WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home | About us | Advertise with us | Contact us
የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ቡድን -20ኛው የዓለም ዋንጫ ...
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sat Aug 07, 2010 10:22 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ወገኖቼ ኢትዮጵያውያን :-

በገነነ መኩሪያ አዘጋጅነት በየሁለት ሣምንቱ ቅዳሜ ቅዳሜ ለሕዝብ ትቀርብ የነበረችዋ የስፖርት ጋዜጣ 'ሊብሮ ' እንደገና በድረ -ገፅ መልክ ብቅ ብላለች ::

ገነነ ስለኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ጠለቅ ያለ ዕውቀት ያለው የስፖርት ጋዜጠኛ ነው :: የኢትዮጵያን እግር ኳስ ለማሻሻል የራሱ የእግር ኳስ ዘይቤ አለው -'በመጠጋጋት መጫወት ' የሚባል :: ስለ ዓለም እግር ኳስ ያለው ዕውቀት ተዝቆ የማያልቅ ነው :: ድረ -ገፁን ጎብኙለት ::

ሊብሮ

ወንድሜ ዞብል :- ለአንተ በተለይ ይህ ድረ -ገፅ ብዙ ነገሮችን ሊያስታውስህ ይችላል እና ጎራ ብለህ እንድትመለከተው እጠቁምሃለሁ ::

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሞፊቲ

ዋና ኮትኳች

Joined: 15 Dec 2005
Posts: 695

PostPosted: Sat Aug 07, 2010 11:18 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

ወንድሜ ተድላ :-ምስጋናዬን እንዴት እንደምገልጽልህ አላውቅም ::በጣም የምወደውንና የማደንቀውን ጋዜጣ
አምጥተህ ስትለጥፍልኝ ማመን አልቻልኩም ::ገነነን በደንብ አውቀዋለሁ ::ጋዜጣውንም ከሀገር እስከወጣሁበ ግዜ ድረስ እየገዛሁ አስቀምጥ ነበር ::
በኢትዮጵያ ፉትቦል ያለውን አመለካከትና እምነት ባልደግፈውም እምነቱ ጠንካራነትና ተስፋ ባለመቁረጡ
ከልብ አደንቀዋለሁ ::በችሎታው ታሪክን ጎርጉሮ በማቅረብ በዜናዎቹ እጅግ እጅግ የምረካበት ጋዜጠኛ ነው ::አሁን
ከወደቀበት በመነሳት የድሮ ብስለቱን ይዞ ኦን ላይን መገኘቱ
ከላይ የገለለጽኩትን መንፈሰ ጠንካራነቱን ይገልጽልኛል ::
ገኔ ! መልካም የስራ ዘመን ይሁንልህ !!!!

ተድልሽ በድጋሚ አመሰግናለሁ ::
_________________
http://www.cyberethiopia.com/warka3/viewtopic.php?t=19378
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sat Aug 07, 2010 11:49 pm    Post subject: Reply with quote

ሞፊቲ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን ::

ወንድሜ ተድላ :-ምስጋናዬን እንዴት እንደምገልጽልህ አላውቅም ::በጣም የምወደውንና የማደንቀውን ጋዜጣ
አምጥተህ ስትለጥፍልኝ ማመን አልቻልኩም ::ገነነን በደንብ አውቀዋለሁ ::ጋዜጣውንም ከሀገር እስከወጣሁበ ግዜ ድረስ እየገዛሁ አስቀምጥ ነበር ::
በኢትዮጵያ ፉትቦል ያለውን አመለካከትና እምነት ባልደግፈውም እምነቱ ጠንካራነትና ተስፋ ባለመቁረጡ
ከልብ አደንቀዋለሁ ::በችሎታው ታሪክን ጎርጉሮ በማቅረብ በዜናዎቹ እጅግ እጅግ የምረካበት ጋዜጠኛ ነው ::አሁን
ከወደቀበት በመነሳት የድሮ ብስለቱን ይዞ ኦን ላይን መገኘቱ
ከላይ የገለለጽኩትን መንፈሰ ጠንካራነቱን ይገልጽልኛል ::
ገኔ ! መልካም የስራ ዘመን ይሁንልህ !!!!

ተድልሽ በድጋሚ አመሰግናለሁ ::

ሰላም ሞፊቲ :-

ከሊብሮ ጋዜጣ ጋር ብዙ ትዝታዎች አሉኝ :: አንድ ጋዜጣ ቤተሰብ እና ጓደኛ እየተቀባበለ በፍቅር የሚያነባት .... ብቻ ተወው ::

የገነነ ጋዜጣ በድረ -ገፅ መውጣቷን ያበሠረው የአውራአምባ ታይምስ ጋዜጣ የዛሬው ዕትም ነው ::

እንግዲህ የቆዩ እና የአሁን ታሪኮችን እየተከታተልን እንኮምኩም Very Happy Very Happy Very Happy ::

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Aug 10, 2010 7:55 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

እስኪ ይህንን የቅምሻ ዜና አንብቡት ...
Quote:
እድሜ እና የእግርኳስ ተጫዋቾች ምርጫ

ሊብሮ ዜና - ሊብሮ ዜና

ሻሻመኔ ላይ በተካሄደው የፕሮጀክት ውድድር እድሜአቸው 15 ዓመት በታች በተባሉ ደቡብ እና ኦሮሚያ ባደረጉት ግጥሚያ ላይ በተደረገው ማጣራት አንድ መምህር ተጫዋች ሆኖ ተገኝቷል የየትኛው ትምሕርት ቤት መምህር እንደሆነ እስከአሁን ባይታወቅም የኮሌጅ መምህር እንዳይሆን ተፈርቷል ፡፡ 1985 . አድሜአቸው 17 ዓመት በታች ለነበረው ለኢትዮጵያ ታደጊ ቡድን አባት እና ልጅ ተመርጠው ነበር፡፡ የበለጠ የሚያስገርመው ቡድኑ ውስጥ በነበረው ቅነሳ ልጅ ተባሮ አባት በቡድኑ ውሰጥ ቀጥሏል፡፡ የዘንድሮው ደግሞ የታዳጊ ሳይሆን የመምህራን ፕሮጀክት ስለሆነ ይሆናል ጩጨው መምህር የገባው፡፡

ምንጭ : ሊብሮ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ዕድገት ዘወትር ቁልቁል የሚነጉደው እንዲህ በድቡሽት ላይ የተገነባ ስለሆነ ነው ::

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ከንቲባ .

ጀማሪ ኮትኳች

Joined: 08 Jan 2010
Posts: 50
Location: Roma

PostPosted: Tue Aug 10, 2010 8:13 pm    Post subject: Reply with quote

ተድልሽ ይመችህ አቦ ዜናዋ በሳቅ ጦሽ ነው ያደረገቺኝ ::
ለመሆኑ የደቡብ አፍሪካው ሯጭ ቀሚስ ነው ተብሎ ተከሶ የነበረው ምን ሆነ ?
የዛሬ ስንት አመት እንደሆነ አላውቅም አርጀንቲና አንደር 21 ውስጥ 6 ዓመት ልጅ ያለው ተጫዋች ተገኝቶ እንደነበር መስማቴ ትዝ ይለኛል የኢትዮጵያው ደሞ ያስቃል አባትና ልጅ ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ !
_________________
Ethiopia tikdem
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Aug 10, 2010 11:08 pm    Post subject: Reply with quote

ከንቲባ . እንደጻፈ(ች)ው:
ተድልሽ ይመችህ አቦ ዜናዋ በሳቅ ጦሽ ነው ያደረገቺኝ ::

እያረርን Evil or Very Mad መሣቅ ነው Laughing ::
Quote:
ለመሆኑ የደቡብ አፍሪካው ሯጭ ቀሚስ ነው ተብሎ ተከሶ የነበረው ምን ሆነ ?

ሴት መሆኗ ተረጋግጦ ውድድር ጀምራለች ::
ምንጭ :-IAAF, Tuesday, 06 July 2010. Caster Semenya may compete
Quote:
የዛሬ ስንት አመት እንደሆነ አላውቅም አርጀንቲና አንደር 21 ውስጥ 6 ዓመት ልጅ ያለው ተጫዋች ተገኝቶ እንደነበር መስማቴ ትዝ ይለኛል የኢትዮጵያው ደሞ ያስቃል አባትና ልጅ ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ !

እኛ እንደ ጥንቱ የሶቪዬት ኮሚኒስት ጋዜጣ አንባቢ ስለ እግር ኳስ ገልብጠን እናነባለን :: አርጀንቲናዎች ደግሞ የልጅ አዋቂዎች ሆነው ኳስን በጨቅላነታቸው ያሽሞነሙኗታል Rolling Eyes ::

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu Aug 19, 2010 7:24 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

የኢትዮጵያ እግር ኳስ የተለመደ ታሪኩን ቀጥሏል ::

Kenya defeats Ethiopia 3-0 in friendly football match

Quote:
Kenya defeats Ethiopia 3-0 in friendly football match

APA-Addis Ababa (Ethiopia) The Kenyan national team defeated the Ethiopian team by 3-0 in a friendly match on Wednesday in Addis Ababa.

The result was a disappointment to Ethiopias sports authorities and supporters.

It is really a shame and discouraging to see such a result and defeat on our own land. It shows that our team is in a difficult situation for the African Cup of Nations qualifiers, said Mekuria Tesema, a football fan in Addis Ababa.

Many supporters are expressing their disappointment with the match during which the team under-performed.

The Kenyan team performed well both in the first and second half of the game. They scored the first goal in the first half and two goals in the second half.

Recently, Ethiopia hired a British coach for the national team who is getting around $8,000 monthly salary.

However, the cost is being covered by an Ethiopian investor who is among the world richest men.

The match was the first match the Ethiopian team, which is under preparations for its future match.

Ethiopia shares a group with Guinea, Nigeria and Madagascar for the African Cup of Nations qualifiers.

The Ethiopian Football Federation was reported to have covered all expenses of the Kenyan team, estimated to be around $ 20,000.

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu Aug 26, 2010 2:00 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን :-

ኢትዮጵያ ውስጥ ፖለቲካው ብቻ ሣይሆን ስፖርቱም በደናቁርት መመራት ከጀመረ ዘመናት ተቆጥረዋል :: በተፈጥሮ በታደሉት ጥንካሬ አትሌቶቻችን በዓለም መድረክ ውጤት ማስመዝገብ ባይችሉ ኖሮ በሁሉም የስፖርት ዓይነቶች በአገር ውስጥ ውድድሮች ብቻ አናብስት ሆነን እንቀር ነበር ::

የእግር ኳስ ስፖርት ከአመሠራረቱ ጀምሮ በሸረኞች የተዋቀረ ስለሆነ ይኼው እስካሁን የአፍሪቃ ውራ ሆነን እንዳክራለን :: ሰሞኑን ከኬንያ ጋር ብሔራዊ ቡድኑ ባደረገው የወዳጅነት ግጥሚያ እንኳን በአገሩ : በሜዳው እና በራሱ ደጋፊ ፊት 3-0 ተሸንፏል :: ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ስፖርት ሥርዬት የሚገኘው አደረጃጀቱ ፕሮፌሽናል : ቡድኖችም ሕዝባዊ ሲሆኑ ብቻ ነው :: ያለበለዚያ በአንድ ቡድን የዘወትር ጋሻ -ጃግሬነት የሚዘወር የሞኖፖሊ ሸቀጥ ሆኖ ይቀጥላል ::

ሌላው አስገራሚ ነገር ደግሞ ለብሔራዊ ቡድኑ አሠልጣኞች የሚከፈለው ደመወዝ ነው :: ቡድኑ በአገር ውስጥ አሠልጣኞች በሚሠለጥንበት ወቅት የአሠልጣኙ ደመወዝ ቢበዛ 5,000 ብር አይበልጥም :: የውጪ አሠልጣኝ ከተቀጠረ ግን ክፍያው በውጪ ምንዛሪ ወይም በከፍተኛ ብር ይሆናል : ውጤታቸው ግን ከአገር ውስጥ አሠልጣኞች የባሠ አሣፋሪ ነው :: ለዋቢነት ያህል በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በቴክኒክ ዳይሬክተርነት እና በአሠልጣኝነት የሚመሩትን ሰዎች የወር ደመወዝ ተመልከቱት ::

የቴክኒክ ዳይሬክተር :- አቶ ዮሐንስ ሳህሌ በትውልድ -ኢትዮጵያዊ : በዜግነት -አሜሪካዊ :: ደሞወዝ በወር ሠላሣ አምስት ሺህ (35,000) ብር ::

አሠልጣኝ :- ኢፊ ኦኑራ በትውልድ -ናይጄሪያዊ : በዜግነት -እንግሊዛዊ :: ደመወዝ በወር አንድ መቶ ሰባ አምስት ሺህ (175,000) ብር ወይም አሥራ ሦሥት ሺህ (13,000) ዶላር ነው ::
ለሁለቱ በአጠቃላይ በወር ሁለት መቶ አሥር ሺህ (210,000) ብር ይከፈላል ::

ነገር ግን ከእነዚህ ሰዎች ተዓምር መጠበቅ አይቻልም : ምክንያቱም የአገሪቱ የእግር ኳስ ስፖርት አደረጃጀት ከጥንቱ አማተሪዝም ፍልሥፍና ባልተላቀቁ ነገር ግን እጅግ በሙስና በተዘፈቁ የመንግሥት ተሻሚዎች የሚመራ በመሆኑ :: በየክለቡ ቋሚ ተሠላፊ ለመሆን ለአሠልጣኞችና ለኮሚቴ አባላት ጉቦ መሥጠት የግድ ነው :: የብሔራዊ ቡድን ተሠላፊ ለመሆን መመዘኛው ከጥንትም ችሎታ ሣይሆን የተወሣሠበ የፌዴሬሽኑ ፖለቲካ ነው :: ታዲያ እኒህ አሠልጣኞች በየወሩ 1 ቢሊዮን ዶላር ደመወዝ እንኳን ቢከፈላቸው በየት አልፈው በእግር ኳስ ስፖርት ችሎታ የሌላቸውን የእግር ኳስ ተጫዋቾች አሠልጥነው ነው ውጤት የሚያመጡት ? "ላም ባልዋለችበት ኩበት ለቀማ ::" ማለት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ስፖርት ነው ::

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
geremew

ኮትኳች

Joined: 28 Dec 2004
Posts: 240
Location: united states

PostPosted: Tue Aug 31, 2010 4:48 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ተድላ ሀይሉ
የጻፍከው ሀሳብ እውነት ለመሆኑ ምንም ጥያቄ የለውም :: ነገር ግን ክፍያውን ማን እንደሚከፍል አብሮ ቢገለጽ የዜናውን ታዐማኒነት ይጨምረዋል እንጂ አይቀንሰውም :: ቴክኒክ ዲሬክተሩ ዮሀንስ ሳህሌ ክፍያም ሆኖ ቅጥር በፊፋ መስፈርት ሲሆን ይህ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ታዳጊ አገሮች የሚውል ሲሆን ትኩረቱን ብሄራዊ ቡድን ላይ ሳይሆን ታዳጊዎች ላይ ነው ::
የአሰልጣኙ ክፍያ ደግሞ በአላሙዲን የሚሸፈን ሲሆን ከበፊቱ የአገራችን አሰልጣኞች ክፍያ ጋር በንጽጽር መቅረቡ አግባብ አይደለም :: ከውጤት አንጻር ግን መመዘኑ እኔም እስማማለሁ :: የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በሱማሌ የተሸነፈው አንድ ጊዜ ነው እሱም ጀርመናዊው አሰልጣኝ ጆሀን ፊገ እና በምክትል አሰልጣኝ አስራት ሀይሌ ጊዜ ነው :: በውጭ አሰልጣኞች ሚስተር ክላውስ ምስራቅ እና መካከለኛውን የአፍሪካ ዋንጫ በሀገራችን የወሰድን ሲሆን ከዛ በሁዋላ ግን ድጋሚ ለማግኘት ብዙ ጊዜ እንደፈጀብን የታወቀ ነው :: ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ግን እስካሁን ያልቻልን ሲሆን ለሀገር ውስጥ አሰልጣኞች ግን ከበቂ በላይ እድል ተሰጥቶዋል ባይ ነኝ :: ለምሳሌ መንግስቱ ወርቁ : ካሳሁን ተካ : አስራት ሀይሌ : ስዩም አባተ : ጌታሁን ገብረጊዎርጊስ : ንጉሴ ገብሬ : ወዘተ :: በክለቦችም ሆነ በብሄራዊ ቡድን ደረጃ ሀገራችንን ለተሻለ ውጤት ስላላበቁ እድሉ ለውጭ አሰልጣኞች መሰጠት የግድ ነው :: ነገር ግን ከውጭ የሚመጣው አሰልጣኝ የተሻለ ውጤት ሊያመጣ ካልቻለ አጠያያቂ ነው :: ነገር ግን ቢያንስ ቢያንስ የአንድ አመት የውድድር ዘመን እድል ሊሰጣችው ይገባል ::

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:

PostPosted: Tue Aug 31, 2010 5:52 pm    Post subject: Reply with quote

geremew እንደጻፈ(ች)ው:

ሰላም "geremew"

ለሠጠኸን ማብራሪያ እና አስተያዬት አመሠግንሃለሁ ::

ሃሣብህን በትክክል ከተረዳሁት ለቴክኒክ ዳይሬክተሩም ሆነ ለአሠልጣኙ የሚከፈለው ገንዘብ በዓለም አቀፍ መሥፈርት መሠረት ሥለሆነ ብዙ አይደለም መሠለኝ የምትለው :: ገንዘብ ብቻውን ውጤት የሚቀይር ቢሆን ኖሮ በቅርቡ በዓለም ዋንጫ ውድድር በሚሊዮን ዶላር ደመወዝ ከፍለው ከውጪ አሠልጣኞችን ቀጥረው የነበሩት የአፍሪቃ ቡድኖች ውጤት እስከምን ድረስ ነበር ? ብዬ እሞግታለሁ ::

ደግሞም ስለአሠልጣኞች ክፍያ ላነሣኸው :- ገንዘቡ ከፌዴሬሽኑም ካዝና ይከፈል ከፊፋ ዕርዳታ ወይም በሼሁ ይሸፈን ዞሮ ዞሮ በኢትዮጵያ ሕዝብ ሥም የሚከፈል ሥለሆነ የአገር እና የሕዝብ ሐብት ነው :: ስለዚህ በሌሉ የእግር ኳስ ተጨዋቾች ሥም ለአሠልጣኝ ተብሎ ገንዘብ መበተን የለበትም :: ሥንት መረዳት ያለበት ደሃ ኢትዮጵያዊ እያለ ለማይሆን ነገር ገንዘብ መባከን አልነበረበትም : የለበትምም :: ነው የእኔ መነሻ ::

የእኔ መሠረታዊ ጥያቄዎች
1 ......... ኢትዮጵያ 85 ሚሊዮን ሕዝብ ኖሯት እንዴት 25 ሚሊዮን የማይሞላ ሕዝብ ካላቸው እንደ -እነ ካሜሩን እና አይቬሪ -ኮስት ወይም ጋና ያነሠ የእግር ኳስ ውጤት ሊኖራት ቻለ ?

2 ........ የአፍሪቃ ቀዳሚ የእግር ኳስ ስፖርት መሥራች ሆነን እያለ ዛሬ ለምን ወደ ኋላ አሽቆለቆልን ? እንዲያውም ይባስ ብሎ በደካማው የምሥራቅ አፍሪቃ ዞን እንኳን ያለን ውጤት የውራዎች ውራ ለምን ሆነ ? ነው ::

የኢትዮጵያን እግር ኳስ ስፖርት እንቅስቃሴ ወደ ዕድገት ለማምጣት ሁለት መሠረታዊ ጉዳዮችን አስቀምጣለሁ :-
1......... የፌዴሬሽኑ አወቃቀር ፕሮፌሽናል መሆን ይኖርበታል :

2......... ክለቦች በሕዝባዊ አደረጃጀት በየሠፈሩ ተዋቅረው በአክሲዮን መልክ በጀታቸውን የሚሸፍኑ እና ሙሉ በሙሉ ከመንግሥት ቁጥጥር ነፃ መሆን ይገባቸዋል ::

3 ......... ክለቦች የግድ በአዳጊ ሕፃናት : በወጣቶች እና በተስፋ ቡድኖች ተጫዋቾችን እንዲያቅፉ ሕግ መደንገግ ይኖርበታል :: የእነዚያ ቡድኖች ውጤት አብሮ ተደምሮ ለዋናው የአዋቂዊች ምድብ ሻምፒዮና ውድድር ውጤት በተወሠነ ፐርሠንት (5 ወይም 10 ወይም ሌላ በሥምምነት የሚደረሥበት ሊሆን ይችላል ) ነጥብ መያዝ ይገባዋል :: እንደዚያ ሲሆን ክለቦች ለታዳጊዎች እና ወጣቶች ትኩረት መሥጠት ይጀምራሉ : ስፖርቱም ይበልጥ ይጎለብታል ::

ይህ ሲሆን ነው በስፖርቱ ውስጥ ጥሩ የውድድር እና የፉክክር ስሜት የሚኖረው :: ያለበለዚያ ምንም ፋይዳ ያለው የእግር ኳስ ውድድር ሣይኖር ከዓመት ዓመት "ሣንጆርጅ ዋንጫዎችን ሁሉ ጠቀለለ ::" የሚሉ ርዕሶችን በየስፖርት ጋዜጦች የፊት ገፆች ላይ ማንበባችን ይቀጥላል ::

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
geremew

ኮትኳች

Joined: 28 Dec 2004
Posts: 240
Location: united states

PostPosted: Tue Aug 31, 2010 6:31 pm    Post subject: Reply with quote

ተድላ
አንተ ባነሳሀቸው የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ ጥያቄ የለኝም :: እንደ አማራጭ ከሚቀርቡት ሀሳቦች መካከል ብዙ ጊዜ የሚነሳ ሀሳብ ስለሆነ :: እኔ ለመናገር የፈለኩትን ሀሳብ ግን እንዳልተረዳህልኝ በመጀመርያው አረፍተ ነገር ላይ ያስተዋልኩት ስለሆነ በድጋሚ ሀሳቤን ግልጽ ላረግ እውዳለሁ ::

የቴክኒክ ዲረክተር ዮሀንስ ሳህሌ በሙያው ብቃት እንዳለው በትምህርት ማስረጃ ማቅረብ የቻለ በተጫዋችነትም ያሳለፈ ብቻ ሳይሆን በአሰልጣኝነት ትምህርት ለቦታው እንደሚመጥን በፊፋ የተረጋገጠ ሲሆን በምንም መስፈርት የፌደረሽኑ ብልሹ አሰራር ተብሎ ሊያስወነጅለው አይችልም :: ለሙያው ብቁ የሚያደርገውን ሁሉ ስላሟላ ማለቴ ነው :: በዚህ ላይ ደሞ ይህ ቴክኒካል ዲረክተር ፊፋ ባይቀጥር ኖሮ እስካሁን እንደነበረው የሚቀጥል ሲሆን ይህ ቅጥር ቢያንስ አንድ ሙከራ (ከዚህ በፊት ያልተደረገ ) ስለሆነ ውጤቱን በትዕግስት መጠበቅ ይኖርብናል :: ያን ጊዜ ብቻ ነው ትክክል ነው ወይንም ስህተት ነው በማለት በእርግጠኛነት መናገር የሚቻለው :: ወጪውን ፊፋ ይከፍላል ሲባል ለቦታው የሚመጥን ሰው ሲኖር ስፖርቱን ለማሳደግ የሚሰጥ እርዳታ እንጂ ለዚህ ቅጥር የሚውለው ክፍያ በሌላ በምንም መልኩ ለሀገራችን ስፖርት እንደማይውል የታወቀ ጉዳይ ነው :: ዮሀንስ ሳህሌ ለቦታው የማይመጥን ሰው ከሆነ ግን ጊዜ ማባከን ስለሆነ እርዳታው ቀርቶብን ሌላ መፍትሄ መሻት የግድ ይኖርብናል :: በኔ እምነት ዮሀንስ ለቦታው የሚመጥን እንደሆነ አስባለሁ ፕሮፈሽናል በሆነ ልምድ ብዙ ያካበተው ነገር ስላለ :: የዚህ ቅጥር አላማ ታዳጊዎች ላይ ትኩረት ማድረጉ ተተኪዎችን በሚገባ ለማዘጋጀት ስለሚያስችል ለሀገራችን ስፖርት ጠቃሚ ነው ::

ለሀገራችን ስልጠና የውጭ አሰልጣኝ ያስፈልጋታል የሚለውን ሀሳብ የምደግፍበት ምክኒያት ለሀገራችን አሰልጣኞች በቂ እድል ስለተሰጠ ብቻ ሳይሆን በሚችሉት አቅም ሁሉ ብዙ እንደሰሩ ነገር ግን ለውጥ ማምጣት ስላልቻሉም ጭምር ነው :: ጋርዚያቶ የሚባለው ፈረንሳዊው አሰልጣኝ ይዞት በነበረው ቡድን ውስጥ የተሻለ ለውጥ ስላየን አዳዲስ ስልጠናዎችን ተጫዋቾቻችን የመቅሰም እድል ስለሚሰጣቸው አስፈላጊ ጉዳይ ነው :: አሁንም ይህ ክፍያ በባለ ሀብት መደገፉ ጥሩ ገጽታው ስለታየኝ ነው ::

እነዚህ ነገሮችን ሳናፈርስ አንተ እና ሌሎች በሚጨምሩት የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ ከተሰራ ውጤት እናመጣለን ብዬ አምናለሁ :: የምናቀርባቸው የመፍትሄ ሀሳቦች የግድ መጠላለፍ አይኖርባቸውን መደጋገፍ እንጂ :: ለሰፊው ችግራችን ብዙ መፍትሄ እንጂ 1 ወይም 2 ብቻ እንደማይበቃ ስለምረዳ የተጀመረው ነገር ይዘን ሌላ እንድንጨምር ለማሳሰብ ነው ::

ሰለ ስፖርት የምትሰጣቸው ሀሳቦች አትሌቲክሱንም ጨምሮ የምከታተል ሲሆን አድናቂህ መሆኔንን በዚህ አጋጣሚ ልገልጽልህ እወዳለሁ ::

ሰላም ሁን ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Aug 31, 2010 7:25 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም "geremew: :-

ሃሣብህን ያልተረዳሁ ከመሥለህ እንደገና ሠፋ አድርጌ ላብራራው ::

ዮሐንስ ሣህሌም ሆነ አኒ -ፊያሬ በሙያቸው ብቃት እንዳላቸው እኔ መሥካሪ መሆን የለብኝም :: እንዲያውም ዮሐንስ በጊዮርጊስ እና ብሔራዊ ቡድን ተሠልፎ ሲጫወት የማውቀው ስፖርተኛ ሲሆን በስፖርቱ መሥክ ገፍቶበት እዚህ ደረጃ ከደረሡት ጥቂት ኢትዮጵያውያን አንዱ በመሆኑ ያኮራናል ::

የእኔ መሠረታዊ ነጥብ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ስፖርት እየቀጨጨ ለመዝለቁ መሠረታዊው ችግር አደረጃጀቱ ነው :: ያንን ሣናስተካክል ከዓለም አንደኛ የሆነውን አሠልጣኝ ቀጥረን ብናመጣም ምንም መሻሻል አይመጣም :: ቤትን በድቡሽት አሸዋ ላይ ገንብቶ እስከመቼ ይዘለቃል ?

አሁንስ ሃሣቤ ግልፅ ሆነልህ ?

ስለአድናቆትህ አመሠግንሃለሁ ::

ተድላ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
geremew

ኮትኳች

Joined: 28 Dec 2004
Posts: 240
Location: united states

PostPosted: Tue Aug 31, 2010 8:49 pm    Post subject: Reply with quote

ሀሳብህን ተረድቻለሁ ብዬ አስባለሁ :: አሁን ፌደሬሽኑ ካደረጋቸው ሁለት ቅጥሮች የበለጠ "መሰረታዊ " ችግር ስላለ እሱ መጀመሪያ ይስተካከል የሚል ሀሳብ ይመስለኛል ::
እኔም መሰረታዊ ከሚለው በስተቀር ባንተ ሀሳብ እስማማለሁ :: ምክኒያቱም እንክዋንስ ውጤታማ ላልሆንበት እግር ኩዋስ ቀርቶ ለአትሌቲክሱም እራሱን በየጊዜው update እያደረገ ልምምዶችን የሚቀያይር አሰልጣኝ ሀገራችን እንደሌላት ሙያተኞች ይገልጻሉ :: ስለ ስልጠና የሚሆን መጽሀፍ ለማበርከት አንዳቸውም እንዳልቻሉ በተጨባጭ የታየ ጉዳይ ነው :: ወደድንም ጠላንም የሀገራችን ስፖርት የሚያድገው ከስር መሰረት ተኮትኩተው በሚያድጉ ታዳጊዎች እስከሆነ ድረስ እነሱን ደሞ ከየሰፈሩ እና ትምህርት ቤቱ በተገቢው የሚያሰለጥኑበትን ማንዋሎች እስካልተዘጋጁ ድረስ ውቴት አይኖረውም ባይ ነኝ :: የዮሀንስ ሳህሌ ሆነ የውጭ አሰልጣኙ ቅጥር ትኩረቱ ይህንን (በኔ እምነት መሰረታዊ የሆነውም የታዳጊዎች ጉዳይ እና አዳዲስ ስልጠናዎችን ) accountability and responsibility ባለው እና በሚወስድ አካል እንዲሰራ መደረጉ ትልቅ ጅምር ነው እላለሁ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
vann

አዲስ

Joined: 18 Apr 2009
Posts: 46

PostPosted: Thu Sep 02, 2010 6:45 am    Post subject: Reply with quote

ተድላ እና ገረመው የጀመራቹት ውይይት ደስ ብላኛለች ...ግን አላነበብኩትም ገና Laughing መሳተፌ አይቀርምና እንዳታቆሙ ! ፌደሬሽን ላይ የሚጻፍ ማንኛውም መጥፎ ነገር ያስደስተኛል ! ያለኝን ለመጨመር ዝግጁነቴን በዚህ አጋጣሚ አሳውቃለው !

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
:

የእኔ መሠረታዊ ጥያቄዎች

1 ......... ኢትዮጵያ 85 ሚሊዮን ሕዝብ ኖሯት እንዴት 25 ሚሊዮን የማይሞላ ሕዝብ ካላቸው እንደ -እነ ካሜሩን እና አይቬሪ -ኮስት ወይም ጋና ያነሠ የእግር ኳስ ውጤት ሊኖራት ቻለ ?

ተድላ

ተድላ ማን ይሙት ......አንድ ካሜሩናዊ ሶስት ተኩል ኢትዮጵያዊ እንደሚወጣው ጠፍቶህ ነው አሁን ?

ለወደፊቱ የኢትዮጵያንና የሌሎች አፍሪካውያንን ህዝብ ብዛት በቁጥር ከማወዳደር ይልቅ በኪሎ ብናወዳድረው ጥሩ መለክያ ይሆናል ::

ውይይታችሁን ቀጥሉ !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ንፍታሌም

ኮትኳች

Joined: 01 Jun 2005
Posts: 250
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Sep 02, 2010 6:49 pm    Post subject: Reply with quote

Quote:
የእኔ መሠረታዊ ጥያቄዎች
1 ......... ኢትዮጵያ 85 ሚሊዮን ሕዝብ ኖሯት እንዴት 25 ሚሊዮን የማይሞላ ሕዝብ ካላቸው እንደ -እነ ካሜሩን እና አይቬሪ -ኮስት ወይም ጋና ያነሠ የእግር ኳስ ውጤት ሊኖራት ቻለ ?

ሰላም ተድላ ይህ መሰረታዊ ጥያቄ ብለህ ያቀረብከው ሀሳብ ራሱ ሌላ ጥያቄ ፈጥሮብኛል

ቻይና 1 ነጥብ 3 ቢልዮን ህዝብ ኖሯት እንዴት 15 ሚልዮን በታች የህዝብ ብዛት ካላቸው ከእነ ኒዘርላንድ ስዊዘርላንድ ..አየር ላንድ ያነሰ የእግር ኳስ ውጤት ሊኖራት ቻለ ?....

የህዝብ ብዛት በብዙ ነገሮች ላይ ያለው አዎንታዊ እና አሉታዊ ሚና እንዳለ ሆኖ ...አንተ ባነሳከው ጉዳይ ላይ ...ለእግር ኳስ ውጤት መገኘት ያንድ አገር የህዝብ ብዛት ሊኖረው የሚችለው ሚና ምንድነው ?......
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8  Next
Page 3 of 8

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia