View previous topic :: View next topic
Author
Message
ክቡራን Joined: 04 Mar 2008 Posts: 4372
Posted: Tue Jan 03, 2012 2:31 am Post subject: ከሰሞኑ ..."ጭር ሲል አልወድም " አለች ..ዶሮ እኮ ነች ::
በዚች ክፍል ውስጥ እለታዊ ዜናዎችን ገጠመኖችን , ፖሎቲካዊ ውሎዎችን , ሳገኝ አካፍልበታለሁ :: ርእሱ ከዚህም ከዚያም ነው ..ያ ማለት ከኢህደጎችም ከኢህደግ ተቃዋሚዎችም ያገኘሁትንና እጄ የገባውን አብረን የምንካፈልበት ነው ማለት ነው :: እስከዛ እቺን ጠቅ ..ያድርጉ ትንሽ አረፍ ካሉ በኌላ እቺን ገጭ ያድርጉ ከመውጣትዎ በፊት አንድ ለመንገድ እቺን ቌ ያድርጉ :: አመሰግናለሁ :: _________________http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com Last edited by ክቡራን on Thu Jul 26, 2012 3:45 pm; edited 19 times in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator

Posted: Tue Jan 03, 2012 5:51 pm Post subject:
የግንቦት 7 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አጠቃላይ የግምገማ ዝግ ውይይት ባሳላፈነው ሳምንት መጨረሻ አካሄደ :: የግንቦት 7 ንቅናቄ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባለ ቡዙ ዘርፍ የሆነውን በድርጅቱ ውስጣዊ ጉዳዮችና በውጭ እየተካሄዱ ባሉ እንቅስቃሴዎች ላይ አጠቃላይ ድርጅታዊ ግምገማና ውይይት ያስተባበረው የኢሮፕ የግንቦት 7 ኑዑስ ኮሚቴ ሲሆን ካሜሪካ , ካውስትራሊያ ካፍሪካ ና ከሩቅ ምስራቅ የተወከሉና ጥሪው የደረሳቸው የአመራር አባላት የተሳተፉበት እንደሆነ ማወቅ ተችሏል :: ውይይቱ ባብዛኛው የመነጋገርሪያ አጀንዳ ያደረገው የአባላት እንቅስቃሴ የመዳከም አዝማሚያን እንዴት መለወጥ እንደሚቻል , እያንዳንዱ አባል ቀደም ብሎ በተሰጠው መመሪያ መሰረት አምስት አምስት አባል ( ጎረቤቱንና ቤተሰቡን ቢሆን ) መመልመል ለምን እንዳልቻለ , መዋጮዎቹ በወቅቱ ወደ ማእከላዊ ቢሮ ለምን እንደማይደርሱ , ወቅታዊ የሆነው የኦነግ ጉዳይ ለግንቦት 7 ያለው ፋይዳ , ግንቦት 7 ህብረ ብሄራዊ ከሆኑ ድርጅቶች ( ለምሳሌ ያርበኖች ግንባር ), እያሸሸ ስለምን ብሄርተኛና መገንጠልን ዋና አጀንዳ ከሚያደርጉ ድርጅቶች ጋር መጣበቅ እንደፈለገ እንዲሁም አንድ አገር አቀፍ ኮንግረስ በኢተርኔት ሳይሆን ባካል መደረግ የሚቻልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት በመመከር ላይ ያተኮረ ነበር :: በውይይቱ ላይ ከፍተኛ የግንቦት 7 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባላት የተገኙ ሲሆኑ ውይይቱ ረጅም ከመሆኑ የተነሳ ጸሀፊው አቶ ሙሉነህ ካባላት የተነስቱትን ጥያቄዎችና አስተያየቶች ብቻ ባራት ገጽ እንዳሰፈሩትና ለሚቀጥለው ጠቅላላ ጉባኤ እንደሚያቀርቡ አስረድተዋል :: በስብሰባው መጀመሪያ ላይ ባወያዩ እንደተገለጸው ሊ /መንበሩ ዶክተር ብርሀኑ በስራ መደራረብ ምክንያት እንደማይገኙ ገልጸው የነበረ ሲሆን ወደ ውይይቱ ማብቂያ ላይ ግን ዶክተር ብርሀኑ ተከስተዋል :: አንዳንዶችን ግራ ያጋባቸው ጉዳይ በስራ ምክንያት ዛሬ አይመጡም የተባሉት ዶክተር እንደገቡ "" የምትናገሩትን ሁሉ ስሰማና ስከታተል ነበር አቶ ሙሉነህም አራት ገጽ ማስታወሻ መያዙንም ሳዳምጥ ተደስቻለሁ "" ብለው ሲናገሩ አንዳንዶች እኚህ ሰውዬ አንደ ታምራት ገለታ አይነት መንፈስ አላቸው እንዴ ? ማለታቸውን መገንዘብ ችለናል :: ዶክተር ብርሀኑ በተለይ እሳቸውን በቀጥታ በሚመለከት ጉዳይ ማለትም በተስፋዬ ገ /አብ የመጽሀፍ ሽፋን ላይ ስለሰጡት አስተያየት ኦፍ -ላይን ሆነው አዳምጠውት ስለነበር መልስ በመስጠት ጀምረዋል :: ዝርዝሩን እነሆ :: እቺን ጠቅ ::
እሪሪሪሪሪ ......እሹሩሩሩ .....ሄዋን ሀሳብ አይግባሽ ..
የአብርሀም በጎች ...እኛ እያለንልሽ .....
http://www.ethioonutube.com/video/118/Eshururu-new-version-of-The-late-Ferew-Hailu-song
_________________http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ሀዲስ 1 Joined: 10 Mar 2010 Posts: 1604
Posted: Tue Jan 03, 2012 6:55 pm Post subject: Re: ከዚህም ከዚያም ...ፖሎቲካዊና አገራዊ ውሎዎች ::
ጎሽ ጋሽ ቃሲም
ሰው እንዲህ ስትሰማ ጥሩ ነው ::
ግን እቺን ማሰብ ተስኖህ ዋርካዋን እስካሁን ከጠዋት እስከማታ ስትለቀልቃት መክረምህ እንደኔ መድከምህን መጃጃትህን የሚያሳይ መሰለኝ ::
አይዞኝ በዚህ ቀጥል :: እኛም ግዜ ስናገኝ ገባ እያልን ክፍልህን እንጎበኝልሀለን ::
ሀዲስ
ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው : በዚች ክፍል ውስጥ እለታዊ ዜናዎችን ገጠመኖችን , ፖሎቲካዊ ውሎዎችን , ሳገኝ አካፍልበታለሁ :: ርእሱ ከዚህም ከዚያም ነው ..ያ ማለት ከኢህደጎችም ከኢህደግ ተቃዋሚዎችም ያገኘሁትንና እጄ የገባውን አብረን የምንካፈልበት ነው ማለት ነው :: እስከዛ እቺን ጠቅ ..ያድርጉ ትንሽ አረፍ ካሉ በኌላ እቺን ገጭ ያድርጉ ከመውጣትዎ በፊት አንድ ለመንገድ እቺን ቌ ያድርጉ :: አመሰግናለሁ ::
_________________ what we learn from history is, we do not learn from history.
http://www.isil.org/resources/philosophy-of-liberty-english.swf
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
የተሞናሞነው Joined: 11 May 2011 Posts: 1126
Posted: Wed Jan 04, 2012 3:37 am Post subject:
አንዳንዴ ምሁርነትህ ነሸጥ ሲያደርግህ በምትራቀቅበት ( ) የቋንቋ ባለቤት በሆኑት በአዲሱ የፈረንጆች አመት በአበስ ገበስ ግባሶ ቆሻሻህ ነጭ ለብሰን አረፍ የምንልባትን የዋርካን ስር ከማቆሸሽባቸው ብለህ በአንድ የቆሻሻ ገንዳ ለማጠራቀም ማቀድህ በውነቱ ሊያስመሰግንህ ይገባል ከዚህ በላይ ከአንተ አይጠበቅምና ቆሻሻውን እዚሁ ገንዳህ እያመጣህ አጠራቅምልን
ልጅ ሞንሟናው _________________http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ክቡራን Joined: 04 Mar 2008 Posts: 4372
Posted: Wed Jan 04, 2012 7:34 am Post subject:
ከዚህም ከዚያም አምዳችን ይቀጥላል :: ባለም ላይ በፋየር ዎርክ ( በተለምዶ የሪችት ተኩስ ) ድንቅ ተብሎ በጊነስ ላይ የተመዘገበው የት እንደሆነ ያውቃሉ ? ወዲያ ወዲህ ስል ያገኘሁትን ቪዲዮ ላካፍልዎት :: እጀ መንገዴንም ፋየር ዎርክ እንዴት ይፈጠራል በሚለው ጉዳይ ሀደ ሀደ ብንልስ ..ብዬ አሰብኩ :: ? እነዚህ የምናያቸው ህብረ ቀለማት ከየት የመጡ ናቸው ? ኬምስትሪው እንደሚያስተምረን እነዚህ የተለያዩ ድብልቅ ሜታልስ ( Ca, Al, Na, Li, K , Cu...) ወዘተ ባንድ ላይ ታሽገው ( በኩል ድርሻ ወይንም ፕሮፖርሽን ቢሆን ይመረጣል ) ከውጭ በሚያገኙት ሀይል ( ኢነርጂ ) ""ኤክሳይትድ "" እንዲሆኑ ይደረጋል :: እነዚህ ንጥረ ነገሮች ከራሳቸው ሳይሆን ከውጭ ፓወር ከማግኘትቻው በፊት ያሉበት ስቴት ""ግራውንድ "" ስቴት ሲሆን ኤክሳይትድ ሲሆኑ ግን የኤሌክትሮኖች ዴንስቲ በፊት ይዘውት የነበረበትን ቦታ ለቀው ወደ ሚቀጥለው ቦታ በተለምዶ (ሸል ይባላል በቦሆር ሞዴል ከሄድን ነው ) Quantum Mechanical model ስለ ሸል አያወራም ( electron density or population ) እያለ ይገልጸዋል ...እና እነዚህ ከያዙት ኦርጂናል ቦታ በምርቃና ( ኤክሳይትመንት ) ዘለው ወደ ሚቀጥለው ኦርቢት ይሄዳሉ :: ግን እዛ አይቆዩም ( coz..they don't belong there.. ) እና ወደ ቦታቸው ይመለሳሉ ሲመለሱ መጀመሪያ ኤክሳይት ሲያደርጉ የወሰዱትን ኢነርጂ ይለቃሉ :: ( the same enrgy ነው ሎስና ጌይን የለም ) :: ያ የሚለቀቀው ኢነርጂ ነው ታዲያ ከለር ሆኖ አይናችን ሊያየው የሚችለው :: የሚገርመው ታዲያ እያንዳንዱ ሜታል የራሱ የሆነ ካራክተርስቲክስ ከለር አለው :: ተመሳሳይ ከለር የሚሰጡ ሜታሎች አይኖሩም ጥሩ የፋየር ዎርክ ለማየት ጥሩ የሜታል ቅይጥ ( Metallic proportion ) ግድ ይላል :: ከዚህም ከዚያም ነው ጉዳያችን ብዬ ነው .. ለማንኛውም ቪዲዮውን ልጋብዝዎ የተከበሩ አንባቢ :: መልካም የፈረንጆች አዲስ አመት :: አንዳንዶች መልካም የፈረንጆች አመት ስላልን ብቻ ኢትዮጵያዊነታችንን ይጠራጠራሉ :: ሳቅ በሳቅ የሚያደርገው ጉዳይ ደሞ የነሱ ስም የፈረንጅ ነው :: ኡፕስ ::
http://www.ethioonutube.com/video/120/The-largest-Firework-Display--Guinness-World-Records _________________http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ክቡራን Joined: 04 Mar 2008 Posts: 4372
Posted: Thu Jan 05, 2012 1:01 am Post subject:
ወይ ጉድ .. እዚች ቤት ገባ ብሎ አስተያየት የሚሰጥ አንድም ሰው እኮ ጠፋ !! እናመስግናለን እግዚኤር የእጅህን ይስጥህ አንድ ቤት ክፈት ብለህ እንዲህ ታስረኝ ..!! ዋርካን ከምስራቅ እስከ ምእራብ እንዳልቀወጥናት ...ወየው ወየው ( just kidding..)
መሬት ወደያዘው እውነታ መልስ ስንል ደሞ እነዚህን አበይት ወሬዎች እናገኛለን :-
**ያዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በጥልፍ ስራና ሽመናን እንዲሁም ድወራን ጭምሮ በተለያዩ መስኮች ምርምር ጀመርኩ አለ ::
** የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የአባይ ግድብ የሚያርፍበትን ጉድጔድ ወደ ታች ሲቆፈር ባይናቸው ተመለከቱ ::
** አፍሪካ ውስጥ የሞባይል ተጠቃሚዎች ቁጥር በማራቶን ፍጥነት እያደገ መምጣቱ ተገለጸ የሚሉትንና ሌሎችንም ይዘናል :: እቺን ቀጭ ::
_________________http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ኮኮቴ Joined: 04 Nov 2009 Posts: 1093
Posted: Thu Jan 05, 2012 2:16 am Post subject: Re: ከዚህም ከዚያም ...ፖሎቲካዊና አገራዊ ውሎዎች ::
ክብራን ወንድማችን
ቤት ከፍተህ ብቻህን እየደጋገምክ ስትጽፍ አይቼ ብቸኝነትህ ስላሳዘነኝ ; እኔም "ቤቱ የጋራችን ; ጨዋታው የግላችን ; ይሄው መዋጯችን " ብዬ የአቤ ቶክቻውን ለጠፍኩልህ ... ቤት ለእምቦሳ ለማለት ያህል ጠቅ ተደርጎ የሚገባበት ሌላ ተቀጥላ ቤት ስለሌለኝ
ኮኮቴ
ኦነግ “የማይበጀን ይገንጠል !” አለ
ኢትዮጵያም ደስ አላት !
አቤ ቶኪቻው
abeto2007@yahoo.com
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ቀረብ ብለው ሲከታተሉ ለቆዩ እና የሀገሪቷ ጉዳይ ግድ ይሰጠናል ለሚሉ “ዋና” የአገር ልጆች ታላቅ የምስራች ተሰምቷል። ይህውም አንጋፋው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ኦነግ በይፋ የመገንጠል ሀሳቡን ትቶ ከሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ጋር በመሆን “ችርቻሮ” ለሚወደው ገዢው መንግስታችን “በጅምላው ሞክረን !” ሊለው ቆርጦ መነሳቱን ማወጁ ነው።
የኛ ሰፈር ፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ፤ “ኢህአዴግ ጥሎበት ችርቻሮ ይወዳል። ሲገዛ በብሄር እና በጎጥ፤ ገፋ ሲልም በሀይማኖት እየቸረቸረ ነው።” ይሉታል። ታድያ አሁን አሁን ሁሉም ነቄ ሆነና በብሄር ልቸርችርህ ሲሉት “ውይ ውይ… አያዋጣም ከቦታውም እንዲህ አልመጣም” ማለት ሲጀምር ለገዢው ትልቅ የራስ ምታት ነው ? ይላሉ።
የምር ግን ወዳጄ… ከቦታው እኮ በችርቻሮ አልመጣንም። አይደል እንዴ ? ከዋናው ቦታ ጀምረን እንቋጠር ካልን ኦኮ ሁሉም “የአዳም እና ሄዋን” በሙስሊሙም ቢሆን “የአደምና ሃዋ” ልጅ ነው። ስለዚህ ከቦታው ሲመጣ አንድ ነው። ታድያ አሁን እንከፋፍልህ (ነጠላ ሰረዝ ) እንቸርችርህ (ነጠላ ሰረዝ ) እንሸንሽንህ ቢሉት፤ ከህገወጥ ግንባታ እና ኮንትሮባንድ ንግድ ተለይቶ እንዴት ይታያል ? እናም ትላንት ከኦነግ የተሰማው የአንድነት ጥሪ፤ የችርቻሮ ዘመን ሊያበቃ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለን ደፍረን መናገር እንችላለን ?
ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሰራዊት… ሲያውቅ በድፍረት፣ አሁንም ሲያውቅ በግዴለሽነት፣ አሁንም ሲያውቅ እግዜርን ባለመፍራት፣ እንዲሁም አልፎ አልፎ፤ ሳያውቅ በስህተት በርካታ ብሶቶችን በህብረተሰቡ ላይ እየዘራ ነው ይሉታል። “ይሉታል” ነው ያልኩት። እኔማ ምን በወጣኝ አህአዴግን በክፉ አነሳዋለሁ… ? አንቀባሮ ካገር ያሰደደኝ አይደለምን ? (“ሎል” አሉ የፌስ ቡክ አራዶች ሳቅ በሳቅ ማለት ነው። ቅንፍ ውስጥ ከገባሁ አይቀር… በነገራችን ላይ ብዬ ቀጥላለሁ… በነገራችን ላይ፤ የፌስ ቡክ ወዳጆቼ ከተሰደድኩበት ቀንና ሰዓት አንስቶ እንደምን አላችሁልኝ ? እኔ ከእናንተ መረጃ እየወሰድኩ የወሬ ጥሜንም እየቆረጥኩ ነውና… ደህና ነኝ። እባካችሁ የምንናፍቃትን ሀገር ወሬ በ “እንደወረደ” ቋንቋ በወዳጃማች የጨዋታ ስልት ሁልግዜም አውጉን…ደስም ይለናል። እላለሁ። )
እናልዎ ወዳጄ ብሶት የወለደው ኢህአዴግ በሰዉ ላይ ብሶት እየዘራ ብሶቱንም ሲያሳድግና ሰያፋፋ አብዛኛውን የሀገሪቱ ክፍል በብሶት ምርት ራሱን ችሎ “በቂ” የሆነ ብሶተኛ በየግዜው እየተመረተ ይገኛል። (እባካችሁ በየ አራት ነጥቡ “አሉ”ን እያስገባችሁ አንብቡልኝ። ኋላ ኢህአዴግዬ የወሬው ምንጭ እኔ እንዳልመስለውና “የአገርን መረጃ አሳልፎ በመስጠት” ብሎ እንዳይከሰኝ። ) ከዚህ ከብሶት ምርት ጋር ተያይዞ፤ አንዳንዶች ምን እንደሚሉ ሰምተውልኛል ? “በየግዜው አስመዘገብን የሚባለው አስራ አንድ ነጥብ ምናምን ከመቶ “የብሶት እንጂ የብልጥግና እድገት !” አይደለም።” እያሉ ሲያሸሙሩ ሰምቻለሁ።
የምር ግን ወዳጄ ሀገራችን በግብርና ምርት ከፍ ማድረግ ሲገባን በብሶት ምርት ከአለም ተወዳዳሪ የሌላት ማድረግ ተገቢ ነው እንዴ ? ይህው አሁን በቅርቡ የሰማሁት አንድ አለማቀፍ ሪፖርት እንደሚለው ከሆነ ኢትዮጵያን ደስታ ከራቃቸው ቀዳሚ ሶስት ሀገሮች ውስጥ መድቧታል። ሪፖርቱን ቀለል ባለ ቋንቋ እንዘርዝረው ካልን ሀገራችን እምዬ ኢትዮጵያ ሀዘን ቤት ሆናለች እንደማለት ነው። አረ ምን ይሔ ብቻ ኢትዮጵያችን በሌላ ሪፖርት ላይ ደግሞ የግለሰቦችን መብት በማክበር ረገድ ከአንድ መቶ አስር ሀገሮች አንድ መቶ ስምንተኛ መሆኗ ተዘግቧል።
በርግጥ ባለፈው ግዜ እሳት የላሱት የኢቲቪ ህትመት ዳሰሳ አዘጋጆች ዘጋርድያንን ጠቅሰው በኢኮኖሚ እብደት ከአለም ሀገሮች አንደኛ ብሏታል ሲሉን ነበር። (ታይፕ ገድፊያለሁ መሰል በኢኮኖሚ እብደት ያልኩት እድገት ለማለት ፈልጌ ነው። ይሄ እድገት የሚሉት ቃል ዘላለሙን እብደት ከሚለው ጋር እንደተመሳሰለብኝ ልኖር ነው ማለት ነው ?) በርግጥ የኢቲቪን ወሬ አብሮኝ ሲሰማ የነበረው ወዳጄ ሰዎቹ ሲተረጉሙ ተሳስተው ነው እንጂ ዘጋርድያን አንደኛ ያለን “በአትሌቲክስ ነው” የሚሆነው ብሎኛል። እኔም ለመንግስቴ በመቆርቆር ስሜት እንዴት እንዴት አትሌቲክስን የኢኮኖሚ እድገት ብለው ይተረጉማሉ ? ብለህ ታስባለህ ? ብዬ ብይዘው… ባለፈው ግዜ ወዳጃችን ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ላይ የቀረበበትን ማስረጃ አስታወሰኝ፤ እውነትም፤ ውቤ ለራሱ አባቱ ታመውበት ከውጪ ሀገር ለደወለለት ወንድሙ “ኦፕሬሽኑ ተካሂዷል። ገንዘብ ብትልክልኝ ደስ ይለኛል።” ብሎ ቢናገር ነው… ስልኩን የጠለፉት ጠላፊዎች “ኦፕሬሽን ያልከው የፖለቲካ ኦፕሬሽን ነው !” ብለው የተረጎሙት ? እናም ይቺ የትርጉም ነገር እውነትም እኛ ዘንድ አታስተማምንም። (እኛ ተብሎ የተጠቀሰው የመንግስት ታማኞችን ነው… (ታማሚ አላልኩም !))
አፈር ስሆን ወዳጄ በጨዋታ መሀል ትዝ ብሎኝ ነው ከ ጋሽ ፍቅሩ ኪዳኔ “የፒያሳ ልጅ” መፅሐፍ ላይ ያነበብኳትን የቀድሞ ዘመን “ነጭ ለባሾች” ስራ ልንገራችሁማ… (ለዛሬ ዘመን ልጆች፤ “ነጭ ለባሽ” ማለት ደህንነት ወይም ሰላይ በአራዳ ቋንቋ “ሲለዩ” ማለት መሆኑን እነግራለሁ ) እነሆ ጨዋታው በአዲስ መስመር…
አንዱ የጋሽ ይድነቃቸው ተሰማ አድናቂ የሆነ ወጣት በመጠጥ ቤት ውስጥ ሆኖ “ጋሽ ይድነቃቸውማ የሀገር መሪ የመሆን ብቃት ያለው ሰው ነው !” ብሎ ተናገረ። ይሄኔ ነጭ ለባሽ ሆዬ “ምን ሲደረግ ንጉሱ እያሉ ሌላ ሰው ለመሪነት ብቁ ነው ትላለህ ?” ሲል አንገቱን አንቆ ወሰደው። ወጣቱ የጋሽ ይድነቃቸው አድናቂም “ባደነቅሁ ታነቅሁ” ብሎ ተርቶ፤ ከዛ ግዜ በኋላ መሳቀቅ ጀመረ። ሲሳቀቅ… ሲሳቀቅ አንድ ግዜ የመኪናው መሪ ተበላሽቶ ኖሮ፤ ጥግ አስይዞ ሊያቆማት መከራውን ሲያይ አንድ ወዳጁ ተመለከተውና ጠየቀው… “መኪናህ ምን ሆነችብህ ?” ቢለው ግዜ “የኔ ጌታ ፖለቲካ አታናግረኝ !” ብሎ መለሰለት። አዎና እንዴት ብሎ “መሪው ተበላሽቷል !” ይበለው ?
ሌላም አለ፤ በዛን ግዜ “ንጉስ” የሚባል ሲጋራ ነበር። አለ ጋሽ ፍቅሩ፤ ታድያ “ንጉስ” ሲጋራ በሱቁ የሌለው ነጋዴ “ንጉስ ስጠኝ” ሲሉት “ንጉስ የለም !” ብሎ ደፍሮ መናገር ይፈራ ነበር። ብሎ አጫውቶናል። (ጋሽ ፍቅሩ ላካፈለን የማይጠገቡ ጨዋታዎች ረጅም እድሜ ይሰጠው ዘንድ መርቀን እንቀጥላለን !)
ምን ብለን ነበር ወጋችንን ያቆምነው ? እ… አዎ… ልማታዊ ጋዜጠኞቻችን በትርጉም ስህተት ይሁን “በማን ያገባዋል” ባይነት እንጃ በተለያየ ግዜ “አንደኛ ነን” ቢሉንም ሰዉ ግን “ስንተኛ እንደሆንን እናውቃለን ብንናገር እናልቃለን” በማለት ዝም ብሏል። እየተባለ በከተማው ይወራል። አሉ።
የኔ ነገር አንዱን ስይዝ አንዱን ስጨብጥ እኮ የጨዋታችን ውል ሊጠፋብኝ ነው። ለነገሩ ወግ ምን ውል አለው… ? ዝም ብለን እንቀጥልማ… እናልዎ ብሶት የወለደው ሰራዊት ዛሬም በርካቶችን ሆድ እያስባሰ ነው። በዚህም ጫካ ያለው ጫካ ገብቶ፤ ጫካ የሌለው ጫካ ገንብቶ “አረ በዛ !” ብሎ ትግሉን አጧጡፏል። በበኩሌ ሀገሬ ንግድ እንጂ በተለይ የነፍጥ ትግል እንዲጧጧፍባት አልፈልግም። (በቅንፍም “ነበር” እላለሁ ) ነበር ስትል ምን ለማለት ፈልገህ ነው ? ብሎ ወጥሮ የሚይዘኝ ካለ ለግዜው ዝርዝር ባይኖረኝም ባለፈው ሳምንት የፍትህ ወዳጃችን (እና አለቃችን ) ተሜ ከጣፋት ውስጥ፤
“ምንም የማያውቀውን በሬ
ነካክተው ነካክተው አደረጉት አውሬ !”
ብሎ የከተባትን ግጥም እጋብዛለሁ። የምር ግን ወዳጄ መንግስታችን “በራሱ ላይ የታጋዮች ምልመላ እያከናወነ ነው።” የሚባል ነገር ሰምተዋል ? አይ የሰሙ አይመስለኝም። እርስዎ የሰሙት ብሄረሰብ ለማመጣጠን ተብሎ እየተደረገ ያለውን የወታደር ምልመላ ነው። እኔ የምልዎት ደግሞ ሌላ ነው… ! ለምሳሌ በዛን ሰሞን ርዮት አለሙን መርማሪዋ ቢላት ቢሰራት የሚፈልገውን አልናገር ብትለው ግዜ አይደለም እንዴ…”እንዲህ በአቋምሽ የፀናሽ ከሆንሽ ለምን ጫካ አተገቢም ?” ብሎ ያላት ! ታድያ ከዚህ የበለጠ ምልመላ የት ይገኛል።
ይህንን የሰማ የርሷ አይነት አቋም ያለው ሁሉ እኮ ቆርጦ ጫካ መግባት ቢያቅተው፤ ልቡን ጫካ ውስጥ ደብቆ ኢህአዴግዬን “ልቤ አይስቅልሽም” የማለት እድሉ ሰፊ ነው። ታድያ ታጋይ መመልመል ማለት ይህ አይደለም ? ቆይ እሺ ሰሞኑን በአዋሬ ገበያ ቤቶች መቃጠላቸውን ሰምተዋል አይደል ? ታድያ… በቃጠሎው ቤት አልባ የሆኑትን ነዋሪዎች መንግስት ነብሴ “እናንተ ድሮውንም ህገወጦች ስለነበራችሁ ማደሪያችሁን ፈልጉ… ብሎ ፊት ነስቷቸዋል አሉ። እንኳን ሌላ ቀርቶ የተባረከው ቀይ መስቀል ድርጅት እንኳ፤ “ድንኳን ልስጣቸው” ቢል “አይመለከትህም አይኔ እያየ እነርሱ መጠለያ አያገኙም !” ብሎ መንግስት ተሟግቷል። ታድያ ይሄ በራስ ላይ ታጋይ ከመመልመል ውጪ ምን ይባላል። ራሱ ኢህአዴግን ጫካ አስገብተው ዛሬ መንግስት ያደረጉት እንዲህ እንዲህ አይነት ምክንያቶች መሆናቸውን የሚያስታውስ አንድ ባለስልጣን እንዴት ይጠፋል ? ጎበዝ ይሄ የራስ ህመም ባለስልጠኖቻችን ላይ እየተጫወተባቸው ሳይሆን አይቀርም ? እግዜር ሀኪሙን ይላክልን እንጂ !
የሆነ ሆኖ መንግስታችን ግማሹን ፊት ሲነሳ፣ ግማሹን ንብረት ሲነሳ፣ ግማሹን ድምፅ ሲነሳ ግማሹን… ብቻ በጥቅሉ በታጋይ ላይ ታጋይ እየጨመረ፣ እየጨመረ ዳግም በዛች ራድዮ ጣቢያ “የዘመናት ብሶት የወለደው…” ተብሎ ሲነገርባት ይታየኛል። ያለኝ አንድ ወዳጄ ነው።
እናልዎ… ኦሮሞ ነፃነት ግንባር፣ ግንቦት ሰባት ንቅናቄ፣ ኦጋዴን ነፃ አውጪ ሁሉም በየፊናው “ኢትዮጵያ የጋራ ቤታችን ናት” ሁላችንም ተከባብረን የምንኖርባት አዲስ ኢትዮጵያ እንመሰርታለን ! ብለው እጅ ለእጅ ተያይዘዋል !” የሚለው ወሬ ዋና መነጋገሪያ ሆኗል። እርስዎ ይህንን ሲሰሙ ምን እንደተሰማዎት እንጃ… ! በመንግስቴ ቤት ግን ጠላቶዎ ክው ይበልና ከሽብር የዘለለ “ክውታን” ፈጥሯል አሉ። እኛም እናንት አሸባሪዎች በተናጠል ያሸበራችሁት አንሶ በጣምራ መንግስትን “ክው” ታደርጉ ዘንድ ያስጨከናችሁ እንደምን ያለው ነው ? ብለን ተደንቀናል።
በመጨረሻም 1
ቀዳማዊ እመቤት
የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ባለቤት ወ /ሮ አዜብ መስፍን ሰሞኑን አንድ ስልጣን አስረክበዋል። (ቆይ ቆይ አይደንግጡ… !) ስልጣኑ ምን መሰልዎ፤ “የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች የፀረ ኤድስ ክበብ ነበራቸው። የእርሱ ሊቀመንበር ደግሞ የእኛው እመቤት ነበሩ። ታድያ አሁን እርሱን ስልጣናቸውን ለናሚቢያው እመቤት አስረከቡ የሚል ወሬ ተነግሯል።
ይህ ዜና ሲነገር ምን ተሰማህ አይሉኝም ? ይጠይቁኝ በሞቴ… እውነቱን ለመናገር ጥቃት ነው የተሰማኝ። ምን ሲደረግ ነው ስልጣን ለቀቁ የሚል ወሬ የምሰማው ? ምንም ቢሆን እኮ የእሳቸው ሚስት ናቸው… እንደሚባለው ከሆነ፤ ከጠቅላይ ሚኒስትሩም ይልቅ ቁጡ እና ሀይለኛ “ወንድ የሆነ ይነካኛል !” ባይ ናቸው… (አረ… በኔና በርሶ ብቻ ይቅር እንጂ ለርሳቸውም የሚመለሱ አይደሉም ሲባልም ሰምቻለሁ !) ታድያ እንዲህ ያሉት ሴት ስልጣን ለቀቁ ሲባል መስማቴ በእውኑ አስደንግጦኝ ነበር። ኋላ ላይ ግን ሳስበው አንድ ጥያቄ በአዕምሮዬ መጣ፤ እኔ የምልዎ ቀዳማዊነዎ… ሊቀመንበርነቱን ከለቀቁ በኋላ ሰላም ነዎት ? እንደ ቀድሞ ይበላሉ ? ይጠጣሉ ? እንቅልፍም ይወስድዎታል ? መልሱ “አዎ” ከሆነ እባክዎ ይሄንን ነገር ለክቡርነታቸውም ይንገሯቸው… “ሊቀመንበር ሳይሆኑ መኖር ይቻላል” ይበሏቸው። መልሱ “አይ” ከሆነ ግን በቸሩ መዳኒአለም ይዤዎታለሁ፤ ምንም እንዳይነግሯቸው !
በመጨረሻም 2
ሰማያዊ ፓርቲ
አዲሳባ ወጣት የነበር ጣት የሆኑ ፖለቲከኞች አንድ ፓርቲ አቋቁመዋል። ፓርቲያቸውም በምርጫ ቦርድ እውቅና አግኝቶ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርተዋል። በነገራችን ላይ ይሄ ነገር ሊበረታታ የሚገባው ነገር ነው። አንዳንድ ወጣቶች የፖለቲካ ፓርቲ ሽሽት “ዴይ ፓርቲ” እያዘጋጁ ከህፃናት ተማሪዎች ጋር ሲደንሱ በሚውሉበት በዚህ ዘመን እንዲህ ሀገራዊ ራዕይ ይዞ ፖለቲካ ፓርቲ ማቋቋም ቀላል ነገር አይደለም።
እናልዎ… ይህ ሰማያዊ ፓርቲ በእንግሊዘኛ ሲጠሩት “ብሉ ፓርቲ” ይሉታል። ይህንን የሰማ ከወዳጆቼ ዋና የሆነው ምን አለኝ መሰልዎ… “እነዚህ ልጆች የአባላት ቁጥር እንዲጨምርላቸው ከፈለጉ ፓርቲውን “ብሉ” ብቻ ከሚሉት “ጠጡ” የሚልም ጨምረውበት “ብሉ ጠጡ ፓርቲ” ቢሉት ጥሩ ነበር።” ብሎኛል። የምር ግን ብሉዎች… እንግዲህ ስሙ አንዴ ወጥቷል ባይሆን ፕሮግራሙ ላይ ይጨመርበታ !
ይበሉ ወዳጄ በሚከተለው ምርቃት እንሰነባበት…
የሚያበላ የሚያጠጣ፣ ነገር የማያመጣ፣ ከሀገር የማያባርር፣ በጥበብ የሚያስተዳድር፣ ዘወር በል ሲሉት የሚሰማ፣ ያልሆነ ገገማ፣ ለህዝቡ የሚስማማ… እርሱ ጥሩውን መሪ ይስጠን… በትልቁ አሜን !
አማን ያሰንብተን ! [ b]
ምንጭ :- http://ethiomedia.com/broad/oneg_yemaibejen_ygentel_alle.pdf
ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው : በዚች ክፍል ውስጥ እለታዊ ዜናዎችን ገጠመኖችን , ፖሎቲካዊ ውሎዎችን , ሳገኝ አካፍልበታለሁ :: ርእሱ ከዚህም ከዚያም ነው ..ያ ማለት ከኢህደጎችም ከኢህደግ ተቃዋሚዎችም ያገኘሁትንና እጄ የገባውን አብረን የምንካፈልበት ነው ማለት ነው :: እስከዛ እቺን ጠቅ ..ያድርጉ ትንሽ አረፍ ካሉ በኌላ እቺን ገጭ ያድርጉ ከመውጣትዎ በፊት አንድ ለመንገድ እቺን ቌ ያድርጉ :: አመሰግናለሁ ::
_________________ o-o-o-o-o-o-o-o-o-o-o-o
ቅናት ጮሆ የማይወጣ አጋንንት ነው!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ክቡራን Joined: 04 Mar 2008 Posts: 4372
Posted: Thu Jan 05, 2012 5:39 am Post subject:
ብቻዬን በባዶ ቤት አጥወልጥሎ ሊጥለኝ ሲል ደረስክልኝ ኮኮቴው ወንድማችን :: የአቤን ወጎች ወደድኩት :: ጥሩ ጣፊ ነው :: ይጥፋል :: ( አንዴ ጠበቅ -አንዴ ላላ አድርገህ አንብበው ይሄ ቃል እንደ ሪዞናንስ ነው ( Resonance ) :: ፖሎቲካዊ እይታው የራሱ ነው ቤቱ የጋራ ጨዋታው የግል new ብለህ የለ ... እንደዛ ነው :: መቼም ዘንድሮ ጉድ ይሰማል ...ኦነግ የማይበጀን ይገንጠል አለ ነው ያለው ? .. እኔማ ስምንተኛው ሺ የደረሰ ነው የመሰለኝ ...ገንጣዩ ኦነግ ተገንጣዮችን ሲያባርር ... ጉዱ ሰዲ ጉዲ አፉር ...አለ ካህሳይ እኮ ነው :: አትጥፋ ኮኮቴው ብቻዬን ከምሆን ታዋየኛለህ ...ሰይጣን እንዳይመታኝ ....እንደ አቤ ወጋ ወጋ ... ወገኛ መሆን አማረኝ :: ሰላም :: _________________http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ክቡራን Joined: 04 Mar 2008 Posts: 4372
Posted: Fri Jan 06, 2012 2:00 am Post subject:
እሺ ... እንዴት ናችሁሳ ..ስዞር ውየ አሁን ተከስትኩላችሁ ( ታየሁ , ተገለጽኩ መጣሁ ...ማለት ነው ...ተከስተኩ ማለት ... ትርጉም የኔ ) ታዲያ ባዶ እጄን እዚህ ቤት አልመጣሁም ...እንደ ኮኮቴው ወንድማችን :: እኔም ዛሬ ዜና አለኝ ::
ዜናዎች በዝርዝር ::
** አልሜዳ ጨርቃ ጭርቅ ፋብሪካ ባለፈው አመት 50 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ አስገባሁ አለ :: የአልሜዳ ስራ አስኪያጅ ጨምረው እንዳስረዱት ...ላገር ውስጥ ገቢያ ከምናቀርበው ምርት ባሻገር ላሜሪካ እየሰራን የሚንልክላት ጂንሶች ና ራንግለሮች ዋናውን ገቢያ ይዞልናል ብለዋል :: **
** የመሬት ባለቤት አለመሆን ሀገራዊ ስሜትንና ኢትዮጵያዊነትን እየተፈታተነ ነው ተባለ :: **
ለዝርዝሩ እቺን ጠቅ :: _________________http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ክቡራን Joined: 04 Mar 2008 Posts: 4372
Posted: Fri Jan 13, 2012 7:14 am Post subject:
ጸሀፊና ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ የሱማሌንና የኢትዮጵያን ችግር አነሳስና አፈታት አስመልክቶ ተሞክሯቸውን ለኢሳቱ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ( የሲሳይ ስም ሲነሳ የበይሉል ውቃቢው አብሮ ይነሳል ለምን እንደሆነ ግን እልገባኝም .. ) ሰፋ ያለ ቆይታ አድርገዋል ::
ሙሉጌታ ሉሌ በደርግ ዘመን ሱማሌ ለኢትዮጵያ ምን ጊዜም የማትተኛ ስለነበረችና ታላቅዋ ሱማሌ በሚል አይዶሎጂ ኦጋዴን ሲዳሞንና እስከ ናዝሬት ድረስ ከተመቻት ደሞ ጅቡቲንም ለመጠቅለል ህልም እንደነበራት ገልጸው የጊዜና የድህነት ጉዳይ ሆኖ እንጂ ዛሬም ቢሆን አምስት ኮከብ ባንዲራዋ ላይ ያደረገችው ያቺ ጎስቌላ አገር ጥያቄዋን ማንሳቷ አይቀሬ ቢሆንም ያቶ መለስ አስተዳደር ባንጻሩ የሱማሌን ችግር ከመፍታት ይልቅ እንደውም አባብሶታል ሲሉ ያስረዳሉ :: ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ ምክንያታቸውን ሲያስረዱ በኛ ( በደርግ ) ጊዜ ሱማሌዎች በጎሳ የተከፋፈሉ በመሆናቸውና ርስ በርስ እንደማይስማሙ ስለተገነዘብን በመካከላቸው በጎሳ ልዩነታቸው ውስጥ እየገባን ሰላም እንዳያገኙ እናደርጋቸው ነበር ...ያም ባንጻራዊእንት የኛን ሰላም አስጠብቆት ቆይቷል .. ይሁን እንጂ አቶ መለስ ግን ይሄን አይነት አካሄደ መሄድ ሲገባቸው ለሳቸው የሚመች (አሻንጉሊት ) መንግስት ሱማሌ ውስጥ መሰረቱ ...ያ የሳቸው ሞዴል መንግስት ታዲያ ችግር ፈቺ ሳይሆን ችግር አምጭ ሆነና አረፈው ሲሉ ይተቻሉ :: ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ ስለ ሱማሌና ሱማሌዎች ያስተነቱበትን ቃለ መልልስ ለመስማት እቺን ይጫኑ :: _________________http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
የዘመኑ ልሳን Joined: 07 Jun 2005 Posts: 2930 Location: USA
Posted: Fri Jan 13, 2012 7:44 am Post subject:
ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው : ጸሀፊና ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ የሱማሌንና የኢትዮጵያን ችግር አነሳስና አፈታት አስመልክቶ ተሞክሯቸውን ለኢሳቱ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ( የሲሳይ ስም ሲነሳ የበይሉል ውቃቢው አብሮ ይነሳል ለምን እንደሆነ ግን እልገባኝም .. ) ሰፋ ያለ ቆይታ አድርገዋል ::
ሙሉጌታ ሉሌ በደርግ ዘመን ሱማሌ ለኢትዮጵያ ምን ጊዜም የማትተኛ ስለነበረችና ታላቅዋ ሱማሌ በሚል አይዶሎጂ ኦጋዴን ሲዳሞንና እስከ ናዝሬት ድረስ ከተመቻት ደሞ ጅቡቲንም ለመጠቅለል ህልም እንደነበራት ገልጸው የጊዜና የድህነት ጉዳይ ሆኖ እንጂ ዛሬም ቢሆን አምስት ኮከብ ባንዲራዋ ላይ ያደረገችው ያቺ ጎስቌላ አገር ጥያቄዋን ማንሳቷ አይቀሬ ቢሆንም ያቶ መለስ አስተዳደር ባንጻሩ የሱማሌን ችግር ከመፍታት ይልቅ እንደውም አባብሶታል ሲሉ ያስረዳሉ :: ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ ምክንያታቸውን ሲያስረዱ በኛ ( በደርግ ) ጊዜ ሱማሌዎች በጎሳ የተከፋፈሉ በመሆናቸውና ርስ በርስ እንደማይስማሙ ስለተገነዘብን በመካከላቸው በጎሳ ልዩነታቸው ውስጥ እየገባን ሰላም እንዳያገኙ እናደርጋቸው ነበር ...ያም ባንጻራዊእንት የኛን ሰላም አስጠብቆት ቆይቷል .. ይሁን እንጂ አቶ መለስ ግን ይሄን አይነት አካሄደ መሄድ ሲገባቸው ለሳቸው የሚመች (አሻንጉሊት ) መንግስት ሱማሌ ውስጥ መሰረቱ ...ያ የሳቸው ሞዴል መንግስት ታዲያ ችግር ፈቺ ሳይሆን ችግር አምጭ ሆነና አረፈው ሲሉ ይተቻሉ :: ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ ስለ ሱማሌና ሱማሌዎች ያስተነቱበትን ቃለ መልልስ ለመስማት እቺን ይጫኑ ::
የጋዜጠኛ ሙልጌታ ሉሌ የሱማሌን ጉዳይ በተመለከተ ያደረገውን ውይይት ከግማሽ በላይ ቀን ላይ አድምጬው ስጨርስ ዋርካ ላይ አመጣዋለሁ እያልኩ ነው አንተ የቀደምከኝ :: ከቃለመ ጠይቁ ከገረመኝ መካከል ሱማሌ ከ 100 አመት በፊት የኢትዮጵያ አካል መሆና እና የአካባቢው መካንት ለማዕከላዊው የኢትዮጵያ መንግስት ይገብሩ እንደነበር የተገለጸው ነው ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
menzewu Joined: 25 Dec 2009 Posts: 368
Posted: Fri Jan 13, 2012 8:12 am Post subject:
ሙሉጌታ ሉሌ ታሪካዊ ግንዛቤው ስጥ እንግዲህ ነው . ሀገራዊ ምስጢር በመጠበቅ በኩል ደሞ ቀዳዳ ነው . ይቁንስ ስለ በአሉ ግርማ ፍጻሜ የሚያውቀው ነገር ካለ ቢናዘዝ ለጽድቅም ይሆናል
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
የዘመኑ ልሳን Joined: 07 Jun 2005 Posts: 2930 Location: USA
Posted: Fri Jan 13, 2012 8:38 am Post subject:
small mind discuss people አይነት ሆነብኝ መንዜው ያንተ ነገር :: ጋዜጠኛው ተሳስቷል የምትለው ቦታ ካለ ጠቆም ብታደርግ አሻልም በባዶ ሜዳ አዋቂ ለመምሰል ከምትሞክር ::
menzewu እንደጻፈ(ች)ው : ሙሉጌታ ሉሌ ታሪካዊ ግንዛቤው ስጥ እንግዲህ ነው . ሀገራዊ ምስጢር በመጠበቅ በኩል ደሞ ቀዳዳ ነው . ይቁንስ ስለ በአሉ ግርማ ፍጻሜ የሚያውቀው ነገር ካለ ቢናዘዝ ለጽድቅም ይሆናል
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
menzewu Joined: 25 Dec 2009 Posts: 368
Posted: Fri Jan 13, 2012 2:12 pm Post subject:
አቶ የዘመኑ እኔ አዋቂ ለምሰልም ለመሆንም የማሳየው የለም . በእድሜና በቦታዎች በመገኘት ስላየሁትና ስለማውቀው ነገር ብዙ ሀተታ ሳላበዛ ጠቆም አደርጋለሁ .
ሡማሌን በሚመለከት ሱማሌ በአገርና በመንግስት ደረጃ አሁን አለችበት ሁኔታ እንድትገኝ ያደረጉዋት የውጭ አስተውጻኦዎች ሊኖሩ ይችላሉ . ሙሉጌታ በጊዜው አንዳንድ ሀገራው ምስጥሮችን ማወቅ /መስማት ከሚችበት ቦታ ላይ ነበር . ያንን ህእገራዊ ምስጢር አደባባይ አውጥቶ መዘክዘክ አይገባውም . ወንጀል ነው . በሞት የሚያስቀጣ .
ሌላውን እመለስበታለሁ
ሳን "]small mind discuss people አይነት ሆነብኝ መንዜው ያንተ ነገር :: ጋዜጠኛው ተሳስቷል የምትለው ቦታ ካለ ጠቆም ብታደርግ አሻልም በባዶ ሜዳ አዋቂ ለመምሰል ከምትሞክር ::
menzewu እንደጻፈ(ች)ው : ሙሉጌታ ሉሌ ታሪካዊ ግንዛቤው ስጥ እንግዲህ ነው . ሀገራዊ ምስጢር በመጠበቅ በኩል ደሞ ቀዳዳ ነው . ይቁንስ ስለ በአሉ ግርማ ፍጻሜ የሚያውቀው ነገር ካለ ቢናዘዝ ለጽድቅም ይሆናል
[/quote]