View previous topic :: View next topic
Author
Message
ናፖሊዮን ዳኘ Joined: 18 Apr 2008 Posts: 1874
Posted: Sun Dec 11, 2011 4:44 pm Post subject: ንቃተ ህሊና
ለፖለቲካ ትግል እጂግ በጣም ወሳኝ ነገር ነው ::
በየትኛውም ሀገር ውስጥ ለውጥ ናፋቂ አና አብዮተኛ ተብሎ የሚታሰበው የህብረተሰብ ክፍል ወጣቱ ነው :: ባለንበት ክፍለ ዘመን ደረጃው ይለያይ እንጂ የተለያዮ ሀገሮች ህዝቦች በእጂ አዙር የባርነት ቀንበር (ባርነት የሚለውን ከነፃነት ትርጉም ጋር -ዘመንንም ጭምር ግምት ውስጥ በማስገባት ልናንጸባርቅበት እና ልንተነትነው የሚገባ ነው ) እንደወደቁ ግልጽ ነው ::
የእኛን ሀገር ታሪክ ለየት የሚያደርገው ከህወሀት ወደ ስልጣን መምጣት በፊት እንደ ሀገር በባርነት ቀንበር ስር ወድቀን የማናውቅ መሆናችን ነው :: (በአምስቱ አመትም የጥሊያን ወረራ ጊዜ ባርነትን አምኖ እንዳልተቀበለ በማሰብ ነው በዚህ መልኩ አሰርት ያደረኩት :
አብዮተኛ እና ለነጻነት ይሞታል ተብሎ የሚታሰበው የህብረተሰብ ክፍል ---ወጣቱ ማለቴ ነው ---ህወሀት የፈጠረውን አይነት የረቀቀ ባርነት ዝምታ በሚባል አይነት ሁኔታ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ በግዴለሽነት የሚያይበት ምክንያት ከንቃተ ህሊና ጋር የተያያዘ ነው ብየ አምናለሁ :: ጉዳዮ ዝምታ አይደለም ፍርሀት ነው ብንል እንኳን ራሱ ---እሱም ከንቃተ ህሊና ጋር የተያያዘ ነገር ነው ::
የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህዝብን የማነቃቃት እና የማደራጀት ስራ ሳስበው --- አለት ላይ ምርጥ ዘር ለመዝራት እንደሚታገል ሰው ያለ በዋል ፈሰስ አይነት ስራ ሆኖ ይሰማኛል :: ትልቁ ችግር የኢትዮጵያ ወጣት በህወሀት መንግስት መሰሪ ፖለቲካ እና በውጭ ተጸዕኖዎችም ምክንያት ንቃተ ህሊናውን አጥቷል ::
እነዚህን ነገሮች በጥልቀት እና በዝርዝር ልንወያይባቸው ይገባል :: ለኢትዮጵያውያን (ህወሀቶችን እና የህወሀት ደጋፊዎችን አይመለከትም ) ወገኖች የማቀርበው ጥያቄ ይሄንን ነገር አንድ ባንድ እያነሳን በጥልቀት እንድንወያይበት ነው ::
ከታላቅ አክብሮት ጋር
ናፖሊዮን ዳኘ :: _________________ ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ናፖሊዮን ዳኘ Joined: 18 Apr 2008 Posts: 1874
Posted: Mon Dec 12, 2011 11:57 pm Post subject:
ምናልባት ላስተላልፍ የሞከርኩት ነገር ግልጽ አልሆነ ይሆናል እንጂ ይሄ ጉዳይ በአጽኖት ውይይት ቢደረግበት በወጣቱ ዘንድ ሊፈጥር የሚችለው ቁርጠኝነት በዋዛ መታየት ያለበት ነገር አይደለም ::
የበለጠ ግልጽ ለመሆን ያህል ይሄንን ጉድይ እንዳነሳ የተገደድኩብት ምክንያት በእኛ በፊት የነበሩትን ኢትዮጵያውያን ለትግል እና ለነጻነት የነበራቸውን ተነሳሽነት እና ቁርጠኝነት ግምት ውስጥ በማስገባት ነው :: በጨረስነው እንኳን ክፍለ ዘመን - ከኢጣሊና ወራሪ ጋር የተፋለሙትን ኢትዮጵያውያን እና ከሀገር ውስጥ ፖለቲካም ጋር ተያይዞ ከ 1960ው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በኍላ የነበረው የፖለቲካ ቁርተኝነት እና የትግል መንፈስ - አሁን ካለው ትውልድ ጋር ሲተያይ የሰማይ እና የምድር ያህል ሆኖ ስለተሰማኝ ነው ::
ምንም እንኳን የፖለቲካ ስልጣን በመያዝ ረገድ ባይሳካላቸውም የኢሀፓ እና የመኢሶን ትውልድ ይባል የነበረው እንኳን የነበራቸውን ቁርጠኝነት ( ""የትግሉ ነው ህይወቴ "') አሁን ካለው ትውልድ ጋር የሚገናኝ መስሎ ስላልተሰማኝ ነው ::
ልዮነቱ በብዙ መልክ ሊተነተን ይችላል :: ነገር ግን ማህበራዊ ንቃተ ህሊና እና ለህይወት ያለን አመለካከት ልዮነቱን ለመተንተን የበለጠ ጠቃሚ ናቸው ብየ አስባለሁ :: በአንድ በኩል ቁርጠኝነት ከንቃተ ህሊና ማደግ ጋር ተያይዞ የሚመጣ እንደሆነ ሳምን በሌላ በኩል ደሞ ንቃተ ህሊናን ለማጥፋት የሚወሰዱ ፖለቲካዊ የማይመስሉ ፖለቲካው ርምጃዎች ( በገዚዥው የህወሀት ፓርቲ ) እና የለየላቸው የፖለቲካ የሚባሉም የማስፈራሪያ ርምጃዎች ወጣቱን የህብረተሰብ ክፍል ማህበራዊ ንቃተ ህሊናን ሊቀሙ ወደሚችሉ ማህበራዊ ልምዶች እና አኗኗሮች እንደሚወስዱት እሙን ነው :: በኢትዮጵያም የታየው ይኼው ነው :: ከዚህ ውጪ ደሞ ""ዘመናዊነት "" የሚባለው ኢንተርፕራይዝ ራሱ የፈጠረው ጫና አለ ::
በነዚህ ባነሳኍቸው ነገሮች ዙርያ ያሉ ሁኔታዎችን በማንሳት ብንወያይባቸው አሁንም ደስ ይለኛል :: ከእያንዳንዱ ሁኔታ መልስ ባይገኝ እንኳን መጠየቁ በራሱ ወሳኝ እንደሆነ ስለማምን ነው :: ለዛሬው ከግራምስቺ የእስር ቤት ደብዳቤዎች ስለ እምነት (የፖለቲካ ) ክብርነት ያንጸባረቃቸውን ሀሳቦች ላካፍል :
“… some call me satanic, some saintly, but I have no intention of appearing a martyr or a hero. I think of myself as an ordinary man who refuses to barter his deep convictions for anything in the world” Gramsci- i p.102
In a letter to his mother Gramsci wrote:
“… I am presently under political arrest and will be a political prisoner. I am not ashamed of this fact. Basically, I myself willed this arrest and condemnation. I’ ve always refused to compromise my ideas and am ready to die for them, not just be put in prison.” (p. 133)
ናፖሊዮን ዳኘ :: _________________ ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ናፖሊዮን ዳኘ Joined: 18 Apr 2008 Posts: 1874
Posted: Thu Dec 15, 2011 10:25 pm Post subject:
ንቃተ ህሊና ማለት ይሄ ነው
http://www.youtube.com/watch?v=ohlDR1SvksQ&feature=share
የክብሮሞች ትጋት
ጥቁሩን ነጭ ለማለት
ስለ ህዳሴ ...ስለ ብሄር ብሄረሰቦች ነጻነት
እምብርት እስኪበጠስ እየበሉ ተጎልተው 'ሚጽፉት
በህገ -መንግስት ስላፈረሱት
አዲስ ኢትዮጵያዊነት
ክሽን አድርጎ ጽፎታል ልጁ ! ጎበዝ ልጂ ::
ስለኛም ነጻነት
ስለ ዘመናዊ ባርነት
...ውስጥ ስለጠቆረበት
ንቃተ ህሊና ማለት ይሄ ነው ! ከውስጥም ከውጭም ያለውን ነገር በጥሞና መመርመር ::
ናፖሊዮን ዳኘ :: _________________ ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ጥልቁ 1 Joined: 27 Jan 2004 Posts: 1560 Location: bhutan
Posted: Thu Dec 15, 2011 11:03 pm Post subject:
ወንድም ናፖሊዮን፡ ያነሳኸው አጀንዳ እጅግ ጥልቅና ብዙ ሊያወያይ የሚችል ነው። ከብዙ አቅጣጫዎችም መታየት የሚችል። ነገር ግን ፣ አጀንዳው ጠበብ ማለት ካልቻለ ስለምን ምን ማለት እንድሚቻል አስቸጋሪ ነው። ለምሳሌ በነጥብ ደረጃ ለመወያየት…
1) አሁን ያለው የወጣቱ ንቃተ -ህሊና ምን ይመስላል ?
2) የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጽንሰ -ሃሳብ እና የመሪዎቻቸው ንቃተ -ህሊና ይህን ትውልድ ይመጥናል ወይ ?
3) የለውጥ ሁሉ ባለቤት የሆነው ወጣት የሆዱን በሆዱ ይዞ የሚገዛበት ምክንያት ምን ይሆን ?
4) ንቃተ ህሊናን የማዳበር እና ትውልድ የማነጽ ሃቅም ያለው የኪነጥበብ ሰው ምን እያደረገ ነው ?
እነዚህን እና የመሳሰሉትን አንስቶ መወያየት ይቻላል…
በርታ…
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
*ፍቅር * Joined: 27 Apr 2011 Posts: 42 Location: usa
Posted: Fri Dec 16, 2011 1:52 am Post subject: Re: ንቃተ ህሊና
ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው : ለፖለቲካ ትግል እጂግ በጣም ወሳኝ ነገር ነው ::
በየትኛውም ሀገር ውስጥ ለውጥ ናፋቂ አና አብዮተኛ ተብሎ የሚታሰበው የህብረተሰብ ክፍል ወጣቱ ነው :: ባለንበት ክፍለ ዘመን ደረጃው ይለያይ እንጂ የተለያዮ ሀገሮች ህዝቦች በእጂ አዙር የባርነት ቀንበር (ባርነት የሚለውን ከነፃነት ትርጉም ጋር -ዘመንንም ጭምር ግምት ውስጥ በማስገባት ልናንጸባርቅበት እና ልንተነትነው የሚገባ ነው ) እንደወደቁ ግልጽ ነው ::
የእኛን ሀገር ታሪክ ለየት የሚያደርገው ከህወሀት ወደ ስልጣን መምጣት በፊት እንደ ሀገር በባርነት ቀንበር ስር ወድቀን የማናውቅ መሆናችን ነው :: (በአምስቱ አመትም የጥሊያን ወረራ ጊዜ ባርነትን አምኖ እንዳልተቀበለ በማሰብ ነው በዚህ መልኩ አሰርት ያደረኩት :
አብዮተኛ እና ለነጻነት ይሞታል ተብሎ የሚታሰበው የህብረተሰብ ክፍል ---ወጣቱ ማለቴ ነው ---ህወሀት የፈጠረውን አይነት የረቀቀ ባርነት ዝምታ በሚባል አይነት ሁኔታ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ በግዴለሽነት የሚያይበት ምክንያት ከንቃተ ህሊና ጋር የተያያዘ ነው ብየ አምናለሁ :: ጉዳዮ ዝምታ አይደለም ፍርሀት ነው ብንል እንኳን ራሱ ---እሱም ከንቃተ ህሊና ጋር የተያያዘ ነገር ነው ::
የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህዝብን የማነቃቃት እና የማደራጀት ስራ ሳስበው --- አለት ላይ ምርጥ ዘር ለመዝራት እንደሚታገል ሰው ያለ በዋል ፈሰስ አይነት ስራ ሆኖ ይሰማኛል :: ትልቁ ችግር የኢትዮጵያ ወጣት በህወሀት መንግስት መሰሪ ፖለቲካ እና በውጭ ተጸዕኖዎችም ምክንያት ንቃተ ህሊናውን አጥቷል ::
እነዚህን ነገሮች በጥልቀት እና በዝርዝር ልንወያይባቸው ይገባል :: ለኢትዮጵያውያን (ህወሀቶችን እና የህወሀት ደጋፊዎችን አይመለከትም ) ወገኖች የማቀርበው ጥያቄ ይሄንን ነገር አንድ ባንድ እያነሳን በጥልቀት እንድንወያይበት ነው ::
ከታላቅ አክብሮት ጋር
ናፖሊዮን ዳኘ ::
ሥላም ናፖና ጥልቈ
እኔ የአማርኛ ችግር እዳለብኝ እድትገነዘቡልኝ እወዳለሁ ::
እደ አንድ ኢትዪጵዊ ዜጋ የሀገሬ ጉዳይ የሚያሳስበኝ 25 ዓመት ልጅ ወጣት ነኝ ::
እኔ የተቋሚ ፖለቲኞች (ሆዳሞች ) እዴት እደማያቸው ልግለጸላችህ ::
1 ሆዳምች ::
2 አደር ባዬች ::
3 አላማ የለላቸው ::
4 በጥቅም የሚገዙ ::
5 ለትውልድ የማያስቡ ::
6 መቻቻል የማይቸሉ ::
7 በደም መፈስ የሚያስቡ ::
8 ዘረኞች ::
9 ቂመኞች ::
እኒህ ናቸው የኛ ፖለቲከኞች ::
እሄን የመሰለ ቆሻሻ አስተሳሰብ ይዘው የኔው ትውልድ እዲከተላቸው የሚፈልጉት ??
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
እቴጌይት Joined: 23 Sep 2007 Posts: 546
Posted: Fri Dec 16, 2011 3:45 am Post subject: Re: ንቃተ ህሊና
ናፖሊዮን ዳኘ እንደጻፈ(ች)ው :
---ህወሀት የፈጠረውን አይነት የረቀቀ ባርነት ዝምታ በሚባል አይነት ሁኔታ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ በግዴለሽነት የሚያይበት ምክንያት ከንቃተ ህሊና ጋር የተያያዘ ነው ብየ አምናለሁ :: ጉዳዮ ዝምታ አይደለም ፍርሀት ነው ብንል እንኳን ራሱ ---እሱም ከንቃተ ህሊና ጋር የተያያዘ ነገር ነው ::
የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህዝብን የማነቃቃት እና የማደራጀት ስራ ሳስበው --- አለት ላይ ምርጥ ዘር ለመዝራት እንደሚታገል ሰው ያለ በዋል ፈሰስ አይነት ስራ ሆኖ ይሰማኛል ::
ሠላም ናፖሊዮን
በጣም መሠረታዊ የሆነ ጥያቄ ነው ያነሳኸው :: እዚህ ላይ ከዚህ በፊት በሀገራችን ለውጥ እንዳይተገብር ትልቅ እንቅፋት ከሆኑ ምክንያቶች ዋነኛው የሕዝባችን ለመስዋዕትነት ዝግጁ አለመሆን እና የንቃተ ሕሊና ጉድለት ነው የሚል መልዕክት ያለው ጽሑፍ ሳቀርብ .....'ሕዝብ አይወቀሰም ....መሪ አጣ እንጂ የሚጠበቅበትን መስዋዕትነት ከፍሏል ' ብለህ በሰፊው ተከራክረኸኝ ነበር :: በሂደት የእኔ ድምዳሜ ላይ መድረስህ መልካም ነው ::
በተረፈ ለዚህ ለባርነት 'ሰላም ' ተገዢ የመሆን የፍርሀት ድባብ እና የንቃተ ሕሊናው ጉድለት ከምን የመጣ ነው የሚለው ጥያቄ እጅግ መሠረታዊና አስፈላጊ ጥያቄ ነው :: ለዛም በቂ መልስ መስጠት ስንችል ነው የለውጥ ትግሉ ያለበትን ቦታ ... የሚቀረውን ጉዞና ስራ በትክክል መረዳት የምንችለው :: እዚህ ጥያቄ ዙርያ ያሉኝን ሀሳቦች ይዤ እመለሳለሁ ::
እስከዛው በሠላም ቆይ ::
ፍቅር :-
እዚህ አምድ ላይ ስለተቃዋሚ ፖለቲከኞች አልመሰለኝም ውይይቱ :: ጥያቄው ስለንቃተ ሕሊና ጉድለት እና ስለመስዋዕትነት (ፍራቻ ) ነው :: በግል ሕይወታቸው በእስርና በእንግልት ትልቅ መስዋዕትነት የከፈሉትን ጨምሮ ሁሉን ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን በጅምላ ለመስደብ ምናልባት የወያኔ ሬዲዮና ቲቪ በቂ ይመስለኛል !!
መልካም ቆይታ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
የዘመኑ ልሳን Joined: 07 Jun 2005 Posts: 2930 Location: USA
Posted: Fri Dec 16, 2011 5:36 am Post subject: Re: ንቃተ ህሊና
ንቃተ ህሊና ስንል ምን ማለታችን ነው የሚለውን በግልጽ ማስቀመጥ ያስፈልጋል :: እኛ እንደምናስበው ካላሰበ ንቃተ ህሊና የለውም እምንል ከሆነ የእኛን ባዶነት የሚያሳይ ይመስለኛል ::
አንዳንዶቻችን ሕዝቡ የወያኔ መንግስትን ሆ ብሎ በአደባባይ ስላልተቃወመ ወኔቢስ ንቃተ ህሊና የሌለው ብለን ለመሳደብ የሚቃጣን ይመስለኛል ::
የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔን ቢቃወምም አማራጭ አቶ ይሆናል ዝም ያለው የሚለውም በሒሳብ ውስጥ መካተት አለበት ::
እኔ በበኩሌ በአሁኑ ወቅት ወያኔን በሰላም ስልጣን ቢለቅ እንኳን ተቋዋሚዎች ተስማምተው ሀገር ይመራሉ ብዬ አላስብም :: አሁን ስልጣን ሳይኖራቸው ምን ያህል ግለኝነትና ግትረኝነት አብሮ ለመስራት እንዳስቸገራቸው የኢትዮጵያ ህዝብ እያየ እንዴት አድርጎ አምኖ ባይደግፈውም መስዋት ከፍሎ ወያኔን ጥሎ እራሱ ላይ ሌላ መከራ ያመጣል
ንቃተ ህሊና የሚያስፈልግ ከሆነ እንኳን በአንደኝነት የሚያስፈልገው እዚህ ዋርካ ላይ ለምንሳተፍ ሰዎች ነው :: ከእኛ የተለየ የፖለቲካ አቋም ያላቸውን በተለይ የወያኔ ደጋፊዎችን እንደ ሌላ ሀገር ዜጋ እና የሀገር ጠላት አድርገን እያየን እንዴት ብሎ ነው በሀገሪቱ ሰላም የሚመጣው ?? እዚህ ዋርካ ላይ እንኳ ሀሳባችንን አቻችለን ተከባብረን መወያየት ያልቻልን ሰዎች የኢትዮጵያ ህዝብን ንቃተ ህሊና የጎደለው ለማለት መድፈራችን እራሱ አስቆኛል ::
በእርግጥ ወያኔ ከመጣ በኃላ የተስፋፉ በሀገር ደረጃ እኔ በበኩሌ እንደ አስፈላጊ የማላያቸው ነገሮች አሉ :: ለምሳሌ የይሮፕ ፕሪሜሊግ ላይ ያለው obsession የመንግስት ሚዲያዎች ሳይቀሩ የሚያራግቡት ነገር ሰዎን ኢትዮጵያዊ ነገር ላይ ከሞክራት ይልቅ የምዕራቢያውያንን ባህል ነፋቂ እንዲሆን ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይመስለኛል :: ሌላው ወያኔ ከመጣ በኃላ የተስፋፋ የጫት መቃም ባህል መረን የለቀቀ ይመስለኛል :: የሙስና : ማጭበርበር የመሳሰሉት እንደ ባህል እየታዩ የመጡ ይመስለኛል :: በአሁኑ ወቅት ቀላል የማይባል በተለይ በከተማ አካባቢ ኢትዮጵያ ውስጥ ተከብሮ ከመኖር ይልቅ ምዕራብ ሀገር ውስጥ ውሻ ሆኜ ብፈጠር ይሻላል ብሎ የሚያስብ ትውልድ አለ :: ወያኔ ያመጣውም ከሀገር ይልቅ በጎሳ የማሰብም ችግርም እንዲሁ :: ለሌላው ሰው እነዚህን ነገሮች እንደ ችግር ላያቸው ይችል ይሆናል :: ዋናው ነጥብ እኔ እንደማስበው ሌላውም ካላሰበ ንቃተ ህሊና ይጎለዋል ፈሪ ነው ወዘተ ማለት ተገቢ አይመስለኝም ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ክቡራን Joined: 04 Mar 2008 Posts: 4260
Posted: Fri Dec 16, 2011 5:46 am Post subject:
የዘመኑ ልሳን እንደጻፈው ..
Quote: Code: ንቃተ ህሊና የሚያስፈልግ ከሆነ እንኳን በአንደኝነት የሚያስፈልገው እዚህ ዋርካ ላይ ለምንሳተፍ ሰዎች ነው :: ከእኛ የተለየ የፖለቲካ አቋም ያላቸውን በተለይ የወያኔ ደጋፊዎችን እንደ ሌላ ሀገር ዜጋ እና የሀገር ጠላት አድርገን እያየን እንዴት ብሎ ነው በሀገሪቱ ሰላም የሚመጣው ?? እዚህ ዋርካ ላይ እንኳ ሀሳባችንን አቻችለን ተከባብረን መወያየት ያልቻልን ሰዎች የኢትዮጵያ ህዝብን ንቃተ ህሊና የጎደለው ለማለት መድፈራችን እራሱ አስቆኛል ::
እርጎዬ እንጀራ ይሉሀል ይሄ ነው :: የዘመኑ ልሳን እውነታውን እንዲህ አድርገው ያስቀመጡት እጆችህ ውለው ይግቡልህ ::
_________________http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ናፖሊዮን ዳኘ Joined: 18 Apr 2008 Posts: 1874
Posted: Fri Dec 16, 2011 6:16 pm Post subject:
የዘመኑ ልዋጭ እንደጻፈው
Quote: ንቃተ ህሊና የሚያስፈልግ ከሆነ እንኳን በአንደኝነት የሚያስፈልገው እዚህ ዋርካ ላይ ለምንሳተፍ ሰዎች ነው :: ከእኛ የተለየ የፖለቲካ አቋም ያላቸውን በተለይ የወያኔ ደጋፊዎችን እንደ ሌላ ሀገር ዜጋ እና የሀገር ጠላት አድርገን እያየን እንዴት ብሎ ነው በሀገሪቱ ሰላም የሚመጣው ?? እዚህ ዋርካ ላይ እንኳ ሀሳባችንን አቻችለን ተከባብረን መወያየት ያልቻልን ሰዎች የኢትዮጵያ ህዝብን ንቃተ ህሊና የጎደለው ለማለት መድፈራችን እራሱ አስቆኛል ::
ስለዚህ ኮሜንትህ በእውነት ምን ማለት እንዳለብኝ አላወቅም ! ህዝብን እና ሀገርን እንደጠላት በማየት በሽታ የተለከፈው ህወሓት እንደሆነ እኛ ካሳየነው በላይ የህወሓት ቡድን ራሱ በተደጋጋሚ አግኝቷል :: ህዝብን እና ሀገርን እንደጠላት የሚያይ ቡድን በኢትዮጵያ ታሪክ ህወሓት የመጀመሪያው ነው :: ይህንን ጥላቻውን በሌሎች ላይ ለማዛመት ያልሞከረው ነገር አልነበረም :: ስንት በይሉኝታ የማይወራ ነገር ስርቷል ህወሓት ! ለመሆኑ ህወሓት አልማዝ መኮን (የኦብኮ አባል አና አመራር የነበረች ) ምን እንዳደረጋት ታውቃለህ ?? ለመጻፍም አልፈልግም ራስህ ጠይቅህ ድረስበት ! የሀገርን ሀብት እንደጠላት ገንዘብ ለውጭ ሰው ባልባሌ ዋጋ የሚቸበችብ መንግስት ድርጊት የሚያሳየው ለኢትዮጵያ ያለውን ፍቅር ነው ?? ይሄ ሁሉ የተዘረፈ ሀብት የሚያሳየው ለኢትዮጵያ ያለውን ፍቅር ነው ?? ጄኖሳይዱስ ?? የዘር ትምክህቱስ ?? አትተንፍሱ የሚለውን የ "አሸባሪነት ' ህግስ ?? ለመሆኑ አንተ ሰው አእምሮ የሚባል ነገር አለህ ?? ምን ያለህ በክት ነህ ባክህ !
ፍቅር የምትባይው ልጂ ...በውይይቱ ላይ ፍላጎት ማሳየትሽን አደንቃለሁ :: ካደረግሽ አይቀር ግን ከልብ ሆነሽ ሌሎች ከርዕሱ ጋር ተዛማጂነት ያላቸውን ጥያቄዎች በታነሺ በጥሞና ልንወያይባቸው እንችላለን :: እቴጊይት እንዳለችሽ የዚህ ትሬድ ርዕስ ከተቃዋሚ ፖለቲከኞች ጋር በቀጥታ የተያያዘ አይደለም :: በያጋጣሚው በውይይት መሀል ማንሳት ካለብን እያነሳን መነጋገር እንችላለን ::
እህት እቴጊይት ---የጉዳዮን አሳሳቢነት በመረዳትሽ ደስ ብሎኛል :: ከዚህ በፊት የጻፍሺው ነገር ጋር በብዛት የሚገናኝ ነገር የለውም :: የሆነ ሆኖ ግን በዚህ ነጥብ ላይ ተመሳሳይ የሆነ ነጥብ የነበረን ከሆነ እና ያልተረዳሁት ከሆነ ይቅርታ መጠየቅ ይኖርብኛል :: የምትጽፊውን ጻፊና በምን ያህል ደረጃ እንደተግባባን እንፈትሻለን ::
ጥልቁ ንቃተ ህሊናን ጥሩ አድርገህ ክላሲፋይ ልታደርገው ሞክረሀል :: ሆኖም ግን የኔ ትኩረት የነበረው ''የለውጥ ሀይል "" ስለሚባለው የህበረተሰብ ክፍል ነው --- ወጣቱ !
የሚገርምህ ነገር ደሞ ባስቀመጥካቸው ካታጎሪዎች ሁሉ ወጣቱ ይብዛም ይነስም አለበት ! የጥበብ ሰዎች የምትላቸው እንደ ጸጋየ ገብረ መድህን ያሉት አርበኞች አልቀው እንደነወጋየሁ አይነቶቹ አልቀው እነ ስራዊት ይሄንን ህዝብ ለባንዳ እንዲገዛ የሚሰሩትን እያየን ነው እነ አስቴር አወቀ (ዛሬ እንዲህ ልታስጠላኝ በጣም ዘፈኗን እወድ ነበር ) አልባሌ ሆነው የህወሓት ትሮጃን ፈረስ በመሆናቸው ዛሬ የቡና ላኪነት ንግድ ውስጥ ሳይቀር ገቡ ! ""ኢትዮጵያ አንድ ሺ ዘመን ተኝታለች "" የሚሉ እና የኢትዮጵያን ባህል እንደ ጭራቅ አድርገው የሚስሉ ጸሀፍትን አየን ! በዚህ በተረገመ ዘመን
ሊዳብር የሚችል ንቃት ይዘው ወደ ፖለቲካ የገቡትን ወጣቶች እነ ብርቱካን ሚዴቅሳን እና የጥበብ ሰዎች እነ ቴዲ አፍሮን ህወሀት ምን እንዳደረሰባቸው አይተናል ! የአርበኝነት ስሜት ይዞ የተነሳ ብዕርም (እስክንድርን እና ሌሎች የነጻ ሜዲያ ሰዎችን ልቦ ይሏል ) ህወሀት ""አሸባሪ "" የሚል ድራማ ለጥፎ ምን አያደረጋቸው እንደሆነ እያየን ነው ! ""የአኬልዳማን ድራማ "" ሳይ የድራማው ያልተዋጣለት መሆን አልነበረም እኔን የገረመኝ ! እኔን የገረመኝ የዚህን ኢትዮጵያዊ ወጣት ኢንተሌክት እንዴት ቢንቁት ነው ? ነው ይሄን ያህል ወጣቱ ንቅተ ህልና አጥቷል በሚል ነው ከራሴ ጋር ሳወራ የነበረው !
ለፖለቲካ ትግል እና ለሀገር ፍቅር የሚያስፈልገውን ንቃተ ህሊና ነው እያወራሁ ያለሁት ! ሀገር ለማሳደግም ግብዐት የሚሆነው እንደዚህ አይነት ንቃት ያለው ---የነፃነት ትርጉም እና ፋይዳ የገባው የህይወት ትርጉም የገባው ዜጋ ነው !
በሌላ በኩል እንግዲህ ህወሀት ንቃተ ህሊናን ለማጥፋት የሚሄዳቸውን አካሄዶች እያየን ነው ! አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ወጣቶች በቡጢ የሚናረቱበትን የፕሪሚየር ሊግ እንዲታይ ሲያደርግ በዛ በሚራብ ህዝዝብ ላይ መቀለዱ ብቻ አልነበረም ! በወጣቱ ኢንተሌክት እንጂ !
የኢትዮጵያዊውን ወጣት የፖለቲካ አመለካከት በገንዘብ ሊገዛ ሲሞክር የለም ህወሀት ከአድዋ ወይ ከደደቢት ያመጣው ገንዘብ የለም ! ከኒዮርክ ስቶክ ኤክስቸንጂ የመጣም አይደለም ! የሀገሬ ሀብት ነው እንደ ዜጋ ይገባኛል በማለት እንደ ሰው እና እንደኢትዮጵያዊ የሚያስብ ወጣት ዘመን ላይ ደርሰናል !
የኢሀፓን እና የመኢሶንን ወጣቶች ታርክ ከላይ ያነሳሁት ያለምክንያት አይደለም ! አብዮተኝነት የሚለው ነገር እንዳለ ሆኖ በትግላቸው ውስጥ የተንጸባረቀው ቁም ነገር የሀገር እና የወገን ፍቅር ነው ! አንድ ከተሜ ወጣት መሬት ላራሹ ብሎ ለማሰብ የሀገር እና የወገን ፍቅር ብሎም ነፃነት እና ፍትህ ወዳድነትን ይጠይቃል እነዚህ ሁሉ ደሞ የንቃተ ህሊና መዳበር ውጤቶች ናቸው ! በሌላ በኩል የኛ ትውልድ ነፃነት የሚባለው ነገር ብዙም የገባውና ግድ የሚሰጠው ሆኖ አይስተዋልም :: የዘመን ባሪያ ሆኗል ! ዘመኑ እንደራዕይ ያመጣብን ነገር ስደትን ነው የዕለት ተዕለት ኑሯችን አካል አድርጎ ያመጣብን ነገር አውሮፓዉያኖቹ በመልቲ ቢሊየን ዮሮ የሚያንቀሳቅሱት የፕሪሚየር ሊግ ንግድ ነው ከዛ ደሞ ይሄ ጫት የሚባል ነገር አለ ! የወጣት የዕለት ተዕለት የኑሮ ገጽታ ሆኖ አርፏል :: ነገ ጫት የሚቃምበት ገንዘብን የማፈላለግ እና የማግኘት ነገር ለወጣቱ ሀሳብ ነው ! ነጻነት ግን ተረስቷል ! ባባዱ ሆዱ እጁን ኪሱ አድሮ አንገቱን ደፍቶ እያፋጨ ወክ ማድረግ ከነፃነት ተቆጠረ !
አንድ ሀገር መሬት ለውጭ ቱጃር ሲሸጥ እና ህወሓት ሀገር ለማልማት ነው እያለ ሲያላግጥ excuse us ያለ ወጣት ኢትዮጵያዊ የለም ! ኢትዮጵያ ላይ ለግብረሰዶማዊነት ህወሀት አንጥፎ ሲጎዘጉዝ ማነው ወንዱ ብለው የወጡት 15 ልጆች ናቸው ! እነኚህ ሁሉ ክስተቶች የንቃተ ህሊና መላሸቅ ወጤቶች የዘመን እስረኛ እና ባሪያ የመሆን ውጤቶች ሲሆኑ ህወሀት በገንዘብም በጉልበትም ይህንን ድባብ ለመፍጠር 17 ዓመት ከታገለው ያላነሰ ታግሏል !
የሚያስቡ እና እንድናስብ የሚያደርጉን ፀሀፍትም ጠፉ ! አሁንም ""ሽብርተኞች "" ናቸው !
በፀረ ግኝ አገዛዝ ትግል በተወሰነ መልኩ ትግሉን ስል ያደረጉት አፍሪካውያን ጸሀፍት ናቸው ! የፈረንሳይ አብዮት የኢንላይትንመት እንቅስቃሴ ውጤት ነው ! በፖለቲካ አመራር ደረጃም ያሉ ሰዎች ራዕይ የራሱ የሆነ አስተዋፆ አለው ! ዶክተር ክዋሜ ንኩሩማ 'seek first thy political kingdom' ሲል ሀይማኖትን ቻሌንጂ ማድረጉ አልነበረም ! ነገር ግን ሰው ተስፋ በመቁረጥ ነገር ዓለሙን ለእግዚያብሄር ሰጥቶ ተንበርክኮ በመጸለይ ብቻ ነጻነት እንደማይገኝ ሲያስታውስ ነው ! እውነትም ደሞ እግዚያብሔር ከሰማይ ወርዶ ሰውን ነፃ አያደርግም ! የትግል ጽናትን እና ብርታትን መጠየቅ ያስፈልጋል :: ተገቢም ነው :: በዛ መልክ ነው እግዚያብሄርም ለነጻነታችን የሚረዳን ::
የሚመሩን ሰዎች አይደንቲቲ ፖለቲክስን በውል ይዘውታል ብየ አላምነም ! ኢትዮጵያውያን ነን :: እንደኢትዮጵያዊነታችን ለዘመናት ከነፃነት ጋር የኖርን ነን ! ኮለል ያለ እና ስሜት የሚሰጥ የህይወት ፍልስፋና የነበረን ነን ! ስግብግቦች አልነበርንም ! ራስ ወዳዶች አልነበርንም ! የኢትዮጵያ ህዝብ ስግብግብ እና ራስ ወዳድ ቢሆን ኖሮ ሀገሩን እንደሸጠው ባንዳ ሁሉ ኢትዮጵያውያን ለገንዘብ አድረው ኢትዮጵያ የጠላት አውድማ በሆነች ነበር :: ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ቤት ሰው የሞተበት ትልቅ ቁም ነገር ነፃነት እና ያገር ፍቅር ነበር !
ዛሬ ህወሀት በጥበብ እና ያለጥበብም ሙሰኛ ለሀገር ግድ የሌለው ዜጋ አፈራ ! ምን አይነት ንቃተ ህሊና እና ነፃ አስተሳሰብ ያለው ኢትዮጵያዊ ነው እንደ መለስ ዜናዊ ያለን አስተዳደር ታግሶ ይሔን ያህል ዘመን የሚኖረው ??
አርበኞቻንንን አጣን :: አርበኛ የብዕር ሰው ! አርበኛ ፖለቲከኛ ! እና ከላይ እንዳልኩት የዘመን እስረኛ ሆንን :: ዘመን ደሞ በብልጠት ባርነትን ይሰብካል :: ቢያንስ ያንን በማወቅ ብንጀምር ትልቅ እመርታ ነበር :: የልጁ ግጥም ደስ ያለኝ ለዛ ነው !
ናፖሊዮን ዳኘ :: _________________ ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ሓየት 11 Joined: 06 Apr 2008 Posts: 2739 Location: ላን'ሊይ
Posted: Fri Dec 16, 2011 7:22 pm Post subject: Re: ንቃተ ህሊና
ህዝብን ተጠያቂ ለምታደርጉ : በተለይ ህዝቡ መስዋዕትነት የሚጠይቅ ስራ ለመስራት ዝግጁ አይደለም የምትሉ : እስኪ መጀመሪያ ራሳችሁን ጠይቁ : ራሳችሁንም አጽዱ :: እነ ታማኝ ማይክራፎን ጨብጠው ኡኡ ከማለት የዘለለ : እነ ግንቦት ሰባት በሬዲዮና በፓልቶክ ከመሸለል አልፈው ምን የሰሩት ነገር አለ :: ለመስዋእትነት የቆመ መሪ ወይም ተቃዋሚ ቢኖር ኖሮ መለስ በልበ ሙሉነት ካገር ወደ አገር ነጋ ጠባ አይዘዋወርም ነበር :: ሰባ ሰባት ነጥብ :::::::: _________________ An eye for an eye, and the whole world would be blind. (KGK)
>>>>>>>>> ገዛ ሓየት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
እቴጌይት Joined: 23 Sep 2007 Posts: 546
Posted: Sat Dec 17, 2011 2:44 am Post subject: Re: ንቃተ ህሊና
ሠላም የዘመኑ
የዘመኑ ልሳን እንደጻፈ(ች)ው : ንቃተ ህሊና ስንል ምን ማለታችን ነው የሚለውን በግልጽ ማስቀመጥ ያስፈልጋል :: እኛ እንደምናስበው ካላሰበ ንቃተ ህሊና የለውም እምንል ከሆነ የእኛን ባዶነት የሚያሳይ ይመስለኛል ::
እኛ የምናስበውን ካላሰበ ንቃተ ሕሊና የለውም የሚል ነጥብ ያነሳ ሰው እስካሁን አላነበብኩም ! ከዛ ውጪ ግን በዚህ ውይይት ንቃተ ሕሊና ስንል ስለምን እያወራን እንደሆነ ለመረዳት ብዙም አዳጋች አይመስለኝም :: አንድ ሰው በዜግነቱ ሙሉ ሰብአዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መብት እንዳለው ግንዛቤ ሲኖረው እና ያንን ደግሞ መንግስት በቸርነቱ የሚመጸውተው እንዳልሆነ ሲረዳ ይሄንን ተፈጥሯዊ መብቱን የሚያግድ መንግስትም ሆነ ሌላ ሀይል ሲመጣ በውስጡ ቁጩትና ለመለወጥ መነሳሳት ስለመኖሩ ደረጃ እያወራን እንደሆነ ግልጽ ነው :: ይሄ ጉዳይ አንድን የተቃዋሚ ፓርቲን ከመደገፍ ወይም የሆነ አስተሳሰብን ከመቀበል ወይም ካለመቀበል ጋር ግንኙነት እንደሌለው መረዳት ያስፈልጋል ::
የዘመኑ ልሳን እንደጻፈ(ች)ው :
አንዳንዶቻችን ሕዝቡ የወያኔ መንግስትን ሆ ብሎ በአደባባይ ስላልተቃወመ ወኔቢስ ንቃተ ህሊና የሌለው ብለን ለመሳደብ የሚቃጣን ይመስለኛል ::
በመጀመሪያ ደረጃ ማህበርሰባችን የሚገኝበትን የንቃተ ሕሊና ደረጃ ላይ ሀሳብ መስጠት ስድብ ያደረገው ማነው ? በቀረበው ሀሳብ የማትስማማ ከሆነ እና የሕብረተሰባችን ንቃተ ሕሊና በጣም የዳበረና በቂ ነው ብለህ የምታምን ከሆነ ያንን በምክንያታዊ ነጥቦች ማስረዳት እንጂ ካንተ የተለየ ሀሳብ ስላጋጠመህ እንደ ስድብ መውሰድ ድክመት ነው እላለሁ !! በሁለተኛ ደረጃ የንቃተ ሕሊናና የቁርጠኛነት ጉድለትን እዚህ ውስጥ ያነሳን ሰዎች ... አለ ለምንለው ጉድለት መሰረታዊ ምክንያቶችን ገና ማቅረብና መዘርዘር ሳንጀምር ... አንተ የእኛ ጭንቅላት ውስጥ ገብተህ ' በአደባባይ ሆ ብሎ ለምን ወያኔን አልተቃወመም ' በሚል ነጠላ ምክንያት ነው ' ብለህ መደመድምህ ስህተት ነው :: መጀመርያ ምክንያቶቻችንን ማዳመጥ የሚቀድም አይመስልህም ?
የዘመኑ ልሳን እንደጻፈ(ች)ው :
የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔን ቢቃወምም አማራጭ አቶ ይሆናል ዝም ያለው የሚለውም በሒሳብ ውስጥ መካተት አለበት ::
እዚህ ላይ እንግዲህ ሲጀመር ገና ሕብረተሰቡ በዝምታ ላይ መሆኑን ተቀበለሀል ማለት ነው !! ሌላው ቢቀር ግማሽ መንገድ ደረስ ተስማማን ማለት ነው !! ክርክርህ ዝምታው በንቃተ ሕሊና ወይም ቁርጠኛነት ጉድለት አሊያም በመስዋዕትነት ፍራቻ ሳይሆን ምናልባት በአማራጭ እጦት ሊሆን ይችላል የሚል ግምት ነው !! በእኔ እይታ ይሄ አስተሳሰብ ራሱ የንቃተ ሕሊና ጉድለቱ አንዱ አካል አድርጌ አየዋለሁኝ :: ምክንያቱም አንድ ሕዝብ ለራሱ እድልና እጣ ፈንታ ባለቤቱ ራሱ መሆኑን መገንዝብ ካልቻለ ...የለውጡ ባለቤትም እርሱ ራሱ መሆኑን ካልተረዳ ..ሌሎች (ፈጣሪ ይሁን ወይም የፖለቲካ ድርጅት ) መጥተው ለውጥ ያመጡልኛል ብሎ አንጋጦ የሚጠብቅ ከሆነ ..... ገና ለእራሱ ሕይወት ባለቤትነትን ለመውሰድ የሚያስችል ንቃተ ሕሊና እና ቁርጠኛነት ላይ ገና አልደረሰም ማለት ነው :: Enlightenment የሚጀመረው ለሰውነትና መብት ዋጋ ከመስጠት እና ለዛም ሀላፊነትን ከመቀብል ይመስለኛል !!
የዘመኑ ልሳን እንደጻፈ(ች)ው :
እኔ በበኩሌ በአሁኑ ወቅት ወያኔን በሰላም ስልጣን ቢለቅ እንኳን ተቋዋሚዎች ተስማምተው ሀገር ይመራሉ ብዬ አላስብም :: አሁን ስልጣን ሳይኖራቸው ምን ያህል ግለኝነትና ግትረኝነት አብሮ ለመስራት እንዳስቸገራቸው የኢትዮጵያ ህዝብ እያየ እንዴት አድርጎ አምኖ ባይደግፈውም መስዋት ከፍሎ ወያኔን ጥሎ እራሱ ላይ ሌላ መከራ ያመጣል
ይቺ ደግሞ ኢቲቪ ላይ በየጊዜው የምንሰማት ጥሩ የወያኔ መከራከሪያን መድገምህ ግር ብሎኛል :-
1ኛ ) ለክርክር ያህል እንደው በጅምላ አንድ ላይ ተቃዋሚዎች ላይ ያደረከው ፍርጃ ትክክል ነው ብለን ብንስማማ እንኳን (በየግል ሕይወታቸው እስር እስከመውረድና አንዳንዶቹም እስከመሞት የከፈሉትን ዋጋ በሙሉ ደምስሰነው ማለት ነው !!)......... እንደዚህ አፈር ድሜ የምታበላቸው ሰዎች እኮ ከጂቡቲ ወይም ሱማሌ የመጡ ሳይሆን ከእኛው ሕብርተሰብ አብራክ የወጡ የአስተሳሰቡና የአሰራሩ ነጽብራቆች መሆናቸውን አስበኸዋል ?? አንበሳ ድመትን ነበር ውሻን አይወልድም እኮ :: የእነርሱ ድክመት በሙሉ የሕብረተሰቡ ድክመት ግልባጭ አይደለምን ??
2ኛ ) ሌላው ትልቁ ጉዳይ ደግሞ መብትን መረዳት እና ለለውጥ በቁርጠኛነት መነሳት የግድ የአንድ የፖለቲካ ድርጅት ወይም መሪ ተከታይ በመሆን ብቻ ነው ያለው ማን ነው ?? ከገዛ መሬቱ በግፍ የሚፈናቀል አንድ ዜጋ ወይም በስሙ የተሰበሰበ ማዳበርያን የተከለከለ ገበሬ 'በቃኝ እምቢ !' ለማለት ሀይሉ ሻወልን መደገፍ አያስፈልገውም :: ሀሳቡን እንዳይገልጽ እንደፈረስ የተለጎመ ሰው እንደ እስክንድር 'እምቢ ' ለማለት የዶ /ር ብርሀኑ ተከታይ መሆን አያስሻውም :: ወገን በአደባባይ በጥይት ግንባሩን ተብሎ ሲገደል አይቶ 'በቃኝ ' ለማለት የአንድነት ድርጅት አባልነትን አይጠይቅም :: የድርጅቶች መጠንከርና መተባበር እምቢታን መስመር ያሲዛል .... ለውጥን ያፍጥናል ወዘተ ...ማለት ሌላ ጉዳይ ነው :: ሲገርፉት ተገርፎ ... ሲገሩት ተገርቶ .... 'ኦሽ ' ሲሉት እሺ የሚል ባህልን የሙጥኝ ብሎ 'በተመስገን አምላኬ ' መኖር ደግሞ ፈጽሞ ሌላ ጉዳይ ነው !!
የዘመኑ ልሳን እንደጻፈ(ች)ው :
ንቃተ ህሊና የሚያስፈልግ ከሆነ እንኳን በአንደኝነት የሚያስፈልገው እዚህ ዋርካ ላይ ለምንሳተፍ ሰዎች ነው :: ከእኛ የተለየ የፖለቲካ አቋም ያላቸውን በተለይ የወያኔ ደጋፊዎችን እንደ ሌላ ሀገር ዜጋ እና የሀገር ጠላት አድርገን እያየን እንዴት ብሎ ነው በሀገሪቱ ሰላም የሚመጣው ?? እዚህ ዋርካ ላይ እንኳ ሀሳባችንን አቻችለን ተከባብረን መወያየት ያልቻልን ሰዎች የኢትዮጵያ ህዝብን ንቃተ ህሊና የጎደለው ለማለት መድፈራችን እራሱ አስቆኛል ::
1ኛ ) ዋርካ ላይ በመቻቻል ላይ የተመሰረተ ጥሩ ውይይት ስለማይደረግ ሕብረተሰባችን ውስጥ እናየዋለን የምንለውን ችግር ማንሳት አንችልም ማለት እንዴት ያለ ሎጂክ ነው ? እዚህ አምድ ላይ የቀረበው የውይይት ርዕስ የማንንም ስብዕና የማይነካ legitimate የሆነ ጥያቄ ነው :: ጥያቄው ላይ የቀረበው ነጥብ ትክክል ካልመስለህ ለምን ትክክል እንዳይደለ ማስረዳት እንጂ ገና ሲጀመር ልክ እንደወያኔ እናንተ እዚህ ላይ መነጋገር አትችሉም ብሎ መደምደም ያኬዳል እንዴ ? በነገራችን ላይ ዋርካ ላይ ስድድብ እና ብዙ ጸያፍ ነገሮች መኖራቸው በበኩሌ ምንም የሚያስገርም ነገር የለውም :: ምክንያቱም እንኳን እንደኛ መልከ ብዙ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ የሚገኝ የማህበረሰብ አባል የሚሳተፍበት ድህረ ገጽ አይደለም የዲሞክራሲ ቁንጮ ላይ ደርሰዋል የምንላቸው አሜሪካኖችም ብሎግ ውስጥ ብትገባ ለጆሮ የሚዘገንኑ በርካታ ነገሮችን ትሰማለህ :: ይሄ ማለት ታዲያ ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ የሚሰማቸውን ከመግለጽ ይታቀቡ አያሰኝም ::
2ኛ ) የእኛ ችግር እንደውም 'ለምን ሀሳብ ለመስጠት ደፈርን ' ሳይሆን ከችግራችን ግዙፍነት አንጻር የባለቤትነት ስሜት ተሰምቶን የምንሳተፈው ሰዎች ቁጥር እጅግ አናሳ ለምን ሆነ የሚለው ነው :: ፖለቲካን እንደ ጦር የመፍራት ባህል !! በዚህ አጋጣሚ ወያኔ ከሚጠቀምበት ትልቅ ፕሮፓጋንዳ አንዱ ዜጎች በተለይ በውጪ ያሉት በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ሀሳባቸውን በድፍረት እንዳይገልጹ ዲስክሬድት አድርጎ ዝም ለማሰኘት መሞክረ ነው !!
ከአክብሮት ጋር
እቴጌይት
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ጥልቁ 1 Joined: 27 Jan 2004 Posts: 1560 Location: bhutan
Posted: Sat Dec 17, 2011 2:45 am Post subject:
ሰላም ለሁሉም :.
ውድ ናፖሊዮን፡ ይህን አምድ ስትከፍት አንድ ያስቀመጥኸው ማስጠንቀቂያ አለ። ይህ አምድ የወያኔ አጥፊነት ጥያቄ ውስጥ በማያስገቡ ኢትዮጵያውያን መሃከል የሚደረግ የውይይት መድረክ ስለሆነ ፣ የወያኔ ርዝራዦች ብቅ ጥልቅ ቢሉና “ወያኔዎችን እንደኢትዮጵያዊ አቅርቡን” ብለው ለሚያነሱት ጥያቄ ስለወያኔ ለማስረዳት መቃጣት ፤ የውይይቱን አቅጣጫ እንደሚያስት ልብ ይሏል። እንደነዚህ አይነቶቹን ምንም አይነት ምላሽ ሳይሰጡ ማለፍ…
ንቃተ -ህሊና…
ከላይ የጠቃቀስኋቸው መነሻ ሃሳቦቸ ፣ አንዳቸው ከአንዳቸው የተያያዙ ናቸው። እንዴውም ሁለት የዘነጋኋቸው (የቤተ -አምልኮዎች እና የትምህርት ተቋማት አስተዋጽኦ ) እና ብዙ ግን የሁሉንም ተሳትፎ የሚጠይቅ (ለመሆኑ ወጣቱ ንቃተ ህሊናው የሚታነጸው የት ነው ?) በሚለው ላይ ሁላችንም የበኩላችንን ልንል ይገባል። ወደራሴ ሃሳብ ከመግባቴ በፊት ግን ፣ በፍቅር የተነሳው ነጥብና በእቴጌይት አላስፈላጊነቱ የተንጸባረቀው “የተቃዋሚ ፖለቲከኞች” ጉዳይ ላይ ማለት የምፈልገው አለኝ።
“ Logical argument” ወይም ትርጉም ያለው ክርክር የሚባለው “ይሄ ቀለም ጥቁር አይደለም” ማለት ሳይሆን “ይሄ ቀለም ጥቁር ሳይሆን … ነው” ብሎ መግለጽ ነው። የወጣቱ ለለውጥ ተነሳሽነት ንቃተ ህሊና ሲፈተሽ ከለውጥ በኋላስ “ወዴት ነው የምሄድ” ብሎ ለሚያነሳው ጥያቄ መልስ ከሌለው ፣ ለምን ለለውጥ ይነሳል ?! እንዴውምኮ ስለንቃተ -ህሊና ልንተረትር የምንሞክረው ሁሉ እንዴው ሃሳብ ለመለዋወጥ ያህል ብቻ ካልሆነ በቀር ፣ የሰው ልጅ ለውጥን የመሻቱ ነገርኮ ተፈጥሯዊ እንጅ የሚሰበክለት ነገር አይደለም። ሰዎች ወያኔን ለመጥላት ፖለቲካ ሊሰበክላቸው ግድ አይልም። ኑሯቸው እራሱ ወያኔ የጫነባቸው ቋጥኝ እንደሆነ ቀን በቀን የሚያዩት ነው። ይህንን ሌላ የትም ሳንሄድ ፣ ወያኔ በ 97 ምርጫ የተናገረውን እንስማ ፤… በመለስ አነጋገር “ለተቃዋሚው ሁሉ የተሰጠው ድምጽ ፣ በወያኔ ላይ ያለን ቅዋሜ ለመግለጽ እንጅ ተቃዋሚዎችን የመደገፍ አይደለም” (Protest vote) ስለዚህ ፣ የተቃዋሚው ጎራ አካሄዱን አሳምሮ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር አሳማኝ እርቅ እስካልመሰረተ ድረስ ፣ ንቃተ -ህሊና ብቻውን ትል የበላው የተቆረጠ የበቆሎ ጮርቃ ነው። (ለማገዶ ብቻ የሚሆን )
በሌሎቹ ነጥቦች ዙሪያ ፣ ሰንበትን አሳልፌ ብቅ እልባቸዋለሁ።
ሰላም
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ናፖሊዮን ዳኘ Joined: 18 Apr 2008 Posts: 1874
Posted: Sat Dec 17, 2011 7:25 am Post subject:
ስላም ጥልቁ
በንቃተ ህሊና ላይ የገባኝን ያህል ሀሳብ ከመሰንዘሬ በፊት አንተ እንዳልከው መልስ ብለህ መታየት አና አብሮ መዳሰስ አለበት የምትለውን ሀሳብ ብታካፍል ደስ ይለኛል ::
እንደኔ እንደኔ መጀመሪያ የሰራሀቸው ክላሲፊኬሺኖች የበለጠ ፋንክሽናል ናቸው :: ምክንያት በቀጥታ የተጠቀሱትን የህብረተሰብ ክፍሎችን ንቃተ ህሊና በመፍጠር እና ባለመፍጠር የሚኖራቸውን አሉታዊም አዎንታዊም አንድምታ ለመመዘን ስለሚያገለግሉ :: አሁን የጨመርካቸው ሁሉት ካታጎሪዎች --የእምነት እና የትምህርት ተቋማት ---እንደ ተቋም መታየት ያለባቸው ናቸው :: ለነገሩ በአንድ ጎኑ ሲታይ የተቋማቱ ጥንካሬ እና ድክመት ወይንም ርባና እና ርባና ቢስነት በተወሰነ መልኩ ተቋማቱን የሚያንቀሳቅሱ እና በተቋማቱም የሚገለገሉ የህብረስተስብ ክፍሎችን ንቃተ ህሊና ነው የሚያመላክቱት :: በሌላ እነጋገር የተጠቃሚው ህበረተሰብ የንቃተ ህሊና ደረጃ ነው የተቋማቱን ፋይዳ (ከንቃተ ህሊና ጋር በተያያዘ ) የሚወስነው :: ለምሳሌ የአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲን ባለፈው ሀምሳ አመት በሀገሪቱ ፖለቲካዊ ህይወት የነበረውን አስተዋጾ ብናይ እንደየዘመኑ እና እንደነበረው ንቃተ ህሊና ይለያያል :: አሁን እንደሚታየው አዲስ አበባ ዮኒቨርሲቱ መንግስት እየገባ በማስፈራራትም ሆነ በጥቅማጥቅም በመያዝ የመንግስት መገልገያ እና የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ተማሪ ማህበራት የሚያደራጂባቸው ተቋም አልነበረም :: ዛሬ ሁኔታው (እንደምሰማው ) በእጂጉ ተቀይሯል ::
የእምነት ተቋማት ትንሽ ለየት ያለ ባህሪ አላቸው :: እሱንም እመለስበታለሁ ::
ናፖሊዮን ዳኘ ::
ጥልቁ 1 እንደጻፈ(ች)ው : ሰላም ለሁሉም :.
ውድ ናፖሊዮን፡ ይህን አምድ ስትከፍት አንድ ያስቀመጥኸው ማስጠንቀቂያ አለ። ይህ አምድ የወያኔ አጥፊነት ጥያቄ ውስጥ በማያስገቡ ኢትዮጵያውያን መሃከል የሚደረግ የውይይት መድረክ ስለሆነ ፣ የወያኔ ርዝራዦች ብቅ ጥልቅ ቢሉና “ወያኔዎችን እንደኢትዮጵያዊ አቅርቡን” ብለው ለሚያነሱት ጥያቄ ስለወያኔ ለማስረዳት መቃጣት ፤ የውይይቱን አቅጣጫ እንደሚያስት ልብ ይሏል። እንደነዚህ አይነቶቹን ምንም አይነት ምላሽ ሳይሰጡ ማለፍ…
ንቃተ -ህሊና…
ከላይ የጠቃቀስኋቸው መነሻ ሃሳቦቸ ፣ አንዳቸው ከአንዳቸው የተያያዙ ናቸው። እንዴውም ሁለት የዘነጋኋቸው (የቤተ -አምልኮዎች እና የትምህርት ተቋማት አስተዋጽኦ ) እና ብዙ ግን የሁሉንም ተሳትፎ የሚጠይቅ (ለመሆኑ ወጣቱ ንቃተ ህሊናው የሚታነጸው የት ነው ?) በሚለው ላይ ሁላችንም የበኩላችንን ልንል ይገባል። ወደራሴ ሃሳብ ከመግባቴ በፊት ግን ፣ በፍቅር የተነሳው ነጥብና በእቴጌይት አላስፈላጊነቱ የተንጸባረቀው “የተቃዋሚ ፖለቲከኞች” ጉዳይ ላይ ማለት የምፈልገው አለኝ።
“ Logical argument” ወይም ትርጉም ያለው ክርክር የሚባለው “ይሄ ቀለም ጥቁር አይደለም” ማለት ሳይሆን “ይሄ ቀለም ጥቁር ሳይሆን … ነው” ብሎ መግለጽ ነው። የወጣቱ ለለውጥ ተነሳሽነት ንቃተ ህሊና ሲፈተሽ ከለውጥ በኋላስ “ወዴት ነው የምሄድ” ብሎ ለሚያነሳው ጥያቄ መልስ ከሌለው ፣ ለምን ለለውጥ ይነሳል ?! እንዴውምኮ ስለንቃተ -ህሊና ልንተረትር የምንሞክረው ሁሉ እንዴው ሃሳብ ለመለዋወጥ ያህል ብቻ ካልሆነ በቀር ፣ የሰው ልጅ ለውጥን የመሻቱ ነገርኮ ተፈጥሯዊ እንጅ የሚሰበክለት ነገር አይደለም። ሰዎች ወያኔን ለመጥላት ፖለቲካ ሊሰበክላቸው ግድ አይልም። ኑሯቸው እራሱ ወያኔ የጫነባቸው ቋጥኝ እንደሆነ ቀን በቀን የሚያዩት ነው። ይህንን ሌላ የትም ሳንሄድ ፣ ወያኔ በ 97 ምርጫ የተናገረውን እንስማ ፤… በመለስ አነጋገር “ለተቃዋሚው ሁሉ የተሰጠው ድምጽ ፣ በወያኔ ላይ ያለን ቅዋሜ ለመግለጽ እንጅ ተቃዋሚዎችን የመደገፍ አይደለም” (Protest vote) ስለዚህ ፣ የተቃዋሚው ጎራ አካሄዱን አሳምሮ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር አሳማኝ እርቅ እስካልመሰረተ ድረስ ፣ ንቃተ -ህሊና ብቻውን ትል የበላው የተቆረጠ የበቆሎ ጮርቃ ነው። (ለማገዶ ብቻ የሚሆን )
በሌሎቹ ነጥቦች ዙሪያ ፣ ሰንበትን አሳልፌ ብቅ እልባቸዋለሁ።
ሰላም
_________________ ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
*ፍቅር * Joined: 27 Apr 2011 Posts: 42 Location: usa
Posted: Sun Dec 18, 2011 12:50 am Post subject:
ሥላም
ሓየት 11
Quote: ህዝብን ተጠያቂ ለምታደርጉ : በተለይ ህዝቡ መስዋዕትነት የሚጠይቅ ስራ ለመስራት ዝግጁ አይደለም የምትሉ :
እስኪ መጀመሪያ ራሳችሁን ጠይቁ : ራሳችሁንም አጽዱ :: Code:
እሄ ጥያቄ መመለስ ያለብህ አተ ነህ :: ብዙ ግዜ በምትጽፋችው ወገነንተኝት ያጠቃሀለ ስለአንድ ግለሰብ ስትክራከር ትታያለ ነጻ አይምሮ ላለሰው ሰው አያመልክም ::
ኢትዬጵያ ውስጥ ህግ ቢኖር ኑሮ የምታመልከው ግለሰብ የሞት እስራት ይፈረድበት ነበር ::
[quote]እነ ታማኝ ማይክራፎን ጨብጠው ኡኡ ከማለት የዘለለ :
ለኔ ታማኝ አበሳነው
Quote: እነ ግንቦት ሰባት Code:
ግንቦት 7 ከኦሮሞ ነጸ አውጭና ኡጋደን የሚያረጉት ጥሩ ጅምርነው ለህዝባችንና ለሀገራችን ካሰቡ ሁሉን ያካተተ የሰደተኙች መንግስት መመስርት :: የስደተኙች መንግስት ከመሰረቱ በኋላ ከተጠቂነት ወደ አጠቂነት መሸጋገር የወያኔን ቱባ ቱባ ባለስልጣን መምታት የወያኔ ንብረቶችን ማውደም :: ትግልና ታጋይ ማለት እሄነው ::
[/quote] በሬዲዮና በፓልቶክ ከመሸለል አልፈው ምን የሰሩት ነገር አለ ::
96% እስማማለሁ
ለመስዋእትነት የቆመ መሪ ወይም ተቃዋሚ ቢኖር ኖሮ መለስ በልበ ሙሉነት ካገር ወደ አገር ነጋ ጠባ አይዘዋወርም ነበር :: ሰባ ሰባት ነጥብ ::::::::[quote]
ትክክል በለሀል ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ሓየት 11 Joined: 06 Apr 2008 Posts: 2739 Location: ላን'ሊይ
Posted: Sun Dec 18, 2011 1:33 am Post subject:
እኔ እንኳን አስተያየቴን የሰጠሁት በፋንታሲ አለም ለሚኖሩ የቀለም አብዮተኞች ነበር :: ቁጭ ብሎ ሲቸከችክና ሲጮህ ይውልና መስዋእት የሚሆን ህዝብ የለም ይላል እንደዚህ አይነት ሰዎችን (ህዝብን ተጠያቂ የሚያደርጉትን ) ነበር የጠየቅኩት : እናንተስ ምን መስዋእትነት የሚጠይቅ ስራ ሰራችሁና ስል :: ተደብቆ ድንፋታ መስዋእትነት ሊሆን አይችልም :: ለመቸክቸኩም እኮ አያውቁበትም :: ትላንት ካወሩት ጋር የዛሬ አስተያየታቸው እንደጉድ ይጣረሳል :: አቋማቸውን ሲቀይሩ ለምን እንደሚቀይሩም ለሚከታተላቸው ሰው አያስረዱም :: ዝም ብሎ በጋለ ስሜት መቸክቸክ : ከዛም ተቃራኒ ሀሳብ ሲመጣ : ስድብና ታግ መለጠፍ :: እንደኔ ችኮ ከሆንክና እስከመጨረሻ ከወሰድካቸው : ትንፋሽ አጥሯቸው ሌላ ዲስኩር ውስጥ ይገቡልሀል :: ልክ አንተ አሁን እንዳልከው ማለት ነው : ሰው አምላኪ ለመሆኔና ስለአንድ ግለሰብ ስከራከር እንደምኖር የምትዘላብደው ማለት ነው :: እስኪ እንደዛ የተጻፈ አምጣና ሞግተኝ ብልህ የምታመጣት አንዲት ነገር አትኖርም :: ትንፋሽ ሲያጥርህ ግን ወደ ሌላ ትርፍ ቃል ትገባና በዛም በኩል ልክህን ስሰጥህ "ተሳዳቢ ነህ " እንደዚህ ነህ እንደዛ ነህ ማለት :: እኔ ግን ዋርካን ገና ስቀላቀል ጀምሮ በግልጽ ቋንቋ ነገሮችን በምን አይነት መንገድ እንደምመክት ተናግሬያለሁ :: ሀሳብን በሀሳብ : ሳይንቲፊክ የሆነ ክርክር ለፈለገም አለሁ : ለዱላና ለስድብም እንዲሁ አለሁ :: እዚህ ካለው አብዛኛው ከብት በተሻለ : ለስድቡም ለብልግናውም ለቁምነገሩም ለእውቀቱም ለመማሩም ለማብሸቁም ለማሾፉም ቅርብ ነኝ :: ሁሉንም እንደየ አመጣጡ ይሏል ይህ ነው ::
እና አንተ ነገረ ስራህን ሳየው ለዋርካ አዲስ አትመስልም የአፍ ወለምታህን እንድትጠግን እመክርሀለሁ :: ወልምታ አይደለም የምትል ከሆነ ደግሞ ከሌላ ከየትም ሳይሆን ከጻፍኩት ከራሴ ጽሁፍ ሰው አምላኪነቴን : ለግለሰብ ስል መከራከሬን እንድታሳየኝ እጠይቅሃለሁ :: ያው ትንፋሽ ካጠረህ ምን እንደሚከተል ወፏ ሹክ ትልሃለች ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ
[quote="*ፍቅር *"]ሥላም
ሓየት 11
Quote: ህዝብን ተጠያቂ ለምታደርጉ : በተለይ ህዝቡ መስዋዕትነት የሚጠይቅ ስራ ለመስራት ዝግጁ አይደለም የምትሉ :
እስኪ መጀመሪያ ራሳችሁን ጠይቁ : ራሳችሁንም አጽዱ :: Code:
እሄ ጥያቄ መመለስ ያለብህ አተ ነህ :: ብዙ ግዜ በምትጽፋችው ወገነንተኝት ያጠቃሀለ ስለአንድ ግለሰብ ስትክራከር ትታያለ ነጻ አይምሮ ላለሰው ሰው አያመልክም ::
ኢትዬጵያ ውስጥ ህግ ቢኖር ኑሮ የምታመልከው ግለሰብ የሞት እስራት ይፈረድበት ነበር ::
[quote]እነ ታማኝ ማይክራፎን ጨብጠው ኡኡ ከማለት የዘለለ :
ለኔ ታማኝ አበሳነው
Quote: እነ ግንቦት ሰባት Code:
ግንቦት 7 ከኦሮሞ ነጸ አውጭና ኡጋደን የሚያረጉት ጥሩ ጅምርነው ለህዝባችንና ለሀገራችን ካሰቡ ሁሉን ያካተተ የሰደተኙች መንግስት መመስርት :: የስደተኙች መንግስት ከመሰረቱ በኋላ ከተጠቂነት ወደ አጠቂነት መሸጋገር የወያኔን ቱባ ቱባ ባለስልጣን መምታት የወያኔ ንብረቶችን ማውደም :: ትግልና ታጋይ ማለት እሄነው ::
[/quote] በሬዲዮና በፓልቶክ ከመሸለል አልፈው ምን የሰሩት ነገር አለ ::
96% እስማማለሁ
ለመስዋእትነት የቆመ መሪ ወይም ተቃዋሚ ቢኖር ኖሮ መለስ በልበ ሙሉነት ካገር ወደ አገር ነጋ ጠባ አይዘዋወርም ነበር :: ሰባ ሰባት ነጥብ :::::::: _________________ An eye for an eye, and the whole world would be blind. (KGK)