WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የዋርካ ቀድሞ አባላት መሰባሰቢያና መወያያ
Goto page 1, 2, 3 ... 12, 13, 14  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2633
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Tue Feb 15, 2011 3:12 am    Post subject: የዋርካ ቀድሞ አባላት መሰባሰቢያና መወያያ Reply with quote

የመረጃ መረቡ መጎልጎያዬ አናት ላይ ጠቃሚ ብዬ ከደረደርኳቸው ማጣቀሻዎች ውስጥ ዋርካ ኢንዴክስ ምትለዋ አቧራ ወርሷት ስትገላምጠኝ ደንቆል አደረግኳት ....
መስመር ላይ ያሉ ጎብኚዎች ብዛት ሁለት ይልና አንድ የንግሊዝ አንድ ያሜሪካ ባንዲራ ይውለበለባል :: ወደ አደግኩበት ሰፈር ጎራ ልበል ብዬ ወደ ባሕልና ስነ -ጽሑፍ ስገባ ከላይ እስከታች ''ያላነበብካቸው ጽሑፎች አሉ '' በሚል ብርቱካንማ ማሳሰቢያዎች ይጨፍራሉ ... የማላውቃቸው ዋርካዊያን ስም ቢበዙም ጥቂት አብሮ አደግ ዋርካዊያን ስማቸው ይታያል :: ሻይ ቡና የሚለኝ ዋርካዊ ፈልጌ ነበር ግን አላጋኘዉም ::
ሠላም ዋርካዊያን /ያት የኔ ነገር 20 11 በግ ሆንኩኝ አይደል ዝም ብዬ ምቀላቀል ?... የዋርካዊያን ቤተሰባዊ ቅርርብ ድንገት እንዲህ እንደ ጉም በኖ ይጠፋል ብዬ ላንድም ቀን አስቤ አላውቅም ነበር መላመድ መጥፎ ነው ያለው ድምጻዊ ማን ነበር ? ከአራቱም መሃዘን በጣፋጭ ቋንቋችን ልናወራ የጀምበር ብቅ -ጥልቅ ሳይገድበን በዓይን የመተያይ ግድ ሳይኖረን ባንድ ልቦና ባንድ መንፈስ ሁሉን አብረን ስኖሆን ብዙ ደመራዎች ተለኮሱ ... የዛሬዉን አያድርገዉና ድሮ በያመቱ የዋርካ ልደቴን ድልልል አድርጌ በፌሽታታ እደግስ ነበር ዘንድሮ ግን 8ተኛ ዓመቴን መያዜን ያወቅኩት ዛሬ ነው :: እስከቅርብ ጊዜ እኔ ብቻ ጠፋው እንጂ ሁሉም ዋርካዊ እንደጥንቱ ከነለዛው አለ የሚል ደስ የሚል ስሜት ነበረኝ አሁን አሁን ግን አልፎ አልፎ ብቅ ብዬ ማነባቸው አብይ ርዕሶች የአሁኑን ዋርካ ሚኮንኑ እና ብዙዎቹም መጥፋታቸው አንዳንዶቹም ከነጭራሹ ራሳቸዉን የቀነሱ እንዳሉ አስተውላለው :: በርግጥ ከጥቂት እጅግ ምቀራረባቸው ዋርካዊያን /ያት ውጪ ምነው ጠፋህ ምነው ጠፋሽ ? ለመባባል ሌላ የመረብ ቀዳዳ አልተቀያየርንም (የዋርካ ካልቸር አይደለምና )
ዋርካ የራሷ ካልቸር አላት አንተ ማን ነህ እስቲ ፊትህን ልይህ አንቺ ማነሽ እስቲ ፎቶሽን ተባብሎ አጓጉል ውትወታ የለም ሁላችንም አንድ በምናብ የፈጠርነው ዓለም ላይ ውስጣችን ከሳልናቸው ገፀ -ባሕሪያት ጋር እንገናኛለን ... ዕውቀቶች እንቀያየራል ... እንጣላለን ... እየተጣላን እንዋደዳለን ... ስለምንዋደድ እንታረቃለን ... ምክር ተቀብለን ምክር ሰጥተን ለችግሮቻችን መፍትሔ እናገኛለን ... ነፍስያችንን በጥበብ ዓለም ዳግም አሽቀንጥረን ከምናብ ዓለም ወደ ሕልም ዓለም እየተዘዋወርን የእድሜዎቻችንን ቀምበጦች እናለመልማለን ... ባገር ጉዳይ ላይ ባንድ ባንዲራ ሦስት ቀለማት ሆነን እነለያይና ግን አንድ አየር ውስጥ የበቀልን ስልሆንን መልሰን አንድ እንሆናለን ... ዋርካዊ መሆን ይሄ ነበር ...
በእርግጥ ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው ... ለመጥፋትም ... ለመብዛትም .... ለመመለስም ... ጊዜ አለው :: እውነተኛ ዋርካዊ /ዊት ግን አንድ ቀን ዳግም ወደዋርካ እንደሚመለስ ያስባል :: ዛሬ እቺን ርዕስ የከፍትኳት እስቲ እየተንጠባጠብን ተጠፋፋን ከመባባል መች ተመልሰን እንገናኝ መባባያ ይሆን ዘን ብዬ ነው ::
አንድ 15 የጠፉ የድሮ ዋርካዊያን /ያት ስም ዝርዝር ከዚች ጽሑፍ ግርጌ ያነበብኩ ለት እዛች የከሰረች ግሮሰሪዬ ጊቢ ዳስ ጥዬ ነው ምደግሠው ''በድሮ በሬ ያረሰ የለም '' እንዳትሉኝ 'ንጂ

እመለሳለሁ ::

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::

Last edited by ዋናው on Fri Feb 25, 2011 1:36 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ሾተል

ዋና አለቃ

Joined: 13 Jan 2005
Posts: 6867
Location: Vienna-Austria

PostPosted: Tue Feb 15, 2011 3:31 am    Post subject: Reply with quote

እናንተ ዋናው እንደምን አላችሁ ....እኛ እግዚአብሄር ይመስገን ደህና ነን ስንል ከላይ የጻፋችሁት ከዋርካ የመጥፋት ታሪክ እኛን አይመለከትም ስንል ምንም ዋርካ ፍቅርና ስነጽሁፍ ሩም እንብዛም ባንታይም በክብርነታችን ሆነን ብዙ ከብቶችን ዋርካ ፖለቲካ ውስጥ ስላፈራን ከላይ እስከታች እንደ የስራ ሰው የነበረው ቆምጫንባው ከብቶቻችንን ሰንገን ይዘን ይኼው ሌት ተቀን ስንፈጋ ሳይደክመን አለን ::ባላየነውና ባልዋልንበት ባልታገልነውና ባልተዋጋንበት ወያኔ ናችሁ ብለው ከጀግኖቹና ተዋጊዎቹ ጎራ ዶለውን ካላችሁማ ደስ ይለናል እንጂ ምን ገዶን ብለን ይኼው ለጭቁኖቹ የዋርካ ከብቶቻችን ብለን እንዳለን አለን ስንል እንደ ሪፖርት ልናቀርብላችሁ ፈልገን ነው እንጂ በአሁንዋ ሰአት በቭየና የሰአት አቆጣጠር 3:27 ኤም ቢሆንም በሳምንት አንዴ የሚከፈተው ቅንጅት ስዊዝ የፓልቶክ ሩም ውስጥ ሆነን ከተለያዩ አቅጣጫዎች ስለአገራችን የሚወያዩትን ውይይት ለመማርና እውቀት ለመሰብሰብ ብለን በጥሞና እያዳመጥን ነው ::

እናንተ ለምን ጠፋችሁ ብለን ብንጠይቃችሁ ትፈቅዳላችሁ ?ከዋርካ ተጠፍቶ ስለማይጠፋ ስለተመለሳችሁ ደስ ብሎናል ስንል ከሌላ ሳንጠብቅ ሁላችንም ለዋርካ ረጅም እድሜ ያለንን ስንሰጥ የነበረውን በቅጣይ እንለግስ ::እኛም እንማራለን እንማማራለን ::

የኼደ ይኺድ ....ያለ ይኑር ::እኛ ግን የነበርንበትን ቦታ ለማኖር የሚኖር ነገር እናኑር ::

ፍቅረኛ ካላችሁ መልካም የፍቅረኞች ቀን ይሁንላችሁ ::

ሾተል ነን ....የድሮውም ሆነ የአሁኑ ወዳጃችሁ
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
www.shottel.webs.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ደርበው

አዲስ

Joined: 21 Sep 2003
Posts: 19

PostPosted: Tue Feb 15, 2011 6:17 am    Post subject: Reply with quote

ዋርካን ሳውቃት ብዙ ግዜ ሆነኝ :: ሆኖም አንባቢ እንጂ ተሳታፊ የመሆን እድል አላገኛውም :: ድሮ ድሮ ዋርካ በጥበቡዋ አስደምማኛ በፓለቲካዋ አስተምራኛ በፍቅሩዋ ማርካኝ ነበር :: ዛሬ ግን በዘሬ የምትሰድበኝ ባለማወቄ የምትሳለቅብኝ እየመሰለኝ ብቅ ማለቱን ከተውኩት ብዙ ግዜ ሆነኝ :: የድሮ ቆይታዬን ካሳመሩት ሰዋች መሀከል አንደኛው ስለሆንክ ልትመሰገን ይገባሀል ፁሁፎችህን ከሚወዱ ብሎም ከሚያደንቁ ሰዋች መካከል ነኝ ለማንኛውም ብቅ እያልክ አንዳንድ ነገር ሞነጫጭርልን በቀኛ ያውለን ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋኖስ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 16 Nov 2004
Posts: 1570
Location: Mars

PostPosted: Tue Feb 15, 2011 6:16 pm    Post subject: ቅቅ Reply with quote

ሰላም ዉድ ዋርካዉያን /ያት

እኛም አለን ! እንደማለት ! አይዋ የድግሱ ካርድ እንዳያልፈኝ ! ቅቅቅ

መልካም የመልሶ መቋቋም መንፈስ በላያችሁ ይሁን !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
yammi

ኮትኳች

Joined: 28 Jul 2006
Posts: 436

PostPosted: Wed Feb 16, 2011 10:43 am    Post subject: Reply with quote

እኔም አለሁ .......ዋንሽዬ ዋርካ ኮስሞቲክ ሰርጀሪ ማድረጓንም ገና ማየቴ ነው ....ምናልባት ለአዲስ ጅምር መንደርደሪያ ቢሆነን ጥሩ ነበር እኔም እንዳንተ ይቺ አምድ የናፈቁኝን ሁሉ በቅርቡ እንደምታሰባስብ ተስፋ አደርጋለሁ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
sleepless girl

ውሃ አጠጪ

Joined: 19 Feb 2006
Posts: 1457
Location: near u!

PostPosted: Wed Feb 16, 2011 3:52 pm    Post subject: Reply with quote

እሚገርም ነው ......... Crying or Very sad Crying or Very sad Crying or Very sad Crying or Very sad የጻፍከው ሆድ ያባባል ዋንቾ .......!! ግን እኮ አንተም እኮ ከጠፉት ውስጥ አንዱ ነበርክ :: ፋይናሊሊሊ ግን ብቅቅቅቅ ማለትህ ደስ ይላል ....እንዲሁም ዋኖስ , ሾተልና ያሚ እንኳን ተመለሳችሁ :: የዋርካ አዚም እኮ ለጊዜው ነው እንጂ የሚያጠፋው አዙሮ ....አዙሮ ግን የጠፉትን ያመጣል ::
አሁንም ገና ብዙ የቀሩ አሉ :: እነደብዚ ..ሞኒክ ...ትርንጎ .....እህምም ....ዶማው ....ውቃው .....ጉዱካሳ ....
ያባቱልጅ ....ሊስትሮው ...ሙዝ 1...ባልዛክ ....ሬቾ .....የግልነሽ .....ስጥእንግዲህ ....T....
ቤቲ _13...ዲጎኔ ....ወለላዬ ....ጦምኔው .......ኽረ ስንቱ ...... Crying or Very sad Crying or Very sad Crying or Very sad

_________________
Nothing is impossible!!

Last edited by sleepless girl on Thu Feb 17, 2011 6:41 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
password

ኮትኳች

Joined: 04 Apr 2008
Posts: 194
Location: Scandic

PostPosted: Wed Feb 16, 2011 5:08 pm    Post subject: Reply with quote

ስላም ዋናው

ለታላቁ ጥሪ ፈጣን ምላሽ !!!

http://www.youtube.com/watch?v=vdB-8eLEW8g

ፓስ .....
_________________
http://babile.webs.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website AIM Address Report post
ጉዱ ካሳ

ኮትኳች

Joined: 22 Oct 2003
Posts: 431

PostPosted: Wed Feb 16, 2011 6:19 pm    Post subject: Reply with quote

...ሰላም ቤቶች ! ጥሪውን እንደግብጾቹ ለሰልፍ ማዕበል እንደተጠቀሙበት tweeter and Facebook ለእኛም ደርሶን እነሆ በዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ አደባባይ ተገኝተናል ::
እንግዲህ ሌሎቹም አንጋፋ ዋርካዊያውያን ብቅ ብቅ እንደሚሉ እምነቴ ነው :: ቶታአው ብቅ ይል ይሆን ? አይዋ ጌታስ ? ጫልቱ ; ሚኦቴ ; ቸኮሌት ;....ይቀጥላል Smile
_________________
ጉዱሻ
____________________________________
የምንወደውን ብንጠላ የምንጠላውን ብንወድ በራሳችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የባህሪ ለውጥ አመጣን ማለት ነው!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ደጉ

ዋና አለቃ

Joined: 15 Dec 2003
Posts: 5177
Location: afghanistan

PostPosted: Wed Feb 16, 2011 7:05 pm    Post subject: :-) Reply with quote

ዋናው ሰላም ሰላም ..እራስህ ጠፍተህ ሰው ትፈልጋለህ ...?Smile

ጉዱ ካሳ እንደጻፈ(ች)ው:
...ሰላም ቤቶች ! ጥሪውን እንደግብጾቹ ለሰልፍ ማዕበል እንደተጠቀሙበት tweeter and Facebook ለእኛም ደርሶን እነሆ በዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ አደባባይ ተገኝተናል ...

...ጉዱ ይህቺ ጥሩ አባባል ነች .. Very Happy
_________________
" STUPID IS AS STUPID DOES " Very Happy
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger MSN Messenger Report post
T

ኮትኳች

Joined: 11 Aug 2007
Posts: 290

PostPosted: Wed Feb 16, 2011 11:41 pm    Post subject: Reply with quote

sleepless girl እንደጻፈ(ች)ው:
እሚገርም ነው ......... Crying or Very sad Crying or Very sad Crying or Very sad Crying or Very sad የጻፍከው ሆድ ያባባል ዋንቾ .......!! ግን እኮ አንተም እኮ ከጠፉት ውስጥ አንዱ ነበርክ :: ፋይናሊሊሊ ግን ብቅቅቅቅ ማለትህ ደስ ይላል ....እንዲሁም ሾተልና ያሚ እንኳን ተመለሳችሁ :: የዋርካ አዚም እኮ ለጊዜው ነው እንጂ የሚያጠፋው አዙሮ ....አዙሮ ግን የጠፉትን ያመጣል ::
አሁንም ገና ብዙ የቀሩ አሉ :: እነደብዚ ..ሞኒክ ...ትርንጎ .....እህምም ....ዶማው ....ውቃው .....ጉዱካሳ ....
ያባቱልጅ ....ሊስትሮው ...ሙዝ 1...ባልዛክ ....ሬቾ .....የግልነሽ .....ስጥእንግዲህ ....T....
ቤቲ _13...ዲጎኔ ....ወለላዬ ....ጦምኔው .......ኽረ ስንቱ ...... Crying or Very sad Crying or Very sad Crying or Very sad

ስሊፕ ሰላም ነው የኔ አስታዋሽ : የስነጽሁፍ አድባር እነ ዋንቾን ያሚታን ዋኖስን አዙራ ወደዋርካ ካመጣቻቸው ለማንበብ እጄን አውጥቻለሁ ::
_________________
“Love is like the wind, you can't see it but you can feel it."
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዋናው

ዋና አለቃ

Joined: 16 Dec 2003
Posts: 2633
Location: ሕልም ዓለም

PostPosted: Thu Feb 17, 2011 2:03 am    Post subject: Reply with quote

እንዴት ደስ ይላል መቼም በዋርካዊያኖቼ ' አፍሬ አላውቅም ... አንጋፋዎች ሁሉ ስለተመለሳችሁ ደስ ብሎኛል
ብያለው ' ማንም በዋርካ ሚጨክን አንዠት ያለው የለም ባይፅፍም ሁሉም ጎራ ብሎ አድባሩን ሳይሳልም ሚያልፍ የለም ...
ሳስበው የጎደለን አንድ ነገር ነው ...
ፍቅር ? ..... አይ .... እሱማ አለን በጣም ፍቅር አለን
መተሳሰብ ...... እሱንም አጥተን አናውቅም ....
የጎደለን መሰባሰብ ብቻ ነው ለዚህ ደግሞ የነጠፉ ብሕሮች ተጠያቂ ናቸው ....
ሾተል .... እንዴት ነህ ? አንተ እውነትም አልጠፋህም የዛፎችህ ቅጠሎች ከምኔው እንዲህ በረከቱ ጃል .... እንኳን ብቻ ኖርክልን ይሄው ስላለህ ስላልጠፋህ አይደል የተገናኘነው

ደርበው ...... ተስፋ አለን ወንድሜ ዋርካ ለዛዋ ይመለሳል ቢያንስ ለማንበቡ እንኳን አትጥፋ

አይዋ ..... አንተ 'ንኳን የጎሪጥም መድብልህን ሚያስተዳድር ጎበዝ ብሕረኛ አግኝተሀል የኛዎቹ ናቸው 'ንጂ ጓሮ የቶዶሉ ... እስቲ ለመልሶ መቋቋሙ ማሟሻ ይሆን ዘንድ ስንኞች ሾርብልን ... ከቅኔ ቤትህ የቋንቋ አዝመራ ...

ያሚታዬ .... እንኳን ተመለስሽ ያቺ ካኪ መልክ ያላት ማስታወሻሽ የወፈረ የብሕር ምራቅ ከብዷት የሰሚ ያለ ስትል ያየዋት መሰለኝ ኸረ ዘመንኛ ሁኚና በኪቦርድ ግልብጪያት ተይ ....

ስሊፕዬ .... ብጠፋ መች ፈለግሽኝ ይሄው በመፈለጉ ቀደምኩሽ አይደል እስቲ አትጥፊ አንቺም ያቺ ሁለገብ አምድሽን ፈላልገሽ ከሳሎን አኑሪያት

ጉድሽ .... እንኳን ደህና መጣህ ... ቆይ ግን እኔ አንተን ፍለጋ ቡራዩ ልሂድ ወይስ ቄራ ...? አሃ ... ለነገሩ ውቅሽ አሣ አጥማጅ እንደሆንክ ነግሮኛል

ድጉሻ ... እንዴት ነህ እስቲ ዋርካ ውጥ ባን ጅምበር ተወልደን ለልደታችን እንኳን አታፈላልገንም ... ይሄው ዓይኔን በጨው አጥቤ እንደጥጋበኛ ውሽማ ሲመቸኝ ብቅ አልኩ ...

Tጂዬ እንዴት ነሽ ? ምነው ከማንበብ ወደ ፀሐፊነት ተሸጋግረሽ የለን '....

ፓስ ... እንዴት ነህ ወንድሜ ... እጅህን ቆጥሪያለሁ ላፋጣኙ ምላሽ ምስጋና ይግባህ
እስቲ ሌሎቻችሁም ብቅ በሉ ማሪያምን እንዳታሳፍሩኝ

_________________
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
recho

ዋና አለቃ

Joined: 20 Sep 2004
Posts: 3000
Location: Earth

PostPosted: Thu Feb 17, 2011 6:00 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም

የድሮ አባል በጽሁፍ ብዛት ወይንስ በተመዘገብንበት አመት ? እንግዲህ ካንዱ ከተመደብኩ አለሁ ... ዋርካ ለቀብርዋ ሳልጠራ አንዴ እንተያይ ካላቹ እንግዲህ ምን ይደረጋል Smile

ዋናው ሰላም ብያለሁ ... Smile
_________________
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ማህቡብ

ኮትኳች

Joined: 18 Aug 2005
Posts: 253

PostPosted: Thu Feb 17, 2011 6:35 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችሑም :- 'ዋናው ' ከረጅም ጊዜ በኋላ ስላየሁህ ደስተኛ ነኝ ::
_________________
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የግልነስ

ዋና ኮትኳች

Joined: 03 Feb 2005
Posts: 783
Location: united states

PostPosted: Thu Feb 17, 2011 3:11 pm    Post subject: Reply with quote

ስላም ስላም ዋንቾዩ እንዴት ነህልኝ ብሮ ሁሉም አማን ስላም Question
ይህው ብቅ ብለናል እንግዲህ ከድሮዎቹ .........

ስሊፕዩ እንዴት ነሽ ቆንጆ አስታውስሽ ስላነሳሽኝ አመስግናለው ቆንጆ .... አንተ ጉድሽካ ደህና ነህ ግን ?? በሉ እንግዲህ በነካ እጃቸው እነ ጌታ , ፓኑየፈረሱ ጌታ እነ ኤሮን ......ጎትታቸው አምጡልና ... ባለሱቅን እንኳዋን እኔ ልከዋለው ቅቅቅቅቅቅቅ ደቢዚንም ሞኒካንም አንዴ ባፍዋጨ ከቸ ይላሉ በሉ እንግዲህ የዋንቾን ቤት ሞቅ ደመቅ ሽብ እረብ እናድርገለትት ማይ ጋድድድ የማይረሳውን ውቅሽሽሽሽሽንን ቶሉ ከቸ አርጉልኝ በባትሪም ቢሆን ፈልጋቸውውውውውውውው ........................

ስላም ዋሉ
የግልልል
ከራስብሩዎቸ ስፈርርር
_________________
ADOLA INTERNATIONAL CHILDREN'S FUND
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ባብ

ኮትኳች

Joined: 23 Mar 2005
Posts: 139
Location: united states

PostPosted: Thu Feb 17, 2011 5:25 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ዋናው ......የቀድሞ አባላት በሚለው ካታጎሪ መመደቤን እርግጠኛ ባልሆንም ለማንኛውም ፌጦ መድሀኒት ነው እንዲሉ ይሄው አለሁ ብያለሁ !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2, 3 ... 12, 13, 14  Next
Page 1 of 14

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia