WARKA Forum Index  
 FAQFAQ   SearchSearch   MemberlistMemberlist   UsergroupsUsergroups   RegisterRegister 
 ProfileProfile   Log in to check your private messagesLog in to check your private messages   Log inLog in 

ዋርካ ቻት - በአማርኛ በቀጥታ ይወያዩ! Warka Live Chat | Home (New!) | About us | Contact us
***አርሰናልን ያላችሁ እስኪ እንያችሁ ***
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 66, 67, 68 ... 118, 119, 120  Next
 
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

View previous topic :: View next topic  
Author Message
ዌስትሀም

ኮትኳች

Joined: 31 Oct 2007
Posts: 121

PostPosted: Sat Nov 10, 2007 12:36 pm    Post subject: Reply with quote

Monica**** እንደጻፈ(ች)ው:
ዋርካ ስፖርት ውስጥ ግርም ያለኝ ኢትዮጵያዊ የሀመርስ ደጋፊውን ዌስት ሀምን ማየቴ ነው ! ቅድም ጽፌለት ዋርካ በላብኝና ተስፋ ቆርጨ ተውኩት Shocked Shocked እኔ እንደው በጭፍኑ ልክ እንደ Millwall የሆኑ ሬሲስት ነገሮች ስለሚመስሉኝ ጨዋታችውን እንክዋን ብዙ አላየውም .......እንደውም አውት ኦፍ ቦርደም እሁድለት ከቦልተን ጋር ሲጫወቱ ሙሉውን ጨዋታ መመልከቴ እኔንም ሲገርመኝ ነው የመሽው !!!!!ደሞ እኮ ለነገሩ እኔም ኢስት ነዋሪ ስለሆንኩኝ ቅርቤ ናችው .........ኖርዝ ለንደን ድረስ መንገድ ከማረዝም ከዌስትሀም ጋር ልዛመድ ይሆን ? Laughing Laughing Laughing Laughing Laughing ግን ዌስትሀምን ከምደግፍ ማንዩናይትድን ኤኒዴይ ይሻለኛል .......!!

ሞኒካዬ ምነው አሳይተሽ ትነሺኛለሽ ?
ምንም እንኳ ለንደን ላይ የአርሰናል ደጋፊ ዌስትሀምን
እንደማይደግፍ ባውቅም ዌስት ካለሽ ዝምድናው ይቀርበናል
ለምን ዌስትሀምን አልደገፍሽም አልልም :: እኔም አርሰናልን ስለማልደግፍ :: ይገርምሻል ካንቺ ብቻ አይደለም የሰማሁት ይህን አማርኛ ብዙ የአርሰናል
ደጋፊዎች ዌስትሀምን ከምደግፍ ማን .ዩናይትድን ብደግፍ
ይሻለኛል ይላሉ : እኔም አርሰናልን ከምደግፍ ማን .ዩናይትድን ብደግፍ ይሻለኛል ::

ሞኒካዬ አንቺ ጠፍተሽ ባታላምጂኝም የዋርካ ስፖርቶቹ ሁሉም አቀባበላቸውና እኔን ለማላመድ ያደረጉትን
ጥረት ምስጋና ስላቀርብበት አላልፍም
በደንብ አማርኛ መጻፍ ስችል እንደማንቼና አርሴ ቤት ባለብዙ ገጽና ባለብዙ አንባቢ እሆናለሁ

! ይህችን ብቻ ለመጻፍ 25 ደቂቃ ..ሰነፍ ነኝ
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መሬውመራራው

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Jun 2007
Posts: 599

PostPosted: Sat Nov 10, 2007 5:29 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ገነርስ ................
የዌይን ሩኒ ጉዳት ቢያንስ ለወር እንደሚያርቀው ትላንት በሰበር ዜና አርሰናል ቤት አንብባችኋል ............! የጉዳቱ መንስኤ ምን እንደነበር ግን አረግጠን እናቀርባለን ባልነው መሰረት አሁን ይቀርባል ............! እንደምታዉቁት ማንዩ ዉስጥ እግር የመስበር ሀላፊነት የተሰጣቸውና ተጣራቢዎች ብዙ አሉ ...........! ትላንትም እግር የመስበር ልምምድ ሲሰሩ በስህተት ሩኒን ሰብረዉት ሊሆን ይችላል ተብሎ ተገምቶ ነበር ...ቢያንስ እኔ ገምቼ ነበር ....!!!! እዉነታው ግን ሩኒ የመለማመጃ ሜዳ ላይ ያለች ትንሽዬ የመለማመጃ መሳርያ ከእግሩ ጋር ተተበተብና ትጥለዋለች ............! ሩኒም መሬት ከመንካቱ ቁርጭምጭሚቱን ይዞ ማለቃቀስ ይጀምራል ............! ወድያው እዛው ትንሽዬ ህክምና አድርገዉለት የጉዳቱን መጠን ለማወቅ ስካን ሊደረግ ሄደ .....! የስካን ዉጤት ካዩ በኋላ ቢያንስ ለአንድ ወር የሚያርቀው ጉዳት እንደሆነ መርዶዉን ለደጋፊዎቹ ተናገሩ .....!!!!

የሩኒ ቁርጭምጭሚት የቱ ነው ....???????????? Shocked Shocked
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መሬውመራራው

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Jun 2007
Posts: 599

PostPosted: Sat Nov 10, 2007 5:55 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ሰላም ሰላም .....................ገነርስ .!

የአፍሪካ ክለቦች ሻምፕዮና ትላንት በካይሮ ተደርጎ የቱኒሲያው ኤቷል ሳህል እንዳሸነፈ ጽፌ ነበር ..........! ከሱ ጋር በተያያዘ .....የግብጹ አህሊ መሸነፍ ያናደዳቸው ደጋፊዎች ከፕረዝደንት ሆንሲ ሙባረክ እጅ ሽልማት ለመቀበል በሚሄዱበት ጊዜ ከተመልካቹ ጠርሙሶችና ሌሎች እቃዎች እንዲሁም "ሚሳኤል " ተወርዉሮባቸዋል ........! ቢቢሲ እንደዘገበው ከሆነ ...ይህ ሁሉ ዉርጅብኝ የመጣው በጣም ዉድ ክፍያ ተከፍሎ ከሚገባበት መቀመጫውችና ከፕረዝደንቱ ፊት ለፊት ከተቀመጡ ደጋፊዎች ነው ...........! ካፍም እርምጃ ለመዉሰድ ሁኔታዉን እየመረመረ ነው ........! ሽንፈት መጥላት ሌላ .....ዱላ ሌላ ......!

አሳፋሪ ............! ማፈርያ ...................! ያሳፍራል ...........! Shocked
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መሬውመራራው

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Jun 2007
Posts: 599

PostPosted: Sat Nov 10, 2007 6:56 pm    Post subject: Reply with quote

እናትዬ እንደጻፈ(ች)ው:
መሬው ምነው እያደርግ ሕጻን ሆንክ ? የምትጽፈውን አታውቅም እንዴ ?
ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ቢኖርህ መልካም ነው !

ምነው እናትዬ ....ምን አጠፋው ....??? እኔ ቁርጭምጭሚቱ የቱ ነው ያለው ብዬ ነው የጠየኩት ....! ፎቶዉንም ቢሆን እኔ አይደለሁም ያነሳሁት ......! እጁንም ያሳረፈው ሩኒ እንጂ እኔ አይደለሁም .....! ታድያ ጥፋቴ የቱ ነው ....? በኢትዮጵያዊ ጨዋነት እኔ ሀጥያተኛ ነኝእንዴ ...? ባለጌ ከተባለ ሩኒ ነው ባለጌ ......! ቁርጭምጭሚቱ የቱጋ እንደሆነ ጠፍቶት ነው ....?? Wink

20 ቀናት በሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ምክንያት ክለባቸዉን ለቀው የሚሄዱ የአፍሪካ ተጫዋቾች ከእንግሊዝ 44 ሲህኑ ይህም ሁለት አመት በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር ከእጥፍ በላይ ጨምሯል ...........በፊት 21 ነበር !

በተለይ ቼሊሲ ኤስየንን ድሮግባንና ጆን ኦቢ ሚኬልን እንዲሁም ካሉን ሊያጣ ይችላል .............! አርሰናል ደሞ ቱሬን እና ኤቡዬን ሊያጣ ይችላል ...........! ሊቨርፑል ደግሞ ሴሴኮን ያጣል .....! ፖርትስመዝ ደግሞ ድዩፕ ...ሙንታሪ ...ካኑንና ኡታካን ያጣል ...........! ዉድድሩ ጥር 20 የሚጀመር ቢሆንም በፊፋ ህግ መሰረት ተጫዋቾቹ ለልምምድ ጥር 6 ክለባቸዉን ለቀው መሄድ ይችላሉ ...........! በተለይ ፖምፒዎችን ቼልሲዎች በጣም እንደሚጎዱ ሲጠበቅ ማንዩ ግን አንድም ተጫዋች አያጣም ......!!! ማነው አፍሪካዊ ..........???????

በህጉ መሰረት በጥር ስድስት አርሰናል ሁለቱን ተጫዋቾቹን ከለቀቀ እነዚህ ጨዋታዎች ልጆቹ ያልፋቸዋል ...
Arsenal v Birmingham
Fulham v Arsenal
Arsenal v Newcastle
Man Cityv Arsenal
Arsenal v Blackburn
ቼልሲ በበኩሉ እነዚህ ጨዋታዎች ላይ አያፈኛቸዉም
Chelsea v Tottenham
Birmingham v Chelsea
Chelsea v Reading
Portsmouth v Chelsea
Chelsea v Liverpool
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መሬውመራራው

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Jun 2007
Posts: 599

PostPosted: Sat Nov 10, 2007 8:11 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ገነርስ ............!

የማንዩን ሊሊዬ የምጠይቃት ጥያቄ ነበርኝ ግን እናትዬ ስለተቆጣች ቤታቸው አታስገባኝምና ጥያቄዬን እዚሁ ላቅርብ .......! በዛዉም ከብዙ ጥያቄዎቿ መካከል አንድ የረሳሁትን እናትዬ አስታዉሳኛለችና ለመመለስ ልሞክር ..............! እናትዬ ለጥያቄዋ መልስ ስሰጥ ስቃብኝ ነው የምታልፈው .......ግን የሚያስቅ አልነበረም ....! ለማንኛዉም ልሞክር .....!!!!!!!!!

በነገራችን ላይ ሊቨርፑልና ፉልሀም እረፍት ወጥተዋል ............00.....!! ሁሉም የተገረመው የሊቨርፑል አሰልጣኝ ቤኒቴዝ ከብዙ ጊዜ በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ቡድኑን ሳይቀይር ይዞ ቀርቧል .......! ባለፈው ማክሰኞ ቤሲክታሽን 80 ያሸነፈው ቡድን እንዳለ ቀርቧል ....! ሰዉ ህሉ ተገርሟል ....!!

ወደሊሊዬ ጥያቄ ላምራ .........! ባለፈው በፕሪምየር ሊጉ ዉስጥ 15 አሰልጣኞች ከዚህ በፊት በማንዩ ተጫዋች የነበሩ ናቸው ብለሽን መልሱን የሰጠሽን አይመስለኝም ......! በጉጉ ብጠብቅ ብጠብቅ ጸጥታ መረጥሽ ሊሊ .......! እስቲ እኔጥቂቱን ልሞክርና ይቀረዉን ጨርሺ ........!

1. የበርሚንግሀም አሰልጣን ብሩስ

2. የዚህ ሳምንት ተጋጣሚያችው ብላክበርን አሰልጣን ሁዩዝ

3.በአርሰናል 2 ቡድን በኤዳው የተደቆሰበት የሼፊልድ ዩናይትድ አሰልጣኝ ራብሰን

4. የማንዩ ጌታ የሴልቲክ አሰልጣኝ ስትራካን

5. የሰንደርላንዱ አሰልጣኝ ኪን

ይሄን ያህል ከተናገርኩ አይበቃም ሊሊዬ .....?አሁን ትዝ አልል ያልሉኝ አንድ ሁለት አሉ ....!

አርሰናልን Boring Arsenal ወደ Magical Arsenal የቀየሩት ...( እንግሊዞች አይደሉም ...በነገራችን ላይ ...)

እናይትዬ የጠየቀችኝ ....በነ ካምቤል ...አዳምስ ....ሲማን ....ኪዎን ጊዜ አርሰናል ዋንጫ በልቶ የለም ወይ ...? ችሎታ ሳይኖራቸው ቀርቶ ነው ወይስ ፈረንሳዊ ስለሆኑ ነው ዋንጫ የበሉት ብላ አስቃኛለች .....!

እናንተም እንድትስቁ ሙሉ ንግግሯን ላቅርብ .....
Quote:
እኔን የሚገርመኝ የመሬው ምሁራዊው አስተያየት ነው ... እንግሊዛውያን ኳስ አያውቁም አለኝና ከዛም በኍላ ለምን ስፔናዊያን ውጤታማ አልሆኑም ስለው ለብሄራዊ ቡድናቸው ግድ ስለሌላቸው ነው ብሎኝ እርፍ ... በሳቅ ነው የገደለኝ ... ያም ሆነ ይህ የመሬውን በእንግሊዝ ተጫዋቾች ላይ ያለውን ጥላቻ ከምን እንደመነጨ ስለማውቀው አለገረመኝም ... ምክንያቱም ባለፈው ጊዜ አንድ ጥያቄ ጠይቄው መልስ መስጠት አልፈለግም ወይም አልቻለም ትቶታል ..... አርሰናልን ለአንቱታ አብቅተውት የነበሩት ሲማን ... ካምቤል .... አሽሊ ኮል .... አይችሉም አይደል ?... የዘንድሮ የፊፋ ፕሮ አሸናፊዎች ዤራርድ እና ጆን ቴሪም ፈረንሳውያን ናቸው አይደል ?....ማን .ዩናይትድ ቡዳ ነው አርሰናል ፍቅር ነውእናትዬ ....አርሰናልን ትልቅ ያደረጉ ብዙ እንግሊዛዉያን አሉ .........! የአርስናልን ታሪክ ጀምሬ የቅርቡን ባለመጨረሴ የማላውቃቸው መሰለሽ እንጂ ብዙ እንግሊዛዉያን ከአርሰናል መንጭተዋል ....!!! ግን ዉጤታቸው ምንድነው ...ብለሽ ብትጠይቂ ... እዛው በአገራቸው FA እና ፕሪምየር ሊጉን ማግበስበስ ብቻ ነው ....! በአዉሮፓ መድረክ ላይ እንኳን ፕሪምየር ሊግ ከተመሰረተ ወዲህ ከእንግሊዝ ቡድኖች ጥሩ ዉጤት እያየን የመጣነው በቅርቡ ነው ......! ትዝ እስከሚለኝ ድረስ ብላክበርን የሊጉን ዋንጫ በልቶ በቻምፕየስን ሊግ ላይ በአሳፋሪ ዉጤት ነው ተሸንፎ በመጀመርያው ዙር የተባረረው .....! ያዉም ቀላል በሚባሉ የምስራቅ ቡድኖች ....! ያንን ቡድን ተመልሰሽ ብታይው .....አብዛኞቹ እንግሊዛዉያን ይመስሉኛል ......! ከአገራቸው ሲወጡ ዉጤታቸው ዜሮ ነው ..........! ማንዩን እንኳን እይው .....! በስንት ትግል ነው የቻምፕየስን ሊግ ዋንጫ የወሰደው ....? ያዉም የዉጭ ልጆች ይዞ ነው ....!!!!! ስለዚህ ለጥያቄሽ ተስማሚ ተረትና ምሳሌ ተሟሙቼ ያገኘሁልሽ መሰለኝ .....አህያ ላህያ ቢራገጥ ጥርስ አይሰባበርም .....! እንግሊዝ ከእንግሊዝ ቢጫወት ለዉጥ የለውም .....! ከሌሎች የአዉሮፓ ቡድኖች ጋር ሲጫወቱ ግን ዉጤታቸው የደከመ ነው ...! ልክ የኢትዮጵያዉን ጊዮርጊስ ዉሰጂ ..........የአገር ዉስጥ አንበሳ አይደል የሚባለው ....??? በእንግሊዝ ተጫዋቾች ብቻ የተመሰረተ ክለብ የእንግሊዝ ጊዮርጊስ ነው ሊሆን የሚችለው ..........!!!!!

እነዤራርድም ካሉበት ሊግ ባሳዩት ብቃት ነው ሊመረጡ
የቻሉት .........!

እናትዬ ..መልሴ ለራሴ አላረካኝም .....! ስለደከመኝ ለመጨረስ ያህል ነው የጽፍኩት ...! ተጨማሪ ማብራርያ ከፈለክሽ ንገሪኝና እንደገና እጽፈዋለው .............!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መሬውመራራው

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Jun 2007
Posts: 599

PostPosted: Sat Nov 10, 2007 8:28 pm    Post subject: Reply with quote

ሰላም ..........!!!!

(ኦፍኮርስ ለገነርስ ብቻ ነው .....ሰላምታው ! Evil or Very Mad )

ሊቨርፑል ፉልሀምን 2 0 በማሸነፍ ወደላይ ተንፏቋል ..........ከቼልሲ እኩል 24 ነጥብ ይዞ በጎል ልዩነት ይመልጣል ......! ግቦቹ የተገኙት 81ኛው ደቂቃ በፈርናንዶ ቶሬ ሲሆን 85ኛው ደቂቃ ዠራርድ በፔናሊቲ አስቆጥሯል ............! ፉልሀም ላይ እስካሁን ከገቡበት ግቦች ዉስጥ ወደ 8 የሚሆኑት በመጨረሻዎቹ 10 ደቂቃ ዉስጥ ነው ..........! የሚገርመው ፉልሀም የዛሬን ጨዋታ ሳይጨምር ከእረፍት በፊት የነበረው ዉጤት ብቻ ቢያዝለት ( ማለትም የሁሉም ቡድኖች ነጥብ በመጀመርያው 45 ደቂቃ ያለው ብቻ ቢያዝ ..) ከሊጉ 25 ነጥብ አንደኛ ይሆኑ ነበር የሚል ጽሁፍ አንብብያለው ...........! የነሱ ዉጤት የሚበላሸው ከእረፍት በኋላ ነው ......! ጨውታውን 45 ደቂቃ ብቻ ቢሆን ፉልሀም ዛሬ 26 ነጥብ ላይ ይገኝና ማንዩ አናት ላይ ይፈነጭ ነበር ......!ወይ ነዶ ....!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መሬውመራራው

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Jun 2007
Posts: 599

PostPosted: Sun Nov 11, 2007 5:57 am    Post subject: Reply with quote

ሰላም ገነርስ ..............!

ልጃችን ፋብሬጋስ ስለ ፕሪምየር ሊግና ስለ ስፔን ሊግ ተጠይቆ የመለሰው ትንሽ ፈገግ ስላደረገኝ .....በጣም ሰለምወዳችሁ Wink እናንተም ፈገግ በሉ ብዬ ይዤው መጣሁ ..........!

ፋቡ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ ያለምንም ጥርጥር ስፔን ጥራት አለ ብሏል ...! ቀጥሎ ዌስትሀም ቦልተን እና ባርሴሎና ቤቲስ ጨዋታዎች ጋር ሲያነጻጽ .......የዌስትሀምና ከቦልተንን ጨዋታ ሳይ እንቅል ሊወስደኝ ምንም አይቀረኝም ብሎ የባርሳና የቤቲስ ግን የተጫዋቾቹ ችሎታ በጣም ያስገርመኛል ብሏል .........ቅቅቅቅቅ ዌስትሀምና ቦልተን .....ማን ነው ጥሩ ጨዋታ ነበር ሲል የሰማሁት ....? እኔም የመጀመርያዉን ግማሽ አይቼ እንቅልፍ ይዞኝ ሄዶ ስነቃ ሌላ ፕሮግራም ነበር ይታይ የነበረው ........... Laughing ! የፋብሬጋስ አባባል እኔን እንደገጠመኝ አይነት ሆነብኝና በጣም አሳቀኝ ...........! እናንተንስ ....? የሚያስቆጣችህም እንደምትኖሩ አዉቃለው .....ይቅርታ !!!!!!!!!!

ፋቡ የቦልተንና የዌስትሀም ጠላት .... Laughing (ቦልተን ግን league two ወርዶ መጫወት አለበት ...)ሌላው ዜና ጌታ ቬንገር ለትላንትናው የስቲቭ ኮፔል ትችት የሰጡት መልስ ይሆናል .............! የሪዲንግ አሰልጣኝ ሲቲቭ ኮፔል አርሰናል በዉጭ ተጫዋቾች በመሞላቱ ጥሩ እንግሊዛዉያን ተጫዋችችን ማፍራት አልቻለምና ኮታ ይኑር የሚለዉን ሀሳብ በደንብ እደግፋለው ብለው ነበር ...! ዜናዉንም በቅንጫቢው አቅርቤ ነበር ...! ቬንገር ዛሬ ለዚህ ምላሽ ባጭሩ ሲሰጡ ....ኮታ መኖር እንደሌለበት የሚያሳየን ምሳሌ ቢኖር የሪዲንግ ክለብ ነው ብለዋል .........!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!.......... የስቲቭ ኮፔል ቡድን ባለፈው አመት እንዳይወርድ ያደረጉት የአርሰናል ልጆች ናቸው ብለው በመሀል ላይ ይጫወቱ የነበሩትን ስቲቭ ሳይድዌልንና ጄምስ ሀርፐርን እንደምሳሌ ጠቅሰዋል .......! ሳይድዌል ወደ ቼልሲ ከመግባቱ በፊት ከሀርፐር ጋር መሀል ላይ ጥሩ ቅንጅት ፈጥረው ነበር ያሉት ቬንገር ... እንደሪዲንግ አይነት ክለቦች ጥራት ያላቸው ግን በአርሰናል ቋሚ መሆን ያልቻሉ ተጫዋቾችን የማግኘት እድላቸው የኮታ ገድብ ቢኖር ኖሮ በጣም ጠባብ ነበር ብለዋል ............! አርሰናል ዉስጥ ቋሚ ተጫዋች መሆን ሳይችሉ ቀርተው ቡድኑን የሚለቁ ሌላ ቦታ ግን በሊጉ ጥሩ የሚባል ቡድን ይወጣቸዋል ብለዋል ........! ከአርሰናል የወጡ የእንግሊዝ ተጫዋቾችን ለረሳችሁ ለማስታወስ ያህል ...(እኔ ያስታወስኩትን ነው ....የቀረ ካለ አምብሬ ይሞላዋል ....!!! ማንዩዎች እናንተም ከማንዩ የተገኙትን ዘርዝሩና ማን እንደሚበልጥ ማየት እንችላለን ........!!) (ሪዲንግ ከአርሰናል የወሰዳቸው ሌሎች ሁለት ተጫዋቾች አሉ ....ግርሀም ስታክ እና ጃን ሆል ናቸው .....! ስቲቭ ኮፐል ዉለታ ቢስ ነው )

ዴቪድ ቤንትሊ ....ባላክበርን

ጀርሜይን ፒናንት ....ሊቨርፑል

ስቲቭ ሳይድዌል ...ቼልሲ

ጄምስ ሀርፐር ....ሪዲንግ

ማቲው አፕሰን ....ዌስትሀም

አንተኒ ስቶክ ....ሰንደርላንድ

....በቃ ? Shocked አምብሬ ሙላበት ......! የወሮበላው መሳቅያ ሳልሆን ....! ዋርካ እግዜር ይስጣት .....አፉን ይዛልኛለች . Laughing
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መሬውመራራው

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Jun 2007
Posts: 599

PostPosted: Sun Nov 11, 2007 6:57 am    Post subject: Reply with quote

የሰኞው ጨዋታ ንጽጽር .....(እናትዬ ሳትቀድሚኝ ... Laughing )
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አንበርብር

ውሃ አጠጪ

Joined: 09 Apr 2005
Posts: 1090
Location: everywhere

PostPosted: Sun Nov 11, 2007 12:37 pm    Post subject: Reply with quote

መሬው የዛሬውን ብቻ ተወኝ ........... ከነገ ጀምሮ ጠዋት እና ማታ ታገኛለህ ........ በሰፊው ልመለስ አንድ ቀን ብቻ ነው ቀረኝ ......... ስመለስ ደግሞ የሰይጣን መውገሪያ ነው ይዠ ነው የምመለሰው .......... ከዚያ እራስ እራስን መቀጥቀጥ ነው ....... የዲያብሎስን ማለቴ ነው ......... በቃ አሁን ወጣሁ !!!!! ከመውጣቴ በፊት ግን ......... ሩኒ የተጎዳው ትሬኒንግ ከሚያደርጉበት equipment ላይ ወድቆ እንደሆነ ሰምተናል ........ እንዴት ሊወድቅ ቻለ ብለው ደጋፊዎቹ የመሰላቸውን ሀሳብ የሰነዘሩትን ላስቀምጠው ......... የተናገሩት በእንግሊዘኛ ስለሆነ እንዳለ አቀርበዋለሁ

አንዱ የሚባለው እንደዚህ አለ .........
Falling over metal equipment in training ? Was he sniffing crack?

ሁለቱ የሚባለው ደግሞ ሲገምት ..........
Silly little fat b*stard, thought he found a pie on the floor and tried to dive for it.

ሶስቱ የሚባለው ደግሞ ሲናገር ....................
hahaha wat a fat loser....i bet he fall off while running on the threadmill or he fail 2 carry a 20 pound weight so it falls on his leg

እኔም ይህንን ላጣራ ዛሬ ወደ ሆስፒታል ሂጀ ከካሜራየ ጋር አስተዋውቄው ነበር ............ ካሜራየ እንዲህ አግኝታዋለች ..........

[img]http://tbn0.google.com/images?q=tbn:10wLm3wp5-NGHM:http://soccernet-akamai.espn.go.com/design05/DJ/20060514/rooneyfoot_lg.jpg[/img]
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
ዌስትሀም

ኮትኳች

Joined: 31 Oct 2007
Posts: 121

PostPosted: Sun Nov 11, 2007 1:47 pm    Post subject: Reply with quote

Quote:
ፋቡ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ ያለምንም ጥርጥር ስፔን ጥራት አለ ብሏል ...! ቀጥሎ ዌስትሀም ቦልተን እና ባርሴሎና ቤቲስ ጨዋታዎች ጋር ሲያነጻጽ .......የዌስትሀምና ከቦልተንን ጨዋታ ሳይ እንቅል ሊወስደኝ ምንም አይቀረኝም ብሎ የባርሳና የቤቲስ ግን የተጫዋቾቹ ችሎታ በጣም ያስገርመኛል ብሏል .........ቅቅቅቅቅ ዌስትሀምና ቦልተን .....ማን ነው ጥሩ ጨዋታ ነበር ሲል የሰማሁት ....? እኔም የመጀመርያዉን ግማሽ አይቼ እንቅልፍ ይዞኝ ሄዶ ስነቃ ሌላ ፕሮግራም ነበር ይታይ የነበረው ........... ! የፋብሬጋስ አባባል እኔን እንደገጠመኝ አይነት ሆነብኝና በጣም አሳቀኝ ...........! እናንተንስ ....? የሚያስቆጣችህም እንደምትኖሩ አዉቃለው .....ይቅርታ !!!!!!!!!!

ፋብሪጋስ እውነት ይሄን ብሎ ከሆነ በሽተኛ ነው : እንዲህ ያለውን መግለጫ ቢሰጥ
ኖሮ ለአንድ ቀንም ለንደን ላይ ላይቀመጥ እንደሚችል ስነግህ ከእንግሊዛውያን ባህሪይ በመነሳት ነው
ካለም ደግሞ በእኔ በኩል ይሄ የቴስት ጉዳይ ይሆናል ... ለምሳሌ እኔ የስፔን ጨዋታ የባርሴሎና : የማድሪድን ብቻ ነው የማየው ::
ሌሎቹ በጣም ያስጠሉኛል የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን በሥራ ካልተጠመድኩ በቀር ግማሾቹን ቢያስን አያለሁ
ሁሉንም በፍቅር ነው የምመለከታቸው
በተለይ ደጋፊዎች ለተጫዋቾች ያላቸው አክብሮት
የስታዲየሞች ጥራት ፉክክሮች ጨዋታዎች ሁሉ ያስደስቱኛል
ምናልባት አንተ የባርሴሎናን እና የማድሪድን ጨዋታ ብቻ ነው የምታየው ::
ቫላዶሊድ እና ጅምናስቲክ ከሚያድርጉት ጨዋታ እና ሰንደላንድ ከሚድልስ ቦሮ ጨዋታ የእንግሊዞቹ ልዩ ነው ...
በሌላ በኩል ፋብሪጋስ ልቡ ወደ ባርሴሎና ሄዷል መሰለኝ : ፋብሪጋስ ማለት ለእኔ የማያድግ ልጅ አር ይበዛበታል አይነት ነው :
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
መሬውመራራው

ዋና ኮትኳች

Joined: 29 Jun 2007
Posts: 599

PostPosted: Sun Nov 11, 2007 4:12 pm    Post subject: Reply with quote

ዌስትሀም እንደጻፈ(ች)ው:
Quote:
ፋቡ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ ያለምንም ጥርጥር ስፔን ጥራት አለ ብሏል ...! ቀጥሎ ዌስትሀም ቦልተን እና ባርሴሎና ቤቲስ ጨዋታዎች ጋር ሲያነጻጽ .......የዌስትሀምና ከቦልተንን ጨዋታ ሳይ እንቅል ሊወስደኝ ምንም አይቀረኝም ብሎ የባርሳና የቤቲስ ግን የተጫዋቾቹ ችሎታ በጣም ያስገርመኛል ብሏል .........ቅቅቅቅቅ ዌስትሀምና ቦልተን .....ማን ነው ጥሩ ጨዋታ ነበር ሲል የሰማሁት ....? እኔም የመጀመርያዉን ግማሽ አይቼ እንቅልፍ ይዞኝ ሄዶ ስነቃ ሌላ ፕሮግራም ነበር ይታይ የነበረው ........... ! የፋብሬጋስ አባባል እኔን እንደገጠመኝ አይነት ሆነብኝና በጣም አሳቀኝ ...........! እናንተንስ ....? የሚያስቆጣችህም እንደምትኖሩ አዉቃለው .....ይቅርታ !!!!!!!!!!

ፋብሪጋስ እውነት ይሄን ብሎ ከሆነ በሽተኛ ነው : እንዲህ ያለውን መግለጫ ቢሰጥ
ኖሮ ለአንድ ቀንም ለንደን ላይ ላይቀመጥ እንደሚችል ስነግህ ከእንግሊዛውያን ባህሪይ በመነሳት ነው
ካለም ደግሞ በእኔ በኩል ይሄ የቴስት ጉዳይ ይሆናል ... ለምሳሌ እኔ የስፔን ጨዋታ የባርሴሎና : የማድሪድን ብቻ ነው የማየው ::
ሌሎቹ በጣም ያስጠሉኛል የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን በሥራ ካልተጠመድኩ በቀር ግማሾቹን ቢያስን አያለሁ
ሁሉንም በፍቅር ነው የምመለከታቸው
በተለይ ደጋፊዎች ለተጫዋቾች ያላቸው አክብሮት
የስታዲየሞች ጥራት ፉክክሮች ጨዋታዎች ሁሉ ያስደስቱኛል
ምናልባት አንተ የባርሴሎናን እና የማድሪድን ጨዋታ ብቻ ነው የምታየው ::
ቫላዶሊድ እና ጅምናስቲክ ከሚያድርጉት ጨዋታ እና ሰንደላንድ ከሚድልስ ቦሮ ጨዋታ የእንግሊዞቹ ልዩ ነው ...
በሌላ በኩል ፋብሪጋስ ልቡ ወደ ባርሴሎና ሄዷል መሰለኝ : ፋብሪጋስ ማለት ለእኔ የማያድግ ልጅ አር ይበዛበታል አይነት ነው :

ልጅ ዌስትሀም እንዴት ነህ .........! ፋቡ ያለችው ነገር እውነት ነው .............! http://www.dailymail.co.uk/pages/live/articles/sport/football.html?in_article_id=492927&in_page_id=1779ሄደህ ብታይ ታገኘዋለህ ...............! እንዳልከው የግል ምርጫ ነው :: አንተ የስኮትላንድን ሊግ ከስፔን ሊግ ትመርጣለህ እኔ ደሞ ከስኮትላንድ ሊግ ፊንላንድን ሊግ መርጣለው .....አይቼዉ ባላውቅም .. Laughing ! ለማለት የፈለኩት የስኮትላንድን ሊግ በጣም ነው የምጠላው እንኳንስ ስፔን ሊግ ላስበልጥ ቀርቶ ...........!
አንተ እንዳልከው በእንግሊዝ የስታድየሙ ጥራት የተመልካቹ ድጋፍና ክብር በአጠቃላይ በብዙ ነገር በአለም ላይ ተወዳጅ ነው ........! ግን በእርግጠኝነት ብነግርህ ተወዳጅ እንዲሆን ካደረጉት ከላይ አንተም ከጠቀስካቸው ምክንያቶች ባልተናነሰ ሁኔታ አንደኛ ፈርጊና በአንድ ወቅት አፍርተዋቸው የነበሩ ጥሩ ልጆች .....ሁለተኛ ቬንገርና የአጨዋወት ስታይሉ ....ሶስተኛ በእንግሊዝ ሊግ መጫወትን በህልማቸው ያላዩ ተጫዋቾች በፕሪምየር ሊጉ መጫወት ሲጀምሩ ተወዳጅነቱም እያደገ ሄደ ...........! ለዚህ እድገት ግን ዋና ተጠቃሾቹ አርሰናል ማንዩ ሊቨርፑል ቼልሲ ስፐርስ እና ሌሎች ጥቂት ክለቦች ናቸው ........!

የቦልተንንና የዊጋን ጭዋታ በአለም ላይ በጉጉት የሚጠበቅ ይመስልሀል ...?? በጭራሽ ...! ግን ከላይ የጠቀስኳቸው የአራቱ ጨዋታ ግን ከማንም ጋር ቢሆን በጉጉት ይጠበቃል .......! ይህም ማለት 4ወይም 5 ዉጪ ያሉት ቡድኖችን አሟሟቂ ያስመስላቸዋል .............! እዛው ለደጋፊያቸው ትልቅ ሊሆን ይችላል .......! እንደዉም አሁን አሁን ደጋፊያቸዉም ስታድየማቸዉን የሚሞላው 4 ክለብ ጋር ሲጫወት ብቻ እየሆነ ነው ......!

ዌስትሀም
Quote:
.....በሌላ በኩል ፋብሪጋስ ልቡ ወደ ባርሴሎና ሄዷል መሰለኝ : ፋብሪጋስ ማለት ለእኔ የማያድግ ልጅ አር ይበዛበታል አይነት ነው
ፋቡ ሁሌም በአርሰናል እንደሚቆይ ተናግሯል .......! አልስማም ካልነው ጮሆ ይነግረናል ........! ግን ባልፈው የባርሳን ጨዋታ ለማየት ከህሌብ ጋር ሄደው ነበርና ጋዜጠኞች ..ወደባርሳ መሄድ ፈልጎ ነው ብለው አስወሩ .........! ነገሩ ግን ወዲህ ነው .......! ከልጁ ጋር አብረዉት ያደጉ ተጫዋቾች አሉ ባርሳ ዉስጥ ......! ባርሳን ትረፍ ሲለው እንጂ ሜሲም የአርስናል ሊሆን ጫፍ ደርሶ ነበር ....! ብቻ የባርሳን ጨዋታ የማያይ እናትዬ ብቻ ሳትሆን አይትቀርም :: እና ፋቡም ኦንሪንና ሌሎች አብሯደግ ጓደኞቹን ለማየት ነው የሄደው ....! ፋቡ ደሞ ከባርሳ የወጣና "በዘሩም " ካታላን ነው ...! ካታላኖች ለባርሳ እንዴት እንደሚሆኑ መናገር አያስፈልግም ........! ግን ፋቡን የማያድግ ህጻን ስትል ምን ለማለት ነው ...??? ከእድሜው በላይ አድጎባቸው አይደል በሚያሳየው ጨዋታ አፋቸዉን ከፍተው የሚያዩት .............????????? አባባልህ ማብራርያ ያስፈልጋታል ዌስትሀም ...!!!!!!

ፋቡ በተናገረው ነገር ለንደን ላይ ለአንድም ቀን መቀመጥ አይችልም ...????? Shocked Shocked Shocked Shocked Shocked
Shocked ሞኒካ እንዳለችው ዌስታሀሞች ጋር ላይሆን ይችላል .....! እንግሊዛዉያንንማ በደፈናው ትግስት የሌላቸውና የሰዉ የመናገር መብት የሚገፉ አድርገህ አትሳላቸው .......! ተመልካች ተራግጦም ለብዙ ጊዜ የተጫወተ አለ ...እንኳን ጨውታው ደበረኝ ያለ ቀርቶ ....! ብቻ ብዙ ለፈለፍኩ ...........! ወሮን ዋርካዬ ይዛልኝ እንጂ 30 መስመር አለቃቀስ ብሎ አንድ ሁለት ይለኝ ነበር .....! ይመችሽ ወሮ ....ባለሽበት .....!!!! Wink ዝም ............!!!!!!!!!!!!!!!!
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አንበርብር

ውሃ አጠጪ

Joined: 09 Apr 2005
Posts: 1090
Location: everywhere

PostPosted: Sun Nov 11, 2007 11:45 pm    Post subject: Reply with quote

ዌስትሀም እንደጻፈ(ች)ው:
Quote:
ፋቡ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ ያለምንም ጥርጥር ስፔን ጥራት አለ ብሏል ...! ቀጥሎ ዌስትሀም ቦልተን እና ባርሴሎና ቤቲስ ጨዋታዎች ጋር ሲያነጻጽ .......የዌስትሀምና ከቦልተንን ጨዋታ ሳይ እንቅል ሊወስደኝ ምንም አይቀረኝም ብሎ የባርሳና የቤቲስ ግን የተጫዋቾቹ ችሎታ በጣም ያስገርመኛል ብሏል .........ቅቅቅቅቅ ዌስትሀምና ቦልተን .....ማን ነው ጥሩ ጨዋታ ነበር ሲል የሰማሁት ....? እኔም የመጀመርያዉን ግማሽ አይቼ እንቅልፍ ይዞኝ ሄዶ ስነቃ ሌላ ፕሮግራም ነበር ይታይ የነበረው ........... ! የፋብሬጋስ አባባል እኔን እንደገጠመኝ አይነት ሆነብኝና በጣም አሳቀኝ ...........! እናንተንስ ....? የሚያስቆጣችህም እንደምትኖሩ አዉቃለው .....ይቅርታ !!!!!!!!!!

ፋብሪጋስ እውነት ይሄን ብሎ ከሆነ በሽተኛ ነው : እንዲህ ያለውን መግለጫ ቢሰጥ
ኖሮ ለአንድ ቀንም ለንደን ላይ ላይቀመጥ እንደሚችል ስነግህ ከእንግሊዛውያን ባህሪይ በመነሳት ነው
ካለም ደግሞ በእኔ በኩል ይሄ የቴስት ጉዳይ ይሆናል ... ለምሳሌ እኔ የስፔን ጨዋታ የባርሴሎና : የማድሪድን ብቻ ነው የማየው ::
ሌሎቹ በጣም ያስጠሉኛል የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን በሥራ ካልተጠመድኩ በቀር ግማሾቹን ቢያስን አያለሁ
ሁሉንም በፍቅር ነው የምመለከታቸው
በተለይ ደጋፊዎች ለተጫዋቾች ያላቸው አክብሮት
የስታዲየሞች ጥራት ፉክክሮች ጨዋታዎች ሁሉ ያስደስቱኛል
ምናልባት አንተ የባርሴሎናን እና የማድሪድን ጨዋታ ብቻ ነው የምታየው ::
ቫላዶሊድ እና ጅምናስቲክ ከሚያድርጉት ጨዋታ እና ሰንደላንድ ከሚድልስ ቦሮ ጨዋታ የእንግሊዞቹ ልዩ ነው ...
በሌላ በኩል ፋብሪጋስ ልቡ ወደ ባርሴሎና ሄዷል መሰለኝ : ፋብሪጋስ ማለት ለእኔ የማያድግ ልጅ አር ይበዛበታል አይነት ነው :

እኔም እስኪ ትንሽ ልጨምርበት ........... እንደሚመስለኝ ግን ቆየት ብየ ዌስትሀም ከየት ወደየት ? በሚል ርዕስ አን ፅሁፍ የምፅፍ ይመስለኛል ......... ስለ ክለቡ ዌስትሀም አይደለም ......... የዋርካ ተሳታፊ ስለሆነው ዌስትሀም እንጅ ........ የዘፈን ዳርዳርታው እስክስታ እየሆነብኝ ስለመጣ ነው ......... ሰይጣን እንኮ የመቀያየር ባህሪ አለው .... ማለቴ አንድም ሁለትም ይሆናል ........ Laughing Laughing Laughing did i get u bro? አርሰናል ውስጥ የመናገር ነፃነት እንዳለህ መሬው ካልነገረህ እኔ ልንገርህ ....... at the same time እኛም የመናገር ነፃነት አለን እና .......... እንደ እናትየ አካኪ ዘራፍ እንዳትልብን አደራ ........... ውይ እረስቸው ዌስትሀም ዳርቢን 5 አቃመው አይደል ? እንኳን ደስ አለህ ........ አንተ እንዳልከው ከላሊጋ የስኮትላንድን የሊግ ጨዋታ ትመርጣለህ አይደል ............ መሬው ደግሞ ከስኮትላንድ የፊንላንድን ! እኔ ደግሞ ከስኮትላንድ ይልቅ ባርሳ አካዳሚክ ውስጥ የሚሰለጥኑትን ህፃናት ባይ ይሻለኛል ......... ቀላል ጥበብ ታያለህ እንዴ ........ በል መልስ ወይም አስተያየት ካለህ ፊል ፍሪ እና እኔም እመለስበታለሁ .............. ሰሞኑን ዋርካን እንደማለቅ በፋበርጋስ ስም ምየ እነግርሀለሁ .............
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አንበርብር

ውሃ አጠጪ

Joined: 09 Apr 2005
Posts: 1090
Location: everywhere

PostPosted: Mon Nov 12, 2007 12:14 am    Post subject: Reply with quoteባለፈው እናትየ ጠቅሳው ያለፈችው የኮንጎ ተወላጅ ሙፑቱ ለሙከራ ከአርሰናል ጋር 10 ቀን ይቆያል .......... ምናልባት ቪንገርን ከማረከ አንድ መሳሪያ ይሰጠው እና ጋነርስ ይሆናል ማለት ነው ............. እድሜው 14 አይደለም 21 ነው ...... አሮጌው ፈርጊ ባለፈው አውስትራሊያዊ 10 አመት ምናምን ህፃን ልጅ ከእናቱ ጡት መንጭቆ አመጣ ሰሞኑን ደግሞ 14 አመት ከአንቀልባ ላይ አስወልቆ አመጣ . ይህንን ሁሉ የተመለከተው ፕላቲ ደግሞ አይኑም ልቡም ቪንገር ላይ ብቻ ሁኖ ፕሮፈሰሩን ይወነጅላል .............. የፕላቲኒ አይን የአሮጌው ፈርጊን ስራ አያይም ወይስ አቤቱታው ማንቸስተርን አያካትትም ??? እረ ፍረዱልን !!!!!!!!!!!!

እስኪ ለዌስትሀም ግንዛቤ ይሆን ዘንድ ፋበርጋስ ተጠይቆ ምን እንዳለ ደግሞ ላስቀምጥለት .............. I cant say Im a great player. And I always say at Arsenal were a very, very good side but not a great side. When we win something together as a group we can say were great but, right now, were just a good side
ፋበርጋስ ጉረኛ አይደለም ...... አቅሙን ያውቃል ማንነቱን አይደብቅም .... በስም መኖሮ አይፍፈልግም በስራ እንጅ .............

Arsenal Hit Nine
ደነገጣችሁ አይደል ? አዎ የሪዲንግ ውጤት እንዳይመስላችሁ ሴቶች ጋነሮች ናቸው 9 ጎል የዘፈዘፉ .......... ካርዲፍ ሲቲ ላይ ነው ሲጨፍሩበት ያመሹ ..... በሌላ ውጤት ደግሞ ኤቨርተን ዋትፎርድን 3-0. ቸልሲ ሊድስ ዩናይትድን 1-0, ሊቨርፑል ደግሞ በዶንካስተር ሮቨርስ 3-0 ተሸነፈ ........... ማንቸስተር ደግሞ አልተጫወተም ..... ምክንያት የሴት ቲም የሚባል የለውም ቅቅቅቅቅ አያሳዝንም ??

ሀትሪክ የሰራችውን ሊያን ሳንደርሰንን ላስተዋውቃችሁ .........
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አንበርብር

ውሃ አጠጪ

Joined: 09 Apr 2005
Posts: 1090
Location: everywhere

PostPosted: Mon Nov 12, 2007 12:41 am    Post subject: Reply with quote

ውይ እረስቸው ...... ሞት ይርሳኝና ......... መሬው እንዳልኩህ ሽልማቱን ነገ ሜዳ ላይ ነው የምታገኘው ....... ሻይ ቦይ ግን አሁን ይህንን ልስጥህ እና ....... አይመቸኝም ካልክ ደግሞ እቀይረዋለሁ .......... አሁን ግዜ ስላለኝ አስመርጥሀለሁ ........ ምንም ችግር የለም .......
http://www.youtube.com/watch?v=HmfQg_S847g
This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
አንበርብር

ውሃ አጠጪ

Joined: 09 Apr 2005
Posts: 1090
Location: everywhere

PostPosted: Mon Nov 12, 2007 1:40 am    Post subject: Reply with quote

Gunnarsson has Cesc in his sightsየመጀመሪያው አላማችን ተሳክቶልናል ይላል ይኸው የመሀል ተጨዋች ..... ወደ ኦልትራንፎርድ ተጉዘው አንድ ነጥብን ተጋርተው የመመለሻቸው አላማ ሲገልፅ እንደዚህ ነበር ያለው ...... እነና ጀምስ ሀርፐር ፓል ስኩልስን እና ካሪክን ተከፋፍለን ነበር ...... ለእኔ ስኩልስ ነበር የደረሰኝ እናም እርሱ በነበረበት ቦታ ሁሉ እኔም ነበርኩ በቃ ምናልፈቻሁ ማንቸስተር ወጥረን ያዝነው ሶስት ወይም አራት ጥሩ ሙከራዎችን ብቻ አገኙ ግን አልተጠቀሙበትም ....... እናም ታርጌታችን ኢላማችንን መትቶ ተመለስን ይህንን አላማ በሜዳችን ላይ እንደግመዋለን ፋበርጋስ ለእኔ ደርሳኛለች ስራየም ነው .... ስራ ተብሎ ከተሰጠህ ደግሞ ስራህን መስራት አለብህ ካለ በኌላ አሁን የተሰጠኝ ስራ ግን ከመቸውም የሚከብድ ነው በማለት ተናግሯል :: ልዩነቶችን ሲያስቀምጥ ደግሞ አርሰናል በሜዳ ላይ ቢያንስ አስር የጎል እድሎችን የመፍጠር ብቃት አላቸው እነዚህን እድሎች ደግሞ ወደ ውጤት የሚቀይሩ 5 እና 6 የሚሆኑ ተጨዋቾች አሏቸው በማለት ማንን መያዝ እንደሚቻልም ያለውን ስጋት ገልፃል :: የኳስ አስተላለፋቸው ከእንቅስቃሴያቸው ጋር ጥራት የታከለበት ነው : ሲጫወቱ እንደሌሎች ክለቦች ከኌላ አራት አቁመው ከመሀል አራት አቁመው አይደለም ......... በቃ ከመቅፅበት ከሁሉም አቅጣጫ መጥተው ይወሩሀል ያኔ ወኔህ ከድቶህ ተንቀጥቅጠህ ዘጭ ትላለህ በማለት ጋነሮችን ሳያካብድ የታየውን ተናግሯል :: ስለ ዛሬው ውጤት ሲናገር እኩል ከወጣን በጣም ጠቃሚ ነጥብ ነው ከዚያ ከፍ ካለ ደግሞ ማን ይጠላል ይለናል ::

የማንነት መገለጫ የሚሆን መረጃ ይዠላችሁ መጣሁ ........... አርሰናልን : ቶትንሀምን : ሊቨርፑልን : ማንቸስተርን እና ቸልሲን ነው የምታዩልኝ .......... ማነው በገንዘብ የሚቆመው ? ማነው ጥሩ አስተዳደር የሚችለው ? ሁሉም አሰልጣኞች እኩል በጀት ቢያወጡ ማን ውጤታማ ይሆናል ?......... ብቻ ብዙ ብዙ ነገሮችን አይታችሁ .... የጋንርን ፍቅር ትቀምሳላችሁ ......... እናም ተቋደሱ ..........

This message expresses the views and opinions of the author and not necessarily those of CyberEthiopia, its staff or its affiliates. If you think this message is inappropriate or violates our rules and regulations , please notify the Administrators by clicking on the report button below.
Back to top
View user's profile Send private message Report post
Display posts from previous:   
Post new topic   Reply to topic    WARKA Forum Index -> Warka Sports - ዋርካ ስፖርት All times are GMT + 1 Hour
Goto page Previous  1, 2, 3 ... 66, 67, 68 ... 118, 119, 120  Next
Page 67 of 120

Jump to:  
You cannot post new topics in this forum
You cannot reply to topics in this forum
You cannot edit your posts in this forum
You cannot delete your posts in this forum
You cannot vote in polls in this forum

Provided by CyberEthiopia.com , powered by phpBB © 2001, 2005 phpBB Group , Original Amharic translation by Ethiopic Open Source Translation modified by CyberEthiopia