WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
እንደምን ሰነበታቹ ወይም ሰባቹ ...ከዚምከዚያም

Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ዘጌ _ዘጋንባው

ኮትኳች

Joined: 18 Aug 2010
Posts: 166

PostPosted: Mon Mar 26, 2012 7:16 pm    Post subject: እንደምን ሰነበታቹ ወይም ሰባቹ ...ከዚምከዚያም Reply with quote

መቼም የስደት ኑሮና መስባት (መለጥለጥ ( እዚጋ ትኩረት አድርጉ ...መለጣለጥ አላኩም !)) ተጓዳኝ /ኮምፕሊመንታሪ ጉድስ መሆናቸውን ሳልነግራቹ ታቁታላቹና ለዛም ነው ሰብጀክቴን "ሰነብታቹ - ሰባቹ " ብዬ መሰየሜ :: ግን ደሞ ይህ ጉዳይ አንዳንድ ወደ ስባት -አልባ ሀገራቶች የተሰደዱትን የኢጥዮጵያ ልጆች አይመለክትም - ለምሳሌ ድጂቡቲ , ድንጃሚና (ቻድ ) ይጠቅሷል :: እኔም የዛሬን አያርገውና 'አንተ ግን ምንም አትወፍርም /አይጠጋክም ....ያው ነክ ካገርቤት እንደመጣከ "' ለሚሉ ቅናት አዘል የአድናቆት አስተያየቶች መልሴ ....እኔ እምወፍር ሰው አይደለሁም .... ...ምግብ በልቼ ጨጓራ ላይ ሳይደርስ ዶግ አመድ የሚያረግ ሀይለኛ ሜታቦሊዝም አለኝ ... ባጭሩ በሞራ ሳይሆን በሞራል የታወኩ ነኝ እያልኩ ስኮፈስ ኖሬ ....ይህውላቹ ሆዴ ዙርያ ደበልበል ማለት ከጀመርኩኝ ሁለት መንፈቅ እንቅጩ ላይ !

ሰላም እንደምናቹ ውድ የዋርካ አባላት ......

እኔ በጣም ደህና ነኝ :: እናንተስ ? ....
አይ ጤና ማርኬቲንግ ነው በሚለው መስተጋብር ....ጤንነታቹን ካወኩ ለኔ ሌላው ቦነስ ነው ::

ዚስ ፓስት ዊኬንድ ምን አረክ ብላቹ ጠይቁኝማ ?

አቡጀዲ ግርግር ...ክስቶ ብዬላቹ ነበር :: ከማጋ ? ከሆነች ጸጉረ ልውጥ ነዋ ! ሌላ ከማጋ ይሆናል ? እናማ ....ከቲኔጀሮች እየተጋፋሁልህ ..... the hunger game የሚሉትን ፊልም አየሁት :: አቤት ወረት !! አቤት አሜሪካ !! አቤት ሆይሆይታ !!! ስንቱን ታዘብኩት !!

ኦብሰሽን ይሉሀል ይህኔ ነው

ግን ለምን ደሞ ሰው ላይ ጣት እጠቁማለው ...እኔ ራሴ ፈላ እያለሁ .....መቶሀያ ለማየት እኛ ቀበሌ ክበብ ቀላል ተጋፍቻለው ? የኦብሰሽን ትንሽ የለውማ !

ግን ለስፕሪንግ እና ለሰመር አንጠፋፋ እሺ

ሪክ ሳንቶረም ነኝ ... i approve this ማሳጅ Very Happy message!!

... ሳልረሳው ...እስራኤል እና ኢራን ሊፏከቱ ነው አሉ :: ምን አሉ ብቻ አሜሪካም በአደባባይ እስራኤን ጃስ እያለች በጓዳ ደሞ አይዞሽ አለሁለሽ (ባራዳ ቋንቋ ደሞ i got your back /ጀርባሽን ይዣለው Laughing ) ብላታለች የሚል ወሬ ነው የሚናፈሰው :: የዶሚኖ ኢፌክቱ የትዬለሌ ( የትዬለሌ ይቺ ቃል ቁምነገር ለማውራት ሳካብድ ለመጠቀም እንዴትትት ትመቸኝ መሰላቹ ) እንደሆነ ሊቃውንቶች እያስቦኩን ነው ::

አባ እስርቾ አምርራለች ነው የማቃድዳቹ ... እነ AIPAC ጡንቻቸውን እንደተለመደው በካፒቶል ላይ እያሳዩ ነው :: እኔ እምለው ሎቢ ማድረግ ወይንም ሎቢስት በአማርኛ ተቀራራቢ ትርጉሙ ምንድነው ግን ? ለማኛውም መልሱን በቶሎ ዱቅ አርጉ እያልኩ

የዛሬውን ስርጭቴን በዱአ /ጸሎት አጠናቅቃለሁ ::

አምላክ ሆይ እባክህ ከሚያስፈራው ነገር ጠብቀን !!
ከወሲበ -እጅ ወደ ልጅ መውለድ ሳልሻገር ( ልጅ እንኳን እንደነሙዝ 1 ዱብ ሳላረግ ) ይህንን የጦርነት ጥቁር ደመና ከላያችን ላይ ግፈፍ ..... ያው ደሞ እምቢ አይሆንም ካልክ ካንተ አልታበትም .... በሰጠከን ፍሪዊል የሚሉት ዲሞክራሲያዊ እምብቴን ተጠቅሜ ..ያለችኝን ቻፖ ካርቶን በርጫ ሽመቼና በምርቃና ለምልሜ ..ዶምዝዴይን በደማቅ አቀባበል እቀበለዋለሁ !!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዉቃው

ዋና ኮትኳች

Joined: 07 Jan 2007
Posts: 970

PostPosted: Tue Mar 27, 2012 5:02 pm    Post subject: Reply with quote

ኬፍ ዘጌው

እኔ እምልህ ቃል በቋንቋ ውስጥ ይወለዳል : ይሞታል የሚባለው ነገር ..ለካ ...እውነት ነውሳ ! አሁን ኬፍን የሚጠቀም እንደነዋናው ያለ ሙታን ቀስቃሽ ካልሆነ ማን ይሆናል ?! ኬፍ ሞቷላ :: አቤ .... ስንትና ስንት ቃሎች እኮ ..እንደዘበት ቀስ በቀስ በሞት ተለዩን :: ለምሳሌ "ሉዓላዊነት " ስለሚለውን ቃል የስንት መንግስት ምሁራን አስረደትውናል :: አሁን እንዲህ ሞቶ ሊቀበር ::

ወደዋናው ፍሬ ጉዳይ ስንገባ ...ምንስ አንተ ብትሰባና ብትድበለበል ሌላውም እንዳንተ የሆነ መስሎህ ክሆነ እንዴት ሰባችሁ ያልከው .....እሱ ትዝብት ላይ ጥሎሃል :: እኛማ ምን አግኝተን ? ቢሆንም አንተ ግን ሽንቀጥ ለማለት ..ሰመሩ ሳይፋፋም ቀደምህ ዱብ ዱብ ብትል ሳይሻል አይቀርም ይላል የዝግጅት ክፍላችን ::

ከዛ በተጨማሪ ሌላው ትዝብት ላይ የጣለህ አንኳር ጉዳይ ...ወራሪ ኢትዮጵያ የተወራሪ ኤርትራን ሉአላዊነት የደፈረችበትን ... የተነኮሰችበትን .... ጠብ የጫረችበትን ..የቆሰቆሰችበትን ... ሳምንታዊ ክብረ በዓል እንዳልሰማ ሆነህ ማለፍህ ነው :: ይህ በውነቱ የሆነ እንደሆነ ..በቃ ተወው ይቅር :: ብቻ ...ዓለም ልትቀዋወጥ እንደሆነ የኔ ዶፕላር ሬዳር ያሳያል :: እነሱ ሳይታኮሱ የጋስ ፕራይስ የትየለሌ ሆኗል :: ሲታኮሱ ደግሞ ምን እንደሚፈጠር ፍርዱን ለተመልካች እተወዋለሁ :: ለብዙ ዓመታት የኢኮኖሚ መለኪያዬ የሆነው ሮማ ቲማቲም ..ባለፈው ቅዳሜ የኔ ሰፈር የገበያ ዉሎ በፓውንድ አንድ ከሰማኒያ ስምንት ሆኗል :: በደጉ ዘመን ባምሳም በስልሳም ስንቲም ሸምትነው ነበር ::

ከዓለም ጉዳይ ወደዩጋንዳ ጉዳይ ስንመለስ ...አቶ ዮሴፍ ኮኒን ባንድ ቀን ዓለም አውቆታል :: ዴም ! ኮኒ ግን ለዚህ ታዋቂነት 20 ዓመት ለፍቶበታል :: ኮኒ በታዋቂነቱ በመዝናናት ላይ እንዳለ ፊልመ -ሰሪው ጄንኪንስ ግን በሳምንቱ ጨርቁን ጥሎ ...መለመሌውን መብራቱ ላይ ጎንበስ ቀና ሲል አይተናል :: ደጉ አሜሪካ ስም መስጠት ያውቃል ...ዲሀይድሬሽን ...ኤግሶስሽን ...ምናምንሽን ..እንትና ሽን ..ሽን ..ሽን ነው አሉ የያዘው በሽታ :: አብዷል ማለት ፈርተው ::

እንግዲህ ዘጌው ..ከዚህ ካለሁበት የዓለም ክፍል ለስርጭት ክፍሉ ትሆናለች በማለት አነስተኛ ዘገባ አቅርቤያለሁ :: ጥያቄህንም ለሎካል የፖለቲካ ተንታኞች አቅርቤ ሎቢይስትን ጀኝጃኝ ከሚለው የቀደሞ ቃል ጋር አቅርራርበውታል :: አይ ቲንክ ቃሉ በሞት ሳይለይ አይቀርም ::

ሁሉም ነገር ወደጦር ግንባር !
አመሰግናለሁ
አባ ዉቃው
_________________
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
መንኮራኩር

ዋና ኮትኳች

Joined: 28 Mar 2006
Posts: 528

PostPosted: Sat Mar 31, 2012 12:39 am    Post subject: Reply with quote

ሎቢ - አማላጅ ይሆን
_________________
Peace has to be created, in order to be maintained. It is the product of Faith, Strength, Energy, Will, Sympathy, Justice, Imagination, and the triumph of principle. It will never be achieved by passivity and quietism.

Dorothy Thompson:
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዘጌ _ዘጋንባው

ኮትኳች

Joined: 18 Aug 2010
Posts: 166

PostPosted: Mon Apr 02, 2012 6:08 am    Post subject: Reply with quote

ይድረስ አቶ ውቃቸው :
በቅድምያ እኔ አመጣጤ ስለኢትዮጵያና ኤርትራ በተመለከተ ወቀሳክን ለማስተባበል ነበር ...ግና ወሬና ጣፊጡ ትኩስ ትኩሱን ነው እንዲሉ ...እሱን ገፋ አድርጌ ከሰሞነኛው ወሬ የተያያዘ ነገር ልል ወደድኩ ::
አየክልኝ እንዴ የበቃውና የነቃው ኢትዮፕያዊው ራያን ሲክሬስ ማለቴ ሰይፉ ፋንታሁን (ወጥ ቀማሹ ) ድንቃድንቅ አርቲስቶቻችንን አስከትሎ ጎጆ ሰበራ ምናምን ?
...አባ ምቾት ያደለበው ገላቸው ያቺን የሰንበሌጥ ቤት ካሁን አሁን በሀይል ተንፍሰውባት ( ተናደው ነበር እኮ ! በህጻኗ መመታት ) ኮላፕስ አረገች አላረገች እያልኩ በጥፍሬ ቆሜ ተሳቅቄ ጨረስኳት :: ማንን ፕሊዝ ለማረግ የታቀደ ሽርጉድ እንደሆነ ግራ ተጋብቼ እኔም ኮምፒተሬን አጨለምኩና ሴትዮዋን ልገፋት ወደመኝታ ክፍል ገባሁላት እልካለው ( እንግዲ ይህ የሆነው 2 ቀን በፊት ነው )
በዚ አጋጥሚ የመከርከኝን ቦርጭ የማስፈራራት ስታርቴጂ ቀይሼ ካሁኑ ለውጥ ማየት ጀርምያለው :: ማለቴ በጀርባዬ ተንቼ ቲቪ ማየት አልችልም ነበር አሁን ግን ተመስጌን አክተሮቹ እስከአንገታቸው ድረስ ይታዩኛል Laughing

ወደ አለማቀፍ እንቶፈንቶዎች ስናልፍ ደሞ .....
ታቃለክ ምንም ነገር የለም የሚማርክ ወሬ

እያልኩ ላሁኑ ስርጭቴን ከማብቃቴ በፊት ....

መንኮራኩርም ..አቶ ውቃውም ያቀረባቹት ትርጉም ከምንም ይሻላል በሚል ተቀብለነዋል !! ጁሪው ነው የወሰነው ::

ብዬ ተጃጂለ ቶምሳ ....
ነገ እንገናኝ ለምሳ

ባይ ባይ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ፕላዞግ

አዲስ

Joined: 06 Dec 2008
Posts: 34

PostPosted: Sat Apr 07, 2012 12:28 am    Post subject: Reply with quote

'ሎቢ ' ማለት ያው ሎሚ እንደማለት ነው :
ሎቢ ማድረግ ማለት ሄዶ ሰዎችን ሎሚ ማድረግ ወይንም ማሟሟት ማለት ነው :: በምላስ እሽት አርጎ ::
እኛ ምን አገባን ስለ ፐርሺያ : ትርጉማችንን ማቀላጠፍ ብቻ ! በምርቃና
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia