WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የአፍሪቃ ሕብረት :- ኤርትራ የአርቲፊሻሏ ግዛት ሕልውና ፍፃሜ ?
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 8, 9, 10, 11, 12  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Oct 21, 2011 3:40 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

ዛሬ እዚህ 'ዋርካ ፖለቲካ ' መድረክ ላይ የሚታየው የወያኔዎች ቱማታ እጅግ የሚገርም ነው :: አለቃቸው ለገሠ (መለስ ) የአል -ቃዳፊ የጡት ልጅ እንዳልሆነና 'የመናዊ ነኝ ' ብሎ አል -ቃዳፊን እንዳላሣመነ ሁሉ : ወያኔን እና ሻቢያን እስካፍንጫቸው ሲያስታጥቅ እንዳልነበረ (ለኮሎኔል መንግሥቱ በአንድ ወቅት ብቻ የሠጠውን የወታደራዊ ዕርዳታ እንደ በቀቀን እየደጋገሙ ያነሣሉ ) : አል -ቃዳፊ ኢትዮጵያን አረባዊ አደርጋታለሁ እያለ ሲደነፋ ለገሠ አብሮ ቁጭ ብሎ ሲከድም እንዳልነበረ : ወዘተርፈ : ብቻ ይኼን ሁሉ ወያኔዎች ሽምጥጥ አድርገው ክደው በአል -ቃዳፊ ሞት ምንም እንዳልተጨነቁ ደጋግመው ይለፈልፋሉ :: ነገሩ ግን ወዲህ ነው :- የአል -ቃዳፊ የሕይወቱ የመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ወያኔዎችን ከላይ ከቁንጮው ጀምሮ እጅግ በጣም ረብሿቸዋል :: "እኛን ወያኔዎችንም የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲህ ዋጋችንን ይሠጠን ይሆን ?" የሚል ሥጋት በእያንዳንዱ ወያኔ ጭንቅላት ውስጥ ደጋግማ እየደወለች ነው :: አዎን ወያኔዎች :- በታሪክ በተደጋጋሚ እንደታየው አምባገነኖች ምንጊዜም በሠፈሩት ቁና መሠፈራቸው አይቀርም ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቢተወደድ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 21 Jul 2009
Posts: 1501
Location: Dabra Za`Yet

PostPosted: Fri Oct 21, 2011 1:17 pm    Post subject: Reply with quote

ማበድህን አይተው ዝም ያሉህን ወዳጆችህ ነው የምኮንነው :: ምንድን ነው ከዚህ በታች የቀባጠርከው ? ምክር ቢጤ ልሰጥህ ነበር ግና እብድ ምን ተብሎ ይመከራል ? Question

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:

When we do it right No-one remembers,
When we do it wrong No-one forgets.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Fri Oct 21, 2011 1:31 pm    Post subject: Reply with quote

አይተ ቢትወደድ

ምንም እንኳን አንድን የደነቆረ ወያኔ ይገባዋልና ወደ ሰውነት ይቀየራል በህሊናውም ማሰብ ይጀምራል ብሎ መጠርጠሩ ከንቱ ቢሆንም እንዲህ የተድላን ተአማኒ መረጃን መሰረት ያደረጉ ጽሁፎችን ተከታትለህ ማንበብህ ግን ምናልባት አንድ ቀን በውንብድናና ሀገር ክህደት ከጨቀየ እሳቤ ወጥተህ በእውነተኛ ሰብአዊነትና ኢትዮጵያዊነት ስሜት ማሰብ ልትጀምር ከኛም ከኢትዮጵያ ልጆች ጋር ልትቀላቀል ትችላለህና ጥሩ ነው እየተከታተልህ አንብበው እልሀለሁ :: ችግሩ ወያኔወች ራሳችሁ ቢያክልም ከበሮ እሳቤያችሁ ግን የዶሮ ... ዶንቆሮ ....ተኩላ ቀበሮ ....ነፍሳቶች በረሮ ነገር ናችሁ Razz

ሞንሟናው ነኝ

ቢተወደድ እንደጻፈ(ች)ው:

http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon Nov 21, 2011 11:44 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

ጥንታዊቷ ምሥር (ግብፅ ) ረዥም ታሪኳ የሚያሣየው በአብዛኛው በየዘመኑ በተነሡ የተለያዩ የዓላም ኃያላን ቅኝ ተገዢነት ማሣለፏን ነው :: የምሥርን ሰዎች ግሪኮች : ሮማውያን : ፋርሶች : መሐመዳውያን አረቦች : ቱርኮች እና እንግሊዞች እየተፈራረቁ ገዝተዋቸዋል :: ይህም ሆኖ 1940 መጀመሪያ ጀምሮ የምሥር ሰዎች የራሣቸው የሚሉት ብሔራዊ ማንነት አዳብረው ፖለቲከኞቻቸውም የሌላውንም የዓረብ ሕዝብ የፖለቲካ አቅጣጫ ተላሚ ለመሆን የሚያስችላቸውን አቅም ማዳበር ችለዋል :: ካለፈው ዓመት ጀምሮ በምሥር ምድር የሚታየው ለውጥ ደግሞ 'መጨረሻው ምን ይሆን ?' የሚያሠኝ ነው ::

1942 .. (... ጁላይ 1952) ጀምሮ ምሥር ስትገዛ የኖረቸው በወታደራዊ አምባገነን ገዢዎች ነው :: ዛሬም በሕዝባዊ አብዮት ጄኔራል ሙባረክ ከሥልጣን ቢወገድም የዕድሜ ልክ ታማኝ ወዳጆቹና ጓደኞቹ አነ ማርሻል ታንታዊ በእርሱ እግር ተተክተው ፈላጭ ቆራጭ የምሥር ገዢዎች ሆነዋል :: ሠሞኑን የምሥር ሕዝብ በእኒህ ወታደራዊ አምባገነኖች ላይ ቁጣውን በአደባባይ እየገለፀ ነው :: የዚህ ሕዝባዊ ቁጣ ግፊት ምናልባትም ምሥርን ከሚከተሉት ወደ አንዱ አቅጣጫ ይመራት ይሆናል :-

1 ..... የግብፅ ወታደራዊ ደርግ ይበልጥ ሥልጣኑን የሙጥኝ ብሎ ካሁኑ በከፋ አገዛዝ ለመቀጠል ይወስናል ::

2 ..... አመቺ ጊዜ ሲጠብቁ የኖሩት 'የእስላማዊ ወንድማማቾች ' እንቅስቃሴ በምርጫ ሽፋን ግብፅን አዲስ የከሊፋ እስላማዊ አገዛዝ ግዛት ያደርጓታል ::

3 ..... የምሥር ምድር ሰዎች ለረዥም ዘመናት ልክ በሊባኖስ እንደተከሠተው በማያባራ የእርስ በእርስ ጦርነት ይታመሣሉ ::

እናንተስ ምን ይታያችኋል ?

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Dec 18, 2011 1:02 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

ልክ የዛሬ አንድ ዓመት ታኅሣሥ 8 ቀን 2003 .. (December 17, 2011) ቱኒዚያዊው ሰማዕት ሙሐመድ ቡአዚዝ በአደረገው ታላቅ ምሣሌያዊ ዕርምጃ ለአገሩ ዜጎች ብቻ ሣይሆን ለሺህዎች ዘመናት አንቀላፍተው ለኖሩት አረቦች ከኖሩበት ከባድ የተገዢነት ዕንቅልፍ እንዲነቁ ምክንያት ሆነላቸው :: ከትውልድ አገሩ ቱኒዚያ በተጨማሪ የምሥር (ግብፅ ) እና ሊቢያ ዜጎች ጨካኝ አምባገነን ገዢዎቻቸውን አሠናብተው በአዲስ (ነገር ግን ምንነቱ ባልለየለት ) ሥርዓት ግንባታ ላይ ናቸው :: የየመን ዜጎች አሊ አብደላ ሣላህን ለማስወገድ ቀናት ይቆጥራሉ :: ሶርያውያን ላለፉት 50 ዓመታት እንደመዥገር ከተጣበቀባቸው አምባገነን የቤተሰብ አገዛዝ ለመገላገል የመረረ ፍልሚያ ላይ ናቸው :: የሞሮኮና የዮርዳኖስ ነገሥታት የሕዝባቸውን ቁጣ ለማብረድ መለስተኛ የአገዛዝ ለውጥ ለማድረግ ተገድደዋል :: የባህሬይን ዜጎች አመፅ በጨካኝ የሡልጣኑ ታማኞች ለጊዜው ተዳፍኗል :: 12ኛው ክፍለ ዘመን የሚኖሩት የሣዑዲ ገዢዎች ሕዝብ እንዳያምፅባቸው ሁሉንም ቀዳዳዎች ለመድፈን ከራሣቸው አገር አልፈው በባሕሬይን እና በየመን የውስጥ ፖለቲካ ጣልቃ እስከመግባት ደርሠዋል :: ይህ ሁሉ ሲሆን በጥቁር አፍሪቃ የታየው የሕዝብ መነቃቃት እጅግ አነስተኛ ብቻ ሣይሆን ሌላ ዙር ማደንዘዣ የተወጋን እስክንመስል ድረስ ካለፉት ዓመታት ባነሠ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ላይ ነን :: እኛ ጥቁር አፍሪቃውያን ከያዘን የቀን ዕንቅልፍ የምንነቃው መቼ ይሆን Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes ?

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Jan 29, 2012 9:35 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

የወያኔ አገዛዝ በቻይና ዕርዳታ በቀድሞው የከርቸሌ እሥር ቤት ቅጽር ግቢ ይዞታ አዲሱን የአፍሪቃ አምባገነኖች ጽሕፈት ቤት 200 ሚሊዮንድ ዶላር የቻይና ዕገዛ አሥገንብቷል :: ይህንን ሕንፃ አፍሪቃውያን በራሣቸው ጥረት መገንባት ሲገባቸው ለአዲሷ ቅኝ ገዢ ቻይና ተንበርክከው ታሪካዊ ክህደታቸውን አረጋግጠዋል :: ወያኔ ይባስ ብሎ ለአፍሪቃ አንድነት ድርጀት መመሥረት ታላቅ አስተዋፅዖ ያደረገችውን ኢትዮጵያን በሚያኮስስ መልኩ የኢትዮጵያ ንጉሠ -ነገሥት ለነበሩት ቀዳማዊ ኃይለሥላሤ ሊገነባ የሚገባውን የመታሠቢያ ሐውልት በያኔው የጋና መሪ ክዋሜ ንክሩማህ ሐውልት እንዲተካ አድርጓል :: በእርግጥ ፕሬዘዳንት ክዋሜ ንክሩማህ የአፍሪቃውያንን አንድነት አስፈላጊነት በማያሠልሥ ሁኔታ የሠበከ እና ያስተማረ አፍሪቃዊ መሪ ነበር :: ያንን ሁሉ ግን ለፍሬ ያበቃው በወቅቱ የነበረው የአፄ ኃይለሥላሤ አገዛዝ እንጂ እነ ክዋሜ ንክሩማህ እድሜ ልካቸውን ቢታትሩ እንክዋን የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት አይመሠረትም ነበር :: እንግዲህ ወያኔ እንዲህ ያለ መሠሪ ከኻዲ ነው ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ

Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Sun Jan 29, 2012 10:44 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወንድም ተድላ
እጂግ ይገርማል ...ወያኔ ታሪክና ሃገር አጥፊ ነው :: ምን ያህል ጠባብና ደካማ ፍጥረት እንደሆኑ የምታውቀው እኮ ቢያንስ ይሄ ለነሱም ክብር ነበር ...ለክብር አልፈጠራቸውም ክብርንም አያውቋትም እንጅ :: መሰረቱ የአፍሪካ አንድነት ድርጂት የሆነው ህብረቱ ሲታሰብ ቀዳማዊ ግርማዊ ሃይለስላሴ በሚናቸው ለሌሎቹ ፈር ቀዳጅ በመሆን ቀዳሚና ለአፍሪካዊያንም ግርማ ናቸው :: የወያኔው መለስ ግን ይህንን በጠባብ ብሄርተኝነት ስሌቱ ስለሚያሰላው አይፈልግም ::

ካነሳህው የህብረቱ ህንጻ በቻይና መሰራቱ አሉታዊ አንድምታው ጋር የተያያዘ አንድ አሁን ያነበብሁት ኮመንታሪ አለና ላካፍልህ ::

http://saharareporters.com/article/au-and-tragedy-new-headquarters-chika-ezeanya

The AU And The Tragedy Of A New Headquarters By Chika Ezeanya
Posted: January 28, 2012 - 07:20

Chika Ezeanya
By Chika Ezeanya
On the 28th of January, 2012 African countries will collectively descend to a new low on the global index of state sovereignty, territorial integrity and actual independence of nations. On that day, Chinese President Hu Jintao will be in Addis Ababa, Ethiopia to commission the new $124 Million African Union Headquarters built and donated to the continent by China. Termed Chinas gift to Africa, the edifice was constructed by the China State Construction Engineering Corporation with over 90% Chinese labor.

It is to the discredit of the African Union and therefore, every individual and country within that regional body that in 2012, a building as symbolic as the African Union Headquarters is designed, built and maintained by a foreign country, it does not matter which country.

The ancient and modern history of donation of buildings and structures from one nation to another is filled with intrigues and subterfuges, conquests, diplomatic schemings, espionage and counter espionage, economic manipulations, political statements and dominations. The construction of the Trojan horse by Odysseus and its donation resulted in the Greek conquest of the ancient city of Troy after 10 years of unending skirmish.

In building the Basilica in Rome termed the greatest of all churches of Christendom, contributions from faithfuls were emphasized rather than donations from friendly nations. Even the gift of the Liberty Statue from France to the United States on occasion of the latters independence was a joint effort, whereby over 120,000 Americans led by Joseph Pulitzer contributed funds for the construction of the pedestal in 1885.

In rare glimpse into the matter, the book Architecture of Diplomacy, Jane C. Loeffler reveals the underlying diplomatic maneuverings and political ramifications that defines the construction of American embassies all over the world . The author states that building an embassy requires as much diplomacy as design. Loeffler enumerates factors seriously considered in the construction of an American embassy building and they include World politics, American agendas, Architectural politics, cultural considerations, security and several others.

Common sense dictates that in an era of increasing exploitation of Africas natural resources by foreign powers including China, that the African Union, rather than the apparent submission signified by acceptance of the construction of its headquarters by China, will be an organization advocating for fairness in the relationship that exists between the continent and the global powers.

Should security considerations be included, then the question arises as to how African heads of state and government could hold confidential meetings in a building they have no idea how it was wired. What guarantee do African governments have that every word uttered in the new headquarters in Addis Ababa is not heard in Beijing? What evidence negates the suspicion that all activities in the just completed building are not replayed on a large screen in Beijing as Chinese secret service agents watch?

Culturally, indigenous Bantu culture abhors dependence on others for sustenance. A favorite Swahili proverb of Mwalimu Julius Nyereres is Mgeni siku mbili; siku ya tatu mpe jembe which means treat your guest as a guest for two days; on the third day give him a hoe. Indigenous African tradition largely abhors dependency of any kind. It is frowned upon for a man not to thatch his rooftops well before the rainy season, or to stay back while others are going to the farm, except he is bedridden. Add this to the logic espoused in Archtitecture of Diplomacy, and one reasonably concludes that it is unacceptable for Africans to accept a building from China that will house what should be the landmark of the continents achievements and its aspirations for the future.

Clearly, much indiscretion was exercised by the African Union officials in the acceptance of the offer of a new headquarters from China. The African Union has since deviated from the ideals of its founding fathers when in the 1960s Kwame Nkrumah and other great African leaders sought to establish an organization that would protect the geographical contiguity and territorial integrity of African nations. Emperor Haile Selassie in his historic 1963 speech stated clearly that the Organization was founded because Africa has been reborn as a free continent and Africans have been reborn as free men. The blood that was shed and sufferings that were endured are today Africas advocates for freedom and unity.

Contrary to his predecessors commitment to the continued freedom of the continent from imperial forces, Ethiopian President Meles Zenawi - currently being accused of selling huge swathes of Ethiopian land to foreign countries on a tour of the facility boasted of how he single handedly lobbied Chinese officials to build the new headquarters and how he exempted taxes on all Chinese imported construction materials.

Gleeful at the opportunity for African heads of state to indulge in their lifestyles of conspicuous consumption during meetings and summits, AU Projects Director Fantahun Hailemikael reports that among the several luxuries of the building is a helicopter landing pad so visiting dignitaries will be flown from the airport. Of course the dignitaries will be spared the sight of the slum that much of Addis Ababa is. They will be flown from the airport to the AU building and from there to Sheraton Addis, reportedly the best of its kind around the world.

While the African Union think it has gained from China by moving into its new ultra-modern facility, the reality is that the continent has lost tremendously in all matters worthy of reasonable consideration. The move to reverse the derogatory perception of Africa and Africans by all non-Africans has suffered another major setback. The resultant effect will be the continued political and economic manipulation and domination of the region by the West, and now China, and soon the rest of the non-African world.

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

የወያኔ አገዛዝ በቻይና ዕርዳታ በቀድሞው የከርቸሌ እሥር ቤት ቅጽር ግቢ ይዞታ አዲሱን የአፍሪቃ አምባገነኖች ጽሕፈት ቤት 200 ሚሊዮንድ ዶላር የቻይና ዕገዛ አሥገንብቷል :: ይህንን ሕንፃ አፍሪቃውያን በራሣቸው ጥረት መገንባት ሲገባቸው ለአዲሷ ቅኝ ገዢ ቻይና ተንበርክከው ታሪካዊ ክህደታቸውን አረጋግጠዋል :: ወያኔ ይባስ ብሎ ለአፍሪቃ አንድነት ድርጀት መመሥረት ታላቅ አስተዋፅዖ ያደረገችውን ኢትዮጵያን በሚያኮስስ መልኩ የኢትዮጵያ ንጉሠ -ነገሥት ለነበሩት ቀዳማዊ ኃይለሥላሤ ሊገነባ የሚገባውን የመታሠቢያ ሐውልት በያኔው የጋና መሪ ክዋሜ ንክሩማህ ሐውልት እንዲተካ አድርጓል :: በእርግጥ ፕሬዘዳንት ክዋሜ ንክሩማህ የአፍሪቃውያንን አንድነት አስፈላጊነት በማያሠልሥ ሁኔታ የሠበከ እና ያስተማረ አፍሪቃዊ መሪ ነበር :: ያንን ሁሉ ግን ለፍሬ ያበቃው በወቅቱ የነበረው የአፄ ኃይለሥላሤ አገዛዝ እንጂ እነ ክዋሜ ንክሩማህ እድሜ ልካቸውን ቢታትሩ እንክዋን የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት አይመሠረትም ነበር :: እንግዲህ ወያኔ እንዲህ ያለ መሠሪ ከኻዲ ነው ::

ተድላ

_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Jan 31, 2012 4:50 am    Post subject: Reply with quote

የተሞናሞነው እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ወንድም ተድላ
እጂግ ይገርማል ...ወያኔ ታሪክና ሃገር አጥፊ ነው :: ምን ያህል ጠባብና ደካማ ፍጥረት እንደሆኑ የምታውቀው እኮ ቢያንስ ይሄ ለነሱም ክብር ነበር ...ለክብር አልፈጠራቸውም ክብርንም አያውቋትም እንጅ :: መሰረቱ የአፍሪካ አንድነት ድርጂት የሆነው ህብረቱ ሲታሰብ ቀዳማዊ ግርማዊ ሃይለስላሴ በሚናቸው ለሌሎቹ ፈር ቀዳጅ በመሆን ቀዳሚና ለአፍሪካዊያንም ግርማ ናቸው :: የወያኔው መለስ ግን ይህንን በጠባብ ብሄርተኝነት ስሌቱ ስለሚያሰላው አይፈልግም ::

ወንድሜ :- "ያዳቆነ ሠይጣን ሣያቀስ አይለቅም :" ይባል የለም Exclamation ወያኔዎችም ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ያላቸው ጥላቻ እንደዚያው ነው :: እዚህ ዋርካ መድረክ ላይ ያሠማሯቸው ጥሩምባዎቻቸው የሚጽፉትንም አብረን እያየን ነው Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes 'ቀን የሠጠው ቅል ድንጋይ ይሠብራል :' ይባላልና አሁን ቀናቸው ስለሆነ በጫጉላ ጊዜያቸው ይደሠቱበት :: ለወደፊቱ የእነርሱ ትውልድ ግን ከፍሎ የማይጨርሠውን ዕዳ አሸከሙት እንጂ Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Jan 31, 2012 5:00 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

ከአፍሪቃ አገሮች በወታደራዊ መፈንቅለ -አገዛዝ ወይም የእርስ በእርስ ጦርነት ያልታመሡት ከእጅ ጣት ቁጥር አይበልጡም :- ከምዕራብ አፍሪቃ ሴኔጋል : ከሰሜን አፍሪቃ ሞሮኮ : ከምሥራቅ አፍሪቃ ኬንያ እና ታንዛኒያ : ከደቡባዊ አፍሪቃ ናሚቢያ : ዚምባብዌ : ዛምቢያ : ማላዊ እና ደቡብ አፍሪቃ የማስታውሣቸው አገሮች ናቸው :: የረሣኋቸው ካሉ ጨምሩባቸው ::

ከምዕራብ አፍሪቃ በአንፃራዊ ሠላምና መረጋጋት የምትታወቀዋ ሴኔጋል ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የጃጁት ፕሬዘዳንት አብዱላይ ዋዴ ሥልጣን ላይ ሙጭጭ ከማለት አልፈው ሕገ -መንግሥቱን እንደፈለጉት እያስቀየሩ አገራቸውን ወደማያስፈልግ ብጥብጥ እየመሯት ይገኛሉ :: በተለይ በቅርብ ቀን በሚደረገውን የፕሬዘዳንት ምርጫ ድጋሚ ምርጫ ለማጭበርበር ብለው የፈጠሩት ሕገ -ወጥ ዕርምጃ እርሣቸውን ለሦሥተኛ ጊዜ እንዲወዳደሩ የሚፈቅድ እና ተቀናቃኞቻቸውን ደግሞ በተለያዩ ሠንካላ ምክንያቶች ከውድድር ውጪ የሚያደርግ በመሆኑ በአገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሕዝባዊ አመፅ እንዲቀሠቀሥ የሚያደርግ ሁኔታ ተፈጥሯል ::

እንዲያው ለመሆኑ በጥቁሩ የአፍሪቃ ሕዝብ ክፍል ፀረ -አምባገነኖች አብዮት የሚቀሠቀሠው እነ ለገሠ (መለስ ) ከሚጫወቱበት ምሥራቅ አፍሪቃ ሣይሆን በአንፃራዊ ሁኔታ በሠላም እና መረጋጋት ከኖረችው ሴኔጋል ይሆን Question

አብረን እናያለን ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sat Feb 04, 2012 12:05 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

አዎን ቅዱስ ዳዊት ጥንት 'ኢትዮጵያ ታበፅህ እደዊኅ ሐበ እግዚአብሔር ' እንዳለው ትላንትም ሆነ ዛሬ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች ::

ፕሮፌሠር መሥፍን ወልደማርያም ወያኔ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ : የቀድሞው ከርቸሌ የአሁኑ 'የአፍሪቃ አምባገነኖች ኅብረት ጽሕፈት ቤት ' ቅፅር ግቢ ውስጥ ለቀድሞው የጋና ፕሬዘዳንት ክዋሜ ንክሩማህ ለምን ሐውልት እንዳቆመ : ድርጊቱ ምን አንድምታ እንዳለው : በዚህም ድርጊት ማን እንደተከበረና ማን እንደተዋረደ አብራርተዋል : አንብቡላቸው ::

ምንጭ :- ፕሮፌሠር መሥፍን ወልደማርያም : ፍትህ ጋዜጣ : አርብ ጥር 25 ቀን 2004 .. :: የአፍሪካ ኀብረት ዓለም በቃኝ ገባ ::

Quote:
የዛሬ አርባ ዘጠኝ ዓመት ግድም በአፍሪካ አዳራሽ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (የዛሬው የአፍሪካ ኀብረት ) ሲመሠረት ተመልካች ሆኜ ገብቼ እዚያው አድሬአለሁ፤ የዛሬዎቹ ወጣቶች ያቺን ኢትዮጵያና እነዚያን ኢትዮጵያውያን የሚያውቋቸው አይመስለኝም፤ አንዳንዴ ሳስበው ግምትም ያላቸው አይመስለኝም፤ የነሱ ጥፋት አይደለም፤ ሥርዓት ባለው መንገድ ሥራዬ ብሎ፣ የአገር ጉዳይ ነው ብሎ ያስተላለፈላቸው የለም፤ ዛሬ የንክሩማ ሐውልት በአፍሪካ ኀብረት ግቢ ቆመ የሚል ወሬ ስሰማ ደርግ በአፍሪካ አዳራሽ መግቢያ ላይ የሌኒንን ሐውልት መትከሉን አስታወሰኝ፤ ዛሬ ደግሞ ወያኔ ከማን አንሼ ብሎ የንክሩማን ሐውልት በአፍሪካ ኀብረት ግቢ ውስጥ ተከለ፤ ንክሩማ ትልቅ አፍሪካዊ ነው፤ ነገር ግን ለአገሩም አልበቃም፤ በምንም ዓይነት መንገድ አጼ ኃይለ ሥላሴን አይተካም፤ ኢትዮጵያ ሰው አጥታ ከጋና መበደርዋ ኢትዮጵያ የወረደችበትን አዘቅት ያሳያል፤ እነማን ይዘዋት እንደወረዱም ግልጽ ነው፤ አንድ ሰው ብቻ፣ አጼ ኃይለ ሥላሴ፣ የተዋረዱ እንዳይመስለን፤ የተዋረደችው ኢትዮጵያ ናት፤ እንደተለመደው ጠምዝዘው ጋናን ማጣጣል ወይም የጋናን ክብር መቀነስ አድርገው የሚያቀርቡት ይኖሩ ይሆናሉ፤ የምለው ጋና ከኢትዮጵያ አትቀድምም፤ ንክሩማም ከአጼ ኃይለ ሥላሴ አይቀድምም ነው፤ ንክሩማም ቢኖር በአፍሪካ ኀብረት ጉዳይ ከአጼ ኃይለ ሥላሴ ጋር ለውድድር አይቀርብም ነበር፤ ጋና ነጻ በወጣችበት እለት በዓሉን ለማድመቅ የሄዱት ልዑል ሣህለ ሥላሴና አቶ አበበ ረታ ነበሩ፤ ከተመለሱ በኋላ አቶ አበበ በብሔራዊ ቤተ መጽሐፍት ስለጋና ንግግር አድርገው አዳምጫለሁ፤ ኢትዮጵያኮ በኢጣልያ ወረራ ጊዜም የአርበኞችዋን ነፍስ ይማርና ሰንደቅ ዓላማዋ ሲውለበለብባት የነበረች አገር ናት፤ የአርበኞችዋን ነፍስ ይማር ! ሐውልት ባናሠራላቸውም ሲናቁብን በአርምሞ ልናልፈው አንችልም፡፡

አርበኞችን ወደዳር ማስወጣትና የሥልጣን ወንበሮችን በባንዳዎች ማስያዝ አጼ ኃይለ ሥላሴ የጀመሩት ቢሆንም ለልጅ ልጅ የሚተላለፍ የአገር ውርደት መሆን የለበትም፤ በቅርቡ ሪፖርተር በርእሰ አንቀጹ የሀሳብ ማጠራቀሚያ (ቲንክ ታንክ ) በሚል ርእስ ጽፎ ነበር፤ ከሹሞቹ ውጭ ሰዎች መኖራቸውን፣ የማሰብ ችሎታ ያላቸው መሆኑን፣ ሀሳባቸውን የሚያዳምጥ መኖሩን ካላረጋገጥን ሀሳቦች ዋጋ የላቸውም፤ የንክሩማን ሐውልት በኢትዮጵያ ለመትከል ወይም የሌኒንን ሐውልት በኢትዮጵያ ለመትከል ከአንድ ሰው በቀር አይወስንም፡፡

የአፍሪካ አንድነት የተቋቋመው ... 1963.. ነው፤ በዚያን ጊዜ ኢትዮጵያ በመላው ዓለም ከፍ ያለና የተከበረ ስም ነበራት፤ በአፍሪካ ያለምንም ጥርጥር ቀዳሚዋ አገር ነበረች፤ ኢትዮጵያን ለዚህ ያበቃት ረጅም የነፃነት ታሪክዋ፣ የህዝቡ ጨዋነት፣ የመሪዎቹ፣ በተለይም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ግርማና ሞገስ አንድ ላይ ሆነው ኢትዮጵያን የተከበረችና የተፈራች አገር አድርገዋት ነበር፡፡

ለአፍሪካ ኀብረት የተሰበሰቡት በዘመኑ የነበሩ ታላላቅ መሪዎች፣ አገሮቻቸውን ከቅኝ አገዛዝ ያወጡ ሰዎች ነበሩ፤ መሪዎቹ በየሰፈራቸው የጎረቤቶች ማኅበር እያቋቋሙ ለትልቁ የአፍሪካ አንድነት እምብዛም ግድ አልነበራቸውም፤ ምናልባትም የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በማቋቋም እያንዳንዳቸው በየአገራቸው ያላቸው ሥልጣን የሚቀነስባቸው መስሎአቸው የነበረ ይመስለኛል፤ አብዛኛዎቹ እናጥናው፣ እናብላላው በማለት የድርጅቱን ምሥረታ ለማስተላለፍ በጣም ይጥሩ ነበር፤ አጼ ኃይለ ሥላሴ ግን የድርጅቱ ሰነድ ሳይፈረም ማናችንም ከአዳራሹ አንወጣም ብለው ገትረው ያዙአቸው፡፡

የአጼ ኃይለ ሥላሴ ትልቅነትና የኢትዮጵያ የመንፈስ መሪነት በገሀድ ታየ፤ እንደናስርና እንደቤን ቤላ ያሉ አብዮተኞች ሳይቀሩ ከጃንሆይ ጋር ሲነጋገሩ ጎንበስ ብለውና እጆቻቸውን ወደኋላ አጣምረው ነበር፤ መቼም የዚህ ፊልም አንድ ቦታ ይኖራል ብዬ ተስፋ አለኝ፤ የዛሬ ወጣቶች ሁሉ ሊያዩት የሚገባ ነው፤ እምቢተኞቹንና አፈንጋጮቹን ሁሉ አንድ በአንድ እያነጋገሩ፣ እንደኒዬሬሪና አሚን ተጣልተው የማይነጋገሩትን እያስታረቁ ሰነዱ ሳይፈረም መውጣት የለም አሉ፤ እንደማስታውሰው ሰነዱ ከሌሊቱ በስምንትና በዘጠኝ መሀከል ተፈርሞ አለቀና ሲነጋ በየቤታችን ገባን፡፡

የአፍሪካ አንድነት በጋዳፊ (ነፍሱን ይማረውና ) ውትወታ የአፍሪካ ኀብረት ተባለ፤ ስልቻ ቀልቀሎ፣ ቀልቀሎ ስልቻ ነው፤ ዓላማው የአፍሪካን ሕዝቦች የኑሮ ደረጃ ከፍ ለማድረግ፣ የአፍሪካ አገሮችን ሉዓላዊነትና ነጻነት ለመጠበቅና ከማናቸውም ዓይነት ቅኝ አገዛዝና ቄሣራዊ ተጽእኖ ለመከላከል ነበር፤ ነበር፤ ነበር፤ በአገሮች መሀከል የሚከሰቱ ችግሮችን ሁሉ በሰላማዊ መንገድ መፍትሔ እንዲገኝላቸው ማድረግ ነበር፤ ነበር፤ ነበር፡፡

እንደዚያ ዕለት በኢትዮጵያዊነቴ ኮርቼ አላውቅም፤ ስለዚህም የኢትዮጵያውያን የዩኒቨርስቲ መምህራን ማኀበር ስብሰባ ጠራሁና ያየሁትን ገልጬ ለአጼ ኃይለ ሥላሴ የምስጋና ደብዳቤ እንጻፍላቸው የሚል ሀሳብ አቀረብኩ፤ አንዳንድ ተቃውሞ ተነሥቶ ከተከራከርንበት በኋላ እንዲጻፍላቸው ተወሰነ፤ ዳብዳቤውን ጽፌ ለጃንሆይ እንዲሰጥልን ለዩኒቨርስቲው ፕሬዚደንት ለልጅ ካሣ ወልደማርያም አስረከብሁት፤ ከጥቂት ቀናት በኋላ ጠራኝና አንተው ወስደህ ብትሰጥ ይሻላል አለኝ፤ የምሄድበትን ቀንና ሰዓት ነገረኝ፤ ወስጄ በእጃቸው ሰጠኋቸው፤ እንዳነበቡት ወይም እንደተነበበላቸው ፍልቅልቅ ባለ ደስታቸው ይታይ ነበር፡፡

ዛሬ የአፍሪካ አንድነት (ኀብረት ) በቻይና ቸርነት ፎቅ ተሠርቶለት ዓለም በቃኝ ገባ አሉ፤ የአፍሪካ መሪዎችም እዚያው ተሰበሰቡ፤ አቶ መለስም ለቻይና አስተዋጽኦ ዋጋ ለመክፈል ለማኦትሴ ቱንግ ተማሪ ሐውልት አስተከለ፤ ቀጥሎም የአፍሪካ መሪዎች በምን ምክንያት ወደ አውሮፓ ዓለም -አቀፍ ፍርድ ቤት ይሄዳሉ በማለት አቶ መለስ ተቆጥቶ በዓለም -በቃኝ ፎቅ ውስጥ የአፍሪካ ፍርድ ቤት ማቋቋም እንችላለን የሚል ሀሳብ አቀረበ ተባለ፤ ማን በማን ላይ እንዲፈርድ ይሆን ? የአውሮፓ ዓለም -አቀፍ ፍርድ ቤት የተፈራው ምኑ ነው ? ወይስ የዓለም -አቀፍ ትርጉም ችግር ሆኖ ነው ? መቼም የአፍሪካ ፍርድ ቤት ዓለም -አቀፍ ደረጃ ላይ ይውጣ ማለት…ምን ማለት ይሆን ? የተባበሩት መንግሥታትስ መቼ ነው ተለይቶ ‹‹አፍሪካዊ›› የሚሆነው ?

ለማናቸውም በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ሆነው የሚመለከቱን የኢትዮጵያ አርበኞች ይቅር ይበሉን፤ ለኢትዮጵያም ከሌኒን ያወጣት አምላክ ያውቃል !
ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ገነትናሰሎሞን

ኮትኳች

Joined: 07 Jul 2009
Posts: 245

PostPosted: Sun Feb 05, 2012 8:33 pm    Post subject: Reply with quote

ኢሕአዴግ /ወያኔ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መሥራች መታሰቢያ : አጼ ኃይለስላሴን ትተው ለጋናው መሪ ብቻ መታሰቢያ ማሰራቱ የሚያናድና የሚያቃጥል ቢሆንም : አጼ ኃይለሥላሴ ያገኙት የእጃቸውን ነው :: እርሳቸውም ቢሆን ከጎጠኝነትና ከዘረኝነት የጸዱ ስላልነበሩ ከባድ ኃዘን የለብኝም :: ኃይለስላሴ መዘከረያ ሀውልት የሚገባቸው አርበኛ አልነበሩም :: በሁለት ወይም በሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች :: አንደኛ እርሳቸውስ ቢሆን በጣሊያን ጦርነት ጊዜ ኢትዮጵያውያን አርበኞችን ጥለው የሽሹና : ሁለተኛ ከርሳቸው በፊት ለነበሩት ሁለት ታላላቅ መሪዎች : ማለትም ለአጼ ዩሐንስና አራተኛ እና : ለመይሳው ካሳ ለአጼ ቴዎድሮስ ሀውልት ካለማሰራታቸውም በላይ : እርሳቸውም ግን በጎጠኝነትና በዘረኝነት መንፈስ ለአጼ ምንይልክ ብቻ ለይተው ሀውልት ያቋሙም ጎጠኛ ነበሩ :: እናም እርሳቸው ከአድሎ የነጹ አልነበሩም እና ያገኙት የእጃቸውን ነው ::

የኢትዮጵያን የታሪክ ነገሥታት : በተለይ ደግሞ የቅርቦችን ስንመለከት ማለትም አጼ ዩሐንስን , አጼ ቴዎድሮስን እና አጼ ምንይልክ ሶስቱም የሰሩትም መጥፎና ጥሩ የታሪክ ጎኖች ቢኖራቸውም : እነዚህ ሶስቱም የቅርብ ጊዜ የኢትዮጵያ መሪዎች : ዩሐንስ , ቴዎድሮስና ምንይልክ በእኩል ሀውልት የሚያስፈልጋቸው ሆኖ እያለ : አንዱን ከሶስቱ ለይቶ ሀውልት ማቋም ግን ዘረኝነት እና ጸረ -ኢትዮጵያዊነት ህብረት ነው ::

ኃይለስላሴ እነዚህ ሶስት የኢትዮጵያ መሪዎችን በእኩልነት አይን ያላዩ መሪ ነበሩ :: በተለይ ለአጼ ቴዎድሮስ እና ለጎንደሬው : እስከ አሁን ድረስ የቀጠለ የጥላቻ ዘር : በመሀል ኢትዮጵያውያን የተከሉ ዘረኛ መሪ ነበሩ : ኢትዮጵያን ከጣሊያን የታደጉ ታላላቅ አርበኞች እንደ አሞራው ውብነህ , ደጃዝማች አያሌው ብሩን እና በላይ ዘለቀን በግዞት አስቀምጠው ሌሎችን ባዳውዎች ሥልጣን የሰጡ ናቸው :: እናም ለእርሳቸው ሀውልት ማቋም አይገባቸውም :: ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት ያደረጉት ሚና እውነት ትክክለኛ Pan-African አላማ ኖሮቸው ሳይሆን ለዲፕሎማሲ ፍጆታ ያደረጉት ብቻ ስለነበር ሀውልት አይገባቸውም :: እናም ያገኙት የእጃቸውን እና የዘሩት ነው ::
_________________
PROPONENTS OF THE ETHIOPIAN PATRIOTIC ARM STRUGGLE AGAINST WEYANE !!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
AddisMeraf

ውሃ አጠጪ

Joined: 01 Nov 2009
Posts: 1471

PostPosted: Sun Feb 05, 2012 10:03 pm    Post subject: Reply with quote

ገነትናሰሎሞን እንደጻፈ(ች)ው:
ኢሕአዴግ /ወያኔ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መሥራች መታሰቢያ : አጼ ኃይለስላሴን ትተው ለጋናው መሪ ብቻ መታሰቢያ ማሰራቱ የሚያናድና የሚያቃጥል ቢሆንም : አጼ ኃይለሥላሴ ያገኙት የእጃቸውን ነው :: እርሳቸውም ቢሆን ከጎጠኝነትና ከዘረኝነት የጸዱ ስላልነበሩ ከባድ ኃዘን የለብኝም :: ኃይለስላሴ መዘከረያ ሀውልት የሚገባቸው አርበኛ አልነበሩም :: በሁለት ወይም በሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች :: አንደኛ እርሳቸውስ ቢሆን በጣሊያን ጦርነት ጊዜ ኢትዮጵያውያን አርበኞችን ጥለው የሽሹና : ሁለተኛ ከርሳቸው በፊት ለነበሩት ሁለት ታላላቅ መሪዎች : ማለትም ለአጼ ዩሐንስና አራተኛ እና : ለመይሳው ካሳ ለአጼ ቴዎድሮስ ሀውልት ካለማሰራታቸውም በላይ : እርሳቸውም ግን በጎጠኝነትና በዘረኝነት መንፈስ ለአጼ ምንይልክ ብቻ ለይተው ሀውልት ያቋሙም ጎጠኛ ነበሩ :: እናም እርሳቸው ከአድሎ የነጹ አልነበሩም እና ያገኙት የእጃቸውን ነው ::

የኢትዮጵያን የታሪክ ነገሥታት : በተለይ ደግሞ የቅርቦችን ስንመለከት ማለትም አጼ ዩሐንስን , አጼ ቴዎድሮስን እና አጼ ምንይልክ ሶስቱም የሰሩትም መጥፎና ጥሩ የታሪክ ጎኖች ቢኖራቸውም : እነዚህ ሶስቱም የቅርብ ጊዜ የኢትዮጵያ መሪዎች : ዩሐንስ , ቴዎድሮስና ምንይልክ በእኩል ሀውልት የሚያስፈልጋቸው ሆኖ እያለ : አንዱን ከሶስቱ ለይቶ ሀውልት ማቋም ግን ዘረኝነት እና ጸረ -ኢትዮጵያዊነት ህብረት ነው ::

ኃይለስላሴ እነዚህ ሶስት የኢትዮጵያ መሪዎችን በእኩልነት አይን ያላዩ መሪ ነበሩ :: በተለይ ለአጼ ቴዎድሮስ እና ለጎንደሬው : እስከ አሁን ድረስ የቀጠለ የጥላቻ ዘር : በመሀል ኢትዮጵያውያን የተከሉ ዘረኛ መሪ ነበሩ : ኢትዮጵያን ከጣሊያን የታደጉ ታላላቅ አርበኞች እንደ አሞራው ውብነህ , ደጃዝማች አያሌው ብሩን እና በላይ ዘለቀን በግዞት አስቀምጠው ሌሎችን ባዳውዎች ሥልጣን የሰጡ ናቸው :: እናም ለእርሳቸው ሀውልት ማቋም አይገባቸውም :: ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት ያደረጉት ሚና እውነት ትክክለኛ Pan-African አላማ ኖሮቸው ሳይሆን ለዲፕሎማሲ ፍጆታ ያደረጉት ብቻ ስለነበር ሀውልት አይገባቸውም :: እናም ያገኙት የእጃቸውን እና የዘሩት ነው ::

የአጼ ዮሀንስም ሆነ የአጼ ቴዎድሮስ ሐውልት አለመሰራቱ ጥፋት ነው :: ታሪክዊ ስራቸው አለመዘከሩ ኢትዮጵያን ነው እንጂ ሰዎቹን አይደለም የሚጎዳው :: የሐይለ ሥላሴም ሐውልት በአፍሪካ ሕብረት ጊቢ አለመቆሙ የኢትዮጵያን አስተውጽኦ ነው የሚያኮስሰው :: ጣሊያንን በበረሀና በሸንተረሩ ሆነው የወጉ አርበኞች መታሰቢያም አለመሰራቱ የመጪውን ትውልድ መኩሪያ ታሪክ ጉድጓድ እንደ መቅበር ነው የሚቆጠረው :: የሰዎችን ጥፋት ስንቃወም የትውልድን በጎ ተግባርና ታሪካዊ ስራ አብረን እንዳንጥል እንጠንቀቅ ::
_________________
Remembering Meles Zenawi's Era! >> http://www.youtube.com/watch?v=uK1oi0-8uyQ&feature=youtu.be
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon Feb 06, 2012 2:05 am    Post subject: Reply with quote

ገነትናሰሎሞን እንደጻፈ(ች)ው:
ኢሕአዴግ /ወያኔ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መሥራች መታሰቢያ : አጼ ኃይለስላሴን ትተው ለጋናው መሪ ብቻ መታሰቢያ ማሰራቱ የሚያናድና የሚያቃጥል ቢሆንም : አጼ ኃይለሥላሴ ያገኙት የእጃቸውን ነው :: እርሳቸውም ቢሆን ከጎጠኝነትና ከዘረኝነት የጸዱ ስላልነበሩ ከባድ ኃዘን የለብኝም :: ኃይለስላሴ መዘከረያ ሀውልት የሚገባቸው አርበኛ አልነበሩም :: በሁለት ወይም በሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች :: አንደኛ እርሳቸውስ ቢሆን በጣሊያን ጦርነት ጊዜ ኢትዮጵያውያን አርበኞችን ጥለው የሽሹና : ሁለተኛ ከርሳቸው በፊት ለነበሩት ሁለት ታላላቅ መሪዎች : ማለትም ለአጼ ዩሐንስና አራተኛ እና : ለመይሳው ካሳ ለአጼ ቴዎድሮስ ሀውልት ካለማሰራታቸውም በላይ : እርሳቸውም ግን በጎጠኝነትና በዘረኝነት መንፈስ ለአጼ ምንይልክ ብቻ ለይተው ሀውልት ያቋሙም ጎጠኛ ነበሩ :: እናም እርሳቸው ከአድሎ የነጹ አልነበሩም እና ያገኙት የእጃቸውን ነው ::

አፄ ኃይለሥላሤ የየትኛው ዘር ስለሆኑ የትኛውን ዘር ለይተው ጎዱ ? ውንጀላው ግልፅ አይደለም ::

ገነትናሰለሞን እንደጻፈ(ች)ው:
የኢትዮጵያን የታሪክ ነገሥታት : በተለይ ደግሞ የቅርቦችን ስንመለከት ማለትም አጼ ዩሐንስን , አጼ ቴዎድሮስን እና አጼ ምንይልክ ሶስቱም የሰሩትም መጥፎና ጥሩ የታሪክ ጎኖች ቢኖራቸውም : እነዚህ ሶስቱም የቅርብ ጊዜ የኢትዮጵያ መሪዎች : ዩሐንስ , ቴዎድሮስና ምንይልክ በእኩል ሀውልት የሚያስፈልጋቸው ሆኖ እያለ : አንዱን ከሶስቱ ለይቶ ሀውልት ማቋም ግን ዘረኝነት እና ጸረ -ኢትዮጵያዊነት ህብረት ነው ::

እኒህ ሦሥት ነገሥታት አንዱ በሌላው ላይ ያደረገውን እናውቃለን :: አፄ ዮሐንስ 4 በአፄ ቴዎድሮስ ላይ መሸፈት ብቻ ሣይሆን እንግሊዝን ያህል ጠላት እየመሩ በቴዎድሮስ ላይ ያስዘመቱ ነበሩ :: ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ደግሞ በዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ላይ ሸፍተው ከእንግሊዝ ጋር የትብብር ሥምምነት እስከ ማድረግ ደርሰዋል :: በተጨማሪም ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በአፄ ዮሐንስ 4 ላይ አምጸው ከጣሊያኖች ጋር የሥምምነት ውል የተፈራረሙ ነበሩ :: አንዱ ለሌላው መታሠቢያ ሐውልት ማሣነፅ ይቅርና የቀደሙትን ገዢዎች ንብረትና ዕቁባቶችን ሣይቀር በሙሉ ወርሠው የሚወስዱ ነበሩ :: ስለዚህ ከእነርሱ በኋላ የነገሡት ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሤ ምን የተለየ አዲስ ጥፋት አጠፉ ?

Quote:
ኃይለስላሴ እነዚህ ሶስት የኢትዮጵያ መሪዎችን በእኩልነት አይን ያላዩ መሪ ነበሩ :: በተለይ ለአጼ ቴዎድሮስ እና ለጎንደሬው : እስከ አሁን ድረስ የቀጠለ የጥላቻ ዘር : በመሀል ኢትዮጵያውያን የተከሉ ዘረኛ መሪ ነበሩ : ኢትዮጵያን ከጣሊያን የታደጉ ታላላቅ አርበኞች እንደ አሞራው ውብነህ , ደጃዝማች አያሌው ብሩን እና በላይ ዘለቀን በግዞት አስቀምጠው ሌሎችን ባዳውዎች ሥልጣን የሰጡ ናቸው :: እናም ለእርሳቸው ሀውልት ማቋም አይገባቸውም :: ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት ያደረጉት ሚና እውነት ትክክለኛ Pan-African አላማ ኖሮቸው ሳይሆን ለዲፕሎማሲ ፍጆታ ያደረጉት ብቻ ስለነበር ሀውልት አይገባቸውም :: እናም ያገኙት የእጃቸውን እና የዘሩት ነው ::

ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሤ ሁሉንም የቀድሞ የኢትዮጵያ ገዢዎች በእኩል ካላዩ የእርሣቸው አመለካከት ነበር :: ጥያቄው 'በእርሣቸው የአገዛዝ ዘመን ከአገራቸው አልፈው ለአፍሪቃ አንድነት ድርጅት መመሥረት ላደረጉት አስተዋፆዖ ሐውልት ሊሠራላቸው ይገባ ነበር :' ነው :: በዚህ ቅር የሚሠኝ ሰው አገሩ በአፍሪቃውያን እና በመላው ጥቁር ወገኖቻችን መከበሯን የማይፈልግ ብቻ ነው :: ምንጊዜም ቢሆን ሁለት ሥህተት አንድ ትክክል አይሆንም :: በእኔ አመለካከት ተመራጩ ኃሣብ 'የኢትዮጵያን አርበኞች እንዘክር : ከፍ ከፍ እናድርጋቸው : ሐውልት ብቻ ሣይሆን ለአገራቸው ላደረጉት አስተዋፅዖ ለዘለዓለሙ የሚፀና ተግባር እንፈፅም :' መሆን ነበረበት ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቢተወደድ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 21 Jul 2009
Posts: 1501
Location: Dabra Za`Yet

PostPosted: Mon Feb 06, 2012 5:05 pm    Post subject: Reply with quote

ድሮስ እብድን የሚድግፈው እብድ አይደለን ? በአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽ ናቹህ :: ጤናቹህ እስኪመለስ ጠብቃለሁ ::

የተሞናሞነው እንደጻፈ(ች)ው:
አይተ ቢትወደድ

ምንም እንኳን አንድን የደነቆረ ወያኔ ይገባዋልና ወደ ሰውነት ይቀየራል በህሊናውም ማሰብ ይጀምራል ብሎ መጠርጠሩ ከንቱ ቢሆንም እንዲህ የተድላን ተአማኒ መረጃን መሰረት ያደረጉ ጽሁፎችን ተከታትለህ ማንበብህ ግን ምናልባት አንድ ቀን በውንብድናና ሀገር ክህደት ከጨቀየ እሳቤ ወጥተህ በእውነተኛ ሰብአዊነትና ኢትዮጵያዊነት ስሜት ማሰብ ልትጀምር ከኛም ከኢትዮጵያ ልጆች ጋር ልትቀላቀል ትችላለህና ጥሩ ነው እየተከታተልህ አንብበው እልሀለሁ :: ችግሩ ወያኔወች ራሳችሁ ቢያክልም ከበሮ እሳቤያችሁ ግን የዶሮ ... ዶንቆሮ ....ተኩላ ቀበሮ ....ነፍሳቶች በረሮ ነገር ናችሁ Razz

ሞንሟናው ነኝ

ቢተወደድ እንደጻፈ(ች)ው:
ማበድህን አይተው ዝም ያሉህን ወዳጆችህ ነው የምኮንነው :: ምንድን ነው ከዚህ በታች የቀባጠርከው ? ምክር ቢጤ ልሰጥህ ነበር ግና እብድ ምን ተብሎ ይመከራል ? Question

ተድላ ሀይሉ እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

ዛሬ እዚህ 'ዋርካ ፖለቲካ ' መድረክ ላይ የሚታየው የወያኔዎች ቱማታ እጅግ የሚገርም ነው :: አለቃቸው ለገሠ (መለስ ) የአል -ቃዳፊ የጡት ልጅ እንዳልሆነና 'የመናዊ ነኝ ' ብሎ አል -ቃዳፊን እንዳላሣመነ ሁሉ : ወያኔን እና ሻቢያን እስካፍንጫቸው ሲያስታጥቅ እንዳልነበረ (ለኮሎኔል መንግሥቱ በአንድ ወቅት ብቻ የሠጠውን የወታደራዊ ዕርዳታ እንደ በቀቀን እየደጋገሙ ያነሣሉ ) : አል -ቃዳፊ ኢትዮጵያን አረባዊ አደርጋታለሁ እያለ ሲደነፋ ለገሠ አብሮ ቁጭ ብሎ ሲከድም እንዳልነበረ : ወዘተርፈ : ብቻ ይኼን ሁሉ ወያኔዎች ሽምጥጥ አድርገው ክደው በአል -ቃዳፊ ሞት ምንም እንዳልተጨነቁ ደጋግመው ይለፈልፋሉ :: ነገሩ ግን ወዲህ ነው :- የአል -ቃዳፊ የሕይወቱ የመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ወያኔዎችን ከላይ ከቁንጮው ጀምሮ እጅግ በጣም ረብሿቸዋል :: "እኛን ወያኔዎችንም የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲህ ዋጋችንን ይሠጠን ይሆን ?" የሚል ሥጋት በእያንዳንዱ ወያኔ ጭንቅላት ውስጥ ደጋግማ እየደወለች ነው :: አዎን ወያኔዎች :- በታሪክ በተደጋጋሚ እንደታየው አምባገነኖች ምንጊዜም በሠፈሩት ቁና መሠፈራቸው አይቀርም ::

ተድላ

_________________
When we do it right No-one remembers,
When we do it wrong No-one forgets.
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4451
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Feb 19, 2012 8:58 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

በየዓመቱ ከአፍሪቃ አኅጉር 50 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የውጪ ምንዛሪ በሕገ -ወጥ መንገድ ወደ ቀሪው ዓለም እንደሚሸሽ የቀድሞው የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዘዳንት ታቦ ምቤኪ ገልጸዋል :: ከዚህ ውስጥ ወያኔ 3 ቢሊዮን የማያንሠውን ገንዘብ እንደሚያሸሽ ቀደም ብሎ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ርዕቱነትን የሚከታተለው 'Global Financial Integrity' የሚሠኘው ተቋም ማሣወቁን እናስታውሣለን ::

ምንጭ :- Vanguard, Posted on February 19, 2012. $50bn exported illegally from Africa annually Mbeki.

Quote:
Former South African President, Thabo Mbeki, says an estimated 50 billion dollars is exported from Africa illegally every year.

Mbeki made the statement in Johannesburg at the inauguration of a UN Economic Commission for Africa (UNECA) investigative panel, saying such money could be used to develop the continent.

UNECA constituted the panel, chaired by Mbeki, to investigate illegal financial flow out of the continent.

Mbeki said the loss should be addressed before it undermined Africas development.

Almost 25 billion dollars comes into the continent; that means it loses twice the capital it receives in financial assistance.

The panel will study the flow of money and understand how it is done.

The African continent will expect the panel to provide practical measures to stop the flow, Mbeki said, stressing that it would take a year for the panel to complete its work.

This is a matter of importance to the continent. In the end the investigation should result in action taken by the continent and individual countries.

As a panel, we have no punitive measures. The panel will make proposals to those with punitive power and explain how the flow of money is done, Mbeki said.

He said the panel would provide sufficient information about the different methods of the outflow. These are over-invoicing and under-pricing of exports and money laundering strategies,’’ Mbeki said.(NAN)

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 8, 9, 10, 11, 12  Next
Page 9 of 12

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia