WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ቤተ እግዚአብሄር ሄጄ አልቅሼ ተመለስኩ ::

 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General


 
View previous topic :: View next topic  
Author Message
ክቡራን

ዋና አለቃ


Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5048

PostPosted: Wed Jan 02, 2013 7:38 pm    Post subject: ቤተ እግዚአብሄር ሄጄ አልቅሼ ተመለስኩ :: Reply with quote

መቼም ነገራችን ሁሉ ከጅብ ቆዳ የተሰራ ይመስል ወሬአችን ሁሉ ብላው ብላው ብላው ..አኡውውውውውው ..ማለት ሆኗል :: አትታዘቡኝና የሰው ጅቦች ሆነናል :: ያዲሱን አመት መግቢያ በጽሞና ለማሳለፍ , እግዛኢብሄር በሁለት አስራ ሁለት የሰራሁትን ኅጢያት ይቅር እንዲለኝና ሁለት አስራ ሶስትን በድል እንዲያሸጋግረኝ ንስህ ለመግባት ወዲህም አምላኬ አመቱን ሙሉ ላደረገልኝ ጥበቃ ምስጋናን ለማቅረብ ዲሴምበር 31ለጃንዋሪ 1 -ዋዜማ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነበርኩ :: እኔ ከራሴ ጋር ከእጊዚአብሄር ጋር ተነጋግሬአለሁ :: አምላኬም ሲንሰር የሆነውን ጸሎቴን ሰሞቶኛል :: እሪ ብዬ ያለቀስሉት ግን አስተማሪው በመድረክ ላይ የሚሉትና እኔ የማውቀው መጽሀፍ ቅዱስ አንድ አልሆን ብለውኝ ነው :: ሰውየው ( ፓስተር እንዳልላቸው የሚያወሩት ስለ ራሳቸው ነው ...) ""ከድንጋይ እርሙታ ከወጀብ ጋጋታ ያወጣኝ አምላክ ዛሬም ጠላቶቼ በኔ ላይ የሚያሴሩትን ሴራ ይበትነዋል .."" ሲሉ እኚህ ሰውዬ ወዴት እየሄዱ ነው ?? አልኩ ...እሳቸው ጠላት የሚሏቸው በኅሳብ ካልተስሟሟቸው የቤተ ክርስቲያኑ ኮንግርጌሽን አባላት ጋር በገቡት እንኪያ ሰላምታ መሆኑን የጋበዘኝ ጔደኛዬ በኌላ አጫወተኝ :: እኚህ ፓስተር በመጽሀፍ ቅዱስ ፋንታ ጔንዴ ቢኖራቸው ከደቀ መዝሙሩ ጀመረው እስከ አሸሩ ድረስ ያሉትን ጌታ አዞኛል ብለው ባንዳንድ ጥይት ሊለቅሟቸው እንደሆነ መንፈስ አሳየኝና እሪ አልኩ :: እረ እሳቸውም ቆይተው ተናገሩት "" ...ድሮ አባቶታችን የሚያናድዳቸው ሰው ወይኔ ላንተ አንድ ጥይት ነበር የሚበቃህ ይሉት ነበር ..."" በማለት መንፈስ ለኔ ያሳየኝን አጸኑልኝ :: እንዲህ ናት ስብከት !! አይ አንቺ ዶላር !!!! ስንቱን ባህል አልባ አደርገሽው !! መጣሁ ..እስኪ የታዘብኩትን እነገራችኌለሁ :: እንድንማማር ነው ይሄን ያመጣሁት እንጂ ከቶውንም ለማማት አይደለም :: የወንድሜ ዲጎኔ መንፈስ ምን ሊያስብ እንደሚችል ቀድሜ ስለማውቅ ነው ይሄን የምለው ::
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ


Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5048

PostPosted: Thu Jan 03, 2013 10:59 pm    Post subject: Reply with quote

ወንድሜ ዲጎኔ እዚች ቤት ደፍሮ ሊመጣ አልቻለም ለምን ይሆን ..? Very Happy እንግዲያስ ልቀጥል መጣሁ ::
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
የተሞናሞነው

ውሃ አጠጪ


Joined: 11 May 2011
Posts: 1126

PostPosted: Thu Jan 03, 2013 11:39 pm    Post subject: Reply with quote

ውሻ /ክርስቲያን ውስጥ ምን ልትሰራ ገባች Rolling Eyes
_________________
http://yetemonamonew.wordpress.com/
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ


Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5048

PostPosted: Fri Jan 04, 2013 5:43 am    Post subject: Reply with quote

መቼም የሆነውን ነገር መናገሬ ለጉራ አይታይብኝ እንጂ አስቀድማቹ ጽድቁን ፈልጉ ሌላው ሁሉ ይጨመርላችኌል የሚለው ቃል ጠጅ ቤት ገብቶ ሞቅ ያለው ዲያቆን ተሳስቶ የተናገረው አይደለም :: የመጽሀፍ ኅቅ ነው አስተዋይ ልብ ላለው ቡዙ ነገርም ገላጭ ነው :: እናም ግድየላቹም እቺ አመት ሳትሆነኝ አትቀርም ... ባዲሱ አመት የእጊዚአብሄርን ፊት ለመሻት አይኖቼን ወደ ሰማይ አቅንቼ እንደነበር ገልጪ ነበር ... አይኖቼን ወደ መሬት ስመለስ አልማዝን አገኘኌት :: አልማዝን አይቼ አልማዝን ሳያት ሁለተኛዋ አልማዝ ብትመጣ ድንገት ሁለቱም አልማዞች ... Very Happy ይበቃል ... Very Happy .
ላንድ አመት እቺን ልጅ ሰፈልጋት ነበር :: በልቤ በጣም እመኛት ነበር ...ግን እሷም ቢዚ ናት ውበቷ በራሱ ክፋቷ ነበር :: ፈላጊዋ ቡዙ ሆነ :: አንዱም እኔ ነበረኩ :: የምችለውን ያህል ሞከርኩ :: ካላት ቢዚ ስኬቹአል እንደምፈልጋት ላገኛት አልቻልኩም :: በመኅል አገር ቤት እናቷ ታማመች ተባለና ሄደች ::እኔም ተስፋ ቆረጥኩ :: አንድ ቀን ስካያፕ ላይ ተገናኝን አንጠፋፋ ስትመጪ ደውዩ አልኩ :: በልቤ ግን ""ባፋንኩሎ ""! ብያታለሁ :: አልዋሻችሁም ...እሺ እደውልላሀለሁ አለች .... እንደማታደርገው ስላወኩ እሺታውን ለታይታ ያህል ተቀበልኩ ::
ልክ ያዲሱ አመት እለት ስልክ ደወለችልኝ ..
""...እንኴን አደርሰህ ልልህ "" ነው ...አለችኝ :: ደስ አለኝ እኔም አጸፋውን መለስኩ :: ብትፈልግ ዛሬ ምሽት መገናኘት እንችላለን አለችኝ ...ከሌሎች ሰዎች ጋር ቀጠሮ ነበረኝ ...አላመነታሁም እሺ አልኩ የነሱ ይደርሳል :: ብነግራቸው የሚያስቸግሩኝ አይደሉም አቢሰኒኢያ ሬስቶራንት ተቃጠርን :: ድሮም ቀይ ናት ከቅላቷ ጋር የሚሄድ ቀይ የእራት ልብስ ከላዩ ላይ ጠቆር ያለ ሹራብ አድርጋ ራሷን ሊያስገባ ትንሽ የሚቀረው ሰማያዊ ቦርሳ ይዛ መጣች :: ለለወጥ ያህል ቀይ ሊፒስቲክ ሳይሆን ወደ ፒንክ ከለር የሚያደላ የከንፈር ቀለም ተቀብታለች :: ስትገባ ተመጋቢውም ከምግቡ ላይ ቀምቃሚውም ከመጠጡ ቀና እያለ ሲገርመማት ""ቫይቡ "" ተሰሞቶኛል :: Cool እረ ዘፋኙም እሷ ስትገባ የባሰ ድምጹን ሳያጮሀው አይቀርም :: ውቅያኖስ ዳር እንደተተከለች ዘምባባ ዘንጠፍ ቀና እያለች በቀጥታ እኔ ወዳለሁበት ጠረጴዛ ስትደርስ ብድግ ብዬ እንደ ተነፋፈቁ ፍቅረኞች ተቃቀፍን :: በልቤ አስቀድማቹ ጽድቁን ፈለጉ የምትለዋ ጥቅስ ጆሮዬ ላይ አንቃጨለችብኝ :: ሜርድ :: ባለፈው አመት ስፈልጋት ቢዚ ሆኗ ተስፋ የቆረጥኩባት ልጅ ዛሬ ሁለታችን ብቻ በመከካላችን በሚበራው የጠረጴዛ ሻም እየተያየን በነጻነት መጫወት ጀመርን :: እንዲህ የፍቅርን አበባ እየቀነጣጠስን ባለንበት ሰአት አንድ አርግራጊ ( ጀብራሬ ) ነገር ለመደንስ ወደ መድረኩ ሲወጣ የሚጠጣውን ውስኪ የያዘ ብርጭቆ እኛ ጠረጰዛ ላይ እንደ ቀልድ አስቀምጦ እሽሩሩ በሚለው የፍሬው ዘፈን መወረገረግ ጀመረ :: እሷ ሳቅ አለች :: እኔ አልሳኩም ፈገግ አልኩ :: ቴክ ኢስ ኢዚ አይነት ነገር ...ይቅርታም አለመጠየቁ አስገርሞኛል ...ዘፈኑ ሲያልቅ ብርጭቆውን መጥቶ ይወስዳል ብዬ ስጠብቅ እንደውም ወደ ሬስት ሩም ሄደ ::
"" ታውቂያዋለሽ እንዴ ??"" ...አልኴት ..
""እረ እኔ ይሄን የት ነው የማውቀው ..?" አለችኝ ...
""እንግዲያው ሊለክፍሽ ፈልጎ ነው አልኩ .."" ስሜቷን ለመረዳት ፊቷን ትክ ብዬ አያየሁ ...
""ውይ ድንቄም ለከፋ !!"" አለች ከንፈሯን ጣል ስታደርገው አንድ ነገር በውስጤ ሲላወስ ተሰማኝ :: ልጅቷ ውብ ናት ውብ መሆኗን እሷም ታውቅወአለች :: አንድ ጊዜ እንደውም ክሊፕ የሚሰሩ ሰዎች ለሆነ አጭር ሾው ሰው ከፈለጉ ወይም ከሰማህ ንገረኝ .."" ብላኝ ነበር ...ውብ መሆኗን እሷም ታውቅዋለች ::
ይሄ ሁሉ ሲሆን ልጁ መጠጡን እኛ ትቶ እሱ ባንኮኒ ሄዶ ሌላ መጠጥ አዞ አየሁት :: አስተናጋጇን ጠርቼ መጠጡን ወስዳ አጠገቡ እንድታስቀምጠው እግረ መነገዷንም ሂሳቡን በደንብ እንድታሰላ በጆሮዋ ሹክ አልኰት :: ""ግርግር ለሌባ ይመቻል "" ስላት ሳቅ ያዛት :: ዘፋኙ ዘፈኑን ጨርሶ ከመድረኩ ሲወርድ ይሄው ቀዌ በመጥጥ ትኩሳት ""ጌታ ይባርክህ ..."" ጌታ ይባርክህ .."" !! አያለ ዘፋኙን ሲያደድንቅ ሰማሁት ::
""እንዴ ይሄ ልጅ ጴንጤ ነው እንዴ ?" አልኴት ..
የምታስተናግደውን ልጅ .
""ውይ አይደለም ...ባይገርምህ ከዚህ ቤት አይለይም ..ደንበኛችን ነው .....ሱማሌ ነው ...የኢትዮጵያ ሱማሌ ነው አለችኝ ...!! ....!! እኔ ግን አትታዘቡኝና ""ጌታ ይባርክህ ሲል ወንድሜ ዲጎኔ ባካል የመጣብኝ ነው የመሰለኝ ...በዚህ ላይ ደሞ ሱማሌ ነው ስትለኝ ወንድሜ ዲጎኔ እኮ ድሮ በኒ ሰፈር እያለ ቁራን እቀራ ነበር ስላለ እሱ መሆን አለበት እያልኩ ማሰቤ አልቀረም ነበር :: Very Happy
ካስቲ ሌላ ቀጠሮ የሚመጣው እሁድ አለኝ :: ግድየላቹም ይቺ አመት የኔ ሳትሆን አትቀርም .....ሰላማት !!

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka General All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

 
Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum


Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia