toolbar creator
View previous topic :: View next topic
Author
Message
ቁምቢ Joined: 26 Nov 2012 Posts: 83
Posted: Thu Dec 20, 2012 10:54 pm Post subject: በዚያን ግዜ
ሰላም ዋርካውያን በፓስተር ተስፋዬ ጋቢሶ የተጻፈውን በዚያን ግዜ የተሰኝውን መፅሀፍ በትንሹም ቢሆን እዚ ልተርክላችሁ ...........እጅግ አስገራሚና አሳዛኝ ታሪኮችን የያዘ መጽሀፍ ነው ::
እንግዲህ መጽሀፍ እንዲህ ብሎ ይጀምራል ....
ሚያዝያ 10 1968 ዓ ,ም በጸሎት ቤቱ ውስጥ በአምልኮ ላይ የነበሩ ምዕመናን ባዳዳሲ እንግዶች በድንገት ተከበቡ .........ከዚያም እንዲወጡና በከተማይቱ ዋና ዋና መንገዶች ላይም ተሰልፈው እንዲሄዱ ታዘዙ ..........አስገዳጆቹም በወቅቱ የነበረው የቀበሌ አመራርና ወጣቶች ነበሩ ..........የእምነት ጥላቻው በተግባር በታገዘ ጠንካራ ተቃውሞ ተገለጠ ::
በእለቱ የነበረው ዙረት ሲያበቃ የተያዙትን ምዕመናና አገልጋዮችን ወደ ቀበሌ ስምንት ወሰዷቸው ................በእጆቻቸውም የተገኙትን መጽሀፍ ቅዱሶች በመሰብሰብ ጋዝ ካርከፈከፉባቸው በኃላ አቃጠሏቸው ......ከዚያም ጭሱን "ታጠኑት !" አሉዋቸው .........
በ 1970 አጋማሽ ላይም በምዕመናኑ ላይ ቀላል የማይባል ስደት ደርሷል .........በዚያን ግዜ አንዳንድ እህቶቻችን መንገድ ላይ ተጥለው እንደ እባብ ጭንቅላታቸውን ተቀጥቅጠዋል ............ሌሎች ደግሞ በደረሰባቸው ከፈተኛ ድብደባ የተነሳ እራሳቸውን እየሳቱ ለሕክምና እርዳታ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል ......በተጨማሪም እንደነ ተፈሪ ኬላ አለማየው መንግስቱ ያሉ .........በሰደፍ እየተፈነከቱ ደማቸው የታሰሩበትን ክፍል አጥለቅልቆታል ..
ከፓሊስ ጣቢያው እንደወጣን .......በአውራው ጎዳና ላይ ፊታችንን ወደ ምዕራብ አድርገን ጥቂት እንደተራመድን .....ሶምሶማ ሩጫ ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ ተሰጠን .....መሮጥ ጀመርን ::..........ጥቂት እንደሮጥን አልማዝ አስሟ ተቀስቅሶ አመማትና ወደ ኃላ ቀረች .......ሙሉ እመቤትም ብትሆን የኛን ያህል መሮጥ ስላልቻለች ተራርቀን አየው ..........ፍጥነቴን ለመቀነስ ሞከርኩኝ ወንዶቹ እያጣደፉ አስቸገሩን .::........እንደምንም ኳስ ሜዳ ደረስን ::.............ትእዛዙም ሩጥ ! ተመለስ ! ተኛ ! ተንከባለል ! አሞራ ጉብ ጉብ ዝለል ! በሚል እየተፈራረቀ ተፋፋመ ::.........ይህ ሁሉ ትዛዝ ከዱላ ከጉማሬና ከእርግጫ ጋር ያጣድፈን ገባ ::
ስፓርቱ ወታደራዊ ቅጣት ማለት ይሻላል ብዙ ታሪክ ነበረው ::........በስፓርት ስም ማንገላታቱ እየደበደቡና እየረገጡ ማሰቃየት እንዲሁም በጭቃ ላይ እያንከባለሊ መጫወት ሁሉም ጋር የተደረገ ሲሆን ለየት የሚሉ ጥቂት ድርጊቶች አልጠፉም ::..........በቀበሌ 01 ለየት የሚለው ሌሊት ሌሊት ወደ ወንዝ ወስዶ በቀዝቃዛ ውሀ ውስጥ መንከርና ከዚያም አውጥቶ በአቧራ እንዲለወሱ ማድረጉ ነበር ..............እነ ከበደ አርጋው .አየለ አበራ . ማርታና ሀና አሰፋ የተባሉ እህትማማቾች የዚህ ጽዋ ተካፋዮች ነበሩ ::...
በቀበሌ 05 የነበሩትን ግን ለ 12 ቀናት ያህል አልፈቷቸውም .....ከሌሎች ስፍራዎች ይልቅ መከራው ተጠናክሮ የተራዘመው እነሱ ጋር ነበር ማለት ይቻላል .......ጫካ እያወረዱ በየገደሉ ላይ እያንከባለሉ ነበር የተጫወቱባቸው ........ከዚህ ሁሉ ጋር ዱላውና እርግጫው ርኅራኄ የማይታይበትና ፋታ የማይሰጥ ነበር ::.........ከኃይሉ በቀለ ሌላ ምንትዋብ አረሩ በድብደባ ብዛት እራሷን ስታ ስታጓራ አስደንጋጭ ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር ..... ይቀጥላል ... _________________ ☻ የሰው ልጅ
መውደድ ሲችል መጥላቱ
መምከር ሲችል ማማቱ
መስራት ሲችል መቅናቱ
ማስታረቅ ሲችል ማጣላቱ
ያሳዝናል የሰው ፍጥረት በሕይወቱ፥፥
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
You cannot post new topics in this forum You cannot reply to topics in this forum You cannot edit your posts in this forum You cannot delete your posts in this forum You cannot vote in polls in this forum