WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ርዕስ ያልወጣለት
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8, 9
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

View previous topic :: View next topic  
Author Message
መልከጻዲቅ

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Aug 2007
Posts: 675

PostPosted: Thu Dec 25, 2008 5:52 am    Post subject: Reply with quote

ልጅቷ የሄደችበትን መንገድ ተከትዬ ብሄድ አቌራጭ እንዳለ አውቃለሁ :: ግን ያንን ባደርግ እሷን የተከተልኴት መስሎ እንዲሰማት ማድረግ ስለመሰለኝ ተውኩት :: ተወድጃለሁ ብላ የልብ ልብ እንዲሰማትና ምናልባትም በለስ ቀንቶኝ እንኴን ግኑኝነት ብንጀምር እንደ ሚዳቌ እየዘለለች እንድታስቸግረኝ አልፈለኩም :: በዚህ የልሂድ ልቅር የሀሳብ ማእበል እንዳለሁ ግን የፍርሀት ጩሀት የሰማሁ ስለመሰለኝ አይኖቼን የጆሮዬ አንቴና ወዳመለከተኝ ቦታ አዞርኴቸው :: አልተሳሳትኩም :: እኔ ወዳለሁበት አቅጣጫ ነፍስ ይዞት እየበረረ የሚመጣ ሀይልና አባራሪው ጥርት ብለው ታዩኝ :: ባንድ በኩል ውስጤ በፍርሀት ቢርድም በሌላ በኩል ደግሞ ድንጋጤው በፈጠረልኝ ጊዜያዊ ጉልበት እየተንደረደረ የሚመጣውን ሀይል ለመጋፈጥ ወሰንኩ :: ሁኔታው ምናልባት "ያላሰብኩትን ሲሳይ እጄ ያስገባዋል አለያም ደግሞ መሳለቂያና መሳቂያ አድርጎና አዋርዶ ያንድ ሰሞን የአቦል ቡና መጠጫ ያደርገኛል " እያልኩ ባለሁበት ሁኔታ እጄን መንጭቃ የሄደችው ልጅና ዉዉዉ ....እያለ የሚያባርራት ጥርሳም ውሻ ከቆምኩበት ቦታ ለመድረስ የቀራቸው የሶስት እርምጃ ርቀት ነበር ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መልከጻዲቅ

ዋና ኮትኳች

Joined: 08 Aug 2007
Posts: 675

PostPosted: Sun Dec 28, 2008 7:03 am    Post subject: Reply with quote

ልጅቷ የሸሚዝ ቁልፎቿ ተከፍተው እጆቿን የቄብ ዶሮ ሸለምጥማጥ ስታይ ክንፎቿን ጥላ እንደምትከንፈው ሁሉ ወደኔ ስትበር በመብረቃዊ ቅጽበት ባይነ ውሀዋ ውስጥ አንድ ነገር ያነበብኩ መሰለኝ :: "" አድነኝ !! ከዚህ ሞት አድነኝ እንጂ ሁሌም ያንተ ነኝ !!!"" የሚል አጭር መልእክት :: ለኔም ለሷም የሚሆን ምንም ጊዜ አልተረፈኝም :: አጠገቤ የነበረውን ሹል ድንጋይ ሳነሳና "" መቻል ተው መቻል አንተ መቻል እስኪ ንካትና ሞክረኝ !!"" የሚል የአንድ ሰው ድምጽ ስሰማ አንድ ሆነ :: ድምጹ ከሰማይ መላእኩ ገብርኤል ከእግዚአብሄር ታዞ የተናገረው መሰለኝ :: አቡነ ገብረ መነፈስ ቅዱስም መሰሉኝ :: ግን በመላክታቱ ፋንታ መቻልን የጠሩት ጠና ያሉ የሌባ መምቻ የሚመስል ዱላ የያዙ ሴት ወይዘሮ ናቸው :: መቻል ብለው የጠሩት አስፈሪ ውሻቸው ድምጻቸውን ሲሰማ ጥርሱን ወደ ሰገባው እንደ ማስመሪያ የቆመ ጭራውን ደግሞ ወደ እግሩ ውስጥ ሲሸጉጥ ልቤ አረፈች :: እፎይ አልኩ :: ውስጤ ሊፈነዳ ነበር :: ባለቤትየዋ መቻልን ዱላ ባልያዘ እጃቸው ይዘው "" አይዞሽ ልጄ አይዞሽ አስደነገጠሽ አይደለ እሱኮ ለማዳ ነው አንዳንዴ ሰው ሲያይ እንዲህ ያደርገዋል እንጂ ...."" አያሉ ሲያጽናኗት በግማሽ ልቤ ነበር የማደምጣቸው :: ሴትየዋ ይህን ካሉ በኌላ መቻል ውሻቸውን ይዘው ሽቅብ ሲወጡ ባይኔ መከተሌን እንጂ ልጅት ድንጋይ ያልያዘውን እጄን አንቃ መያዟን እንኴን አላስተዋልኩም ነበር ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጦምኔው

ውሃ አጠጪ

Joined: 14 Jan 2007
Posts: 1433
Location: Right here

PostPosted: Thu May 24, 2012 10:09 pm    Post subject: Reply with quote

እጇ እጄ ላይ ማረፉን እንዳየው የሰውነቴ የደም ፍሰት የቆመ መሰለኝ :: ሁሉ ነገር ጸጥ አለብኝ :: ከእጇ ወደ እኔ እጅ የሚነዝር ዓይነት ነገር ይተላለፍ ነበር :: ልቤ በአንድ ጊዜ በፍጥነት እና በቀስታ የሚመታ መሰለኝ :: ልጅቱ ቁና ቁና ትተነፍሳለች :: እኔም እንደሷው ትንፋሼን መቆጣጠር አልቻልኩም :: ከሆኑ ደቂቃዎች ወይም ሰአታት ወይም ቀናይ በኍላ ልጅቱ እጇን ከእጄ መንጭቃ ፈገግ አለች :: የሀፍረት ዓይነት ፈገግታ :: እኔም ፈገግ አልኩላት እና ልናገር ሞከርኩ :: ቃላቱ የታባታቸው እንደገቡ እንጃ የምለው ሁሉ ጠፋብኝ ::

"ያምሮት " ብላ እጇን ለመጨበጥ ዘረጋችልኝ ::

እኔም እጄን ዘረጋሁላት :: ከአፌ የወጣው ቃል ግን "....." የሚል ብቻ ነው ::

እንተጋገዝ እስኪ ጃል ይህቺ ጨዋታ ላይ ..ከዓመታት በኍላ ....
_________________
http://www.youtube.com/watch?v=_jIwsS_eT5w

http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=22540&start=105
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8, 9
Page 9 of 9

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia