፍ ምክንያት ድርጅቱ በቅንጅት ደጋፊዎች ተብጠልጥሎ ነበር :: ከሁለት ዓመታት በፊት በድርጅቱ ውስጥ ዳግም በተከሠተ የአንጃ መከፈል ምክንያት በሌላኛው ወገን የቆመውን የእነ በላይነህ ንጋቱን (መርሻ ዮሴፍን ) አንጃ የሚያብጠለጥል ሠነድ በተነ :: ሠሞኑን ደግሞ ይኼው አንጃ የኮሎኔል መንግሥቱን መጽሐፍ በሕገ -ወጥ መንገድ በኢንተርኔት ለቅቆታል :: እስኪ ካለፉ ውይይቶች ትምህርት የሚገኝ እንደሆነ በሚል እሣቤ ይህንን ርዕስ ወደፊት አምጥቼዋልሁ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu Feb 02, 2012 10:49 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም 17 ዓመት የአገዛዝ ዘመናቸው ምንም ዓይነት ኃጢያት ያልፈጸሙ ጻድቅ ናቸው ብሎ ከመከራከር ግመልን በመርፌ ቀዳዳ ማሾለክ ይቀልላል :: በሌላው ወገን ለደርግ ተፃራሪ ሆነው ከቆሙት ኃይሎች መካከል ኢሕአፓ እንዲያ በከተማ እና ገጠር ሽብር ሲያካሂድ 'ሁሉም ለኢትዮጵያውያን ልዕልና ነበር ' ብሎ መሟገቱ ጉንጭ አልፋ ሙግት ይሆናል :: ምክንያቱም በኢሕአፓ ስኳዶች ጥይት የወደቁት ሁሉ ወንጀል የነበረባቸው ኢትዮጵያውያን አልነበሩም :: የኢሕአፓ ሰዎች የሌሎችን ድርጅቶች ኃጥያት አክብደው ዘወትር እንደተበደሉ የሚያማርሩትን ያህል እስከዛሬም ድረስ በእነርሱም ወገን በኢሕአፓ ወይም ከኢሕአፓ ተፈልፍለው የተራረፉት ድርጅቶች በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ስላደረሡት በደል አንዳቸውም በይፋ በአደባባይ ይቅርታ ሲጠይቁ ዐይተንም : ሠምተንም አናውቅም :: ይባስ ብሎ ከዚያን የሽብር ዘመን የኢሕአፓ መሪዎች መካከል ኢሕአፓ በከተማ ይፈጽም የነበረውን ግድያ ይመራ የነበረው ክፍሉ ታደሰ ' ትውልድ - The Generation' በሚል ርዕስ መጽሐፍ ጽፎ ለአንባቢ አሠራጭቷል :: ስለዚህ እኔም ሆንኩ በሚሊዮኖች የምንቆጠር ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚቀርቡ መረጃዎችን አገናዝበን ዕውነቱን ለማወቅ የምናደርገውን ጥረት ለምን በአቶ ኢያሱ አለማየሁ የሚመራው የኢሕአፓ አንዱ አንጃ ደንቃራ ይሆንብናል ? እነርሱ ስለራሣቸው ትክክለኛነት የሚሠብኩትን ያህል ሌሎችም የእነርሱ የዚያን ዘመን ተቀናቃኞች የሚሉት ይኖራቸዋል :: ወይስ ደግሞ ኮሎኔሉ አሁን የሚያፍረጠርጡት ሚሥጢር ይኖራል ብለው ፈሩ Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes

ለማንኛውም በዚህ የእነ አቶ እያሱ አለማየሁ አንጃ ተግባር ከተለያዩ አቅጣጫዎች ውግዘት መጉረፉን ቀጥሏል :-

ምንጮች :-
1 ..... ክፍሌ ሙላት (የኢነጋማ ፕሬዘዳንት ) : ሐሙስ ጥር 25 ቀን 2004 .. :: ግልጽ ደብዳቤ (ፀሐይ አሳታሚና /ኮሎኔል መንግሥቱ ) (ሊያነቡት የሚገባ )::

2 ..... Professor Donald N. Levine, Addis Voice, Wednesday, February 1, 2012 @ 05:02 PM ed. Illegal PDF of Mengistu Haile Mariams Memoir.

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Jul 06, 2012 5:25 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ነገደ -አርበኛ ዘዋርካ :-

አቶ ነብዩ ስብሐት (የኢሕአፓ አባል የነበሩ ) ስላዘጋጁት ' ትውልድ ድረ -ገፅ ' በኢሣት ቴሌቪዥን ማብራሪያ አቅርበዋል :: በእኔ አስተያዬት የጀመሩት በጎ ሥራ የዚያን ዘመን ታሪክ በተገቢው መንገድ ለመገንዘብ የመጀመሪያ ትክክለኛ ዕርምጃ ነው ብዬ አምናለሁ : ተከታተሏቸው ::

ምንጭ :- ESATelevision, Published on Jun 30, 2012. ESAT Ato Nesibu Sibehat July 2012 yatewlde web page Ethiopia.

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5
Page 5 of 5

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia