WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home | About us | Advertise with us | Contact us
28ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ -ኢኳቶሪያል ጊኒ እና ጋቦን
Goto page 1, 2, 3  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Jan 17, 2012 5:19 am    Post subject: 28ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ -ኢኳቶሪያል ጊኒ እና ጋቦን Reply with quote

ሰላም ውድ ወገኖቼ :-

በአፍሪቃ ዋንጫ የፍጻሜ ውድድሮች ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ የተሣተፈችው መቼ ነበር ? 1974 .. በሊቢያ በተደረገው 13ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ - ለዚያውም ደረጃዋ ውራ ነበር :: ከዚያ በኋላ ለአፍሪቃ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታዎች ማለፍ የሠማይ ያህል ርቆብን እንገኛለን :: ለማንኛውም 28ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ የፍጻሜ ውድድሮች ከመጪው ቅዳሜ ጥር 12 ቀን (Saturday, January 21, 2012) በጋቦን እና ኢኳቶሪያል ጊኒ የጋራ አዘጋጅነት 24 ቀናት ይከናወናል :: አሥራ ስድስት ቡድኖች 4 ምድቦች ተከፍለው የመጀመሪያውን ዙር ውድድር ያደርጉና ከዚያ ከየምድቦቹ 1 እና 2 የወጡት ለተከታዩ የጥሎ ማለፍ ማጣሪያ ያልፋሉ :: ምድቦቹን ላሣውቃችሁ :-

ምንጭ :- CAF (2012). Orange Africa Cup Of Nations - Groups and Standings.

ምድብ
1 ... ኢኳቶሪያል ጊኒ
2 ... ሊቢያ
3 ... ሴኔጋል
4 .... ዛምቢያ

ምድብ
1 ... ኮት -ዴቯር
2 ... ሱዳን
3 ... ቡርኪና ፋሦ
4 ... አንጎላ

ምድብ
1 ... ጋቦን
2 ... ኒጀር
3 ... ሞሮኮ
4 ... ቱኒዚያ

ምድብ
1 ... ጋና
2 ... ቦትስዋና
3 ... ማሊ
4 ... ጊኒ

የጥሎ ማለፍ ዙር -ሩብ ፍጻሜ
[1] ... የምድብ 1 ከምድብ 2
[2] ... የምድብ 1 ከምድብ 2
[3] ... የምድብ 1 ከምድብ 2
[4] ... የምድብ 1 ከምድብ 2

የግማሽ ፍታሜ
[@1] ... የምድብ [1] አሸናፊ ከምድብ [4] አሸናፊ
[@2] ... የምድብ [2] አሸናፊ ከምድብ [3] አሸናፊ

3 ደረጃ
የምድብ [@1] ተሸናፊ ከምድብ [@2] ተሸናፊ

የፍጻሜ የዋንጫ ጨዋታ
የምድብ [@1] አሸናፊ ከምድብ [@2] አሸናፊ

እስኪ ለእኒህ ጥያቄዎች ግምታችሁን ሥጡ :- በዚህ የአፍሪቃ ዋንጫ
1 .... ከየምድቡ እነማን ቡድኖች የመጀመሪያውን ዙር ውድድር ያልፋሉ ?
2 .... የትኞቹ ቡድኖች ለሩብ ፍጻሜ ያልፋሉ ?
3 .... የትኞቹ ቡድኖች ለግማሽ ፍጻሜ ያልፋሉ ?
4 .... የትኞቹ ቡድኖች ለደረጃ ይጫወታሉ ?
5 .... የትኖቹ ቡድኖች ለዋንጫ ይፋለማሉ ?

ግምታችሁን አሥፍሩና አሸናፊ የሚኖነው ጎበዝ ገማች ከዋርካ ተሣታፊዎች የሚቀርብለት ሽልማት ይኖረዋል ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዘርዐይ ደረስ

ውሃ አጠጪ

Joined: 23 Oct 2004
Posts: 1087
Location: ethiopia

PostPosted: Thu Jan 19, 2012 7:55 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ተድላ :-

ይህን ርእስ በከፈትክበት ቀን አስተያየት ፅፌ ልልከው ስል የዋርካ ጋኔን በላብኝ ::ዛሬ ደግሞ እንደገና ሞራሌ ስለመጣ የኔን ግምት አቀርባለሁ ::

ለመንደርደርያ ያህል :-እኔ እንኳ የአፍሪካን እግርኳስ መከታተል ካቆምኩ የሰነበትኩ ቢሆንም ብዙ ትዝታዎች ግን አሉኝ ::ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ አፍሪካ ዋንጫ ላይ የተሳተፈችው እንዳልከውበ 1974 13ኛው ላይ ነው ::መጨረሻ እንደወጣን ግን አላስታውስም ነበር ::

ለሩብ ፍፃሜ የሚያልፉት

ከምድብ ...............ሴኔጋልና ዛምቢያ

ከምድብ ...............ኮት ቭዋርና አንጎላ

ከምድብ ..............ሞሮኮና ቱኒዚያ

ከምድብ .............ጋናና ማሊ

ሩብ ፍፃሜ [/i]

1)ሴኔጋል xአንጎላ

2)ኮት ቭዋር xዛምቢያ

3)ሞሮኮ xማሊ

4)ጋና xቱኒዚያ

ግማሽ ፍፃሜ [/b]

1)ሴኔጋል xጋና

2)ኮት ቭዋር xሞሮኮ

3 ደረጃ

ሴኔጋል xሞሮኮ :-ሞሮኮ 3 ደረጃ ይይዛል :.የዋንጫ

ጋና xኮት ቭዋር

ጋና የዋንጫው ባለቤት ይሆናል !

*ቅደም ተከተሉን እንዳላሳሳትኩ ተስፋ አደርጋለሁ ::

ይህ ግምት የጨዋታን ችሎታ ብቻ ሳይሆን የየአገሮቹን ኢኮኖሚያዊ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን በመመርመር የተቀናበረ Laughing
_________________
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu Jan 19, 2012 10:20 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

ሰላም ዘርዐይ ደረሰ :-

የአፍሪቃን ዋንጫ ውድድሮች ባትከታተል አልፈርድብህም : እኛ ተመልካች እንጂ ተሣታፊ ከሆንን ረዥም ዓመታት ተቆጥረዋልና ! አሁን አሁን ደግሞ ዋና ዋና ተጫዋቾች ለክለባቸው የሚያደርጉትን መስዋዕትነት በአፍሪቃ ዋንጫ ለአገራቸው ቡድን ስለማያሣዩ ውድድሩ ያን ያህል አይስብም ::

ስለ አፍሪቃ ዋንጫ አንዳንድ አስገራሚ ታሪኮች የሊብሮ ጋዜጣ አዘጋጅ ገነነ መኩሪያ ቀምሞ ያቀርበዋል :: ስለዚህ የእርሱን ትንታኔ ብትከታተል ብዙ ዕውቀት ታገኛለህ :: እስኪ ለቅምሻ ያህል ዛሬ የለጠፈው እነሆ ::

ምንጭ :- ገነነ መኩሪያ : ሊብሮ : ሐሙስ ጥር 10 ቀን 2004 .. :: የአፍሪቃ ዋንጫ ::

Quote:
የአፍሪካ ዋንጫ

1942 . ሄሊኒካ የተባለ ቡድን ወደ አዲስ አበባ መጣ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በክለብ ደረጃ ለመግጠም አዲስ አበባ የመጣ ቡድን ነው፡፡ ይህ ቡድን ነዋሪነቱ በግብፅ ሆኖ አሌክሳንደሪያ ከተማ የሚኖሩ የግሪክ ማህበረሰብ የቋቋሙት ቡድን ነው፡፡ ይህ ቡድን ወደ አዲስ አበባ እንዲመጣ ያመቻቸውና ወጪውን የሸፈነው ኦሎምፒያ አካባቢ የሚኖሩ የኦሎምፒያኮስ ቡድን አባላት ናቸው፡፡ በዋነኛነት ትልቁን ሚና የተጫወተው ዲሚትሪ ስጎሎምቢስ ነበሩ፡፡ (እኚህ ሰው 26 ዓመት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባል ከመሆናቸውም ሌላ 3ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቡድናችን ዋንጫ ሲያገኝ ቡድን መሪ ነበሩ፡፡ አሁንም በአሜሪካ ይኖራሉ፡፡ ) ጨዋታው በኢንተርናሽናል ዳኛ መመራት አለበት ስለተባለ ከግብፅ ስማኤል ካሌብ የተባለ ዳኛ እንዲመጣ ተደረገ፡፡ ( ይህ ዳኛ የሲውድን ቡድንም ሲመጣ እንዲዳኝ ተደርጓል፡፡ ) የኛ ሰዎች ውድድሩ ስለጣማቸው ግጥሚያው እንዲቀጥል ውይይት ማድረግ ፈለጉ፡፡ የፌዴሬሽኑ ተመራጭ የሆኑ /ስላሴ ኦዳ ከቤተሰባቸው ጋር ተመካከሩ፡፡ የኦዳ ቤተሰብ ማለት /ስላሴ ኦዳ፣ ቀኛዝማች /መስቀል ኦዳ ፊታውራሪ /የስ ኦዳ ለቡድኑ የእራት ግብዣ አደረጉ፡፡ ኢትዮጵያና ግብፅ አፍሪካን የሚወክል ውድድር ለምን አያካሂዱም ተባለ፡፡ ከበደ ቶምፖሊኖ ተፈሪ ሻራ፣ አመለወርቅ /ዜና ፣ይድነቃቸው ተሰማ፣ አማን አንዶም ውይይቱን አጧጧፉት፡፡ ከግብፅ ፌዴሬሽን ጋር መልክት ተለዋወጡ ነገሩ እየዳበረ ሄደ ፡፡ ውድድሩን ለመጀመር ሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች በቀኝ ግዛት ስር ስለነበሩ የራሳቸው ብሔራዊ ቡድን ስለሌላቸው እነሱን መቀላቀል አልተቻለም፡፡ ከኢትዮጵያ ወገን ሀሳቡን የጠነሰሱት ነገሩን ገፉበት፡፡ 1944 የኢትዮጵያ ቡድን ወደ ግሪክ ሄደ፡፡ አውሮፓ እየመጣችሁ ከምትጫወቱ ለምን አፍሪካ ውስጥ ቡድኖችን አትጠሩም ተባለ፡፡ 1948 የሱዳን ቡድን ጥሪ ተደረገለት አሁንም ግብዣ ተደረገና ሱዳን በትላንቱ ሀሳብ ተስማማ፡፡ 1 ወር በኋላ በፖርቱጋል ሊዝበን የፊፋ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ የጠነሰሰችውን ሀሳብ ሱዳንና ግብፅ አንስተው ደቡብ አፍሪካ ተቀላቀለች፡፡ 8 ወር በኋላ ካርቱም ላይ ተገናኙ፡፡ ደቡብ አፍሪካ ከመጀመሪያውም ኢትዮጵያ እንድትሳተፍ አልፈለገችም ጉባኤው ተካሄደ፡፡ 2 ቀን በኋላ ውድደሩ እንዲካሄድ ተወሰነ፡፡ 4 ቡድኖች እጣ ወጣ፡፡ ግብፅ ከሱዳን ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪካ ይጫወታሉ፡፡ አሸናፊዎቹ ለዋንጫ ያልፋሉ፡፡ ኢትየጵያ ደቡብ አፍሪካን ጥቁርና ነጭን መቀላቀል አለባችሁ ብላ ከሰሰች፡፡ ደቡብ አፍሪካም የሀገሬ ህግ አይፈቅደም አለች፡፡ በዚህ የተነሳ ከውድድሩ ተሰናበተች፡፡ ደቡብ አፍሪካ መጀመሪያም ኢትዮጰያን የፈራችው ለዚህ ነበር፡፡ ካፍን ለመጀመሪያ ጊዜ በፕሬዘዳንትነት የመሩት የግብፁ አብዱል አዚዝ ሳለሚ ናቸው፡፡ ከሁለት ዓመት በኋላ ደግሞ የግብፁ ጀነራል አብዱል አዝዝ ሙስጠፋ ሲሆን 10 ዓመት መርተዋል፡፡ 3ተኛነት የሱዳኑ ዶክተር አብድልሀሊም መሐመድ ሲሆኑ 4 ዓመት መርተዋል፡፡ 4ተኛነት ኢትዮጵያዊ ይድነቃቸው ተሰማ 16 ዓመት መርተው ነበር ለአንድ ዓመት / ሀሊም በጊዜያዊነት ያዙና በምርጫ 1980 . ጀምሮ ኢሳህ ሀያቱ ስልጣን ላይ ይገኛሉ፡፡

የአፍሪካ ዋንጫ እውነታና ትዝታ

- በአፍሪካ ዋንጫ 3 ጊዜ በተከታታይ ዋንጫ ያመጣ አሰልጣኝ የግብፅ ሐሰን ሸሃት ነው፡፡ ሸሃት 10ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አዲስ አበባ ላይ ከጊኒ ጋር ጎል አስቆጥሯል፡፡ ኢትዮጵያ ከውድድር ስትሰናበት ትልቁን ሚና ያሳየውም እሱ ነው፡፡

- በዘንድሮ 28ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ መስራቾች ኢትየጵያና ግብፅ አይሳተፉም፡፡ ሱዳን ብቻ ትገኛለች፡፡

- በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያውን ግብ ያስቆጠረው የግብፅ ራፋት ነው፡፡ 100ኛውን ጎል ያስቆጠረው ደግሞ ሉቻኖ ባሳሎ ነው፡፡ ሁለቱም በሪጎሬ የተገኙ ናቸው፡፡ ለራፋት ሪጎሬውን የሰጠው ኢትዮጵያዊ ዳኛ ነው፡፡ ለሉቻያኖ ደግሞ ረጎሬውን የሰጠው የግብፅ ዳኛ ነው፡፡

- 12ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ጀምሮ በተለያየ ጊዜ የምስራቅ አፍሪካ ሐገሮች ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ ችለዋል፡፡ ሁለት ሆነው የገቡበት ጊዜ የለም፡፡ አንዳቸውም ግን ከምድባቸው አልፈው አያውቁም፡ ጨዋታውንም አያሸንፉም፡፡ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሱዳን፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያ ይጠቀሳሉ፡፡

- ብዙ ፋይናል ላይ የተገኘ ተጫዋች አራት የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘው የግብፅ ኢብራሂም ሐሰን ነው፡፡

- ብዙ ጊዜ ለዋንጫ መድረስ የቻሉ ግብፅና ጋና ናቸው፡፡ ሁለቱም 8 ጊዜ ለዋንጫ ደርሰዋል፡፡ ግብፅ 8 7ቱን አግኝቷል፡፡ አንድን ጊዜ ያስጣለቻት ሐገር ኢትዮጵያ ናት፡፡ ለሌሎቹ ግን እጅ አልሰጠችም 3ተኛነት ካሜሩንና ናይጄሪያ እኩል 6 ጊዜ ያህል ለዋንጫ ቀርበዋል፡፡ ካሜሩን 6 ሁለቱን ብቻ ነው ያጣችው፡፡

- በአፍሪካ ዋንጫ በሐገሮቻቸው ለዋንጫ ተገናኝተው የተሸናነፉት ናይጄሪያና አልጄሪያ ናቸው፡፡ 12ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ናይጄሪያ በሐገሩ አልጄርያን 30 አሸንፎ ዋንጫ ሲወስድ 17ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ አልጄሪያ ሐገሩ ላይ ናይጄሪያን 10 አሸንፎ ዋንጫ ወስዷል፡፡

- በግለሰብ ደረጃ በአፍሪካ ዋንጫ ብዙ ከተጫወቱት ውስጥ አንድም ጨዋታ ሳይቀየር በተከታታይ 26 ጨዋታ ያደረገው የናይጄሪያው አጥቂ ሙዳ ላዋል ነው፡፡ 10ኛው እስከ 15ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ተጫውቷል፡፡ በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያውን ጨዋታ ያደረገው ድሬዳዋ ላይ ነው፡፡ ጊዜውም 1968 . ነው፡፡ ናይጄሪያ ከነሞሮኮ ጋር ድሬዳዋ ላይ ነው የተመደበው፡፡ በውድድሩ 3ተኛ ነው የወጣው፡፡ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝቷል፡፡ አዲስ አበባ ላይ ግብፅን 3 2 ረታው የነሐስ ሜዳሊያ ሲወስዱ የማሸነፊያውን ግብ ያስቆጠረው እሱ ነበር፡፡ ከጨዋታ በኋላ ማሊያውን አውልቆ ጥላ ፎቅ ላሉት ወርውሮ ሰጥቷቸዋል፡፡ ይህ ማሊያ ያለው ማን እጅ ላይ ይሆን ?

- በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያውን ጨዋታ የመራው ሻለቃ (በኋላ ኮነሬል ) ገበየሁ ዱቤ ነው፡፡ ገበየሁ ኢንተርናሽናል ዳኛ አልነበረም፡፡ ይህንን ካጫወተ 10 ዓመት በኋላ ነው የፊፋን ባጅ ያገኘው፡፡ ለማንኛውም በአፍሪካ ዋጫ የመጀመሪያውን ፊሽካ የነፋው የኢትዮጵያ ወታደር ነው፡፡

- በአንድ አፍሪካ ዋንጫ 10 ግብ የደረሰ ሰው ጠፍቷል፡፡ ከፍተኛው 9 ጎል ነው፡፡ ይህንንም ያስቆጠረው የዛየሩ ሙላንባ ነው፡፡ ጊዜውም 9ነኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነው፡፡ አነስተኛ ግብ የተቆጠረው 16ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሲሆን ኮከብ ግብ አግቢ የተሸለመው በሁለት ግብ ነው፡፡ የካሜሩኑ ሚላ የአልጄሪያው፣ ቤሉሚ የአይቮሪኮስቱ ትራዊሪ እና የግብፁ አብድል ሐሚድ በጋራ ሁለት ጎል በማስቆጠር ኮከብ የሆኑበት ነው፡፡

- በአፍሪካ ዋንጫ ከፍተኛ ጋዜጠኞች በአንድ ጊዜ የተገኙበት 23ተኛው ማሊ ላይ ሲሆን 1100 ጋዜጠኞች ለመዘገብ ገብተዋል፡፡ ዝቅተኛው ደግሞ 3ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ አዲስ አበባ ላይ አምስት ጋዜጠኞች ወደ ሐገር ውስጥ የገቡበት ነው፡፡ ግብፅ 3 ቱኒዚያ 2፡፡

- ከምስራቅ አፍሪካ ሐገሮች በአፍሪካ ዋንጫ ብዙ በመሳተፍ ኢትዮጵያ የተሻለ ሪከርድ አላት፡፡ 9 ጊዜ ተገኝታለች ከዘጠኙ ማጣሪያውን ያለፈችው በሁለቱ ብቻ ነው፡፡ ሌላውን በአዘጋጅነት በክስ ሌላው ደግሞ ቀደም ሲል ማጣሪያ ያለመደረጉ ነው፡፡ በጠቅላላ 24 ጨዋታ አድርጋ 7ቱን አሸንፋለች፡፡ ከሰባቱ 6ቱን ያሸነፈችው አዲስ አበባ ላይ በተደረገ ውድድር ነው፡፡ሁለት ጊዜ አቻ ወጥታለች፡፡የተቀረውን ተሸንፋለች፡፤ 53 ጎል ተቆጥሯል፡፡ አብዛኛው ጎል የገባው 1ኛው እስከ 7ተኛው ባለው የአፍሪካ ዋንጫ ነው፡፡

- በአፍሪካ ዋንጫ ከኢትዮጵያ ወገን የመጨረሻውን ጎለ ያስቆጠረው መሐመድ (ሸዳድ ) ነው፡፡ ጨዋታው ተደረገው ከግብፅ ጋር ነው፡፡

- በሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የዋንጫው ክዳን ጠፍቶ 3 ቀን ሙሉ ሲፈለግ ጣይቱ ሆቴል ተገኝቷል፡፡ ግብፆች መጀመሪያ መጥተው ያረፉት እዛ ነበር ክዳኑ ተሰረቀ ብለው አመልክተው ነበር፡፡ ባይገኝ ኖሮ የዚያን ቀን ያለክዳን ነበር ለኢትዮጵያ የሚሰጠው፡፡

- በአፍሪካ ዋንጫ ምንም ግጥሚያ ሳታደርግ ለዋንጫ የደረሰቸው ኢትዮጵያ ብቻ ነች፡፡ የተገኙት 4 ቡድኖች ናቸው፡፡ ግብፅ ከሱዳን ኢትዮጵያ ደግሞ ከደቡብ አፍሪካ ተደለደሉ፡፡ደቡብ አፍሪካ ጥቁርና ነጭ ተጫዋች አልቀላቅልም በማለቷ ከውድድር ተሰናበተች፡፡ ኢትዮጵያ ከማንም ሳትጫወት ለዋንጫ ደረሰች፡፡

- በአፍሪካ ዋንጫ ፍፃሜ በአንድ ጨዋታ 4 ጎል ያገባ ብቸኛ ተጫዋች የግብፁ አዲዳየብ ነው፡፡ እስካሁን ይህ ሪከርድ አልተሰበረም፡፡ ጊዜውም 1ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሲሆን ግቡንም ያስቆጠረው ኢትዮጵያ ላይ ነው፡፡ ይህ ተጫዋች 6ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ዳኛ ሆኖ አዲስ አበባ መጥቷል፡፡ ለእኛ ቡድን ሪጎሬ ሰጥቷል፡፡ ምናልባት ሪጎሬ ካልተሰጣቸው አያገቡም ብሎ ይሆን ?

- በዘንድሮ የአፍሪካ ዋንጫ ቀደም ሲል ዋንጫ ካነሱት ውስጥ ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ካሜሩን ፣ኮንጎ ብራዛቢል፣ ኮንጎ ኪንሻሳ፣ አልጄሪያ ናይጄሪያ አይሳተፉም፡፡ ዋንጫ ወስደው እዚህ ውድድር ላይ የተገኙት አይቮሪኮስት፣ቱኒዚያ ጋናና ሞሮኮ ናቸው፡፡

- በአፍሪካ ዋንጫ ብዙ ሪኮርድ ያላት ኢትዮጵያ ናት፡፡ በአንድ ጨዋታ 6 ጎል ተቆጥሯል፡፡ አንድ ተጨዋች ለብቻው 5 አግብቷል (ፓኩ ) ፡፡ በምድብ ጨዋታ 12 ጎል የተቆጠረበት ኢትዮጵያ ናት፡፡ በፋይናል ጨዋታ 4 ጎል ልዩነት የተሸነፈ ሐገር የለም፡፡ ኢትዮጵያ ብቻ ናት፡፡ እነዚህ ሁሉ ሪከርዶች አሰከአሁን አልተሰበሩም፡፡ ይህን ሪከርድ ለቀጣዩ ትውልድ አሰረክበው የሄዱ ተጨዋቾች ‹‹ ፉትቦል በእኛ ጊዜ ቀረ›› ይላሉ፡፡

- በፋይናል ናይጄሪያ ካሜሩንን አልቻለውም፡፡ 3 ጊዜ ለዋንጫ ተገናኙ፡፡ አቢጃን ላይ 31 ካዛብላንካ ላይ 10 ሌጎስ ላይ ደግሞ በመለያ ምት ካሜሩን ዋንጫውን ወስዷል፡፡ ናይጄሪያ መቼ ይሆን በፋይናል ካሜሩንን የሚረታው ?

- በአፍሪካ ዋንጫ በአቻ ውጤት ዋንጫ የተገኘው 10 ነው፡፡ ሞሮኮና ጊኒ አዲስ አበባ ላይ ለዋንጫ ቀርበው አቻ በመለያየታቸው ሞሮኮ ዋንጫ ወሰደ፡፡ አራቱም ቡድኖች በዘር እንዲጫወቱ መደረጉ ነው፡፡

- በአፍሪካ ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ በቀይ የወጣው ነጸረ ወልደስላሴ ነው፡፡ ጊዜው 1ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነው፡፡ ዳኛው ጨዋታው ሊጠናቀቅ አካባቢ ሰዓት በትክክል አልያዝክልንም በሚል ጭቅጭቅ ከሜደ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡

- በአፍሪካ ዋንጫ ብዙ ተመልካች የተገኘው 15ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ካይሮ ላይ ነው፡፡ የተገናኙት ግብፅና ካሜሩን ናቸው :: በፋይናል የተገኘው 120 ተመልካች ካይሮ ሲሆን እዚያው ካይሮ ላይ 9ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አነስተኛው ዛየርና ዛምቢያ ባደረጉት የዋንጫ ጨዋታ 2 ተመልካች ተገኝቷል፡፡

- የአፍሪካን ዋንጫ ደጋግመው መስጠት የቻሉት ጃንሆይ ናቸው፡፡ 3ተኛውና 6ተኛውን ለአሸናፊዎቹ ሸልመዋል፡፡

- ከኢትዮጵያ ወገን በአፍሪካ ዋንጫ በብቸኝነት ኮከብ ግብ አግቢ ተብሎ የተሸለመው መንግሥቱ ወርቁ ብቻ ነው፡፡

- በአፍሪካ ዋንጫ በጋዜጠኞች ከኢትዮያ ወገን በጋዜጠኞች ኮከብ ተብለው የተመረጡት 6ተኛው ሉቻኖ 10ኛው ደግሞ ካሣሁንና ቡከር ናቸው፡፡

- በአፍሪካ ዋንጫ ብዙ ያጫወተ ዳኛ የሞርሸየሱ ሊም ነው፡፡ 14 ጨዋታ በአምስት የአፍሪካ ዋንጫ መርቷል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አንድ ጊዜ ፋይናሉን ዳኝቷል፡፡ በሁለተኝነት ደረጃ የተቀመጠው ተስፋ /የሱስ ሲሆን 7 የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፏል፡፡ ሁለት ጊዜ ፋይናል መርቷል፡፡ ተስፋዬ ይህን ጨዋታ ያጫወተው በኢትዮጵያ ስም ነው፡፡

- በአፍሪካ ዋንጫ በተከታታይ ለዋንጫ መቅረብ የቻለው ጋና ነው፡፡ በአራተኛ፣ በአምስተኛ፣በስድስተኛ እና በሰባተኛው ነው፡፡

- የአፍሪካ ዋንጫ ምዕራቡ በመውሰድ ይመራል፡፡ካሜሩን 4 ጊዜ ጋና 4 ጊዜ ናይጄሪያ 2 ጊዜ ዛየር 2 ጊዜ አይቮሪኮስት ኮንጎ ብራዛቢል አንድ አንድ ጊዜ በድምሩ 14 ዋንጫ ወስደዋል፡፡ ሰሜን አፍሪካ ግብፅ 7 ቱኒዚያ ሞሮኮና አልጄሪያ አንድ አንድ በድምሩ 10 ጊዜ ወስደዋል፡፡ ምስራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያና ሱዳን 1 ጊዜ አስገኝተዋል፡፡ ደቡብ አፍሪካ 1 ጊዜ ወስዷል፡፡

- ጋናና ግብፅ 2 ጊዜ ወስደው ለሶስተኛ ጊዜ ዋንጫውን ለማስቀረት የመጡት ኢትዮጵያ ላይ ነበር፡፡ ግብፅን 3ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ አስጣለቻት፡፡ ጋናን ደግሞ 6ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ዛየር በፍፃሜው አስጣለው፡፡

- የአፍሪካ ዋንጫ 1949 . ነው የተጀመረው፡፡ ቁጥሩ ጎደሎ ነው ውድድሩ በየሁለት ዓመቱ ስለሚካሄድ ቀጣዩ 1951 . ተካሄደ፡፤ 3ተኛው 1953 . በጥር ወር አዲስ አበባ ላይ ይካሄዳል ተብሎ ሲጠበቅ በታህሳስ 5 ክብር ዘበኛ በመራው መፈንቅለ መንግሰት በፀጥታ ምክንያት ውድድሩ ወደቀጣዩ ዓመት ተላለፈና ሙሉ ቁጥር ላይ ተቀመጠ፡፡ ይህም ከሶስተኛው አፍሪካ ዋንጫ ጀምሮ በሙሉ ቁጥር ቀጥሏል፡፡ 2013 ጀምሮ ተመልሶ ጎዶሎ ቁጥር ላይ ይገባል፡፡ያኔ ክብር ዘበኛ ነው ያተራመሰው አሁን ግን ከዓለም ዋንጫ ጋር እንዳይገናኝ ነው ወደ ጎደሎ የመለሱት፡፡

- በአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ እስካሁን ከፍተኛ ጎል የተቀጠረው ኢትዮጵያ ላይ ነው፡፡ 3ተኛው አፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ግብፅን 42 ያሸነፈችበት ሲሆን በድምሩ 6 ጎል የተቆጠረበት ነው፡፡ እስካሁን በፍፃሜ ጨዋታ 6 ጎል የተቆጠረበት ጨዋታ የለም፡፡

- 3ተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ጫዋታ ጃንሆይ አርፍደው በመምጣታቸው ውድድሩ ዘግይቶ ነው የተጀመረው፡፡ ቡድኖቹ ሁለት ለሁለት ሆነው 90 ደቂቃውን በመጨረሻቸው 30 ደቂቃ ተጨመረ፡፡ መንግስቱ ወርቁ 4ተኛ ጎል ሲያገባ ስለመሻ ለአይን ያዝ አድረጎ ነበር፡፡ በዚን ጊዜ አዲስ አበባ ስታዲየም መብራት ስላልነበረው የግብጹ በረኛ ሰለጨለመ አይታየኝም ብሎ ባነሳው ጥያቄ የግብፅ ተጫዋቾች ስለመሸ አንጫወትም በሚል ባነሱት ጥያቄ ጥቂት ደቀቃ ተቋርጦ ነበር፡፡ ጨዋተወን ለማስደገም የአምስት ቀን ጠቅላላ ወጪውን መቻል አለባቹ ስለተባለ ግብፅም አንገራገረ፡፡ ኬኒያዊው ዳኛ ብሩክስ ኳሱን አስጀመረ ወዲያውኑ ፊሽካ ነፋና አልቋል አለ፡፡

- የዛየር ቡድን 10ኛው አፍሪካ ዋንጫ ወደ ኢትዮጵያ መጣ፡፡ የተመደበው ድሬዳዋ ላይ ነው፡፡ ዝንጀሮ በሳጥን ሰብስበው ነው የመጡት፡፡ የከተማው ሰው ዝንጀሮ እንደሚበሉ ሰማ፡፡ ከኛ ባህል አንፃር ስለማይሄድ ተቃውሞ ገጠማቸው፡፡ ያረፉበት ሆቴልም በነሱ የተነሳ ገበያ እንዳያጣ የኔን ድስት እንዳትነካ የምሰራበትም ኩሽና እንዳትገባ፡፡ ዛየር ጊቢ ውስጥ ድንኳን ተክሎ ድስት ገዝቶ ኩሽና ሰርቶ ዝንጀሮ ጠብሶ መብላት ጀመረ፡፡ የዛየር ቡድን በዚህ የተነሳ ደጋፊ አልነበረውም፡፡ አንዳንድ ተመልካቾች ከደንገጎ ጋራ ዝንጀሮውን ጨረሰ በማለት ረገመው መሰለኝ ከዚያ በኋላ ዋንጫ አግኝቶ አያውቅም፡፡ ዛየር ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫ ያገኘው 6ተኛ አፍሪ ዋንጫ ኢትዮጵያ ላይ ነው፡፡

ይቀጥላል፡፡

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Jan 22, 2012 12:17 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች :-

ዛምቢያ በአፍሪቃ ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ ሴኔጋልን 2 1 አሸንፏል :: ዛምቢያዎች ጎሎቹን ያስቆጠሩት በመልሶ ማጥቃት የአጨዋወት ሥልት በመታገዝ 12ኛው ደቂቃ በኢማኑኤል ማዩካ እና 20ኛው ደቂቃ በሬንፎርድ ካላባ አማካይነት ነበር :: ሴኔጋል በባዶ ከመሸነፍ የምታድነውን የማስተዛዘኛ ጎል በሁለተኛው ግማሽ ዳሜ ንዶዬ 74ኛው ደቂቃ በጥሩ ሁኔታ በጎሉ በቀኝ ጎን አሣርፏል :: ሴኔጋል ጉልበት በተቀላቀለበት አጨዋወት አብዛኛውን የኳስ ባለቤትነት ቢይዝም ዛምቢያዎች ጠንክረው በመከላከልና በመልሶ ማጥቃት አሸናፊነቱን ወስደዋል :: የካሜሩኑ አጫዋች የኃይል አጨዋወትን ሙሉ በሙሉ የደገፉ ይመስላል :: በተለይ ሴኔጋሎች የዛምቢያን በረጃ ሣይቀር በእርግጫ እየተራገጡ ዳኛው አንድም የቢጫ ወይም ቀይ ካርድ ሣያሣዩ ጨዋታው ተጠናቋል ::

የዛምቢያ ቡድን በሚያዝያ 19 ቀን 1985 .. ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከዚሁ ከሴኔጋል ቡድን ጋር ለነበረባቸው ግጥሚያ ወደ ዳካር ሲያመሩ አውሮፕላናቸው ጋቦን ማረፍ ነበረበት :: ያልታደለ ቡድን ተጫዋቾቹ በአውሮፕላን አደጋ ከጋቦን ሲነሱ በሙሉ አለቁ :: ያጋጣሚ ነገር የቡድኑ አምበልና ኮከብ ተጨዋች ካሉሻ ቡዋሊያ በዚያ አውሮፕላን ላይ አልነበረም :: እርሱ ተርፎ ከዚያ በኋላ ለረዥም ጊዜ ተጫውቷል :: ነገር ግን የዛምቢያ ቡድን ከዚያ በኋላ ለማገገም ረዥም ዓመትት ወስዶበታል :: አሁን እንደገና እየተነሱ ይሆን Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes

ምንጭ :- CAF 29th Orange Cup of Nations. Zambia Vs. Senegal - Match Report.

በመክፈቻው ጨዋታ አዘጋጇ አገር ኢኳቶሪያል ጊኒ ሊቢያን 1 0 አሸንፋለች ::

ምንጭ :- CAF 29th Orange Cup of Nations. Equatorial Guinea Vs. Libya - Match Report.

መልካም የአፍሪቃ ዋንጫ ጨዋታዎች ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሻቬዝ -x

ኮትኳች

Joined: 17 Nov 2009
Posts: 200

PostPosted: Sun Jan 22, 2012 12:03 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ተድላ

ጨዋታዎቹ የሚካሄዱበትን ሰአት በተለይ ዋና ዋና የሚባሉትን በኛ አቆጣጠር GMT+3 ብትገልጽልን ለመከታተል ይረዳን ነበረ እንዲሁም በምን መንገድ ላይቭ ልንከታተል እንደምንችል ብትጠቁመን በጣም አመሰግናለው

አሸናፊውን ገምቱ ላልከው ግን መቸም እኔ የረጀም አመታት ፐርፎርማንሳቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት ዋንጫው ከጅቡቲ አያልፍም እላለው Very Happy ስልህ አቋማቸውን በአንድ ጨዋታ እንኳን ሳናይ መገመት ይከብዳል ለማለት ነው

ሰላም ሁን
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Jan 22, 2012 11:14 pm    Post subject: Reply with quote

ሻቬዝ -x እንደጻፈ(ች)ው:
ሰላም ተድላ

ጨዋታዎቹ የሚካሄዱበትን ሰአት በተለይ ዋና ዋና የሚባሉትን በኛ አቆጣጠር GMT+3 ብትገልጽልን ለመከታተል ይረዳን ነበረ እንዲሁም በምን መንገድ ላይቭ ልንከታተል እንደምንችል ብትጠቁመን በጣም አመሰግናለው

ጋቦን እና ኢኳቶሪያል ጊኒ GMT+1 የሰዓት ክልል ውስጥ ናቸው :: ለማንኛውም ሙሉ ፕሮግራሙ ይኸውልህ ::
ምንጭ :- CAF, Jan2012. Orange Cup of Nations - Fixtures.

ውድድሮቹን በቀጥታ ለመከታተል ይኼን አድራሻ ሞክር :-

የቀጥታ ቲቪ ሥርጭት ::
ከቻናሎቹ መካከል አንዱ ጨዋታዎችን በቀጥታ ያስተላልፋል ::

[quote"ሻቬዝ -x"]አሸናፊውን ገምቱ ላልከው ግን መቸም እኔ የረጀም አመታት ፐርፎርማንሳቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት ዋንጫው ከጅቡቲ አያልፍም እላለው Very Happy ስልህ አቋማቸውን በአንድ ጨዋታ እንኳን ሳናይ መገመት ይከብዳል ለማለት ነው

ሰላም ሁን [/quote]
መቼም አያልቅበት ነህ Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing ይመችህ

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Jan 22, 2012 11:36 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለእግር ኳስ አፍቃሪዎች :-

የደቡባዊ አፍሪቃ ቡድኖች ዘንድሮ የምዕራብ አፍሪቃ ቡድኖችን ተራ በተራ 2 1 እየሸኙ ነው :: ትላንት ዛምቢያ ሴኔጋልን : ዛሬ ደግሞ አንጎላ ቡርኪና ፋሦን በተመሣሣይ 2 1 አሸንፈዋል :: ለዚህ ዕድል ያልበቃው የምሥራቅ አፍሪቃው ተወካይ የሱዳን ቡድን ነው :: ኮት --ቯር በመጀመሪያው ግማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ድሮግባ 39ኛው ደቂቃ በጭንቅላቱ ገጭቶ ባገባት ጎል 1 0 ሱዳንን አሸንፏል ::

ነገ ሰኞ ጥር 14 ቀን 2004 .. የሚደረጉት ውድድሮች :-
ጋቦን ከኒጀር
ሞሮኮ ከቱኒዚያ

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሻቬዝ -x

ኮትኳች

Joined: 17 Nov 2009
Posts: 200

PostPosted: Mon Jan 23, 2012 2:58 pm    Post subject: Reply with quote

አመሰግናለው ተድላ

ሊንኩ ከሰራልኝ እንግዲህ ልሞክር ነው
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon Jan 23, 2012 10:42 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች :-

የመጀመሪያውን ጨዋታ (ጋቦን እና ኒጀር ያደረጉትን ) ሣልመለከት አመለጠኝ :: አዘጋጁ አገር ማሸነፉ ግን ለውድድሩ ጥሩ ገፅታ ይሠጠዋል ::

በሁለተኛው ጨዋታ ሞሮኮ ኃይል በተቀላቀለበት ሁኔታ ተጭኖ እያጠቃ ነገር ግን በቱኒዚያ የመልሶ ማጥቃት አይበገሬነት ሣይሣካለት ቀርቷል : ድሮውንስ የሰሜን አፍሪቃ ቡድኖች (በተለይ ቱኒዚያ ) ለመከላከል ጨዋታ :: ቱኒዚያ ሞሮኮን 2 1 አሸንፎ ከምድቡ 2 ሆኗል :: በዚህ ውድድር እስካሁን ጥሩ ጨዋታ ያየሁት ይኼን ነው :: ዳኛው ከፈረንሣይ ስለመጣ ይሁን ወይም ጨዋታው ትንሽ ኃይል ስለተቀላቀለበት እንጃ : ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ የአፍሪቃ ዋንጫ ሦሥት ቢጫ ካርዶች ሲወጡ አይቻለሁ ::

እንግዲህ የነገ ሰው ይበለን እና ጋና ከቦትስዋና እንዲሁም ማሊ ከጊኒ የሚያደርጉትን ጨዋታ ነገ እንከታተላለን ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Tue Jan 24, 2012 10:02 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች :-

ማሊ እና ጊኒ በጣም አሪፍ ጨዋታ አሣዩ :: እስከዛሬ በተደረጉት የአራት ቀናት ጨዋታዎች እንደዚህ ጨዋታ ያረካኝ የለም :: ማሊ በመጀመሪያው ግማሽ የጨዋታ ጊዜ 31ኛው ደቂቃ ፈረንሣይ አገር ተወልዶ እዚያው በፈረንሣይ አገር ለኤ .. ናንሲ ክለብ የሚጫወተው 15 ቁጥሩ ባካዬ ትራኦሬ ባስቆጠራት ግሩም ጎል 1 0 ጊኒን አሸንፏል :: በአጠቃላይ ማሊ በጉልበትም : በጨዋታም በጊኒ ላይ ብልጫ ነበረው ::

የመጀመሪያውን ጨዋታ ሙሉውን ባልከታተለውም ጋና በአሣሞያ ጎል 1 0 ቦትስዋናን አሸንፏል ::

በዛሬው ዕለት በተደረጉት ጨዋታዎች በመጀመሪያው ግጥሚያ የጋናው አሣሞያ በፕሮፌሽናል ፋወል በቀይ ካርድ ወጥቷል :: በሁለተኛው ግጥሚያ ደግሞ 4 ቢጫ ካርዶች ታይተዋል - ሁለት -ሁለት ደርሷቸዋል ::

የዛሬ ግጥሚያዎች ሲጠቃለሉ እያንዳንዱ ቡድን አንድ -አንድ ጊዜ ግጥሚያ አድርጎጓል ::

ነገ ረቡዕ ደግሞ የምድብ ቡድኖች ሁለተኛ ዙር ግጥሚያዎቻቸውን ያደርጋሉ :-
ሊቢያ ከዛምቢያ
ኢኳቶሪያል ጊኒ ከሴኔጋል

መልካም የአፍሪቃ ዋንጫ ጨዋታዎች ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Wed Jan 25, 2012 11:32 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች :-

የዛሬው ጨዋታ በዝናብ ምክንያት 1 ሰዓት 45 ደቂቃ ያህል ዘግይቶ እንዲጀመር አስገድዷል :: በዝናቡ ምክንያት ሜዳው ውኃ በመቋጠሩ የቀናቸው ቡድኖች ጉልበተኞቹ ሣይሆኑ በዘዴ የሚጫወቱት ናቸው ::

በመጀመሪያው ጨዋታ ሊቢያ ሁለት ጊዜ ሙሉ በአህመድ ዖስማን ጎሎች ቢመራም (5 እና 47 ደቂቃዎች ) ዛምቢያዎች እኩል የሚያደርጓቸውን ጎሎች ተከታትለው እያስቆጠሩ (ኢማኑኤል ማዩካ 29 ደቂቃ እና ክሪስቶፈር ካቶንጎ 54 ደቂቃ ) ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል :: በጨዋታ ግን ዛምቢያ ዛሬ ቀዝቀዝ ብለዋል ::

ሁለተኛው ጨዋታ የተደረገው በአዘጋጇ አገር ኢኳቶሪያል ጊኒ እና በሴኔጋል መካከል ነበር :: የሴኔጋል ቡድን እንደ ዴምባ ያሉ ታላላቅ ፕሮፌሽናል ተጨዋቾች ስላሉት በውድድሩ ለዋንጫ ይደርሣሉ ተብለው ከተገመቱት መካከል ነበሩ :: ምክንያቱም ሴኔጋል ለዚህ የፍጻሜ ውድድር ያለፉት ካሜሩንን በማጣሪያው ውድድር ከደረጃ ውጪ አድርገው ነው :: ነገር ግን ዛሬ ድሉ ያልታሠቡት የኢኳቶሪያል ጊኒ ቡድን ሆኗል :: በተለይ የቡድኑ 3 ቁጥር እና የኋላ መሥመር ተከላካይ ዴቪድ አልቫሬዝ አልጉዌሬ 62ኛው ደቂቃ ላይ የመጀመሪያዋን ጎል እንዲያገባ 8 ቁጥሩ ኢባን ኢያንጋ ትራቪሶ በማቀበልና በተጨማሪ ሰዓት 94ኛው ደቂቃ 35 ሜትር ርቀት በቀጥታ መትቶ ግሩም ጎል በማግባት የዛሬው ጨዋታ ኮከብ ሆኗል :: ከዚህ ጎል በፊት ሴኔጋል 89ኛው ደቂቃ ተቀይሮ በገባው 7 ቁጥሩ በሙሣ ሦው አማካይነት አንድ ጎል አስቆጥሮ ነበር : ደስታቸው አልዘለቀም እንጂ :: በተከታዮቹም ጨዋታዎች መልካም ዕድል ለኢኳቶሪያ ጊኒ :: በዚህ መሠረት ሴኔጋል ከዚህ ውድድር የመጀመሪያው ተሠናባች ቡድን ሆኗል ::

ነገ ደግሞ ሱዳን ከአንጎላ : ኮት --ቯር ከቡርኪና ፋሦ ጠንካራ ፉክክር እንደሚያደርጉ እጠብቃለሁ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Thu Jan 26, 2012 10:12 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች :-

ኮት --ቯር አዘጋጇን አገር ኢኳቶሪያል ጊኒን ተከትሎ ለሩብ ፍጻሜው ውድድር ለማለፍ ሁለተኛው ቡድን ሆኗል :: በርግጥ ኮት --ቯር የዛሬውን ጨዋታ በልጠው ስለተጫወቱ 2 0 ብቻ ማሸነፍ ያንሣቸዋል :: የቡርኪና ፋሦ ቡድን የዛሬ 14ዓመት 1990 .. የአፍሪቃን ዋንጫ ሲያዘጋጁ ከነበራቸው የአጨዋወት ሥልት የቀየሩት ነገር የለም :: ኳስ ከኋላ መሥመር በረዥሙ ይጠልዙና ከዚያ በክንፍ ቅብብል መሯሯጥ ነው :: በዚያ ላይ አይቀመሴዎቹ የኮት --ቯር አማካዮች መሐል ሜዳውን ስለተቆጣጠሩት ቡርኪናቤዎች ኳስ በቀላሉ ተቀባብለው ጎል መድረስ አልቻሉም :: መደበኛ የጨዋታው ጊዜ ሊጠናቀቅ 8 ደቂቃዎች ሲቀሩት የጨነቀው የቡርኪና ፋሦው የኋላ መሥመር የመሐል ተከላካይ ባካሪ ኮኔ ከረዥም ርቀት የኮት --ቯር ተከላካይ የመታትን ኳስ ወደ ውጪ አወጣለሁ ብሎ በራሱ ጎል ላይ አገባና አረፈው Sad

የመጀመሪያው ጨዋታ በአንጎላ የጎል ቀዳሚነት : በሱዳን ተከታይነት 2 እኩል ተጠናቋል :: ሱዳኖች ከአንጎላዎች የተሻለ የኳስ ችሎታ እንዳላቸው አያጠያይቅም :: አንጎላን ማሸነፍ ግን አልቻሉም ::

ለነገው ደግሞ እስኪ ሰሜን አፍሪቃ ከምዕራብ አፍሪቃ በጥንድ የሚያደርጉትን ፍልሚያ እናያለን :- ቱኒዚያ ከኒጀር : ጋቦን ከሞሮኮ ::

የነገ ሰው ይበለን ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Fri Jan 27, 2012 10:13 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች :-

ቱኒዚያና አዘጋጇ አገር ጋቦን ቀደም ብለው ለሩብ ፍጻሜ ያለፉትን ቡድኖች ኢኳቶሪያል ጊኒን እና ኮት --ቯር ተቀላቅለዋል :: በአንጻሩ ደግሞ ኒጀር እና ሞሮኮ በዚህ ዙር ተሠናባች ቡድኖች መሆናቸውን አረጋግጠዋል ::

ቱኒዚያ እና ኒጀር :-
ይህንን ጨዋታ አልተከታተልኩትም :: ውጤት :- ቱኒዚያ 2 ኒጀር 1::

ጋቦን እና ሞሮኮ :-
ሞሮኮ 25ኛው ደቂቃ በሁሴን ካርጃ አማካይነት አስቀድሞ ጎል ካስቆጠረ በኋላ ጋቦን 9 ቁጥሩ ፒዬር ኤምሪክ ኦውባሜያንግ የማስተካከያዋን ጎል እስኪያስቆጥር ድረስ ጨዋታው እጅግ አሠልቺ ነበር :: ሁለቱ ቡድኖች እኩል ከሆኑ በኋላ ሞሮኮዎች 8 ተከላካይ ያጠሩትን በራቸውን ትንሽ ከፈት ማድረግ እና ወደፊት መጫወት ጀመሩ :: ከሦሥት ደቂቃ በኋላ አሁንም ጋቦኖች 10 ቁጥሩ ዳንኤል ሚሸል ከዚን ሁለተኛውን ጎል ደገሙ :: በጭማሪው ሰዓት የመጀመሪያ ደቂቃ ሞሮኮዎች የፍጹም ቅጣት ምት አገኙና የመጀመሪያዋን ጎል ያገባው 13 ቁጥሩ ሁሴን ካርጃ መትቶ እኩል 2 ሆኑ :: ጨዋታው በዚህ ውጤት ይጠናቀቃል ተብሎ ሲጠበቅ በጭማሪው ሰዓት የመጨረሻ ደቂቃ በግምት 30 ሜትር ላይ የተሠጠውን የቅጣት ምት 5 ቁጥሩ ብሩኖ ኢኩዌሌ ማንጋ በግሩም ሁኔታ በቁርጥ ምት ከመረብ አሣረፈና ጨዋታውን ጋቦን 3 2 እንድታሸንፍ አደረጋት :: የመጨረሻዎቹ 20 ደቂቃዎች 4 ጎሎች የተቆጠሩባቸው ነበሩ ::

ለነገ ደግሞ ጋና ከማሊ እንዲሁም ቦትስዋና ከጊኒ ከባድ ፍልሚያ ያደርጋሉ ::

የነገ ሰው ይበለን ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sat Jan 28, 2012 10:41 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም የእግር ኳስ አፍቃሪዎች :-

ጊኒ እና ቦትስዋና (6 1)

የዛሬው ቅዳሜ የመጀመሪያ ጨዋታ የጎል ምርት የታየበት ነበር : 7 ጎሎች :: ጊኒ ቦትስዋናን 6 1 ባሸነፈበት ጨዋታ ጊኒ በጎል ብቻ ሣይሆን በችሎታም ቦትስዋናን በልጦ አሸንፏል :: የቦትስዋና በረኛ እና ተከላካዮች የጊኒን አጥቂዎች ማቆም አልቻሉም :: በዚህ ውጤት መሠረት 42 ዓመታት በፊት 1962 .. ሱዳን ላይ ተደርጎ በነበረው 7ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ የኮት --ቯር ቡድን በኢትዮጵያ ቡድን ላይ ያስቆጠረውን 6 ጎል ተስተካክሏል :: በዚያ ውድድር ፓኩ የተባለው የኮት --ቯር ተጫዋች በኢትዮጵያ ቡድን ላይ 5 ጎል አስቆጥሮ ነበር : እስካሁን በአፍሪቃ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታዎች ላይ አንድ ተጫዋች በአንድ ጨዋታ ያስቆጠረው ከፍተኛው ሬኮርድ ነው ::

የጊኒ እና የቦትስዋና ጨዋታ ጎሎች ...
ምንጭ :- Uploaded by MattMzansi on Jan 28, 2012, Botswana 1 - 6 Guinea - AFCON 2012 -All Goals - Eng Commentary - Botswana vs Guinea.

ጋና እና ማሊ (2 0)

ሁለተኛው ጨዋታ ከመጀመሪያው የተሻለ ፉክክር ነበረበት :: በእርግጥ ጋና እና ማሊ ሁለቱም የምዕራብ አፍሪቃ ቡድኖች ቢሆንም የአጨዋወት ሥልታቸው ይለያያል :: ማሊ 4-4-2 አሠላለፍ ይዘው በረዥም ኳስ እየተቀባበሉ ለማጥቃት ሲሞክሩ ጋና ደግሞ 3-5-2 አእሠላለፍ መሐል ሜዳውን ተቆጣጥረው በአጭር ቅብብል ተጋጣሚያቸውን ያስጨንቃሉ :: ውጤቱም በግልፅ እንደሚያሣየው ጋና የበለጠ አጥቅቶ ተጫውቶ በሁለት ጎል አሸንፏል :: የጋናው አሣሞያ ጋያን 63ኛው ደቂቃ የመጀመሪያዋን ጎል በቅጣት ምት ሲያስቆጥር : ሁለተኛዋን ጎል ደግሞ የአቤዲ ፔሌ ልጅ አንድሬይ አዩ 74ኛው ደቂቃ ሁለት ተከላካዮችን አብዶ ሠርቶ በጎሉ ግራ ጠርዝ ግሩም ጎል አስቆጥሯል ::

ነገ የመጀመሪያው ዙር የማጠናቀቂያ ውድድሮች ይጀምራሉ :-
ዛምቢያ ከኢኳቶሪያል ጊኒ
ሊቢያ ከሴኔጋል

የነገ ሰው ይበለን ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Sun Jan 29, 2012 9:07 pm    Post subject: Reply with quote

እሑድ ጥር 20 ቀን 2004 ..

ዛምቢያ ከኢኳቶሪያል ጊኒ (1 0)
ሊቢያ ከሴኔጋል (2 1)

በአብዛኛው የተከታተልኩት የዛምቢያ እና ኢኳቶሪያል ጊኒን ጨዋታ ነበር :: ዛምቢያ ከመጀመሪያው ግማሽ በተሻለ በሁለተኛው ግማሽ አጥቅቶ የኢኳቶሪያል ጊኒን ጎል ደጋግሞ ፈትሿል :: ስለሆነም በአምበሉ በክሪስቶፈር ካቶንጎ አማካይነት 68ኛው ደቂቃ ብቸኛዋን እና የማሸነፊያዋን ጎል አስቆጥሯል ::

በዚህ የአፍሪቃ ዋንጫ ምናልባት ያልተጠበቀው ውጤት የሴኔጋል ቡድን አንድም ጨዋታ ሣያሸንፍ 0 ነጥብ ከውድድሩ መሠናበቱ ነው :: የሴኔጋል ቡድን ዝነኛውን የካሜሩንን ቡድን ከዚህ ውድድር ውጪ ያደረገ ስለሆነ ለዋንጫው ከፍተኛ ግምት ከተሠጣቸው አንዱ ነበር :: በተቃራኒው ደግሞ ብዙም ግምት ያልተሠጠው የኢኳቶሪያል ጊኒ ቡድን ሁለት ጨዋታዎች አሸንፎ (ሊቢያን 1 0 : ሴኔጋልን 2 1) ለሩብ ፍጻሜ ማለፍ መቻሉ ውድድሩን ጥሩ ድምቀት ሠጥቶታል ::

የነገ ሰኞ ጥር 21 ቀን 2004 .. ግጥሚያዎች :-

ሱዳን ከቡርኪና ፋሦ
ኮት --ቯር ከአንጎላ

የነገ ሰው ይበለን ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት All times are GMT + 1 Hour
Goto page 1, 2, 3  Next
Page 1 of 3

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia