WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ወያኔ : ሼህ መሐመድ እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8, 9, 10  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ሀሪከን 2

ዋና ኮትኳች

Joined: 31 Oct 2008
Posts: 753

PostPosted: Tue Mar 24, 2009 4:56 am    Post subject: Reply with quote

ተድላ ሀይሉ
Quote:
ለሀሪከን 2 ወይም ሀሪከን ወይም ሰልማ 1 ወይም ...

ከተጻፉ ጽሑፎች ገልብጦ ቃል በቃል እንደ ፓሮት ያንኑ መድገም እና ትንተና የተለያዩ ነገሮች ናቸው

ስድቡን ተወው እና አላሙዲ እና ወያኔ አለመጣላታቸውን እንዲሁም የተጣሉት አማረ አረጋዊ እና አላሙዲ መሆናቸውን እመን ስህተትህንም አርም

ለወደፊቱ ደግሞ ስለማታቀው ነገር ላለመተንተን ሞክር ነው ያልኩህ . ምክንያት አንተ የምታቅ የሚመስላቸው አንዳንድ የዋህ የዲያስፓር ፓለቲከኞች ስላሉ እነሱን ላለማሳሳት ስትል ጥንቃቄ አድርግ
_________________
each mind is a different world
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Ahmed-1

ኮትኳች

Joined: 19 Mar 2007
Posts: 151

PostPosted: Tue Mar 24, 2009 10:06 am    Post subject: Reply with quote

የዚህ አምድ ጠቀሜታው አልታየኝም :: አላሙዲን ከወያኔ ጋር ተጣላ ... ዋት ???? እንኳን ደስ ያለን ነው ወይስ የእብድ ገላጋይ እንፈልግ ? ኮምሬድ ተድላ ጸባቸው ለምን እንዳስደሰተህ ይገባኛል በዚያው መጠን አርዕስት ከፍተህ እዚህ የምትሳለቅበት ትንሽነትህ ተመችቶኛል :: ተራ ወሬ ቢሆንም ከዚህ አርዕስት ጀርባ ያለው ፕሮፓጋንዳ የአንተ መርዘኛ የሀይማኖት ተልዕኮ ነው :: አላሙዲን ለብዙዎች የስራ እድል የከፈተ ለሀገሪቱም ኢኮኖሚ ማደግ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከተ ኢንቨስተር እንጂ ኢትዮጵያን የጎዳ ጠላታችን አይደለም :: ሼኹ ብሩን ወደ መሳሪያ ለውጦ ወያኔን እንዲያስወግድ ትጠብቃለህ ልበል ? የውጭ ኢንቨስተሮች በዲሞክራሲ መንገድም ሆነ በጦር ሀይል ወይም በቅንጅት ........ ስልጣን ከያዘው መንግስት ጋር አብሮ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ይግባህ !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4459
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Mar 25, 2009 9:43 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁሉም :-

በዚህ ዓምድ በታኅሣሥ 30 ቀን 2001 .. (January 8, 2009) ባቀረብኩት ጽሑፍ አንድ ጠቋሚ አስተያዬት አቅርቤ ነበር ::

Quote:
ወያኔ ለሥልጣን ከበቃ ጀምሮ በተለያየ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባውን የውጪ ምንዛሪ መልሶ በተለያዩ አገሮች እንደሚያከማች እና በተለያዩ የውጪ ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች እንደሚያውለው ፀሐይ የሞቀው ሃቅ ነው :: ከዚህም መካከል በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በሚታወቁ የአክሲዮን ገበያዎች በተለያዩ ሽፋኖች መሣተፉ አይቀርም :: በቅርብ ወራት እንደታየው የአክሲዮን ገበያ በከፍተኛ ደረጃ ኪሣራ ላይ ወድቋል :: ስለዚህ ወያኔ ለአክሲዮን ግዢ ካዋለው ገንዘብ የተወሰነው ከሥሯል ማለት ነው :: ይህንን ኪሣራ ለማካካስ እና በውጪ ያለውን የኃብት ክምችት ቢቻል ለማሣደግ ካልተቻለም ባለው ደረጃ ለማቆየት ወያኔ የውጪ ምንዛሪ ምንጭ የሚሆኑትን መንገዶች ሁሉ መፈለግ ይኖርበታል :- የአገሪቱን ብሔራዊ ባንክ ያለምንም የውጪ ምንዛሪ ጥሪት የሚያስቀር ርምጃ እንኳን ቢሆን ::

አሁን የወያኔ አገዛዝ በብሔራዊ ባንክ የሚቀመጠውን የአገሪቱን የመጠባበቂያ የውጪ ምንዛሪ አሟጦ መጨረሱን መካድ አይቻልም :: ከዚህ አንጻር :-

. ባለፈው ሣምንት የኮካ ኮላ ፋብሪካ ከውጪ የሚያስመጣው ጥሬ ዕቃ በውጪ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ማግኘት ባለመቻሉ ፋብሪካው ማምረት ማቆሙ ምንጭ :- ሪፖርተር ጋዜጣ : እሁድ መጋቢት 6 ቀን 2001 .. :: ኮካኮላ ፋብሪካ ማምረት አቆመ :

. ዛሬ (ረቡዕ መጋቢት 16 ቀን 2001 .. ) ደግሞ 89 ቡና ላኪ ድርጅቶችን መጋዝን የወያኔ አገዛዝ ማሸጉ : (ምንጭ :- ሪፖርተር ጋዜጣ : ረቡዕ መጋቢት 16 ቀን 2001 .. :: ከፍተኛ ቡና ላኪዎች ታገዱ ) እና

. ሌሎችም ...

የችግሩ ሥፋት ምልክቶች እንጂ የችግሩን ጥልቀት እና ችግሩ ሊያስከትል የሚችለውን አጠቃላይ ቀውስ ሙሉ በሙሉ ሊያመለክቱ አይችሉም ::

ይልቁንስ የወያኔው ቁንጮ ለገሠ (መለስ ) ዜናዊ "የአፍሪቃ አገሮች አጣዳፊ የውጪ ዕርዳታ ካልተደረገላቸው የተወሰኑ አገሮች የመፈራረስ ዕጣ ይጠብቃቸዋል ::" ብሎ የተናገረው ቃል መሠመር አለበት :: ይህ ቃል ለገሠ ለሌላ ሣይሆን ኢትዮጵያን አፈራርሶ ወደ ትግራይ -ትግሪኝ ለመጠቃለል ያለውን የመጨረሻ እርምጃ ሊያመለክት የሚችል አባባል ነው ::

ስለዚህ :- ለወያኔ አገዛዝ ምንም ዓይነት የውጪ ዕርዳታና ድጋፍ እንዳይደረግለት ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ መወትወትና ለማሣመን መሞከር ያስፈልጋል :: በተጨማሪም የወያኔ አገዛዝ ምን ዓይነት የአገዛዝ ፖሊሲ ተከትሎ እንዲህ ያለውን ቀውስ በኢትዮጵያ ላይ ሊያመጣ እንደቻለ በማሣዬት ማለትም :-

. የግለሰብን መሠረታዊ መብት እና የግል ባለሃብትን የማይቀበል በጎሣ ላይ የተመሠረተ ኢኮኖሚያዊ : ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ ሥርዓት መዘርጋቱ :

. ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የሚያስችል ህገ -መንግሥት ማጽደቅና በሥራ ላይ ማዋሉ :

. ከአካባቢው አገሮች ጋር ለወደፊት በሠላም መኖር እንዳይቻል የተለየዩ ግጭቶችን መፍጠሩ እና ማባባሱ :: ለምሣሌም በጎረቤት አገር ሶማሊያ ላይ ያልተገባ ጣልቃ -ገብ ጦርነት ማካሄድና የአገሪቷን (የኢትዮጵያን ) አምራች የሰው ኃይል እና የጥሪት አቅሟን ማሟጠጡ :

. ወዘተርፈ ...

ለዚህ አማራጩ በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ዕርቅ የሚያመቻች እና ሁሉን አቀፍ መንግሥት የሚመሠረትበትን የሚፈጥር ማዕቀፍ መፍጠር መሆኑን ማስገንዘብ ያስፈልጋል ::

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4459
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu Apr 23, 2009 4:40 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁሉም :-

አማረ አረጋዊ እንደዛሬው በሼሁ ላይ ተሣልቆ አያውቅም ::

ምንጭ :- ሪፖርተር ጋዜጣ :: ሚያዝያ 14 ቀን 2001 .. :: ክቡር ሚኒስትር ::

Quote:
ክቡር ሚኒስትር l
Wednesday, 22 April 2009

(ካቢኔው ኢንቬስተሮችን ለማበረታታት አንዳንድ እርምጃዎችን ለመውሰድ ወስኗል፡፡ እጅግ በጣም ጥሩና እጅግ በጣም መጥፎ የተባሉ የኢንቬስትመንት ዓይነቶችን ለይቶ በማጥናት ለሕዝብም ለኢንቬስተሮችም ማሳየት፣ ማስተማር የሚለው ውሳኔውንም ተግባራዊ ለማድረግም በክቡር ሚኒስትሩ የሚመራ ኮሚቴ አቋቁሟል፡፡ ይህን ለባለሃብቱ ለማሳወቅ በሚሌንየም አዳራሽ ስብሰባ እየተካሄደ ነው )

- ክቡር ሚኒስትር የስብሰባው ዓላማ ገብቶኛል፡፡ ጥሩውና መጥፎው ተለይቶ ዓለም ይወቀው ማለታችሁም ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን የእኔ ጥያቄ ይህን ለመለየት እውነት ልዩ ጥናት ያስፈልጋል ነው ወይ ? የሚል ነው፡፡ ታውቁታላችሁ፡፡ መንግሥት ግን እያወቀ ይደብቀዋል፣ ያድበሰብሰዋል የሚል እምነት ነው ያለኝ፡፡
- ሃሳብህን በግልጽ በመናገርህ ጥሩ ነው፡፡ ግልጽ መሆንህ ካልቀረ በግልጽ መንግሥት ይህን እያወቀ ይህን ደበቀ አድበሰበሰ ብለህ ተናገር፡፡
- እናገራለሁ ክቡር ሚኒስትር ሩቅም አልሄድም፡፡ የተሰበሰብንበት አዳራሽ ራሱ በቂ ማስረጃ ነው፡፡ መንግሥት ይህ የተሰበሰብንበት መጋዝን እንዲሰራ አይደለም መጀመሪያ ፈቃድ የሰጠው፡፡ ሆቴሎችና ኮንቬንሽን ሴንተር እንዲሰራ ነው ፈቃድ የሰጠው፡፡ የተሰራው ግን መጋዘን ነው፡፡
- እና እንዴት ነው ያድበሰበስነው ?
- ባለሃብቱ በተሰጠው የኢንቬስትመንት ፈቃድ መሠረት አልሰራም ከማለት ይልቅ ከፕላኑ ውጭ በተሰራ መጋዘን ውስጥ የሚሌንየሙ የሚገርም እኮ ነው የሚሌንየሙ ማለት የሺህ ዓመቱ ሰው ብላችሁ ሸለማችሁ፡፡ ተሳሳትኩ ክቡር ሚኒስትር ?
- እኮ ይህን ሁሉ ለመመርመር እኮ ነው ጥናት ተደርጎ ጥሩውንና መጥፎውን ተለይቶ ለእጅግ በጣም ጥሩ ሽልማት፣ ለእጅግ በጣም መጥፎ ደግሞ አስፈላጊው እርምጃ ይወሰድ የተባለው፡፡
- እርምጃ የሚወሰድ ከሆነ ጥሩ (ሌላ ተናጋሪ )
- መንግስትኮ የተሳሳተ አካሄድ ከነበረው በሚገባ ለማየት ለማረምና ተገቢ የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ ብሎ ነው ይህ ውሳኔ ያሳለፈው፡፡ የሃኪም ትዕዛዝ እኮ አይደለም፡፡ መንግሥት በፈቃደኝነትና በራሱ ተነሳሻነት እያደረገው ያለ ነው፡፡
- ክቡር ሚኒስትር መንግሥት መንግሥትን ያምናል ወይ ?
- አልገባኝም !መንግሥት መንግሥትን ያምናል ወይ ? የሚለው አልገባኝም፡፡
- ክቡር ሚኒስትር አባባሌ ... መንግሥት ትናንት የሺህ ዓመቱ ኢንቬስተር ብሎ የሸለመውን ዛሬ እጅግ በጣም የተበላሸ ኢንቬስትመንት ብሎ እርምጃ ለመውስድ ድፍረቱ ይኖረዋል ወይ ማለቴ ነው፡፡
- ጥናቱ እሱን የሚያረጋግጥ ከሆነ እምነቱም ድፍረቱም በተጨባጭ አለ፡፡ ይህ መንግሥት የራሱን ስህተት በይፋ ለሕዝብ ሲያቀርብ የቆየ መንግሥት ነው፡፡ ታሪኩም ይህን ያረጋግጣል፡፡ ጥናቱ ካረጋገጠ በመንግሥት ቁርጠኝነት አትጠራጠሩ፡፡ የተቋቋመው ኮሚቴ ይህን ቆራጥ አቋም ለማሳወቅ ከፍተኛ እምነት የተጣለበት ነው፡፡ አስፈላጊ ጥቆማም ሃሳብም ላኩልን፡፡
(ስብሰባው በመግባባት ተጠናቅቆ ኮሚቴው ስራውን ጀመረ፡፡ ጥቆማዎች እየመጡ፣ ፋይሎች እየተገለባበጡ ጥናት እየተካሄደ ነው፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ ዝግ የኮሚቴው ስብሰባ እየመሩ ናቸው፡፡ በኮሚቴው አባላት ሰፊ ውይይትና ክርክር እየተካሄደ ነው )
- እንግዲህ ከሚገባ በላይ፣ ከጠበቅነው ውጪ በሚገርም ሁኔታ መረጃ እየጎረፈ ነው ያለው፡፡ ሶስት ወራችን ነው፣ አሁንም መረጃ እየጎረፈ ነው፡፡ እንዴት እያያችሁት ነው ?
- እኔ በዚህ ኮሚቴ ውስጥ ባልገባ ኖሮ የተሳሳተ አመለካከት ይዤ ነበር፡፡ አባል በመሆኔ በእጅጉ ዓይኔ ተከፍቷል አመሰግናለሁ፡፡ እጅግ በጣም ጥሩ የሚለውን ማሳያ ለመለየት ትንሽ ጊዜ የሚያስፈልገን ይመስለኛል፡፡ እጅግ በጣም መጥፎ ኢንቬስትመንት የሚለው ግን ምንም ችግር የሚያጋጥመን አይመስለኝም፡፡ "ግልጽና ግልጽ " ነው፡፡
- ሌሎቻችሁስ እንዴት እያያችሁት ነው ?
- (ሌላ አባል ) ያው እሱ እንዳለው ነው፡፡ ጥሩውን ለመለየት እንጂ መጥፎውን ለመለየት በቂ ማስረጃ አለ፡፡
- ሌላ ሃሳብ አለ ?
- (ሌላ አባል ) ክቡር ሚኒስትር እነሱ ባሉት ላይ እስማማለሁ፡፡ ነገር ግን ኃላፊነታችን በሚገባ እንድንወጣና ከተጠየቅንም አደባባይ ወጥተን እንድንናገር ከመስሪያ ቤቱ ሰዎች ማለት ኃላፊዎች ጠርተን ከተቻለም ባለቤቱ ራሳቸው ቀርበው እንዲያስረዱን እናድርግ፡፡
- ጥሩ ሃሳብ ነው፡፡ እኔም የሚመጣው መረጃ እያስደነገጠኝ ስለመጣ ተጠርተው መጥተው ጥያቄውን ይመልሱ፡፡
- (ሌላ አባል ) ጥሩ ሃሳብ ነው፡፡ አስረጂ ይጠራ ወይም ይጠሩ ... በመመዘኛው መሰረት በማኔጅመንት፣ በሰው ሃይል እድገት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በሃብት ፈጠራና ትርፋማነት፣ ሕግ በተከተለ አካሄድ ወዘተ ሊያስረዱ የሚችሉ ይጠሩ፡፡
- ጥሩ፡፡
- ግን ክቡር ሚኒስትር አደረጃጀታቸው ራሱ ደብልቅልቅ ያለ ስለሆነ ማን ምን እንደሚመለከተው ግልፅ አይደለም፡፡ ባለቤቱ ራሳቸው ቢመጡ ነው ጥሩ የሚሆነው፡፡
- እኛ ጥሪውን አሁኑኑ እናስተላልፍ የሚመጡትን እነሱ ይወስኑ፡፡
(ጥሪው ተላለፈ፣ እንዲያስረዱ ሶስት ሰዎች መጡ፡፡ ባለቤቱ ራሳቸው፣ አደገኛ ምስለኔ እየተባለ የሚታወቀውና ሌላ የተለያዩ ድርጅቶችን ያስተዳድራሉ የሚባሉት )
- ለእኔ ለምን እንድተጠራን ግልፅ አይደለም ክቡር ሚኒስትር፡፡
- በመንግሥት ውሳኔ መሠረት ጥሩና መጥፎ ኢንቬስትመንት እያጠናን ነው፡፡ ስለእናንተ ኢንቬስትመንት እየመጣ ያለው መረጃ እጅግ በጣም መጥፎ ስለሆነ ከእናንተ ሳንሰማ ለማጠቃለል ስላልፈለግን እንድታስረዱን ነው፡፡
- (ባለቤቱ ባለሃብቱ ) የእኔ ኢንቬስትመንት በዓለም አሉ ከሚባሉትና ከሚደነቁት አንዱ ነው፡፡ በዓለም ሰራተኛ ሲባረርና ደሞዙ ሲቀነስ እኔ ራሴ በቅርቡ በገዛሁት ኮሌጅ ላሉት አስተማሪዎች ደመወዝ እንዲጨመር አድርጌያለሁ፡፡
- ስለኢንቬስትመንት ነው እያወራን ያለው፡፡ ስለኮሌጁ ደመወዝ ጭማሪ ካወራችሁ በዛሬው ቀን ደግሞ ከሚድሮክ ኮንስትራክሽን ስላበረራችኋቸው ሰራተኞች ማውራት እንችላለን፡፡
- ለልብ ህሙማን ሆስፒታል የሰጠሁት ገንዘብ ያስከተለው አድናቆት የምታውቁት መሰለኝ፡፡
- ስለኢንቬስትመንት ነው እያወራን ያለነው፡፡ ሰላም ሆስፒታልም ሌሎች ሪፈራል ሆስፒታሎችም እሰራለሁ ብለው መሬትና ፈቃድ ተሰጥቷቸው ለምን ኢንቬስትመንቱ እውን አልሆነም ነው ጥያቄያችን፡፡ መዋጮው ጥሩ ነው ግን አጀንዳችን ኢንቬስትመንት እንጂ መዋጮ አይደለም፡፡
- በእውነቱ ትናንትና የፋሲካን በዓል ምክንያ በማድረግ ድግስ ነበረን፡፡ ሕዝቡ በደስታ እንዴት ይጨፍር እንደነበር ብታዩ፡፡
- ስለኢንቬስትመንት ነው እያወራን ያለነው፡፡ አንድ አዳራሽ ውስጥ ስለነበረ ጭፈራ ሳይሆን ጭፈራ የተደረገበት ሆቴል በተሰጠው ፈቃድና ባሳየው ፕላን መሰረት ለምን አላለቀም ነው ጥያቄያችን፡፡
- ክቡር ሚኒስትር በጋምቤላ ስላሰብኩት ኢንቬስትመንት በኤፍ .ኤም ተናግሬ ነበር፡፡
- ስለኢንቬስትመንት ነው እያወራን ያለነው፡፡ ስለታለመው ሳይሆን በተጨባጭ ፈቃድ ተሰጥቶዎት ስላላከናወኑት ኢንቬስትመንት ነው እያወራን ያለነው፡፡ በጥቁር ውሃ፣ በመቂ፣ በሆለታ፣ በደብረ ዘይት፣ በጎጃም ወዘተ . ስላለው ኢንቬስትመንት ነው እያወራን ያለነው፡፡ ግብር አልተከፈለም፣ የመሬት ዋጋ አልከፈላችሁም፣ የባንክ ብድር አልፈከላችሁም፣ እየተነጠቃችሁ ነው፡፡ ምን የሚሉት ኢንቬስትመንት ነው ? ይህ እየወደቀ እያለ ስለጋምቤላ አታውሩን፡፡
- ክቡር ሚኒስትር በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ጊዜ ከመንግሥት ጋር በፅናት ቆሜያለሁ፡፡
- ስለኢንቬስትመንት ነው እያወራን ያለነው፡፡
- ታመው ያሳከምኳቸው ሰዎች ምርቃት ዋጋ የለውም ማለታችሁ ነው ?
- ስለኢንቬስትመንት ነው እያወራን ያለነው፡፡ ከዚያ ውጭ በእርሶ እርዳታ ታክመን ዳንን የሚሉ አሉ፡፡ ጥሩ ነው፡፡ በእርስዎ ምክንያት ለበሽታ ተዳረግን የሚሉም አሉ፡፡ እውነት ከሆነ ያሳዝናል፡፡ እኛ ግን ስለኢንቬስትመንት ነው እያወራን ያለነው፡፡
- እና ለሴካፋ ስፖንሰር ያደረግኩት ዋጋ የለውም ማለት ነው ?
- ስለኢንቬስትመንት ነው እያወራ ያለው፡፡ ቺፕ ውድ ፋብሪካ ሳይጀመር አስራ ሁለት ዓመት አለፈው፡፡ ገበሬ ተፈናቅሏል፡፡ ለምን ?
- ወደ ስፖርቱ ልመለስ፣ በሴካፋ ውድድር ስንት ሰው ሲመርቀኝ አልነበረም ወይ ክቡር ሚኒስትር ?
- መርቆ ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ደግሞ እርስዎ ኢትዮጵያ ከፊፋ እንድትባረር ምክንያት ሆነዋል፣ በስፖርቱ ሕብረተሰብ ዘንድ መከፋፈል ፈጥረዋል፣ ስታዲየሞች ይሰራሉ ተብሎ አጉል ተስፋ ሆነው ቀርተዋል ተብለውም ይወቀሳሉ፡፡ ፕሬሱንም ከፋፈሉት፣ አርቲስቱንም ከፋፈሉት ". አሽከር እንጂ ባለሙያ አይፈጥሩም እየተባለ ብዙ ይወራል፡፡ የሚደርሰን መረጃም ያሳዝናል፡፡
- ቢዮንሴ
- የለም የለም ወሬያችን ስለኢንቬስትመንት ይሁን፡፡
- (ምስለኔው ) ...... ይቅርታ ከእንቅልፌ በድንገት ስለተጠራሁ ነው፡፡ እና ወደ ቁም ነገሩ ልግባ፡፡ ዶክተር አሸብር ".
- እባካችሁ ስለኢንቬስትመንት እናውራ፡፡ አንተ ለምሳሌ በመድሃኒት ፋብሪካው አለህበት፤ ነገር ግን ወድቆ ቀርቷል፡፡ በቦሌ ታወር አለህበት፣ ቆሞ ቀርቷል፡፡ እንደውም ገና ሳናየውና ሂሳብ ሳይዘጋ አትርፈናልና ከትርፉ ገንዘብ ይሰጠኝ እያልክ ወስደሃል የሚል ጥቆማ ደርሶናል፡፡
- (ሶስተኛው አስረጂ ) እሳቸው የኢትዮጵያ ስም በአፍሪካ እንዲገን አድርገዋል፡፡
- እባካችሁ ስለኢንቬስትመንት እናውራ፡፡ የፈጠራችሁት ሃብት፣ ያመጣችሁት ቴክኖሎጂ፣ ያዳበራችሁት የሰው ኃይል፣ የገነባችሁት የማኔጅመንት አቅም ወዘተ . ስለአፍሪካ ካነሳችሁ በአፍሪካ ሕብረት ይሰራል የተባለው ሆቴል ምነው ሰውየው ሳይጀምሩት ቀሩ ? የሚል ቅሬታ ነው ለመንግሥታችን የተጻፈው፡፡ የሆቴል ኢንቬስትመንቱ የለም፡፡
- አንድ ሆቴል ዘገየ ተብሎ ". ክቡር ሚኒስትር፡፡
- አንድ ሆቴል አይደለም የባህርዳር ሆቴልም የለም፣ ሆራ ሆቴልም የለም፣ ሸራተን ሆቴልም አላለቀም፡፡
- አርባ ሶስተኛ ".
- እባካችሁ ስለኢንቬስትመንት እናውራ፡፡ በተጨባጭ በኢትዮጵያ ያለው ኢንቬስትመንት ምንድነው ? ምን ይመስላል ? ችግሩ ምንድነው ?
- ክቡር ሚኒስትር የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪ ""
- እባካችሁ ስለኢንቬስትመንት እናውራ፡፡
- ስለሳቸው የተሰራው ፊልም ራሱ ...
- እባካችሁ ስለኢንቬስትመንት እናውራ፡፡ በነገራችን ላይ በፈቃደኝነት ነው ማስረዳት ያለባችሁ፡፡ ቅር ካላችሁ ልትተውት ትችላላችሁ፡፡ ሳናናግራችሁ ለመደምደም ስላልፈለግን ነው፡፡
- የስዊድን ንጉሥ ሽልማት ሲሰጡኝ !
- እባካችሁ በኢትዮጵያ ስላለው ኢንቬስትመንት እናውራ፡፡ ንጉሡ ሸለሙኝ ከማለት ይልቅ የአፍሪካ ልማት ባንክ ለምን ብድር ከለከለኝ ብለው ቢያስቡ ይሻላል፡፡
- ለክሊንተን ፋውንዴሽን ...
- እባካችሁ በኢትዮጵያ ስላለው ኢንቬስትመንት እናውራ፡፡
- ሪፖርተር ጋዜጣ ...
- እባካችሁ፣ እባካችሁ ስለኢንቬስትመንት እናውራ፡፡ እኛኮ ኢንቬስትመንት ላይ እናተኩር ብለን ነው እንጂ የሚደርሰን ጥቆማ የእነሱ የጥበቃ አባል ሰው መታ፣ ሰው ገደለ፣ እከሊት ወልጄላቸዋለሁ አለች " ከሰሰች፣ ሞተች ወዘተ . የሚል ቅሬታ አለ፡፡ ኢንቬስትመንት ላይ እናተኩር ነው ያልነው፡፡
- እኔ በሚሌንየም በዓል ጊዜ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ስጨፍር ".
- እባካችሁ ስለኢንቬስትመንት እናውራ
(ብዙም ፍሬያማ አልነበረምና ተቋረጠ፡፡ አስረጂዎች የተባሉት ወጡ፡፡ ኮሚቴው ውይይቱን ቀጠለ )
- ወይ ጣጣ !
- ክቡር ሚኒስትር እንግዲህ ነገሩን እናጠቃልል፡፡ እጅግ በጣም ጥሩ ኢንቬስትመንት ለሚለው ተጨማሪ አንድ ወር ያስፈልገናል፡፡ በጣም እርግጠኛ ለመሆን እጅግ በጣም መጥፎ ኢንቬስትመንት ለሚለው ግን ይህ በቂና ከበቂ በላይ ነው፡፡ አስር ዓመት ብንቆም እንደዚህ ዓይነት የተጨማለቀ ኢንቬስትመንት የሚያጋጥም አይመስለኝም፡፡
- (ሌሎቹም ) የእኛ አስተያየትም እንደዚሁ ነው፡፡ መጥፎውን እናጠቃልልና ጥሩውን ፍለጋ ጥናቱ ይቀጥል፡፡
- እኔ የገረመኝ ግን አለ፡፡
- (አንዱ ) ምንድነው የገረመዎት ክቡር ሚኒስትር ?
- ስለኢንቬስትመንት አውሩ ስንላቸው አንዳቸውም ማውራት አልፈለጉም አይገርምም፡፡
- እሱ እንኳ የእኛ ጥፋት ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
- ስለኢንቬስትመንታችሁ አውሩ ማለታችን ምንድነው ጥፋቱ ?
- ስለሌለ ነገር አውሩ አልናቸዋ "
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ያየሁትን ልናገ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 30 May 2006
Posts: 72

PostPosted: Sun Apr 26, 2009 8:08 pm    Post subject: Reply with quote

ሚድሮክ ደርባን 7 ሚሊዮን ብር በላይ ...
Sunday, 26 April 2009
ሚድሮክ ደርባን 7 ሚሊዮን ብር በላይ የኤሌክትሪክ እዳ አለበት

- አልመሽ የቺፑድ ፋብሪካ 14 ዓመቱ አልተጠናቀቀም

በጋዜጣው ሪፖርተር

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ሚድሮክ ደርባን የሲሚንቶ ፕሮጀክት ላይ 7 ሚሊዮን ብር ክፍያ እንዳልተከናወነለት ተገለጸ፡፡ አልመሽ (የወቅቱ መጠሪያው ) አዋሳ ማስገንባት የጀመረው የቺፑውድ ፋብሪካ 14 ዓመት ቢያስቆጥርም እስካሁን አልተጠናቀቀም፡፡

ከኮርፖሬሽኑ የሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን የጫንጮ ዲስትሪክት አገልግሎት መስጫ ማዕከል ቁጥር 7 ሚድሮክ ደርባን ያለበትን ዕዳ አስመልክቶ ለተጠየቀው ዝርዝር ጉዳዩን አላብራራም፡፡ ይሁን እንጂ ፕሮጀክቱ ካለበት እዳ ውስጥ ሁለት ሚሊየን ብር መክፈሉን ግን አልሸሸገም፡፡

የሰሜን አዲስ አበባ ዲስትሪክት በበኩሉ ስለጉዳዩ ማብራሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ ባይሆንም ፕሮጀክቱ ከነበረበት አጠቃላይ 9 ሚሊዮን ብር እዳ ውስጥ 7 ሚሊዮን ብር በላይ እዳ እንዳለበት አልሸሸገም፡፡

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውና ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ለሪፖርተር እንደገለፁት ሚድሮክ ደርባን ያለበት እዳ ፕሮጀክቱ ድረስ የኤሌክትሪክ ኃይል የተዘረጋበት ሲሆን ሚድሮክ ደርባን በተለያዩ ጊዜያት ክፍያውን እንዲፈፅም በተደጋጋሚ በደብዳቤ ተጠይቋል፡፡

በወቅቱ የምሰሶ ችግር እንደነበር ያስታወሱት እነዚህ ክፍሎች በትዕዛዝ ከየአቅጣጫው በተሰበሰበ ፕሮጀክት ፕሮጀክቱ አጣዳፊ በመሆኑና የሲሚንቶ አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ ስራው በርብርቦሽ መስራቱን ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም የዲስትሪክቱ የስነ ምግባር ጽህፈት ቤት መዝገቡን እየመረመረው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በሌላ ዜና 1986-87 ሲጀመር በሁለት ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል የተባለው አልመሽ የቺፒውድ ፋብሪካ አሁን ድረስ እንዳልተጠናቀቀ የሪፖርተር ምንጮች ተናገሩ፡፡

የአዋሳ ምንጮች እንደገለፁት ፋብሪካው ስራ በመጓተቱ በወቅቱ የነበሩ የክልሉ ባለሥልጣናት መሬቱን በመቀማት ለሌላ አልሚ እንደሚሰጡ ማሳሰባቸውን አስታውሰዋል፡፡

“አልመሽ” a በሚል መጠሪያ ግንባታው የተጀመረው ፋብሪካ በዋናው ባለሀብት ሼህ መሐመድ ሁሴን አልአሙዲና አቶ መሸሻ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ፕሮጀክቱ 8 ዓመት ያህል መቋረጡን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ክፍሎች ተናግረዋል፡፡

8 ዓመት በኋላ 1992 . ስራው እንዲጀመር ሲደረግ ቀደም ሲል ግንባታውን የጀመረው የግል የኮንስትራክሽን ድርጅት ስራውን አቋርጦ ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ተረክቦት እንደነበር የገለፁት ውስጥ አዋቂዎች ከጣሊያን ተገዝቶ የመጣውን ማሽን ለመትከል ከጣሊያን የመጡ ባለሙያዎች ማሽኑን ማንቀሳቀስ አቅቷቸው መመለሳቸውን ገልፀዋል፡፡

እነዚሁ ክፍሎች እንዳሉት ለፋብሪካው በጥሬ እቃነት የሚያገለግለው የዛፍ እርሻ ቢደርስም ፋብሪካው ተጠናቆ ስራ ሊጀምር ባለመቻሉ፣ የተገዙት ማሽኖችም ተተክለው ሊንቀሳቀሱ እንዳልቻሉ አመላክተዋል፡፡ አያይዘውም 2 ዓመት ይጠናቀቃል የተባለ ፋብሪካ 14 ዓመት አስቆጥሮም ሊሰራ አለመቻሉ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል፡፡

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:

I Am an Ethiopian
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ያየሁትን ልናገ

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 30 May 2006
Posts: 72

PostPosted: Sun Apr 26, 2009 8:10 pm    Post subject: Reply with quote

PostPosted: Wed Jul 15, 2009 6:04 pm    Post subject: Reply with quote

---

Last edited by ተድላ ሀይሉ on Wed Jul 15, 2009 6:11 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4459
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Jul 15, 2009 6:08 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁሉም :-
ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
...
Posted: Wed Feb 11, 2009 8:06 pm

ለመሆኑ ይህ አማረ 'ክቡር ሚኒስትር ' እያለ የሚተርክለት ሰው አንድ ሰው ብቻ ነው ? ከሆነስ በወያኔ አደረጃጀት መዋቅር ማን ይህን ያህል መረጃ ሊያገኝ ይችላል ? ቀደም ብሎ አማረ ከሟቹ ክንፈ ገብረ መድህን መረጃ ያገኝ እንደነበረ ተስፋዬ ገብረአብ ገልፆልናል :: ክንፈ ሲሞት ለአማረ የመረጃ ምንጭ የሆነለት ማን ነው ? ግምት ለማስቀመጥ ያህል ሙሉጌታ አለምሰገድ (የለገሠ (መለስ ) ዜናዊ ) የጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ይሆን ይህ ሰው ለለገሠ በጣም ቅርብ እና ታማኝ የሥጋ ዘመዱ እንደሆነ ይወራል :: ለማንኛውም የእነ አማረ ሠፈር ሰሞኑን በብሽቀት ሌላ የሚያውቁትን ሚሥጢር ቢያወጡ እንዴት ያሥቅ ይሆን Rolling Eyes ...

ስለዚህ ሰው ማንነት አቶ አማረ አረጋዊ ዛሬ ረቡዕ ሐምሌ 8 ቀን 2001 .. ባወጣው የሪፖርተር ጋዜጣው ግልጽ በሆነ ቋንቋ አስቀምጦልናል :: ሥም ባይጠቅሥም አቶ ሙሉጌታ አለምሰገድ 'ክቡር ሚኒስትር ' ተብሎ የሚቀርበው ዓምድ ዋና ተዋናይ ነው ::

Quote:
- ...
ከውጭ ወደዚህ በቃልም በጽሑፍም ብዙ አቤቱታ ይመጣል፡፡ እሱ ቅሬታ እየፈጠረበት ነው፡፡ በአንዳንድ ሰዎች ምክንያት ለምን የጽሕፈት ቤቱ ስም ይጠፋል ? ለምንስ አንዳንድ ሰዎች ይነግዱበታል ? እያለ ነው፡፡ ግምገማው ይካሄዳል የሚል ስለሰማ አሁን ሠራተኛው ደስ ብሎታል፡፡
-ማን ነው የፈቀደላቸው ?
-ለዋናው አመልክተው ስለችግራችሁ መወያየትና ችግራችሁን መፍታት መብታችሁ ነው፡፡ እንኳን ከእናንተ መጥቶ እኛም ቀደም ብለን ማድረግ የነበረብን ነው ተብሎ ከበላይ ተፈቅዶላቸዋል ይባላል፡፡
-እኔ አላወቅኩትም
-እርስዎን የሚመለከት ስለሆነ ላይሰሙት ይችላሉ፡፡
-እንዴት እኔን ?
-አቤቱታና ቅሬታው እርስዎ ላይ ነው፡፡
-እኔ በተራ ሠራተኛ ልገመገም ? ስማ ደረጃዬኮ በሚኒስትር ደረጃ ነው፡፡ እንዲያውም ዝም አልኩህ እንጂ ክቡር ሚኒስትር እያልክ ማነጋገርም ነበረብህ፡፡
-ይቅርታ ክቡር ሚኒስትር ስለምንቀራረብ እንጂ ንቀት አይደለም
-ስማ እኛ በለፋነው ሌላው እየተሾመ ነው፡፡ እኔ በታገልኩት ሌላው እየተጠቀመ ነው፡፡ ከሌላው እሻላለሁ እንጂ አላንስም፡፡
-አንዱ በሠራተኛው ዘንድ ያለው ቅሬታ እርስዎ አልተሾምኩም እያሉ ውስጥ ለውስጥ ያወራሉ የሚል ነው፡፡
-አልገባኝም ?
-ባለፈው ጊዜ የሚኒስትሮች ሹም ሽር ሲደረግ እርስዎ ስላልተሾሙና ሚኒስትር ሆኜ ያን መሥሪያ ቤት እመራለሁ ብለው ጠብቀው ስላልተሾሙ "እኔ በታገልኩት ሌላው ተሾመ " እያሉ አንድ ሆቴል ውስጥ በመጠጥ ሃይል ተገፋፍተው ተናግረዋል ይባላል፡፡
-የት ሆቴል ተባለ ?
-ክቡር ሚኒስትር በምሣ ሰዓት ሁሌ እየሄዱ በነፃ የሚበሉበት ትልቁ ሆቴል ውስጥ ነው የተባለው
-በል ሌላ ጊዜ በስፋት እናወራለን፡፡ አሁን ሰውየው ውጭ አገር ለስብሰባ ስለሚሄዱ እዚያ የሚያደርጉትን ንግግር ላርቅቅላቸው፡፡
ክቡር ሚኒስትር በሠራተኛው ዘንድ ያለው ሌላው ቅሬታም ይህ ነው፡፡ "ለዋናው ሰው ንግግር የማረቅላቸው እኔ ነኝ " እያሉ ያወራሉ ይባላል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከድሮ ጀምሮ እስከ አሁን ብዙ የሚያነቡ፣ የሚፅፉ ጐበዝ ተናጋሪ መሆናቸው እየታወቀ እርስዎ እኔ ነኝ የማረቅላቸው ብለው ሲያወሩ ሠራተኛው ይታዘባል፣ ይስቃል፡፡
-አንተም እንደ ሠራተኛው ነህ ማለት ነው፡፡ በሠራተኛው አባባል የተደሰትክ ትመስላለህ
-አይደለም ክቡር ሚኒስትር እዚያ ሰምተው ከሚደነግጡ አንዳንዱን ልንገርዎት ብዬ ነው፡፡ ሠራተኛው ስለ እርስዎ የተለያዩ መረጃዎች ከተለያዩ መሥሪያ ቤቶች እያሰባሰበ ይመስለኛል፡፡
-ከየት ከየት መሥሪያ ቤቶች ...

ምንጭ :- ሪፖርተር ጋዜጣ : ረቡዕ ሐምሌ 8 ቀን 2001 .. :: ክቡር ሚኒስትር

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4459
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Jul 26, 2009 11:39 pm    Post subject: Reply with quote

---

Last edited by ተድላ ሀይሉ on Sun Jul 26, 2009 11:45 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4459
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Jul 26, 2009 11:42 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁሉም :-

ወያኔ ለሰላዮቹ እና ለቅጥር ነፍሰ -ገዳዮች የሚበትነው ብር እያነሠው የመጣ ይመሥላል :: ለዚህም ይመሥላል የብርን የምንዛሪ መጠን ዝቅ በማድረግ ተጨማሪ የውጪ ገንዘብ ይገኝ ይሆን ብሎ ባለፈው ሣምንት ውስጥ የብርን ከአሜሪካን ዶላር ጋር ያለውን ምንዛሪ 10 በመቶ ዝቅ ያደረገው :: ይህ ወያኔ የተዘፈቀበት የፋይናንስ ቀውስ ወዴት ይገፋው ይሆን ? ምናልባት በሼሁ ንብረት ላይ የውርስ ርምጃ መውሰዱን በተጠናከረ ሁኔታ እንዲቀጥል ሊገፋው ይችላል ብዬ አስባለሁ :: አሁንም ወያኔ ፈራ ተባ እያለ በሼሁ ተቋሞች ላይ ክሥ ማንቀሣቀሱን አላቋረጠም ::

ሪፖርተር ጋዜጣ : እሁድ ሐምሌ 19 ቀን 2001 .. :: ሚድሮክ ተከሰሰ ::

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጆጆ

ኮትኳች

Joined: 06 Oct 2003
Posts: 139

PostPosted: Tue Jul 28, 2009 5:12 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም
አላሙዲ ጂኒ ወላ ነፋስ ገባ ተያይዘው ገደል ይግቡ !
አንድም ነገር ላይተርፈን ባይወራስ . ግዜ በደንብ እንዳላች ያስታውቃል መታደል ነው ግዜ መገኘቱ ::ደካማዎች ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4459
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Jul 28, 2009 11:18 pm    Post subject: Reply with quote

---

Last edited by ተድላ ሀይሉ on Tue Jul 28, 2009 11:24 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4459
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Jul 28, 2009 11:20 pm    Post subject: Reply with quote

ጆጆ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም
አላሙዲ ጂኒ ወላ ነፋስ ገባ ተያይዘው ገደል ይግቡ !
ሌላውን ምስኪኑን ኢትዮጵያዊ ገደል ያገባሉ እንጂ እነርሱ እስካሁን ገደል አልገቡም Very Happy Very Happy Very Happy Very Happy Very Happy
Quote:
አንድም ነገር ላይተርፈን ባይወራስ .

ከምኑ ነው ያልተረፈን ? ኪሣራው እንደሆነ የአሁኑ ብቻ ሣይሆን የወደፊቱም ትውልድ ኪሣራ ጭምር ነው :: ማውራቱን ግን የፈለገ ያወራል : ያልፈለገ ይተዋል :: እንዲህ እንደ ጆጆ ያለው የዞረበት ደግሞ ይዘባርቃል ::
Quote:
ግዜ በደንብ እንዳላች ያስታውቃል መታደል ነው ግዜ መገኘቱ ::

ያንተን ጊዜ መትረፍ የሚያሣየው ለገንቢ አስተያዬት ወይም ውይይት ሣይሆን ለስድብ የምታደርገው እሽቅድድም ነው ::
Quote:
ደካማዎች ::
አዬ ድሮውንስ ከምን ጋር ጨዋታ ይባል የለም Very Happy Very Happy Very Happy Very Happy Very Happy Very Happy

በርታ በስድብ ችሎታህ ተመርቀህ ዲግሪ ትጭናለህ Razz Razz Razz Razz ::

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4459
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Aug 25, 2009 5:43 pm    Post subject: Reply with quote

በዋርካ ችግር ምክንያት የተደገመ ::

Last edited by ተድላ ሀይሉ on Tue Aug 25, 2009 6:15 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4459
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Aug 25, 2009 5:47 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁሉም :-

በዚህ መድረክም ሆነ በሌሎች መድረኮች ሼህ መሐመድ አላሙዲን ለኢትዮጵያ ታላቅ ባለውለታ እንደሆኑና ያለእርሣቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያልቅለት እንደነበረ የሚወተውቱ ብዙ እበላ ባዮች : አስመሣዮችና ግራ የተጋቡ ሰዎች ሲዘግቡ ኖረዋል :: ሃቁ ነው ወይ ?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ባደረገው ሪፖርት መሠረት በውጪ ሃገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚልኩት ገንዘብ ዋነኛው የገቢ ምንጭ እንደሆነ ወያኔ ራሱ አምኗል ::

ዓመት _____________________የገቢ መጠን (በአሜሪካን ዶላር )
1998 .. (2005/06)__________________355,000,000
1999 .. (2006/07)__________________633,000,000
2000 .. (2007/08 )_________________805,000,000

መረጃው እንደሚያመለክተው ይህ በኦፊሴል በባንክ የተላከው የገንዘብ መጠን ሲሆን በግለሰቦች የተላከውን ገንዘብ እና በዓይነት (በቁሣቁስ ) መልክ ወደ ኢትዮጵያ የገባውን አያጠቃልልም ::

ምንጭ :- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 2000 .. ዓመታዊ ሪፖርት :: ገጽ 88

እንግዲህ ይህንን ዓይነት ያፈጠጠ ዕውነት ተክዶ ነው ሼህ መሐመድ አላሙዲን የኢትዮጵያ አዳኝ ናቸው ተብሎ የሚደሰኮረው :: እርሣቸው የወያኔ የዘረፋ ቡድን መሪ እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ አዳኝ ሊሆኑ አይችሉም ::

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8, 9, 10  Next
Page 8 of 10

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia