WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
ወቸው ጉድ !
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 24, 25, 26 ... 108, 109, 110  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ጦምኔው

ውሃ አጠጪ

Joined: 14 Jan 2007
Posts: 1433
Location: Right here

PostPosted: Wed Jul 11, 2012 3:17 pm    Post subject: Reply with quote

ሠላም ሰዎች

ተኬደለት :: ዓርብ ቀን ባህል ምሽት ነበር ዝግጅቱ RFK Stadium. በሩ ላይ አንድ ፒክ አፕ መኪና ቆሞ መፈክር ያሰማል ምን እንደሚል ብዙም አልሰማሁትም እኔ የገባሁት በሌላኛው በር ነበርና :: ውስጥ ስገባ ብዙ የሚባል ሰው ነበር :: ስታዲየሙ ትልቅ ስለሆነ ስዉ ትንሽ ይመስላል እንጂ :: ዝግጅቱ እጅግ ደስ የሚል ነበር :: እንዬ (ተመዛዋዧ ) ለመጀመሪያ ጊዜ ማየቴ እጅግ ነበር ያስተደተኝ :: ሀገራዊ ስሜት ያለው ዝግጅት ነበር :: የብሄር ብሄረሰቦችን ባህላዊ ጨዋታ በጥሩ ተወዛዋዦች አቅርበዋል :: መጨረሻ ላይ ሀመልማል አባተ "ኢይቶጵያ ሀገሬ " የሚለውን ቀረርቶ እና ፉከራ ያቀረበችው እጅግ ጥሩ ነበር :: ትንሽ ያበሳጨኝ ቢራ 10 ብር ውሀ 4 ብር እየሸቀሉ የበዘበዙን ነገር ነው :: Laughing

ቅዳሜ ምሽት ኮንቬንሽን ሴንተር የተዘጋጀ ኮንሰርት ነበር :: ታደለ ሮባ , ማዲንጎ አፈዎርቅ , ሀመልማል አባተ ..አብርሀም ገብረመድህን ..ታደለ ገመቹ ....ጆኒ ራጋ ..እዮብ ...እንዬ ተገኝታ ነበር :: እሷ ሴትዮ አታረጅም ጃል :: አለባበሷ እና ፈገግታዋ ልክ እንደ ሕዝብ ለሕዝብ ላይ እንዳለችው ነበር :: አሁንም በደንብ ትጨፍራለች ::

አዳራሹ መግቢያ በር ላይ አንድ እጅግ የሚያደብን ነገር አጋጥሞኛል :: 15-17 የሚደርሱ ሀበሾች ባንዲራ እና መፈክሮች ይዘው ተቃውሞ እያቀረቡ ነበር :: አንደ መፈክራቸው Blood Money Concert" ይላል :: መቃወማቸው ባልከፋ ነገር ግን እጅግ ያደበነኝ እያንዳንዱ ወደ ኮንሰርቱ የሚገባውን ተመልካች "ሆዳም ..ሌባ " እያሉ ወደ አዳራሹ መሸኘታቸው ነው :: ይህ እጅግ ከልክ ያለፈ ብልግና ነው :: ማንም ሰው እኮ የራሱ አመለካከት አለው :: የግድ ካንተ አመለካከት ጋር ስላልተመሳሰለ ብቻ መሰደብ የለበትም :: በዚያ ላይ ፊታቸው እና ድምጻቸው ላይ ትልቅ ጥላቻ ይታያል :: ሁኔታቸው ሁሎኡም ሰው ከነርሱ ጋር አንድ ዓይነት አመለካከት እንዲኖረው የመፈለግ አይነት ነው :: እኔ በጣም ነበር የበሸቅሁት :: I had to give them a finger (actually it was the 5 of us who gave them fingers Very Happy ). የኔ አመለካከት : I am agrown ass man. I don't get a dime from anybody. I work my ass off to live my life and to provide to my family. I don't give a ---- about what anybody has to say. I have my own ideas and principles which I follow. If anyone tries to tell me otherwise, I have to say "---- off" and be on my way.

እናም ተቃዋሚ ተብዬዎቹ Please know ማንን እንደምትቃመዉ :: ሁላችንም Iትዮጵያዊያን ነን :: ስርዓቱን ከሆነ ተቃውሟቹ ያንን የሚያመላከት ሰልፍ አካሂዱ Instead of በጭፍን የሰው ሰውን ከመስደብ ::

እኔ የዚያን ቀን ኮንሰርቱን ልገባ የፈለኩት (ገንዘቤን ከፍዬ እኮ ነው ደሞ የገባሁት ) ሙዚቃ ለማየት ነው :: አለቀ :: I don't care what the fight between the DC and Dallas አዘጋጆች መሀል is. As a matter of fact ---- both of them. ልዩነታቸውን መፍታት ሳይችሉ እኛን ግራ ያጋቡን እነሱ ራሳቸው :: I live in DC and whoever comes to DC with Music gets my attention and my payment. I am not gonna travel nowhere, but if you come to my door steps, you are welcome to party with me.

ኢፍ ....ተረቴን መልሱ ....
_________________
http://www.youtube.com/watch?v=_jIwsS_eT5w

http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=22540&start=105
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
recho

ዋና አለቃ

Joined: 20 Sep 2004
Posts: 2991
Location: Earth

PostPosted: Wed Jul 11, 2012 6:09 pm    Post subject: Reply with quote

http://allafrica.com/stories/201206280363.html

ነፍስ የሚያሳቅቅ ዜና ... ከተፈጸመ አንድ ሳምንት ቢያልፈውም ይሄ ደግሞ ይበልጥ ያሳዝናል ... እነዚህ ምስኪን ወገኖቻችን ድንነትን እና ረሀብን ሽሽት በበረሀ ሞተው ቀሩ .. ድህነት , ረሀብ ክፉ ነው .. ምን ያክል ቢመራቸው ነው በመጀመሪያው ዙር የሞቱትን እያዩ ሁለተኛዎቹ የተከተሉት ? እዛ ሆነው ከሞሞቱ እድላቸውን ሞክረው ቢሞቱ መረጡ .. እናም ሞተው በሰው አገር , በማያቁት አፈር ተቀበሩ .. የማያቁዋቸው ቦታ ለማስለቀቅ ያክል ሲሉ ቀበሩዋቸው ... ድሮ ድሮ .. ላገሬ አፈር አብቃኝ ሲባል አይገባኝም ነበር .. ለካ ዝም ብለው አይደል የተረቱት .. 43 ወገኖቻችን በማያቁዋቸው , በማይጎዱና በማይጠቅሙዋቸው ሰዎች ተቀበሩ .. የሞት ደግ ባይኖረውም ይሄ ግን ምርር አርጎ አስከፋኝ ... አቤት የኢቲዩዺያ አምላክ ዝም አትበል .... ይብቃቹ በለን ...

በምድር ያልደላቹ ወገኖቼ .... ነፍሳችሁን የአብርሀም እና የይስሀቅ አምላክ በገነት ያኑር .... !
_________________
ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጌታ

ዋና አለቃ

Joined: 17 Apr 2005
Posts: 3225
Location: ዶሮ ተራ

PostPosted: Thu Jul 12, 2012 2:20 pm    Post subject: Reply with quote

ሪቾ - በጣም ልብ የሚነካ ዜና ነው Crying or Very sad Crying or Very sad Crying or Very sad ኖሯቸው አላማረ አሟሟታቸውም እንደዛው :: Crying or Very sad Crying or Very sad Crying or Very sad

ጦምን - እኔ ያልገባኝ ነገር ዝግጅቱን ወይም አዘጋጆችን መቃወም ይቻል ይሆናል ነገር ግን ገንዘቡን ከፍሎ ጊዜውን ሰውቶ ሊዝናና የሚሔድን ሰው መቃወም ወይም መሳደብ ይቻላል ? ስለማላውቅ ነው ምናልባት ይቻል ይሆናል Wink ቁምነገሩ ግን በክፍፍሉ ዲሲ ነው ወይስ ዳላስ ትክክል የሚለውን ለሕዝብ ፍርድ ቢተዉት ይመረጥ ነበር :: አዎ ዝግጅቶቹ የኢትዮጵያውያን እንደመሆናቸው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በራሱ አዕምሮ በመመራት የፈለገበት የመሔድ ነጻነት ያስፈልገዋል :: አንተ ፈልገህ የሄድክበትን ቦታ እኔ መጥቼ ልክ አይደለህም ስልህ እኔስ ልክ ለመሆን ማን መብት ሰጥቶኝ ነው ?

ባፋንኩሎ !!! Laughing Laughing Laughing Laughing
_________________
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Send e-mail Visit poster's website Yahoo Messenger Report post
ጦምኔው

ውሃ አጠጪ

Joined: 14 Jan 2007
Posts: 1433
Location: Right here

PostPosted: Thu Jul 12, 2012 3:18 pm    Post subject: Reply with quote

ጌታ እንደጻፈ(ች)ው:

ጦምን - እኔ ያልገባኝ ነገር ዝግጅቱን ወይም አዘጋጆችን መቃወም ይቻል ይሆናል ነገር ግን ገንዘቡን ከፍሎ ጊዜውን ሰውቶ ሊዝናና የሚሔድን ሰው መቃወም ወይም መሳደብ ይቻላል ? ስለማላውቅ ነው ምናልባት ይቻል ይሆናል Wink ቁምነገሩ ግን በክፍፍሉ ዲሲ ነው ወይስ ዳላስ ትክክል የሚለውን ለሕዝብ ፍርድ ቢተዉት ይመረጥ ነበር :: አዎ ዝግጅቶቹ የኢትዮጵያውያን እንደመሆናቸው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በራሱ አዕምሮ በመመራት የፈለገበት የመሔድ ነጻነት ያስፈልገዋል :: አንተ ፈልገህ የሄድክበትን ቦታ እኔ መጥቼ ልክ አይደለህም ስልህ እኔስ ልክ ለመሆን ማን መብት ሰጥቶኝ ነው ?

ባፋንኩሎ !!! Laughing Laughing Laughing Laughing

Exactly!!!
_________________
http://www.youtube.com/watch?v=_jIwsS_eT5w

http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=22540&start=105
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ሾተል

ዋና አለቃ

Joined: 13 Jan 2005
Posts: 6808
Location: Vienna-Austria

PostPosted: Thu Jul 12, 2012 3:22 pm    Post subject: Reply with quote

recho እንደጻፈ(ች)ው:
http://allafrica.com/stories/201206280363.html

ነፍስ የሚያሳቅቅ ዜና ... ከተፈጸመ አንድ ሳምንት ቢያልፈውም ይሄ ደግሞ ይበልጥ ያሳዝናል ... እነዚህ ምስኪን ወገኖቻችን ድንነትን እና ረሀብን ሽሽት በበረሀ ሞተው ቀሩ .. ድህነት , ረሀብ ክፉ ነው .. ምን ያክል ቢመራቸው ነው በመጀመሪያው ዙር የሞቱትን እያዩ ሁለተኛዎቹ የተከተሉት ? እዛ ሆነው ከሞሞቱ እድላቸውን ሞክረው ቢሞቱ መረጡ .. እናም ሞተው በሰው አገር , በማያቁት አፈር ተቀበሩ .. የማያቁዋቸው ቦታ ለማስለቀቅ ያክል ሲሉ ቀበሩዋቸው ... ድሮ ድሮ .. ላገሬ አፈር አብቃኝ ሲባል አይገባኝም ነበር .. ለካ ዝም ብለው አይደል የተረቱት .. 43 ወገኖቻችን በማያቁዋቸው , በማይጎዱና በማይጠቅሙዋቸው ሰዎች ተቀበሩ .. የሞት ደግ ባይኖረውም ይሄ ግን ምርር አርጎ አስከፋኝ ... አቤት የኢቲዩዺያ አምላክ ዝም አትበል .... ይብቃቹ በለን ...

በምድር ያልደላቹ ወገኖቼ .... ነፍሳችሁን የአብርሀም እና የይስሀቅ አምላክ በገነት ያኑር .... !

ሰላም ሪቾ ......እንዳልሽው ዜናው ቆየት ያለ ቢሆንም ሁሌም የሚያሳዝን ክስተትና እጦት ነው ::በነገራችን ላይ ኢትዮዽያ እያለሁ የታዘብኩትን አንድ ነገር ልበልሽ ....ምን አልባት ሙድ ከብቶቼ ላይ የመያዣ ጊዜዬን ወድያልኝ ብዬ ቁም ነገር ለመጻፍ ጊዜና ገቱ ሲኖረኝ ኢትዮዽያ እያለሁ የታዘብኩዋቸውን ነገሮች ከቪድዮና አውድዮ ጋር አብሬ እስካቀርብ ጊዜ አሁን ባለሁበት እንዳለሁ ይፈቀድልኝና ካመጣሽው ቶፒክ ጋር አንድ የታዘብኩትን ነገር ልንገርሽ ::

መቼም ኢትዮዽያ ውስጥ ከታዘብኩዋቸው ነገሮች ውስጥ የህዝቡ ጫት ቃሚነት ባህልና ለመውጣት የተመቸውም ይሁን ያልተመቸው ውጭ ለመውጣት የሚላላጠው ወይም የሚመኘው ሰው መብዛቱ ነው ::ታድያልሽ መቼም ይኼ የጫት ባህል እንደ ጉድ አንሰራፍቶ አገራችንን ስለወረራት ወደድሽም ጠላሽ ከስጋ ዘመዶችሽ አንዱ ወይም አንዷ ወይም ብዙዎቹ የዚህ ባህል ተጠቂዎች ናቸው ::ይኽ በእንዲህ እንዳለ አንድ ወጣት የስጋ ዘመዴ የዚህ ባህል ተጠቂ ሆኗልና አንዳንዴ ልጠይቀው በቤተሰቦቹ የተሰጠው ሰርቪስ ቤት ውስጥ ስሄድ እንደሱ ሀያ መጀመርያዎቹ እድሜ ክልል ያሉ ብዙ እሱን መሰል ወጣቶች ተሰብስበው ቀኑ 14 ሰአት ጀምሮ እስከለሊቱ ዜሮ ሰአት ድረስ የስማበለው ወሬ እየደሰኮሩ ጫት ይቅማሉ :: ጫት ይቃማል ...ሲሻ ይጨሳል .....ታድያ አንዳንዴ ጨዋታቸው ወይም ባዶነት ያለው ጨዋታቸው እየናፈቀኝ ምንም ባልቅምም እነሱ ጋር እየሄድኩ የስማበለውና የቢሆን አለም ጨዋታቸውን አዳምጣለሁ .....ጨዋታው ውስጥ እሳተፋለሁ ....ወይም የምጠየቃቸው ጥያቄዎች ካሉ ጥያቄዬን ይማሩ ዘንድ ሰፋ አድርጌ በመመለስ ተስማምቼ እውላለሁ ::ይኽ በእንዲህ አሁንም እንዳለ ከዛ ወጣት ጫት ቃሚ አብላጫው የደህና ቤተሰብ ልጆች ....እንዲሁም በጣም ትልቅ የሆነ ሸቀጣሸቀጥ ሱቅ መሸጫ መደብራቸውን ጆሮውን ብለው ሳውዝ አፍሪካ ካሉ ሰው አስኮብላይ ማፍያዎች 1 ስልክ ብቻ የሚጠብቁ ለሞት እራሳቸውን ያዘጋጁ ወጣቶችን አይቼ ታዝቤያለሁ ::

እግዚአብሄር በሚያውቀው እውነቴን ነው የምልሽ ....ብዙ ስቶክ ያለውንና ጥሩ ትርፍ የሚያመጣውን ሸቀጣሸቀጥ መሸጫ ሱቃቸውን ሸጠው በሉ ተነሱ እስኪባሉ ድረስ ጫት እየቃሙ በጫት ምርቃናና በተስፈኝነት የተነሳ ከጉዋደኞቻቸው አድራሻ እያሰባሰቡ ያሰቡበት ገንዘብ የሚታፈስበት የላም አለኝ በሰማይ አገራቸው ገብተው ገንዘብ ባካፋ ሲያፍሱ ለጉዋደኞቻቸው የሆነ ትልቅ ነገር ለማድረግ ተስፋ የሚመግቡ ወጣቶችን ባይን በብረቱ አይቼ ከማየትም አልፌ ብመክራቸውም ሙድ ተይዞብኝ ምከረው ምከረው እምቢ ካለ መከራ ይምከረው ብዬ በውስጤ እሺ እንዳላችሁት ይሁን ሳልል ነገሮች ሲከሰቱብህ ወይም በነገሮች በምሬት ታሽተኽ ያሰብክበት መንገድ ስትደርስ አደራ አትርሳኝ ብዬ እነሱ ጋር የነበሩኝን ጊዜያቶች ጊዜያቶች አድርጌ ከነሱ ተለይቻለሁ ::

ሌላው ደግሞ ከዚህ በተነሳ አንድ አንድ ጥናቶችን ሳደርግ ኢትዮዽያ ውስጥ እንዲሰሩ የተፈቀደላቸው የግልም ሆነ የመንግስት ጋዤቶችና መጽሄቶች ላይ በተለያየ ጊዜ እንዲሁም የመንግስት ቴሌቪዥን ላይ ፕሮግራም ተሰርቶባቸው ሆነ ከዚህ አሰቃቂ የስደት ጉዞ ችግር አይተው ከሞት ተርፈው ላገራቸው አፈር የበቁትን ባለልምዶችን ኢንተርቪው እያደረጉ ለህዝቡ ታሪካቸውን እያወጡ ይኼንን አደገኛ መንገድ ሰዎች እንዳይሞክሩት ....ታንዛንያ ላይ ያልታሰረ .....ያልተሰቃየ ....እንዲሁም ሴቶችን ጨምሮ ያልተደፈረ ወንድ የለም እኛም ተደፍረናል ብለው ምስክርነት የሰጡትን ተመላሾች የጋዜጣ የመጽሄትና የቴሌቪዥን ፕሮግራም ባይኔ በብረቱ አይቻለሁ ....አንብቤያለሁ .......ታድያ ይኼ እያለ ነው በየቀኑ በተለያየ መንገድ ሄድን ብለው አንዴ ኮንቴነር ውስጥ ተቀቅለው ሞተው የሚገኙት ....አንዴ በባህር ...አንዴ በምግብና በውሀ ጥም ምክንያት በየቦታው ረግፈው የሚገኙት ::

እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ከትንሽ ተነስቶ ሳይሆን ባንዴ ሀብታም የመሆን ምኞት በሽተኛነት አገራችን ስለበዛ የፈለገ መንግስት በተለያየ ሜድያ ቢለፈልፍ ...ግለሰቦች ቢጽፉ እንደኛ ኤክስፒሪያንስ ያለው ቢመክራቸው የሚሰማ ስለሌለ ምንም ማድረግ ስለማይቻል ሲሞቱ እየሰሙ ከማዘን ሌላ ምን ማድረግ ይቻላል ?

ባህር ዳርን ልጎበን ሄጄ ሳለ ሁለት ያክስቴ ልጆች ጸጉራችንን ካልተሰራን ብለው የሆነ ጸጉር ቤት ሲገቡ ምሽት ስለነበር የእህቴን ልጅ ህጻን ልጅ ይዤ ስለነበር ውጭ እነሱን ከምጠብቅ ለምን ጸጉር ቤቱ ውስጥ ገብቼ አልቀድም ብዬ ጩጬዋን አቅፌ ወንበር ተሰጥቶኝ ቁጭ ብዬ ልጆቹ ጸጉራቸውን እየተሽሞነሞኑ እያለ ቀደዳ ተጀምሮ ስለነበር ከጸጉር ሰሪዋ ጋር የባጥ የቆጡን ስንቀድ የነገ ፕሮግራሟን ሳንጠይቃት ትነግረናለች ::
የልጅቷ ፕሮግራም ነገ ከአረብ አገር የመጣችን ልጅ ለመጎብኘት ነው ::ታድያ ይኼንን ፕሮግራም ስትነግረን ቆንጅዬ ፍልቅልቅ ፊቷ ባንዴ በሀዘን ከሰል መስሎ ነበር ::እኔም የፊትዋን መለዋወጥ አይቼ ምነው ፊትሽ ተለዋወጠ ስላት የሚያሳዝን ታሪክ ነገረችን ::

ታሪኩ እንደዚህ ነው ::
የሆነች በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ ከሚኖሩ ቤተሰቦች ምንም ሳታጣ ያደገች እድሜዋ 20ዎቹ ያለች ተማሪ የነበረች ልጅ ነች ::ይኼ የውጭ አገር ድሪም ኢትዮዽያ ውስት እንዳትኖር ውህች አገር ሄዶ ሀብታም የመሆን ምኞት ስላስቸገራት ቤተሰቦች ቢሉዋት ቢመክሯት እምቢ ብላ አረብ አገር ትሄዳለች ::ታድያ በሄደች በሶስተኛው ወር እዛው አረብ አገር እያለች እሷን ጨምሮ ሁለት ኢትዮዽያዊያን ሴቶች ባጠቃላይ ሶስት ኢትዮዽያዊያን ሴቶችን ማዳሟ ቀውሳ ይመስለኛል እነዚህን ምስኪኖች ከፎቅ ትወረውራቸዋለች ::ሁለቱ ሴት ኢትዮዽያዊያን ሴቶች እንደዚች ልጅ የከበደ እድለኖች ሆነው አደጋ ባይደርስባቸውም የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል .....ታድያ ይቺ ልጅ ምን የሆነች ይመስልሻል ?.............................
.............................
............................
ገመትሽ ?
እስቲ ገምቺ ................
....................
..........................
ከፎቅ በማዳሟ የተነሳ ከፎቅ በመወርወሯ የተነሳ በሄደች 3 ወሯ ሙሉ ፓራላይዝድ ሆና በዊልቼር አገሯ ተመለሰች .......ታድያ ያቺ ጸጉር ሰራተኛ እንደ ነገ ፓራላይዝድ የሆነችው ጉዋደኛዋን ልትጎበኝ እንደምትሄድና እኛም አብረናት መሄድ የምንፈልግ ከሆነ አር ዌልካም ብላ በዜናው እንድናዝን አደረገችን .....እንደ ነገ ሌላ ፕሮግራም ስለነበረን ባንሄድምና ይቺን እምቢተኛ ምስኪን ባላያትም እስካሁን ድረስ ያላየሁዋት ልጅ ልቤ ውስጥ በማዘን አለች ::

እንግዲህ ይታይሽ ምንም ሳታጣ ወደ ግርድና ....እሱም አልሳካ ብሎ የዘላለም ፓራላይዝድ ::

እና ምን ማድረግ እንደሚቻል ያስቸግራል ::ምንም የሌለው ኑሮን ለማሸነፍና ድሀ ቤተሰቦቹን ለመርዳት ይውጣ ....ወይም ፖለቲካ ውስጥ እጁ አለበት ተብሎ በመንግስት ስለሚሳደድ ይውጣ .....ነገር ግን በአሁኑ ሰአት ያለው በትንሹ እስከ 300,00ሺኽ የኢትዮዽያ ብር እየከፈለ በሳውዝ አፍሪካ ወይም በሊብያ ወይም በሱዳን በኩል ወደ አውሮፓ ሆነ አሜሪካ እንዲሁም አውስትራሊያና እስራኤል ለመሄድ ከፍሎ እዛው ታንዛንያ ,ሱዳን ,እረ ገና ካገር ሳይወጡ አፋር ምድርና ወሎ ምድር ኬሚሴ በራብ ,ወይም በኮንቴይነር ሙቀት ሞተው የሚገኙት ::

ብቻ ስለዚህ ነገር ተወርቶ አያልቅም ::

ለሁሉም አሰቃቂውን ዜና ላዩና ለሰሙ ልቦና ኖሮዋቸው ይኼንን አደገኛ ለመሞት ስደት ባይሞክሩት ጥሩ ነው እያልን በክብርነታችን ሆነን ጽሁፋችንን ስናቆም ፖለቲካ ሩም ከብቶቻችን ላይ ለማላገጥ ለመሄድ በመዘጋጀት ነው ::

ሾተል ነን ..........ያዳምና የኼዋን ልጅ ሆይ .....ከሰው ተመክሮ ተማር ::
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
www.shottel.webs.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ገላጋይ -1

ኮትኳች

Joined: 25 Aug 2006
Posts: 492

PostPosted: Thu Jul 12, 2012 4:02 pm    Post subject: Reply with quote

ሾጠል እንደጻፈ(ች)ው:

... ወጣቶች ተሰብስበው ቀኑ 14 ሰአት ጀምሮ እስከለሊቱ ዜሮ ሰአት ድረስ የስማበለው ወሬ እየደሰኮሩ ጫት ይቅማሉ :: ጫት ይቃማል ...ሲሻ ይጨሳል .....ታድያ አንዳንዴ ጨዋታቸው ወይም ባዶነት ያለው ጨዋታቸው እየናፈቀኝ ምንም ባልቅምም እነሱ ጋር እየሄድኩ ... ጨዋታቸውን አዳምጣለሁ .....

... ሾጠል .... በዘመድህ ቅናት የያዘህ ይመስላል ...

Last edited by ገላጋይ-1 on Thu Jul 12, 2012 4:19 pm; edited 1 time in total
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
recho

ዋና አለቃ

Joined: 20 Sep 2004
Posts: 2991
Location: Earth

PostPosted: Thu Jul 12, 2012 4:19 pm    Post subject: Reply with quote

ጦምኔው እንደጻፈ(ች)ው:
ጌታ እንደጻፈ(ች)ው:

ጦምን - እኔ ያልገባኝ ነገር ዝግጅቱን ወይም አዘጋጆችን መቃወም ይቻል ይሆናል ነገር ግን ገንዘቡን ከፍሎ ጊዜውን ሰውቶ ሊዝናና የሚሔድን ሰው መቃወም ወይም መሳደብ ይቻላል ? ስለማላውቅ ነው ምናልባት ይቻል ይሆናል Wink ቁምነገሩ ግን በክፍፍሉ ዲሲ ነው ወይስ ዳላስ ትክክል የሚለውን ለሕዝብ ፍርድ ቢተዉት ይመረጥ ነበር :: አዎ ዝግጅቶቹ የኢትዮጵያውያን እንደመሆናቸው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በራሱ አዕምሮ በመመራት የፈለገበት የመሔድ ነጻነት ያስፈልገዋል :: አንተ ፈልገህ የሄድክበትን ቦታ እኔ መጥቼ ልክ አይደለህም ስልህ እኔስ ልክ ለመሆን ማን መብት ሰጥቶኝ ነው ?

ባፋንኩሎ !!! Laughing Laughing Laughing Laughing

Exactly!!!
የግዛክትሊ ! አንዳንድ ጊዜ መቃወም ምን ማለት እንደሆነ ዴፊኒሽን ራሱ ሳያስፈልግ አይቀርም .. አሁን እዚህ ዋርካ ላይ ሪቾ ዳግማዊ ወያኔው ጋር ስላወራች ወያኔ እንዲሁም ናት ሁሉ ብለው በስድብ ያጥረገረጉኝ ነበርሩ ... ያዩ አይመስሉም ? ጦምን መሄድህን ካመንክበት እና ካዝናናህ መሄድህ መብትህ ነው .. ማለት ያንተን የፖለቲካ አቁዋም አያሳይም .. በርላይ ቆሞም ሲያላዝኑ መዋል ጅልነት ወይንም ስራ ፈትነት ነው ለኔ ... ዲሲ አካባቢ ብሆን ኖሮ ልሄድ እችል ይሆናል .. እነ I. T. ለማየት ( ቅቅቅ አይ ክብዬ ) ከዛ ውጪ እነ ጦኔውን በርላይ ቆሞ ሌባ ሌባ በማለት የሚገኝ ፖለቲካዊ ለውጥ ይኖራል ብዬ አላምንም Laughing እንኩዋን ተዝናናህ ለማንኛውም ...
_________________
ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
recho

ዋና አለቃ

Joined: 20 Sep 2004
Posts: 2991
Location: Earth

PostPosted: Thu Jul 12, 2012 6:54 pm    Post subject: Reply with quote

ሾተል የከብቶች ባለቤት Laughing እንደምን አለህ ? ሪቾ ዋርካ ለዋርካ እያውደለደለች አለችው ያው ..

በጣም አሪፍ ትዝብት ነው .. ኢትዩዽያ ያለው ሁኔታ እኔም በተለያየ ሚዲያ እና ከዘመድ አዝማድ እንደምሰማው በጣም አስፈሪ ነው ... ምንም ያክል ቢጣር ልጆቹ ከመሞከር ወደሁዋላ አይሉም ... በየአረብ አገሩ ከሚሰቃዩት ጀምረህ ..ወረቀት ስለሌላቸው ብቻ በሰለጠነ አገር ላይ ዘመናዊ ባርነት እስከተጫነባቸው ድረስ ማየት ይቻላል ... መቸም ስራ አጦቹን እረዳቸዋለሁ .. እኔ የሚገርመኝ ሱቅ , ቤት እንዲሁም ንብረት በሙሉ ሸጠው ለስደት የሚዘጋጁትን ነው ... እግዚአብሄር ይድረስልን እንጂ አስጊ ነው .. በቀን 5000 ሰው በላይ ፓስፖርት ለማውጣት ከተሰለፈ .. ምን ሰው ተርፍዋል ??? የትስ ነው የሚሄዱት ? ፓስፖርት ለማግኘት በአሁኑ ሰአት 3ወር መጠበቅ ይኖርብሀል ... 2 እና 3 ቀን ሲሰጥ ነው እኔ የማስታውሰው ... ! እንግዲህ ...የኢትዩዽያ አምላክ ዝም አትበል ከማለት በላይ ምን ይባላል ? Crying or Very sad
_________________
ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ገልብጤ

ውሃ አጠጪ

Joined: 26 Jun 2010
Posts: 1108

PostPosted: Thu Jul 12, 2012 8:22 pm    Post subject: Reply with quote

recho እንደጻፈ(ች)ው:
ጦምኔው እንደጻፈ(ች)ው:
ጌታ እንደጻፈ(ች)ው:

ጦምን - እኔ ያልገባኝ ነገር ዝግጅቱን ወይም አዘጋጆችን መቃወም ይቻል ይሆናል ነገር ግን ገንዘቡን ከፍሎ ጊዜውን ሰውቶ ሊዝናና የሚሔድን ሰው መቃወም ወይም መሳደብ ይቻላል ? ስለማላውቅ ነው ምናልባት ይቻል ይሆናል Wink ቁምነገሩ ግን በክፍፍሉ ዲሲ ነው ወይስ ዳላስ ትክክል የሚለውን ለሕዝብ ፍርድ ቢተዉት ይመረጥ ነበር :: አዎ ዝግጅቶቹ የኢትዮጵያውያን እንደመሆናቸው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በራሱ አዕምሮ በመመራት የፈለገበት የመሔድ ነጻነት ያስፈልገዋል :: አንተ ፈልገህ የሄድክበትን ቦታ እኔ መጥቼ ልክ አይደለህም ስልህ እኔስ ልክ ለመሆን ማን መብት ሰጥቶኝ ነው ?

ባፋንኩሎ !!! Laughing Laughing Laughing Laughing

Exactly!!!
የግዛክትሊ ! አንዳንድ ጊዜ መቃወም ምን ማለት እንደሆነ ዴፊኒሽን ራሱ ሳያስፈልግ አይቀርም .. አሁን እዚህ ዋርካ ላይ ሪቾ ዳግማዊ ወያኔው ጋር ስላወራች ወያኔ እንዲሁም ናት ሁሉ ብለው በስድብ ያጥረገረጉኝ ነበርሩ ... ያዩ አይመስሉም ? ጦምን መሄድህን ካመንክበት እና ካዝናናህ መሄድህ መብትህ ነው .. ማለት ያንተን የፖለቲካ አቁዋም አያሳይም .. በርላይ ቆሞም ሲያላዝኑ መዋል ጅልነት ወይንም ስራ ፈትነት ነው ለኔ ... ዲሲ አካባቢ ብሆን ኖሮ ልሄድ እችል ይሆናል .. እነ I. T. ለማየት ( ቅቅቅ አይ ክብዬ ) ከዛ ውጪ እነ ጦኔውን በርላይ ቆሞ ሌባ ሌባ በማለት የሚገኝ ፖለቲካዊ ለውጥ ይኖራል ብዬ አላምንም Laughing እንኩዋን ተዝናናህ ለማንኛውም ...

Quote:
አሁን እዚህ ዋርካ ላይ ሪቾ ዳግማዊ ወያኔው ጋር ስላወራች ወያኔ እንዲሁም ናት ሁሉ ብለው በስድብ
ያጥረገረጉኝ ነበርሩ ...

እነማን Question Question እስኪ እንዲህ ብሎ የተሰደብሽበትን ፖስት እዚህ ዱቅ አድርጊው ...እኔ እንኳን እስካሁን እንዲህ ብሎ የሰደበሽን አላየሁምም አላነበብኩምምምም ...ወይስ
_________________
SEX IS NOT THE ANSWIER, SEX IS THE QUESTION '* YES* IS THE ANSWIER
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Yahoo Messenger Report post
recho

ዋና አለቃ

Joined: 20 Sep 2004
Posts: 2991
Location: Earth

PostPosted: Fri Jul 13, 2012 8:12 pm    Post subject: Reply with quote

ፍራይዴይ ሱፐርስቲሽን ...

From the Christian bible:
- Friday is reputed to be the day Eve gave Adam the apple.
- It is said to be the day Adam & Eve were expelled from the Garden of Eden.
- Friday is also reputed to be the day they (Adam & Eve) died.
- The Great Flood is supposed to have started on a Friday.
- God was said to have struck the builders of the Towel of Babel and created the confusion of many tongues, on a Friday.
- The Temple of Solomon was destroyed on a Friday.
- Christ was crucified and died on a Friday.

በተጨማሪም ...

- Clothing made on a Friday will never fit properly.

- Visiting your doctor on Friday will not have a good result.

- Never change your bed on a Friday, as it will result in nightmares and bad dreams.

- One should not move their residence or marry on a Friday, if they expect any good to come of it.

- Cut your nails of Friday and you cut them for sorrow.

- Ill news received on a Friday will etch wrinkles in the face of the recipient, more so than the same news received on any other day.

- Friday is an inauspicious day to start a trip as "misfortune will bound to follow."

Laughing
_________________
ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዳግማዊ ዋለልኝ

አለቃ

Joined: 20 Oct 2010
Posts: 2359

PostPosted: Fri Jul 13, 2012 10:36 pm    Post subject: Reply with quote

recho እንደጻፈ(ች)ው:
አይይይይ ደግሞ እኮ ጨዋታ አምጪ ... ቆይ የራሴን ሀሳብ ልጨማምርበት ምናምን ይባልልኛል Laughing

አንቺ ልጅ .....የቤቱን ርእስ በየቀኑ እየለዋወጥሽ ውይይቱን ቀልብ ነሳሽው Laughing Laughing

ሠላም ነሽ recho.......TGIF Exclamation Wink
_________________
“Meles Zenawi's passion was in abolishing poverty" Former Prime Minister of United Kingdom Gordon Brown
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዉቃው

ዋና ኮትኳች

Joined: 07 Jan 2007
Posts: 968

PostPosted: Sat Jul 14, 2012 3:50 am    Post subject: Reply with quote

recho እንደጻፈ(ች)ው:
ከለር ምርጫ .. በፈጠራቹ እዚህ አገር ከለር ያያሉ .. ወንድሞቼ ፒንክ ላንች ፔል ወይንም ፐርፕል ቦግ ያለውን መርጣቹ አትልበሱ ...እንደዚሁም ... መንገድ ላይስትሄዱ አትያያዙ .. እኔ ይገባኛል እጅ ለእጅ መያያዝ አይደለም ተቃቅፋቹ ተኝታቹ ባይ ምንም እያረጋቹ አይደለም ( አይ ሆፕ ኖት Laughing ) እዚህ አገር እስካለን እረስ ወደድንም ጠላንም በነሱ ባህል መገራት ይኖርብናል ...

ስትራመድ ቂጥህን እየወዘወዝክ አትሂድ .. አይ ኖው ይሄንን በምን አቃለሁ እንደምትል .. ከእግርህ ነጠር ነጠር ብለህ ትከሻህን ቀጥ አርገህ ሂድ እንጂ የሰውነት እንቅስቃሴ አያስፈልግም .. (ይቀርታ ወንድሞቼ )

እባክሽ አትቅለስለሺ ... ሲያናግሩሽ አይ ኮንታክት አታስወግጂ .. እነሱ የሚያዩት ትሁትዋን አንቺን ሳይሆን ፍለርት ልታረጋቸው የምትጣጣር አንዲት ደካማ ልጅን ነው .. ትደፈሪያለሽ .. ስለዚህ ሲያናግሩሽ አይንሽን አትስበሪ .. ድምጽሽን ጭክ አርገሽ ተናገሪ .. ሞጥሙዋጣ አይሉሽም !

አትደፈሪ ... ማንም እንዲረማመድብሽ አትፍቀጂ .. መብት አለሽ .. እዚህ (አበሻ ወንድን ጨምሮ ) አግባብ የለሽ ንግግርም ሆነ ንክክኪ ካለፍላጎትሽ ሊዳፈርሽ ከሞከረ አስቁሚው ... ስራ ቦታ በተለይ ምንም አይነት ጾታዊ ንክክ በማድረግ የሚገጅ ትልቅ ጥቅም ይኖራል ብለሽ አትዳፈሪ .. አንድ ጊዜ ስምሽ ከወጣ ወጣ ነው .. በነሱ ሚስጥር አይደለም .. ዛሬ ያቺን ኢቲዩዺያኢትዋን ልጅ እኮ ***&)&*&*0 ብሎ ያርፈዋል .. አለቀ ማለት ነው ..ጥንቅር ብሎ ይቅርብሽ .. ክብርሽን ጠብቂ .. !

ወንድማለም .. አለቃ ሲያዝህ እንቢ የማለት መብት የለህም .. ሀሳብህን የምግለጽ ግን መብት አለህ .. ያለ አግባብ የሆነ ትዛዝ ጭቆናም ሆነ ምን ካለ ከመጋተርህ በፊት ... እንደውም እንደተቀጠርክ . የመስሪያቤትህን ህግ ለማጥናት ሞክር .. መብትና ግዴታህን እወቅ .. በተለይ መተዳደሪያ ህግ ካለ በደንብ ለመረዳት ሞክር .. ማምለጫህ ነው ..

አትፍሩ .. አቦ ሰው ታሞ እንጂ ፈርቶ አይሞትም .. ቁዋንቁዋ እጥረት ካለ ምንም አይደል .. ኦልሞስት ሁሉ ቦታ አስተርጉዋሚ የመጠየቅ መብት አለን .. የነሱን ቁዋንቁዋ በደንብ አልተናገርንም ማለት እውር ደንቆሮ መሀይም ነን ማለት አይደለም .. የአራሳችን ባህልእና መብባቢያ አለን ... ሽምቅቅ አትበሉ .. አዝ ፋር አዝ አይ ኖው .. አሜሪካ የሁላችንም አገር ናት .. ዌር አር ፍሮም ሲሉኝ ኢቲዩዺያ .. ዋት አባውት ? ስንተኛ ጀነሬሽን ነህ ከፋሚሊህ አሜሪካዊ በመሆን ? Laughing

እንግዲህ ይሄ የራሴ ድምዳሜ ነው .. ትክክልም ስተትም ልሆን እችላለሁ .. ለሚያርመኝ .. ለመታረም ዝግጁ ነኝ Smile

ሪጮ ...ያቀረብሸው ጥሩ ነው :: አዲስ ለሚመጡ ..ለመጡ እና ቆይተውም ቢሆን ግትር አቋም ላላቸው የሚሆን ነው :: በተባለው ላይ የራሴን አመለካከት ብጨምር ::

ባሜሪካ መስረቅ ጥሩ ነው :: ስትሰርቅ ግን የመጨረሻ አሪፍ ሁን ..እንዳትያዝ :: ሁልጊዜ ሜክ ሹር ከቨር ዮር አስ :: አለዚያ የነሱ ሰለባ ትሆናለህ :: ስርቆት የሚባለው ከሰቨን ኢለቨን እስከ ታክስ ሪተርን ያለውን የገንዘብ ማግኛ ዘዴ ያጠቃልላል ::

በመስሪያ ቤት አካባቢ የምትውል ከሆነ ማግሳትን ማስተር አርግ :: አንተ እየበላህ ወዳጆቻችን በልተው እያገሱ በብስናቱ ቢያውዱህ አትግረም :: ነገ ገና ምግባቸውን ከፍተው ሊበሉ ሲጀምሩ በግሳት ቀደስላቸው :: ከዚያ ድክም ባለች ሰላላ ድምጽ ሶሪ በል ::

መኪና ...ቤት ስተገዛ ...ስተከራይ ...ስራ ስትቀጠር ወዘተ የማይነግሩህ ነገሮች በጣም ብዙ ነገሮች አሉ :: የሚያስፈርሙንን ዲቴል ስለማናነብ .. የቤት ስራህን አስቀድምህ መስራት እና ሪስርች ማድረግ ኋላ ከማለቃቀስ በጅጉ ይረዳሃል ::

ዲፈንሲቭ አትሁን :: እንደኳስ እየተቀባበሉ ይጫወቱብሃል :: ሁሌም ባካፕ ፕላን ...ወይም ከፕላን ሌላ ፕላን እና ሲን አትርሳ :: በራስህ ላይ ቀልድ :: ኢትዮጵያ የሶስት ሺህ ዘመን ታሪክ ያላት ..አድዋ ላይ ነጭን ድል ማድረጋችንን ከኔ ጋር ቢራ ስንጠጣ እናወራዋለን :: ወዳጄ ሆይ ... እነሱ ይህንን መስማት አይፈልጉም :: ያገራችንን ኢሜጅ አንተ በኔበርሁዱ በምታደርጋት ትንንጥዬ ዲስኩር አይለወጥም ..አይታመንንም :: ስለዚህ አትልፋ :: ምግብ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀመስከው አሜሪካ እንደሆነ ከነገርካቸው አፋቸውን ከፍተው ያዳምጡሃል ...ትንኮሳቸውንና የዝቅተኛነት ስሜት እንዲሰማህ የሚያድረጉትን ነገር በራሳቸው ጊዜ ይተዉልሃል ::

ታጠቅ :: የጦር መሳሪያ ይኑርህ :: ራስህን ቤተሰብህን ትጠብቅበታለህ :: "እግዜር እንጂ ሽጉጥ ማንን ይጠብቃል " ካልክም የራስህ ጉዳይ :: ለታንክስ ጊቪንግ እና ከሪስማስ ተራ የሸቀጥ ቅናሽ ለማግኘት ሲል ህዝቡ እንዴት በየስቶሩ እንደሚባላ አይተሃል :: አንድ ኬኦቲክ የሆነ ነገር ቢፈጠር ..ፒፕሉ ሪአክት የሚያድረገው ለክ እንደዚያ ነው :: ስለታጠቀም ርህራሄ አይኖረውም የለውምም ::

ዴዚደራታዬ ነካ ነካ ናት እንጂ በጣም ብዙ የምለው ነበረኝ :: አድማጭን ማስለቸት ይሆናል እንጂ

አባ ዉቃው
ከሴክሽን 8
_________________
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ዳግማዊ ዋለልኝ

አለቃ

Joined: 20 Oct 2010
Posts: 2359

PostPosted: Sun Jul 15, 2012 9:50 am    Post subject: Reply with quote

ዉቃው እንደጻፈ(ች)ው:
ከዚያ ድክም ባለች ሰላላ ድምጽ ሶሪ በል ::

Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing

በሰላላ ድምፅ ያሰማኸውን "ሶሪ " የሚለውን ቃል ካሰማህ በኽላ ልክ የእነሱን አይነት የፉገራ ፈገግታ ጥርስህን ብቻ ብልጭ አድርገህ አሳያቸው .....icing on the cake ይሉታል መሰለኝ

Quote:
ዲፈንሲቭ አትሁን :: እንደኳስ እየተቀባበሉ ይጫወቱብሃል :: ሁሌም ባካፕ ፕላን ...ወይም ከፕላን ሌላ ፕላን እና ሲን አትርሳ :: በራስህ ላይ ቀልድ :: ኢትዮጵያ የሶስት ሺህ ዘመን ታሪክ ያላት ..አድዋ ላይ ነጭን ድል ማድረጋችንን ከኔ ጋር ቢራ ስንጠጣ እናወራዋለን :: ወዳጄ ሆይ ... እነሱ ይህንን መስማት አይፈልጉም :: ያገራችንን ኢሜጅ አንተ በኔበርሁዱ በምታደርጋት ትንንጥዬ ዲስኩር አይለወጥም ..አይታመንንም :: ስለዚህ አትልፋ :: ምግብ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀመስከው አሜሪካ እንደሆነ ከነገርካቸው አፋቸውን ከፍተው ያዳምጡሃል ...ትንኮሳቸውንና የዝቅተኛነት ስሜት እንዲሰማህ የሚያድረጉትን ነገር በራሳቸው ጊዜ ይተዉልሃል ::

ሁሌም በራስህ ላይ ብቻ አትቀልድ ......አንዳንዴም ወደጥቃት ተሸጋገር ....ዘና ብለህ ;እንደቀልድ አድርገህ የኒንጃ ቦምብህን ጨዋታ መሀል ጣል አድርገው ....ለምሳሌ ሰሞኑ ኢንዲፔንደንስ ዴይ ላይ ክሪስ ራክ ትዊት እንዳደረገው ....."Happy white peoples Independence Day the slaves weren't free but I'm sure they enjoyed fireworks." Laughing Laughing

ቢሆንም ቢሆንም ለፉገራ ፈገግታውም ሆነ ለጥቃት ቀልዱ ከማን ጋር እንደምትጋፋ ሁልጊዜም አስተውል ......ጓድ ውቃው እንዳለው ሙከራህ ከንቱ ልፋት ሆኖ ለባሰ ጥቃት ሊያጋልጥህ ይችላልና .....ምክንያቱም ክሪስ ራክ አይደለህምና Wink

ኻላ ውርድ ከራሴ ...ተናግሬአለሁ Rolling Eyes
_________________
“Meles Zenawi's passion was in abolishing poverty" Former Prime Minister of United Kingdom Gordon Brown
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
recho

ዋና አለቃ

Joined: 20 Sep 2004
Posts: 2991
Location: Earth

PostPosted: Mon Jul 16, 2012 4:10 pm    Post subject: Reply with quote

ዉቃው እንደጻፈ(ች)ው:

ሪጮ ...ያቀረብሸው ጥሩ ነው ::
ሰላም ውቄው ... ታንኩ ፎር ፓርቲሲፔቲንግ .. ከምርን አድናቂህ ከመቂ Laughing

Quote:
አሜሪካ መስረቅ ጥሩ ነው :: ስትሰርቅ ግን የመጨረሻ አሪፍ ሁን ..እንዳትያዝ :: ሁልጊዜ ሜክ ሹር ከቨር ዮር አስ :: አለዚያ የነሱ ሰለባ ትሆናለህ :: ስርቆት የሚባለው ከሰቨን ኢለቨን እስከ ታክስ ሪተርን ያለውን የገንዘብ ማግኛ ዘዴ ያጠቃልላል ::

አይ አር ኤስ ጋር በዚህ ጉዳይ ዲል የምታረግ ከሆነ እና ከተያዝክ .. አንተን አንዳያደርገኝ ዘወትር ተግቼ ጸልያለሁ ... አንድ ቲፕ ልስጥህ ወንድሜ ያገሬ ልጅ ..ይሄንን ለማድረግ ከወሰንክ ሚስጥርህን ያዝ ... ከሚስትህ እንኩዋን ጥሩ ግንኙነት ከሌላቹ አንናገር ... ሰዎቹ የቤትህ እቃ ላይ እንኩዋን ሳይቀር አይን አላቸው ...

Quote:
በመስሪያ ቤት አካባቢ የምትውል ከሆነ ማግሳትን ማስተር አርግ :: አንተ እየበላህ ወዳጆቻችን በልተው እያገሱ በብስናቱ ቢያውዱህ አትግረም :: ነገ ገና ምግባቸውን ከፍተው ሊበሉ ሲጀምሩ በግሳት ቀደስላቸው :: ከዚያ ድክም ባለች ሰላላ ድምጽ ሶሪ በል ::
ምነው ፈስ ተረሳ ? ማይ ጋድ ይሄንንስ ለናንተ አልመክርም ከምርን .. ሰዎቹ በላይም በታችም ዝም ብለው ይለቁታል .. እኔ እስካሁን አልለመድኩላቸውም .. !!! Evil or Very Mad Twisted Evil

Quote:
መኪና ...ቤት ስተገዛ ...ስተከራይ ...ስራ ስትቀጠር ወዘተ የማይነግሩህ ነገሮች በጣም ብዙ ነገሮች አሉ :: የሚያስፈርሙንን ዲቴል ስለማናነብ .. የቤት ስራህን አስቀድምህ መስራት እና ሪስርች ማድረግ ኋላ ከማለቃቀስ በጅጉ ይረዳሃል ::
Laughing Laughing ካለዛ እንደሪቾ 1200 ብር ትላቀቃለህ ! ቤት አከራዬ ትልቅ ድርጅት ያንን ያክል ብር ባልተደራጀ ጉልበቴ አቅምሰውኛል .. ነገሩ ቀላል ነው .. ሙቭ ላረግ እንደሆነ ቀኑን ጠብቄ ሄጄ ተናገርኩ .. ሊዝ ኦፊስ ያለችዋ ሴት ምነው ምናምን .. አይ በቃ መልቀቅ ፈልኩ .. ፕሮብሌም ... ! እኔ በኔቤት ለቅቂያለሁ .. ለካ መፈረም ያለበት ወረቀት አለ ( ሊዘ ላይ ቁልጭ ብሎ አለ ) ስለዚህ ለልጅትዋ በአፍ ስትናገሩ ለካ ወረቀት መስጠትና ማስፈረም ነበረባት ኖቲስ መስጠቴ ህጋዊ እንዲሆን .. ግን አላረገችም .. ስለዚህ በሶስተኛው ሳምንት ላይ ዝም ዝም ሲሉኝ ድጋሚ ምንድነው ነገሩ ብዬ ብጠይቅ ወረቀትሽ የለም .. Laughing በአፍ ነገርኩሽኮ ስል .. እሱንማ ያው በኔና ባንቺ መካከል ነገርሽኝ እንጂ እንደኖቲስ አይቆጠርም Laughing አር ማይ $% ፍሬንድ ላንቺ መጥቼ ፕላኔን የምነግርሽ ስራሽን እንድትሰሪ እንጂ .. እስዋ ምን አግብትዋት .. በፕላስቲክ ፈገግታዋ ታጅባ .. ሊዝሽ ላይ አለ .. አንቺም ስላላስታወስሺኝ እኔም ረሳሁት .. ስለዚህ የሚቀጥለውን ወር ሙሉና የዚህን ወር የቀረውን ከፍለሽ መውጣት ትችያለሽ .. ከፈለግሽ ሙቭ ካረግሽ ቡሀላ የከፈልሽበትን አንድ ወር ቁልፉን መያዝ ትችያለሽ .. ዋት አም አይ ጎና ሁለት ቤት ውስጥ ? ያማታል ? ለሁሉም ሌላ ቤት ለመከራየት የዚህች ሴት ሪፈረንስ ስለሚያስፈልግ ያው ተከፈላታ .. አንጀቴ እያረረ .. ግን ጥፋቱ የማን ነው .. የሪቾ የራስዋ ! ሊዜን ማንበብ ነበረብኝ .. ኦቪየስሊ አላነበብኩትም .. አሁን ምንም ነገር ስከራይ ሆነ ስከራይ .. መነጽሬን አቀብሉኝ እናንተ ብዬ ጥንፍፍ አርጌ አነባለሁ Laughing

Quote:
ታጠቅ :: የጦር መሳሪያ ይኑርህ :: ራስህን ቤተሰብህን ትጠብቅበታለህ :: "እግዜር እንጂ ሽጉጥ ማንን ይጠብቃል " ካልክም የራስህ ጉዳይ :: ለታንክስ ጊቪንግ እና ከሪስማስ ተራ የሸቀጥ ቅናሽ ለማግኘት ሲል ህዝቡ እንዴት በየስቶሩ እንደሚባላ አይተሃል :: አንድ ኬኦቲክ የሆነ ነገር ቢፈጠር ..ፒፕሉ ሪአክት የሚያድረገው ለክ እንደዚያ ነው :: ስለታጠቀም ርህራሄ አይኖረውም የለውምም ::
እነሱም ያረጉታል .. አትፍራ ፍሬንዴ .. የድሮ ሩም ሜቴ .. ዛት ሚስኪን ቀጫጫ ነጫጭባ መዛ ያወጣችውን ከአባትዋ የወረሰችው የሚመስል ከስዋ ቁመት በላይ ጠመንጃ ካየሁ ቡሀላ .. ልጄ ልብና ወኔ ካለ ቢኖር ይመረጣል .. እኔና ጠመንጃ ግን አንድ ቤት ካደርን ያቃዠኛል .. Laughing
_________________
ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ጦምኔው

ውሃ አጠጪ

Joined: 14 Jan 2007
Posts: 1433
Location: Right here

PostPosted: Mon Jul 16, 2012 4:59 pm    Post subject: Reply with quote

ምስኪን ሪችዬ 1200 ብርሽ እሪሪሪሪ እያለች ተሸበለለቻ Laughing ሊዝ ስትዪ እኛም አሁን ያለሁበት ቤት ሙቭ ስናደርግ ቺኳ (ሊዚንግ ኦፊስ ያለችው ናታ !) ሊዛቹን በዲሴምበር ፈርሙት እና ግን ያው ጃኑዋሪ ላይ ትገባላቹ :: የዲሴምበሩ ያው ለኦፊሻል ዶኩመንቴሽን እንጂ ፋይናንሺያሊ እናንተ ሪስፖንሲብል አይደላቹም ስትለን እኔና ፍሬንዴ እሺ ብለን መፈረሚንግ :: እናቱ ከሶስት ወር በኍላ አውት ስታንዲንግ ቢል አለባቹ ብለው የዲሴምበሩን ካልከፈላቹ ብላብላብላ ....ያው የፈረምነውን ወረቀት ይዘው ከች አሉና ከሜይን ኦፊስ ነን ምናምን የሚሉ ፋት አስ ነጮች $$$$ ወስደው ከበጀት ውጪ አደረጉን :: Laughing እና ያው ምንም ነገር መፈረምም ሆነ አለመፈረም ጣጣ አለው :: አጠንፍፎ ማንበቡ ያዋጣል ::

ሌላው ክሬዲት ካርድ ሲወጣ መጀመሪያ ተርሞቹን በደቃቃ ፎንት ሳይዝ ፕሪንት አድርገው ነው የሚሰጡን :: እኔማ በቃ ገና ሳየው እንኳን ላነበው ደሜ ነው የሚፈላው :: እና በቃ ሳይነበብ ይፈረምለታል በየወሩ የማይገቡ ቻርጆች ይመጣሉ :: ምነው ? ስትሉ "ተርሙ ላይ ተስማምተው የፈረሙት ነው ' ትባላላቹ :: ስለዚህ ጊዜን ወስዶ አስተርጓሚም ፈልጎ አፈላልጎም ቢሆን ማንበቡ ይመከራል ::

ሌላ አንድ ምክር ....አንጅ ጀለሴ ፓርኪንግ እዚህ ዲሲ የሚሰራ ምርር ብሎት የነገረኝ እሮሮው ነው :: ሀበሾች መኪና ይዘው ፓርክ ለማድረግ ይመጡና ጠቀስ ጠቀስ አድርገው በነጻ ለማቆም ተስፋ ያደርጋሉ :: የሆነ ሀበሽነታቸው ሰም ካይንድ ኦፍ ፓስ እንደሆነ ነገር :: ይሄ በፓርኪንግ ብቻ ሳይሆን የትም ሀበሻ ባለበት ቦታ ያለ ነው :: ሆቴል ራሱ ይመጡና ፍሮንት ዴስክ ላይ ሀበሻ ካዩ ኤክስትሪም ዲስካውንት ይጠብቃሉ :: ኧረ በመጻ ሁሉ ለማደር ይቋምጣሉ Laughing ፋክ ዛት :: ያው ሀበሻ እዚያ ቦታ ላይ ስራውን እየሰራ እንደሆነ ይግባቹ :: ፔይ ፍሪኪንግ $$ እንደማንኛውን ሰርቪስ ተጠቃሚ :: በናይስነት ያደረገላቹን እገዛ አፕሪሺየት አድርጋቹ አመስግናቹ አምልጡ :: አንዳንዱማ ጭራሽ ሊበሳጭ ሁሉ ይሞክራል :: የሆነ ዲሳፖይንትድ ምናምን ይሆናል :: ኤክስፔክቴሽኑ ስላልተሟላ ::

ሌላው ነጭም ይሁን ጥቁር እኩል ሰርቭ አድርጉ :: በእውነት ስላየሁት ነው :: አብዛኛው ሀበሻ ነጭ ሲያይ ያሸረግዳል :: ጥቁር ደሞ ሲያይ ያው ስቴሪዮታይፕ አለ አይደል ድራግ እና ሹቲንግ ያስባል :: ሰው ሰው ነው :: እኩል ነን ሁላችንም :: ከማንም አናንስም ከማንምም አንበልጥም ::

ውቅሽ መታጠቅ ያልከው ሙድ ያለው ሀሳብ ነው :: እኔ እንደውም ሹቲንግ ስልጠና ሁሉ ጀምሬያለሁ :: ከሰሞኑ ይሸመትለታል :: ያው ሽግር አለ ?? ሽግር ካለ ሽጉጥ አለ እንደሚባለው ነው ::

ፒስ
_________________
http://www.youtube.com/watch?v=_jIwsS_eT5w

http://www.cyberethiopia.com/warka4/viewtopic.php?t=22540&start=105
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 24, 25, 26 ... 108, 109, 110  Next
Page 25 of 110

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia