WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home | About us | Advertise with us | Contact us
28ኛው የአፍሪቃ ዋንጫ -ኢኳቶሪያል ጊኒ እና ጋቦን
Goto page Previous  1, 2, 3
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ጥልቁ 1

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 27 Jan 2004
Posts: 1560
Location: bhutan

PostPosted: Mon Feb 13, 2012 5:43 pm    Post subject: Reply with quote

ተድላ ሀይሉ :
አንተንም እንኳን ደስ አለህ ! እኔ እራሴ ዛምቢያዎች ቢቻል በጨዋታ ; ባይቻል በፔናሊቲ እንዲያሸንፉ የነበረኝ ምኞት ; ክፉኛ ልቤን አስጨንቆኝ ነበር ::

ድሮግባም ፔናሊቲ መሳቱ ለጋናው ጂያን አስተዋጽኦ አለው ::

በቀጣዩ አመት ደቡብ አፍሪካ ያገናኘን :: ያኔስ እኛም እናልፍ ይሆናል Laughing
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message MSN Messenger Report post
ጌታ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Apr 2005
Posts: 3486
Location: ዶሮ ተራ

PostPosted: Mon Feb 13, 2012 6:59 pm    Post subject: Reply with quote

ተድላ ጥልቁ 1 ጥሩ ዜና አሰማችሁኝ :: የኮትዲቯር ቡድን አስራ አንዱም በአውሮፓ ክለቦች የሚጫወቱ ኮከቦች ሲኖሩት የዛምቢያው ግን 8 እዛው አገራቸው የሚጫወቱ በመሆናቸው የማሸነፍ ግምቱ ለኮትዶቯር ነበር የተሰጠው :: ይቺ ድቡልቡል ኳስ ግን ፍርዱን ለሚገባው ሰጥታለች ::

ዩቱብ ላይ የድሮግባን ፔናልቲ እና ባጠቃላይም ፔናልቲ ሹታውቱን ተከታትዬ ሁለት ነገሮች ገርመውኛል :

1. ድሮግባን የገፈተረው የዛምቢያ ተጫዋች ቀይ ካርድ ማግኘት ነበረበት ብዬ አምናለሁ :: በዚህም የጩቡ አምላክ ለነድሮግባ አልሰራም Laughing

2. የዛምቢያው በረኛ ያዳናት 3 ምት እውነት መሰረዝ ነበረባት ?

ትናንት ከጨዋታው በፊት ሉሳካ ክተማ ቀውጢ እንደነበረች አንብቤ ነበረ :: ወንድማችን የዛምቢያ ሕዝብ እንኳንም ደስ አለው Smile አይቮሪኮስቶችም በዚህ ሁኔታቸው በቅርቡ ዋንጫ አያጡም ::
_________________
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon Feb 13, 2012 9:01 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ጥልቁ እና ጌታ :-

እንኳን አብሮ ደስ ያለን :: እንደ እኔ እንደ እኔ የአፍሪቃ ዋንጫ እንደ ላቲን አሜሪካ ፌዴሬሽን ውድድር በየዓመቱ 32 ቡድኖች መካከል ቢደረግ እመርጣለሁ :: ምክንያቱም ብዙ አገሮች የመካፈልና ውድድሩን የማዘጋጀት ዕድል ያገኛሉ ::

ጌታ ላነሣሃቸው ጥያቄዎች :-

1 ..... የዛምቢያው አምበል 11 ቁጥሩ ኢማኑኤል ማዩካ ድሮግባን በእግሩ ቅጥልሙን የመምታት ዓይነት ድርጊት ፈጽሟል :: ነገር ግን ፊልሙ ላይ ያየሁት የመቀላለድ ይሁን ከምር ለመለየት አልቻልኩም :: ከድርጊት በኋላ ሁለቱም ሲነጋገሩ ይታዩ ነበር : የጸብ ይሁን የቀልድ :: የመረረ ነገር ቢሆን ኖሮ ሁለቱም የየቡድናቸው አምበሎች ስለሆኑ ዳኛው ቢያንስ ሁለቱንም ጠርቶ ያነጋግራቸው ነነር ::

2 ..... የኮት --ቯሩ 22 ቁጥር ቤምባ በመጀመሪያ የፍጹም ቅጣት ምቱን ከመምታቱ በፊት ገና ፊሽካ ሣይነፋ የዛምቢያው በረኛ ኬኔዲ ምዌኔ ተንቀሣቅሷል : የጎሉን መሥመሩንም ለቅቋል :: ስለዚህ የመሥመር ዳኛው ምልክት የሠጠው በትክክል ነው : ዳኛውም ፍጹም ቅጣት ምቱ ድጋሚ እንዲመታ የሠጠው ውሣኔ ተገቢ ነበር :: የሚከተለው የዩ -ቲዩብ ፊልም ላይ 39ኛው ደቂቃ ጀምሮ ማዬትና ማረጋገጥ ትችላለህ ::
ምንጭ :- Uploaded by raychauke on Feb 13, 2012. Zambia vs Ivory Coast 2012 AFCON Final Highlights 8-7 Penalty.

በሉ ለአፍሪቃ ዋንጫ ከርሞ እንገናኝ :: የጥልቁ ምኞት ቅዱስ ምኞት ስለሆነ 'እንደ ቃልህ ያድርግልን ' ብያለሁ ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጌታ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Apr 2005
Posts: 3486
Location: ዶሮ ተራ

PostPosted: Mon Feb 13, 2012 9:26 pm    Post subject: Reply with quote

ተድላ

የሁለተኛውን ጥያቄዬን መልስ ተቀብያለሁ ::

ወደመጀመሪያው ጥያቄ ስንመለስ ግን ድሮግባን የገፈተረው 8 ቁጥሩ የዛምቢያ ተጫዋች ሲሆን 23 ቁጥሩ በግርግር ተጠልፎ ነው ድሮግባ ላይ የወደቀው :: ቢጫ ካርድ የተሰጠው 23 ቁጥሩ ሲሆን እሱም ውሳኔውን ተቃውሞ በመነጫነጩ ይመስለኛል :: 8 ቁጥሩ ግን ወደጎል ክልል እያመራ ያለን ተጫዋች በእጁ ገፍትሮ ጥሎ ከፔናልቲው ውጪ ምንም ቅጣት አልደረሰበትም :: አሁንም ዛምቢያ በማሸነፉ ደስተኛ ብሆንም በዳኝነት ስህተት 10 ተጫዋች ከመጫወት ድነዋል ባይ ነኝ ::

በእግርኳስ (ሶከር ) ሪፕሌይ ተመልክቶ የዳኛን ውሳኔ ማስተካከል ቢቻል ጥሩ ይመስለኛል :: እስቲ ይህንን ተመልከት :

http://www.youtube.com/watch?v=3sNfqJdJRD0
_________________
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ተድላ ሀይሉ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Mar 2006
Posts: 4490
Location: ኢትዮጵያ

PostPosted: Mon Feb 13, 2012 10:06 pm    Post subject: Reply with quote

ጌታ እንደጻፈ(ች)ው:
ተድላ

የሁለተኛውን ጥያቄዬን መልስ ተቀብያለሁ ::

ወደመጀመሪያው ጥያቄ ስንመለስ ግን ድሮግባን የገፈተረው 8 ቁጥሩ የዛምቢያ ተጫዋች ሲሆን 23 ቁጥሩ በግርግር ተጠልፎ ነው ድሮግባ ላይ የወደቀው :: ቢጫ ካርድ የተሰጠው 23 ቁጥሩ ሲሆን እሱም ውሳኔውን ተቃውሞ በመነጫነጩ ይመስለኛል :: 8 ቁጥሩ ግን ወደጎል ክልል እያመራ ያለን ተጫዋች በእጁ ገፍትሮ ጥሎ ከፔናልቲው ውጪ ምንም ቅጣት አልደረሰበትም :: አሁንም ዛምቢያ በማሸነፉ ደስተኛ ብሆንም በዳኝነት ስህተት 10 ተጫዋች ከመጫወት ድነዋል ባይ ነኝ ::

በእግርኳስ (ሶከር ) ሪፕሌይ ተመልክቶ የዳኛን ውሳኔ ማስተካከል ቢቻል ጥሩ ይመስለኛል :: እስቲ ይህንን ተመልከት :

http://www.youtube.com/watch?v=3sNfqJdJRD0

ሰላም ጌታ :-

አንተ ባልኸው መሠረት ጥፋቱ 8 ቁጥሩ ኢሣክ ቻንሣ ብቻ ጥፋት አልነበረም :: የሚከተለውን ፊልም በደንብ እየው :- 8ኛው ሴኮንድ ላይ ኢሣክ ቻንሣ የኮት --ቯርን 10 ቁጥር ጀርቪንሆን (ድሮግባን አይደለም ) ከፍጹም ቅጣት ምት ክልል ውጪ ሲገፋው ታያለህ ::
Ivory Coast stars fail to shine in final, another gloomy night for 'golden generation'

በዚህኛው ፊልም ላይ ደግሞ 43ኛው ሴኮንድ ላይ የዛምቢያ 23 ቁጥር ኒያምቤ ሙሌንጋ ፍጹም ቅጣም ምት ክልል ውስጥ በቀኝ ጉልበቱ የጀርቪንሆን ቀኝ ታፋ ገጭቶታል ::
Zambia vs Cote D'Ivoire Drogba Misses Penalty, 2012 Africa Cup of Nations Final.

ስለዚህ ዳኛው ከፍተኛ ቅጣት የሚያሠጠውን (ፍጹም ቅጣት ምት ) ጥፋት የፈጸመውን ተጫዋች (23 ቁጥሩን ) ብቻ በቢጫ ካርድ ቀጥቶታል :: ከዚያ በላይ ቀይ ካርድ ለመስጠት ግን ሕጉ የሚፈቅድለት አይመስለኝም : አደገኛና የተቃራኒ ተጫዋችን በጣም የሚጎዳ አጨዋወት አልነበረምና :: እንግዲህ የእግር ኳስ ጨዋታ ዳኝነት እጅግ አስቸጋሪ የሆነው በዚህ ምክንያት ነው :: ፊፋ ደግሞ ሕጉን የሚያሻሽለው በእንግሊዞች ድምፅን በድምፅ የመሻር ሥልጣን ሥር ሆኖ ስለሆነ እነርሱ ያልፈለጉት አሠራር (ሪፕሌይን መጠቀም ) ሥራ ላይ አይውልም ::

ተድላ
_________________
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3
Page 3 of 3

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia