WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
የአሳዛኙ ዜና ኅዘን -የንፋስ ስልክ ትዝታ
Goto page Previous  1, 2, 3
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ወለላዬ

ዋና ኮትኳች

Joined: 26 Jan 2005
Posts: 516
Location: united states

PostPosted: Wed Feb 22, 2012 8:16 pm    Post subject: Reply with quote

ዝናዬ እንዲህ ቀጥሏል

To: ወለላዬ
Posted: Tue Feb 21, 2012 2:31 am
Subject: ሰላም ወንድሜ ሆይ Quote message
እጅ ነስቻለሁ ወለላዬ :

የአሁኑ አመጣጤ እንኩዋን የህገር ልጅ ዲጎኔ ባነሳው ጥያቄ ላይ አንድ ነገር ለማለት ነው ::

ሰላም ለአንተ ይሁን ዲጎኔ ::
ሱራፌል ካባን እንዴት አስታወስከው :: እጅግ ድንቅ ነው :: ሱራፌል ካባን ከሶስተኛ ወደ አለም በቃኝ ከተዘዋወርኩ በሁዋላ ነበር ያወኩት :: አለም በቃኝ ውስጥ ክፍል ቁጥር 18 ውስጥ እስረኛ ነበር :: በነገራችን ላይ አለም በቃኝ ውስጥ 57 የእስር ክፍሎች ሲኖሩ ከአንድ ሶስት ወይ አራቱ በስተቀር ተመሳሳይ ስፋት ያላቸው ነበሩ :: ዛሬ ላይ ሆኜ ሱራፌልን ሳስታውሰው : ጠይም ዘለግ ያለ ቁመት ያለውና ጺም ቅርጽ ይላጭ ነበር :: ሱራፌል . . . . አባል ሳይሆን በወቅቱ ኤል ኤፍ (ሻእቢያ ) ለጎሪላ ዋርፌር አማካሪነት ወደ . . . . ተዘዋውሮ እንደመጣ ይነገር እንደነበረ አስታውሳለሁ :: ተፈጥሮው ግን (እርጋታው : አንጋገሩ እና ጨዋነቱ ሲናገር ደፋር ግስ አለመጠቀሙ እና አለመንቀዥቀዡ ) የዚያ አካባቢ ሰው አያስመስለውም ::

ግራዚያኒ መንግስቱን ለማደን በታቀደው እቅድ ላይ ሱራፌል ካባ ነበር :: ግንባር ቀደም ተፋላሚው መምህር በላይ ቢሆንም ሱራፌል የወጣው ለመህሩ ሽፋን ለመስጠት እንደነበር ያኔ እስር ቤት የሰማሁት ዛሬም ትዝ ይለኛል :: ሌላው ደግሞ እዛው አለም በቃኝ ውስጥ መኮንን የሚባል ሲቪል ኢንጅነር 31 ቁጥር ታስሮ የነበረ ብስል ቀይ ደልደል ያለ ሰውነት ያለውና መሀከለኛ ቁመት የነበረው እዚያ ሚሽን ላይ ተሰማርቶ የነበረ ነበር :: ግራዚያኒ መንግስቱ አምሽቶ ከስራ ቢወጣም የሚወጣባቸው ሰአታት ተመሳሳይነት ሳይኖራቸው ይልቁንም የተለያዩ የነበሩና ለጥናትም የማያመቹ ነበሩ :: በተጨማሪም ከደርግ ጽህፈት ቤት ወጥቶ ወደ ማደሪያው 4 ክፍለ ጦር ሲሄድ ከአራት እስከ ስድስት መኪና ቢያጅበውም በየቀኑ በተለያዩ መኪኖች ይጉዋጉዋዝ ነበር እንጂ አንድ አይነት መኪና ውስጥ አዘውትሮ አይታይም ነበር :: በዚያን እለት ግራዚያኒ መንግስቱ የነበረበትን መኪና ከላይ ከፊት በር ሆኖ በባትሪ ብርሀን ኮድ ስንተኛው መኪና ውስጥ እንደነበር ምልክት የሚስጥና እነ በላይ እስካደፈጡበት ድረስ በባትሪ ብርሀን ብልጭ ድርግም በማድረግ መል እክት ይለዋወጡ እንደነበር : በዚያ የኮድ ልውውጥ ኮሎኔሉ ላንድ ሮቨር ውስጥ መኖሩ ተረጋግጦ መምህር በላይ እርምጃ ወሰደ :: ለመንግስቱ የተላኩት ጥይቶች መንግስቱ ላይ በተኙት አንድ ተራ ወታደርና አንድ አስር አለቃ (ቦዲ ጋርዶች ) ላይ አርፈው እነሱን ሲጨርሱ የቀረችዋ አንድዋ ጥይት የመንግስቱ መዋሂት ውስጥ ተደበቀች :: አዎ ሱራፌል ካባ እዚያ ቦታ ላይ ለሽፋን ተሰማርቶ ነበር :: ከዚያ በሁዋላ ነው መንግስቱን መውጫ መግቢያ ቢያሳጣው መንግስቱ የባህታ ቤተክርስትያንን አሽጎ ኑሮውንም ስራውንም እዚያው ደርግ ጽህፈት ቤት አድርጎ ነበር ::

ዲጎኔ የመምህር በላይ ስም ለምን በዚያ ዘመን እንደ ገነነ ሌላ አንድ ነገር ላጫውትህ :: 69 . . መጀመሪያ ላይ ሰንዳፋ ፖሊስ ማሰልጠኛ ይሁን ወይም ሰንዳፋ አባ ዲና ፖሊስ ኮሌጅ የመሳርያ ግምጃ ቤት በኢ ስኩዋድ ቡድን ተበርግዶ ይከፈትና መሳሪያው በተዘጋጀው የወታደር መኪና ላይ ይጫናል :: በወቅቱ ጥበቃ ላይ የነበሩ ወታደሮች ተኩስ ቢከፍቱም ለማስጣል አልቻሉም :: ከጥበቃ ወታደሮች መሀልም : : የቤላ ልጅ የነበረ ወታደር ጌቱ በቀለ የሚባል የድርጅት አባል ነበርና እስኩዋዶቹን እየሸፈነ መሳሪያ የጫነው ማክ ከጊቢ ወጥቶ አመለጠ :: የማሰልጠኛ ጥበቃ ላይ የነበሩ ወታደሮች ይህን ለኢ ጎሪላዎች ሽፋን ይሰጥ የነበረውን የራሳቸው ባልደረባ የሆነውን ወታደር ጢሻ ለጢሻ ሲከታተሉት ጥይት ጨርሶ ነበርና ይይዙታል :: በማግስቱም ወደ 3 ፖሊስ ጣብያም ይላካል ::

መሳሪያ የጫነ ማክ የት የሄደ ይመስልሀል ???? መምህር በላይ ቤት :: የመምህር በላይ ቤት ከከተማ ውጪ ወይም ጫካ ውስጥ ወይም ሰወር ያለ ቦታ ይሁን አላውቅም :: የማውቀው መምህሩ የተከሰሰባቸውን ኬዞች ነው :: መሳርያ የተራገፈበትን የደርግ ሴኩሪቲው በሶስተኛው ቀን ደርሶበት ነበር ግን ከአንድ ማክ መኪና ሙሉ መሳርያ ውስጥ አንድ የወደቀ ቀለሀ እንኩዋን አልተገኘም መምህር በላይም ደብዛው የለም :: ከተማው ውስጥ ሌላ ድርጅታዊ ስራ ላይ ነበርና ::

መምህር በላይ ምን ይሰራ ይሆን ብለህ ትገምታለህ ????????? አንድ ሚሺን ለማካሄድ ንድፍ እየነደፈ ነበር ::

የደርግ ጽህፈት ቤት ምርመራ ክፍል ሀላፊ በነበረው በሻምበል ብርሀኑ ከበደ የተፈረመ ወይም አስመስሎ የተፈረም ደብዳቤ የፕሮቶኮል ቁጥር ይዞ ከደርግ ጽህፈት ቤት ወጣ ወይም ከደርግ ጽህፈት ቤት ወጣ ተባለ :: አራት ጦር ሰራዊት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው (ከነ ሄልሜት )የጫነች እና መትረየስ የተጠመደባት ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያን በር ዘልቃ ገብታ ከደርግ ጽህፈት ቤት ተጻፈ የተባለውን ደብዳቤ ለሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ ክፍል ሀላፊ ለሀምሳ አለቃ ተሾመ ይሰጠዋል ::

ደብዳቤው ምን ይላል ???????????

ወታደር ጌቱ በቀለን ለጥብቅ ምርመራ ለሶስት ቀን ወደ ደርግ ጽህፈት ቤት ምርመራ ክፍል በውሰት እንዲላክ የሚል ነው :: እነኚህ 4 ጦር ሰራዊቶች ወታደር ጌቱን በውሰት 3 ጣቢያ ወሰዱት :: በሳምንቱ ሀምሳ አለቃ ተሾመ ወታደሩን መልሱልን የሚል ደብዳቤ ጻፈ :: የደርግ ጽህፈት ቤት ምክትል ምርመራ ሀላፊው መቶ አለቃ እሸቱ ተሳለቀ :: ይህ ደብዳቤ ከደርግ ጽህፈት ቤት ምርመራ ክፍል የተጻፈ አይደለም ወታደሩንም በውሰት አልወሰድንም አለ :: ጉድ ፈላ ::መንግስቱ ሀይለ ማርያም የሰንዳፋ ጉዳይ ምርመራው ከምን ደረሰ ይላል ጌቱ በቀለ የሚባል ወታደር ግን እምጥ ይግባ ወይ ስምጥ የሚያውቅ ጠፋ ::

ይህ ተልእኮ የታለመው : የተነደፈውና መሪ ሆኖ ራሱ ተሳትፎ ለውጤት ያደረሰው መምህር በላይ ነበር ::መምህር በላይ ከአራቱ ጦር ሰራዊቶች አንዱ እና የቡድን አዛዡ ነበር ::

አሁን መምህር በላይ ማነው ለምን ዝናው ናኘ ለሚለው ጥያቄ እነዚህ ጥቂቶቹ መልሶች ናቸው :: ጌቱ በቀለ ተፈቷል :: ወይም መምህሩ አስፈታው :: ይገድሉት እንደነበር ዛሬም አልጠራጠርም ::

ለማጠቃለልም : ምምህር በላይ መጀመርያ ለሞት የወጣው መጋቢት 69 አጋምሽ ቢህንም የሞተው ግን ዳግም ሞት ተፈርዶበት ሲወጣ ግንቦት አካባቢ ይመስለኛል :: ሱራፌል ካባ እና መኮንን ግን የተገደሉት 1970 . . መስከረም መጨረሻ ላይ አለም በቃኝ ተወስደው ነው ::

በላይነህ ገብረ ማርያም የወንድ ቁና ማለት ይህ ነው ::
አመሰግናለሁ ::

ወንድሜ ወለላዬ ስለ ሁልጊዜ እርዳታህ ዳግም እጅ ነስቻለሁ ::
View user's profile
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ዲጎኔ

ዋና አለቃ

Joined: 19 Aug 2005
Posts: 3830
Location: united states

PostPosted: Wed Feb 22, 2012 9:24 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችን
ውድ ዝናዬ አሁንም ድንቅ እጥፍ ምስጋና ስለዚያ ዘመን እንቁ ድንቅ የህዝባዊ ትግል አራማጆች ገድል ::አሁን ገባኝ ሱራፌል ሽፋን መምህር በላይ ዋና መሆኑ ::ሁሉም የድንቅ ድንቅ የህዝባዊ አርነት ዘላለማዊ ሰማእታት ናቸው ::
ድሮ ፓርላማ እጩ የነበረ የጋሼ ግርማቸው ልጅ ዮሀንስና ሱራፌል ይምታቱብኛል ሁለቱም ጀግኖች የከረቸሌ ወዳጆቼ ነበሩና ::የዮሀንስ እህትን ሁውላ ሂልተን አግኝቻት ወንድሟ ህያው መሆኑን አውግቻታለሁ ::ዝናዬ በነካ እጅ ደርግ ሊገድላት ይፈልጋት የነበረች የስነጽሁፍ ልእልት እኛን ያስተማረች የመጀመሪያ ህዝባዊ ማተሚያ ኮከብ መስራች መዝገብ ነሽ አባያ የት ደረሰች ?እመለሳለሁ .....
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
feredewnetu

ኮትኳች

Joined: 24 Sep 2009
Posts: 202

PostPosted: Fri Feb 24, 2012 1:07 am    Post subject: Reply with quote

ስላም ወገኖቼ ክሳር ቤት አካባቢ ይመጡ የነበሩ ልጆችን ለማስታወስ ብሞክር ስንዝሮ በለጠ በቀለ ትዝ አሉኝ ከቄራ ልጆች ነፍሱን ይማርና በላቸው መተኪያ (ቁራ ) ጭልፋ ምእራፍና አልሳቤጥ ቾምቤ ትዝ አሉኝ :: የጋሽ በላይ ነገር ሲነሳ ሌላ በጣም ትዝ ያለኝ ከሞርጌድ ህንፃ ላይ ወድቆ ራሱን የስዋው የንፋስልኩ ሀይለልኡል ግዛው አንዱና የማይረሳው ነው በትምህርት በጣም ጎበዝ ነበር የኢህእፓ ነገር አመራሩ በጣም ደካማ በመሆኑ ነው ስንት አሪፍ አሪፍ ልጆች በከንቱ ያለቁት ለምድረ ዱርዬ ወታደር መገዛት ኢትዮጵያን ካበቅዋት ኢሀአፓ የስራው ስህተት ትልቅ አስተዋጻኦ አድርግዋል :: ሳር ቅጠሉ ኢህአፓን ይደግፍ ነበር ቢባል ማጋነን አይሆንም ነገር ግን ያልበስሉ አማራሮቹ ለውድቀት ድርጅቱን ብቻ ሳይሆን አንጡራ ምርጥ ልጆችን በከንቱ አስፈጁት ቀኝ መንገደኛ ግራ መንገደኛ ነጭ ሽብር ቀይ ሽብር አየተባለ :: ሌላው አንድ አስካሁን አንደ ባህል የተያዘው ደግሞ በአንድነት ስም አንዱ ሌላውን ሲያጥላላ ኢትዮጵያዊነት አነሱ በተርጎሙት ብቻ የሚገለጽ አንጂ በጋራ ፍላጎት ላይ ያልሆነ መሆኑን በተግባር መገለጡ ነው :: አይ አንች አገር መቸ ይሆን የሚያልፍልሽ በተለይ ታሪክ አየተዛባ አንዲህ ከቀጠለ ኦሮማይ ኣዲዮስ ነው የኛ ነገር ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወለላዬ

ዋና ኮትኳች

Joined: 26 Jan 2005
Posts: 516
Location: united states

PostPosted: Fri Feb 24, 2012 9:31 am    Post subject: Reply with quote

ከዚህ በፊት ዝናዬ ቀጥሏል ያልኩት የዝናዬ ጽሁፍ ሳይሆን በውስጥ መጻጻፊያ የሚጽፍ ሰው ነው ይኔንን ዝናዬ እንዲታረም ልኮልኛል ::

በኢሜልም ሁነ በውስጥ መጻጻፊያ የምትልኩልኝ በቀጥታ ብትጽፉ ጥሩ ነው
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ዲጎኔ

ዋና አለቃ

Joined: 19 Aug 2005
Posts: 3830
Location: united states

PostPosted: Fri Feb 24, 2012 10:15 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችን
ውድ ወለላዬ ለአምዱ ድጋሚ እጥፍ ምስጋና አቀርባለሁ ::
ይህን ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ትረካ ሳነብ አመታቶቹ 30ዎቹ ሳይሆን የሳምንት ያህል ትውስ ይሉኝ ጀመር ::
በተለይ የዝናዬ ልዩ ትዝታና መረጃ አለው !ያለፈውን በግሌ ማስታወሴ ለክፉት ለበቀል ለጉራ ሳይሆን ለህዝቦች መብት የተሰዉ የታሰሩ የተሰደዱ ክብር እንዲሰጣቸውና ለመጭው ትውልድም መታነጽ እንዲገኝ ነው ::የሚያሳዝነው ለመሬት ላራሹ የተዋደቁና ገባሮች ከሰውእኩል እንዲቆጠሩ ያበቁት ሙታን ሲተቹ ያሳዝናል ::ያመራርና ፖለቲካ ስህተት ይኖራል የመስዋትነት ስህተት ግን የለም ::ለህዝቦች አርነት መገረፍ መገደል ትልቅ መታደል ነው ::
ከአንድ ቤተሰብ ሁለት ሶስት ልጆች ያጡ ዛሬ ሊሸማቀቁ ሳይሆን በልጆቻቸው ታሪክ ሊኮሩ ይገባል ::
ይህን መሳዩ ያለፈ ዘመን ትዝታ የቀድሞ ታጋዮች የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጲያ ተማሪዎች ትግል መሪዎች ከሁለቱም ጎራ ልጆቻቸው ሲናገሩ ብዙዎች በእንባ ታጥበዋል በተለይ እኛ ያኔ ይሰቀል ያልነው የዶ / ሰናይ ልኬ ልጅ !
/ አክሎግ ቢራራ በሜይዴይ ሰልፍ ላይ ይሰቀል ብለን ነበር ዛሬ ግን ለዛች ሀገር በጎ ከሚያስቡ አንዱ ነው !

ስለሳርቤት ልጆች ፍርድእውነት ያልከው ልክ ነው የዋርካው ያየህይራድ ሚንስትሩ ከሆነ የእህቱ ልጆች ተስፋዬ አሸናፊ ሰናይት አሸናፊ የዚያ ድንቅ ትውልድ አባላት ከሳር ቤት ነበሩ ::
ዲጎኔ ሞረቴው ከያ ትውልድ እልቂት በክርስቶስ የተረፈው
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ወለላዬ

ዋና ኮትኳች

Joined: 26 Jan 2005
Posts: 516
Location: united states

PostPosted: Tue Feb 28, 2012 10:52 pm    Post subject: Reply with quote

ዝናዬና በውስጥ መጻጻፊያ የምትልኩልኝ የአጻፉ ሁኔታ ግራ እንዳጋባ በውስጥ መፃፃፊያ እየተጻፈልኝ ስለሆነ ይሄንን የዝናዬን ጽሁፍ ከለጠፍኩ በኍላ ሌላ ማስተናገድ ይከብደኛል እባካችሁ እራሳችሁ በቀጥታ ጻፉት

ሠላም የስብስቴ ልጆች ወለላዬ፤ ፍርድ ዕውነቱ፤ መላጣው፤ ቆንጂት እንዲሁም ሌሎች እንደምን ሰነበታችሁ ? ምነው ቆንጅትን የበላ ጅብ አልጮህ አለ ብቅ ብላ የእህቶቻችንን ገድል እንዳታወጋን

ሠላም ወለላዬ፤ ላደረከው እርማት የከበረ የወንድምነት ምስጋናዬ ይድረስህ፤

በተሰባበሩ መስታዎቶች ባሻገር እንደሚመለከት ሰው ነበር እንባ ባቆረዘዙ እይኖቼ መሃከል ድብዝብዝ ባለ እይታ የልጅነት ጓረኛዬን የይጥና አብሬን መርዶ ዲጎኔ በዘመኑ የመከተቢያ መሳሪያ መስኮት ያረዳኝ ::
ዲጎኔ እግዜር ይስጥህ የኔ ወንድም : የልጅነት መርዶዬን አድጌ ሰው ልበለው : ሰው ሆኜ አረዳኸኝ እኔም በዘመን የርቀት መነጥር አሾልቄ ሳይሆን አፍጥጬ ተመለከትኩት : እሱም መልሶ አፍጥጦ እየተመለከተኝ እነሱ ላመኑበት አላማ ህይወታቸውን ሰጡ አንተስ ? ሲል መልሶ አፈጠጠብኝ እኔም ከእድሜዬ ቆንጥሬ ከአከላቴ . ብዬ ልነግረው አሰብኩና ከነሱ የህይወት መስዋእትነት ጋር ሲወዳደር የኔ ድርሻ ደቂቅ ትብያ ሆነችብኝና አፍሬ ዝም አልኩ ::
አዎ ብዙ ልብ የሚያደሙ አጥንት ሰርስረው የሚሰሙ ስሜቶች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ ይገባኛል ታዲያ ይህን ፈርተን ያየነውንና የሆነን እውነታ ሳንናገር አብሮን ቢሞት ነብሳችን የሰላም እረፍት አታ ዘወትር ከመወራጨቷም በላይ የታሪክ ተወቃሾች እንሆናለን ::

እንዳይሆን መራራም ቢሆን ዋጥ እያደረግን ገድላቸውን በደማቸው እያጠቀስን የመከተብ ግዴታ አለብንና በርትተን እንጻፍ
በትግል የወደቁ ወንድሞቻችንና ህቶቻችን ነብስ ሃሴት : በአሁኑ ትውልድ ላይ የህይወት እስትንፋስ እፍ ብሎበት ምናልባት ከተኛበት የንቅልፍ ሰመመን ብንን ብሎ ይነቃ ይሆናልና ሳትሰለቹ ጻፉ ::

ወንድሜ ሀዲስ «እስቲ በፈጠረህ ስለ ተስፋ ልመታ የምታውቀውን አሳውቀኝ ?» ብለሀል
እውነቱን ለመናገር ተስፋን አላውቀውም አብረንም አልታሰርንም ከዩኒቨርስቲ ትምርቴን አቋርጬ እንደወጣን (በዚህ ጉዳይ ላይ ወደፊት እመለስበታለሁ ) የሴት ጓደኛዬ እቤት ድረስ መጥታ እናቴን እንደሚፈልጉኝ ስለነገረቻት ወዲያውኑ አዲስ አበባን ለቅቄ ወደ ሃገር ሄጄ ነበርና ከዛ በኋላ የኔ ተሳትፎ ሃገር ነበር ::

ምናልባት የምናውቃቸው የጨርቆስ የፖፖላሬ፤ የማሞ ካቻ (አቶ ማሞ ይንበርበሩ ) መቶቢሲ ማሞ ካቻ…… ተብሎ የተዘፈነላቸው ጠንቋይ ስሙ ጠፋኝ ሰፈሩ በሱ ስም ይጠራ ነበር እና የቄራ ልጆች ድንገት በዚህ ቤት ብቅ ካሉ ይነግሩን ይሆናልና ተስፋ አትቁረጥ ::
በነገራችን ላይ ዲጎኔ እንዳለው ትልቁ የኢህአፓ የተቃውሞ ሰልፍ በሜይ 1969 ነበር

ዲጎኔ መንግስቱ ማርያም ላይ የተኮሰው ሱራፌል ዳባ አልነበረም ወይ ላልከው እኔ ሳልሆን ዝናዬ እንዲህ ቀጥሏል በሚለው ገጽ 3 ላይ መልሱን የሰጠ ሰው ስላለ ያነበብከው ይመስለኛል
እንግዲህ
ቂርቆስም እንበለው ጨርቆስ አፋፉ ላይ ካለው የጨርቆስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ሆነን ቁልቁል ስንመለከት ያሁኑን ባላውቅም ህዝባችን እንዳቅሙ የሚገበያይበት የጉልት ገበያ ተንጣሎ ሽሮው በርበሬው ከሰሉ ጨርቃጨርቁ ጌሾው በቆሎው ገብሱ የዶሮ ገበያው ባንድላይ የሚያሰሙት ህብረ ድምጽ የአንድ መደብ ቋንቋ ያንድ መደብ ትንፋሽ ያንድ መደብ ድምጽና ዜማ ሆኖ አብረው ዥዋዥዌ ይጫወቱ ነበር እኔም ብዙ ጊዜ እቃ ግዛ ተብዬ እየተላኩ የዥዋዥዌው ተካፋይ ሆኛለሁ ::
ዛሬ ላይ ሆኜ ትናንትን ስቃኘው………………
ፍርድእውነቱ የሳር ቤቶች ልጆችን ስትጠቅስ ስንዝሮንና በለጠን ስላስታወስከኝ አመሰግናለሁ በመጀመሪያው ተሳትፎዬ ከቄራ ልጆች በላቸው (ቁራን ) ጌታቸው ያልኩትንም አርሚለሁ፤

ሲያመቸኝ ብቅ እላለሁ ::
http://www.youtube.com/watch?v=Q6vXoA3ohMs&feature=related ትምህርት ቤቴን
ጋብዣለሁ አክባሪ ወንድማችሁ ዝናዬ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Report post
ዲጎኔ

ዋና አለቃ

Joined: 19 Aug 2005
Posts: 3830
Location: united states

PostPosted: Wed Feb 29, 2012 4:26 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁሉም
ወለላዬ ..ዝናዬ ሌሎችም
ይህ ወር የካቲት የህዝቦች ትግል ከነጩ ግራሲያኒ እስከ ጥቁሩ ግራሲያኒ ያሉትን ለማስወገድ የተደረገው ትግል የሚዘከርበት ወር ነው ::እዚህ አሜሪካ የተገፉ ከሰውበታች እንደእቃ የተሸጡ ጥቁሮች ትግል በያመቱ የሚዘከርበት የመሆኑ መገጣጣም ወሩ ሳይልቅ ትንሽ እንድል አነሳሳኝ !
የካቲት 11/1966 የኢህአፓ ታጋዮች ባልዩ አምሮዎች ግርማ አሰግድና ዘሪሁን ከፊትበር የተሰዉ አስረሳኝ ስብስቴ የቦሌና ሌሎችም መጀመሪያ ኢንፎርሜሽን ትምህርት ማቆም ነግረውኝ ትግሉ በይፋ ጀመርኩ ::የካቲት 11 ታላቁ የህዝቦች አብዮት በኢሀፓ ተጀመረ ::መምህራን ተማሪዎች ታክሲ ሾፌሮች ትግሉን ለኮሱ ትግል ተቀጣጥሎ መሬት ላራሹ የገባር ልጆች የተናቀ ባህላቸው ቁዋንቁዋቸው ማንነታቸው በይፋ እውቅና አገኘ በፋሽስቱ ደርግና በወያኔ ታሪኩ ቢነጠቅም አስደናቂ ለውጦች በህዝቦች ዘንድ ተዘገቡ እሰይ አሜን !
በዚያ እልህ አስጨራሽ የለጋ ወጣቶችን ህይወት ባስከፈለ ትግል በመሳተፋችን ሁላችን እዚህ የምንተርክ ሁሉ ደስ ሊለን ይገባል ይህ አምድም የጀግናው መምህር በላይና መሰሎቹን ድንቅ ታሪክ የተወሳበት ስለሆነ አሳዛኝ ሳይሆን አስደናቂ ታሪክ ሊባል ይገባል ::ከላይ ስለሴቶች እንዲወሳ በተባለ መሰረት ታጋዮች እህቶች መሀል የማስታውሳቸውን እዘክራለሁ ::
1.መዝገብ ነሽ አባያ ከኮከብ አሳታሚዎች አንዷ የጎህ መጽሄት አዘጋጅ
2.ሀጎሳ ንግድ ሚንስቴር ኢኮኒሚስት ፋይናስ ኤክስፐርት 70 የተገደለች
3.ገነት በርሄ ድንቅ ጋዜጠኛ 1970 ሳርቤት ተይዛ ከርቸሌ የተፈረደባት
4.ሰናይት /ቤቲ ? ክፍሌ ከወንድሟ ናሁሰናይ ክፍሌ ጋር በደርግ የተረሸነች
5.ሰናይት አቸናፊ ጡቷ በደርግስ ለት ተቆርጦ ከርቸሌ የታሰረች ታጋይ
5.በግርማ ከበደ ሳንጃ የታረደች ብርሀንናሰላም ማተሚያ ታጋይና እህቶቿ
6.ማርታ መብራቱ የጄነራሉ ልጅ ህይወቷ በአውሮፕላን ጠለፋ የከፈለች
7.ሳባ /ማርያም ከወንድሟ ይልማ ጋር ታስራ ተገረፈች ሁውላ የወየኑ

በያ ትውልድ አስደናቂ የትግል ተሳትፎ ህዝቦች ዛሬ ላገኙች የመሬት ባለቤትነት የገባሮቹ እኩልነት እኒያ ታጋዮች በተለይ ሰማታቱ ዘላለም ሲወደሱ ይኖራሉ !
ዝናዬ ይቅርታ የይጥና አብሬን መርዶ ነጋሪ መሆኔ ... ይጥና ለግድያ ሲጠራ ሮችማኑ በርሄ ጀርባውን በቺቺ እየደቆሰ ነበር ጌቱም የቄራ ልጅ እንዲሁ ሲወጣ አዲስ የመጣለት ጫማ ለእናቴ ስጡልኝ ብሎ ወጣ አባተ ይርዳው አላልኩሽም ? ያለኝ ይህ ነፍሰገዳይ ሳይገድለን አይቀርም እያልን አብረን ያወራነው ነበር !ባይገርምህ የልብ የለጋነት ትግል ጉዋዴ የኤርቦርን ጫማው አውልቆ የሰጠኝ ዳንኤል ዘርአይ በትግል መሰዋቱን ብጠረጥርም በይፋ የተረዳሁት ከሁለት አመት በፊት በሌላ በተረፈ ታጋይ እዚህ አሜሪካ ነው :: አላልቀስኩም ታሪኩን አወደስኩ እንጂ !
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ቆንጂት 08

ዋና ኮትኳች

Joined: 19 Dec 2007
Posts: 734

PostPosted: Sat Mar 03, 2012 10:29 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወለላየ ሰላም የሰፈር የመንደረ ሰዎች አልጠፋሁም እንዲያው የምትጽፉትን በትዝታ እየተከታተልኩ ነው በኢሀፓ ዘመን እንኩዋን የማስታውሰው የምለው ስላልነበረኝ ነው ወደ አዳማጭነት የገባሁት በዚያን ሰአት በጣም ልጆች ነበርን ግን አንዴ የማስታውስው ጎረቤታችን አንድቀን የአሰሳ ቀን ነው ተብሎ ሰው በየቤቱ በነበረበት ምሽት እናተ ሳታየኝ ዘይት ግዥልኝ ብላ ትልከኛልች እኔ ሳንቲሙንና ጠርሙሴን ይዤ ወደ ሱቅ ስሄድ ልክ አጋዚያን /ቤት ስደርስ ምሽትና ጽጥ ረጭ ያለ ሌሊት ነበር እና
አሳሾቹ አብዮት ጥባቂዎች ጥበንጃና ዱላ ይዘው ያጋጥሙኛል እኔም በድንጋጤ ወደ አጋዚያን በር ጠጋ ብየ ሳያቸው አንደኛው ወደ እኔ ሲገሰግስ ሌሎቹ አንተ ልጅናት እንዳትነካት ሲሉት ደንግጨ ተመለሼ ወደቤቴ ስሮጥ ጭማየና የየዝኩት ሳንቲም በየአቅጥጫው ሲቀር ከፊትለፊት ኮሌኔል ጎበና ካፖርታችውን ለብሰው ማዶማዶ በሀዘን ሲመለክቱ የነንም ሩጫና ድንጋጠ አይተው ኖሮ በርሬ አባባ ብየ ከከፖርታቸው ውስጥ እንዴት እንደገባሁ እሳቸውም አይዞሽ አልተከቱሉሽም በልው እንባየን ጥረርገው ወደቤተ ሸኙኝ እኔም የዚያች ጎርቤት አደሬዋ ከናተ ጋር ስትጣላ ስልስነበረች ምናልብት ለብቀላ አታላ በዚያ ቀውጢ ቀን ትላከኝ ወይስ ምን ይሁን እስካሁን ትዝ ሲለኝ ይገርመኛል ግን የዛንለት የሆነውን ለቤተሰቦቼ አልተናገርኩም ነበር ከዛ በተርፈ የማስታውሰው ቢኖር እንደታላቅ ወንድሞቻችናን እህቶቻችን የምንወዳቸውና እምንከተላቸው የነበሩት የንፋስልክ ወጣቶች እንደጤዛ ባንድ ወቅት ከሰፈር መጥፋታቸውንና የሰፈር ታዳጊ ልጆች የነብርነው ከያንዳንዱ ጊቢ እገሌ እዚህ ንበር እዚ ንበረች እያልን በናፍቆት ማደጋችንን ነው የተወሰኑትን አሁን በፌስቡክ ከተለያየ ህገር እያገኘሁዋቸው ነው ...ከማስታውሳአቸው መህል ሺበሺ ,ነቢያ ኢብራሂም , አብዶሽ ጅብሪል ...ነብዩ ጎበና ወዴት እንዳሉ አላቅም እነሱም ቅር ጎረቤቶቼ ስለንብሩ ነው የማስታውሳቸው ...
በተረፈ ጨዋታች ሁንን ቀጥሉ ብዙ ማወቅ ያስችላል በተለይ ስሊሀፓ ማንነት ያደረጉትን ትውልድ የከፈሉትን መስዋእትነት ማካፈሉ የታሪክም ግድ /እታ ይመስለኝል ...
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
dannyboy

ኮትኳች

Joined: 25 Jul 2007
Posts: 101

PostPosted: Tue Mar 06, 2012 7:39 pm    Post subject: Reply with quote

ሄይ ንፋስልኮች ታዲያስ ? አንደው ስብስቴን ሳስታውስ ማን ትዝ አለኝ መስላችሁ አሹ በዳዳ የምትባል ድንክ በየአመቱ የምትወድቅ አሁን ሳስበው ምንም አይነት ድጋፍ በሌለበት ህብረተስብ ውስጥ ማደግ አንዴት ከባድ አንደሆነ አንደው ታወስኝ በሌላ በኩል ደግሞ በየግዜው ይፈጠር የነበረው የመኪና አደጋ ከዛ አብዮት የሚባል መአበል መጣና ኢትዮጵያዊነትን ከንስሩ ነቅሎ ቁጭ ኣይ መአልቲ አሉ ወይዘሮ አረጋሽ ለኔ ኢሀአፓም መኢሶንም ደርግም ወያኔም አንድ ናቸው ታሪክ የሚያጠፉ አገር የሚሽጡ ትውልድ የሚያጠፉ አጥፊ አንጂ አልሚ ጠፋ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዲጎኔ

ዋና አለቃ

Joined: 19 Aug 2005
Posts: 3830
Location: united states

PostPosted: Tue Mar 13, 2012 8:29 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችን ይሁን
ውድ የዚያ ዘመን ተራፊዎች እስኪ መልካሙን ትረካ ቀጥሉበት !

dannyboy ስለዛ ዘመን ምን መሆኑ ባለህበት ከተማ ተራፊዎች አይጠፉምና ቁጭ ብለህ ተማር ታሪኩን አጥና ::
እዚህ አንድ ያደርግሀቸውን ቡድኖች የማውቀውን ላብራራልህ እውነትን የሚቀበል ልብ ካለህ :-
ኢህአፓና መኢሶን የተፈጠሩት በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጲያ ተማሪዎች ይባል ከነበረው 1960ዎቹ አጋማሽ ላይ ነበር ::
ኢህአፓ -የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ ከደርግ ጋር በጋራ የሚሰራበት አማራጭ የለም ብሎ የአልባኒያና ቻይና ስታይል ማርሲዝም ያስተማረ ለጊዜያዊ ህዝባዊ መንግስት የታገለ ነበር ::መኢሶን -መላው ኢትዮጲያ ሶሻሊስት ንቅናቄ ደግሞ ከደርግ ጋር በጋራ መስራት ይቻላል ብለው ደርግ ቤተመንግስት ገብተው በጊዜው የነበረውን የህዝብ ድርጅት የሚባለውን በማዋቀር የሶቪየት ህብረት ስታይል ማርሲዝም ሲያራምዱ ቆዩና የኢሀፓን ጥይት ሲቀምሱ ለደርግ ጠቁዋሚ ሆነው ብዙ ካስፈጁ በሁዋላ ራሳቸው ቀኝ መንገደኛ ተባሉና በደርግ እስር ግርፋትና ሞት የተቀበሉ ናቸው ::ደርግ ማብራሪያ የማይሻ በአጼ ላይ በተነሳው ህዝባዊ አብዮት ከጦር ካምፕ የተወከሉ መኮንኖችና ባለሌላ ማረጎች ቡድን ሲሆን መንግስቱ ሀይለማርያም ብቸኛው አምባገነ ሆኖ ተፊካካሪዎቹን አስወግዶ ሁሉንም የፖለቲካ ቡድን ከራሱ ሰደድ በስተቀር በአሰከፊ እስራትና ግድያ ያጠፋ ቡድን ነው ::ወያኔ ደግሞ 1967 በረሀ በገቡ ብሄረተኛ የትግራይ ወጣቶች የተዋቀረ በአልባኒያ ስታይል ማርክሲዝም አያሌዎችን አሰልፎ ሲዋጋ ቆይቶ በልዩልዩ ብሄሮች ስም በተለጣፊ ድርጅቶችና ከምእራባዊያን ባገኘው ድጋፍ ደርግን አስወግዶ ዛሬም ህዝቦችን በመሳሪያ ያለምርጫቸው የሚገዛ ቡድን ነው ::

እውነተኛው ነገር መኢሶንና የመሰሉት የደርግ ደጋፊ ፖሎቲካ ቡድኖች ጥቅም ፈላጊ ሲሆኑ የኢህአፓ አባላትና ደጋፊዎች ግን መስዋእትነትን ለመቀበል ቆርጠው የገቡ ጥቅም ሳይሆን ህዝባዊ አላማ ያላቸው ነበሩ ::
የማይካድ ጥቂት የደርግ ፖለቲካ ደጋፊዎች በእውነት የህዝቦች መብት የሚገዳቸው ተሳስተው የገቡ እነባሮ ቱምሳን የመስሉ ነበሩባቸው ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
dannyboy

ኮትኳች

Joined: 25 Jul 2007
Posts: 101

PostPosted: Wed Mar 14, 2012 4:42 pm    Post subject: Reply with quote

ወንድም ዲጎኔ አንዳልከኝ በጥሞና ለማዳመጥ በወደድኩ ሆኖም ባለፈ ነገር መከራከሩ ጥቅም ያለው አይመስለኝም ብየ ነው : ለማንኛውም ለኢህእፓ አመራር የለኝ አመለካከት ሊቀየር የቻለው አዲስ አበባ ዩኒበርስቲ የመጀመርያ አመት አያለን 1969 መጨረሻ ላይ ይመስለኛል አንጃ ተፈጥሮ ወጣቱ መግቢያ አጥቶ በሚንደፋደፍበት ግዜ በአመራር ላይ የነበሩት አንዳንዶቹ ከደርግ ጋራ በማበር ወጣቱን ማሳደድ በጀመሩበት ግዜ አኔም የዚሁ ስላባ ሆኜ ስለነበር ነው :: አዎ ኢሀአፓ ቆራጥ መስዋአት ለመክፈል በተዘጋጁ ወጣቶች የተሞላ ድርጅት ነበር ህብር ብሄር ነበር : ግን ጠንካራ ድርጅት አልነበርም ለማለት ፈልጌ አንጂ ከደርግ ከዋያኔ ጋራ በአላማ አንድ ናቸው ለማለት አይደለም :: ደርግ ፋሽሽት አገር ኣጥፈ ወያነ ደግሞ ዘረኛ በህያ አመት የስልጣን ዘመን አንክዋን ለመሻሻል ጥረት የማያደርግ አጥፊ ድርጅት ::
ዲጎኔ አኔ ከአሁን በሁዋላ ማደረግ የምችለው ለምወዳት ኢትዮጵያ መጸለይ አግዚአብሄር በኪነ ጥበቡ የሚበጀንን አንዲያረግልን ነው :: ያለንበት ግዜ በጣም አሳዛኝ ሆዳም የበዛበት ሆንዋል አውነት ከጠፋች ስንብታለች :; ከኢትዮጵያውያን ታሪክ ባህል ይልቅ የግለስቦች ታሪክና አምነት የጎላበት ከንቱ ብላሽ የሆነ ዘመን ላይ ደርስናል ::
ዲጎኔ ከተሳሳትኩ አርመኝ ለመተንፍስ ብዬ ነው ውንድሜ አኛ ያደግንበትን ግዜ ሳስትውሰው ተረት ይመስለኛል ለልጆቼ ሥነግራቸው ማመን ይሳናቸዋል ምክንያቱም ከማደግ ይልቅ ወደህዋላ መሄዳችንን ነው የሚገነዘቡት :: ስላም !!!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዲጎኔ

ዋና አለቃ

Joined: 19 Aug 2005
Posts: 3830
Location: united states

PostPosted: Wed Mar 14, 2012 6:38 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ለሁላችን ይሁን
ውድ ወንድምዬ dannyboy ያልከው አባባልን እስማማበታለሁ ::እንዲያ የህይወት መስዋእትነት በመቶሺዎች የሰጡለት ድርጅት አንጃ እየተባባልን የተላለቅነው ክፉ ትዝታችን ሲሆን የባሰው ደግሞ በጥቆማ መዋቅሩን ለመናድ የተደረገውና ሌላው አንጃ ከኢትዮጲያዊ የጋራ አጀንዳ ይልቅ የጎሳ አላማ ወደያዘው ወያኔ ገብቶ ራሱን ኢህዲን ማለቱም ነበር ::እኔም እንዳንተው ለዚያች ሀገርና ህዝቦች ትክክለኛ ፍትህ ክርስቶስ ብቻ እንደሆነ ስለገባኝ ጸሎቴ አልተጉዋደለም ::ነገር ግን አሁን ያንን ዘመን ስንዘክር ለወደፊቱ ትምህርት እርምት ለተሰዉ ውዶችና ቤተሰቦች አክብሮት ነው የማሳስበው ::የነዚያ ቀዳማይ የወጣቱ ትግል ድርጅቶች መሪዎች ለማሰብ ባለፈው ከሁሉም አቅጣጫ ልጆቻቸው ሲመሰክሩ ጉባኤው እንባ በእንባ ሆኖ ነበር ::ተጸጽተን ሳንቀር ለዛች ሀገርና ዛሬም ለሚገፉ ህዝቦቿ ምን እናድርግ ነው የወቅቱ አጀንዳ :: ለልጆቻችን ስንተርክ ለቂምበቀል ሳይሆን ለይቅርታና ለምህረት ለጋራ ጠቀሜታ የሁዋሊት ሳይሆን ወደፊት ይሁን ::
አክባሪህ
ዲጎኔ ሞረቴው ከዚያ ትውልድ ተራፊው

dannyboy እንደጻፈ(ች)ው:
ወንድም ዲጎኔ አንዳልከኝ በጥሞና ለማዳመጥ በወደድኩ ሆኖም ባለፈ ነገር መከራከሩ ጥቅም ያለው አይመስለኝም ብየ ነው : ለማንኛውም ለኢህእፓ አመራር የለኝ አመለካከት ሊቀየር የቻለው አዲስ አበባ ዩኒበርስቲ የመጀመርያ አመት አያለን 1969 መጨረሻ ላይ ይመስለኛል አንጃ ተፈጥሮ ወጣቱ መግቢያ አጥቶ በሚንደፋደፍበት ግዜ በአመራር ላይ የነበሩት አንዳንዶቹ ከደርግ ጋራ በማበር ወጣቱን ማሳደድ በጀመሩበት ግዜ አኔም የዚሁ ስላባ ሆኜ ስለነበር ነው :: አዎ ኢሀአፓ ቆራጥ መስዋአት ለመክፈል በተዘጋጁ ወጣቶች የተሞላ ድርጅት ነበር ህብር ብሄር ነበር : ግን ጠንካራ ድርጅት አልነበርም ለማለት ፈልጌ አንጂ ከደርግ ከዋያኔ ጋራ በአላማ አንድ ናቸው ለማለት አይደለም :: ደርግ ፋሽሽት አገር ኣጥፈ ወያነ ደግሞ ዘረኛ በህያ አመት የስልጣን ዘመን አንክዋን ለመሻሻል ጥረት የማያደርግ አጥፊ ድርጅት ::
ዲጎኔ አኔ ከአሁን በሁዋላ ማደረግ የምችለው ለምወዳት ኢትዮጵያ መጸለይ አግዚአብሄር በኪነ ጥበቡ የሚበጀንን አንዲያረግልን ነው :: ያለንበት ግዜ በጣም አሳዛኝ ሆዳም የበዛበት ሆንዋል አውነት ከጠፋች ስንብታለች :; ከኢትዮጵያውያን ታሪክ ባህል ይልቅ የግለስቦች ታሪክና አምነት የጎላበት ከንቱ ብላሽ የሆነ ዘመን ላይ ደርስናል ::
ዲጎኔ ከተሳሳትኩ አርመኝ ለመተንፍስ ብዬ ነው ውንድሜ አኛ ያደግንበትን ግዜ ሳስትውሰው ተረት ይመስለኛል ለልጆቼ ሥነግራቸው ማመን ይሳናቸዋል ምክንያቱም ከማደግ ይልቅ ወደህዋላ መሄዳችንን ነው የሚገነዘቡት :: ስላም !!!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3
Page 3 of 3

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia