WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የኢትዮጵያ አንድ ብር ላይ ያለው "ልጅ " በአድማስ ሬዲዮ ...
Goto page Previous  1, 2, 3, ... 16, 17, 18  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
Monica****

ዋና አለቃ

Joined: 26 Dec 2003
Posts: 3937
Location: 999 Total eclipse st. Venus

PostPosted: Tue Jul 22, 2008 7:18 pm    Post subject: Reply with quote

Is it tianes or tetanus? Tetanus is more appropriated name for you if you ask me!!!! Rolling Eyes Anyway..... who ever you are........የሆንክ የወያኔ አጫፋሪ ነገር ትመስላለህ !!!!
ከዚህ በፊት ስለቴዲ ብዙ ተብሏል ብዙ ብያለሁ .....እና ለምን እንደዛ እንዳልኩ እንደመጠየቅ ፋንታ you came to conclusion ቅል ራስ ለመሆኔ !!! Evil or Very Mad
የተገጨው ስው ከቴዲ ያንሳል ወይም ቴዲ ከሱ ይበልጣል አላልኩም .....since no one is above the law.
ቅል እራስ እንዳንተ ያለው ሪያሊቲንና ፋንታሲን መለየት ያቃተው ለጥቅም ፍትህን የሽጠ ነው እና ....you need time to reflect before you throw a stone at others.
ኡፍ ስንት አይነት ስው አለ !!!!
tianes እንደጻፈ(ች)ው:

!

ይቺ ቅል ራስ ነገሩን ያየችው፣ ከዘፈን ቀረብኝ መአዘን ነው። ከግል ጥቅሙዋ አንጻር። ከጥቅም አንጻር ስናየው የቴዲ ቲፎዞች ልክ ናቸው። ከጥቅም አንጻር እናንተም አልተሳሳታችሁም። እኔም በናንተ ቦታ ብሆን ከእውነት ይልቅ አድማጮቼ መስማት የሚፈልጉትን የማቀርብ ይመስለኛል። መገለል፣ መክሰር፣ መሰደብ ስለምፈራ። ፈሪ ይኖራል። እየሞተም ቢሆን ይኖራል። እናንተ እንደምትኖሩት ይኖራል።

_________________
Yesterday is history, tomorrow is mystery, but today is a gift and that is why they call it the present!!!

Last edited by Monica**** on Tue Jul 22, 2008 7:28 pm; edited 2 times in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Monica****

ዋና አለቃ

Joined: 26 Dec 2003
Posts: 3937
Location: 999 Total eclipse st. Venus

PostPosted: Tue Jul 22, 2008 7:25 pm    Post subject: Reply with quote

Idea Idea
_________________
Yesterday is history, tomorrow is mystery, but today is a gift and that is why they call it the present!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሾተል

ዋና አለቃ

Joined: 13 Jan 2005
Posts: 6808
Location: Vienna-Austria

PostPosted: Tue Jul 22, 2008 7:50 pm    Post subject: Reply with quote

[quote="tianes"]
Quote:
እውነት ቴዲ አፍሮ ያንን ድሀ ገጭቶት ከሆነ የኢትዮዽያ የህግ አንቀጽ በሚለው ይፈረድበት :: መገደልም ከሆነ በፈላ ዉሀ ይቀቅሉት ::

Quote:

ባንተ አልፈርድም። ከላይ የጠቀስከው እንደህብረተ ሰብ ምን ያህል መዝቀጣችንን ያሳያል። ባንተ ዐይን ፍትህ ማለት በፈላ ውሀ ውስጥ ከትቶ መቀቀል ነው።

ወደዘለፋ አትቁጠረውና እስከስንተኛ ክፍል ተምረኻል ወይስ የማገናዘብ ችሎታህ የቱን ያህል ነው ?ለማገናዘብ የግድ ትምህርት አያስፈልግም ...በተፈጥሮም የበሰሉ አገናዛቢዎች አሉ ::የገጠሪቱ ኢትዮዽያ ህዝቦች ለዛውም ሳይማሩ እኛ ተማርንና አወቅነው ከምንለው ይበልጡናል ...ግን ማንበብና መጻፍ እንደምትችል ያው ጽፈህ መልሼ ጽፌልህ አንብበህ እንደጻፍከው ፕሩቭ ሳላደረኩት ምን አልባት አንብቦ መረዳት ላይ ችግር ሊኖርብህ ይችላል ::እስቲ ያጣቀስከውን ነገር ደጋግመህ አንብበው ::ወደየት ሸተት ሸተት ነው ::እኔ ያልኩት ቴዲ አፍሮ ጥፋተኛ ሆኖ እንደገና የኢትዮዽያ ህገመንግስት በመኪና የሰውን ልጅ የሚያክል ነገር ገሎ የሄደንን ሰው ወንጀለኛ ነው ብሎ ካረጋገጠና ህጉ ላይ ሰውን እስከመቀቀል የሚያስቀጣ ከሆነ ይቀቅሉት ግን ልጁ ወንጀለኛ ናይደለምና መታሰር የለበትም ...ግን የታሰረው በፖለቲካኛ ስለተጣላቸው ሊበቀሉት ነው ነው ::እና ጥፋተኛ ከሆነና ህጉ ላይ ያጠፋ በመቀቀል ይቀጣ የሚል ከሆነ ነውና ይሄንን ነገር በቀይ እስክርቢቶ አስምረኽልኝ ግድግዳህ ላይ ለጥፍና እንደጌጥ ተጠቀምበት ::አይምሮህ ይስራ ...ፍየል ወደዚህ ቅምዝምዝ ወደዚያ አይሁን ...ወያኔዎችና ዼንጤዎች ናቸው መላ ሀሳቡንና ጽሁፉን ሳይሆን ጥቅስ ብቻ እየመረጡ ሰውን የሚያሳስቱት ወይም ሚወነጅሉት ...አንተም ያው የነሱ ስለሆንክ ያንኑ ነው እያደረክ ያለኸው ::ይቅርታ እውነትን በግድ ስላጋትኩህ ::
ደግሞ በኢትዮዽያ ህገ መንግስት ውስጥ የሞት ፍርድም አለ ...እንዲመቻችሁ አድርጋችሁ ጠላታችን ናቸው ያላችሁትን በሞት ለመቅጣት የጻፋችሁት ህግ ነው ::ነገ ለናንተም እንደሚሰራ እንዳትረሱ ::
እና ሰውን የገደለ ወንጀለኛ በመግደል ታላቅዋ አሜሪካም ትቀጣለች ...ስንዴ ለተራበው ህዝባችን ስትልክ ስንዴውን ሸጣችሁ መሳሪያ እየገዛችሁበት ህዝባችንን እየጨረሳችሁና ጎረቤት አገሮች ጋር እያጣላችሁን የዘላለም እየቆየ የሚፈነዳ ፈንጅ በትውልዱ ላይ አጥምዳችሁበት ተገኛችሁ እንጂ ....
አንድ አገር በህግ ትተዳደራለች ...ህጉ ደግሞ ጨካኝ ሆኖ ወንጀለኛን በሞት ከቀጣና ያንን ህግ ፓርላመንቱ ካጸደቀ ምን ያስደንቃል ....ግን እውነተኛ ፓርላመንት ህዝብ ያጸደቀው ከሆነ ያው ጨካኙ ህዝቡም ጭምር ነው :.የት ነው ያለኸው ግን ?
ቴዲ ወንጀለኛ አይደለም ...የፖለቲካ እስረኛ ነው ...ቴዲ ድሀውን ልጅ አልገጨም ....መቶ ነጥብ ....ደም ተንጠባጥቦባችሁ አዙሯችሁ እለቁና ...

Quote:
የራስክን ሀቀኝኘነት ለማስመስከር ያን ያህል ግፍ በወገንህ ላይ ለመፈጸም ትጨክናልህ። አንዲህ አይነት ግፍ በደርግ ጊዜ ተፈጽሟል . ፈጻሚዎቹ አንግዲህ ያንተ አይነቱ አረመኔ አንደነበሩ አያጠያይቅም .

አቤት አሁንም ፍየል ወደዚህ ቅምዝምዝ ወደዛ ....ደግሞ ደርግ ከወያኔ የበለጠ አፋኝ መሰሪ ገዳይ መንግስት ሆነ ?ጉድ ነው ::ደርግ 17 አመት ውስጥ ካፈነውና ከገደለው የናንተ በለጠ እኮ ...ምን ሆንክ ....ለእኔ እንኩዋን ደርግ አይደለም ሀይለስላሴም ወያኔም ሁሉም አንድ ናቸው ::ሁሉም ያው ነው : አንተው :.እኔ ደርግም አይደለሁም ,ወያኔም አይደለሁም ,ቅንጅትም አይደለሁም ,ኦነግም አይደለሁም ...እኔ አባተ ደጀኔ ወይም ሾተል አንድ ተራ ሰው ነኝ ...በነጻነት የምኖር ...ነጻ ሆኜመኖር የምፈልግና ለአገሬ ሰላምን የምመኝ ....በዘወትር ጸሎቴ አገሬን የማስብ ....ህመምዋ የሚሰማኝ ...እርዛትዋ እኔንም የሚበርደኝ ..ጥሙዋ የሚያሳርረኝ ...እራብዋ የሚሞረሙረኝ በቃ ተራ ኦስትሪያ ውስጥ የምኖር ሰው ነኝ ....በዘር ማንዘር ኢትዮዽያዊ ለወደፊቱ በዜግነት አውሮፓዊ የምሆን ወይም የማልሆን በቃ ዘረ ኢትዮዽያዊና እስከሞት ድረስ ስለእውነት የምለፈልፍ ሰው ነኝ ....ደርግም ወያኔም ለዘለአለም ገደል ይግቡ ::ግን ኢትዮዽያና ንጹህ ህዝቦችዋ ለዘላለም በሰላምና በብልጽግና ከጥሩ መሪ ጋር ይኑሩ ::ገባህ የምልህ ....ሳይገባህ ቅርና ::አትቀላቅል ....ወያኔን መከተል ማምለክ መብትህ ነው ::ታድያ ዲሞክራሲ ማለት የፈለግከውን መሆን ነው ::ወያኔ አስተዳደሩ ጥሩ ያልሆነ በሀይል የሚያምን ስለሆነና ክፋቱ አጥንት ድረስ ስለሚጠዘጥዝና ስለሚጨፈጭፍ እንጂ ያንን ትቶ በህዝብ ምርጫ ተመርጦ ህዝቡን እኩል አድርጎና አገር ሳይሰጥ የሚያስተዳድር ከሆነ ምን ገዶኝ ....በርግጥ ልለፍልፍ እንጂ ምንም ለውጥ እንደማላመጣ አውቃለሁ ...ግን የአይምሮ እርካታና አለኝ ....ያባቶቼን አደራ እንደመወጣትም ነው ::የምትከተለውም ማንም የለም እኮ ...ሁሉም ምለራሱ ነው ...ዲሞክራሲን ሳያውቅ ...የመናገር ነጻነትን ሳያውቅ ስለመናገር መጻፍ ነጻነት ይሰብክህና በነጻ ሀሳብህን ስትገልጽ ይቃወምሀል ...

Quote:
ወያኔ ምናምን አልክ , አሁን ያንተ አይነቱ ከወያኔ የሚለይበትን ማወቅ ብችል ደስ ይለኝ ነበር።

ከወያኔ የምለይበት ምን መሰለህ ....የምንም ፖለቲካ ደጋፊ አለመሆኔና ወያኔ ስለስራው ስለምቃወም ::እንዳንተ ያሉ ወያኔዎችን መንጥሬ ስለማወጣና ስህተትህን ስለምነግርህ ::ውሸት እንድትቀባጥር ስለማልፈቅድልህ ....ሆዳም መሆንህን ስለምነግርህ ...አንተማ ወያኔ ልትሆን አትችልም ....አንተ ምንድን ነህ መሰለህ ለሆድ አዳሪ አዛባ አጋሰስ ...ነገ ፊሽካ ነፍተው ቀይ ሲሰጡህ ሌላ ፖለቲካ ድርጅት ውስጥ ትገባና ወያኔን ስታወግዝ ትውላለህ ...ከዻዻሶቹ በልጠኽ እኔ የወያኔን ክፋት ምናምን አውቃለሁ ብለህ እንደ እውነተኛ ኤክስፐርት ትሰብካለህ ...እናይሀለን ...

Quote:
ቴዲን እንተርሰህ የሞጫጨርከው ሰው እንዲያጨበጭብልህ እንጂ ፍሬ ነግር እንደሌለው ሳታውቅ አትቀርም። ካዲያስፖራ ሚዲያ ባጠናከርከው ዜና ቴዲ ንጹህ ነው . ማስረጃ ማለት ላንተ , 'ኢቶ ዛረ ዜና ነው . ልዩነታችን አዛ ላይ ነው .

ምንድነው ምታወራው ...ታጨሳለኽ እንዴ ....ቀባጠርክ ...እኔ እኮ ሾተል ነኝ ...ከፈለክ ከጥቂቶች ጨዋዎች በስተቀር ዋርካዎችን ብዳቸው ወይም አስፈንድደው ይልቀቁብህ ...እኔ ሚያጨበጭብልኝን አልወድም ...ውዳሴ ከንቱን ለማጥፋት ስል ነው ከስንት ወዳጆቼ ጋር የተጣላሁት ...ምነው እኔን ካላወቅከኝ ከዛሬ ጀምሮ እወቀኝ ...እኔ ሰው እንዲያመሰግነኝ ሆነ እንዲያጨበጭብልኝ አልፈልግም ....ምኖረው ለህሊናዬ ነው ::ማንንም ደጋፊ አልፈልግም ...ለምን ብትል አለቅላቂ ብቻ ስለሆነ ...ሆዳም ለቀፈቱ የሚኖር ድቤ በተመታበት ፈሱን እያንዛረጠ ወደዛ ስለሚሄድ ....በራሱ የሚቆምበት እግር ስለሌለው ...ሚዛን የማይደፋ ሲንብሮ ሲንብሮ በነፈሰበት የሚወሰድ አለቅላቂ ብቻ ነው ያለውና ማንንም አልፈልግም ::ስለዚህ እዚህ እራሱ ቀላቅለሀል ...

Quote:
እንድተዛለፍከው ሆዳም እንኩዋን ብሆን በኒክ ስም፣ ብሳይበር ስፔስ እንደ ፓልቶከኞች የልቤን መጻፍ የሚከለክለኝ እንዴለለ አውቃለሁ። ስለዚህ ከንተ የተለይ ሀሳብ ያለውን ሁሉ ሆዳም፣ ወያኔ፣ ባንዳ አትበል። ብልግና ነው , ከገባህ ..

እንደዛ ያልኩህ እኮ ባንደር ከቨር ተመሳስለህ አልመጣህም ...አዲስ ምልምል ወያኔ ነህ መሰለኝ እንደወረድክ ዱብ አልካ :.እስቲ የጻፍከውን አንብበው ::ሰው ነው እንዴ የጻፈልኽ ?ይሄንንም የሀሳብ ነጻነት አልከው ?ሰው ያለጥፋቱ ተወንጅሎ ስለታሰረ ትክክል ነው ማለት የሀሳብ ነጻነት ነው ?ያው መርዝህን ለመንዛት ነው የመጣኸው ግን ባይሆን እውነቱን በግድም በውድም ትጋታለኽ ...ምንም ጊዜው ያንተ ቢሆንም ...

Quote:
በተረፈ ካንተ ጋር እንካ ስላምቲያ መጫወት ስለማልፈልግ በዚሁ እቁሜያልሁ።

ስለምከብድህ ነው አይደል ?ችግሩ መርዝ መርጨት እንጂ ያስተማሩህ የረጨኸውን መርዝ ሰው ተከላክሎ መልሶ ቢረጭብህ መከላከል አትችልም ...አጠገብህ ብሆን ያው በታጠቅከው ጊዜው ያንተ ነውና ግንባሬን ትለዋለኽ ...ግን ያው አጠገብህ ስላልሆንኩ የመልስ ምቱን መመለስ ሳትችል ስትቀር ጥቅስ ለይተህ እያወውጣህ ልትወነጅለን ሞከርክ ...የተለመደ የፋራ ውንጀላ ...የተበላበት ፋራነት ...ቡፍ ...አለች አሳንቴ ....

ለህሊናህ ኑር እንጂ ለሆድህ አታንቁዋልጥ ....

ሾተል ...................ማንንም ሳይወግን ለእውነት ሲል ውሸተኞችን የማያላውስ
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
www.shottel.webs.com

admasradio

ኮትኳች

Joined: 18 Mar 2008
Posts: 152

PostPosted: Tue Jul 22, 2008 9:18 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም በድጋሚ

ሁልጊዜም ቢሆን የአድማስ ሬዲዮ ባልደረቦች የሚሰራ ሰው ሊሳሳት እንደሚችል የምናምን - ስህተት ከሰራን ፈጥነን የምናርም እና አዋቂ ነን ባይ ተመጻዳቂዎች እንዳልሆንን ለማሳወቅ እንፈልጋለን ::

በማንኛውም መንገድ ከአድማጮች የሚስጡንን ምክሮች እና አስተያየቶች እንቀበላለን :: አላማችን ከአተካሮና ስም ከማጥፋት የወጣ ወቅታዊ መረጃና ትምህርት ማስተላለፍ ነው ::

ከአክብሮት ጋር
አድማስ ሬዲዮ
_________________
The #1 Ethiopian infotainment radio in USA

Every Saturday from 2-6 pm (Eastern time) @1100AM(Atlanta) .... or LIVE at www.admasradio.info or LIVE from your cell phone (951) 262 4343 code 193902#
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ኮሎኔል

ኮትኳች

Joined: 07 Apr 2006
Posts: 196
Location: zimbabwe

PostPosted: Tue Jul 22, 2008 10:11 pm    Post subject: Reply with quote

ወንድሜ tianes ጥቂት የግንዛቤ ስህተቶችን ያየሁ ቢሆንም ላቀረብከው ሀሳብ የተሰጡህ ምላሾች በቂ ሆነው ስላገኘኍችው እኔ ምንም ልጨምር አልፈለኩም ::
አየህ ወዳጄ ፍርድቤቱን ወይንም ዳኛውን ወይንም ደሞ መረጃ አሰባሳቢውን አልያም አቃቤ ህጉን በምታይበት አይን እስቲ ተከሳሹን ሥራውን ማንነቱን አቋሙን ተመልከት :: ትልቅ ልዩነት አላቸው ::
የልጁ አገልግሎትም ይህንንው ሀሰተኛ ስራቸውን መቃወም ነው :: ብዙ ለማለት ባልሻም የአሁኑን የአዲስ አበባውን ወህኒቤት ያጣበበው ወንጀለኛ ሳይሆን እውነተኛ ነው :: በከንቱ ደሙ የፈሰሰው በጎዳና ላይ የወደቀው ጎልማሳ ወጣትና አዛውንት ወንጀለኛ ሳይሆን ፍትህ ፈላጊው ነበር :: ይህንን አንተም የምትክደው አይመስለኝም ::
አይተን የማናውቀውን ፍትህ አሁን ልናይ ነው ማለትህ ከሆነ ይሁንልህ ::
ኢሀዴግ ከስንትናስንት ህዝብ ለደጉ ሞት አስቦ ክስ መሰረተ
ቢባል ያስቅ እንደሁ እንጂ አያስገርምም :: መቶ ሺህ ደጉዎች በወያኔ አረር ረግፈዋል :: ለእስርና ስቃይ ተዳርገዋል :: ስለዚህ ተወን እባክህ ውነት ከኢሀዴግ ዘንድ አለ ብለን ለማመን አይቻለንምና የፍትህን ቀን ከላይ እንድናገኝ አምላክ ይርዳን ::

አሜን
_________________
Ethiopia
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኮሎኔል

ኮትኳች

Joined: 07 Apr 2006
Posts: 196
Location: zimbabwe

PostPosted: Tue Jul 22, 2008 10:12 pm    Post subject: Reply with quote

ወንድሜ tianes ጥቂት የግንዛቤ ስህተቶችን ያየሁ ቢሆንም ላቀረብከው ሀሳብ የተሰጡህ ምላሾች በቂ ሆነው ስላገኘኍችው እኔ ምንም ልጨምር አልፈለኩም ::
አየህ ወዳጄ ፍርድቤቱን ወይንም ዳኛውን ወይንም ደሞ መረጃ አሰባሳቢውን አልያም አቃቤ ህጉን በምታይበት አይን እስቲ ተከሳሹን ሥራውን ማንነቱን አቋሙን ተመልከት :: ትልቅ ልዩነት አላቸው ::
የልጁ አገልግሎትም ይህንንው ሀሰተኛ ስራቸውን መቃወም ነው :: ብዙ ለማለት ባልሻም የአሁኑን የአዲስ አበባውን ወህኒቤት ያጣበበው ወንጀለኛ ሳይሆን እውነተኛ ነው :: በከንቱ ደሙ የፈሰሰው በጎዳና ላይ የወደቀው ጎልማሳ ወጣትና አዛውንት ወንጀለኛ ሳይሆን ፍትህ ፈላጊው ነበር :: ይህንን አንተም የምትክደው አይመስለኝም ::
አይተን የማናውቀውን ፍትህ አሁን ልናይ ነው ማለትህ ከሆነ ይሁንልህ ::
ኢሀዴግ ከስንትናስንት ህዝብ ለደጉ ሞት አስቦ ክስ መሰረተ
ቢባል ያስቅ እንደሁ እንጂ አያስገርምም :: መቶ ሺህ ደጉዎች በወያኔ አረር ረግፈዋል :: ለእስርና ስቃይ ተዳርገዋል :: ስለዚህ ተወን እባክህ ውነት ከኢሀዴግ ዘንድ አለ ብለን ለማመን አይቻለንምና የፍትህን ቀን ከላይ እንድናገኝ አምላክ ይርዳን ::

አሜን
_________________
Ethiopia
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
እህምም

አለቃ

Joined: 19 Dec 2005
Posts: 2392
Location: on a small rock; between an ocean and a sea.

PostPosted: Wed Jul 23, 2008 1:17 am    Post subject: Reply with quote

Quote:
አይተን የማናውቀውን ፍትህ አሁን ልናይ ነው ማለትህ ከሆነ ይሁንልህ ::
ኢሀዴግ ከስንትናስንት ህዝብ ለደጉ ሞት አስቦ ክስ መሰረተ
ቢባል ያስቅ እንደሁ እንጂ አያስገርምም :: መቶ ሺህ ደጉዎች በወያኔ አረር ረግፈዋል :: ለእስርና ስቃይ ተዳርገዋል :: ስለዚህ ተወን እባክህ ውነት ከኢሀዴግ ዘንድ አለ ብለን ለማመን አይቻለንምና የፍትህን ቀን ከላይ እንድናገኝ አምላክ ይርዳን ::

I still don't see how your reasoning makes Teddy innocent. am I the only person who don't see Teddy afro as a threat to gvmt? Specailly after 3yrs. and as far as his rlshp with the gvmt, I think his fans tainted his reputation. His lyrics wasn't against weyane specifically per se. He talked about how little progress we've made and that includes derg too.....(but I'm always amazed how everyone ማውለብለብስ የላይን ኦፍ ጁዳ ያለበት ባንዲራ and yet dare to call me a feudal......oh the irony Rolling Eyes anyway) I think ppl ማካበድ 'ed way tooo much. weather or not he's innocent or guilty or he's been framed by EPDRF or not.....................he's will go through the legal system just like ever other ethiopian has. I don't understand all this outcry for him to be released and condemning the constitution while according to you there are million of ethios behind bars with no fault. If you are so ተቆርቁዋሪ for the innocent, then why not fight for those who don't have public faces, and no voices? all I gotta say is give me a break!!!!

Quote:
የአዲስ አበባውን ወህኒቤት ያጣበበው ወንጀለኛ ሳይሆን እውነተኛ ነው ::

if you truely believed this, then where were you for the past 17yrs? what makes teddy any better than these people you talk about. you are being a hypocart to say the innocent must be free but only if they are famous.

*btw, I am not woyane ( Laughing i know that was coming) I like when ppl talk about the gvmnt is lacking on because I believe that would lead to progress..........but my problem is with how you complain. It doesn't make sense. Your argument in itself is a contradiction!

oh and in Ethio, is one innocent 'till proven guilty or guilty 'till proven innocent?......it seems like the latter Confused
_________________
Homage to darkness : http://yekolotemari.blog.com/2010/02/09/homage-to-darkness/

"Is it stealing
if I take
the pains of others

and make it my healing?"
http://elicitbeauty.blogspot.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ግድንግድ ላጀ

መንገደኛ

Joined: 20 Jul 2008
Posts: 8

PostPosted: Wed Jul 23, 2008 3:47 am    Post subject: Reply with quote

ሳሂቦቼ --ቴዲ ይፈታል :: ግን ቢያንስ 2 አመት ያስሩታል :: የወያኔ ታክቲክ እስካሁን ካልገባቹ ምን መሰላቹ --- በአሰልቺ ችሎት እያመላለሰ ዲሞራላይዝ እና ቴረራይዝ አድርጎ በመፍታት ስብእናን አኮላሽቶ በጥላክ እየደነገጥክ እንድትኖር የሚያደርጉበት እርፍና አላቸው :: እናም
ስለቴዲ መፈታት አመት ሸቤ ያቆዩትና በል ሩጥ ይሉታል ::
ጥያቄው ከቃሊቲ ሲወጣ ምን ያህል የድሮው ቴዲ ሆኖ ይወጣል ? እንክዋን እሱ አደገኛ ባላንጣዎቻቸው እነ ስዬ አባይ ማነው ደሞ ሀይሉ ሻውል እና ብርሀኑ ነጋንም አስደንግጦ ሁለተኛ አይለመደኝም አስብለው ለቀዋል :: የቴዲም እጣ ከዛ አይርቅም ::
ዛትስ ኢት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ShyBoy

ዋና ኮትኳች

Joined: 04 Apr 2006
Posts: 904
Location: Gojjam

PostPosted: Wed Jul 23, 2008 4:24 am    Post subject: ቴዲ አፍሮ ...... Reply with quote

ሰላም እህምም !

በቴዲ አፍሮ ጉዳይ ግራ የተጋባሽ ስለመሰለኝ የራሴን ሀሳብ ለመስጠት ያህል ነው :: ሌሎች ሰዎች "ቴዲ አፍሮ ጥፋተኛ አይደለም " ብለው ያቀረቡት ትንተና ያሳመነሽ አይመስልም :: ባንጻሩ አንችም "ጥፋተኛ ሊሆን ይችላል " ብለሽ ያቀረብሽው አንድም ምክንያት የለም :: ለኔ የሚታየኝ ነገር ቴዲ አፍሮ እንደማነኛውም ሰው መኪና ሲያሽከረክር ጉዳት አድርሶ ሊሆን ይችላል :: ግን ታዲያ አዲስ አበባ ውስጥ 100,000 ተሽከርካሪዎች ቢኖሩ ይሄንን 'ስፔስፊክ ' አደጋ እሱ የማድረሱ እድል 1/100,000 ወይም ደሞ 0.00001 ነው :: ከዛ ውጪ ግን ቴዲን ሰው ገጨ ብለው ነው ያሰሩት የሚለው በጭራሽ አያስሄድም :: ግልጽ የሆነ ፖለቲካዊ ነገር ነው እየተሰራ ያለው :: ለዚህም አጠቃላይ ሂደቱን ማየት ያስፈልጋል :: እዚህ 'ትሪድ ' ውስጥ አንደኛው ገጽ ላይ ሾተል ግማሹን ፓርት ኮፒ አድርጎ ያመጣውን ይሄንን አርቲክል ብታነቢው ሂደቱን 'ሰመራይዝ ' አድርገው አቅርበውታል :: http://www.ethiopiazare.com/the-news/1-latest-news/345-teddy-afro

ወያኔ ካሁን በፊት ተቃዋሚዎቹን እንዴት እንደሚያጠቃ ለተገነዘበ እና የቴዲን የፍርድ ሂደት ለተመለከተ ሁሉም ነገር የበቀል መሆኑን መረዳት አያዳግትም :: እውነት ሰው ገጭቶ በማምለጥ ወንጀል ከሆነ ቴዲ የተከሰሰው ለምን እንደሌላው ወንጀለኛ ትሪት አይደረግም ? ጨለማ ቤት ውስጥ ማሰርን ምን አመጣው ? ፍርድ ቤት የሄዱትን ሰዎች ሰበብ እየፈጠሩ ማሰር ምን አመጣው ? እስር ቤት ሂዶ ሰው እንዳይጠይቀው ለምን ይደረጋል ? ሌላው ሁሉ ይቅርና የዶክተር ማስረጃው ድራማው ከምን የመጣ ነው ? ሰበብ አስባብ እየፈጠሩ ለምን ፍርዱን ያጓትቱታል ? ሁሉንም ነገር ብትመለከችው (ከዳኛው ጀምሮ ) ቴዲ ልክ እንደቅንጅት ታሳሪዎች ነው ትሪት እየተደረገ ያለው ::

ቴዲ ወያኔን መቸ ነው የተቃወመው ላልሽው ........አንድነትን የሰበከ ሁሉ ለወያኔ ጠላት ነው :: ቴዲ ደሞ አንድነትን ይሰብካል :: የምፈልገውን ዘፈን እንድዘፍን ካልተፈቀደልኝ ሸራተን አልዘፍንም ብሎ 1998.. ጥሎ መውጣቱ አሁን ደግሞ ለሚሊኒየም አላሙዲ ካዘጋጀው ኮንሰርት የልቅ ስተዲየም በነጻ መዝፈኑ ወያኔዎቹን አስከፍቷቸዋል (የአላሙዲን እና የወያኔን ግንኙነት ደሞ አገር ያወቀው ነገር ነው ):: ሌላው ደግሞ ካንድ አመት በፊት አካባቢ ትዝ ይለኛል አዲስ አድማስ ላይ የሆነ ኢንተርቪው ነበርው (እኔ ራሴ እዚህ ዋርካ ላይ ለጥፌው ነበር ..........አሁን ላመጣው ፈልጌ የአዲስ አድማስ ዌብሳይት ራሱ ለጊዜው አይሰራም ):: እዛ ኢንተርቪው ላይ ቴዲ በግልጽ መንግስትን ወቅሷል :: "ባሁኑ ሰዓት ምንም የሰላም አየር አይነፍስም : ዕርቅ ያስፈልጋል : መንግስት ነገሮችን መለወጥ አለበት " አይነት ነገር ነው የተናገረው :: በዛ ሰዓት ቅንጅቶች ገና አልተፈቱም ነበር :: ብቻ በወቅቱ ቴዲ የተናገረው ነገር በዛ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ በዘመኑ የወያኔ ብሂል "የሀገር መክዳት ወንጀል " የሚያስብለው ነበር :: እንግዲህ ሁሉንም ነገር ለመዘርዘር ከባድ ነው :: አንች እንደተቃውሞ የማትቆጥሪው ነገር በሙሉ ለወያኔ ቅዋሚ /ወንጀል ነው :: ምናልባት አንች ለብዙ ጊዜ ከኢትዮጵያ ውጭ ስለቆየሽ የሀገር ቤቱ ሁኔታ አልተገነዘብሽ ይሆናል :: እኔ በምርጫ ሰሞን ኢትዮጵያ ስለነበርሁ ወያኔ ምን አይነት የወሮበላ ስራ እንደሚሰራ አይቻለሁ :: ከወያኔ ይልቅ ቴዲን 10000000000000 ጊዜ ማመን ይቀላል !!!!

ሳላስበው ብዙ ነገር ዘበዘብሁ ........ይቅርታ ! ለምን ለሌሎች ታሳሪዎች ተቆርቋሪ ጠፋ ያልሽው ላይ ትንሽ ለማለት ያህል :-- የቅንጅት መሪዎች እና ቴዲ ብዙ ህዝብ ስለሚያውቃቸው እና ለሚዲያው ቅርብ ስለሆኑ ብዙ መረጃ ይገኛል :: ሰዉም ስማቸውን እየጠራ ስለደረሰባቸው በደል እና ፍትህ እንዲያገኙ አቤቱታ ያቀርባል :: ሌላውንም ሰው ስፐሲፊካሊ እነማን እንደሆኑ ባይታወቅም አጠቃላይ በሆነ መልኩ ግን በየሚዲያውም ሆነ እዚህ ዋርካ ላይ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ይወራል :: እናም እህምም የኔ ሀሳብ ከሙሉ በኩሉ ይሄንን ይመስላል (ጭንቅላቴ ውስጥ ያለውን ሁሉ ነገር በደንብ ማብራራት ባለመቻሌ ይቅርታ ):: እስኪ አንች ደሞ ቴዲ በፖለኢካ /ቂም ሳይሆን ሰው ስለገጨ ነው የታሰረው የምትይበትን ምክንያት እንዲሁም ደግሞ እስካሁን ስላለው የቴዲ የፍርድ ሂደት ፍትሀዊነት አብራሪልኝ ::

መልካም ጊዜ !!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Jul 23, 2008 5:11 am    Post subject: Re: ቴዲ አፍሮ ...... Reply with quote

"ShyBoy"] :-

ጎበዝ :: እንዲህ ኃሣብህን ደርዝ ባለው አቀራረብ : በጨዋ አገላለፅ ስላቀረብከው ኃሣብህን የሚደግፉት ብቻ ሣይሆኑ የሚቃወሙህም ሊያነቡት ይገፋፋሉ :: በርታ !!!

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አንበርብር

ውሃ አጠጪ

Joined: 09 Apr 2005
Posts: 1090
Location: everywhere

PostPosted: Wed Jul 23, 2008 8:18 am    Post subject: Reply with quote

Quote:
His lyrics wasn't against weyane specifically per se. He talked about how little progress we've made and that includes derg too.....(

ውድ እህቴ እህምም ... በአሁኑ ሰሀት የሀገራችን ንፁህ ዜጎች የወያኔ ሰለባ እየሆኑ ያሉት የወያኔ ተቃዋሚ ስለሆኑ ብቻ አይደለም :: በህዝብ ዘንድ እውቅናን ካገኘሽና በተለያየ የሙያ ዘርፍ ብዙ ደጋፊዎችን ማግኘት ከቻልሽ በወያኔ ራዳር ውስጥ ነሽ :: በወያኔ ድብቅ ሴራ ውስጥ : አንድ ሰው በህዝብ ህሊና ውስጥ ሰርፆ መግባትና ተወዳጅነትን ማትረፍ የለበትም :: ያንን ማድረግ የሚችል ሰው ከተገኘና ይህ ሰው የወያኔ አባል ካልሆነ መጨረሻው የሚሆነው ጥፋት ነው :: ሀገራችን ንፁህ ዜጎችን እንድታፈራ ወያኔ አይፈልግም ........ ንፁህ ከሆንሽ እውነትን ከደገፍሽ ለግዜ ጥቅም እራስሽን አሳልፈሽ ካልሰጠሽ ሁሌም የወያኔ ጠላት ነሽ :: ቴዲን በወያኔ ቀለበት ውስጥ ከከተተው አንዱ ነገር ወያኔን ስላልደገፈ ወይም ስለተቃወመ ሳይሆን ንፁህ ዜጋ ሁኖ ስለተገኘ ነው ::

Quote:
btw, I am not woyane

ምን አስፈራሽ ? ከሆንሽም አምነሽበት ወይም ለጥቅም ብለሽ የገባሽበት ሊሆን ይችላል :: እስካመንሽበትና ጥቅም እስካገኘሽበት ድረስ ሰው ምንም ቢልሽ ሊያሳስብሽ አይገባም :: እኔ እንደሚመስለኝ ወያኔ ካልሆንሽ ቫይረሱ እንዳለብሽ ግን ለመገመት ቀላል ነው ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሾተል

ዋና አለቃ

Joined: 13 Jan 2005
Posts: 6808
Location: Vienna-Austria

PostPosted: Wed Jul 23, 2008 10:36 am    Post subject: Reply with quote

http://www.ethiopiazare.com/the-news/1-latest-news/350-teddy-afro

5 ዛሬ /ቤት ቀረቡ [/i
ትናንት የቴዲ አፍሮን ችሎት ከተከታተሉት አስሩ ታስረው፣ 5 ዛሬ /ቤት ቀረቡ PDF Print E-mail
Tuesday, 22 July 2008 12:15

Teddy Afroየታሰሩት “ችሎት ረብሻችኋል፣ ድንጋይ ወርውራችኋል” በሚል ነው

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሐምሌ 15 ቀን 2000 .. July 22, 2008) በትናትናው ዕለት የቴዲ አፍሮን ችሎት ለመከታተል ከመጡ ችሎት ተከታታዮች መካከል አስሩ ታሰሩ። በዛሬው ዕለትም ፖሊስ ሜክሲኮ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ ነክ ፍርድ ቤት አምስቱን አቅርቧቸው 14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ የጠየቀባቸው ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ ፈቅዶለታል።

በትናንትናው የቴዲ አፍሮ ችሎት ዳኛው ሥራቸውን ጨርሰውና ችሎት በትነው ከሄዱ በኋላ ቴዲ እጁን ወደላይ ቀስሮ ”እግዚያብሔር ያውቃል ! ሲል፤ አብዛኛው ሰው ”ቴዲዬ አይዞህ ! እንወድሃለን ! ሲል የጮኸና ያለቀሰ ሲሆን፣ ወዲያውም ”ማንም ሰው ሳንፈቀድለት እንዳይወጣ” የሚል ትዕዛዝ በፖሊስ አዛዡ ስለተሰጠ ችሎቱን ሊከታተሉ የገቡት ሰዎች አምስት ደቂቃ ከችሎቱ ሳይወጡ ለመቀመጥ ተገድደዋል።

ከዚያም ”ውጡ” ሲባል የችሎቱ ታዳሚ መውጣት ይጀምራል። ወዲያውም ከችሎቱ ውስጥ ከወጡት ሰዎች ውስጥ አስሩ ሰዎች ተለቅመው ይወሰዳሉ። ጉዳዩን የተከታተሉ ወገኖች እንደሚሉት ከሆነ በዲጂታል ቪዲዮ ይቀርጹ የነበሩት ሲቪል የለበሱ ደህንነቶች የችሎቱ ታዳሚ እንዳይወጣ በታዘዘበትና በታገተበት 5 ደቂቃዎች ውስጥ የተቀረጸውን ቪዲዮ መልሰው በማየት ያለቀሱትንና ቴዲ አፍሮን የሚያበረታቱ ቃላት ተናግረዋል ብለው የገመቷቸውን ሰዎች ነው የያዙዋቸው።

ትናንት ችሎቱ ከተበተነ በኋላ የተያዙት እነዚህ አስር ሰዎች ወደ ልደታ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው መታሰራቸውን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገልጸዋል። ሰዎቹ የተያዙበት ምክንያት ሁለት ሲሆን፣ አንደኛው ”ችሎት ረብሻችኋል”፤ ሁተኛው ደግሞ ”ድንጋይ ወርውራችኋል” በሚል መሆኑን እነዚሁ ምንጮቻችን ገልጸዋል። ከአስሩ ሰዎች ውስጥ አምስቱ ከሰዓት በኋላ የተፈቱ ሲሆን፣ አምስቱ ግን በፖሊስ ጣቢያው ታስረው አድረው ዛሬ ፍርድ ቤት ፖሊስ አቅርቧቸው 14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ ተፈቅዶለታል።

ከታሰሩትና ዛሬ ፍርድ ቤት ከቀረቡት ሰዎች ውስጥ የሚጥል (ኢፕሊፕሲ ) በሽታ እንዳለባት የምትታወቀው / ቅድስት በቀለ የተባለችና ምርጫ 97 ተከትሎ ከቅንጅቱ አመራሮች ጋር ”ጎማ አቃጥለሻል” በሚል ሁለት ዓመት ታስራ የተፈታችው ግለሰብ እንደምትገኝበት እነዚሁ የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገልጸዋል። ከወ / ቅድስት በተጨማሪ ሌሎች ሴቶችም መታሰራቸውን ለመረዳት ችለናል።

በስፍራው የነበሩ የዓይን ምስክሮች ድንጋይ ሲወረወር እንዳላዩ ለኢትዮጵያ ዛሬ የገለጹ ሲሆን፤ ሰዎች ድምፃቸውን ማሰማት የጀመሩት ዳኛው ሥራቸውን ጨርሰው ችሎቱን ከበተኑና እሳቸውም ችሎቱን ጥለው ከወጡ በኋላ እንደሆነ አክለው ገልጸዋል።

ችሎት ተገኝተው የነበሩ በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው አንድ የሕግ ባለሙያ ”ታሳሪዎቹ ችሎቱን ረብሸው ከሆነ መጠየቅ ያለባቸው በዛው ችሎት ነበር። ነገር ግን የተላቀሱትና ’ቴዲዬ እንወድሃለን ! ሲሉ ድምፃቸውን አውጥተው የተናገሩት ችሎቱ ከተበተነ በኋላ ስለሆነና ዳኛው ባላዩትና ባልታወኩበት ረብሻ ’ችሎት ተረበሸ’ ብለው መቅጣት እንደማይችሉ ስለሚታወቅ ’ድንጋይ ወርውረዋል’ የሚል ቅጥያ ተጨምሮበት በሌላ ችሎት እንዲቀርቡ ተደረገ ሲሉ ሙያዊ ትንተናቸውን ለኢትዮጵያ ዛሬ ሰጥተዋል።
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
www.shottel.webs.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሾተል

ዋና አለቃ

Joined: 13 Jan 2005
Posts: 6808
Location: Vienna-Austria

PostPosted: Wed Jul 23, 2008 11:28 am    Post subject: Reply with quote

መጀመርያ የበሰለ ትንተና ለሰጣችሁ መንፌው (ጸባየ -ወርቅ ...በነገራችን ላይ እባካችሁ ያገዳችሁት ይህእንን ስም ፍቱለት ብዬ በማክበር እጠይቃለሁ ...ምንም ያደረገው ነገር አልነበረም ),እንዲሁም ለሻይ ቦይና ለአንበርብር የላቀ አክብሮቴንና ምስጋናየን አቀርባለሁ ::የተማረ የተመራመረ አገናዛቢ ለእውነት የሚኖር ሰው ያስደስተኛል ::

እና ተባረኩ ::

ሾተል
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
www.shottel.webs.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሾተል

ዋና አለቃ

Joined: 13 Jan 2005
Posts: 6808
Location: Vienna-Austria

PostPosted: Wed Jul 23, 2008 11:30 am    Post subject: Reply with quote

ለኮሎኔልም እንደዚሁ የበሰለ ትንተና ስለሰጠኽ አክብሮት የሞላው ምስጋናዬን አቀርብልሀለሁ ::

ሾተል
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
www.shottel.webs.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, ... 16, 17, 18  Next
Page 2 of 18

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia