WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ርዕስ ያልወጣለት
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8, 9  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ጌታ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Apr 2005
Posts: 3226
Location: ዶሮ ተራ

PostPosted: Sun May 04, 2008 8:51 am    Post subject: Reply with quote

'ዋት ኮኢንሲደንስ ? እኔም እኮ በጥዋት የተነሳሁት ወደዛው ወደ ቸርች ለመሄድ ነው ' በማለት 'ጆይን ባደርጋቹ ቅር ይላችኋል ?' ስላት ፊቷ ባንዴ ቅይርይር ሲል ተሰማኝ ::
_________________
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
30-73

ኮትኳች

Joined: 02 Oct 2007
Posts: 101

PostPosted: Sun May 04, 2008 10:16 am    Post subject: Reply with quote

በድንገት ከየት መጣ ሳይባል ውሻዋ ቦቢ ዘሎ ተከመረብኝ :: ወይኔ ወይኔ ድረሱልኝ ኧረ አስጥይኝ እያልኩ ጮህኩኝ :: እሷ አንተ ቦቢ ቦቢ ቦቢ ተነስ ከላዩ ላይ ብላ ልታስጥለኝ ጣረች ..... ልቤ ደክሞ አይኔ ተስለምልሞ ዝልፍልፍ ብዬ ወደቅኩ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ብራንጎናትርን

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Dec 2006
Posts: 608

PostPosted: Sun May 04, 2008 12:53 pm    Post subject: Reply with quote

ለካስ ብሌን በደንብ ታስተውለኝ ኖርዋል "እንዴ በሰላም ነው ? ፍዝዝ አልክሳ ? በሐሳብ የተዋጥክ ትመስላለህ " ስትለኝ ከገባሁበት የቀን ቅዠት ብንን አልኩ :: ዓይኖችዋ የሚስቁብኝ ከንፈሮችዋ ደግሞ የሆነ ተንኮል የሚሸርቡብኝ ይመስላሉ :: ዓይኖችዋ እንደ እንቁ ያበራሉ :: ከንፈሮችዋ የልብ ቅርጽ ሲኖራቸው ከእንጆሪ የቀሉ ናቸው :: አስጎመዡኝ :: ቦቢ ግድንግድ ቦቢ ያው እንደ ቀድሞው እስዋን እየተሻሻት ነው :: ሰውነቴንም ብፈትሽ የተሞነጫጨረ ነገር አጣሁበት :: የቀባጠርኩት እንግሊዝኛም በሀሳቤ ብቻ ነው :: "ድንቅ ነው " አልኩኝ በሆዴ :: "ምንድነው ይሄ ክፉ ክፉ የሚያሳስበኝ ነገር ?" እያልኩ ራሴን ጠየኩና ወደስዋ መለስ ብዬ "ቅር የማይልሽ ከሆነ የትኛው ቸርች ነው የምትሄጅው ?" አልክዋት ፈራ ተባ እያልኩ :: ውብ ፈገግታዋ ከመቼው በላይ እንደ ጠዋትዋ ጸሀይ እያበራብኝ ነው :: "ምነው ጥያቄ አበዛህሳ ?" ስትለኝ እንዴት ድንግጥ እንዳልኩ :: ሆኖም ሐሳቤን ሰብሰብ አደረኩና "ውይ ይቅርታ ...ቅር ካለሽ ተይው " ስላት ከሳቅ ጋር እየታገለች "እኔ የምሄድበት ቸርች የሀገር ፍቅር ትያትር ይባላል " ብላኝ አረፈችው :: ጥሩ አሹዋፊ ትመስላለች :: አሁን የቀልድዋን ይሁን የምርዋን የተገለጸልኝ ነገር የለም :: ብሌን ገጽታዋ በፈገግታ ተሞልቶ ወደ ፊት እየተራመደች ነው :: የኔ ከጎንዋ መኖር የረበሻት አይመስልም :: "ምነው ያንቺን ልብ በሰጠኝ " አልኩ በልቤ :: እኔና ብሌን መድረክ ላይ ሆነን የምናወራ ተዋንያኖች ይመስለኝም ጀመር :: የጀመርነውን ወሬ እንዳላቆረፍድ ፈራሁ :: ከስዋ ጋር ያልኝን ቆይታ እንደምንም ብዬ ማራዘም እንዳለብኝ ግን አውቄዋለሁ :: እናም ቀጥዬ ምን ማለት እንዳለብኝ እያሰላሰልኩና የዳሌዋን አወራረድ እያስተዋልኩ ከስዋ እኩል ራመድ ራመድ አልኩ -- ወደፊት ::
_________________
"The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መልከጻዲቅ

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Aug 2007
Posts: 675

PostPosted: Sun May 04, 2008 5:16 pm    Post subject: Reply with quote

ዳገቱን ጨርሰን ወደ ዋናው መንገድ ስንጠጋ ጎን ለጎን እንደ ፍቅረኞች ስንሄድ ያዩን አንዳንድ ልጆች ሲጠቃቀሱብን ታዘብኩና ኩራት ተሰማኝ :: እንደዛ ሲያደርጉም የእውነት ጔደኛዋ የሆንኩ ስለመሰለኝ ደስ አለኝ :: ከጎና ሆኜ መሄዴ በጣም ተስማማኝ :: ሳያት እሷም እንደተመቻት ስለተገነዘብኩ ""ምናለ ሀገሩ ሁሉ መንገድ በሆነልኝ "" ብዬ ተመኘሁ :: ""ምናለ ህንጻው ቤቱ ሱቁ ሁሉ ፈርሶ መንገድ ብቻ በሆነ እያልኩ ሳስብ ..........
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ብራንጎናትርን

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Dec 2006
Posts: 608

PostPosted: Sun May 04, 2008 5:27 pm    Post subject: Reply with quote

ድንገት ከሩቅ አንድ ላዳ ከተፍ አለች :: ብሌንም እጅዋን እያውለበለበች ላዳዋን አስቆመቻትና "ናሆም " በማለት ትንሹን ወንድምዋን ጠርታ ቦቢን ቤት እንዲያስገባውና ለናታቸው ደግሞ ላዳ ተሳፍራ መሄድዋን እንዲነግራቸው በመግለጽ ሸኘችው :: እኔንም በዓይኖችዋ ተሰናብታኝ ላዳ ውስጥ ገባች :: ቻው እንክዋ አላለችኝም :: እኔም የምላት አልነበረኝም :: ከላዳዋ ሹፌር ጋር የሚተዋወቁ ይመስላሉ :: መድረሻዋን ሳትነግረው ነው የተሳፈረችው :: "ምስጥ !" አልኩኝ መለሎ ቁመናዋን ላዳዋ ውስጥ ስታስገባ በንዴትና በስስት እየቃኘሁ :: "ወኔ ቢስ !" በማለት ራሴንም ተራገምኩ :: ተጠማሁዋት :: ተራብኩዋት በቆምኩበት :: ረዥሙን ጸጉርዋን ዘንፈል አድርጋ ወደ ሁዋላ ደግፍ ብላ ስትቀመጥ ቅናት ውስጤን ያቀጣጥለው ጀመር :: "የት አባትዋ ነው የምትሄደው ? ቸርች ያውም የሀገር ፍቅር ትያትር ነው የምሄደው አላለችኝም ? እውን ሀገር ፍቅር ነው ምትሄደው ወይንስ ስትደልለኝ ነው ? በዚህ ጠዋት ደግሞ ሀገር ፍቅር ምን የሚሉት ትያትር አለ ?" እያልኩ ከራሴ ጋር እጨቃጨቃለሁ :: በዚህ መሀል ላዳዋ ዓይኖቼ እያዩዋት እዚያው በቆምኩበት ጥላኝ ጢስዋን ልክ ግሥላ እንደሚያጨስ ሰው ቡልቅ ቡልቅ እያደረገች ወደፊት ከነፈች :: ብሌኔን ይዛ በረረች :: እየራቀች በሄደች ቁጥር ብሌንዬን የማግኘት ተስፋዬም እየራቀኝ የሄደ መሰለኝ :: በቆምኩበት ፈዝዤ ቀረሁ ::
_________________
"The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መልከጻዲቅ

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Aug 2007
Posts: 675

PostPosted: Sun May 04, 2008 6:05 pm    Post subject: Reply with quote

""ይድፋህ "" አልኩት ባለላዳውን :: ""ስምህን ለፍታት ቄስ ይጥራው "" ላዳህን ፍሬኑ የተበጠሰ ትሬንታ ኴትሮ ተንደርድሮ መጥቶ ይግጫት ደሞም ግጭቶ እንደ ጠላ ጣሳ ያጨራምታት "" አልኩት :: ምኗም ይሁን ምን እጄ የገባውን ደስታ ስለወሰደብኝ አብሽቆኛል :: በቆምኩበት ሆኜ የላዳዋ ጎማ እንዲፈነዳ ወይም ደግሞ ቤንዚኗ አልቆ ተፍገምግማ እንድትቆም ጥብቅ ጸሎት ያዝኩ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ብራንጎናትርን

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Dec 2006
Posts: 608

PostPosted: Sun May 04, 2008 6:09 pm    Post subject: Reply with quote

ሆኖም ለላዳዋ ክፉ መመኘቴ ለብሌን እንደተመኘሁ አድርጌ ስለቆጠርኩትና ተገቢ አለመሆኑንም ስለተረዳሁ ለላዳዋ ያሰብኩትን ሁሉ ለራሴ እንዲያደርገው እጸልይና እመኝ ጀመር :: "ሆሆይ ተው ጌታዬ በጎ በጎ አሳስበኝ " በማለት ወደ ሰማዩ ተመለከትኩ :: መለስ ብዬም "እስዋም አትሙት እኔም ልኑር :: የፍቅርዋ ራብ ብቻ የሚገድል ከሆነ ይግደለኝ :: አይ ሞት ለማንም አይበጅ :: ህይወትን ገና መች አጣጣምኩዋትና ?" በማለት ራሴን አጽናናም ጀመር :: መላቅጥዋ የጠፋባት ደንባራ በቅሎ እመስላለሁ አስተውሎ ላየኝ :: ዞር ስል ናሆም ቦቢን እያባረረ የመጣበትን ዳገት ቁልቁል ሲወርደው አየሁና አንድ ሐሳብ መጣልኝ ::
_________________
"The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መልከጻዲቅ

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Aug 2007
Posts: 675

PostPosted: Sun May 04, 2008 6:54 pm    Post subject: Reply with quote

ብሌንን ባለአራት እግሩ ሰውዬ ጠልፎብኝ ስለሄደ ሞቱን ብመኝለትም ሳስበው ደግሞ ለካ ብሌንም አብራው ነች Exclamation በቃ ይሁን አሁን እንኴን አይሙት .....ቀኑ ሲደርስ ራሱ ይሞታት የለ አልኩና ታናሽ ወንድሟ ናሆም የሄደበትን አቅጣጫ ተከትዬ ሄድኩ :: ምን እንደምለው ግን እኔም አላውቅም ብቻ ሄድኩ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ብራንጎናትርን

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Dec 2006
Posts: 608

PostPosted: Sun May 04, 2008 7:10 pm    Post subject: Reply with quote

ድንገት ሳላስበው "እስራኤል " የሚል ያልጠበቁት የሴት ድምጽ ተጣራኝ :: ሳልዞር ማን እንደሆነች ስላወቅኩ "እቺ ደግሞ ምን አባትዋ እዚህ ሰፈር ትሰራለች ?" አልኩ ብግን ብዬ :: ዞሬ አየሁዋት :: የበፊት ጉዋደኛዬ ቤዛዊት ነች :: አጠር ብላ የደስ ደስ ያላት ሆኖም በምላስዋ እሳት የምትተፋ ቆንጆ ሴት ነች :: ለስድስት ወራት እንዴት አብረን እንደዘለቅን እስከዛሬ ይገርመኛል :: በቁንጅናቸው የሚመኩ ሴቶች ቢኖሩ ቤዛዊት ቀዳሚ ነች :: ፍንጭት ጥርስዋን ብልጭ እያደረገች መጥታ ተጠመጠመችብኝ :: በርቀት ከሚታየው ሙዚቃ ቤት "አይ ዘንድሮ ....አወይ ዛሬ ....አቤት ውበት እንዴት በዝትዋል ....ስንቱን ቆጥሮ ይዘለቃል ....ጠይም ቢታይ ...ቆንጆ ቆንጆ ....ጥቁር ቢባል ....ቆንጆ ቆንጆ ....አጭር ቢታይ ....ቆንጆ ቆንጆ ....ሎጋም ቢባል ...ቆንጆ ቆንጆ " የሚለው የሚካኤል ዘፈን ሰፈሩን አድምቆታል ::
_________________
"The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መልከጻዲቅ

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Aug 2007
Posts: 675

PostPosted: Mon May 05, 2008 7:28 am    Post subject: Reply with quote

""አዬ ቤዛዊት አንቺ የጉራጌ ሚጥሚጣ ....አንቺ የመድሀኒት ብልቃጥ "" አልኴት በልቤ :: ያለፈው የግንኙነታችን ትዝታ ባእምሮዬ ተሳለ :: የቤዛዊት ያልተለመደ ሰላምታ ግን ይበልጥ አስገረመኝ :: ቤዛዊትን ሳውቃት እንዲህ አልነበረችም :: በእርግጥ ተፈጥሮ የቸራት ውበት ቢኖራትም ጸባየ -ጨበሬ ስለመሆኗ ምስክር መጥራት አያስፈልገኝም :: እንዴት እንደተለያየን የራሱ የሆነ ረጅም ታሪክ ቢኖረውም ሁሉንም ነገር ረስታ ተነፋፍቀው እንደከረሙ ጔደኛሞች መጥታ ስትጠመጠብኝ ባለፉት ስድስት ወራት ስለቤዛዊት ያልተገነዘብኩትን አንድ ነገር አወኩ :: ቤዛዊት ትንጫጫለች እንጂ ቅንና ልበ ሩህሩህ ናት :: ስለሷ ይህንን ሳስብ የሀዘንም የመገረምም ስሜት ተቀላቀለብኝ :: ከማዶ የሚመጣው ሙዚቃ ስልቱን እየለዋወጠ አሁንም ቀጥሏል ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ብራንጎናትርን

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Dec 2006
Posts: 608

PostPosted: Mon May 05, 2008 2:30 pm    Post subject: Reply with quote

"እስሪሽ እዚህ ሰፈር የሚያመጣ ምን ነገር ተገኘ ?" አለችኝ በጥርጣሬና በመገረም እየተመለከተችኝ :: "ምን አለ ብለሽ ነው ? እንደው ያጋጣሚ ነገር ሆኖ እግር ጥሎኝ እንጂ " አልኩዋት ሌላ ጥያቄ እንዳትጠይቀኝ በልቤ እየተመኘሁ :: ናሆም ካይኔ ተሰውርዋል :: በልቤ ረገምኩዋት :: "አሁን ምናለ ቻው ብላኝ ብትሄድ " ስልም አሰብኩ :: ሆኖም እስዋ አይደለም ቻው ልትል "ሻይ ቡና ልበልሀ :: መቼም ያንተ ኩራት ካቅምህ በላይ ነው " በማለት እያሽሙዋጠጠች ወደ አቅራቢያው ኬክ ቤት ይዛኝ ሄደች :: በውስጤ ግን የማስበው ከዚህ በሁዋላ እንዴት አድርጌ ብሌንን እንደማገኛት ነው ::
_________________
"The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጦምኔው

ውሃ አጠጪ

Joined: 14 Jan 2007
Posts: 1433
Location: Right here

PostPosted: Mon May 05, 2008 6:44 pm    Post subject: Reply with quote

" ምነው እስርሽ ሀሳብ የገባህ ትመስላለህ ?' አለችኝ ቤዛ ገና ከካፌው ገብተን ወንበር ስበን እንደተቀመጥን ::

" ምን ? አይ ደህና ነኝ " አልኳት ስለብሌን እያሰብኩ ከነበረበት የቀን ቅዠት ብንን ብዬ

" እንዴ ወንበር እንኳን እኮ እኔ ነኝ የሳብኩልህ :: ወይ ተገላቢጦሽ "

" ጀመረች ደሞ ይህንን ንዝነዛዋን " አልኩ በልቤ :: ምነው አሁን ብትተወኝና አርፌ ባስብበት :; ድሮም ይኸው ያለቦታዋ መገኘቷ ነው ከኔ ያለያያት ::

" እኔ የምልህ ....." አለችኝ ቤዛ ዓይን ዓይኔን እያየችኝ ;; ዓይኗ እንዲህ ያምር ነበር እንዴ ያኔ ድሮ ? ከሷ እና ከብሌንዬ ዓይን የማን ያምር ይሆን ? ከብሌን ጋር ተቀምጦ ማውራቱ የሚሰጠኝን ደስታ እያሰላሰልኩ አብሬያት መሆንን ተመኘሁ ::

" ?" አልኳት ቶሎ ነግራኝ ብገላገል ብዬ :; ካፌው ውስጥ የአስቴር " የኔ ውብ አበባ እንደድሯችን " የሚለው ዘፈን በስሱ ተለቋአል :: በዚህ መሀል አንዲት ጠየም ያለች አስተናጋጅ መጣችና " ምን ልታዘዝ " አለችን :: እኔና ቤዛ አንቺ ቅደሚ አንተ ቅደም በመባባል ዓይነት ስሜት ለደቂቃዎች ተያየን "" አስተናጋጇ ደግማ " ተመልሸ ልምጣ ይሆን ?" አለችን ትህትና በተመላበት ድምጽ "

" መልካም የኔ እመቤት " ስላት ተመልሳ ወደ ባሬስታው ሄዳ ታንሾካሹክ ጀመር :: ከዚያም ሁለቱም ይስቁ ጀመር ::

" የማናት መንቃራ !" ቤዛ ነበረች ;:: " ምን እንዲህ ያረጋታል ? ታውቃታለህ እንዴ ? በዓይኗ አንስታ አፈረጠችኝ እኮ :: ሞዛዛ :: ልኳን ነበር ማስገባት "

" ምን ?' ማለት የቻልኩት ይህንን ብቻ ነበር ::
_________________
http://www.youtube.com/watch?v=_jIwsS_eT5w

http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=22540&start=105
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ብራንጎናትርን

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Dec 2006
Posts: 608

PostPosted: Mon May 05, 2008 7:10 pm    Post subject: Reply with quote

አስተናጋጅዋ ቤዛዊትን አብሽቂ ተብላ የተመከረች ይመስል ብዙም ሳትቆይ ተመልሳ መጣች ::

"አሁንስ ለማዘዝ ዝግጁ ናችሁ ?"

"እንዴ ...ምነው አንቺ ትንፋሽ ስጭና !" ቤዛዊት ነች ::

"ይቅርታ ... በቃ እሺ ስትዘጋጁ ጥሩኝ " በማለት ተመልሳ ሄደች -- አስተናጋጅዋ :: የበሸቀች ትመስላለች ::

አሳዘነችኝ :: ወይ ዳሌ ሰጥትዋታል :: ቁመናዋም ከቤዛ ሻል ያለ ነው :: የቤዛዊት መገለማመጥ አይጣል ነው :: በዓይንዋ እንደ ቀንደኛ ላም አስተናጋጅዋን ወጋጋቻት :: እኔ ግን አስተናጋጅዋ አሁንም ቶሎ ተመልሳ እንድትመጣ ተመኘሁ :: ቤዛዊት ወሬ ከያዘች የምትለቅ ጉድ አይደለችም :: በዚያ ላይ ትሞታታለች እንጂ ለጠየቀችው ጥያቄ መልስ ሳይሰጣት የሚንቀሳቀስ የለም :: አስተናጋጅዋ ያስቴርን ክር "ወሴ ባሳ " በሚለው የጉራግኛ ዘፈን ተካችው :: "ድንቅ ነው " አልኩኝ በሆዴ ሳቅ እየወጠረኝ :: ሴት ለሴት አይጣል ነው መቼስ ::

"እኔ የምልህ ..." አለችና ንዝንዝዋን ጀመረች -- አስተናጋጅዋን በጥላቻ እያየቻት ::

"እህ ..." አልኩዋት ሰልቸት ብዬ ::
_________________
"The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጦምኔው

ውሃ አጠጪ

Joined: 14 Jan 2007
Posts: 1433
Location: Right here

PostPosted: Mon May 05, 2008 7:50 pm    Post subject: Reply with quote

" ባለፈው የጠየቁህን እንዴት አደረግኸው ?" እጄን ከጠረጴዛው ላይ አፈፍ አድርጋ ትደባብሰኝ ጀመር :: ቆረቆረችኝ ::

" የቱን ?" አልኳት ለመጨረሻ ጊዜ ከርሷ ጋር ያወራሁበትን ቀን ለማስታወስ እየሞከርኩ :: በመሀል እጄን ከጇ ገላለገኝ -ስልኬ :;

ከኪሴ ሳወጣው ሚሚ ነች :: ያቺ ከውካዋ ታናሽ እህቴ :: ደሞ ምን ፈልጋ ነው ? ያው የተለመደውን የደብተር መግዣ አምጣ ነው :; ከየታባቴ አመጣላታለሁ ? ነገር ግን እንደዛሬ ውለታ ውላልኝ አታውቅም :: ከዚህች ነዝናዛ እዬዬ የሷን "ብር አምጣ " ወደድኩት - ለመጀመሪያ ጊዜ ::

" ይቅርታ ቤዝ ሲስተር ናት " አልኳት እና ስልኩን አነሳሁት :: " ሄለው ?"
_________________
http://www.youtube.com/watch?v=_jIwsS_eT5w

http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=22540&start=105
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ብራንጎናትርን

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Dec 2006
Posts: 608

PostPosted: Mon May 05, 2008 8:45 pm    Post subject: Reply with quote

"ሰላም ወንድም ጋሼ ? ደህና ነህልኝ ?"

አቤት ልስላሴ :: የኔን ልብ ለማባባት ስታውቅበት ::

"እሺ ሚሚዬ ምን ፈልገሽ ነው ?" አልኩዋት ምን እንደምትፈልግ ቢገባኝም ::

"የሆነች ቤቲ የምትባል ልጅ ደውላ እንዲደውልልኝ ንገሪው ብላኝ ነው ::" ወይ ተዓምር እስዋ ደግሞ ምን ፈልጋ ነው ? ዛሬ ከየት አባታቸው ሁሉም ብቅ አሉ ? ሆሆ ... አወይ መዓልቲ ::

"እሺ ሚሚዬ እደውላለሁ ::" አልኩዋት ቤዛ ለማን እንደምደውል እንዳታውቅ ስለፈለኩ ::

" ... ወንድም ጋሼ " አለች የኔዋ ሚጥሚጣ ::

"እሺ ....በቃኮ መልክቱን ነገርሽኝ :: ስልኩን ዝጊው ::" አልኩዋት ሌላ ጣጣ እንዳትጠይቀኝ ፈርቼ ::

"ትምህርት ቤት አምስት ብር አምጡ ተብለናል :: ማሚ ደግሞ ወንድምሽን ጠይቂው አለችኝ ::" የህቴ ጣጣ ማብቂያ የለውም :: ቤዛ እየተቁነጠነጠች ነው :: እህቴ አጠገቤ ብትኖር እንደምታጮላት ነው ::

"እቤት ተመልሼ ስመጣ ሰጥሻለሁ " አልኩዋት :: እህቴ ስልኩ ላይ ስትፍለቀለቅ ይታየኛል :: ዬኔ ውሸትዋን ነው :: ከጉዋደኞችዋ ጋር ለመዝናናት ስትፈልግ ሰበብ አስባብ ፈጥራ ኪሴን ማራቆት ይሆንላታል ::

"ያንተ ቤት ሰዎች ደግሞ ነጻ ሀገር ውስጥ እየኖሩ ስለ ነጻነት የሚያውቁ አይመስሉም :: በሄድክበት ሁሉ በሞባይል አንተን ማሩዋሩዋጥ ነው ስራቸው ::" ቤዛ ናት :: ሁሌም እንዲህ እንዳማረረች ነው :: በዚህ ጉዳይ እኔና እስዋ ብዙ ተጨቃጭቀንበታል :: የመለያየታችን ተጠቃሽ ምክንያት ሊሆንም ይችላል :: ስልኩን ዘግቼ ኪሴ ውስጥ እንደ ከተትኩ እጆቼን ከጠረጴዛው ላይ ስባ ጣቶቼን በጣቶችዋ ታፍተለትላቸው ጀመር :: የልብ ምቴ ሲጨምር ይሰማኛል :: የመዳፍዋ ልስላሴ የድሮ የኔና የስዋን ያልጋ ውስጥ ትዝታ ቀሰቀሰብኝ ::

የቅድሙን ጥያቄ ደግማ ሳታነሳ አስተናጋጅዋን ቆንጆ በዓይኔ ጠራሁዋት ::
_________________
"The purpose of education is not to fill buckets, but to light fires." – Yeats
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8, 9  Next
Page 3 of 9

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia