WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
እረ አይዋሽ ! እውነቱን እንዘግብ !!

Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5066

PostPosted: Fri Jun 08, 2012 1:01 pm    Post subject: እረ አይዋሽ ! እውነቱን እንዘግብ !! Reply with quote

""በምድር ያሰራችሁት በሰማይ የታሰረ ይሆናል ...በምድር የፈታችሁት በሰማይ የተፈታ ይሆናል "" የምትለዋን ሰማያዊ ቃል ...አንዳንድ የዳቤ ፍቅር በመንፈሳቸው ውስጥ ያደረ ካህናት ግዘትን ለመግለጽ የተነገረ አድርገው ሲያስተምሩ ይግርመኛል ...እወነቱ እሱ አይደለም ..እውነቱ ያለው ወዲህ ነው ...ወደፊት መንፈስ እንዳሳሰበኝ እንግርዎታለሁ የተከበሩ አንባቢዬ ሆይ :: "" እውነትን ተናገር እሷም ነጻ ታወጣሀለች "" ይላል ..ታላቁ መጽሀፍ ሌላ ቦታ ደሞ :: እንዲህ ሆነልዎ ..አቶ ዳዊት ከበደ ልያዝ መሆኑ ውስጥ አዋቂ ስለነገረኝ ወደ አሜሪካ መጣሁ ካሉ በኍላ በሙያቸውና በክህሎታቸው አገር ቤት የጀመሩትን ስራ እዚህ ይቀጥላሉ ...አውራ አምባን ባሜሪካ !! መቼም እቺ አሜሪካ እኮ የኢትዮጵያ ትግል የመጨረሻ መዳረሻና ማሳረጊያ ሆናልዎታለች :: ዳዊት እዚህ መጥቶ የሆቴል ማናጀርነት ስራ ወይም ፓርኪንግ አቴንዳንት እንዲሆን የወሰነው በሙያው ( በጋዜጠኝነት ) መንቀሳቀስን ነው :: መልካም ነው ::ለመግባት ቀላል የሆነ ስራ ዘንድሮ እሷ ናት ችግሩ ግን ኢቲክሱን ጠብቆ መቆየቱ ነው ከባድ ...!! እና አቶ ዳዊት ናይ እለቱ ዋና ዜና ብሎ ይሄን ይጽፋል "" ባዲስ አበባ ወይራ ሰፈር የሚገኘው የደብረ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የእሳት ቃጠሎ ደረሰበት "" ብሎ ይጽፋል :: ዜናው ይሀው :: የቤተ ክርስቲያንና የሀይማኖት ጉዳይ ሰሞኑን ለዜና አሪፍ አኪር ነው ... ይሄ ዜና ያስደነገጠውና ባህኑ ሰአት አዲስ አበባ ያለው የኢትዮጵያ ፈርስቱ ቢኒያም ደሞ እንዴት እኔ እዚህ ቁጭ ብዬ ሳልሰማ ይልና ወዲህም እርሙን ለማውጣት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን እየበረረ ይሄዳል ሲደርስ ተቃጥሏል የተእባልው ቤተ ክርስቲያን ምንም አይነት የሳት ወላፈን እንዳልነካው ሲያይ ..ተሳልሞ ምጽዋት ሰጥቶ ክላራይሶን ለነ ዳዊት አድርሶ ይመለሳል :: ተቃጠለ የተባለለት ቤተ ክርስቲያን ፎቶግራፍ ይሄን ይመስላል :: እቺን ጠቅ የተከበሩ :: ወንድሜ ዳዊት አንባቢ አገኛለሁ ብለህ ያልሆነ ነገር ድህረ ገጽህ ላይ አትጻፍ !! ሰዎች እውነቱን ካወቁ በኌላ "እሱ እባክህ ቁጨኛ ነው "" እያሉ ይላጡብሀል :: ሰላም ቀን ::
_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
ስልኪ

ዋና ውሃ አጠጪ

Joined: 22 Aug 2007
Posts: 1823

PostPosted: Fri Jun 08, 2012 4:03 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ክቡራን ወንድሜ ,

ፖስትህን ሳላይ ከታች ያለውን እንደ አዲስ ርእስ ለጥፌ ነበር :: ይቅርታ አርሜዋለሁ !!!

ምድረ ራስ ወዳድ የሀገርና የህዝብ ጠላት ነውጤ ሰሞኑን ብዙ የውሸት ፋብሪካዎቻቸው እያስመረቁ ነው :: ዋናው ፋብሪካ ኢሣት በመለስ አሜሪካ ጉዞ ቆርጦ ሲቀጥል እነስልኪና ሌሎች እውነተኞች እጅ ከፍንጅ ይዘነዋል , የግም -ቦት 7 የፖለቲካ ቆርጦ ቀጥልነት አገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ስለሆነ እዚህ መግለፅ አያሻኝም - ባለ 500 ዶላር ሜዳልያዎች ታውቁታላችሁ ::

ዛሬ ደግሞ አዲስ ፋብሪካ ተቋቁሞ "ሀገር ተቃጠለች " ውሸቱን ለጤነኞች ሳይሆን ለዘገምተኞች ሲሸጥ ተይዟል :: ይሄውና ተቃጠለ የተባለው ጊዮርጊስ ከቃጠሎው በኋላ ከሙታን ተነስቶ ይሁን ሳይቃጠል ቀርቶ እዚህ አምሮበት ታዩታላችሁ ::

http://www.ethiopiafirst.info/news/

በውሸት ፋብሪካው የተቃጠለው ጊዮርጊስ ደግሞ እዩ :-

http://www.awrambatimes.com/?p=1319

እኛ እዚህ ያለነው ወያኔዎችና እንዲሁም ሀቅ እንዲዘገብ የሚፈልጉ ነፃሰዎች አላማችን ውሸት ማን ይበለው ማን እርቃኑ እንዲወጣ ማጋለጥ ነው እንጂ ከፊውዶ ደብተራና ፋሺስት ስርአት ቅሪቶች እንካስላንቲያ መባባል አይደለም :: ውሸትን የምናጋልጠው ደግሞ የዋህ ወገን እውነት መስሎት እንዳይወናበድ እንጂ ውሸታሞችን ለማረም አይደለም - አውቆ የተኛን መቀስቀስ ስለሚሆን :: እነሱ ጋር የሽብር ወይም የፍልሚያ ቦታ ስለምንገናኝ ችግር የለውም ::

ስልኪ
ወዲ መስመር
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
የዘመኑ ልሳን

ዋና አለቃ

Joined: 07 Jun 2005
Posts: 2930
Location: USA

PostPosted: Fri Jun 08, 2012 4:29 pm    Post subject: Reply with quote

እንዴት ነው ነገሩ በኢትዮጵያውያን መኃል plagiarism የሚባል ነገር የለም እንዴ Question Question Question Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes Rolling Eyes አራንባው ታይምስ ቤተ ክርስቲያኑ ተቃጠለ እና ምዕመናኑ እርስበርስ ተጋጩ የሚለውን ከመጨመሩ በስተቀር ሌላውን የዜናውን ጽሁፍ ቃል በቃል የወሰደው ከደጀ ሰላም ዘገባ ላይ ነው ::

ለደጀ ሰላም acknowledge ሳያደርግ ከወሰደው በስተቀር ሌላው ያልተጣራ ነገር ነው :: በተለይ ምዕመኑ እርስ በርሳቸው ተጋጩ የሚለው የግጭቱን ሁኔታ ያላጣራ ሰው እንደጻፈው ያሳብቃል ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ክቡራን

ዋና አለቃ

Joined: 04 Mar 2008
Posts: 5066

PostPosted: Fri Jun 08, 2012 7:14 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ወዲ መስመርና የዘመኑ :-
አዎ ስፐድ ስፔድ ማለት መቻል አለብን :: ለመነብብ , ስም ለማግኘት ከዛም አልፎ ጭር ሲል አልወድም በሚል ጋዜጠኛ አይኮንም :: ጋዜጠኝነት እውነትን ይዞ በውነት በራሪ መብረር ነው :: መሬት ላይ ያለችዋን እውነታ እየነቀስን እናወጣለን ...ይሄ እውነት ደሞ ከግድግዳ ጋር ያላተማቸውና ወደፊትም በተከታታይ የሚያላትማቸው የዋርካ አጁዛዎች ሀቁን ከመጋፈጥ ይልቅ ጨለማ ውስጥ መታጎርን መረጡ :: ለኛ የምናየውን እውነት ያለ ከልካይ እንድንመሰክር መንገዱን አጸዱልን :: የኢትዮጵያ አምላክ ምን ይሳነዋል ..?? ሰላም ሁኑልኝ Very Happy

_________________
http://www.ethiopianthisweek.com
http://www.ethioonutube.com
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Visit poster's website Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ All times are GMT + 1 Hour
Page 1 of 1

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia