WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
%@#$?&
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 47, 48, 49
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
T

ኮትኳች

Joined: 11 Aug 2007
Posts: 290

PostPosted: Thu Jul 14, 2011 9:46 pm    Post subject: Reply with quote

ትርንጎ * እንደጻፈ(ች)ው:
<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<ውሸት አንድ እዚህ ዋርካ የሚመጣ ጉዋደኛዬ የነገረኝ አጭር ቁም ነገር ልቤ ውስጥ ዛሬ ስትብሰለሰል ዋለች :: 'የምትወጃቸውንና የምታከብሪያቸውን ሰዎች በጣም ቀርበሽ ውስጣቸውን ለማወቅ አትሞክሪ : ሁላችንም የተደበቀ ጉድፍ አይጠፋንምና ' !

ትርንግሻ ሰላም ነው ? ውድድ ያደረክዋት አባባል :
_________________
“Love is like the wind, you can't see it but you can feel it."
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ትርንጎ *

ዋና ኮትኳች

Joined: 06 Oct 2008
Posts: 501

PostPosted: Fri Jul 15, 2011 12:10 pm    Post subject: Reply with quote

<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<ደስታና ምንጩ >>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>

"አንድ ነገር ሆኛለሁ : ደስታ በፍፁም አይሰማኝም " ያለኝን ጉዋደኛዬን አፍጥጬ አየሁት :: ለምን እንደሆነ ገባውና "አውቃለሁ : እግዜር የሰጠኝን ተመስገን ማለት ሲገባኝ ..." አንጠልጥሎ ተወው :: "አይዞህ " ከማለት ሌላ ምን እንደምለው ግራ ገባኝ :: በልቤ የራሴውን አባባል አሰላሰልኩ :: እዚችው አምድ ላይ እንኩዋን ስለደስታ የጫርኩዋት ፅሁፍ አለች ...ገንዘብ ደስታ እንደማያመጣ : ይመስለናል እንጂ :: ይህ ሰው በህይወቱ የሰራቸው ቁምነገሮችና አሁን ያለበት ቦታ የት የሌለ ነው : በተለይም የሰራሽው ቁምነገርና ያፈራሽው ሀብት ተብዬ ብጠየቅ የልጆቼን ስም ከመቁጠር ሌላ ቤሳቤስቲን ከሌለኝ እኔይቱ ጋር ቢወዳደር :: "እንግዲህ " አልኩት ፈገግ ባስብለው ብዬ "እንግዲህ በባዶ ሜዳ ፍንጥር ፍንጥር የሚያደርገኝን ደስታ አላካፍልህ ነገር ..." ግቤን መታሁ ::

የደስታ ምንጩ ምንድነው ? እኔ መልሱን አላውቀውም : ምንጩም ብዙ ይመስለኛል :: ጤና : ፍቅር : ቤተሰብ : ጉዋደኛ : ልጆች : ጥሩ ስራ : የፈለጉበት ቦታ መድረስ : ውበት : ገንዘብ ... ሊባል ይችላል : እንደመላሹ ማለቴ ነው :: እንደኔ እንደኔ መጀመሪያ ዛሬ ምንም ትሁን ምንም በእጃችን ያለችውን "ተመስገን " ብለን ባለን መደሰትን የመሰለ ነገር የለም : ሁሌም የባሰ ቦታ ላይ ያለ ሰው አለና :: "ጫማ የለኝም ብዬ ሳዝን እግር የሌለው አየሁ " የምትለዋ አባባል ትልቅ ቁም ነገር ነች :: አይናችን ታውሮ ነው እንጂ ስንት የሚያስደስት ነገር በየቀኑ ይፈጠራል :: ማታ እንቅልፍ ሲወስደን ፀጋ ነው : ስንቶች አንቅልፍ አጥተው ሲንቆራጠጡና መድሀኒት ሲቅሙ ያድራሉና :: ጠዋት ስንነቃ በረከት ነው : ብዙዎች አልታደሉምና :: ከቤታችን ወጥተን በሰላም መመለሳችን መታደል ነው : እንደወጡ የቀሩ አሉና :: ቢያመን ወይም አደጋ ቢደርስብን እንኩዋን 'በዚሁ ይለፍ " ማለት መቻል አለብን : ስንት የባሰ ህመምና አደጋ አለና :: ስላለፍኩበት ማውራት ቀላል አትበሉኝና የባሰው ቢደርስብን እንኩዋን ህክምና በማግኘታችንና አስታማሚ ባለማጣታችን ተመስገን ብንለው ምናለበት ::

በቀደም እዚሁ konjitዬን ፖስት አንዲት አረብ አገር ሄዳ ኑሮ ሲያስመርራት መርዝ የጠጣች ልጅ ታሪክ ሳነብ በሌላው አገር በተለይም አሜሪካ ተቀምጠን "የዚህ አገር ኑሮ ሰለቸኝ : አሁን ይሄ ኑሮ ነው ?" የምንለውን ግፈኞች አሰብኩና እንደው እንዴት ለእግዜሩም ግራ የምናጋባ ፍጡራን እንሆን ብዬ ተገረምኩ :: አንዳንዶቻችን ምድረ -ገነትን ከፍቶ ቢያስገባንም አቤቱታችን የሚያቆም አይመስለኝም ::

በሉ አንድ ጉዋደኛዬ እንዳለኝ ብሶት አላብዛባችሁና የኔ ማሮች ዛሬ እጃችን ላይ ያለችውን ተመስገን ብለን እንደሰትባት : በረከቱንም እንዲጨምርልን :: ያለንን ይባርክልን : ፀጋ በረከቱን ያውርድልን : ከሁሉም በላይ ጤናውን አይንሳን :: በርቱልኝ !

የኔዋ T እንዴት ነሽልኝ :: ሁሉ ሰላም ነው እሙ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Report post
መንኮራኩር

ዋና ኮትኳች

Joined: 28 Mar 2006
Posts: 528

PostPosted: Sat Jul 16, 2011 2:31 pm    Post subject: Reply with quote

ቀጭኑን ባንቀጫቅጨው ተንቀጫቅጮ ቀረብኝ ! በደህና ነው ?

አንዳንዴ ሳስበው ሁለመናሽ ለፍልስፍና የተፈጠርሽ ይመስለኛል . አብዛኛዎቻችን ከስንት አመት በፊት የተነገረውን እያደመጥን ራሳችንን እንሸነግላለን አንቺ ደግሞ ከስነ ልቦና ጋር ገጥመሻል ::

ትርንጎ * እንደጻፈ(ች)ው:
<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<<ደስታና ምንጩ >>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>

"አንድ ነገር ሆኛለሁ : ደስታ በፍፁም አይሰማኝም " ያለኝን ጉዋደኛዬን አፍጥጬ አየሁት :: ለምን እንደሆነ ገባውና "አውቃለሁ : እግዜር የሰጠኝን ተመስገን ማለት ሲገባኝ ..." አንጠልጥሎ ተወው :: "አይዞህ " ከማለት ሌላ ምን እንደምለው ግራ ገባኝ :: በልቤ የራሴውን አባባል አሰላሰልኩ :: እዚችው አምድ ላይ እንኩዋን ስለደስታ የጫርኩዋት ፅሁፍ አለች ...ገንዘብ ደስታ እንደማያመጣ : ይመስለናል እንጂ :: ይህ ሰው በህይወቱ የሰራቸው ቁምነገሮችና አሁን ያለበት ቦታ የት የሌለ ነው : በተለይም የሰራሽው ቁምነገርና ያፈራሽው ሀብት ተብዬ ብጠየቅ የልጆቼን ስም ከመቁጠር ሌላ ቤሳቤስቲን ከሌለኝ እኔይቱ ጋር ቢወዳደር :: "እንግዲህ " አልኩት ፈገግ ባስብለው ብዬ "እንግዲህ በባዶ ሜዳ ፍንጥር ፍንጥር የሚያደርገኝን ደስታ አላካፍልህ ነገር ..." ግቤን መታሁ ::

የደስታ ምንጩ ምንድነው ? እኔ መልሱን አላውቀውም : ምንጩም ብዙ ይመስለኛል :: ጤና : ፍቅር : ቤተሰብ : ጉዋደኛ : ልጆች : ጥሩ ስራ : የፈለጉበት ቦታ መድረስ : ውበት : ገንዘብ ... ሊባል ይችላል : እንደመላሹ ማለቴ ነው :: እንደኔ እንደኔ መጀመሪያ ዛሬ ምንም ትሁን ምንም በእጃችን ያለችውን "ተመስገን " ብለን ባለን መደሰትን የመሰለ ነገር የለም : ሁሌም የባሰ ቦታ ላይ ያለ ሰው አለና :: "ጫማ የለኝም ብዬ ሳዝን እግር የሌለው አየሁ " የምትለዋ አባባል ትልቅ ቁም ነገር ነች :: አይናችን ታውሮ ነው እንጂ ስንት የሚያስደስት ነገር በየቀኑ ይፈጠራል :: ማታ እንቅልፍ ሲወስደን ፀጋ ነው : ስንቶች አንቅልፍ አጥተው ሲንቆራጠጡና መድሀኒት ሲቅሙ ያድራሉና :: ጠዋት ስንነቃ በረከት ነው : ብዙዎች አልታደሉምና :: ከቤታችን ወጥተን በሰላም መመለሳችን መታደል ነው : እንደወጡ የቀሩ አሉና :: ቢያመን ወይም አደጋ ቢደርስብን እንኩዋን 'በዚሁ ይለፍ " ማለት መቻል አለብን : ስንት የባሰ ህመምና አደጋ አለና :: ስላለፍኩበት ማውራት ቀላል አትበሉኝና የባሰው ቢደርስብን እንኩዋን ህክምና በማግኘታችንና አስታማሚ ባለማጣታችን ተመስገን ብንለው ምናለበት ::

በቀደም እዚሁ konjitዬን ፖስት አንዲት አረብ አገር ሄዳ ኑሮ ሲያስመርራት መርዝ የጠጣች ልጅ ታሪክ ሳነብ በሌላው አገር በተለይም አሜሪካ ተቀምጠን "የዚህ አገር ኑሮ ሰለቸኝ : አሁን ይሄ ኑሮ ነው ?" የምንለውን ግፈኞች አሰብኩና እንደው እንዴት ለእግዜሩም ግራ የምናጋባ ፍጡራን እንሆን ብዬ ተገረምኩ :: አንዳንዶቻችን ምድረ -ገነትን ከፍቶ ቢያስገባንም አቤቱታችን የሚያቆም አይመስለኝም ::

በሉ አንድ ጉዋደኛዬ እንዳለኝ ብሶት አላብዛባችሁና የኔ ማሮች ዛሬ እጃችን ላይ ያለችውን ተመስገን ብለን እንደሰትባት : በረከቱንም እንዲጨምርልን :: ያለንን ይባርክልን : ፀጋ በረከቱን ያውርድልን : ከሁሉም በላይ ጤናውን አይንሳን :: በርቱልኝ !

የኔዋ T እንዴት ነሽልኝ :: ሁሉ ሰላም ነው እሙ ::

_________________
Peace has to be created, in order to be maintained. It is the product of Faith, Strength, Energy, Will, Sympathy, Justice, Imagination, and the triumph of principle. It will never be achieved by passivity and quietism.

Dorothy Thompson:
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ከምካሚው

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 23 Mar 2008
Posts: 66

PostPosted: Sun Jul 17, 2011 3:14 am    Post subject: Reply with quote

ነገሮች : ያለን :አመለካከት : ለደስተኝነታችን : ወሳኝ : ነዉ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መንኮራኩር

ዋና ኮትኳች

Joined: 28 Mar 2006
Posts: 528

PostPosted: Sun Jul 17, 2011 11:24 am    Post subject: Reply with quote

የደስታ ምንጩ አእምሮ ሲያስብና ልብ ሲያመዛዝን ነው ::

ያጣነውን ሳይሆን የሰጠንን እያሰብን እግዚአብሄርን የምናመሰግን ከሆነ !

የተዘጋውን ሳይሆን የተከፈተው በር ላይ የምናተኩር ከሆነ !

አእምሮአችን አስቦ ልባችን ፈቅዶ የምናፈቅር ከሆነ !

ሰዎች ሲበድሉን ይቅር የምንል ከሆነ !
እኛም ስንበድል ይቅርታን የምጠይቅ ከሆነ !
ሃሰትን ንቀን እውነትን የምንከተል ከሆነ !

ለሰው ፍቅር ለጌታ ክብር የምንሰጥ ከሆነ

ውሳጣዊ ደስታ ማግኘታችን የግድ ነው ::
_________________
Peace has to be created, in order to be maintained. It is the product of Faith, Strength, Energy, Will, Sympathy, Justice, Imagination, and the triumph of principle. It will never be achieved by passivity and quietism.

Dorothy Thompson:
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ትርንጎ *

ዋና ኮትኳች

Joined: 06 Oct 2008
Posts: 501

PostPosted: Wed Jul 20, 2011 6:10 pm    Post subject: Reply with quote

ከምካሚው እንደጻፈ(ች)ው:
ነገሮች : ያለን :አመለካከት : ለደስተኝነታችን : ወሳኝ : ነዉ ::

ከምሽ በጣም ልክ ብለሀል :: ትንሽ ብታሰፋት ደግ ነበር :: ለእኔ እንደገባኝ ከሆነ በፈረንጆቹ አባባል 'Is the glass half empty or half full?' መልሱን የሚወስነው የራሳችን አመለካከት ይመስለኛል ::

መንኩራኩሬ እንዴት ነህልኝ ? አቤት ቁም ነገር !!! ቀጭኑ ምቀኛ ሆኖ ነው እንጂ የተለወጠ ነገር የለም :: እጅ ነስቻለሁ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Dec 06, 2011 6:41 am    Post subject: Reply with quote

በባለቤቶቻቸው ከተረሱ ቤቶች Arrow

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ትርንጎ *

ዋና ኮትኳች

Joined: 06 Oct 2008
Posts: 501

PostPosted: Sat Dec 31, 2011 12:47 pm    Post subject: Reply with quote

እንዴት ናችሁልኝ ? ኑሮ : ጤና : ቤተሰብ : ስራ : ትምህርት : ቀየው : እርሻው ሁሉ ደህና ? እኔ እንዳለሁ አለሁላችሁ : የፈጣሪያችን ክብሩ ይስፋ :: ግን ምነው እንዲህ ጥፍት አላችሁ ግን ? Very Happy

ሰሞኑን በስራም በዙረትም ተዳክሜ የዛሬን ሌሊት እንዴት ሽዋዋዋ ባለች እንቅልፍ እንደማሳልፋት ሳቅድ ነበር ትላንት የዋልኩት : ድንቄም -:: እግሬን ማነቃነቅ ሲያቅተኝ ቀና ብል የኔ ቀጮ ከግርጌዬ ብርድልብሱን እንደተከናነበ ተኝቶዋል :: 'ሳትወልድ ተኛ " ነው ያለው ያገሬ ሰው ? አልጋዬን ለቅቄ ይኸው ወደናንተ መጣሁ :: ልቤ ውስጥ ነበራችሁና ጥሩ አጋጣሚ ሆነልኝ ::

ይች አመት ለኔ የተባረከች አመት ነበረች : በሚገርም ሁኔታ :: የህይወት ህልሜ እውን ሆኖ ሌላ ህልም የተፈጠረባት : የልጆቼ ሰላምና ጤንነት የገነነባት : ብዙ ኧረ እጅግ ብዙ የህይወት ትምህርት የቀሰምኩባት : ድንቅ ሰዎች የተዋወኩባት : ከህይወቴ የወጡ ሰዎችን መልሼ ያገኘሁባት : ህይወቴን የሚረብሹ ሰዎችን ደግሞ ድፍረት አግኝቼ እቅጩን ተናግሬ የሸኘሁባት : ውብ ጉዋደኞቼን እንደድሮው ባያገኙኝም ሳይቀየሙ በማበረታታት ከሁዋላዬ የቆሙባት (ትልቅ ነገር ): የምፈራው ሞትን 'ለካስ እንቅልፍ ነህ " እያልኩ የተዳፈርኩበት : ከሁሉ በላይ ----- የተላበስኩባት አመት ነች :: እውነቴን ነው የምላችሁ በአይምሮ እድሜዬ ላይ አምስት አመት የጨመርኩ ነው የመሰለኝ ...ህይወት ትምህርት ቤት !

አዲሱ አመት ከደጃፍ ቆሞዋል :: ከሁሉ በላይ አቅፎና ደግፎ ለዚህ ያበቃን አምላክ ይመስገን :: አዲስ አመት አዲስ ተስፋ ነው :: መልካሙን ሁሉ እንዲያዘንብልን : ፀጋውን እንዲያበዛልን : ጤንነቱን እንዲያርከፈክፍልን : አገራችን እንዲያስብልን ከልቤ እመኛለሁ :: በቸር ያገናኘን !

ብሩክ አዲስ አመት !

ከትልቅ አክብሮት ጋር እህታችሁ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Report post
ስርርር

ዋና ኮትኳች

Joined: 05 Mar 2010
Posts: 732

PostPosted: Tue Jan 03, 2012 11:31 pm    Post subject: Reply with quote

Smile እንክዋን አደረሰሽ እናቱ !....ጥፍት ስትይ ግዜ ቤትሽም ራሱ ወና ሆኖ ወደታሪክነት ሊቀዬር ምንም እልቀረውም ነበር :: አይ ሚስ !
ላቭ
ትንሹ ወንድምሽ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ትርንጎ *

ዋና ኮትኳች

Joined: 06 Oct 2008
Posts: 501

PostPosted: Wed Jan 11, 2012 3:48 pm    Post subject: Reply with quote

ወንድምዬዬዬ እጅ ነስቻለሁ !!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Mar 14, 2012 5:04 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ትርንጎ :-

የሚጻፍ ቢጠፋም ለእግዚአብሔር ሰላምታ ብቅ ይባላል ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ኤልሳ *

ኮትኳች

Joined: 27 Jul 2006
Posts: 191

PostPosted: Sat Jun 16, 2012 12:54 am    Post subject: Reply with quote

ትርንጎዬ የት ጠፋሽ ቆንጆ .... ጠይሙ ባሌ አንቺ የጻፍሽው ልብወለድ ... አድማስ ሬድዮ ላይ ሰምቼው እንዴት ደስ ይላል መሰለሽ .... ቆይ ግን ያቀረበችው ልጅ አንቺ ነሽ እንዴ Laughing አትጥፊ ቆንጆ ሲመቺሽ አለሁ በይን ...
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Jan 02, 2013 4:03 am    Post subject: Reply with quote

ኧረ ትርንጎ የት ጠፋሽ Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 47, 48, 49
Page 49 of 49

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia