View previous topic :: View next topic
Author
Message
ዉቃው Joined: 07 Jan 2007 Posts: 968
Posted: Fri Mar 02, 2012 5:18 am Post subject: አቶ ስብሃት ተገደለ ወይስ ሞተ ?
"ይህንን ህግ ስትጥስ የማነው ይሄ ቅሌታም ሽማግሌ ትባላለህ " አለ ስብሃት :: በጨዋታ ፕሮግራም :: ቁም ነገሩ ሪጮ የዋርካዋ ቅሌቱን ባይኗ በጆሮዋ በበረቱ ታዝባለች ::
ይህንን ጥያቄ ለመጠየቅ ያሳሰበኝ ..እንደው አቧራ አስነስቶ ...የማያባራ አተካሮ ለመፍጠር ሳይሆን ....ምናላባች አቶ ስብሃት ከሞተ በኋላ ..ሞተ ...በቃ አርጅቶ ...ወዶ ለዘመናት ያጤሰውም ሲጋራ ወይም በህግ የተፈቀደለኝ ያለው ዕጸ -ፋርስ የጉሮሮ ካንሰር አምጥቶ አሳምሞት ..መጠጡና ..ጫቱም ተጨመሮ ....እያልን ምክንያቶች ማቅረብ ይቻላል ::
ግን ደግሞ .....በጉሮሮ ካንሰር ..በቅርቡ አሜሪካዊው ..አቶ ማይክል ዳግላስ ....ከብዙ መጠጥና ማጤስ ብዛት ለዚህ በቅቻለሁ ...ብሎ በናሽናል ቴሌቪዥን ከታወጀና ..ብዙም ሳይቆይ ..አሁን ለጊዜውም ቢሆን ጤና አግኝቶ እያየነው ነው :: [ያው አሜሪካ ..ገንዘቡ ...ህክምናው ምናምን ......እንዳትሉኝ ] ጉዳዬ እሱ አየደለምና !
ሊዲንግ ሲ ማን ዘነበ ወላ [ያልተነጠቀ ማዕረጉን አክብሬ ].... ሲያብራራ [አወራሩ የመንደር ዱርዬ መስሎብኛል (ለኔ )] http://www.youtube.com/watch?v=0Ly6b53uP-M ከአቶ ስብሐት ጋር ሰለሞት ብዙ እንዳወሩ ..ደምሰው {አቶ ስብሃት የሚያሳድገው የተባለ ጸጉሩ ገባ ያለ ወጣት } ሚስ ኮል አረገልኝ ...አይ የለም ኤሴኤም ኤስ አረገልኝና ...ጋሽ ስብሐት ስሪንጁን ነቅሎ ጣለው አለኝ ...ባላ ብላ ..እያለ ያብራራል :: እናም ..ስሪንጁ [{ፊዲንግ ቲዩቡ } ወይም አይቪ ፍሉዱ ] እንደህግ ተከበረና ..እንደ ሊዲንግ ሲ ማን ዘነበ ወላ አባባል ..(እኔ ያልኩት ሆነ )
ከዛ ሊዲንግ ሲማን ዘነበ ወላ በአዲስ አድማስ ዌብ -ሳይት ይህ አለ ::
Quote: የስብሃት የመጨረሻ ቀናት እንዴት ነበሩ ?
በሽታው የጉሮሮ ካንሰር መሆኑ ከታወቀ በኋላ ውጭ አገር ወስዶ ለማሳከም በጣም ጥረት ተደርጐ ነበር፡፡ የሬዲዮ ፕሮግራም ሁሉ ሊሰራ ታቅዶ ነበር፡፡ ዶ /ር ወንድሙ ተወልደም በጣም ደክሟል፡፡ ግን ሁኔታው ተስፋ አስቆራጭ መሆኑን ካወቅን በኋላ የሠላም እረፍት እንዲያገኝ ዝም ብለን መንከባከብ ጀመርን፡፡ እኔ ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት ሐሙስ ዕለት ነው፡፡ እሱ የሚያሳድገው ደምሰው የሚባል ልጅ አለ - ሆስፒታል ውስጥ እየጠበቀው ነበር፡፡ እሱ እንደነገረኝ ከምሽቱ 5 ሰዓት ከምናምን ላይ ምግቡን በቲዩብ ሰጠው፡፡
ያንን ወሰደ፡፡ ትንሽ ጋደም ካልኩበት ስነቃ ስብሃት ለምግብ መውሰጃ የተሰራለትን ቱቦ (ቲዩብ ) ነቃቅሎ ጣለው “ምነው ?” ስለው “ከዚህ በላይ እየተሰቃየሁ መኖር አልፈልግም፡፡ በጣም የምወድህ ልጅ ነህ፤ የዛኑ ያህል እንድጠላህ እያደረከኝ ነው፡፡ ምክንያቱም መኖር አልፈልግም እያልኩህ በግድ እንድኖር እያስገደድከኝ ነው” አለኝ ብሎ ነገረኝ፡፡ ቃሉ እንደ ህግ እንዲከበርለት ፈልገናል፡፡
ሐሙስ ዕለት ተረኛው እኔ ነበርኩ፡፡ እየጠበኩት እያለ ቀን ላይ ብንን አለና በምልክት ወረቀት ስጠኝ አለኝ ሰጠሁት፡፡ በግራ እጁ “ተኛ” ብሎ ፃፈልኝ፡፡ እሺ አልኩት፡፡ በዛን ወቅት ጉሮሮው ላይ ኩርር የሚል ነገር እያስቸገረው ነበር፡፡
ለምን መሰለህ እንዲህ የሚያደርግህ ? ምግብ ስለማትወስድ ነው የሚያሰቃይህ አልኩትና ቲዩቡ ተመልሶ እንዲገባልህ ትፈልጋለህ ወይ ? አልኩት አዎ አለኝ፡፡
ከቤተሰቦቹ ጋር ሆነን ቱዩቡ እንደገና እንዲቀጠልለት ለማድረግ ስንሞክር የጉሮሮው እጢ አብጦ ቱዩቡን አላስገባ አለን፡፡ በቃ ያኔ ተስፋ ቆረጥኩ፡፡ የመጨረሻችንም ዕለት ያቺ ሆነች፡፡
http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_content&view=article&id=1820:2012-02-25-14-43-46&catid=96:3d-computer-graphics&Itemid=503
ይሄ ኮንስፓይረሲ አይደለም :: ስብሃት ከሞተ በኍላ ..በኢትዮጵያ ናሽናል ቴሌቭዥን [ለጊዜው ናሽናል ይባልልኝ ]...አትንካው የኔን አቋም ይቀበላሉ {በኔ ትርጉም ሌት ሂም ዳይ ) ያለው ሰውዬ ..ስብሃት ትዩቡ ተቀጥሎለት ከሰቃዩ ተንፈስ እንዲል ሲሞክር ይታያል ::
መች ይህ ብቻ ? ስብሃት ... ሰባት ቤት ሽምግልንና ሞትን እንደሚፈራ ሰምተና አንበናል :: (http://www.shegerfm.com/ የስብሐት ገብረእግዚአብሄር መታሰቢያ ከደረጄ ሃይሌ ጋር part one Feb 25, 2012) አጋፋሪ እንደሻው ..ሞቱን የሚፈሩት እኮ ..እኛው ራሳችን ነኝ ..ይላል :: ስብሃት በመጨረሻው ሰዓትም ቢሆን ..ሞትን ፈልጎ እንዳልነበር ሁኔታዎች ያስረዳሉ : በኔ እምነት :: ዕድምሜ ልኩን ሞትን እፈራለሁ ያለ ..ሞት ጥርሱ አግጥጦ ሲመጣ ...?????
ለመሆኑ ..ቴሪ ሻይቮ ....በቱዩብም ሆነ በሌላ ዘለዓለም ትኑርልን ..ያሉቱ ..ይወለዷዋት ወላጆቿ ወይስ ባሏ ? አዎን ወላጆቿ ትኑር ሲሉ ባሏ በቃ አለ :: ዳኛው እስትንፋሷ በባሏ ይወሰን አለ :: በባሏም ተወሰነ :: ባሏ ግን እንኳን ሞተችለት አገባ ! http://www.cbsnews.com/8301-201_162-1227404.html ይሞታል እንዴ !
ስብሃት ሞተ ::
ዘነበ ወላስ ?
Quote: ደስ የሚለኝ ነገር እሱ ከማለፉ በፊት አርትኦት ችዬ አሳይቼው ነው ያለፈው፡፡ አሁንም እጄ ላይ ያሉ ሥራዎች አሉ፤ እነሱንና የቀሩኝን ሃሳቦች ጨማምሬ እንዲሁም እሱን ለማዳን የተደረጉ ሙከራዎችን ጨማምሬ “ማስታወሻ”ን ከሁለትና ከሶስት ወራት በኋላ እንደገና አሳትመዋለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
ይመቻችሁ :: ማስታወሻ ደግሞ ሊታተም ነው :: ገቢው ...ህም .. ለኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ይሁን :: _________________ ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
recho Joined: 20 Sep 2004 Posts: 2991 Location: Earth
Posted: Fri Mar 02, 2012 2:51 pm Post subject: Re: አቶ ስብሃት ተገደለ ወይስ ሞተ ?
ዉቃው እንደጻፈ(ች)ው : "ይህንን ህግ ስትጥስ የማነው ይሄ ቅሌታም ሽማግሌ ትባላለህ " አለ ስብሃት :: በጨዋታ ፕሮግራም :: ቁም ነገሩ ሪጮ የዋርካዋ ቅሌቱን ባይኗ በጆሮዋ በበረቱ ታዝባለች ::
ዌል ስሜን ባታነሳ ኖሮ በስብሀት ዙሪያ ዋርካ ላይ ምንም ላለማለት ወስኜ ነበር ... ማብራራት ካለብኝ ግን ... ስብሀትም ሆነ ማንም ላይ ግላዊ የሆነ ግጭት የለኝም ሰው ሁሉ ሰዋዊ ለሆኑ ህጎች ሁሉ ይገዙም አልልም .. ብዙ ሰዎች መጥፎ ስለሆኑ ሳይሆን ስላላመኑብት የሶሳይቱውን ህግ ሳይጠብቁም ሳያከብሩም ኖረዋል ..
ስብሀት ... ደራሲ ስብሀት .. ጸሀፊ ስብሀት ... ያላችሁትን በሉት ... ለኢትዩዽያ ስነጽሁፍ እድገት አስተዋጾ አድርጎ ሊሆን ይችላል .. አድርግዋል ወይንም አላረገም ብዬ ለመናገር ግን በጥልቀት የማውቀው ነገር የለም እንደዚሁም መስፈርቱንም አላውቅም ... በይ ግን ከተባልኩ ዋርካ ላይ የማውቃቸው ጨዋ ጸሀፊያን ዋናው , ፓኑ , ዋኖስ , ወለላዬ , ውቃው ... ለኔ ብዙ ያበረክቱ ጸሀፊያን ናቸው .. እንግዲህ ሰው የሚያውቀውን ነው የሚፈርደው ... ከዛ ውጪ አቶ ስብሀት ከስሩ የሚያስከትላቸው የልጅ ልጅ የሚሆኑትን ወጣቶች ምን እያስተማራቸው እንደሆነስ ልብ ብለናል ? ልቅነት ውበት ከሆነ ይሄን እኔ አላቅም .. ልቅነት , አደንዛዥ እጽ ተገዥነት , እንደ እንሰሳ ልቅ ወሲብን ሲያስቡና በተግባርም እንዲያውሉት መመከር እናም ደግሞ የ እግዜሩም ህግ የሆነውን ታላቅ ስተት እንደቀልድ ምንም አይደል ብለው እንዲያልፉት ጭንቅላታቸውን መቅረጽ ታላቅ ሰው ያስብላል ? እኔ እንግዲህ ከአገር ከወጣሁ 4አመት በላይ ሆነኝ መሰል ... በዛን ጊዜ ዳታ ነው የማወራው ... ስብሀት ሲባል ራሱ ያቅለሸልሸኛል .. ጥሩ ሰው ሊሆን ይችላል ስራው ግን የዲያቢሎስ ነው .. ምን አለበት እነዛን ከስሩ የሚያስከትላቸውን ቡችላዎቹን ስነጽሁፍን ቢያስተምራቸው ሀሽሽ ማጨስ ምንም ማለት እንዳልሆነና ሴክስ ከዚችም ከዛችም ጋር እያረጉ ስለሱ እየቀለዱ መዋል ምንም አለመሆኑን ከሚያስተምር ? እንግዲህ እርፍ በሉት .. ለነ ስብሀት ተራ ዱርዬ ነው .. ሞተ ? ዌል ማን ይቀራል .. ለሚወዱት "አድናቂዎቹ " መጽናናት ይስጣቸው .. እርግጥ ታላቅ አጥፊ አጥተዋል ... ግን ስብሀት የዘራው ዘር ለስንት ጀነሬሽን ይበቃ ይሆን ... ለመሁኑ በይፋ ሀሽሽ የሚያጨስ የሚያስጨስ መንግስታዊ ፍቃድ ያለው አንድ ስው ለኢትዩዺያ ወጣት በርግጥ ችግር ፈቺ .. አስተማሪ ነበረ ብላቹ ልትከራከሩኝ ነው ? እርግጥ ወጣቱ ችግሩን በሚያጨሰው ምናምን እንዲረሳ አድርጎታል .. ለዛ ታላቅ ምስጋና ይገባዋል .. ማለት ችግር መርሳት መፍትሄ ከሆነ
ማይ ፐርሰናል ኤክሲፕሪያንስ ...እናትሽን ል #$ት ብሎ ሲሳደብ በዛ ሽበትና እርጅናው ላይ በጣም ደንግጫለሁ !!!
በሉ ተሳደቡ , አንቁዋሹኝ , ያላችሁትን በሉ .. እንደሰው ጥሩ ሊሆን ይችላል .. ስራው ከ እድሜው አይሄድም .. !!!
ሪቾ _________________ ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ጩጉዳ Joined: 31 Jan 2005 Posts: 1198 Location: Studio City, Wilson Republic
Posted: Fri Mar 02, 2012 3:13 pm Post subject:
ዌል ስብሐት የ 76 ዐመት አዛውንት መሆኑን አንዘንጋ ጎበዝ (ለዚያውም ትክክለኛ የልደት ቀን ሪከርድ ስለማይታወቅ ዕድሜው እሱ ነው እንበለውና ) በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ሰውዬው ኑሮው ዕድሜውን ሁሉ አልኮል ቤት የኖረ መሆኑም አይረሳ ይህ ሁሉ ተጨማምሮበት የኑሮ ሁኔታና የሕክምና ኬር እምብዛም በሆነበት አገራችን ምን ይጠበቃል ? ?
ሬቾ ከሞላ ጎደል ሀሳብሽን እጋራለሁ ሰውዬው ለወጣቱ መልካም ምሣሌ አልነበረም ግን በጣም ታለንትድ የሆነ የሥነጽሑፍ እውቀት የነበረው ግለሰብ እንደነበረና ብዙዎችንም ኢንስፓየር ያረገ እኔንም ጭምር በልጅነቴ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የእሱን አምድ እያነበብኩ ትርጉሙን እያብሰለሰለኩ ነው ያደኩት ::
ሬቾ : ሞት ለማንም የማይቀር መሆኑ እርግጥ ቢሆንም ያ ቀን እስኪደርስ ሁሉም ለቤሰሰቡና ለ loved ones በጣም አስፈላጊ ፍጡር ነውና ሞትን የመሰለ ነገር መመኘት ጥሩ አይደለም :: ግን አንቺ ግን .... ከአገር ቤት ከወጣሁ አራት ዐመት ሆነኝ መሰለኝ ያልሽ መሰለኝ ተይ እንጂ ..... ዋርካን ጆይን ካረግሽ እንኳ ይሄው 8 ዐመት ደፈንሽ ወይስ አንዷ ከኍላ ጠፍታብሽ ነው ወይም ደግሞ አገር ቤት እንደገና ቪዚት ካረግሺበት አንስቶ ...... መሆኑ ነው ?? ባልሳሳት ዋርካ ሥራዋን በጀመረች ገና በአመቷ 2001 ተጀምራ ወዲያው ጨለመች :: አይደል እንዴ ? _________________ መታገስንና መቻልን የመሰለ ብቀላ የለም ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
recho Joined: 20 Sep 2004 Posts: 2991 Location: Earth
Posted: Fri Mar 02, 2012 3:35 pm Post subject:
ጩጉዳ እንደጻፈ(ች)ው :
ሬቾ ከሞላ ጎደል ሀሳብሽን እጋራለሁ ሰውዬው ለወጣቱ መልካም ምሣሌ አልነበረም ግን በጣም ታለንትድ የሆነ የሥነጽሑፍ እውቀት የነበረው ግለሰብ እንደነበረና ብዙዎችንም ኢንስፓየር ያረገ እኔንም ጭምር በልጅነቴ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የእሱን አምድ እያነበብኩ ትርጉሙን እያብሰለሰለኩ ነው ያደኩት ::
ታንክስ ብሮ .. ሀሳቤን የተሙዋላ አርገህዋል .. ጥሩ ይጽፋል .. አንዳንዴ የሚናገራቸው (ጨዋዎቹን ) ንግግሮቹን ወድለታለሁ .. ፈኒም ነው .. ግን ያለውን ችሎታ እና ኤነርጂ አላስፈላጊ ነገር ላይ አባክኖታል ብዬ አምናለሁ .. እንዳልከው ለወጣቱ ጥሩ አርአያ አይደለም .. ጋሽ ስብሀትት ብለው ነው እየተከተሉት ያሉት እና ከሱም ምን ተማሩ ???? መልሱት ...
Quote: ሬቾ : ሞት ለማንም የማይቀር መሆኑ እርግጥ ቢሆንም ያ ቀን እስኪደርስ ሁሉም ለቤሰሰቡና ለ loved ones በጣም አስፈላጊ ፍጡር ነውና ሞትን የመሰለ ነገር መመኘት ጥሩ አይደለም ::
ሞቱን ተመኘሁ እንዴ ? እንደዛ ያልኩ አልመሰለኝም .. ካልኩ ስተት ነው ይታረማል ... ማንም አይሙት ..ለሚወዱት ቤተሰቦቹ እና አድናቂዎቹ ቢኖርላቸው ጥሩ ነው .. ! መጽናናቱን ይስጣቸው .. !
Quote: ግን አንቺ ግን .... ከአገር ቤት ከወጣሁ አራት ዐመት ሆነኝ መሰለኝ ያልሽ መሰለኝ ተይ እንጂ ..... ዋርካን ጆይን ካረግሽ እንኳ ይሄው 8 ዐመት ደፈንሽ ወይስ አንዷ ከኍላ ጠፍታብሽ ነው ወይም ደግሞ አገር ቤት እንደገና ቪዚት ካረግሺበት አንስቶ ...... መሆኑ ነው ?? ባልሳሳት ዋርካ ሥራዋን በጀመረች ገና በአመቷ 2001 ተጀምራ ወዲያው ጨለመች :: አይደል እንዴ ?
ቅቅ አገርቤት እያለሁ ነው ዋርካን እጠቀም የነበረው .. ከተዘጋ ቡሀላም መግባት እችል ነበር .. ያ ከሆነ ጥያቄህ ማለት ነው .. [/quote] _________________ ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ኮ ር ማ ው Joined: 17 Oct 2010 Posts: 312
Posted: Fri Mar 02, 2012 7:17 pm Post subject:
Quote: ዋርካ ላይ የማውቃቸው ጨዋ ጸሀፊያን ዋናው , ፓኑ , ዋኖስ , ወለላዬ , ውቃው ... ለኔ ብዙ ያበረክቱ ጸሀፊያን ናቸው
[url]ይሽምማል [/url] ሪቾ እኛስ ግን እኛ እኮ ላንመስገን ወይ ላይሰጠን ዝም ብለን እንለፋለን ..ልፋ ያለው በምን ይለፋል ነበር የተባለው ( ለሴቶች ) ቢሆንም
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
-...- Joined: 09 Feb 2012 Posts: 312
Posted: Sat Mar 03, 2012 4:39 am Post subject:
ምነው ብትተዉት
አንድ ሰካራም ዶፕሄድ ከኢትዮጵያውያን ባህል ጋር የማይሄድ ባለጌ ሽማግሌ ሞተና ምን ሊያጎድል ነው ? ሾተል ለቅሶ ቢቀመጥለት ይገባኛል እናንተ ግን ተዉት ይረፍበት
አፈሩን ያቅልለት _________________ እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ናፖሊዮን ዳኘ Joined: 18 Apr 2008 Posts: 1874
Posted: Sat Mar 03, 2012 6:41 am Post subject: Re: አቶ ስብሃት ተገደለ ወይስ ሞተ ?
አሜን እንዳትይኝ እንጂ በዚህኛው ጽሁፍሽ አፌ ቁርጥ ይበልልሽ !
ስነ -ጽሁፉንም አስተምሯቸው ቢሆን እኮ ስነ -ጽሁፉ እንዲሁ ወሲብ ነው ! ፓሪስ ሄዶ የተከተበውን ነገር ልክ በዓለም ላይ የስብሀት ተደርጎ በዚህ ትውልድ መወሰዱ ራሱ ከስብሀት የበለጠ ትውልዱን እንድታዘበው አድርጎኛል ::
recho እንደጻፈ(ች)ው : ዉቃው እንደጻፈ(ች)ው : "ይህንን ህግ ስትጥስ የማነው ይሄ ቅሌታም ሽማግሌ ትባላለህ " አለ ስብሃት :: በጨዋታ ፕሮግራም :: ቁም ነገሩ ሪጮ የዋርካዋ ቅሌቱን ባይኗ በጆሮዋ በበረቱ ታዝባለች ::
ዌል ስሜን ባታነሳ ኖሮ በስብሀት ዙሪያ ዋርካ ላይ ምንም ላለማለት ወስኜ ነበር ... ማብራራት ካለብኝ ግን ... ስብሀትም ሆነ ማንም ላይ ግላዊ የሆነ ግጭት የለኝም ሰው ሁሉ ሰዋዊ ለሆኑ ህጎች ሁሉ ይገዙም አልልም .. ብዙ ሰዎች መጥፎ ስለሆኑ ሳይሆን ስላላመኑብት የሶሳይቱውን ህግ ሳይጠብቁም ሳያከብሩም ኖረዋል ..
ስብሀት ... ደራሲ ስብሀት .. ጸሀፊ ስብሀት ... ያላችሁትን በሉት ... ለኢትዩዽያ ስነጽሁፍ እድገት አስተዋጾ አድርጎ ሊሆን ይችላል .. አድርግዋል ወይንም አላረገም ብዬ ለመናገር ግን በጥልቀት የማውቀው ነገር የለም እንደዚሁም መስፈርቱንም አላውቅም ... በይ ግን ከተባልኩ ዋርካ ላይ የማውቃቸው ጨዋ ጸሀፊያን ዋናው , ፓኑ , ዋኖስ , ወለላዬ , ውቃው ... ለኔ ብዙ ያበረክቱ ጸሀፊያን ናቸው .. እንግዲህ ሰው የሚያውቀውን ነው የሚፈርደው ... ከዛ ውጪ አቶ ስብሀት ከስሩ የሚያስከትላቸው የልጅ ልጅ የሚሆኑትን ወጣቶች ምን እያስተማራቸው እንደሆነስ ልብ ብለናል ? ልቅነት ውበት ከሆነ ይሄን እኔ አላቅም .. ልቅነት , አደንዛዥ እጽ ተገዥነት , እንደ እንሰሳ ልቅ ወሲብን ሲያስቡና በተግባርም እንዲያውሉት መመከር እናም ደግሞ የ እግዜሩም ህግ የሆነውን ታላቅ ስተት እንደቀልድ ምንም አይደል ብለው እንዲያልፉት ጭንቅላታቸውን መቅረጽ ታላቅ ሰው ያስብላል ? እኔ እንግዲህ ከአገር ከወጣሁ 4አመት በላይ ሆነኝ መሰል ... በዛን ጊዜ ዳታ ነው የማወራው ... ስብሀት ሲባል ራሱ ያቅለሸልሸኛል .. ጥሩ ሰው ሊሆን ይችላል ስራው ግን የዲያቢሎስ ነው .. ምን አለበት እነዛን ከስሩ የሚያስከትላቸውን ቡችላዎቹን ስነጽሁፍን ቢያስተምራቸው ሀሽሽ ማጨስ ምንም ማለት እንዳልሆነና ሴክስ ከዚችም ከዛችም ጋር እያረጉ ስለሱ እየቀለዱ መዋል ምንም አለመሆኑን ከሚያስተምር ? እንግዲህ እርፍ በሉት .. ለነ ስብሀት ተራ ዱርዬ ነው .. ሞተ ? ዌል ማን ይቀራል .. ለሚወዱት "አድናቂዎቹ " መጽናናት ይስጣቸው .. እርግጥ ታላቅ አጥፊ አጥተዋል ... ግን ስብሀት የዘራው ዘር ለስንት ጀነሬሽን ይበቃ ይሆን ... ለመሁኑ በይፋ ሀሽሽ የሚያጨስ የሚያስጨስ መንግስታዊ ፍቃድ ያለው አንድ ስው ለኢትዩዺያ ወጣት በርግጥ ችግር ፈቺ .. አስተማሪ ነበረ ብላቹ ልትከራከሩኝ ነው ? እርግጥ ወጣቱ ችግሩን በሚያጨሰው ምናምን እንዲረሳ አድርጎታል .. ለዛ ታላቅ ምስጋና ይገባዋል .. ማለት ችግር መርሳት መፍትሄ ከሆነ
ማይ ፐርሰናል ኤክሲፕሪያንስ ...እናትሽን ል #$ት ብሎ ሲሳደብ በዛ ሽበትና እርጅናው ላይ በጣም ደንግጫለሁ !!!
በሉ ተሳደቡ , አንቁዋሹኝ , ያላችሁትን በሉ .. እንደሰው ጥሩ ሊሆን ይችላል .. ስራው ከ እድሜው አይሄድም .. !!!
ሪቾ
_________________ ሰው ህሊናውን የሚሸጠው ክህሊና በላይ ዋጋ ያለው ምን ነገር ሊገዛበት ነው?
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ሀሪከን 2 Joined: 31 Oct 2008 Posts: 721
Posted: Sat Mar 03, 2012 4:26 pm Post subject:
ውቃው እንዳጭበረበረው
Quote: ይህን ጥያቄ ለመጠየቅ ያሳሰበኝ .. እንደው አቧራ አስነስቶ የማያባራ አተካሮ ለመፍጠር ሳይሆን
ቢሳካልሽ ኖሮማ ምን አቧራ ብቻ ዝናብ ሁሉ አዘንበሽ ዋርካን እና አካባቢዋን ሁካታ በሁካታ ልታደርጊ ነበር የኛ ኮንስፓይራሲ ቲዮሪስት :lol
ጋሽ ስብሀት ሂወትን እሱ እንደፈለገው እና እንደመረጠው ኖሯት አለፈ በቃ : ውቃው እና ግብረ አበሮቹ ስም እጠቅሳለሁ .. ጌታ , ሙዝ እግር , ግን ሂወትን እነሱ እንደፈለጉት ሳይሆን ማህበረሰቡ እንደፈለገው ስለሚኖሩ በጋሽ ስብሀት ሂወት እንደሚቀኑ ግፍም ሲል እንደሚንተከተኩ ለመገመት አያዳግትም
በነገራችን ላይ መለስ ዜናዊም እንደ ጋሽ ስብሀት አይነት የኑሮ ፍልስፍና እንደሚከተል ማንበቤን አስታውሳለሁ እንደ መለስ ዜናዊ ከሆነ ምርጥ ኑሮ ማለት የፈለግከውን ተናግረህ እና አድርገህ መኖር ማለት ነው
ስለ እውነት ግን ከስብሀት እና ከመለስ ዜናዊማነው ሂወትን እንደፈለገው የኖራት ? መለስ ሲፈልግ ብድግ ብሎ ባንዲራ የሚያክል ነገር በድፍረት ጨርቅ ነው ይልሀል እንዴ ባንዲራ ጨርቅ አይደለም ብለህ ስትንጫጫ ታዲያ ብረት ነው እንዴ ብሎ መልሶ ያላግጥብሀል ውይ ውይ መለስ ጋ ምን ወሰደኝ አቦይ ስብሀት ነጋስ አሉ አይደል እንዴ ሂወትን እራሱ እንደፈለጋት መኖር ብቻ ሳይሆን እኛ ኢትዮጵያዊያን ራሳችንን እሱ እንደፈለገው እንድንኖር ያደረገን እንዳውም ሂወትን እንደ ፈለጉት ኖሮ ማለፍ ማለት እንደ ስብሀት ገብረ እግዛብሄር ሳይሆን እንደ ስብሀት ነጋ እና መለስ ዜናዊ ነው
በነገራችን ላይ ስብሀት እጅግ የበዙ አድናቂወች በአሉ ግርማን ጨምሮ እንዳሉት እንጅ እንደ ሪቾ አይነት ነቃፊወች እንዳሉት አላቅም ነበር ይህ ነገር እንደሰላምታም እንደ ነቆራም ይወሰድልኝ ስል በትህትና እጠይቃለሁ
ሪቾ ስትነሳ እህምምስ ለምን ትረሳ ...... የቀድሞዋ ኮረዳ የዛሬዋ ሙሉ ሴት እህምም በዚህ በዋርካ አካባቢ ካለፍሽ ሰላም ብያለሁ _________________ each mind is a different world
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ማካሮቭ Joined: 07 Dec 2004 Posts: 462 Location: united states
Posted: Mon Mar 05, 2012 4:00 am Post subject:
ስብሐት ወደ ቤቱ ሲገባ ጠብቀው የወያኔ ወታደሮች ብዙ ተኩሰውበት ቶሎ ሊሞት ባለመቻሉ በብዙ መትርየስ ደብድበው ገደሉት ይባላል :: _________________ Wisdom is better than weapons of war: but one sinner destroyeth much good.