WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
***አርሰናልን ያላችሁ እስኪ እንያችሁ ***
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 64, 65, 66 ... 118, 119, 120  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

View previous topic :: View next topic  
Author Message
አንበርብር

ውሃ አጠጪ

Joined: 09 Apr 2005
Posts: 1090
Location: everywhere

PostPosted: Fri Nov 09, 2007 12:55 am    Post subject: Reply with quote

ልጀ የትም ንቅንቅ አይልም አሉ የቤንዴር አባት ቶማስ :: በርሚንግሀምን ወደ ሊጉ ጎትቶ ያመጣው ቤንደር አምና ባሰለፈው ውሰት ለበርሚንግሀም 13 ጎሎችን መረብ ላይ ያሳረፈ ሲሆን አሁንም ለኔ ይገባኛል በማለት የክለቡ አሰልጣኝ ብሩስ የቪንገርን በር ጠዋት ማታ ማንኳኳቱን ቀጥለውበታል :: ይህንን የተመለክቱ የልጁ አባት ቶማስ ደግሞ ልጀ ከጋነር ውጭ የትም አይሄድም ቪንገርም በሩን ለማንም መክፈት የለባቸውም በማለት እንቅጩን ተናግረዋል :: ኢንተር ሚላን ልጁን በአድሪያኖ ቀይሩን እያሉ ሲወተውቱ እንደነበር እና ቪንገር አድሪያኖ ለጋነር አይገባም በማለት ሲመልሱ ........ ኢንተሮች አሁን ደግሞ በገንዘባችን ቀይሩን ማለታቸውን ቀጥለውበታል :: የልጁ አባት ቶማስ ግን የምንሰማበት ጀሮ የለንም ብለዋል :: ልጀ 19 አመቱ ነው ያለበት አቋምም ጥሩ ነው ስለዚህ ወደፊት ቋሚ ተሰላፊ ለመሆን ጠንክሮ መስራ አለብት እንጅ አርሰናልን መልቀቅ የለበትም ካሉ በኌላ በእርግጥ ልጁ እድልን ማግኘት አለበት አሰልጣኝ ቪንገርም ለልጀ እድል እንደሚሰጡት እርግጠኛ ነኝ በማለት ያላቸውን ተስፋ አጋርተውናል ::

This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መሬውመራራው

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Jun 2007
Posts: 599

PostPosted: Fri Nov 09, 2007 1:01 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ገነርስ .....!
አምብሬ ....ለትንሽ ቀደምከኝ .........! ምን አዲስ ነገር አለ ብዬ ቤታችንን ባይ ባዶ ሆነብኝና ለመጻፍ ስነናዳ ያንተ ጽሁፍ ከች አለ .....!

ፋብሬጋስ ላይ አይኑን ያልጣለ ማን አለ አምብሬ ....? ጌታ ፈርጊም እንደማይሆን ስላወቁ ተይቄ አፌን አላበላሽም ብለው እንጂ ዉስጣቸው ፋብሬጋስ አምጣ አምጣ ይላቸዋል .......!(ስለፈርጊ በዚሁ ላብቃ ......ደሞ እነ እናትዬ እንዳይነሱብኝ ..ሆሆ )

አንበርብር እንደጻፈ(ች)ው:
መሬው :
Quote:
አምብሬ .....በዉጭ ተጫዋቾች መብዛት ላይ እየመጣ ያለው ተቃውሞ ለኔ አይገባኝም .....! ጥሩ ጥሩ ተጫዋቾችን አባራችሁ የደከሙ እንግሊዛዉያንን አስገቡ በቡድናችሁ ዉስጥ ማለት ትክክል አይመስለኝም ....! አዉሮፓ ወደ አንድ ሀገርነት እየተቀየረች ባለበት በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት ህግ ግብዝነት ነው .....! ከአካዳሚ ተመርቀው የሚወጡት የእንግሊዝ ልጆች ፕሪምየር ሊግ ገብተው መጫወት ካቃጣቸው ወደቤልጅየም ....ሆላንድ ....ፈረንሳይ ...ቱርክ እየሄዱ ይጫወት ...ችሎታቸው የሚመጥን ከሆነ ነው እንግዲህ :: ጥሩ ተጫዋቾች ከፈረንሳይ በቀላሉ ማግኘት እየቻልክ ...ከአፍሪካ ማግኘት እየቻልክ ....አንድ የማይረባ የአካዳሚ እንግሊዛዊ ተመራቂ ሚልየን ፓውንድ አፍስሰህ የምትገዛ ከሆነ ...ስህተት ነው ...! የእንግሊዝ ከለቦችም ይህ ህግ ከወጣና ተግባራዊ ከሆነ ....አሁንም ያላቸው የማትረባ የአዉሮፓ ዋንጫ ዉጤታቸው ያሽቆለቁላል ....!

በፈረንሳይ ሊግ ስንቱ ነው ፈረሳዊ ተጫዋች ......? ስንት አፍሪካዊ ተጫዋች ነው የሚጫወተው ..? ግን የብሄራዊ ቡድናቸው ዉጤት እንዴት ነው ...? ለምን የእንግሊዝ ዉጤት እንደነሱ አላማረም ...? ይህን ሁሉ ማየት ያስፈልጋል ...እንደፈርጊ የዉጭ ተጫዋቾች ላይ ከማሳበብ ...! ፈርጊ ተንኮል ከደማቸው ስለሆነ ነው በአርሰናል ነጥብ በጣሉ ማግስት ይህን ነጥብ ያነሱትና ያጨበጨቡት ...!!!! በአጭሩ አምብሬ ....በጣም እቃወማለው ........!!!!!

በእኔ በኩል ስለ ፕላተር እና ሽማግሌው አስተያየት የሩቁን ያልዳሰሰ ሀሳብ እለዋለሁ :: ከሁሉም የሚገርመው ምንም አይነት አስተያየት ሳይሰጥ የቆየው ሽሜው አሁን የጋነር ወጣቶችን የወደፊት ተስፋ አይቶ ይህንን አስተያየት መስጠቱ lack of self-confidence and selfishness ብየዋለሁ :: ምክንያቱም የወጣቶችን የወደፊት ብቃት እና ችሎታ በአይኑ በብረቱ አይቷል እናም ይህ የቪንገር መዋቅር ለወደፊቱ ለሚያሰለጥነው ክለብ ቀንደኛ ተፎካካሪ መሆኑን ሲያረጋግጥ በጭፍኑ ያንን አስተያየት ሰነዘረ :: አንተ እንዳልከው የእንግሊዝ የብሄራዊ ቡድን ውድቀት የውጭ ተጨዎቾች መብዛት አይደለም :: እንግሊዝ ጥሩ ተጨዋቾች አሏት :: እንደውም ባለፈው የአለም ዋንጫ ግዜ ዋንጫውን ይወስዱታል ብየ ካልኳቸው ሀገሮች እንግሊዝ ቀዳሚዋ ነበረች :: ከተከላካይ እስከ አጥቂ ያሉትን ተጨዋቾች አስብ በእርግጥ የሩኒ በጉዳት መቆየት እና የማይክል ኦውን አቋም የአጥቂውን ክፍል ጎድቶታል :: ያም ሆነ ይህ ግን ሁሉም የእንግሊዝ ተጨዋቾች የሚጫወቱት እና የሚከተሉት ስልት አንድ ወጥ ነው :: ሁሉም ሊጉ ውስጥ ናቸው :: ላሊጋ ላይ አታያቸውም ...... ሴሪያ ላይም እንደዚሁ ........ ቡንደስሊጋም ብታስፈልጋቸው ታጣቸዋል ! ፈረንሳይ ውስጥ አይታሰብም ........... እንደውም የእንግሊዝ ክለቦች በሙሉ በውጭ ተጨዋቾች ተሞልተው እንግሊዛውያን ወደ ሌላ ክለቦች መሰደድ አለባቸው :: ከስደት ብዙ ልምዶችን አካብተው መምጣት ይችሉ ነበር :: ከላሊጋ ጥበብን ይማራሉ ከሴሪያ ደግሞ ግፊያን ይቀስማሉ Laughing Laughing ከቡንደስሊጋው ደግሞ ጥለዛን ሰንቀው እንደ ተቃራኒ ቡድን አመጣጥ ስልትን በመቀያየር ውጤትን ማግኘት ይችሉ ነበር :: ጆን ቴሪ : አሽሊ ኮል : ኮል : ራይት ፊሊፕስ : ላምፓርድ አንድ ክለብ ውስጥ ቀን በቀን እየተገናኙ የሚሰለጥኑ ናቸው :: ፈርዲናንድ : ጋሪ ኔቭል : ሀርጋሪቭስ : ሩኒ : ካሪክም እንዲሁ ........ በቃ ምናለፋህ ሁሉም አንድ ቤት ውስጥ ናቸው :: ታዲያ አንድ ላይ እየኖሩ ጥሩ ውጤት ማምጣት ካልቻሉ መንስሄው ምን ይሆናል ትላላችሁ :: መልሱ አንድ ብቻ ነው ! መበታተን !!!! ከዚያ ውጤቱ ምን እንደሚሆን መመልከት :: የብራዚል ብሄራዊ ቡድን ተጨዋቾች ከየት ነው የሚመጡት ? የፈረንሳይስ ? የፓርቱጋል ? የአርጀቲና ? እኔ እንደሚመስለኝ የእንግሊዝ ስፓርት ፌዴሬሽን እያንቀላፋ ይገኛል :: ቀስቅሱት ........

አምብሬ ....ከላይ ባልከው በሙሉ እስማማለው ............! ትክክል ብለሀል .......! በተለይ እንግሊዛዉያን ከአገራቸው ዉጪ ሲጫወቱ እምብዛም አይታዩም ............! ዉጪ ሄድው ለመጫወት የሞከሩትም ሳይሳካላቸው ወንበር አሙቀው ነው ጥለው የሚመለሱት ........! ማይክል ኦወን ፐርፎርማንሱ ድንቅ በተባለለት ጊዜ ወደማድሪድ ሄዶ ወንበር ሲያሞቅ ከርሞ መጣ ....! ሌላው እንግሊዛዊ ጆናታን ዉድጌት የክፍለዘመኑ (ልብ በሉ የአመቱ አይደለም ......የክፍለዘመኑ ) የስፔን worst signing የሚል ትልቅ የስድብ ማእረግ ተሸክሞ በትልቅ ክብር የለቀቃትን ሀገር በትልቅ ሀፍረት ተመለሰባት ............! ዉድጌት እንግሊዞች የት ይደርሳል ብለው የሚጠብቁት የሊድስ ዩናይትድ ተጫዋች የነበረ ሲሆን ማድሪድ ገብቶ በቆየባቸው ጥቂት አመታት በጣም ጥቂት ጨዋታቾች ላይ ተሰልፎ ተጫዉቶ ነው የተመለሰው ....! እርግጥ ጉዳትም ነበረበት ........! ከአገሩ ወጥቶ ትንሽ የተሳካለት እኔ እስከማዉቀው ቤካም በማድሪድና ድሮ ፖል ኢንስ ኢንተርሚላን ናቸው ..............! ሌላ የእንግሊዝ ተጫዋች ካለ ረስቼ ይሆናልና አስታዉሱኝ .............! ሀርግሪቭ በጀርመን ለባየር ሙኒክ ይጫወት ነበር .........! ግን ልጁ ከእንግሊዝ አካዳሚ የወጣ ሳይሆን ከሌላ ቦታ ነው የተገኘው ...! እንግሊዛዊነቱንም የተቀበለው ተለምኖ መሰለኝ ...ቅቅቅቅቅ ....!

ለምን ከአገራቸው ዉጪ አይሳካላቸውም ...? ምክንያቱም ችሎታቸው እምብዛም ስለህነ የሚፈልጋቸው ስለሌለ ..........!!!!!!!!!!!!!!! አካዳሚዎች የሚያስመርቋቸው ተጫዋቾች ከብዙ ጥቂቱ እንጂ የተቀሩት እዚ ግባ የሚባል ብቃት የላቸውም ......! ታድያ ለዚ ድክመት ተጠያቂው አርሰናልና ቬንገር መሆን አለባቸው ...?????????? አካዳሚያቸዉን ይመርምሩ .........! እንግሊዞች በግል ቴክኒክ በኩል ከሌሎች አገራት ጋር ሲነጻጸሩ ትልቅ ድክመት አለባቸው ...........! ስለዚህ ማሰልጠኛቸው ዉስጥ የሚሰጠዉን ትምህርት መቀየርና ማሻሻል እንጂ እንደፈርጊ አርሰናል ላይ ጥፋቱን መደፍደፍ ወንጀል ነው .........!!! ፈርጊ እንደመስቀል ዎፍ አንዴ ብቅ የሚል ችሎታ ያለው ተጫዋች በገንዘባቸው በመግዛት ይሰበስቡና ሌሎቹን ክለቦች አራቁተዉ ሲያበቁ ......በዉጭ ተጫዋች የተሞሉ ናቸው ብለው መናገራቸው ለመፍትሄ ሳይሆን ለዉንጀላና ተቀናቃኝን ለማዳከም አስበው ብቻ ነው .......!!!! ይቅርታ ማንዩዎች .......ይህን ሼባ ፈርጊ ድሮም ጀምሮ በጣም ነው የምጠላው ........!!!! አፉ ትልቅ ነው .....!!!!!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አንበርብር

ውሃ አጠጪ

Joined: 09 Apr 2005
Posts: 1090
Location: everywhere

PostPosted: Fri Nov 09, 2007 1:08 am    Post subject: Reply with quote

አርሰናሎች ከፈለጉኝ ሬሳየ ከኢምሬትስ ይውጣ እንጅ የትም አልሄድም በማለት ደስተኛ ያልሆነው ጅልበርቶ ሲሊቫ ተናገረ :: ሲዝኑ ከተጀመረ ወንበርን ማሞቅ የተላመደው ጅልበርቶ ምንም እንኳ ያለሁበት ሁኔታ የማይስደስት ቢሆንም አርሰናሎች የሚፈልጉኝ ከሆን አሁንም ኩንትራቴን ለማደስ ፈቃደኛ ነኝ በማለት ታማኝነቱን ገልፆል :: ጁቬንትስ በጃንዋሪው ዝውውር ተጨዋቹን ለሞሞትለፍ ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ጅልበርቶ ቢረዳም እኔ ግን ማድረግ ያለብኝ ተረጋግቶ መቆየት እና ቦታየን መልሸ ለመረከብ ጠንክሬ መስራት ነው በማለት በሳል አስተያየቱን ሰጥቷል :: እውነት ነው ለብራዚል ብሄራዊ ቡድን የምትጫወት ከሆነ ክለብህ ውስጥ ሁሌም መጫወት ይኖርብሀል ካልሆነ ግን ለብራዚል የመሰለፉ እድል እንደ ክር ይቀጥንብሀል ካለ በኌላ እስኪ ሁሉንም ወደፊት የምናየው ይሆናል በማለት ነገን እየጠበቀ ይገኛል :: ጅልበርቶ ጋነርን የተቀላቀለው 2002 ሲሆን ቪንገር ልጁን ለማምጣት 16M ፓውንድ ሳይሆን 4.5M ፓውንድ ብቻ ነበር ያወጡት :: የሲሊቫ ኩንትራት የሚያልቀው 18 ወራት በኌላ ነው ::

This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መሬውመራራው

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Jun 2007
Posts: 599

PostPosted: Fri Nov 09, 2007 1:44 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ገነርስ .......................!

ሰኞ ሪዲንግን እንደምናስተናግድና እንደምናሸንፈው ከተናገርኩኝ ቆየሁ ..................! ግን የሪዲንግ ልጆች አርሰናልን ነጥብ ለማስጣል እየተዘጋጁ ነው ..........! ትንንሽ ቡድኖች በተለይ ያልተሸነፈ ቡድን አሸንፈው ትልቅ ዜና ለመፍጠር ስለሚፈልጉ ጨዋታቸው ከባድ ይሆናል .........!ልክ የዋንጫ ጨዋታ የሚጫወቱ ነው የሚመስሉት .............! አርሰናልም አርሰናል ነው ...! .....አይደናበሩም ..........አይፈሩም .............ሰከንድ ቢቀርም ግብ ከማግባት ወደኋላ አይሉም ...........!!!!!! አሳይተው ..ልብ ሰቅለው ..አስጎምጅተው ሲያበቁ በመጨረሻ ይቀሟቸዋል ......! ተንኮለኞች ..! Laughing ምሳሌ መጥቀስ አለብኝ እንዴ ሰዎች ....????

ሪዲንግ ካልፈው ጨዋታቸው ወዲህ ስለአርሰናል ማሰብ ጀምረው ተጫዋቾቻቸው በክለቡ ድህረገጽ ላይ ቀርብው የመሰላቸዉን ሲናገሩ ነበር ....! ያው ዞሮ ዞሮ እንደተለመደው አርሰናልን እንዴት እንደሚያስቆሙት ነው የሚናገሩት ....!!!!እንኳን እነሱ ሌሎቹም አልቻሉ ....ቅቅቅቅቅ !!!!!!

አንድ የሚገርም ነገር በሪዲንግ ዌብሳይት ላይ ተጽፎ አይቼ ዋሬዎች .... (የዋርካ አምባብያን ለማለት ነው ....!ታስኬዳለች ...????).....መስማት አለባቸው ብዬ ተሽቀዳድሜ መጣው .....! እሽቅድምድሙን ምን አመጣው ? አላችሁኝ ...? ካላችሁኝ እሺ ልንገራችው .....!እነ እናትዬ አንድ የአርሰናል ዜና ወይ ጽፈው በድንብ አይጽፉት ወይ ለኛ አይተዉልን ብቻ ቁምጥምጥ አድርገው ባጭሩ ያስቀምጧትና ....እነአምበርብር ምን ይጽፋሉ አሁን ... እያሉ እንዳይላጡብን ብዬ ነው የተሽቀዳደምኩት .....! ዜናዉን እንደነበርና አሳምረን ለማቅረብ ስንሞክር ....ሌላ ቤት የተጻፈ ዜና ለምን ትደግማላችሁ ...? የቆየ ዜና እያመጣችሁ አታሰልቹን ....! እያሉ መልሰው ልባችንን ያወልቁታል ......! አርሰናላዉያን ደሞ ለሚያነበው ሰው ሀላፊነት አለብን ....አይደል እንዴ ገነርስ ...!!!?? ዜና አናጣምም ....አንዋሽ ....! እንደነበረች ቁጭ ቁጭ ማድረግ ነው የለመድነው ...!!!!!! (እለፉኝ ማንዩዎች ....)

ዘላበድክ ሳልባል ወደሚገርመው የሪዲንግ ዜና ልምራችሁ ........! ኢብራሂም ሶንኮ የተባለ የሪዲንግ ተጫዋች ታዉቃላችሁ ...? አዎ ሴኔጋላዊ ነው .....! ስለአርሰናል ጨዋታ አስተያየት ከሰጡት መሀል አንዱ እሱ ነው ...! እኔም በሱ ላይ ነው የማተኩረው ....! የኛን ..'የጅብ ጥላ ' ሳኛን አሁን የማያዉቀው ያለ አይመስለኝም ...! ሳኛ እና ሶንኮ የትዉልድ አካባቢያቸው አንድ ነው ...ሴኔጋል ዉስጥ ....! ሳኛ በልጅነቱ መሰለኝ ወደፈረንሳይ ከቤተሰቡ ጋር የሄደው ....!

ሳኛ ትልቅ ደረጃ ደርሶ ፈረንሳይ ከለብ ሲጫወት ሶንኮ በወሬ ደረጃ ጭምጭምታ ይሰማ ነበር .....! ሶንኮ ሪዲንግ ገብቶ እየተጫወተ እያለ ነው ሳኛ ለአርሰናል የፈረመዉ .........! የሶንኮ እናት ሳኛ የሚባል ልጅ እንግሊዝ አገር ይጫወታል ብላ ለሶንኮ ሲትነግረው .....ሶንኮ የሚያስበው ሌላ ሳኛ የሚባል ዘመዱ ከጥቂት ጊዜ በፊት ባርኔት ለሚባል ክለብ ለሙከራ መጥቶ ነበርና እሱ ነው ትዝ የሚለው ....! እኔም እንደገባኝ ሶንኮ እናቱን አጥብቆ አልጠየቀም .....! በዚህ መሀል የሪዲንግና የአርስናል ጨዋታ ቀርቦ ከሳምንት በታች ቀናት ሲቀረው የሶንኮ ወንድም ደዉሎ እንደገና የሳኛን ስም ያነሳበታል .........! ሶንኮም ነገሩ ግራ ይገባዋል .....! የሶንኮ ወንድም ሳኛ cousinናችን ነው ይለዋል ....! ደንባራው ሶንኮ አሁንም የሚያስበው ባርኔት ልምምድ ላይ ያለዉን ዘመዱ ሳኛን እንጂ የአርሰናሉን ሳኛ አልነበረም .....! ትንሽ ከተመላለሱ በኋላ ግን ፍንትው ብሎ ተገለጸለት .............! የአርሰናሉ ሳኛ በጣም የቅርብ ዘመዱ እንደሆነ ተገለጸለት .........! ከበፊት ጀምሮ እናትዬው የምትነግረው ስለአርሰናሉ ሳኛ ነበር ....! የሚገርመው የሶንኮ ወንድም ከባካሪ ሳኛ ጋር ይተዋወቃሉ ....! ግን ሶንኮና ሳኛ ግን አይተዋወቁም .....! ሶንኮም ባካሪ ሳኛ የሱ ዘመድ መሆኑን በዚህ ሳምንት ነው ያወቀው ........! ሰኞ ቀን ሜዳ ላይ በደንብ ይተዋወቃሉ ............! አይገርም .....!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መሬውመራራው

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Jun 2007
Posts: 599

PostPosted: Fri Nov 09, 2007 2:26 am    Post subject: Reply with quote

እሺ ገነርስ ..............!

ከላይ ታሪኩን የነገርኳችው ኢብራሂም ሶንኮ ለአርሰናል ጨዋታ የሚዘጋጅባቸው መንገዶች በጣም የተለዩ ሆኑብኝና እንደገና ስለሱ ልጽፍ ተነሳሁ ................! ዳንኤል ቦካንዴ የሚባል ተጫዋች ባለፈው አመት ሪዲንግ ለመግባት ሙከራ ላይ ነበር ..........! አሁን ቡድኑ ዉስጥ ስለሌለ የሙከራው ጊዜ ጥሩ እንዳልነበር መገመት ይቻላል ..........! ዳንኤል ሶንኮ cousin ነው ...ቅቅቅቅቅ ! ዘመዶቹ በሙሉ ኳስ ተጫዋቾች ናቸው መሰል ....! Laughing ቦካንዴ ፈረንሳይ ዉስጥ በሜትዝ Metz ክለብ .......(ወሮ ...አጻጻፉን ልክ ነኝ ...? እንደ le'equipe??? Laughing).... እያለ አብሮት አደባዮ ይጫወት ነበር ..............! ዳንኤል ሶንኮ የአደባዮን ሚስጥሮች እያጋራው ነው ....! በተለይ አደባዮን እንዴት ማስቆም እንደሚችል .....ጠንካራ ጎኑ ምን እንደሆነ ....ድክመቱ ምን እንደሆነ ሁሉ በዝርዝር ለሶንኮ ነግሮታል ............!

በተለይ አደባዮ እንደቁመቱ ሳይሆን ከኳስ ጋና ያለኳስ በጣም ፈጣን እንደሆነ ለሶንኮ ተነግሮታል .....! ይህ የሶንኮ ዘመድና የአደባዮ የቀድሞ የቡድን አባል መፍትሄዉንም ሲናገር ........አደባዮርን ማስቆምያው ያለው ብቸኛ አማራጭ መምታት (መጣረብ ) ነው ...ብሎ ወንድማዊና አፍሪካዊ ምክር መክሮታል ...!!!!! ዳንኤል ሲቀጥል ...አደባዬ በጨዋታ ላይ እያለ ፈገግታ የሚያሳይ ከሆነ ...ያኔ በደንብ እየተጫወተ ነው ማለት ነው ብሏል ....ቅቅቅቅ Laughing Laughing ! ሶንኮም የአደባዮን ፈገግታ ከፊቱ ላይ ብቻ ሳይሆን ከምድረገጽ ለማጥፋት እንደሚገባ ነው የሚጠበቀው ............!

ሰው የቅርብ ዘመዱን ...ያዉም ተዋቂ የሆነን እንዴት ሊረሳ እንደሚችል አይገባኝም .....!!! አንድ ሀበሻ እንኳን አርሰናል የመን አገር ሄዶ ሲጫወት እንኳን ዘመዱ ይቅርና ድፍን ሀበሻ ያዉቀዋል .....እነሱ ግን የቀረበ ዝምድና ኖሯቸው ያዉም አርሰናልን የሚያክል ቡድን ዉስጥ እየተጫወተ አንዱ አዱን አያዉቅም ....! Surprised Surprised Surprised Surprised Surprised
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አንበርብር

ውሃ አጠጪ

Joined: 09 Apr 2005
Posts: 1090
Location: everywhere

PostPosted: Fri Nov 09, 2007 2:46 am    Post subject: Reply with quote

Quote:
ሰው የቅርብ ዘመዱን ...ያዉም ተዋቂ የሆነን እንዴት ሊረሳ እንደሚችል አይገባኝም .....!!! አንድ ሀበሻ እንኳን አርሰናል የመን አገር ሄዶ ሲጫወት እንኳን ዘመዱ ይቅርና ድፍን ሀበሻ ያዉቀዋል .....እነሱ ግን የቀረበ ዝምድና ኖሯቸው ያዉም አርሰናልን የሚያክል ቡድን ዉስጥ እየተጫወተ አንዱ አዱን አያዉቅም ....! Surprised Surprised Surprised Surprised Surprised

መሬው ጥሩ ታሪክ ነው :: አንዱ አንዱን ዘመዱን አለማወቁ አይግረምህ ............. የማንቸስተሩ ኢቭራ ስንት ወንድም እና እህቶች እንዳሉት ታውቃለህ አይደል ?? አንድ ደርዘን ተኩል የሚጠጉ ወደ 16 አካባቢ መሰሉኝ :: እናም እነዚህም ዘረ ብዙዎች ናቸው ማለት ነው ...... ቅቅቅቅቅ ማሽ አላህ ይላል አረብ Laughing Laughing እናትየን አረበኛ እንደምችል ለማስረዳት ነው Laughing Laughing

መሬው አደባዮ አሁን ያለበት አቋም ለእኔ ምንም አልጣመኝም ....... ባለፈው በዳርቢ ሀትሪክ መስራቱ መመዘኛ አይሆንም ..... በተለይ እንደ ቁመታምነቱ በእራስ ገጭቶ ያስቆጠራቸው ጎሎችን መፈለግ አቅቶኛል ......... በእርግጥ በተከላካይ ላይ ከፍተኛ ጫናን የመፍጠር ብቃት አለው ሆኖም ግን ጨዋታ የመለወጥ ኳሊቲ የለውም ..... ቪንገር ቤንደርን እንደ አደባዮ እድል ቢሰጡት መልካም ነበር ........... ቫንፐርሲም መመለሻው ደርሷል ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አንበርብር

ውሃ አጠጪ

Joined: 09 Apr 2005
Posts: 1090
Location: everywhere

PostPosted: Fri Nov 09, 2007 3:48 am    Post subject: Reply with quote

Reading V Arsenal

መጣሁ !!!!!!! ቁጭ በሉ አይገባም !!!!! አዎ ለግንዛቤ ያህል .... አርሰናል እና ሪዲንግ እስካሁን በታሪክ ያደረጓቸው ጨዋታዎች 70 አይደሉም ...... 10 አይሞሉም ....... ሰኞ Madejski Stadium ሲገናኙ 8 ግዜ ይሆናቸዋል :: ሪዲንግ እና ጋነር ለመጀመሪያ ግዜ የተገናኙት ሁለተኛው የአለም ጦርነት ከመጀመሩ ቀደም ብሎ ነበር :: የተገናኙት FA ካፕ ሲሆን ትህክለኛ ግዜውም 1934 ነበር :: ጋነር በዚህ ጨዋታ 1-0 አሸንፎ ጨዋታውን ሲያጠናቅቅ ከዚህ ድል በኌላ ሪዲንግ እንኳን አርሰናልን ሊያሸንፍ እኩል መውጣት እንኳ እንቢ ብሎት እነሆ ዘመናት ተቆጥረው ሰኞ ላይ ደረሱ :: ጋነር ከሪዲንግ ጋር ያደረጋቸውን 7ቱን ጨዋታዎች በማሸነፍ ሲያጠናቅቅ በአምናው ፕሪምየር ሊግ ጋነር በእንግድነት ተቀብለው 2-1 ቸብ አድርገው ሲሸኟቸው ወደሜዳቸው ተጉዘው 4-0 አቅመዋቸው :: ዘንድሮስ ?ቲዎ ውልኮት የጥሪ ወረቀት ደረሰው :: ጥሪውን የተቀበለው Stuart Pearce ሲሆን የተጋበዘበት ቀንም ኖቬምበር 16 ነው :: 21 እድሜ በታች ያሉት እንግሊዛውያን ቡልጋሪያን ለአውሮፓ ሻምፒወን ማጣሪያ በዚሁ ቀን ከተጋፈጡ በኌላ ከአራት ቀን በኌላ ደግሞ ፓርቱጋልን ይፈትናሉ :: ኢንግላንድ እስካሁን ያደረገቻቸውን አራት ጨዋታዎች በማሸነፍ ምድቡን ስትመራ ቲዎ ውልኮት የአጥቂውን መስመር እንዲመራ ከአሰልጣኙ ትእዛዙን ተቀብሏል :: አጣብቂኝ ውስጥ ለገባው ለእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ውልኮት ሊካተት ይችል ይሆናል የሚል ጭምጭምታ ቢሰማም ማክላረን ግን ጀሮ ዳባ ልበስ ብለው አልፈውታል :: ውልኮት ባለፈው በስላቪያ ያገባቸው ሁለት የቻምፒወን ጎሎች በሩኒ የተያዘውን የእድሜ ሪከርድ ሊቀሙ ችለዋል :: ሩኒ እና ውልኮት የሪከድ ርክክቡን ባለፈው አከናውነዋል ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መሬውመራራው

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Jun 2007
Posts: 599

PostPosted: Fri Nov 09, 2007 4:02 am    Post subject: Reply with quote

አምብሬ ....... የአደባዮ አቋም ብዙም የተለወጠ አይመስለኝም ...በኔ እይታ ...! ግን ጌታ ቬንገር እንዳሉት ለብቻው ተነጥሎ መቅረቱ በተለይ በማንዩ ጨዋታ ላይ ትንሽ ጨዋታዉን አበላሽቶበታል ....!ምክንያቱም ከፊት አጋዡ የነበረው ህሌብ ሲሆን እሱም ከኋላው ሆኖ ነበር ሲጫወት የነበረው .....! እንዳልከው እንደቁመቱ የጭንቅላት ምቱ የተስተካከለ አይደለም .....! ብዙ ሲስት ነው የሚታየው ...! እንደኔ አመለካከት አደባዮ ኤፊሸንሲ ነው የሚያንሰው ...........! ወደፊት ቫንፒርሲ ሲመለስ ሸክሙን ቀለል ስለሚያደርግለት ለዉጥ ይኖረዋል እላለው .....! ከዚህ በላይ ትንተና ለዋርካስተሮች ትቻለው ........!! ሪዲንግ ላይ ስንት የምናገባ ይመስልሀል ....አምብሬ ? ይህ ቡድን ባለፈው 7 የገባበት እንደመሆኑ እኛ 9 አናገባባቸዉም ትላለህ ? Wink
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Monica****

ዋና አለቃ

Joined: 26 Dec 2003
Posts: 3937
Location: 999 Total eclipse st. Venus

PostPosted: Fri Nov 09, 2007 4:17 am    Post subject: Reply with quote

ለምወዳችሁና ለምትወዱኝ , ለማውቃችሁና ለምታውቁኝ , ለማላውቃችሁና ለማታውቁኝ ሁሉ ስላምታዬ በስፊው ይድረሳችሁ
አንቤ የኔ ቆንጆ መሬው ማዊትዬ እና የአርስናል ወዳጆች ሁሉ እንደምናችሁ ?
እንደው ናፍቆቴን ለመወጣት ነው ብቅ ያልኩት እናንተ ስው ሲጠፋ እንክዋን ፍለጋ አትሄዱም ???? Laughing Laughing Laughing
ዋርካ ስፖርት ውስጥ ግርም ያለኝ ኢትዮጵያዊ የሀመርስ ደጋፊውን ዌስት ሀምን ማየቴ ነው ! ቅድም ጽፌለት ዋርካ በላብኝና ተስፋ ቆርጨ ተውኩት Shocked Shocked እኔ እንደው በጭፍኑ ልክ እንደ Millwall የሆኑ ሬሲስት ነገሮች ስለሚመስሉኝ ጨዋታችውን እንክዋን ብዙ አላየውም .......እንደውም አውት ኦፍ ቦርደም እሁድለት ከቦልተን ጋር ሲጫወቱ ሙሉውን ጨዋታ መመልከቴ እኔንም ሲገርመኝ ነው የመሽው !!!!!ደሞ እኮ ለነገሩ እኔም ኢስት ነዋሪ ስለሆንኩኝ ቅርቤ ናችው .........ኖርዝ ለንደን ድረስ መንገድ ከማረዝም ከዌስትሀም ጋር ልዛመድ ይሆን ? Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing ግን ዌስትሀምን ከምደግፍ ማንዩናይትድን ኤኒዴይ ይሻለኛል .......!!
በተረፈ የምወዳችሁ ገነርሶች እረ አትጥፉ ! ስጠፋም አድራሻዬ እንደሚከተለው ነው
ኤምሬት ስቴዲየም ስልክ ቁጥር 020 7999 **** የቀረው እንደክሬዲት ካርድ ፔይመንት በስታሮች ይደበቅ ለሴኪዩሪቲ ኢሹ Razz
መልካም ቀን
ገነርስ ፎርኤቨር !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መሬውመራራው

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Jun 2007
Posts: 599

PostPosted: Fri Nov 09, 2007 4:35 am    Post subject: Reply with quote

አምብሬ ........! የፕሪምየር ሊግ ቡድኖች በአለም ላይ ተወዳጅ እንደመሆናቸው መጠን ከዚህ ተወዳጅነት ለማትረፍ ሩጫ ከጀመሩ ቆዩ .........! በተለይ እንደ ቻይና እንደ ታይላንድና ኢንዶኔሽያ የመሳስሉ አገራት የፕሪምየር ሊግ ተወዳጅነት ትልቅ ስለሆነ ክለቦች እነዚህን ደጋፊዎች ለመሳብ አንድም እዛው አገር በመሄድ የወዳጅነት ጨዋታ ሲያደርጉ አንዳንዶቹ በቋንቋቸው ዌብሳይት ከፍተውላቸው እንቅስቃሴ ሲያደጉ ይታያሉ .....! ባለፈው ሰሞን አርሰናል አዲስ ለቻይናውያን ብቻ የሚሆን ዌብሳይት መክፈቱ ይታወሳል ....! እኔ እስከማዉቀው አርሰናል የቻይናዉን ጨምሮ በታይላንድና በኮርያ ቋንቋዎች ዌብሳይት አለው ......! ከሁሉም ለየት ያለው ግን ቼልሲ ዛሬ የከፈተው ዌብሳይት ነው .........! ዌብሳይቱ በተለየ ቋንቋ ሳይሆን በእንግሊዝኛ ነው .........! አላማው ማንን ለማግኘት ነው ....? የአሜሪካ አንባብያንን ..........! ከታች የምታዩት የቼልሲ ዌብሳይት ዛሬ ተከፍቶ የጀመረ ሲሆን ደመቅመቅ ያለ ነገር ለሚወዱ አሜሪካዉያን እንደሆነ ባይናገሩም ያስታዉቅ ነበር .............! በተለይ እንደምታዩትር በቀይ በነጭና በሰማያዊ ቀለማት ያሸበረቀ ነው .....!ግን በቼልሲ ማልያ ላይ ቀይ የሚባል ቀለም እንደሌለ ይታወቃል .....! አላማው ...የአሜሪካንን ባንዲራ ቀለም በማስመሰል ....አንጀታቸዉን ለመብላት የታሰበ ነው .....! ማንዩዎች ተቀደማችሁ ......!

This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መሬውመራራው

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Jun 2007
Posts: 599

PostPosted: Fri Nov 09, 2007 5:11 am    Post subject: Reply with quote

ሞኒካ ......! እንክዋን ደህና መጣሽልን .....!!!!!!!!!!!! ምነው እንደው ጭልጥ ብለሽ ጠፋሽብን ...?? ዌስትሀምም ቤት አለው ...ሞኒክ ...! አትገረሚ ...! ምነው ሞኒክ ዌስትሀምን እንደፍየል ቆዳ ወጥረሽ ያዝሽው ...???? ሬሲስት ናቸው ያልሽዉን ብታብራሪልኝ ጠላትነቴን በብዙ ትጨምሪልኛለሽ ....! ከዛ ከልጅ ዌስትሀም ጋር እዳትና ጭድ እንሆናለን ....! እኔነኝ ግን እሳት ....! Laughing
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አንበርብር

ውሃ አጠጪ

Joined: 09 Apr 2005
Posts: 1090
Location: everywhere

PostPosted: Fri Nov 09, 2007 8:38 am    Post subject: Reply with quote

Monica**** እንደጻፈ(ች)ው:
ለምወዳችሁና ለምትወዱኝ , ለማውቃችሁና ለምታውቁኝ , ለማላውቃችሁና ለማታውቁኝ ሁሉ ስላምታዬ በስፊው ይድረሳችሁ
አንቤ የኔ ቆንጆ መሬው ማዊትዬ እና የአርስናል ወዳጆች ሁሉ እንደምናችሁ ?
እንደው ናፍቆቴን ለመወጣት ነው ብቅ ያልኩት እናንተ ስው ሲጠፋ እንክዋን ፍለጋ አትሄዱም ???? Laughing Laughing Laughing
ዋርካ ስፖርት ውስጥ ግርም ያለኝ ኢትዮጵያዊ የሀመርስ ደጋፊውን ዌስት ሀምን ማየቴ ነው ! ቅድም ጽፌለት ዋርካ በላብኝና ተስፋ ቆርጨ ተውኩት Shocked Shocked እኔ እንደው በጭፍኑ ልክ እንደ Millwall የሆኑ ሬሲስት ነገሮች ስለሚመስሉኝ ጨዋታችውን እንክዋን ብዙ አላየውም .......እንደውም አውት ኦፍ ቦርደም እሁድለት ከቦልተን ጋር ሲጫወቱ ሙሉውን ጨዋታ መመልከቴ እኔንም ሲገርመኝ ነው የመሽው !!!!!ደሞ እኮ ለነገሩ እኔም ኢስት ነዋሪ ስለሆንኩኝ ቅርቤ ናችው .........ኖርዝ ለንደን ድረስ መንገድ ከማረዝም ከዌስትሀም ጋር ልዛመድ ይሆን ? Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing ግን ዌስትሀምን ከምደግፍ ማንዩናይትድን ኤኒዴይ ይሻለኛል .......!!
በተረፈ የምወዳችሁ ገነርሶች እረ አትጥፉ ! ስጠፋም አድራሻዬ እንደሚከተለው ነው
ኤምሬት ስቴዲየም ስልክ ቁጥር 020 7999 **** የቀረው እንደክሬዲት ካርድ ፔይመንት በስታሮች ይደበቅ ለሴኪዩሪቲ ኢሹ Razz
መልካም ቀን
ገነርስ ፎርኤቨር !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

አይ ሞኒካ ቅቅቅቅ መጣሽ ? እኛማ ፈልገን ፈልገን በቃ ተስፋ ቆርጠን ተቀምጠን ነበር :: ቡና ቤትሽን ጫረታ እንዳወጣሽው ሁሉ ተመለከትን !!!! ባለፈው ከስላቪያው ጨዋታ በኌላ ጋነሮችን ቡና ልጋብዛቸው ፈልጌ ሞኒካ ከለለች ሁሉ ነገር አይጥምም ብየ ለሌላ ግዜ ቀጠርኳቸው ....... በይ ስትጠፊ አያምርብሽም !! Laughing Laughing ማዊት ሞኒካ ሞኒካ ብላ ስትጮህ እንኳን በምድር ያሉት በሰማይ ያሉት ይሰሙ ነበር :: ሳጋንነው Laughing Laughing እንኳን ደህና መጣሽ ብለናል !!!!!!!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አንበርብር

ውሃ አጠጪ

Joined: 09 Apr 2005
Posts: 1090
Location: everywhere

PostPosted: Fri Nov 09, 2007 9:19 am    Post subject: Reply with quoteየአሜሪካው ሎሳንጀለስ ጋላክሲ ሩድ ጉሌትን የክለቡ አሰልጣኝ አደረገ :: የቀድሞው እና ታዋቂው የአምስተርዳሙ ተወላጅ ሩድ ጉሌት ለሶስት አመት የሚያቆየውን ስምምነት ፈርሟል :: ከችሎታው በላይ ስሙ የገነነውን ዴቪድ ቤካምን በመልቲ ሚሊየን ዶላር ያስፈረመው ይኸው የጋላክሲ ክለብ አሁንም ደጋፊን ለመሳብ ሲል ይህንን ታዋቂ ተጨዋች አሰልጣኙ አድርጎ ማስፈረሙ የአሜሪካን ህዝብ ወደ እግር ኳስ ለመመለስ የታቀደ አላማ እንደሆነ ግልፅ ነው :: አራት ግዜ የሆላንድ ምርጥ ተጨዋች ...... ሁለት ግዜ የአለማችን ምርጥ ተጨዋች እና አንድ ግዜ የአውሮፓ ምርጥ ተጨዋች በመሆን የኳስ ዘመኑን የጨረሰው ሩድ ጉሌት ቸልሲን : ኒውካስል ዩናይትድን እና ሀገሩን ክለብ ፌይኖርድ ሮተርዳምን ከዚህ በፊት አሰልጥኗል ::

የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ዶሞኒች ቴሬዝጌን ከቡድኔ አልቀላቅለውም አሉ :: 24 ተጨዋቾችን ከሞሮኮ ጋር ለሚያደርጉት የወዳጅነት ጨዋታ የሰበሰቡት ዶሚኒች ቴሬዝጌን በአፍንጫ ይውጣ በማለት ዘጭ አድርገውታል :: ቴሬዝጌ ሴሪያውን በኮከብ ግብ አግቢነት የሚመራ ሲሆን በቅርብ ግዜ ሁለቴ ለጁቬንትስ ሀትሪክ ቢሰራም ምንም አልተማረኩበትም ብለዋል :: ፈረንሳይ ህዳር 21 ቀን ወሳኝ የሆነውን የአውሮፓ ዋንጫ ማጣሪያ ከዩክሬን ጋር የምታደርግ ሲሆን የማንቸስተሩን ሉዪስ ሰሀን እና ቴሬዝጌን አላካትትም ብለዋል :: የፈረንሳይን የአጥቂ መስመር ቲየሪ ኦንሪ : ኒኮላስ አኔልካ እንደሚመሩትም ይታወቃል ::

ኢላማዋን የሳተችው እና የፈረንሳይ ደጋፊን ያስለቀሰችው ምት ::

ኤሲ ሚላን አይናችንን ሰርጅኦ ራሞስ ላይ ተክለናል ይላሉ :: በሴሪያው ምድብ 9 ላይ ጉብ ያለው ሚላን ራሞስን የግላችን ማድረግ እንፈልጋለን ሲሉ ሪያል ማድሪድም ተስፋ ባለመቁረጥ ካካ ወደ ማድሪድ የሚያቀና ከሆኑ ስምምነት ሊደረስ ይችላል በማለት ሚዲያዎች የመሰላቸውን አስተያየት ሰጥተዋል :: ሰርጆ ራሞስ ሴቪላን ለቆ ማድሪድ ከተቀላቀለ በኌላ ለክለቡ ያበረከተው ጥቅም እንደ ጤፍ ተቆጥሮ እንደማያልቅ ሁሉም ይመሰክራል ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አንበርብር

ውሃ አጠጪ

Joined: 09 Apr 2005
Posts: 1090
Location: everywhere

PostPosted: Fri Nov 09, 2007 10:19 am    Post subject: Reply with quote

ዛሬ ደግሞ አንቤው ሀብታም ፍለጋ ሄዷል Laughing Laughing ፈተሽ ፈተሽ ሳደርግ የሀብታሞችን ስም እንደዚህ አገኘሁት ........ ሀብትነቱ በንግድ ሳይሆን በስፓርት የተገኘ ነው ........ ስፓርትስ ንግድ አይደል ካላችሁ !!! እሽ ይሁን !
Richest Athletes
Name Annual Income
1. Tiger Woods $100 million (እግዞ እግዞ አግበስብሶታል Laughing Laughing )
2. Oscar De La Hoya $43 million (አሜሪካዊ ቦክሰኛ ነው )
3. Phil Mickelson $42 million (አሜሪካዊ ጎልፈር )
4. Kimi Raikkonen $40 million(ፊላንዳዊ ፎርሙላ 1 ድራይቨር )
5. Michael Schumacher $36 million(ጀርመናዊ ፎርሙላ 1 ድራይቨር )
6. David Beckham $33 million(ቅቅቅቅ Laughing Laughing )
7. Kobe Bryant $33 million (ብላክ ማምባ በመባል የሚታወቀው የቅርጫት ኳስ ተጨዋች )
8. Shaquille O'Neal $32 million (ግዙፉ ቅርጫት ኳስ ተጨዋቹ )
9. Ronaldinho $31 million (ጥበበኛው ሱፐር ስታሩ )
10. Michael Jordan $31 million ( የድሮው አንበሳ )
11. Valentino Rossi $30 million ( ጣሊያናዊ ሞተረኛ )
12. Alex Rodriguez $29 million (የቤዝ ቦሉ አለቃ )
13. Roger Federer $29 million( አይበገሬው የቴንሱ ጀግና )
14. Derek Jeter $28 million(የቤዝ ቦል ምክትል አለቃ ቅቅቅቅቅ )
15. LeBron James $27 million (አንበሳው ኪንግ ጀምስ ዳንክ Laughing Laughing )
16. Maria Sharapova $23 million ( ወጣቷ ራሺያዊ የቴኒስ ተጫዋቿ )
17. Michelle Wie $19 million(18 አመቷ ጎልፈኛ እምምምምም )
18. Serena Williams $14 million ( ግብዳዋ ጀግና በቴኒስም ......)
19. Annika Sorenstam $10 million(37 አመቷ ስዊድናዊ ጎልፈኛ
20. Anberber ye warkaw $0.000001 million (የአርሰናል ቀንደኛ ደጋፊ Laughing Laughing )
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አንበርብር

ውሃ አጠጪ

Joined: 09 Apr 2005
Posts: 1090
Location: everywhere

PostPosted: Fri Nov 09, 2007 10:47 am    Post subject: Reply with quote

1.ለሶስት አመት በተከታታይ ምርጥ የአውሮፓ ተጨዋች በመባል የተመረጠ ማነው ? ዜግነቱ ? ሲጫወት የነበረበት ክለብስ ?

2. ብዙ የአውሮፓ ምርጥ ተጨዋቾች በማስባል ያስመረጠ ሀገር ማነው ? ክለብስ ?

3. ምርጥ የአውሮፓ ተጨዋች በመሆን የተመረጡ እንግሊዛውያን ስንት ናቸው ? ጀርመናዊያንስ ?

4. በከፍተኛ የድምፅ ብልጫ ምርጥ የአውሮፓ ተጨዋች በመሆን የተመረጠ ማነው ? መቸ ?ቀድሞ ለመለሰ ሽልማት ይኖረኛል ::
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 64, 65, 66 ... 118, 119, 120  Next
Page 65 of 120

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia