View previous topic :: View next topic
Author
Message
ክቡራን Joined: 04 Mar 2008 Posts: 4256
Posted: Wed Mar 28, 2012 5:59 am Post subject: በጣም አስቸኴይ ..ይሄን ቪዲዮ ለምታውቌቸው አዳርሱ ...
***.....ጊዜ ሊፈጅ ይችላል ...ካለው ወይም በየጊዜው ከሚደርሰው ችግር አንጻር ይሄኛው ውቅያኖስን በጭልፋ የመጨለፍ ያህል መስሎ ሊታይ ይችላል :: ግን መልክት ማስተላለፍ ግድ ይላል :: በ ቪዲኦ ያልተቀዳ , ባውዲዮ ያልተቀረጸ ና ያልተሰማ ግፋ -ግፍ በየጔዳውና በየጉራንጉሩ በየቀኑ ስለመፈጸሙ ይሄ አሳዛኝ ትእይንት አንድ ማስረጃ ነው :: የእነዚህን ህጻናት ግፍ የሚሰማ ጆሮና የሚያይ አይን አንድ ቀን ይኖር ይሆናል ...ሌላ እስኪሰማቸው ድረስ አንጠብቅ !!!! እኛ የሰማነውን ላልሰማው እናዳርስ ...ቡዙ ቻይልድ አቢሲየሮች ( ኢትዮጵያውያን ኮኒዎች ) በየሰፈሩ በየማድ ቤቱ አሉ ከሰማይ የወረደ ሰይፍ እስኪበላቸው ድረስ በምንችለው ሁሉ እኛ እንብላቸው !! ሰይጣንና ጭፍሮቹን ለፍርድ ስናቀርብና ስንተባበር እኮ የሰማይ ቅዱሳን ደስ ይላቸዋል ... ምናልባትም ሊሸልሙንም ይችላሉ :: ጊዜው ይርዘም እንጂ እቺ ጋለሞታ ( እናቷ እንዳልሆነች የራሴ ውሳኔ ላይ ደርሻለሁ ......)አሁን ቪዲዎው በጣም ጥርት ብሎ ይሰማል ..) እናም ለፍርድ ማቅረቧ አይቀርም :: ጥሩ ሪሶሉሽን እንዲኖረው ያደረጉትን ወገኖቻችንን እግዚአብሄር ይባርካቸው ::
ቪዲዮውን ለምታውቌቸው ድርጅቶች , ግለ - ሰቦች የህይማኖት ተቌሞች የህግ አካላት , የሰባዊ መብት ተማጎአቾች እንድታስተላልፉ በተደብዳቢዋ ህጻን ስም ትጠየቃላችሁ ::
እቺን ይጫኑ :: *** _________________http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
እናመሰግንሃለ Joined: 01 Jun 2009 Posts: 805
Posted: Wed Mar 28, 2012 3:55 pm Post subject:
ክቡራን :
ቪድዮውን አስመልክቶ የሴትዮዋን ጭካኔ የምገልጽበት ቃል የለኝም :: እንዲህ ያለ ድርጊት ፈጽሞ መቆም አለበት !!
እኔ ልል የገባሁት ግን ሌላም መቆም ያለበትን ነገር ለመጠቆም ነው :: ከቪድዮው ጎን ያለውን ዲስክሪፕሽን አይተኸዋል ? እንዲህ ያሉ ድርጊቶችን "deeply rooted in culture" ብሎ ነው የገለጻቸው :: ካልቸራችሁ ቻይልድ አቢዩዘር ነው ነው የሚለን :: (ስለርሱ እንነጋገር ከተባለ የአሜሪካና የአውሮፓ ጉራንጉር ስንት ያሳየናል ?! በዚያ ሰበብ ግን ካልቸራቸውን ሰድበው አያውቁም :: ) እኛን ድኅነት መራር አድርጎን ሊሆን ይችላል :: ካልቸራችን ግን ቻይልድ አቢዩሲቭ ተብሎ መሰደብ የለበትም !!!!!!! አይደለምና !!!!!!!!! እየለያችሁ ተናገሩ ልንላቸው ይገባል - እነዚህን የውጭ ነጫጭባ የኤን ጂ ኦ እና የዩ ኤን ተንኮለኞች :: ካልቸርን በጭፍን ሲያወግዙ ለልጆቹ ተቆርቁረው አይደለም :: ያሉትን የመጨረሻ ሶሻል ፋብሪኮች ሊበጣጥሱ ቆርጠው ስለተነሱ ነው :: በዚህ ዙርያ "ሪሰርች " ተብለው የሚጻፉ ነገሮችን ለማብበብ ዕድሉ ገጥሞኛል :: ሁሉም ዘለው የሚወቅሱት : እናቶችን : አባቶችን : ልጁን ለመቅጣት ኃላፊነት አለብኝ ብሎ የሚያምነውን ታላቅ ወንድም ታላቅ እኅት ቤተዘመድን : እና ሃይማኖትን (በተለይ ያቺ የፈረደባትን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እንጂ ሙስሊሞችንና ፕሮቴስታንቶችን እንደተራማጅ ነው የሚያዩዋቸው ) ነው :: ደግሞ እንዲህ ብላ የምታወራው ቀንደኛ የሪሰርቸሮች አዝማች የሴቭ ዘ ችልድረን ዓይን በኢትዮጵያ እኮ ሃይማኖት አያስፈልግም ብላ የምታምን ስዊድናዊት ናት :: መጽሐፏን አንብቤዋለሁ :: አቤት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ፈተናና መከራ !! አቤት የ "ሥነ - ሥርዓት " ወግና ባሕላችን ወቀሳው አበዛዙ !!
እና : ቪድዮዎች ለምን ፕሮፓጋንዳ እንደሚውሉ እያስተዋልን ! እንዲህ ያሉ ነገሮችን ሳይ "አጼ ኃይለ ሥላሴ የወሎ ሕዝብ ሲራብ እሳቸው 80 ዓመት ልደታቸውን በቤተመንግሥት በፌሽታ ያከብሩ ነበር " የሚለው አብዮተኞች በብዙ መልኩ የተጠቀሙበት ፕሮፓጋንዳ ትዝ ይለኛል :: ዛሬ በኢትዮጵያ እነሆ የልጅ መብት ተከብሮ .... ተከብሮ .... ተከብሮ ...... የደረስንበት ውጤት (ከዩኒቨርስቲ መምህራን እንደምሰማው ) "መብታቸንው ብቻ እንጂ ግዴታቸውን የማያውቁ : ፈጽሞ በዕውቀት ባሕር አንድ ጠብታ የጎደላቸው የማይመስላቸው : መምህራን የቤት ሥራ አበዙብን ብለው ስትራይክ በየሴሜስተሩ የሚወጡ : ሰነፍና ያልበሰሉ ተማሪዎች " የሞሉበትን ትውልድ ነው ::
የሕጻናት መብት ይከበር ! የሕጻናት መብት ይከበር ዘንድ ይህን ይህን አስወግዱ ብለው እንደአልቲሜተም የሚደሰኩሩልንን ዲስኩር ግን እያስተዋልን !! እነርሱ ለልጆቻችንም ለኛም ግድ የላቸውም ! ቢኖራቸው ኖሮ : አገሪቱን እንደጉድ ያሰቃያትን በውጭ "ቱሪዝም " ስም የሚደገፈውን ድረግ እና ሴክስ ትራፊኪንግ : የሕጻናት መሠረቅና የኦርጋን ሽያጭ : የድንበር ጦርነትና የመሳሰሉትን ነበር ማሰብ ያለባቸው :: እናቶች እኅቶች አባቶች ቤተዘመዶች የመሳሰሉትን መምከርና ማስተማር : እምቢ ካሉም ቅጣት እንዲጣል ዐዋጅ ማውጣት ብቻ በቂ ነው :: እነርሱ እንደመንግሥታትና አለማቀፍ ድርጅቶች ደናቁርት አይደሉምና ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ዲጎኔ Joined: 19 Aug 2005 Posts: 3832 Location: united states
Posted: Wed Mar 28, 2012 4:12 pm Post subject:
ሰላም ለሁላችን ይሁን
ልጆችን በቅጣት ስም መደብደብ የተወገዘ ድርጊት ነው ::እንደዚሁም ልጆችን ኩዋስ ሜዳ ላይ 'ወያኔ ወደመቀሌ ' ስላሉ በታጣቂ መረሸንም የበለጠ ሊወገዝ ይገባዋል ::ለብላቴናዎቹ እሱባለውና ኑረዲን አዲስ ከተማና መሳለሚያ ኩዋስ ሜዳ ላይ ያረደ ወያኔ በባህሉም ሆነ ዘመናዊ ህግ ጉማ /ካሳ ለቤተሰብ ስይሰጥ እዚህ በወኪሎቹ አዲስ ድራማ ማሰራጨት አስፋሪ ነው ::ይቺ ህጻን ስትመታ ድምጹ ከድርጊቱ ቀድሞ ይጮሀል ይቺ ቀራጭ የተባለች ስትገለፍጥ የሚሰማው አሳፋሪ ሲሆን እናት ተብዬዋም 'ፊልም ታነሻለች ?' ያለችው መጨረሻ ላይ ነው ::በባህላችን ልጆች ሲመቱ ሙጥኝ ብለው ውደደሌላ ሰ ይሮጣሉ ይህ የተቀናበር ፊልም ባይሆን ኖሮ ህጻኗ ወደቀራጭ ተብዬዋ ትሮጥ ነበር ::ጭራሽ ህጻኗ ቀራጭ ተብየዋን አንዴም አታያት እንዴት ? አይ የወያኔ ድራማ አኬል ዳማ አልሰራ ሲል በዚህ መጡ ?ደርግ ጨፍጫፊ ቢሆን የህጻናት ኮሚሽን አውቅሯል ምርጥ ምርጡን ለህጻናት መፈክርን አስፋፍቷል ::
ዲጎኔ ሞረቴ በወያኔ ከተባረሩ የኢትዮህጻናት ሾው አባት ተስፋዬ ሳህሉ ሰፈር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
ክቡራን Joined: 04 Mar 2008 Posts: 4256
Posted: Wed Mar 28, 2012 6:04 pm Post subject:
ሰላም እናመሰግናለን ..ስሜትህን ከሞላ ጎደል እጋራለሁ :: ችግሮች አሉብን :: እንዳለክው ወይም እነሱ አንዳሉት ባህላችን በደምሳሳው አቡዪዚቭ አይደለም :: ተካፍሎ መብላት , እንጀራ ባንድ ትሪ መቁረስ ,, እረ እንብላ ማለት , አዋቂ ሲመጣ ብድግ ብሎ ወንበር መልቀቅ ላአለም ያሳየነው ባህላችን ነው :: እኔ ኢንደሚክ እለዋለሁ :: የዚህ አገር ልጆች ከሳህናቸው ላይ ከበላህ ፕራይቬሲዬን ነካህ ብሎ ይሰድብሀል ..ምናልባትም አቢዩሰር ነህ ብሎም ሊከስህ ይችላል :: ያም ማለት ግን ህብረተሰባችን ውስጥ ችግር የለም ማለት አይደለም ...ጎዷው ና ሰፈሩ ይመስክር ...ወላጆች የኑሮ ቁጭታችወን ና ብሶታቸውን የሚወጡት በልጆቻቸው ነው :: በየቀኑ እየተደበደቡ እየተገረፉ ያደጉ ልጆች በራሳቸው የማይተማመኑ ይሆናሉ ፈሪም ይሆናሉ ...ይሄ አገራችንንም ይጎዳል ..ሁላችንም የዛ ውጤቶች ነን :: ዛሬ ነፍስ አውቀናል ... ችግሩ የት ጋ እንዳለ እናውቃለን እኛ ያለፍንበትን ልጆቻችን ማለፍ የለባቸውም ...ይሄን ማሳየት አለብን :: አዌርነስ መፍጠር ያስፈልጋል :: ችግሩ ይሄን አዌርነስ ለመፍጠር በቅንነት ስንሰራና ህብረተሰባችንን ለመታደግ ስንሯሯጥ እነዚህ ጉማሬዎች በጎን ለራሳቸው የግል ጥቅም ብቻ አን ሰብታንሽያል እርጉየመንት ይዘው ይመጣሉ ...ዋናው ግባቸው ገንዘብ ነው ...ሌላው ደሞ ካልቸራችንን ለማዋረድም ነው :: ይሄን ጉዳይ ደሞ ለማጋለጥ ደሞ ገንዘብና የሰው ሀይል ያስፈልገሀል :: ሪሶርስ ናቸው :: ቡዙ እንዳይሄዱ ገመዱን አሳጥሮ መያዝ ብልጠት ነው :: ለምን እንደሆነ ባይገባይኝም ሁሌም የሀይል ሚዛኑ ለነሱ ያደላል :: ሪሶርሳቸውንም ስንጠቀም አይናችንን ግን ከፊታቸው ማንሳት የለብንም :: ነጫጭ ሰይጣኖች እነሱም መሀል አሉ :: መቼም በችኮላ ነው የጻፍኩት ግን ሀሳቤ ይገበሀል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ :... _________________http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily
those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message
is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
toolbar creator
እናመሰግንሃለ Joined: 01 Jun 2009 Posts: 805
Posted: Wed Mar 28, 2012 6:45 pm Post subject:
ክቡራን እንደጻፈ(ች)ው : ሰላም እናመሰግናለን ..ስሜትህን ከሞላ ጎደል እጋራለሁ :: ችግሮች አሉብን :: እንዳለክው ወይም እነሱ አንዳሉት ባህላችን በደምሳሳው አቡዪዚቭ አይደለም :: ተካፍሎ መብላት , እንጀራ ባንድ ትሪ መቁረስ ,, እረ እንብላ ማለት , አዋቂ ሲመጣ ብድግ ብሎ ወንበር መልቀቅ ላአለም ያሳየነው ባህላችን ነው :: እኔ ኢንደሚክ እለዋለሁ :: የዚህ አገር ልጆች ከሳህናቸው ላይ ከበላህ ፕራይቬሲዬን ነካህ ብሎ ይሰድብሀል ..ምናልባትም አቢዩሰር ነህ ብሎም ሊከስህ ይችላል :: ያም ማለት ግን ህብረተሰባችን ውስጥ ችግር የለም ማለት አይደለም ...ጎዷው ና ሰፈሩ ይመስክር ...ወላጆች የኑሮ ቁጭታችወን ና ብሶታቸውን የሚወጡት በልጆቻቸው ነው :: በየቀኑ እየተደበደቡ እየተገረፉ ያደጉ ልጆች በራሳቸው የማይተማመኑ ይሆናሉ ፈሪም ይሆናሉ ...ይሄ አገራችንንም ይጎዳል ..ሁላችንም የዛ ውጤቶች ነን :: ዛሬ ነፍስ አውቀናል ... ችግሩ የት ጋ እንዳለ እናውቃለን እኛ ያለፍንበትን ልጆቻችን ማለፍ የለባቸውም ...ይሄን ማሳየት አለብን :: አዌርነስ መፍጠር ያስፈልጋል :: ችግሩ ይሄን አዌርነስ ለመፍጠር በቅንነት ስንሰራና ህብረተሰባችንን ለመታደግ ስንሯሯጥ እነዚህ ጉማሬዎች በጎን ለራሳቸው የግል ጥቅም ብቻ አን ሰብታንሽያል እርጉየመንት ይዘው ይመጣሉ ...ዋናው ግባቸው ገንዘብ ነው ...ሌላው ደሞ ካልቸራችንን ለማዋረድም ነው :: ይሄን ጉዳይ ደሞ ለማጋለጥ ደሞ ገንዘብና የሰው ሀይል ያስፈልገሀል :: ሪሶርስ ናቸው :: ቡዙ እንዳይሄዱ ገመዱን አሳጥሮ መያዝ ብልጠት ነው :: ለምን እንደሆነ ባይገባይኝም ሁሌም የሀይል ሚዛኑ ለነሱ ያደላል :: ሪሶርሳቸውንም ስንጠቀም አይናችንን ግን ከፊታቸው ማንሳት የለብንም :: ነጫጭ ሰይጣኖች እነሱም መሀል አሉ :: መቼም በችኮላ ነው የጻፍኩት ግን ሀሳቤ ይገበሀል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ :...
ተግባብተናል :: የምለው ገብቶሃል ::