WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የሙኒከ ቅዱስ ገብርኤል አስተዳዳሪ ችግር
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ


 
View previous topic :: View next topic  
Author Message
ሰዋሰው

አዲስ


Joined: 25 Nov 2003
Posts: 20

PostPosted: Tue Feb 15, 2011 4:08 am    Post subject: Reply with quote

ውድ የሆናችሁት ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላለፉት ሣምንታት እዚህ ቤተክርስቲያናችን አካባቢ ስላለው ግርግር ቢከፋም ቢለማም በሚል በየትኛዉም ክፍለ ዓለም ያሉ ያገሬ ሕዝቦች እንዲያዉቁት በምችለው አቅሜ ስሞጫጭር እና ሳሰለቻችሁ ነበር :: ከላይ እንደምታዩት 12/02 የሙኒክ አካባቢ ሕዝብ ስብሰባ ተሰብስቦ አገልግሎት ላይ የነበሩት ቄስ መስፍን /ማርያም (ወደ ፊት ስጽፍ አያት ስም መጨመር እሞክራለሁ ) ከአገልግሎታቸዉ እንዲሰናበቱ ወስኑዋል :: ስለ ዝርዝር ሁኔታው ከመግባቴ በፊት ግን ብቅድሚያ በእዉነት የተሰማኝን ስሜት ሳልናገር ባልፍ እና ስለ ደብሩ ምእመናን የኢትዮጵያዊ ጨዋነት በአለምላይ ላላችሁት ኢትዮጵያዉያኖች ባልጽፍ ህሊናዬ ዪወቅሰኛል ብዬ ስለማስብ በመጀመርያ ስለ ምእመኑ ላዉጋችሁ ::
ከሁሉ በማስቀደም ሃይማኖታችን የጸደቀች የተከበረች ያማረች ትሁንልን የሙኒክ ምእመናን ስላኮራችሁኝ እግዚአብሔር ከሁሉ ነገር ጠብቆ ለሀገራችሁ ያብቃችሁ :: ተመልከቱ እንግዲህ ይህንን የመሰለን ትህትና የእግዚአብሔርን ፍቅር ሰው አክባሪነትን አስተዋይነትን ይቅር ባይነትን መንፈሣዊነትን ወንድማማች /እህትማማችነትን ስለ ሃይማኖታችን ተቆርቁዋሪነታችንን ነው ቄስ መስፍን እርስ በርስ ለማናቆር ከላይ ታች ሲሉ የቆዩት :: እኔ በተለይ ጊዜአቸዉን ስዉተዉ ይሄንን ጉዳይ እዚህ ደረጃ ላይ ላደረሱልን ሰዎች በሙኒክ ምእመናን ስም እግዚአብሔር ይስጥልኝ እላለሁኝ :: ይሄ ነው ኢትዮጵያዊነት አንድ መጥፎ ነገር ከአፋቸዉ ኮሽ ሳትል በአክብሮት በትህትና በሃይማኖታዊ መንፈስ እረ ቃላት ያጥራል ( አባት ልጁን መንፈሣዊነትን ሲያስተምር ? ለዛዉም ቄሱን ? ይገርማል ! ይሄ ነው ጨዋነት ይሄ ነው አስተዋይነት የቄስ መስፍንን የወደፊት ህይወት ባላዉቅም በዚህች ቀን ብዙ ነገር እንደተማሩ በጣም እርግጠኛ ነኝ :: ምንም አያዉቁም ሲሉዋቸዉ የኖሩት ፖለቲከኞች ሲሉዋቸዉ የኖሩት ሰዎች ከሃይማኖታቸው ሌላ ምንም ፍላጎትና ግብ እንደሌላቸዉ በጳጳስ ፊት ማን ፖለቲከኛና አግባብ የጎደለው እንደሆነ በንጽህናቸዉ በቤተ ክርስቲያናቸዉ በመልአኩ በቅ /ገብርኤል ቤት ዉስጥ ማንነታቸዉን አስመስክረዋል ቄስ መስፍን ሲንቁዋቸዉ አንገታቸዉን ደፍተዉ ሃይማኖታቸዉን ሙጥኝ ብለው እንዴት አድርገዉ ልጆቻቸዉን ማሳደግ እንደሚችሉ ሰዉ እንዲህ አይነት አዋቂ ወንድምና እህቶችም አሉልን እንዴ እስከሚል ድረስ ነፃ ኢትዮጵያዉያን መሆናቸዉን አሳዉቀዋል :: ይሄ ከንግዲህ በሁዋላ የትም ይሂዱ የትም ሌላም ስራ ሰርተዉ ይተዳደሩ ወይንም እግዚአብሔርን ካልፈሩ (በክህነትም ቢኖሩ ) በብዙ ብር የማይገኝ ትምህርት ነው የዚያች ቀን የተማሩት ለወደፊት ኑሮዋቸዉ በጣም ይጠቅማቸዋል ብዬ አስባለሁ እርግጠኛ ነኝ እራሳቸዉንም እንዲታዘቡ ሆነዋል ::
እኔ በበኩሌ እንዴት ቄስ የቤተክርስቲያን ገንዘብ ዘርፎ እንደገና እዛዉ ታቦት ቤት ይቆማል ? እኔ እዉነቴን ነው በጣም ደፋርነት ነው ትልቅም ኃጢአት ነው ምን ዓይነት ህሊና እንዳላቸዉ እግዚአብሔር ይወቅ , ስለ እርሳቸዉ እስከዛሬ በጣም ሳስብ ነበር :: እንግዲህ አሁንም እኔ ምንም የምመኝላቸዉ ነገር ብዙ የለም ግን እንድ አንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ እግዚአብሔር አሁንም አይልለያቸዉ የሰዉ ልጅ በሰዉ ልጅ ላይ ፈራጅ መሆን የለበትም የሚል የራሴ የሆነና ሃይማኖታችንም እንደሚያስተምረው እምነት አለኝ ስለዚህ ፈራጅ እግዚአብሔር ነዉ ነገር ግን አሁንም በተለይ ከዚህ አካባቢ እና የትም ቢሆን ከቤተክርስቲያን በጣም እንዲርቁልኝ በጥሞና እለምናቸዋለሁ :: እንደ ኦርቶዶክስ ምእመን ሆነዉ የመኖር መብታቸዉ ሆኖ ከእንግዲህ ግን በአገልግሎት ሰበብ ወደ ሌላ ዘርፋ እንዳይተላለፉ በሚቀጥለው ጽሑፌ አለም ላይ ያለ ሕዝብ እንዲያዉቅ ፎቶዋቸዉን እዚህ ላይ ለማዉጣት እሞክራለሁ ::
የሆነ ሰዉ በዚሁ የስብሰባ ቀን የሽቱትጋርቱ ቄስ ጴንጤ ናቸዉ ሲል ነበር (እግዚአብሔር ምን ጊዜ ላይ እንዳደረሰን ተመልከቱ ወገኖቼ ! እስቲ ይሄንን ቁጭ ብሎ መስማት አይዘገንንም ? ያዉም ጳጳስ ፊት ነው እንግዲህ እንዲህ የሚባለው ደግሞም ጳጳሱም ሁኔታዉን እንደሚያዉቁ ተናግረው እርርፍፍ .. እረ ሃይማኖታችንን እናድን ?) ስለሌላው ሌላ ጊዜ አሁን እዚህ ስላለዉ ስለ ቄስ መስፍን ......ስለዚህ ጴንጤዎች ዱሮ ዱርዬዉቹን ሲመለምሉ እግዚአብሔር የሚወድደዉ ሌባዉን ጫት ቃሚዉን ሴተኛ አዳሪዉን ሲሉ ሰምቼአለሁ እርሳቸዉንም እንግዲህ ክራይቴርያ ሰለሚያሙዋልሉ እንደዉም ወደ እርሳቸዉ ቤት ሰሞኑን ይመጣሉ የሚልና እዚህ ላይ የጴንጤ መቀለጃ ሊያደርጉን ነው ብዬ ጽፌ አልነበረም በነጋታዉ የጴንጤዎች ኮንስርት ላይ ለቄስ መስፍን አንድ መዝሙር እና ኦርቶዶክሶችን ስላስቀየሙ የመንፈስ ጸሎት (እርግጠኛ አይደለሁም የጫት ቤት ወሬም ሊሆን ይችላል ) ተደርጎላቸዋል ይባላል :: ያም ሆነ ይህ ግን አማራጭ አለ ለማለት ያክል ነዉ ::
በነገራችን ላይ ሀገር ቤት እዉነት ይሁን ዉሽት አላዉቅም ጴንጤዎች ጳጳስ ኮንቨርት አደረግን ብለው ቪድዮ አዉጥተዋል ይባላል :: እዚህም እንግዲህ ላይቭ ያሳዩን ::
በተረፈ ዛሬ ስለ ስብሰባዉ አጠቃላይ ይዘት ጊዜ ስለሌለኝ ለመጻፍ አልፈልግም ወደፊት ግን ቆንጆ ትንታኔ ይዤላችሁ እመጣለሁ ለአሁን ግን ወደ እለቱ ቁም ነገር ስንመለስ እንግዲህ ቄስ መስፍን 20 ዓመት የዲክታተር ቤተክርስቲያን አስተዳደር በሁዋላ ሆስኒ ሙባረክ ላይ ስላልደረሱበት እያዘኑ ሆስኒ ሙባረክ አርብ እሳቸዉ ቅዳሜ የግዴታ ቤተክርስቲያናችንን እንዲሰናበቱ ተደርገዋል ሆስኒ ስዊትዘርላንድ እሳቸዉ ደግሞ በጣም በትንሹ 165 ሺህ ኦይሮ የት እንዳስቀመጡት እስካሁን እርሳቸዉም የሚያዉቁት እኛም የደረስንበት የለም ጉዳዩን ግን ለጊዜዉ አብሻ ኢንተርፖሎች (ፕራይቬት ዲቴክቲቮቻችን = ማለት ዉስጥ አዋቂዎች )ይዘዉታል የሚባል ጭምጭታ አለ :: ያም ሆነ ይህ ግን አሁን ሁሉም ሰዉ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ዪችላል በእርሳቸዉ ምትክ ለጊዜዉ በርሊን ያሉት ቅዳሴ ባለ ቀን እየመጡ ያገለግላሉ ሲባል ሕዝቡ እልልታ አዳራሹን አደበላለቀው ምን አይነት የታደሉ ሰዉ ናቸው ! ብቻ ሁሉም ሰው በጣም ነው ደስ ያለዉ :: ሌላው እሳቸዉን እንዲያግዙዋቸዉ የተደረጉት መርጌታ ዳዊት እዚህ ቅርብ ኑርንበርግ ያሉት ናቸዉ :: እለቱ ያሳዝን ነበር የቄስ መስፍን በንደዚህ ዓይነት ሁኔታ እንደዛ ከሚያከብራቸዉ ህዝብ ጋር መለያየት እኔን አሳዝኖኛል ግማሾቹም ሲለቃቀሱ ነበር ::

ኤግዚአብሔር ህገራችንንና ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን ::

ይቀጥላል .................................................
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሰዋሰው

አዲስ


Joined: 25 Nov 2003
Posts: 20

PostPosted: Sat Feb 19, 2011 11:07 pm    Post subject: Reply with quote

ጤናይስጥልኝ የተከበራችሁት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ወዳጆች ወደ የጋዜጠኝነት ሥራዬ ከመግባቴ በፊት ማስታወቅ የምፈልገዉ አንዳንድ ነገሮች አሉኝ :: ይሄም ምንድነው ለምን በድህረ ገጾች ላይ ጽፎ አያወጣም ደግሞ ለምን ያሰለቸናል እኛ ስለ ሙኒክ ቤተክርስቲያን ለምን ማወቅ ያስፈልገናል ወይንም ምናልባት የሆነ የሚፈልገዉ ነገር አለ እኚህን ቄስ በጣም በግሉ ቂም ስላለው ወይንም ስለሚጠላቸዉ ነው ተብለዉ ሊጠየቁ ለሚችሉ ጥያቄዎች ከወዲሁ መልስ ዓይነት ነገር ለመናገር ነው ::
1 : ዋርካ ላይ የምጽፍበት ምክንያት ማንኛዉንም ኦርቶዶክስ የሆነ ኢትዮጵያዊን ስለሚመለከት ነው :: ዋርካ ላይ ሁሉም (ወያኔዉም ጤነኛዉም ኦንግጉም ዱርዬዉም ጨዋዉም በፖለቲካም ይሁን በምንም ነገር የሚልለያየዉ በሙሉ እዚህ ስለሚገባ ነው ) :: ከራሴ በመጀመር እኔ ለምሣሌ አንዳንድ የማላያቸዉ ማየት የማልፈልጋቸዉ ዌብሳይቶች አሉ ስለዚህ ሌላዉም ሰዉ በተለያየ ምክንያት የሌላዉን ዌብሳይት ላይመለከት ይችላል ብዬ ስላሰብኩኝ እና ይሄን ጉዳይ ደግሞ ማንኛዉም ኦርቶዶክሳዊ ሊያውቅ እንደሚገባዉ ነው ::
2: ሌላው ይሄንን ጉዳይ ኢንተርኔት ላይ አንብቦ ሁሉም ሰው ስለየ አጥቢያ ቤትክርስቲያኑ እንዲያስብ ያደርገዋል በተለይ ዉጭ ሀገር ለምንኖረዉ ትልቅ ትምህርት ይሆናል ብዬ ስለማስብ ነው እንጂ ከዚህ በተረፈ ከቄሱ ጋር የተለየም አቅርቦት አልነበረኝም ወይንም እሳቸዉን በግል እንድጠላቸዉ ያደረገኝ ምንም ምክንያት ነገር የለኝም : አሁንም እንኩዋን ይሄን ስጽፍ በጥላቻ ሳይሆን የሰሩት በደል ቅድመ አያቶቻችን ከሁሉ ነገር ተከላክለው አንድ ያስቀሩልንን ቤተክርስቲያናችንን ማርከሳቸዉ በጣም ትልቅ አረመኔነት መሆኑን ሁሉም ሰው እንዲረዳዉና ጉዳዩን በየአካባቢዉ ከእንደዚህ አይነት አደጋ እንዲጠነቀቅ ነው ::
3 ሃይማኖት ፖለቲካ አይደለም ሃይማኖት የሁሉም ነው ስለዚህ ነው ዋርካ ፖለቲካ ላይ የማልጽፈዉ ::

እንግዲህ ወደ ቁምነገራችን ስንገባ እንደነገርኩዋችሁ ቤተክርስቲያናችን ክብሩዋ በልጆቹዋ ተመልሱዋል :: በነገራችን ላይ እኔ ቄስ መስፍን ገንዘቡን ይመልሳሉ የሚል ቅንጣት ያክል እምነት የለኝም ምክንያቱም እዚህ ሀገር ባንክ ዉስጥ እንኩዋን በስማቸዉ ወይንም በሆነ ምክንያት ደብቀው ባንክ እንዳያስቀምጡት ከየት የመጣ ገንዘብ ነው ተብለዉ እዛዉ ባንክ ይጠየቃሉ :: ስለዚህ እኔ ስለ ገንዘቡ ምንም መናገር አልፈልግም ነገር ግን እዚህ ማስረዳት የምፈልገዉ አንድ ካህን በክርስትናዉ በመከበሩ ምን ያህል እብሪተኛ እና ከሀዲ እንደሚሆን በተጨባጭ በቤተክርስቲያን ቤተመቅደስ ቆመው ሲዋሽሹን የኖሩትን ቄስ ቆሜ ስመለከት ስለኖርኩ ነው :: አሣዛኝ ነው :: የቤተክርስቲያናችን ቓሚ ምእመን የሆነቺው ዘነበወርቅ (እኔ እስከ ዛሬ ዘመዳቸዉ ትመስለኝ ነበር ) በእዉነት ትልቅ አነጋገር ነው የተናገረችዉ :: "በዉነት እንደ ቄስ መስፍን እስከ መጨረሻዋ ቀን ድረስ እድለኛ ሰው የለም የቤተክርስቲያን ገንዘብ ዘርፎ እየተለመነ የተከበረ ሰዉ የለም እስከ መጨረሻዋ እለት እግዚአብሔር ያሣያችሁ !"

ጉዳዩ እንግዲህ እንዲህ ነው :

ኢንግላንድ የመጡት የአዉሮፓዉ ሊቀ ጳጳስ ,የጀርመን ተጠሪ / መርአዊ እና የሌሎች ቤተክርስቲያናት ቀሳዉስት በተገኙበት ከህዝብ የተወከለው ኮሚቴ ለጳጳሱ እና ግልባጭ ለዶ / መርአዊ የተጻፈው ደብዳቤ ለህዝቡ ከተነበበ በሁዋላ (በዚህ ምክንያት / መርአዊ የስራ መልቀቂያ ስለጻፉላቸዉ ) ቄስ መስፍን እሳቸዉንና ህዝቡን ደስ ባላቸዉ አይነት አጻጻፍ ......አንዳንድ የፖለቲካ አመለካከታቸዉ ይህንን መንግስት የማይቀበል ከሆኑ ሰዎች ጋር በመሆን / መርአዊ ከስራዬ ሊያባርሩኝ አስበዋል እኔ ግን ላለፉት 20 ዓመታት ፓለቲካ ነጻ እና ህዝቡን አንድ በማድረግ ከፍተኛ አገልግሎት ሳበረክት ኖሬያለሁ ብለዉ የተለመደ ጉዳዩን ወደ ፖለቲካ ሊለዉጡ በዚህ ሁሉ ዘመን ይጠቀሙት የነበረዉን ታክቲክ ዛሬ በጽሑፍ ጳጳስ ፊት ወንጅለዉን ሲያነብቡልን ምን ዓይነት ደረቅ አረመኔ ዱርዬ ስዉ መሆናቸዉን በመጨረሻዋ ቀን እንኩዋን እንድንታዘባቸዉ አድርገው አሁንም በአክብሮት እኛ አላማቺን እንዲህ አይነት ሌባ ቄስ ቤተክርስቲያናችን ዉስጥ እንዳይደርስ መሆኑን አሁንም እምነታችን ላይ ቆመን ሌላ ሌላዉን ችላ ብለን ትተን ለመዉሰዳቸዉ ላመኑት ገንዘብ ፊርማ እንዲፈርሙልን ልመናችንን ተያያዝነዉ ይባስ ብለዉ እከስሳችሁዋለሁ መርማሪዎቹን አልቀበላቸዉም ስለ ሂሣብ አይዉቁም ዓይነት የተለመደ ንቀታቸዉን ሲዘላብዱ ወደ ህግ ቦታ ቢሄዱ እርሳቸዉ እንደሚጎዱ እና ሂሣቡ እንደገና ይመርመርልኝ የሚሉ ከሆነ ይሄ 165 ሽህ ኦይሮ ሶስት መቶ ሽህ ይደርሳል እዚህ ሀገር በጉቦ ወይንም ጊዜ ለሰጣቸዉ ባለስልጣኖች ሂደዉ ቢያጎበድዱም ከህግ በላይ ምንም ነገር ስለሌለ የሚቀይሩት ነገር የለም ነጻ የሚወጡት ገንዘቡን ብቻ ወደ ቤተክርስቲያናችን ሲመልሱ ነው ተብለዉ ምክንያቱም ሂሣቡን ስንመረምር የወጪ ደረሰኞች ለዛዉም ለምን እንደወጣ ያልተጠቀሰባቸዉ ደረሰኞች እንጂ የገቢ ደራሰኝ ባጠቃላይ አለማየታቸዉን ወይንም የተወሰኑ የገቢ ደረሰኞችን ማየታቸዉን ተናግረው ይሄ አይነት አሰራር በየትም ሀገር ላይ እንደሌለና ወንጀል መሆኑን አስረድተዋቸዉ እባክዎትን እንደ ዱርዬ ዝም ብለው አይዘላብዱ ስነ ስርዓት ይዘዉ መናገር የሚፈልጉትን ነገር ይናገሩ ጳጳስ ፊት አይዋሹ እየተባሉ ወደፊት ህይወታቸዉ እስር ቤት እንዳይሆን ስለእርሳቸዉ ብቻ በማሰብ ህዝቡ በትህትና ሲለምናቸዉ ነው የዋለዉ ::
ህዝቡ ከሁሉም ነገር በፊት ጳጳሱን ዉሣኔ ስለፈለገ ያዉ ጳጳሱም የህዝቡን ትህትና እና ጥንካሬ ስላዩት ሌላ አማራጭ እንደማይኖር በመረዳት ቄስ መስፍን የቤተክርስቲያናችንን እቃ አስረክበዉ ከቤተ ክርስቲያናችን ራቅ ብለዉ የሚቀጥለዉን ዉርደት ደግሞ እንዲጠብቁ ተነግሩዋቸዉ ለዛን ቀን በዚህ ተለያየን ::

እግዚአብሔር ሃይማኖታችንን ይባርክልን ሀገራችንን ይጠብቅልን ::

ይቀጥላል ...................................................
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሰዋሰው

አዲስ


Joined: 25 Nov 2003
Posts: 20

PostPosted: Mon Feb 21, 2011 2:05 pm    Post subject: Reply with quote

ጤናይስጥልኝ ዉድ ያገር ልጆች ክርስቶስ ቤተሰቦች የድንግል ማርያም ወዳጆች ......ትንሽ ጊዜ ስትኖር ዛሬም ተመለስኩኝ ::
መቼም ከኔ በላይ ስለ ቤተክርስቲያናችን ብዙ የሚያዉቁ ሰዎች አሉ እነርሱ ለምን ዝም እንደሚሉ አላዉቅም እንዲህ አይነት ነገር ግን በደንብ ተጩሆ መነገር ያለበት እነርሱ በዉስጠ ምስጢር አዋቂዎች እና እንደው እዛዉ ቤተክርስቲያኑዋን እንደ ሁለተኛ ቤታቸዉ አድርገዉ ቀን ተሌሊት ምንጣፍ ሲያነጥፉ ሲጠርጉ ሲያጥቡ ሲያስተናግዱ ጎንበስ ቀና ሲሉ የኖሩት ተመስግነው የማይጠገቡት እህትና ወንድሞች /ገብርኤል አገልጋዮች ነበር ነገር ግን እንደማየው እነርሱ ወደዚህ መምጣቱ ደስ የሚላቸዉ አይመስልም ስለዚህ እኔ ይበቃል ብዬ የማስበዉን ያክል ኢንፎርሜሽን በሌላ ክፍለ ዓለም የሚኖሩ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ አማኞች ስለዚህ ቤተክርስቲያን በቂ እዉቀት እንዲያገኙና በየ አካባቢያቸዉ ያሉትን ቤተክርስቲያናት አስተዳደር ሳይፈሩ የሚፈለገዉን ቁጥጥር ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት ጋር እንዲከታተሉ ስለምፈልግ ነው ::
የሰው ልጅ መከበሪያዉ ስራዉ እንጂ በማስመሰል ጸባዩ እንዳይሆን :: ከእንግዲህ ወዲህ ጀርመን ሀገር ዉስጥ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ስም ቢያንስ አሁን ያለነው እድሜያችን ደርሶ እስክንሞት ወይንም እግዚአብሔር ሀገራችንን ከመሰሪዎች ነጻ አድርጎልን ወደ ሀገራችን እስከምንመለስ ድረስ ቅስናዉን ተመክክቶ ገንዘብ ሊበላ ወይንም ሊሰርቅ የሚያስብ ቄስ ቤተመቅደስ ዉስጥ ቆሞ እንደተመኘ ኃጢአቱን በራሱ ላይ ይከምራል እንጂ አንድ ሣንቲም የቤተክርስቲያንን ንብረት አይነካትም :: ከእዚህ በላይ ትምህርት የለም ......እኛ ትልቅ ትምህርት ተምረናል :: አይናችን እያየ አንድ ቄስ በስብከት ፋንታ ስለ ኢንቨስትመንት ልማት በስብከት ፋንታ ስድብ , ሀሜት , እብሪተኛነትን ሲሰብኩ ከቀን ወደ ቀን የሚናገሩት ሃይማኖታዊ አነጋገር ሲያልቅባቸዉ እና ከወንጌሉ ቃል ይልቅ የፖለቲካ ቃላቶችን እንደነ ኢንቨስትሜንት , ዴቨሎፕሜንት , ኦፖዚሽን , ትራንስፎርሜሽን የመሳሰሉትን ልብሰተክህኖ ለብሰዉ ሲዘላብዱ ቢያንስ አስር ዓመት አይተናቸዋል ሰምተናቸዋል :: በመጨረሻ ሰሞን እኮ እሳቸዉ ከሚሉት ነገር ሌላ ሀሣብ ያለዉ ሰዉ ልክ እንደ ወያኔዎቹ (ዘረኛ ሊያሳድምባቸዉ የፈለገ ሀገር ቤት ስልጣን ፈላጊ ገንዘብ ፈላጊ የስድብ ዓይነት አይቀርም ) ከአቶ መለሰ ዜናዊ ብሰው ነው ቁጭ ያሉት ::
እኔን ሁልጊዜ ከሚረብሸኝ ነገር አንዱን ባለፈዉ ጉባኤ ላይ አንዱ ወንድሜ ሲናገር ሰማሁት ይሄ ሰዉ በጣም ተገርሞ ነው " ቤተ ክርስቲያን ዉስጥ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ማየት ለምን አስፈለገ ?" ቴሌቭዥን ባጠቃላይ ቤተክርስቲያን ዉስጥ ምን ይሰራል ? በእዉነት ምን ይሠራል ? ስለ ክርስትናችን እናስብ ከተባለ ? ከፈለጉ እቤታቸዉ ለምን አያስገቡም ? ሌላዉ ደግሞ እስከዛሬ ድረስ ከአእምሮዬ ልሠርዘዉ ያልቻልኩት ለቤተክርስቲያን ግንባታ እያሉ (ሴንድሊንገር ቶር የነበርን ጊዜ (ሌላ አድራሻ ነው ) አዳራሹ እንደ መጸልለያም እንጠቀምበት ስለነበር ) ቢራ አዳራሹ ዉስጥ ሲሸጡ ጫት ቃሚዎች ጫታቸዉን በኪሳቸዉ ወይንም ባፋቸዉ ሳይጉመጠመጡት ቤተክርስቲያናችንን እስከሚያቆሽሹት ድረስ ሲጨፍሩባት የነበረዉ ነው .......... አንባቢዎች እንድታዉቁት እንዲህ ዓይነት ከቤተክርስቲያን ህግና ስነሥርዓት ጋር የማይጣጣሙ ነገሮች በተደጋጋሚ ለቄሱ በቀጥታም ወይንም በተዘዋዋሪ ይነገራቸዉ ነበር (ዛሬ ብቻ አይደለም እንዲህ የሚባሉት ) ነገር ግን ከሳቸዉ በላይ ለዚች ቤተክርስቲያን የሚያስብ ሰው ስለሌለ ንቀው ወይንም ተሳድበው ይተዉታል :: በእኔ አመለካከት አንድን ቄስ መጥፎ አታድርግ የሚለው የሚያነብበዉ መጽሐፍ ቅዱስ የሚደግመዉ ዉዳሴማርያም ነው ስለዚህ ነው እስከዛሬም ከዛሬ ነገ የተሻለ የራሳችን የሆነ ቤተክርስቲያን ሲኖረን የተሙዋሉ ካህናት ሲኖረን ብለን እያየን እንዳላየ እያወቅን እንዳላወቀ ሆነን አንዳንድ አስተሳሰባቸዉ ከራሳቸው እና ከጉዋደኛቸዉ ሌላ ለማንም እንደማይጠቅም የማያዉቁት ነገሮችን ለመወሰን የሚቸኩሉና ለመረበሽ ቀዳዳ ብቻ ፈላጊዎች ቄሱ ቆሞ እንደመጋፈጥ ዘልለዉ የሰዉ ቤት ተከራይተዉ ቤተክርስቲያን ብለዉ ለመክፈት አቡነ ጳዉሎስን አንቀበልም ! መፈክር ይዘዉ ድራሻቸዉ እንደጠፋዉ ሳንሆን የለም አቡነ ጳዉሎስ መቀበል አለመቀበል ጉዳይ ሌላ የኛ ጉዳይ ግን ቤተክርስቲያናችንን መጠበቅ ብለን አጅሬዉ ጋር እስከ አሁን ድረስ ገብርኤል እራሳቸዉን እንዲያጋልጡ እስካደረጋቸዉ ቀን ድረስ ፍጥጥ ብለን የቆምነዉ :: በመጀመሪያ እራስንና አጠገብ ያለዉን ነገር ፈር ካስያዝን በሁዋላ ነው ወደ ሁለተኛ ጥያቄያችን የሚክኬደው ይሄ የማንኛዉም ሰው ትክክለኛ ይህይወት መመሪያም ይመስለኛል ልጅ ለማሳደግ እራስን በመጀመሪያ ማሳደግ ::
እዚህ ሀገር የሚኖር ሰዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚስሰራዉን ነገር በተለይ በቤተክርስቲያን አካባቢ የማያዉቅ ያለ አይመስለኝም :: ስለ አቡነ ጳዉሎስም ጉዳይ ምናልባት ከአዲሶቹ አማኞችና የቤተክርስቲያን መሥራች ሰዎች እኛ እንሻላለን ብዬ አስባለሁ :: ፖሊቲካል አጀንዳም ከሆነ ቤተክርስቲያን እኮ ሣትበታተን ዋናዉን አስተዋጾ ታደርጋለች :: የእነ ፖላንድ የእነ ምሥራቅ ጀርመንን ያልደረቀ ታሪክ ዞር ብለን መመልከት እንችላለን ከቤተክርስቲያናችን አንወጣም የትም አንሄድም ብለው ነው ቤተክርስቲያናቸዉ ዉስጥ ሁሉን ነገር ያዘጋጁት ::
ነገርን ነገር ያነሣዋል ይባል የለ ? ከተነሣ ላይቀር ግን ሙኒክ ስለተመሰረተዉ አዲሱ ማርያም ቤተክርስቲያን ( በነገራችን ላይ ይሄ እኔ የማዉቀው እና አንድ ሁለት ቀን ሄጄ ያየሁት ነው ነገር ግን ወደ ሁለት ??? ሌላ ቤተክርስቲያን ተመስርቱዋል ይባላል :: ግን እርግጠኛ አይደለሁም ) ያም ሆነ ይህ ግን እስቲ አስቡት ሙኒክ እና አካባቢዉ ያለዉ ኢትዮጵያዊ በግምት ቢበዛ ወደ ሦስት ሺህ ይሆናል ከዛ ዉስጥ ጴንጤዉና እስላሙ ተቀንሶ ወደ ከሁለት ሺህ በላይ የቤተክርስቲያን አባል አለኝ ሲሉ ሰምቻለሁ ደግሞም ወደ 2500 ሊደርስ ይችላል ብዬ አስባለሁ :: ይሄ ምዕመን ቤተክርስቲያን ለማስሠራት ተብሎ ግማሹ ወር ደመወዙን ግማሹም ከሁለት እስከ ሶስት ወር ደመውዙን ለቤተክርስቲያናችን የመጸወተ ብዙ ነው ታዲያ አንድ ቄስ ሲቀጥፍ አይቶ ይሄንን ሁሉ የተሰበሰበ ገንዘብ ጥሎና መሠረት የያዘን ቤተክርስቲያን ትቶ አዲስ ማቁዋቁዋም ለሌላዉ እንደዚሁም ቤተክርስቲያን ዉስጥ እንዲህ ዓይነት ሰዎችን ሰግስጎ የኦርቶዶክስን ስም ማጉደፍ ለሚፈልገዉ ሰዉ ዉሰደዉ እኔ አልፈልገዉም ማለት አይሆንም ? ምን ዓይነት ስሜትስ ከዛ በሁዋላ (ካስወሰድን በሁዋላ ) ሊሰማን ነው ??? በእዉነት ያሣዝናል :: እዚህ ሀገር ሁለት ዓይነት የግሪክ ቤተክርስቲያን ነው ያለው (ግሪኮች ኦርቶዶክሶች ናቸዉ ሙኒክ ዉስጥ ብቻ እኔ ብቻ የማዉቀው አራት የግሪኮች ቤተክርስቲያን አለ ) ግማሾቹ በዓላቸዉን ልክ እንደ ካቶሊኮቹ ነው የሚያከብሩት ግማሾቹ ደግሞ ለብቻቸዉ ሀገራቸዉ እንደሚያከብሩትነው የሚያከብሩት :: ስለዚህ እዚህም ይኛ ጉዳይ በዚህ ከቀጠለ ከዚህ አያልፍም ::

ቤተክርስቲያን ሲመሰረት ደግሞ ዝም ብሎ ከመሬት ተነስቶ አይደለም በመጀመርያ እራስን መመርመር ያስፈልጋል ምን ያህል ክርስትናዬን እወዳልለሁ አከብራለሁ ? ለሰዉ አርአያ መሆን እችላለሁ ? ሰዉ እኔ የማደርገውን ነገር ይወደዋል ወይ ? ለምንድነዉ ይሄንንስ ነገር የማደርገው ? ለምን ያስፈልገኛል ? እንዲህ ዓይነት ቀላል የሆኑ ጥያቄዎች ግን ትልቅ ቁም ነገር የያዙ ነገሮችን ማገናዘብ ያስፈልጋል ::
ከዛ ውጭ ግን ዝም ብሎ ቡና ቤት ተሰብስቦ በድምጽ ብልጫ ወስኖ ቤተክርስቲያን ማለት ህዝብን ማደናበርና ትልቅ የመብበታተኛ መንገድ መክፈት , መስሰደቢያ ወይንም ለሌላ ነገሮች እንቅፋት መሆን ብቻ ነው እንጂ በግል ሃይማኖት ላይ እዚህ ተሄደ እዛ ተሄደ የሚለዉጠዉ ምንም ነገር የለም የበለጠ ሰዉን በቀላሉ ያስገምታል የማንኛዉም ሰዉ ሃይማኖቱ ልቡ ዉስጥ ያለዉ ነገር ብቻ ነው :: ለዚህ ነው እዚህ ምንም ቄሱ የተጠሉ ቢሆኑም ሰዉ ወደዛ የማይሄደዉ : በመጀመሪያ አስፈላጊነቱን ማንም ስላልመከረበት :: በንጽህና ቢሆንማ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በየ 50 ሜትሩ ቢኖር ደስ ይለኛል ::

ዛሬ መጻፍ ያለብኝን ጉዳይ አይደለም የጻፍኩት ይሁን እንጂ ይሄም አልለ ለማለት ነው :: በሚቀጥለው ጊዜ ወደ አርእስቴ እመለሣለሁ እስከዛው ድረስ :::.::::::

እግዚአብሄር ጤና ይስጠን ሀገራችንንና ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን ::

[/u]
ይቀጥላል .......................
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የገብርኤል

መንገደኛ


Joined: 24 Feb 2011
Posts: 2

PostPosted: Fri Feb 25, 2011 8:27 am    Post subject: Reply with quote

[size=18][/size]
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የገብርኤል

መንገደኛ


Joined: 24 Feb 2011
Posts: 2

PostPosted: Fri Feb 25, 2011 10:52 am    Post subject: Reply with quote

ሠላም ለሁላችሁም Exclamation የሠላም አባት እግዚአብሔር ሠላሙን ያድለን
እግዚኦ ለምሕረትሕ አሁንስ ምነው ቤተክርስቲያን ለመጠቃቀሚያና እንደ ባንዲራ ከፍ ብሎ ለመታወቅ እሽቅድምድሙ በዛ ብቻ እንደቸርነቱ ይቅር ይበለን

ምነው እርስዎ አቶ ሰዋሰው ጊዜዎትን ሰውተው ሌላውም ትምህርት እንዲሆነው ስለኝህ ሌባ የውሸት ቄስ እስከ አሁን ጊዜ ጉዳቸውን ሲያጋልጡልን ከርመው አሁን እየደበላልቁ አብረው ከቄሱ ሲቦርቁ ወሬ ሲያቀብሉ እናም ሐይማኖቴ ብለው ወደ ቤተክርስቲያን የሚመጡትን ሰዎች በቤተክርስቲያን ደጅ ሲገላምጡ ጠበል ጠዲቅ ሊቀምሱ የገቡትን ሰው ከሰው እየለዩ እንደ ባይተዋር እየተጠቃቀሱ ሲያሽካኩባቸው የነበሩትን ሰዎች አሁን እርስዎ እየካቡ ሲጽፉ በማየታችን በጣም ገርመውናል እዚህ ላይ ሲጽፉ እዚሁ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለን ብዙ ሰዎች እንደምናነበውና እርስዎም ከትዝብት ውስጥ እየገቡ ስለሆነ ማስተዋልን ይስጦት
አንዳንዶች አምላክነቱን የማያውቁ የእግዚአብሄር ሰዎች በቤተክርስቲያን ሽር ጉድ እያሉ የሚያገለግሉ በተንኮል የተሞሉትን ሐሚተኞችን አሉባልተኞችን የሰው ስም አጥፊዎችን እርስዎ እዚህ ላይ ያወድሱዋቸው ጀምረዋል ሁላችንም እኮ እንተዋወቃለን ማን ማን ከቄሱ ስር ሆኖ ሲጠቃቀሙ የኖሩና ጥቅሙ ሲቀርባቸው እናም ሲነካኩ ቄሱን ለማጋለጥ የተነሱትን ዛሬ ለቤተክርስቲያን ተቆርቆዋሪ ሆነው እንደ ፍየል ስለተጮኸ በተለየ / ዘነበወርቅን ስሙዋን በመጻፍ ትልቅ አነጋገር ነው የተናገረችው ብለው በመጻፎት እጅግ ያሳዝናል

እኔ ይህን በመናገሬም የግል ጥላቻም ኖሮኝም አይደል ገንዘባችንን የበላውን ቄስ ያጋለጠውም እራሱ ቅዱስ ገብርኤል ታግሶ ታግሶ እርስ በእርሳቸው እንዲነሱ ስላደረገ ብቻ ነው አሁንም ንሰህ ገብተው ተንኮለኝነታቸውን ካልተው እራሱ መላኩ ቤቱን ያጸዳል ::
ዘነበወርቅ (ዘኒ ) ማለት እኝሁ ሌባ ቄስ ባለውለታዋ ነበሩ በፊት እንደመጣች እዚሁ አገር ስትኖር የጀርመን መንግስት የመኖሪያ ፈቃድ ከልክሎዋት የምትገባበት ስታጣ ቄሱ በጅ በግር ብለው ባል በሰው አፈላልገውላት ባልዋን ብርሐኑን በቤተክርስቲያን ውስጥ በቅዳሴ ላይ እንዲመጣና እንዲያያት ተደርጎ እስዋም ክንብንብሽን ወደታች አድርጊና ተኩዋኩለሽ ዘንጠሽ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንድትገኚ እንደተባለችው በቅዳሴ ሰአት ነጠላዋን ከደረትዋ በታች እያወርደች ስትገለፍጥ ከበሮዋን ይዛ ሽር ሽር ስትል ይኽው ሌባ ቄስም ቅዳሴው ቅዳሴ ሳይመስላቸው ወዲያ ወዲህ እየገለፈጠ ሁለቱንም በአይኑ ሲቃኛቸው እኛም ቀድመን ሰምተን የነበርነው ሁሉ ቅዳሴውን መከታተል ትተን አብረን በሐጢያት ተጨመላልቀን ፊልማችንን ስናይ ባልየውም ፈቃደኛ መሆኑን በአይኑ ከቄሱ ሲነጋገር ሲገለፋፍጡ ቅዳሴውም አልቆ ጉድ እያልን አብረን ተኮንነን ወደየቤታችን ሄድን እግዚአብሄርን የማይፈሩ ሰውንም የማያፍሩ ምን ያህልስ ቢዳፈሩ ነው ካላጡት ቦታ ያውም ስርአተ ቅዳሴ ላይ እንግዲህ እንደዚች አይነቱዋን ነው ትልቅ አነጋገር ተናገራለች ብለው ስሙዋን የጻፉላት ያሳዝናል ሰዎችን ከላይ ከላይ እያየን ነው ገደል የምንገባው ገንዘባችንንም የተበላው ገንዘቡስ 165 euro ብቻ ነው ? ፓፓሱስ ቢሆኑ ቄሱን ካልከሰሳችሁ ይፈርሙላችሁ ማለታቸውስ የሚገርም ነው Cool የበላው ቄስ ካለምንንም ፍርድ ይዞ ይሄዳል ሌላ ደግሞ በተራው ይመጣል እነዚህ ሴቶች እንደገና ይከቡትና ሽር ሽር እያሉ አባታችን አባታችን እያሉ ከለላ ሆነው ለሁለትኛም ያስበሉናል ጥቅም የለመደ አይለቀውም መቼም የራሳቸው ጉድ ሲወራባቸውማነው ያወራው ግልምጫቸው ስም ማጥፋታቸው አይድርስ ነው የሰው ጉድ ሲያቦኩ ግን አይድርስ ነው ከአህያ የዋለች ጊደር ፈስ ተምራ ትምጣልች እንደሚባለው ከነዚህ ሰዎች የሚውሉ ሰዎች ወዲያው እንደንሱ ሆነው ሲለወጡ ይታያል እግዚኦ በድሜያቸው ጠና ያሉ ግን ስራቸው የሴይጣን መቼም እንተዋወቃለን አንዳንዶቹ ስማቸውን ቀይረው እድሜያቸውን ጎምደው አስመዝግበው እድሜ ጀርመን አገር በረዶውም ነው መሰልኝ መጨማደድም የለ አያስታውቁም ግን ጊዜያቸው በአሉባልታ እንዳለቀ እንኩዋን አይስትውሉም ::

ማርያም መሕእበር ይባላል ለስሙ ጽዋ እንጠታለን የሆድ ተስካራችንን ከሞላን በሁዋላ ዞር ብለው አንዱዋን አንዱዋ መቦጨቅ በሰው መጣላት የሚደሰቱ አቤት እግዚኦ አረ ትጽፎ አያልቅም የያንዳንዱዋን ጉድ ቄሱ እና ከሚስትየው የሰሩትን ለጥቅም ሲሉ በቤተክርስቲያን ውስጥ እሱ አምላክ ምህረቱ የበዛ ነውና ይቅር ይበላቸው እኛም ገብርኤልን እያልን አይቶ እንዳልየ በመሆን አለን

እግዚአብሄር በአፍ አይደለም የሚሸነፈው እግዚአብሔር በመንፈሳዊ ሕይወት እና በጸሎት ነው የምናሸንፈው እሱ ተንኮልና ሐሜታውን ትተን በንጹህ ልቦና ቤተክርስቲያን ለመምጣት እንሞክር ያለበለዚያ ትርፌ ዘጥ ዘጥ ነውና የአምላክ ቸርነት አይለየን ሀይማኖታችንን ይጠብቅልን አሜን
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጎንጉል

መንገደኛ


Joined: 26 Jul 2010
Posts: 2

PostPosted: Sun Feb 27, 2011 7:31 pm    Post subject: Reply with quote

ጤና ይስጥልኝ ክርስቲያን ወገኖች
እንዲሁም ወንድሜ ሰዋሰው ምነው ጥፈው ጥፈው በስተሁዋላ ፍየል ወዲህ ቅዝምቅም ወዲያ ሆነብን ካለ እርእሱ ገብተው በስደት /ማርያም ቤተክርስቲያን የመሰረቱትን መዝለፍ ምን አመጣው Question ማንም የሚያውቀው እነሱን የሚመራው በስደት ያለው የኢትዮፕያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሲሆን እኛን ደግሞ ኢትዮፕያ ያለው ወያኔ ያስቀመጠው አቡነ ፓውሎስ (/መድህን ) አራት ነጥብ :: ልዩነቱ ይሄ ነው :: እኛ ስርአት የሌለውን ምንቸገረን እግዚያብሄር ያመጣውን እሱ ይመልሰው እያልን እራሳችንን ስናታልል ለሌባው ቄስ ከለላ የሆን እኛ ነን ማንነታችን ያልታወቀ አሁን እንዲህ ነው እንዲህ ነበር መስሎን ነው ምናምን እያልን ምክንያት እናበዛለን ቤተክርስቲያናችንን እንዴት ጠብቀናታል Laughing ወንድሜ ሰዋሰው

የቅ /ማርያም ቤተክርስቲያን መስራቾች ሊኮሩና ሊመሰገኑ የሚገባቸው ናቸው :: ቄስ ነኝ ባዩን መስፍንንም በወቅቱ አስደንግጠውታል የመንደር ሴቶችም ወሬኞች ቤተክርስቲያን እንዴት ይቆቆማል ሄደን እንስደባቸው እናፈራርሳቸው በማለት /መቅደስ እና የላስታወርቅ (ሚሚ )ላገኙት ሁሉ በለመደው አፋቸው ስም ሲያጠፉ በአፋቸው እንዳሩ አሉ ወሬ ከቡና እናቶቻቸው አስለምደው አሳድገዋቸው መቼ አፋቸው ካላማ ይበላቸዋል Rolling Eyes እዛ ቤተክርስቲያን እንዳትሄዱ አቤት አቤት ስም ማጥፋት ሌላውም እየተነሳ ማቡካት ማቡካት እንደው አሁን የክርስቲያን ስራ ነወይ የሚሰራ Questionምናለ ብንተዋቸው ይህም ተንኮላችንም ነው ልባችንን ንጹህ ባለመሆኑ ገንዘባችንን የተበላነው ዛሬ /ማርያም /ክርስቲያን በትንሽ ጊዜ ውስጥ ህግ አውቆዋቸው ከእኛው 20 አመት ከሞላን እኩል ሆነዋል በዚህ ድንቅ ስራቸው ልናከብራቸው ይገባን ነበር የራስዋ እያረረባት የሰው ታማስላለች አይነት ሆነን መቅረታችን እጅግ ያሳዝና Embarassed ወደ ማርያም ቤተክርስቲያን ሰው የማይሄደው ለዚህ ነው ብለው የሰጡት ምክንያትም ውሸት በመሆኑ ትንሽ አሳቀን ምነው ወንድሜ ሰዋሰው እነዚህ ሴቶች ብምላሳቸው ደባበሶት እንዴ ?ወይስ እርስዎ ማን ነዎት ?አሁን እዚህ ያለው ሰው ቤተክርስቲያን የሚመጣው አብዛኛው እግዚአብሄርን ሳይሆን ሰው ሰውን እያየም አይደል ቤተክርስቲያን የሚመጣው ሰው ሰውን ለማግኘት እንጂ እውነት እግዚአብሄርን ፍለጋ ነውን ?ሁላችንም እኮ እንተዋወቃለን

ወንድሜ ሰዋሰው ሁለትም ሶስትም ሆናችሁ በስሜ ብትጸልዩ እኔ በመካከላችሁ እገኛለሁ ብሎዋል እና አምላካችን ሰው በመብዛት ብቻ አይደለም እግዚአብሄር የሚገኘው እነሱን እንተዋቸውና እስኪ የራሳችንን ጉድፍ እናጥራ Mattews 7:1-5 እስኪ ያንቡት

የማይገናኝ የግሪክ ታሪክ መጻፍም አያስፈልጎትም ለማንኛውም ይቅር ይበለን እኛ ነን ሌባውን ፓፓስ አቡነ ፓውሎስን በቅዳሴ ላይ ይጠብቅልን ሲባል አሜን እያልን እግዚአብሄርን የምናታልል የጥቅም ሰዎች ሆነን የቀረነው እውነትኞቹማ አይተው አይተው ተሰድበው ተዋርደው ታግሰው ታገሰው ሰው ከምንከተል እና ገደል ከምንገባ ብለው የግዚያብሄርን መንገድ ለመከተል ትተው ሄደዋል እኛ ግን በሐሚታ አላስቀምጥ አልናቸው Rolling Eyes ወንድሙን የሚያማ እንደ ነፍሰ ገዳይ ነውና የሚቆጠርው ንሰህ መግባቱ ጥሩ ይመስልኛል

እግዚአብሄር አምላክ ደብሮችን (ቤተክርስቲያኖችን ) ያብዛልን በነጻነት የፈለግንበት ሄደን አምላካችንን እንድናመሰግ አሜን ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሰዋሰው

አዲስ


Joined: 25 Nov 2003
Posts: 20

PostPosted: Mon Feb 28, 2011 4:30 am    Post subject: Reply with quote

ጤናይስጥልኝ ክርስቶስ ቤተሰቦች ድንግል ማርያም ወዳጆች እንደምን ሰንብታችሁዋል ?
ወደ ጀመርኩት ዘገባዬ ከመግባቴ በፊት ግን ከላይ ለተጻፉት critiques እዚህ የምጽፈው ነገር ሀሜት ወይንም ዝንባሌ እንዳይመስል መልስ መጻፍ እፈልጋለሁ :: በነገራችን ላይ እንዲህ የምንወያይበት ፎረም አካባቢያችን ቢኖር በጣም ትልቅ ጥቅም ያለው ነበር ምክንያቱም ስለ ዉስጣችን (ዓለም )ማንም ሳያዉቅብን እዚሁ የዉስጣችንን ጉዳይ እንጨርስ ነበር ነገር ግን ሙኒክ እንኩዋን እንዲህ ዓይነት ነገር ሊኖር ኢትዮጵያን ኮምዩኒቲ እንኩዋን የለም :: ቢያንስ ወደ 1500 ኢትዮጵያዊ ሙኒክ ከተማዋ ዉስጥ ብቻ ይኖራል ::
የገብርኤል እና ጎንጉል ስለ ክሪቲክሳችሁ በመጀመርያ ተገቢ መስሎ ከታያችሁ እና በተለይ የገብርኤል አስተያይቶት ለእዚህ ውይይት አስፈላጊ ከሆነ ቀጥሉበት እኔ ምንም ችግር የለብኝም :: የገብርኤል በሚቀጥለዉ ጊዜ ሲጽፉ አደራዎትን ስም ዝርዝር እንዳይረሱ እርስዎ የማይፈልጉዋቸው ሰዎች ስም ጥሩ ቢያደርጉም አደረጉ ተብለዉ እንዳይጻፉ ::
ጎንጉል : ለእኔ በአንድ አንድ ቀበሌ ህዝብ በማይሞላ ኢትዮጵያዉያን ባልሉበት ቦታ ከአንድ ቤተክርስቲያን ሌላ ቤተክርስቲያን ብሎ ዝም ብሎ አሜሪካ እንደዚህ ነዉ (ነዋሪዉን ብዛቱን ሳያስተያዩ ) በጉዋደኝነት ወይንም ዝም ብሎ በጥላቻ አዲስ ነገር መጀመር ለዛዉም ቢከፋም ቢለማም ጠንከር ያለ መሠረት ያለዉ ቤተክርስቲያን እያልለ ህዝብን መከፋፈል ማደናበርና ሃይማኖታችንን ርካሽ ማድረግ ነው ደግሞስ ያለንን ነገር ጥለን እንዴት ሌላ ቦታ እንሄዳለን መሽነፍ አይደለም እንዴ ለማለት ያክል ነው እንጂ ከመሰላችሁ ቀጥሉበት በጣም እግዚአብሔር ይቅናችሁ አደራ የምለው ግን ከሁሉም ነገር በፊት ክብር ለክብርት ኦርቶዶክስ እንዲሆን ነው :: ግን ሌላዉን ሌላዉን ተወዉና የኔ አስተያየቴ አሁንም ልነግርህ የምፈልገዉ የራስህን ቤት ግድግዳው ፈረሰ ብለህ ለሌላ ሰዉ ዉሰድ ብለህ ጥለህ መሄድ ሞኝነት ወይንም መሀይምነት ነው ::
ሌላዉ ግን አሁንም የሰዉን ስም እየጠሩ በዓለም ላይ ያለ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የማይፈልገዉን ነገር እንዲያነብብ እና እንዲስሰላች ማድረግ ነውር ነው ::
እኔ በግሌ ደስ የማይለኝ ነገር ደግሞ ማንም ሰው ከፈለገ ማድረግ የሚችለዉን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ...... በእግዚአብሔር አያስፈልግም ( ሀገር ቤት ትምህርት ቤቴ ወደ ቤቴ የምትወስደኝ አዉቶብስ ሶስት ቁጥር ነበረች ታድያ ታውቁት የለም የዛን ሀገር ኑሮ አንዳንድ ጊዜ ሳልከፍል ስሄድ እኔ ኮንትሮል ገባ እያልኩ አዉቶቡሱ ባቆመ ቁጥር ልቤ ሲደነግጥ (በነገራችን ላይ ኢትዮጵያ ያሁኑን አላዉቅም በደጉ ዘመን ተቆጣጣሪ ያለ ፌርማታ አዉቶብስ አስቁሞ መግባት ይችል ነበር ) ለካ እነ አጅሬ ሌቦች አዉቶቡሱ ዉስጥ ነበሩልኝ አንዱን ሽማግሌ ጡረታቸዉን እንደተቀበሉ የያዙትን ብር ለቀም አድርገዋቸዋል ......ሽማግሌው ኡኡታቸዉን ያቀልጡታል .....አዉቶብሱ ይቆማል ልክ ፓስታ ቤት ነው ሴንትራል ባንክ ፊትለፊት ልጁ መስረቁ ሲታወቅበት ገንዘቡን ይጥለዋል ....ሰዎች ሲጥል ያዩታል ....ከዛ የወረደበት የዱላ ዓይነት አይድረስ .......በዚህን ሰዓት ልጁ እግዚአብሔር ያሣያችሁ ይጠራቸዉ የነበሩት ቤተክርስቲያናት ስም አንዳንዱን እኔ እስክዛሬ ሰምቻቸው አላዉቅም በዚህን ስዓት እኔ እንዴት ይሄን ሃይማኖተኛ የገጠር ልጅ ሲሰርቅ ሳያዩ ይደበድቡታል ብዬ ወደ አንድ ሣምንት ስለዚህ ልጅ ሳስብ ጭንቅላቴ ሲርረበሽ ነበር በሁዋላ ነው ነገር እየገባኝ ሲመጣ ለካስ ሌባ መሆኑን ያወቅኩት :: እና የመጽሐፍ ቅዱሱን ጥቅስ እንደ አዉቃለሁ መረጃ በቦታው ቢሆን ይሻላል :: እዚህ እኔ በበኩሌ የማወራዉ የሃይማኖታችንን እዉቀት እንድንፈታተን ሣይሆን በመጀመሪያ ሃይማኖታችንን እንድንጠብቅ ነው :: ሌላዉን ለጊዜዉ እንተወዉ ለሁሉም ጊዜ አለው ::
እኔን ባሁኑ ጊዜ የሚረብሸኝ ዋናዉ ሃይማኖታችንን የሚያረክሱ ሰዎች መብዛታቸውና እኔ የማዉቃት ኦርቶዶክስ ዶግማዋ አሁን ከማየው ጋር በጣም እየተለየ ስለመጣብኝ ነው እንጂ ቤተክርስቲያን የሚመጣ ሰው idividual behaviour አይደለም ደግሞ የትም ያልለ ነው :: ባለቤቴ አንድ ደስ የማይለኝ መጥፎ ጸባይ አልላት ብዬ ልጆቼን ጥዬ ወደየትም አልሄድም ::
ባለውፈው ጉባኤ ላይ ተገኝታችሁ ከሆነ ጳጳሱ ምን እንደተናገሩ ሰምታችሁ ይሆናል :: ቄስ መስፍንን አሁንም ቢሆን ከሙኒክ ቤተክርስቲያን አገልጋይነት ነው እንጂ የታገዱት የክህነት ማዕረጋቸውን መግፈፍ አይቻልም ነው ያሉት ይሄ ማለት እንግዲህ ነገ ሮዘንሀይም አንድ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ተቓቓመ ቢባል ቄስ መስፍን ገብተው የመቀደስ ሙሉ መብታቸዉ ነው :: መነጋገር ያልለብን ስለ እንደዚህ ዓይነት ጉዳዮች ነው ዓለም ላይ ያልለ ኦርቶዶክስ ዘበኛ ኢትዮጵያዊም ማወቅ ያልለበትም ሄንን ነው እንጂ ስለ ዘነበወርቅ እና ስለ ብርሃኑ ጋብቻ አይደለም እንዲህ አይነት ነገር ስለ ሰው ፕራይቬት ጉዳይ ወይንም ችግርም ቢባል አካባቢን ችግር ለማይመለከተዉ በዓለም ላይ ለተበተነ ኢትዮጵያዊ እና ለቤተሰብ ሣይቀር እንዲያነብ እዚህ መጻፍ ሰዉ ያስንቃል እዉነት አሣፋሪ ነው ስለዚህ እንዲህ ዓይነት አስጠሊታ ነገር ቢቀር ጥሩ ነው ::

እግዚአብሔር ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን

ይቅጥላል ..........................................
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሰዋሰው

አዲስ


Joined: 25 Nov 2003
Posts: 20

PostPosted: Mon Feb 28, 2011 9:45 pm    Post subject: Reply with quote

ጤናይስጥልኝ ዉድ የሀገር ሰዎች ላለፉት ሁለት ተከታታይ አስተያየቶች አርእስቴ ወጣ ያሉ ነገር ግን ከአሁኑ ውጣዉረድ ጋርና እዚህ ካልለው ከህብረተሰባችን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ትያያዥ ስለሆኑ ነገሮች ጠቆም በማድረጌ ሪአክሽን ለመጀመሪያ ጊዜ አስተያየት ስለተጻፈ መመለስ ግዴታ ስለሆነ ያው እንግዲህ እንደምታዩት ወርቁዋ ጊዜ በዛ ባክናለች :: ዛሬ ግን ወደ ጀመርኩት አርእስት ነው የምመለሰዉ ::
እስቲ ይሄንን እዚህ ላይ ስለሞጫጨርኩኝ ታዋቂ ልሁን !
እንደነገርኩዋችሁ ቤተ ክርስቲያናችን ጠረኑዋ ተመልሶ በደስታ ቅዳሴ ይቀደስባት ጀምሩዋል :: እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን :: የሰዉ ልጅ ከምንም ነገር በላይ መዉደድ ያልለበት የህሊና ነጻነቱን ነው :: የህሊና ነጻነት ከምንም ነገር በላይ ይበልጣል የሰዉ ልጅ ነጻ የሆነ ከሆነ በራሱ ይተማመናል የማንንም ሀሣብ ወይንም አመለካካት በፍራቻ ወይንም እራስን ባለመተማመን አይደግፍም ወይንም አያጎድፍም :: በአብዛኛው ወደ ጴንጤነት የሚለወጡት ኢትዮጵያዉያኖች ችግራቸው የአንዳንዶቹ ግራመጋባት ወይንም ሃይማኖታቸዉን ቢለዉጡ ለጊዜያዊ ችግራቸው በአቁዋራጭ መፍትሔ የሚያመጡ እየመሰላቸው ሲሆን የሌላዎቹ ደግሞ ዋናዉ በራስ አለመተማመንና የእዉቀት ማነስ ብቻ ነው :: አእምሮዉ ነጻ የሆነ ሰው አንዳንድ ወሳኝ የሆኑ ነገሮችን ለመወሰን በደንብ ማመዛዘን ይጀምራል እዚህም አሁን በሰዉ ፊት ላይ የሚታየዉ ይሄው ደስታ ነው ....... በራስ መተማመን :: ቤተክርስቲያናችንን ማንም አይወስድብንም ለማንም ሰዉም ጥለን አንሄድም እኛ እዚህ ሀገር ስለምንኖር ነው ማንም ይመስርታት ማንም ለእኛ ተብላ በእኛ ስም ነው (ይህን ያክል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች እዚህ አካባቢ አልሉኝ በማለት ነው ከካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሣይቀር ገንዘብ ሲታፈስ የኖረዉ ) በእኛ ኃይል ነው እስከዛሬም ያለችዉ ፍቅሩን ጤናዉን እና ሰላሙን ይስጠን እንጂ ............ የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው አይደለም ? ቤተክርስቲያን ደግሞ እግዚአብሔር ቤት ስለሆነች ሁሉን ነገር በጥበብ በሲኖዶስ ህግ የማናደርግበት ምንም ምክንያት ሊኖረን አይችልም ስለዚህ ዋናዉ ትግስትና አስተዋይነት መተሳሰብና መተማመንን ከጸሎታችን ጋር ሁልጊዜ አለመርሳት ነው ::
ይልቅ ከእንግዲህ በሁዋላ በደንብ መታሰብ ያልለበት ትልቅ ጉዳይ የሚመስለኝ ምን አይነት ሰዉ (ቄስ ) እዚህ ቤተክርስቲያን ዉስጥ ለማገልገል የሚመጣዉ ? ማን ነውስ የሚያመጣው ? ከእንግዲህ በሁዋላ እንዲህ ዓይነት ነገር ዓይናችን እያየ ጆሯችን እየሰማ ለምሣሌ :- የሽቱትጋርት ቄስ ጴንጤ የሙኒክ ቄስ ሌባ የፍራንክፈርትም ቄስ ተነስተው እራስን ማጋለጥ ያክል እንዲህ ዓይነት ምስቅልቅላቸዉ የወጣ ነገሮች እዉነት የኢትዮጵያ ሲኖዶስ አልለ ወይ እስከሚባል ድረስ ቤተክርስቲያናችን ስትዋረድ እያየን ጳጳሳትንስ እናምናቸዋለን ወይ ? እኔ አሁንም ቢሆን ወያኔን ዘረኛነት ከምንም ነገር በላይ አድርጌ የምቃወምበትና እነሱንም እንድጠላቸዉ ዋንኛዉ ምክንያቴ ትግሬዎችን በየቦታዉ አጋጣሚ ባገኙ ቁጥር ስለሚሰገስጉ ነው :: እኚህም ጳጳስ ለተሰጣችዉ ሃላፊነት ትግሬነታቸው እንጂ እዉቀታቸዉ አይመስለኝም :: እኔ እስከ ዛሬ ድረስ ስኖር እንኩዋን አንድ ጳጳስ አወላግዶ ሊዘምር እና ጮክ ብሎ ሲናገር ሰምቼም አላዉቅም :: የቅዳሴ ሥነስርዓት ላይ እንኩዋን የጳጳስ ድምጽ ረጋ ያለና ለዛ ያልለው ነው :: ምን ዓይነት ጊዜ ላይ እንደተደረሰ እግዚአብሔር ይወቅ :: ጉባኤው ሲካሄድ የሆነ የመወያያው መድረክ ለአንድ ደቂቃ ዝም ሲባል ጳጳስ ተብዬዉ ተነስተው መዝሙር ማውጣት ! ይሄ ዓይነቱ ነገር ለእኔ በአንድ በኩል የሰዉን ሀሣብ ለመበታተን ሁለተኛም ቄሶችና ዲያቆናት እዛዉ እያልሉላቸው እሳቸው መዝሙረኛ መሆናቸዉ ክብርንና ሃይማኖትን ማርከስ ነው :: ስለዚህ ወደፊት የሚመጣዉ ነገር ትልቅ አሣሣቢ መሆኑን ካሁኑ መገንዘብ ጠቃሚ ነው ምክንያቱም አንዳንድ ደስ የማይሉ ምልክቶች አባቶች ላይ ስለሚታይ ቤተክርስቲያን እንዳትረክስ የሁላችንም በሃይማኖትና በእዉነት መቆም እና አንዳንድ ዘመን አመጣሽ አጉዋጉል ነገሮችን አያስፈልገንም ማለት ከመጀመሪያዉ ይገብባል :: እንደዚህ ስል የሚመጡት አባት በአጋጣሚ ትግሬ ቢሆኑና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን የሚያስከብሩ አዋቂ ትህትና አስተማሪ እንደ ቄስ መስፍን የማይወደዱ የወያኔ ቡችላ ከወንጌሉ ወደ ፖለቲካዉ የማይዘልሉ ከሆኑ ችግር የለብኝም :: ግን እንዲህ ዓይነት ነገሮችም ሊኖሩ ስለሚችሉ ውድ ጎረቤቶቼ ለመወያየት ዝግጅት ያስፈልጋል :: ቤተ ክርስቲያናችን በቄስ ፋንታ ካድሬ መጥቶ ደግሞ በዚህ መቶ ስልሳ አምስት ሽህ ተዘርፈን በሁዋላ ደግሞ ጠቅላላ ቤተክርስቲያናችንን ሽልማት እንዳንሰጥ ከወዲሁ የሰዉን ስም እዚህ እያመጡ ከማቆሽሽ እነ ጎንጉልንም ሃይማኖታዊ ጥሪ ለጥሩ ተግባር በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስም አደርግላችሁዋለሁ ::

አሁንም እግዚአብሔር ሳይለያየን ሃይማኖታችንን ያጽናልን ::

ሰዋስወብርሃን ግሮስ ሀደርን ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሰዋሰው

አዲስ


Joined: 25 Nov 2003
Posts: 20

PostPosted: Fri Mar 11, 2011 10:10 pm    Post subject: Reply with quote

ጤናይስጥልኝ እንደምን ከርማችሁዋል ክርስቶስ ቤተሰቦች ድንግል ማርያም ወዳጆች ::
እንደተነገረዉ እንግዲህ እሁድ ማንም እንዳይቀር የሚቀጥለዉን ስቴፕ ለመጀመር ሁላችሁም ተገኝታችሁ እንድንወያይ ይሁን :: አይዟችሁ እግዚአብሔር ጸሎታችንን ሰምቶናል ::
13.03.2011 ከጸሎት በሁዋላ
እግዚአብሔር ይጠብቃችሁ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሊቶስጥራ

አዲስ


Joined: 16 Mar 2011
Posts: 13

PostPosted: Wed Mar 16, 2011 1:41 am    Post subject: የሙኒክ አስተዳዳሪ ጉዳይ Reply with quote

እንዴት አላችሁ እግዚአብሄር ይመስገን ምነው ዝም ዝም አላችሁ ? የእሁዱ ስብሰባ እንዴት ነበር ? እኔ ለምን እንደሆን እኔጃ ሳይመችኝ አለቀ :: እንዳሁን ቀደሙ አልጣመኝም :: መጀመሪያ ላይ ሰው በምን እንደሆን ሳላውቅ ማልቀስ ጀምሮ ነበር :: ቅድም ደሞ ዘውዱና ስብሰባውን ሲመራ የነበረው ሰውዬ ሚስት ነች አሉ "ዘነበወርቅ " የስብሰባ መሪው ሳይቀር ሲያለቅሱ ነበር አሉ :: ንግግር ያረጉት ቄስ ዱሮ ሀይለኛ የጦር ሜዳ ኣርበኛ ነበሩ ሲሉ ሰማሁና እንደዛ እንደሴት ንፍጣቸው እየተዝረከረከ ሲያለቅሱ ወይ መንጌ እንደነዚህ አይነቶቹን ይዘህ እንኩዋን ዚምባቤ ባቢሌ ገደል ብትገባም አይግረም በማለት እጅግ በጣም አልጥምህ አለኝና አፈርኩ :: የሰረቁት ቄስ ምን እንደበደላቸው እንኩዋ አልገባኝም :: የመቶ አለቃ የነበረ አዛዥ እንዴት ያለቅሳል ? ለዛውም ንፍጡ እስከሚዝረከረክ ! ንግግራቸውም የሚያስለቅስ መስሎ አልታየኝም ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ethio-german

መንገደኛ


Joined: 20 Dec 2010
Posts: 9

PostPosted: Thu Mar 17, 2011 3:27 pm    Post subject: Reply with quote

ምነው እዚህ ቤተክርስቲያን ቲያትር ሰሪው በዛ Question እግዚኦ Shocked
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሰዋሰው

አዲስ


Joined: 25 Nov 2003
Posts: 20

PostPosted: Tue Mar 22, 2011 7:29 am    Post subject: Reply with quote

ጤናይስጥልኝ ኦርቶዶክስ ቤተሰቦች የእግዚአብሔር የድንግልማርያም ወዳጆች እንደምን ከርማችሁዋል እግዚአብሔር ጤንነትን እና ፍቅርን አይለይባችሁ :: እንግዲህ ሁላችንም እንደምንመለከተዉ ቤተክርስቲያናችን ዉርደት ዉስጥ በየትኛዉም በኩል እየገባች መሆኑዋን ነው ስለዚህ የኛ ጥንካሬ ከመቼዉም በላይ አስፈላጊ እየሆነ መምጣቱ ለማንም ሰው ግልጽ እየሆነ ነው :: እንወያይበታለን ብለን ያነሣነው ርእስ ቤተክርስቲያናችንን ስለዘረፉት ቄስ መስፍን /ማርያም ፈለቀ ነው :: ይህእዉም ከላይ በተከታታይ እንደተገለጸው ህዝብ እንዳከበራቸው ሌባ ቤተክርስቲያናችን ዉስጥ አያስፈልግም በማለት አሰናብቷቸዋል :: የእሁዱም ስብሰባ እንግዲህ እንዴት ጉዳዩን ከቤተክርስቲያን ወደ ፍርድ ቤት ድረስ እናድርሰዉ ? በምን አይነት መንገድ ? በየትኛዉ ወንጀል (ብዙ ወንጀል ስላለባቸው )::
1. አታልለዉ ውክልና ማስፈረም
2. አታልለው ከካቶሊክ ቸርች ገንዘብ መዉሰድ
3. የባንክ ቡኮችን በተለያየ ምክንያት (የሳቸዉ ያልሆነን ንብረት እንደልባቸዉ ለማድረግ ወንጀል ላይሆን ቢችልም ያስጠይቃቸዋል
4. ህዝቡን በፖለቲካ ወይንም በተለያየ መንገድ መለያየት
5. ቢያንስ ቢያንስ 165 ሽህ የሙኒክ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንን ብር መዝረፋቸዉ
6. ሰነድ ማወናበዳቸዉ
7. ሃይማኖታችንን በመጥፎ ሥነምግባር ማስጠራታቸዉ
8. ሌላ ሌላ ብዙ ነገሮችም አሉ ...በተለያየ ዓይነት ስድብ ሲሞለጩ የኖሩት ሰዎች ሁሉ እንግዲህ እንደ ቄስ መኮንን ዓይነቶች ብዙ ስላሉ ተጨማሪ መረጃዎች ይሆናሉ ::
ዉድ የኦርቶዶክስ ቤተሰቦች ስለእዉነት እላችሁአለሁ ከእንግዲህ ወዲህ ምንም ነገር አልጽፍም እኔ ምንድነኝ ? ምንስ አገባኝ ? ጊዜዬንስ ለምን አባክናለሁ ? ለምን ሌላ ሰዉ ከእኔ የበለጠ ቤተክርስቲያኑ ቅርብ የሆነ ሰዉ የበለጠ ኢንፎርሜሽን ያለዉ ሰው አይጽፍም ? ምናምን ብዬ ልተወዉ ብዬ ነበር ግን ይኸዉ እንደምታዩት ማንም ምንም ለማለት አልተዘጋጀም ወይንም አንዳንዶቹም የሚጽፉት በእኔ አመለካከት ስለ ቤተክርስቲያኒቱዋ ችግር ሳይሆን ለምሳሌ ከላይ እንደተጻፈው (personal emotions ) ምንም ለሃይማኖቱ እድገት ወይንም ግድፈት መልእክት የሌለዉ ነገር ነው :: ስለዚህ ነው እንግዲህ ታዋቂ ለመሆን እዚህ የምንገዳገደዉ :: ይገርማችሁዋል ግን ከብዙ ሰዎች ጋር ስነጋገር ይሄንን ዋርካ ላይ የምጽፈው እኔ መሆኔን የማያዉቁ ሰዎች ለእኔዉ ለእራሴ እንዴት እንደሚሞልጩኝ ብታዩ ወይ የሰዉ ልጅ ? ያስብላችሁዋል :: ክርክራቸው :- እስከዛሬ የት ነበረ ? ይሄኔ ከሳቸዉ ጋር ገንዘቡን የተካፈለ ነው ? እስቲ በምን አድርገዉ ነው እንደዚህ ሊያስቡት የቻሉት :: እሳቸዉን እንዳትነኩዋቸው እያለ ሲያቃጥር የኖረ ነው ? ይሄ የአቡን ጳዉሎስ ተላላኪ እግዚአብሔርን የማይባል ነገር የለም እኔን ግን ምንም እነስሱ እንደሚሉት አንድም ነገር የሚመለከተኝ የለም እኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ ስኖር የማዉቃትን ኦርቶዶክስ ለምን አጣታለሁ ? ጀርመኖችና ሌሎች አዉሮፓዉያኖች ሃይማኖታቸዉንና ባህላቸዉን ለገንዘብ ለሀብት በማለት ሲቪላይዝድ ኔሽን ..እራሳቸዉን በማለት ሁሉን ነገር ድምጥማጡን ካጠፉት በሁዋላ ይኸዉ አሁን ወደሁዋላ ለመመለስ የማይቻል ደረጃ ላይ ደርሰው ሃይማኖታቸውን ምንም ዋጋ ስላሳጡት ሃይማኖታቸዉን የሚያጠብቁ ሙስሊሞችን ሲመጡ ምዉጫ መግቢያ ማሳጣት , ትላንት ባለትዳር የነበረችዉ ሴትዮ ዛሬ ሴት እጮኛ ይዛ ከእርሱዋ በሰርግ በህግ ካልተጋባሁ , ወንድ ለወንድም ተጋብቶ ልጅ ከኢትዮጵያ (እድሜ ለጽሀዩ መንግስት ) ወይንም ታይላንድ አምጥተን ካላሳደግን , ወዘተ ... ነው በየ ፓርላሜንቱ በየ ቴሌቪዥኑ ውይይታቸዉ :: ከዛሬ እርግጠኛ አይደለሁም 7-8 ዓመት በፊት ድረስ እዚህ ባቫሪያ ዉስጥ በየትምህርት ቤቶች ክላስሩም ዉስጥ ግድግዳ ላይ መስቀል ነበር አሁን ከእኛ ጋር የሚኖሩ ሙስሊሞች ስለበዙ የኛ ሃይማኖት ያን ያህል አስፈላጊ አይደለም ብለዉ ነው ከእያንዳንዱ እለመንተሪ ስኩል ክላስሩም ዉስጥ መስቀሉን ያወረዱት ሃይማኖታችን ይሄን አይፈቅድም የሚል ነገር ወይንም ባህላችን ይህን አይፈቅድም የሚል ነገር እኔ እስከዛሬ ድረስ ሰምቼ አላዉቅም :: እና ሃይማኖቴን በማውቃት ህግ እንድትኖር ስለምፈልግ ብቻ ነው :: የማዝነዉ ግን ፈጽሞ እኔ ከምጽፈዉ ነገር ጋር እንኩዋን እንነሱ ሊጽፉ ንክኪ የሌላቸዉን ሰዎች ከጥላቻ ጋር የተቀላቀለ አስተያየት ስሰማ በጣም ነው የደነገጥኩት ::
ይሄ ነው እንግዲህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና በጀርመን ሀገር ዉስጥ ጥሩም ይስሩ በጎ እስከዛሬ ላቆዩልን አባቶች እያመሰገንን ቆንጆ ስምና ክብር ነበራት ከእንግዲህ በሁዋላ ግን ይህ አምድ ተዘግቱዋል :: ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክ አንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቄስ በፈረንጅ ሀገር የቤተክርስቲያን ገንዘብ ዘርፎ ወህኒ ቤት ሊገባ ነው :: ይሄ ነው ሀገርን እና ህዝብን ማዋረድ እንደዉ ሌላዉ ሃይማኖቱን ምናምኑን እንኩዋን ብንተወዉ ማናለብኝ እኔ ነኝ አዋቂ እኔ ነኝ ፈላጭ ቆራጭ እኔነኝ ኃይለኛ ከእራስ ተርፎ ሀገርን ህዝብን ለማዋረድ ይተርፋል ......እዚህ ሀገር እንግዲህ የወያኔ ፓርቲ አባልነት ወይንም ዝምድና ወይንም የድሮዉ ማጎብደድ አይሰራም እዚህ ሀገር ህግ ምን እንደሆነ ተምረዉ ይወጣሉ :: ግን አሁንም የሀገሬ ሰዎች መንቃት ያስፈልጋል የኢትዮጵያ መንግስት ነኝ ባዩ አስተዳደር ሀገራችንን ስሙዋን ለማጉደፍ ቆርጦ የተነሳ የትግራይ ዱርዬዎች ጥርቅም ነው እንደሰማሁት ከሆነ እግዚአብሔር እዉነት አያድርገዉ እና ታቦት እንደ ቀበሌ ስኩዋር እያከፋፈለ ነው :: ይሄ የሚደረገዉ ሃይማኖቱን ለማስናቅ ነው ርካሽ ለማድረግ ነው ስለዚህ ስለ ሀይማኖታችን የምንል ከሆነ ድርጊቶችን ማጥናት አለብን የታቦታትን አመጣጥ ህጋዊነትን ሁሉ ማየት አለብን :: የመጽሐፍ ቅዱስን ሽፋን በተለያየ ቀለም ማድረግ ይቻላል ነገር ግን የመጽሐፍ ቅዱስን የጽሑፉን ይዘት መቀየር የክርስቶስን ቃል መቀየር ማለት ነው :: ይዘቱ ተቀየረ ማለት መልእክቱ ተቀየረ ማለት ዋጋ ቢስ ሆነ ማለት ነው ስለዚህ ለማንኛዉም የሀገራችን ዉድቀት በስልጣን ላይ ያለዉ አረመኔ እና ሃይማኖትን በራሱ አመለካከት የተረጎመ ማናለብኝ የሚለው የልጅነት ወይንም የወጣትነት ዘመናቸዉን በእስላም ሀገር ጫት ቤት ወይንም መስጊድ ዉስጥ ያሳለፉ ትህትናን የማያዉቁ ልቅ ባለጌ ሰዎች ጥርቅም መንግስት ተብዬ ሆን ብሎ የሚያደርገዉ ነገር ስለሆነ ነገሮችን አብሰልስለን ማየት አለብን :: የሚገርመው ነገር እዚህ ሀገር ብቻ ሣይሆን አዲስ ድምጽ ራዲዮ ኢንተርኔት ስሰማ ዋሽንግተን ዉስጥም እንዲህ ዓይነት ሌብነት በአሁኑ ሰዓት እንዳለ ነው የተረዳሁት ምናልባት ግን ቄስ መስፍን እና የዋሽንግተኑ ዘመዳሞች እንዳይሆኑ :: እኔ የማዉቀው በጸሀዩ የወያኔ መንግስት ገንዘብ ለመስረቅና ቆንጆ ስልጣን ለማግኘት ዲግሪ ምናምን ያለዉ ሰው ሳይሆን እነሱ የሚፈልጉት ከእነርሱ ጋር ሆኖ የሚሰርቅ እና እስከተወሰነ ጊዜ ተጠቅመዉበት የሚወረዉሩት ጅል ሰዉ ለጥቅም ሲል ወደሁዋላ ዞሮ የማያይ እንደደነበረ ፈረስ ቶሎ ቶሎ የሚተነፍሰ ዘላለም እየተገላመጡ የሚኖሩ ያልተረጋጉ ስዎችን ነዉ :: ነገር ግን ገንዘብ ለመስረቅ ሆን ተብሎ ቄስ የሚኮንበት ዘመን ላይ መድረሳችን ስምንተኛዉ ሽህ ብቻ ሳይሆን ወደ ዘጠነኛዉ ሽህ ሳንገባ አንቀርም ባይ ነኝ :: እስቲ እኚህ ቄስ መስፍን ምን አለበት ከበፊቱ ሌላ ዓይነት ስራ ለምሳሌ የኤልክትሪክ መብራት ቆጣሪ አንባቢ እንጨት ፈላጭ ጭቃ ማቡካት ኩሊነት ወይንም ዘፋኝ ወይም ደግሞ መንገድ ተዳዳሪ ድኩማን እርዳታ ድርጅት አቕቁመው ሀላፊ ቢሆኑና ገንዘብ ቢሰርቁ ስለ እዉነት ማንም አይፈርድባቸዉም ነበር ቸግሩአቸዉ ነው ይባላል :: ጎንደር ገጠር ጀርመን ሀገር መጥተው በወር እስከ ቢያንስ 1 ሽህ ኦይሮ (እርግጠኛ አይደለሁም ) ከቤት ኪራይ ዉጭ እየተከፈላቸዉ ተንደላቅቅው እየኖሩ ቤተክርስቲያንን ማርከሣቸው የሚነግረን ይሄንን በዓለም ላይ የተሰራጨዉን በደንብ የተዋቀረን የወያኔን የስርቆሽ ትምህርት ቤት ነው ::

እግዚአብሔር እኛንም ቤተክርስቲያናችንንም ይጠብቅልን ............

ሰዋስወብርሃን ግሮስ ሀደርን ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሊቶስጥራ

አዲስ


Joined: 16 Mar 2011
Posts: 13

PostPosted: Wed Mar 23, 2011 1:52 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላምታዬ ይድረሳችሁ !
ዘራፊ የዘረፈውን መመለስ አለያም መከሰስ ህግ ባለበት ሀገር ደንብ ነውና ይቅናችሁ :: ቄስ መስፍን ልቡ እንደተወጠረች ምላሱ መርዝ እንደረጨች እግሩም ለጥፋት እንደቸኮለች አቅጣጫዋ ወደ ስታድልሀይም መሆኑዋ ያሳዝናል :: አንተ የምትስቅ ሰው ስለማትመስል ቁም ነገር ከመጻፌ በፊት እስቲ ልኮርኩርህ ከተሳካልኝና ካሳኩህ !!
አያትህ ሲሞቱ ጤፍ 10ብር ነበር
አባትህ ሲሞቱ ጤፍ 100ብር ነበር

አንተ ስትሞት ግን ጤፍ በሺ ተሸጠ
ጎበዝ እንዳንተ ነው ችግር ያመለጠ .... አለች አስለቃሽ ሀገሬ ያለውን የኑሮ ውድነት አንድ ዘመዴ ሞቶ ስላመለጠ ቤተሰባችንን ስታጽናና !!

ሰዋስው ለምትሰጠው አስተያየት ሁሉ አድናቆቴን እየገለጽኩ እንዳይቀርብኝ ላምል ታክል ሀሣቤን ጣል ላርግልህ ::
1) ስዋስው የሚለው ስም በቂህ ይሁን :: ከብርሀን በሁዋላ ሁል ጊዜ ጨለማ ይከተላልና :: መላከ ብርሀን መስፍን እኮ ነው 19ኛው ሰዓት ወደ መላከ ጽልመትነት ወይም ወደ መላከ ሙስና የተቀየረው ::
2)ቄስ መስፍንን እንደ አንድ ተራ ሰው ቁጠረው :: ስለወያኔ ያለህን የግል አስተያየት ከጨማመርክለት ያንተን ጽሁፍ ኮፒ አርጎ የሐሰት ክሱን እውን ሊያስመስለው ይችላል ::
3)ከረዥም ዘመን በሁዋላ ስለመጣሁ ለኔና መሰሎቼ እነዛ ነጠላ አዘቅዝቀው ነው የሚሄዱት የሚባሉትን ሴቶች ስም ብታሳውቀን አፋችን ከመዘባረቁ በፊት መጠንቀቅ እንችላለን ::
4)ከመጻፍ አትቦዝን :: ክፉም ይሁን በጎ የሚሰጥ አስተያየትና የሚተላለፉ ኢንፎርሜሽኖች ጥቅማቸው ጥሩ ነው :: አንተም ሆንክ እኔ የምንጽፋቸው አስተያየቶች እንደዛ የእምዬ ማርያምን ስም ሲጠራ ጉሮሮው ላይ ጠብ እንዳደረገለት ነብሰ በላ ሰውዬ ውኃ አርገህ ውሰደው :: ቁምነገሩ አስተያየቶቹን ለጠጥ አርጎ የማየቱ ጉዳይ ነው ::
የማይጽፈውንም አትኮንነው :: አልተመቸውም ብለህ እለፈው ::ሁሉም ሰው ጉዳዩ ነው ያገባዋል :: ወዳጄ በቄሱ ሚስት ከሚመራው የወሬ ፓርላማ በስተቀር የክሱን አጀማመርና የቄስ መስፍንን መጨረሻ የሚያወሩልህ እኔ ባለሁባት በዚች ትንሺ ከተማ እንኩዋ ጫካ የማይኖሩ ብልህ ጦጣዎች ስንት አሉ መሰለህ !!
ሀገርህ እንዳልከው አስቂኝ እየሆነች ነው :: ኃይማኖታችን ግን እውነትህን ነው የኅብረት ሱቅ መሆን የለባትም :: አውራ አውራውን ነገር ስለጠቀስከው አልደግመውም :: ሌላ ጊዜ ግን እመለስበት ይሆናል ::ለማኝ ሆኖ ታላቅነት ደረጃ የሚደረስባት ከታላቅነት ወደ ሌብነት የሚሸጋገሩባት ከሌብነት ወህኒ የሚወርዱባት ሁሉም ዓይነት የሕይወት ፕሮሰስ ያለባት ጉድ እየተወለደ ጉድ የሚፈላባት ጉድ የሚመጣባት ሀገር !
የጠቀስካቸው ወንጀሎች ስንት ስንት ዓመት እንደሚያስፈርዱ ብትጠቁመው መላከ ሙስና ካሁኑ ስንቅ አመላላሽ መድቦ እንዲገባ ትረዳው ነበር :: ሰውዬው በትእቢት የተወጠረ በትምክሕት የደነቆረ በፍቅረ -ንዋይ ያበደና የታወረ ሀገርና ኃይማኖትን አሰዳቢ ጠማማ ስለሆነ እንኩዋን ተውከው :: ይደርስበታልና !!
የቤት ኪራይ የመብራት የስልክ የውኃ የትራንስፖርት የቤት አስቤዛ በወር 1000ኤሮ የኪስ ገንዘብ ያልበቃው ዘራፊ ኪሳችን መግባት ሳይጀምር ጉሮሮው ላይ መቆማችሁን እጅግ በጣም ወድጄዋለሁ ::
እየጠቡ ሲነክሱሺ
ሰው አድርገሺ ! አሳድገሺ !
ከልመናም አውጥተሺ

ወዳጅ መስለው
ለምዳቸውን ተጀቡነው
ጉያሺ ሆነው የሌላ
አባት መስሎ ደላላ ! ሌባ !

ለዛሬው በፍቅር እንለያይ !!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ethio-german

መንገደኛ


Joined: 20 Dec 2010
Posts: 9

PostPosted: Sat Mar 26, 2011 6:33 pm    Post subject: Reply with quote

ሠላም ወገኖች እንዴት ናችሁ ? ባለፈው ወደ ቤተክርስቲያን ባለመሄዴም የቤተክርስቲያኑ ቲያትር ሊቶስጥራ የጻፍከውን አይቼ ገርሞኝ ጊዜም ስላልነበረኝ አስተያየትም ሳልጽፍ ነበር Laughing Laughing Laughing Laughing ሊቶስጥራ አሳከን እያዝናናህ እውነቱን የምትናገር ጥሩ ጠሀፊ ነህ እስከዛሬ የት ነበርክ አቦ ?የአዞ እንባቸውን ሲያረግፉ አይተህ አልጥምም ያለህም ድራማ ሰሪዎቹ ቀደም ሲል ከሌባው ቄስ ጋር ዳንኪራ እየረገጡ የቄሱ ከለላ የነበሩ የተጠቃቀሙ ሰዎች "ጅብ ከሄደ ውሻ ጮሀ " እንደሚባለው ገንዘባችን ከተበላ በሁዋላ ይመርመርልን ይጣራልን ምን ዋጋ አለው ? ሰውን በአሉ ባልታና በወሬ እየከፋፈሉ ለቄሱ እና ለሚስትየዋ ወሬ ይዘው ከመሮጥ ትኩረታቸው ሐይማኖታቸው ላይ ቢሆን ይሄ ሁሉ ባልደረሰብን እነሱም ዛሬ ቄሱን ባልኮነኑ ነበር :: የሌባውም ቄስ የነኝህም ጉደኞች ያለፈ ቆሻሻ ስራቸውን ለሌላው በየአገሩ ላሉት ወገኖች ግን ትምህርት ይሆናልና እዚህ ላይ መጻፉን እደግፈዋለሁ

ሊቶስጥራ ስለመንጌ የጻፍከውን ሳነበው Laughing አንተ ፈሪና ልክስክስ የማትወድ ሰው መሆንህ ያስታውቃል ወንድሜ በስመ ወታደር ሁሉም ወታደር መሰለህ በስተ መጨረሻ መንጌ በየ 3 ወሩ ለብ ለብ አድርጎ ያሰለጠናቸው ሁሉ አብረው ከሌሎቹ እኩል ማየትም የለብንም እንደነ መንገደኛው ዳርጌ መሸሻ አይነቶችም አሉና እስኪ ESAT TV ክፈትና ጀግናው ዳርጌ መሸሻን እይልኝ እሱን ማየቱ ይሻለናል አሳፋሪ ወታደር ከማየት በነገራችን ላይ አሁን የተባለው ቄስ መቶ አለቃ መሆኑንም እምናውቀው ነገር የለም ወታደር መሆኑን ነው ሁለት የተለያየ መጠሪያ ስሞች እንዳሉትም ነው የምናውቀው የተወሰኑ አመታቶች ከሌባው ከቄስ መስፍን ወዳጅ በነበሩበት ወቅት ቄስ ለመሆን አብረው ከቄስ መስፍን ገብርኤል ቤተክርስቲያንን እናገለግላለን ተባብለው ተስማምተው ቄስ መስፍንም ወደ አገር ቤት ልከውት 3 ወር ጊዜ ውስጥ ቄስ ሆኖ አገር ቤት ቅስና ተሹሞ መጣ ተብሎ አብሮ ሲሰራ አበሮ ዘጥ ዘጥ ሲል ነበር የምናየው ከዛም መስፍን እንደፈለገ እንደልማዱ ሊያሽከረክረው ሲል ይሄኛውም ቅስናዬን ከያዝኩ በሁዋላ አንተ እንደፈለከው አልሆንልህም ለብቻዬ ወደፊት ሰው ሰብስቤ የራሴን ቤተክርስቲያን አቁዋቁማለሁ በሎ ከቤተክርስቲያኑ ጠፋ እንደው በነገራችን ላይ ቅስና ተምሮ ጨርሶ አንድ ቄስ - ቄስ ለመሆን ለመባል አገር ቤት ሄዶ 3ወር ጊዜ ውስጥ ምንም የማያውቀው ቅስና ተምሮ መጨረስስ ይችላል ? ይሄን መልስ ለአዋቂዎች ትቸዋለሁ Sad አብረው ሚስቶቻቸው ሳይቀሩ ዳንኪራ ሲመቱ የነበሩ ዛሬ ደግሞ ፍርድ ቤት መስካሪም ለመሆን እየተጋበዘ ነው አቤት የዘንድሮ ቄሶች Sad የቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን እንደተቁዋቁዋመም ሰምቶ ለማገልገል ቤተክርስቲያን በመሄድ ካየ በሁዋላ ቤተክርስቲያኑን የሚመራው በስደት ያለው የኢትዮፕያ ቤተክርስቲያን መሆኑን ሲያውቅ አልፈልግም ብሎ በዛው እንደቀረ ነው የሚናገረው አገር ቤት ካለው ወያኔው ፓውሎስ የሚመራው ካልሆነ ብሎ መሸሹስ የጤና ነውን ? እንደው አንዳድ ቄስ ነኝ ባዮች እግዚአብሄርን እረስተው እንደሚመቻቸው ብቻ ካልሄድን ሆነ እነሱ እንደሚመቻቸው ሲፈልጉ እኛንም ግራ ያገቡናል

እግዚአብሄር አምላክ ሕእይማኖታችንን ይጠብቅልን !
ይቀጥላል ...
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ምንቸቱ

መንገደኛ


Joined: 26 Jan 2011
Posts: 2

PostPosted: Mon Mar 28, 2011 5:44 pm    Post subject: Reply with quote

ሠላም የክርስቶስ ቤተሰቦች
እግዚአብሄር አይቸኩልም ግን ይፈርዳል ቄስ መስፍን /ማርያም ሰውን እየገላመጡ እና እያንቀጠቀጡ ጄኔራል ሆነው 20 አመታት ከኖሩበት ስልጣን በሰው ፊት በውርደት ሲባረሩ ከዚህ በላይ ምን ፍርድ አለ ብላችሁ ነው Questionእንኩዋንም አልሆንኩ እንጂ እኔ እንደሳቸው ብሆን ኖሮ አገሩን ጥዬ እጠፋ ነበር እዛው ገንዘቡን ያከማቸሁበት አገር እንደው ምን አይነት ደፋር ቢሆኑ ነው እስካሁንም እዚሁ ቁጭ ብለው ከአጫፋሪዎቻቸው የሚኖሩት እኔ ለነሱ አፈርኩ ::
እውነትም ቲያትር በእሳቸው ውርደት ነጠላ አዘቅዝቀው ሽር ሽር ሲሉ የነበሩት እናም እንደ ጀግና የማርያም ቤተክርስቲያን ሄደውም ለመሳደብ አፋቸውን ሲያሾሉ የነበሩት ጉዳቸው እዚህ ላይ ስለተጻፈባቸው አንደኛዋ እንደለመደችው ጉዳቸውን ለመሸፈን እናም የጻፉትን ሰዎች ውሸታም እናስደርጋቸው ብላ ተመካክራ ሹክክ ብላ እግሩዋን እየጎተተች ማርያም ቤተክርስቲያን ሄዳ ቆርባ ወሬዋን ለቃቅማ ተመለሰች ቲያትሩዋን ሰርታ Rolling Eyes አቤት እግዚኦ አይ ቆራቢ እስከዛሬስ የት ነበረች Question ለማንኛውም እዛ ያላችሁ ሴቶች እህቶቼ አፋችሁን ቆጠብ አድርጉ እከሊት እንዲህ አለችኝ እከሌ እንዲህ አለኝ እየተባለ ነገር እንዳይመጣባችሁ :: ውሻ አድርጎ ቄስ መስፍን ከቤተክርስቲያን ያባረራት ነበርች እንደገና በስንት በመከራ ተለማምጣ ወሬ አቀብላ የውሸት እንባዋን አርግፋ ወደ ቤተክርስቲያን የተጠጋችው እና አንዴ ወዲህ አንዴ ወዲያ የምትረግጠው ይቅር ይበላችሁ እንደ በፊቱ ቲያትር እየሰራችሁ መኖር አሁንም አይበቃችሁም Question ከቄሱ ሚስት ጀምሮ እየቆረባችሁ የምትሰሩት ተንኮል አያድርስ ነው ከዚህ ከድፍረት ሰውረን ነው Exclamation ለማንኛውም ወገን እንጠንቀቅ Exclamation
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7  Next
Page 3 of 7

 
Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum


Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia