toolbar creator
View previous topic :: View next topic
Author
Message
ሙዝ 1 Joined: 22 Feb 2006 Posts: 2614
Posted: Sat Sep 29, 2012 1:23 pm Post subject: ቅዳሜ ከሰዐት ...
ሰላም ወገኖች .... ቀደምቶቹም ... ዘመኔን ተጋሪዎችም ... ተከታዮችም ....
ያኔ እንዲህ እንዳሁኑ ኑሮ በግራ በቀኝ እኔን መካከል ጋር አድርጋ ሳትወጥረኝ ቀኖች ሁሉ ቀን ነበሩ ... ... ቀንነትም ነበራቸዉ ... እሁድን ለኳስ ሜዳ .... ቅዳሜን ለብድ ሜዳ ... ባንልም .... ከሰኞ እከ አርብ በትምህርት ቤት --- ለነገሩ የኔ ዘመን ጥሩ ነበር መሰለኝ የምንማረዉ በፈረቃ ስለነበረ ግምሽ ቀን ነዉ ትምህርት ቤት የማሳልፈዉ ... ቀሪዉ ግማሽ ቀን በጥናት ... ምናምን ያልፋል ... ታዲያ ምንም ነገር ማስታወስ የማልፈልግባት ቀን ብትኖር ቅዳሜ ከሰዐት ነበርች ... .... እንደ አዝማሪዉ ይደገም ቅዳሜ ባልልም .... ለቅዳሜ ከሰዐት በሗላ ግን ከፍተኛ ፍቅር ነበረኝ ...
የኔና የቅዳሜ በፍቅር መዉደቅ ጊዜዉ ሲሰላ በኛ አቆጣጠር በ 1980ዎቹ አጋማሽ እድሜዬ በ 20ዎቹ ዙሪያ ላይ ነበር ... ... ያ ወቅት ምን ያክል የምኞትና የምኞቱም ምህዳር በጣም ጠባብ ... ... ከስኒከርና ከጂንስ .... ስኒከርና ጂንሱንም ለምንም ሳይሆን ለነ ሪቾ መታያ ... ከዛ በላይ ምን ነበር ? ... እርግጥ ነዉ ምን መሆን ትፈልጋላችሁ ተብለን ስንጠየቅ የምንለዉ አናጣም ... ያልነዉን ለመሆን ግን ትዝ የሚለኝ ስትራቴጂክ እቅድ አልነበረንም ... በቃ እንሆናለን .. ... መሆን ለምንፈልገዉ የምከፍለዉ ጊዜ ... ሀሳብ ...ግን ለነ ሪቾ የምከፍለዉን ያክል አልነበረም ... ....
ታዲያ በዛ ዘመን ቅዳሜን የምንወዳት ለምን ይሆን ? እስኪ ወጣትነታችሁን ሀረር አካባቢ ያሳለፋችሁ እጃጩን አዉጡ ? ... የጥናት ቤት እና ሀረርጌ በወጣትነት በደንብ ይታወቃሉ ... ... ቅዳሜ ካንዱ ጀለሳችን የጥናት ቤት እንከትማለን ... ያንን ጀለሳችንን ስንመርጥ በመልኩ አይደለም ... .... ያ ጀለሳችን ሰፈር ዉስጥ ባለዉ ጉልቤነትም አይደለም ... ያ ጀለሳችን ምርጥ የሰፈር ኳስ ተጨዋች መሆን አይጠበቅበትም ... ብቻ ሱፐርሶኒክም ትሁን አርቴች ቴፕ ልትኖረዉ ይገባል ... ... ካለችዉ ይመረጣል ... ... ሁሉም ከየቤቱ ለዕለቱ የካሴት መዋጮ ያደርጋል ... የሚመለስ ነዉ ታዲያ ...
ጥናት ቤቷ መሽሞንሞን የምትጀምረዉ ከጠሗቱ 4 ሰዐት አካባቢ ነዉ ... ርግጠኛ ነኝ በዛ ሰዐት ቡና የሚያፈሉ እንስቶች እቤታቸዉ ሁነዉ ... ወይ ገላቸዉን እየተጣጠቡ ነዉ አልያም ድርያቸዉን ከእናቶቻቸዉ የሰረቁትን ሽቶ እየነሰነሱ ነዉ .. .. .... ፍራሹ ይራገፋል ... ቤቱ ይጠረጋል ... ይወለወላል .... አንሶላ ...ይነጠፋል ... ትራስ ---- ሀሀሀሀ ሀረር የትራስ ሀገር ነች ,,, የቡና ረከቦት ቦታዉን ይይዛል .... የቅዳሜ ዉበቷ ከዛ ይጀምራል .. ሀረር ከተማዉ ? አላችሁ ? .... ወደ ሀረር አራተኛ አልያም ሸዋበር ይኬዳል ... ከአካባቢዉ ከመጡ የኦሮሞ ማህበረሰቦች ... ሚጬዮ .... አዮ ... ሜቃ ቢቴ .... ሜቃ ጉጉራ ምናምን እየተባባልን ... ... ጫታችንን ሸማምተን እንመለሳለን ... ... የእለቱ ዲጄ ይመረጣል ... ... የእለቱ ሹፌር (ጫት አቀባይ ) .... የእለቱ ቡና አፍሊ ... ሽር ጉድ .... ከሰል ለማቀጣጠል .... ሽር ብትን ... ከዚህ ሁሉ ወከባ በሗላ ሁሉም ቦታ ቦታዉ ይዞ ይጀመራል ... ... አንዳንዴ ሙድ ስንይዝ እንመራረቃለን ... ... ይጨጫሳል .... እጣኑ ሰንደሉ ... የቡናዉ ጭስስስስስ ... ህምምም ቡና እኮ የሚጠጣዉ በአይንም ጭምር ነዉ ... ሲፈላ ሲያዩት ደስ ይላል ... ... _________________ አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
You cannot post new topics in this forum You cannot reply to topics in this forum You cannot edit your posts in this forum You cannot delete your posts in this forum You cannot vote in polls in this forum